cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Prophet Muhammed's Ummah

"እኛ ማነፅ የምንፈልገው ትውልድ እስልምናን የሚሸከም ትውልድ እንጂ ኢስላም እሱን የሚሸከመው ትውልድ አይደለም፡፡" ኢማም ሀሰነ አል-በና For any suggestion . . . . . . . . . . . . . . @ justlive998

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
127
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን የታላቁ አንዋር መስጂድ ምክትል ኢማም ሼይኽ ሁሴን ወደ አኼራ ሄዱ! አቡ ዳውድ ኡስማን የታላቁ አንዋር መስጂድ ምክትል ኢማም በመሆን ለረጅም አመት ህዝበ ሙስሊሙን ሲያገለግሉ የቆዩት ሼይኽ ሁሴን በድንገት ወደ አኼራ ሄደዋል:: ሼይኽ ሁሴን እጅግ ተወዳጅ፣አላህን ፈሪ፣የሙስሊሙን አንድነት አጥበቀው የሚሹ ታላቅ ኢማም ነበሩ:: በአንዋር መስጂድ እሳቸው ኢማም በሚሆኑበት ወቅት ጀምዓው በደንብ ተሰባስቦ ይሰግድ እንደነበር ሁሉም የሚመሰክረው ሲሆን ሙስሊሙን ኡማ የሚጠቅም ትምህርቶችን በመስጂዱ ከማስተማር ውጪ አንዳችም ክፉ ቃል በአላህ ቤት ውስጥም ሆነ ውጪ ተናግረው የማያውቁ አላህን ፈሪ የሆኑ ኢማም ነበሩ:: ሼይኽ ሁሴን ህዝበ ሙስሊሙ የመንግስትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሰላማዊ ትግል በሚያካሂድበት ወቅት "አብሽሩ አላህ ይረዳናል፣ በርቱ አላህ ከተበዳዮች ጎን ነው እያሉ ያበረታቱ ነበር:: በኢድ ቀንም የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ሙስሊሙ ላይ የበቀል እና የሃይል እርምጃ በወሰዱበት ወቅት ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸው የነበረ ሲሆን እሳቸው ግን "ቀደምት ሙስሊሞች በመጋዝ ሁለት ቦታ አናታቸው እየተሰነጠቀ ለዲኑ መስዋት ከፍለዋል ይህ ለኢስላም ምንም ማለት አይደለም" በማለት ለሚጠይቃቸው ሰው ይናገሩ ነበር:: እኚህን የመሰለ ሃቀኛ፣ለስልጣን እና ለገንዘብ ሲሉ ከሙስሊም ጠላቶች ጋር የማያብሩ፣በተንኮል ላይ ፈፅሞ የማይተባበሩ ፣የሙስሊሙ ጭቆና እና ህመም እጅግ የሚያሳምማቸው፣ ልታይ ልታይ የማይሉ፣ከአንደበታቸው መጥፎ ቃል የማይወጣ ተወዳጅ ኢማምን በዚህ ወቅት ማጣት ልብ ይሰብራል:: ሼይኽ ሁሴን በዱንያ ላይ በነበሩበት ወቅት በዲናቸው ለነበራቸው አቋም ሁሉም የሚመስክርላቸው ኢማም ነበሩ! አላህ ይዘንላቸው፣ ማረፊያቸውን በጀነተል ፊርዶስ ያድርግላቸው! አላህ ሆይ እኛ እንደ ሰው የምናውቀውን መስክረናል አንተ ደግሞ ውስጥ አዋቂ ነህና ታላቅ ደረጃን በጀነት አጎናፅፋቸው! አሚንን
Показать все...
«ውሃን በመጎንጨት ቢሆን እንኳ ስሁርን ተጠቀሙ።» ነብዩ ሙሐመድ (ሰዐወ)
Показать все...
ትኩረት ለጎንደር ሙስሊሞች‼ የጎንደር ተደጋጋሚ ሰሞንኛ የሽብር ጥቃት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ‼️ በ07/08/2013 ትናንት ምሽት በጎንደር ከተማ ፒያሳ አካባቢ እርግብበር መስጅድ ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የመጡ የተደራጁ አክራሪ የኦርቶዶክስ ወጣቶች ወደ መስጅዱ ዲንጋይ በመወርወር እና ጥይት በመተኮስ ጥቃት ለማድረስ ሲሞክሩ ያዩ የአካባቢው ሙስሊም ወጣቶች "መስጅዱን አናስመታችሁም" ብለው የተከላከሉ ሲሆን ጥቃት አድራሽ የተደራጁ ቡድኖች መሳሪያ በመተኮስ እና ሙስሊም ወጣቶችን በመደብደብ ጥቃት አድርሰው ከአካባቢው ሸሽተዋል። ፖሊስም ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ጥቃቱ ወደደረሰበት የሰፈሩ መስጅድ መጥቶ መስጅዱን ከጥቃት የተከላከሉ ሙስሊም የሰፈር ታዳጊ ወጣቶችን በመውሰድ ባላጠፉት ጥፋት የኃይማኖት ግጭት ልትቀሰቅሱ ነው በማለት ለዕስር ያልደረሱ ታዳጊ ወጣቶችን ወስዶ በመደብደብና በጭስ በማፈን አሰቃቂ የሆነ የሰብአዊ ጥሰትን ሲፈፅምባቸው እንዳደረ የታሰሪ ቤተሰቦች ተናግረዋል። ከታሰሩት ወጣቶች ውስጥ አንደኛው ላይ በፖሊሶች ድብደባ ምክንያት እጁ እና እግሩ እንደተሰበረ የልጁ ቤተሰቦችና ጓደኞች ተናግረዋል። የታሳሪ ቤተሰቦች አክለውም እንደተናገሩት ጥቃት ያደረሱት አክራሪ ፅንፈኛ ቡድኖችን እንዳልታሰሩ እና እንዴውም ይባስ ብሎ ከ2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በመምጣት <<ይህ ወለጋ አይደለም። ወንድሞቻችንን እንዳረዳችኋቸው እኛ አንታረድላችሁም>> በማለት ሲዝቱ አምሽተዋል። ፖሊሶችም ይህን ዛቻ እና የግርግር ሙከራ እያዩና እየሰሙ ዝም ማለትን መርጠዋል። እነኚህ የተደራጁ ፅንፈኛ ሀይሎች ረመዳን ከገባ ወዲህም ለተራዊህ ሰላት የሚወጡ እህቶችን ፆታዊ ጥቃት ለማድረስ ሲሞክሩ እንደነበረ እና በወንድ ሰጋጆችም ላይ አፍኖ በመደብደብ እና በመዝረፍ የከተማውን ሙስሊም ሲያሳቅቁ እንደሰነበቱ የሚታወቅ ነው። ከሰሞኑም በሁሉም የጎንደር ዞኖች ይህ የፅንፈኛነት ተግባራቸው ተዛምቶ በተለያዩ ወረዳዎች አማኝ ሙስሊሙ ላይ በተደራጀ መልኩ ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ መሆኑን ከተለያዩ ቦታዎች ያገኘናቸው የድረሱልን እና መልዕክት አድርሱልን የሚሉ ሙስሊም ወገኖች ጩኸት አመላክቷል። ለአብነትም በሰሜን ጎንደር ዞን በትክልዲንጋይ እና በገደብየ ከተማ ሙስሊሙን ከከተማችን ልቀቁ በማለት ዝርፊያ እየፈፀሙ የማስፈራራት ሙከራዎችን እየፈፀሙ መሆኑ ከአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ የደረሱን ተደጋጋሚ መልዕክቶች አረጋግጠዋል። በትክልዲንጋይ ከተማም ፋሽን የሆነውን የሱፊ ሰለፊ የአመለካከት ልዩነቶችን በመጠቀም የነባሩን እስልምና እንጅ የአክራሪ እስልምና አማኞችን ስለማንፈልግ በሚል ለጥቃት ያመቻቸው ዘንድ ከፋፋይ አጀንዳ በመጠቀም ሙስሊሙን ለማፈናቀል እና እርምጃ ለመውሰድ በተህሳስ 10/2012 በምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ ላይ የተፈፀመውን አይነት የሽብር ተግባር ለመድገም አሁን ባሳለፍነው ሳምንት (ቅዳሜ ለዕሁድ ጠዋት) የተለያዩ በራሪ ወረቀቶችን ሲበትኑ እንዳደሩ ፖሊስም ደርሶበታል። ለጊዜውም ቢሆን ድርጊት ፈፃሚ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን የወረዳው ፖሊስ ያሰሩ ሲሆን ጉዳዩንም ፖሊስ በመከታተል ለላይ መሆኑን የከተማዋ ሙስሊም ኗሪ ግለሰቦች አሳውቀውናል። በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ እንፍራዝ ከተማ በታላቁ አንዋር መስጅድ ላይ ለሶስተኛ ጊዜ በቀን 05/08/2013 ማክሰኞ ምሽት ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ለሶስተኛ ጊዜ ጥቃት ደርሶበት የመስጅዱ መስኮት እና የቁባው መስታዎቶች ተሰባብረዋል። በዚህም ምክንያት የመጀመሪያው ተራዊህ ሰላት አልተሰገደም ሲሉ የመስጅዱ ማህበረሰብ አሳውቀዋል። ከአንድም ሶስት ጊዜ ጥቃት ሲደርስበት የከተማው ፖሊስ የደረሰውን ጉዳት ገብቶ ከማየት በዘለለ በስርዓቱ እንኳ ክሱን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም። ይባስ ብሎ በማሾፍና በማላገጥ ስሜት ሂዱና ያሲናችሁን ቅሩ ሲል መልስ መልሶላቸዋል።
Показать все...
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት የጠቅላላ ጉባኤ አፈጻጸም ክትትል ጊዜያዊ ኮሚቴ የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች አፈጻጸም ሁኔታን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ሚያዚያ 06 ቀን 2013 አዲስ አበባ
Показать все...
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የሙስሊም AlD አሜሪካ ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅትን በማስተባበር ለሀላባ ዞን ከ25 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና መገለገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ . . የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጌታቸው እንደገለጹት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ አማካኝነት ከ25 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል። . በኡስታዝ አቡበክር አህመድ አማካኝነት የተገኘው የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ እና በሀላባ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ሀቢብ ዳቆሮ ርክክብ ተደርጓል፡፡ . በርክክብ ስነ-ስረዓቱ ላይ የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተወካይ የሆኑት አቶ ሱልጣን ናስር ተገኝተዋል። . በዚህም የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የAID አሜሪካን ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅትን በማስተባበር ለሀላባ ዞን ላደረጉት የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ በሀላባ ህዝብ ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ . ዋና አስተዳዳሪው አያይዘውም በኡስታዝ አቡበክር አህመድ አማካኝንነት የተደረገውን ድጋፍ በማስተባበር ወደ ሀላባ ዞን በአፋጣኝ እንዲደርስ ከማድረግ አኳያ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ለነበሩት ለዞኑ ጤና መምሪያና ለዞኑ ፋይንናስ መምሪያ እንዲሁም ለአቶ ሱልጣን ናስር ምስጋና ችረዋል፡፡ . የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀማል ኑርዬ በበኩላቸው በኡስታዝ አቡበከር አህመድ አማካኝነት የተደረገው ድጋፍ በአፋጣኝ ወደ ዞን እንዲደርስ ለማስቻል በተቀናጀ መልኩ ተሰርቷል፡፡ . በዚህም ለሙስሊም AlD አሜሪካ ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅትን ኣንዲሁም ለኡስታዝ አቡበክር አህመድ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
Показать все...
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹የረመዷንን ወር በኢማንና ከአላህ ብቻ አጅርን በመፈለግ #የፆመ ሰው ከዚህ በፊት የሰራው #ወንጀል በሙሉ ይማርለታል›› #ቡኻሪና_ሙስሊም
Показать все...
በትላንትናው እለት ሮመዷን 1 ላይ በከፋ ዞን የጎቶ መስጂድ ሙሉ ለሙሉ መቃጠሉ ታወቀ። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬ Mujib Amino ሚያዚያ 6/2013 ረቡዕ በደቡብ ክልል ከፋ ዞን ሾታ ቀበሌ ቢታ ወረዳ በትላንትናው እለት ምሽት ላይ መስጂድ መቃጠሉ ታወቀ። በከፋ ዞን የጎቶ መስጂድ በትላንትናው እለት ምዕመናን የሮመዷን ፆማቸውን ገድፈው የመግሪብ ሶላት በመስገድ ወደየቤታቸው ከተበተኑ ቡኃላ ምሽት ላይ መቃጠሉን የከፋ ዞን እስልምና ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሐሰን ሁሴይን በስልክ ባደረግነው ልውውጥ ገልጸውልኛል። የከፋ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መስጂዱ መቃጠሉን በመግለጽ እስከአሁን አደጋ ያደረሰውን አካል በትክክል ማወቅ እንዳልተቻለና ከፀጥታ አካላትም ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ነግረውናል። አያይዘውም መስጂዱን ያቃጠሉት አካላት ማንነትና ምክንያት በፖሊስ እስኪረጋገጥ መገመት እንደማይችሉ ጠቅሰዋል። የዞን የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ከፖሊስ ጋር በመተባበር በርካታ ተጠርጣሪዎችን የያዘና በቀጣይም በሌሎች ላይ ምርመራ የሚያደርግ መሆኑን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። 👉||በደቡብ ክልል ከፋ ዞን ሾታ ቀበሌ የሚገኘው የጎቶ መስጂድ ገጠርማ አከባቢ የሚገኝ ሲሆን ምስል ለማስቀረት አደጋች መሆኑና ኔትዎርክም እጅግ አስቸጋሪ መሆኑን እንገልጻለን።|| ▬▬▬▬▬▬▬▬▬ የቴሌግራም ቻናል-https://t.me/MujibbinISLAM ስለፍትህ እንጮሀለን፣ ሠላምን እንሰብካለን፣ አንድነትንና መከባበርን እንሻለን!
Показать все...
በምርጫ ዋዜማ ኢስላማዊ ባንኮችን ለመናድ እንደተዘጋጀ የገለጸው ኢዜማ! ▬▬▬▬▬▬▬▬▬ Mujib Amino ሚያዚያ 6/2013 ረቡዕ ወለድ አልባና ለሕብረተሰብ ጠንቅ ከሆኑ አገልግሎቶች ነጻ የሆኑ ኢስላማዊ ባንኮችን አከስማለው የሚለው የኢዜማ ውድቀት! ኢስላማዊ የባንክ አሠራር ከሸሪዓ የወሰዳቸው ደንቦች አሉት። መርሆቹን ከሸሪዓ መውሰዱ ግን የእምነት ተቋም አያሰኘውም። የእምነት ተቋማት ቢሆኑም ችግር የላቸውም። በእምነት ሽፋን አርግዛችሁ የወለዳችኃቸው ስውር የፖለቲካ ፓርቲዎችና ባንኮች አያሌነታቸውን አንዘነጋውም! ወለድ አልባ ባንክ በአጭሩ ቢዝነስ እንጂ ሌላ አይደለም። በዚህ አገልግሎት የሚስተናግዱና አገልግሎቱን የሚሹት ልክ አራጣን እንደሚጸየፉ የተለያየ እምነት ተከታዮች ሁሉ፤ ወለድን የማይፈቅዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች አሉ፣ ሙስሊሞች ማለት ነው። እነኚህን ለማካተት የፋይናንስ አማራጭ ማቅረብ አለብን። ለምን አማራጭ የፋይናንስ አቅጣጫ ብሎ መቃወምና ጭራ መቁላት አማኞቹንና እምነቱን ከመጥላት የሚመነጭ ለመሆኑ አስረጂ ነው። ኢስላማዊ ባንክ ከቢራ ፋብሪካ ምንም አይነት ግንኙነት ማድረግ አይችልም። ኅብረተሰብን ይጎዳሉ፤ የሞራል ዝቅጠት ያደርሳሉ የሚባሉ ዘርፎች በሙሉ ወለድ ነጻ ባንክ በሩቁም ቢሆን አይነካካም። መጠጥ፣ ዝሙት፣ ቁማርና ሌሎች ለኅብረተሰብ ጠንቅ ናቸው በሚባሉ ቢዝነሶች/ኢንዱስትሪዎች ንክኪ የለውም። ማስታወቂያ አይሰጥም፣ አያበድርም፣ ተቀማጭም አያደርግም ...ወዘተረፈ ከዚህ ንክኪ ነጻ የሆነ ሞራሉ ብቁ የሆነ ሙስሊም ማሕበረሰብ እንዳይኖር እንደምትንቀሳቀሱ ስላወቅንና ስላሳወቃችሁን ምስጋናችንን በካርዳችን እንገልጻለን። ትግላችሁና ሐሰባችሁ ሕዝባችንን በፋይናንስ በኢኮኖሚው ዘርፍ አክርካሪውን በመምታት የኑሮ መሻሻል እንዳይኖረውና የድሀ ድሀ ሆኖ ለማኝ ትውልድ እንዲፈጠር በመሆኑ ሙስሊሙ ማሕብረሰብ ይመርጠኛል ብላችሁ አትድከሙ። ላለፉት ለ11 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋከልቲ ያስተማሩትንና የዓለም አቀፉ የቢዝነስ ጥናት ኩባንያ ዴሎይት የኢትዮጵያ ቢሮ የሂውማን ካፒታል ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ ሙከሚል በድሩ ''ለአንድ ባንክ ሁለቱንም አገልግሎት መሳ ለመሳ መስጠት ምንድነው ችግሩ? በወለድም ያለ ወለድም ማለቴ ነው።ራሱን የቻለ 'ኢስላሚክ' ባንክ ማቋቋም ለምን አስፈለገ?'' ተብለው ከ BBC ጋዜጠኛ ለተጠየቁት ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፦ በእምነት ምክንያት ወይም በግል የሕይወት መርህና ፍልስፍና ወለድን የማይጠቀሙ የኅብረተሰብ ክፍሎች አሉ። ልክ አራጣን እንደሚጸየፉ የተለያየ እምነት ተከታዮች ሁሉ፤ ወለድን የማይፈቅዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች አሉ። እነኚህን ለማካተት የፋይናንስ አማራጭ ማቅረብ አለብን። ለዚያም ነው ወለድ አልባ ባንክ 'ኢንክሉሲቭ ባንክ' የሚባለው። 'አካታች ባንክ' እንደማለት። በአገር ደረጃ ብዙ ቁጥር ነው ይሄ። እነዚህን [የኅብረተሰብ ክፍሎች] ወደ ፋይናንስ ተቋም ካላመጣናቸው ምጣኔ ሀብቱ የተቀነጨረ የተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍል እየፈጠርን ነው ማለት ነው። ይህ ደግሞ ዞሮ ዞሮ አገርን ይጎዳል። ጠያቂው፦"ራሱን የቻለ 'ኢስላሚክ' ባንክ ማቋቋም ለምን አስፈለገ ነው የኔ ጥያቄ?' ወለድ ነጻ የሚፈልግ ተገልጋዮች የባንክ መስኮቶች አሉላቸው አይደለም እንዴ? ለዚያውም 10 ባንኮች..." ●በብዙ ደረጃ [የተንሸዋረረ] አስተሳሰብን ያዘለ ጥያቄ ነው የጠየቅከኝ። አንደኛ ባንክ ማቋቋም መብት ነው። በቂ ሱቆች አሉና ንግድ ፍቃድ አታውጡ ይባላል እንዴ? በቢዝነስ መርህ የሚያስኬድም አይደለም። አዋሽ ባንክ እያለ ለምን ዳሽን ተከፈተ እንደማለት ነው። በአመክንዮም ስሜት የሚሰጥ ነገር አይደለም። አገልግሎቱን አስፍቼ ብከፍት ያዋጣኛል ያለን ነጋዴ/ባለሀብት ግዴለም ጠባብ መስኮት ይበቃሃልና ይቅርብህ አይባልም። ●ሁለተኛ የዛሬ 10 ዓመት ገደማ ነው ብሔራዊ ባንክ ለወለድ ነጻ አገልግሎት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍላጎት አለ የሚል ጥናት ያወጣው። በመስኮት ደረጃ ያሉ ባንኮች የሚሰጡት አገልግሎት ደግሞ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። [የወለድ ባንክ ሊያቀርባቸው የሚችሉ] አገልግሎቶቹ ተሟልተው እየተሰጡ አይደለም። አገልገሎቱ በደንብ እየተሰጠ ነው የሚባለው ምናልባት 'ሙራባሃ' የሚባለው ሰርቪስ ብቻ ነው። ይቺ ግን አንድ አገልግሎት ብቻ ናት። በአሁኑ ሰዓት በመስኮት የማይሰጡ በጣም ብዙ የወለድ ነጻ የፋይናንስ አገልግሎቶች አሉ። መስኮቱ ጠባብ ነው። ይሄን ያዩ ሰዎች መስኮቱን ባንክ እናድርገው ቢሉ ምንድነው ችግሩ? ●ሦስተኛ ከወለድ ጋ [በሩቁም ቢሆን] አልነካካም ብሎ ከፋይናንስ ዘርፉ ገለል ያለ በርካታ ሕዝብ አለ። ይህንን የምልህ ባንክ ተጠቃሚን ብቻ አይደለም። ባንክ ላይ ባለቤት መሆን የሚፈልግም ጭምር ነው የምልህ። አሁን [ለምን ራሱን የቻለ] የወለድ ነጻ ባንክ ትከፍታለህ ስትለው በሌላ ቋንቋ ምን እያልከው ነው...ግዴለም ከኔ ሱቅ ስኳርም ሳሙናም ግዛኝ። አንተ ግን ሱቅ እንዳትከፍት እያልከው ነው። ጠያቂ፦"በወለድ የሚሠሩ ባንኮች ከወለድ ነጻ አገልግሎት እየሰጡም ከነሱ ጋ መሥራት የማይፈልግ ሰዎች አሉ እያሉኝ ነው?'' ●[ትክክል] ለዚህ ሌላ ማሳያ የሚሆን ነገር ልንገርህ። በወለድ ምክንያት ከባንኮች ጋ ላለመነካካት በርካታ ሰዎች ኮንዶሚንየም ዕድልን አሳልፈዋል። ብዙ ጥናቶች ዜጎች በወለድ ከሚሠሩ ባንኮች ጋ ላለመነካካት ገንዘባቸውን ወደ ባንክ ይዘው እንደማይመጡ አሳይተዋል። ዜጋን በሚከተለው መርህና እምነቱ ከፋይናንስ ተጠቃሚነት ማግለል ደግሞ ኢፍትሃዊነት ነው። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬ የቴሌግራም ቻናል-https://t.me/MujibbinISLAM ስለፍትህ እንጮሀለን፣ ሠላምን እንሰብካለን፣ አንድነትንና መከባበርን እንሻለን!
Показать все...