cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)

ይህ የጳውሎስ ፈቃዱ አገልግሎት ሲሆን፣ አብያተ ክርስቲያናትና ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀት እንዲጎለብቱ መትጋትን በዓላማነት አንግቧል። youtube.com/PaulosFekadu fb.com/PaulsPulpit/ +44-7491-896592

Больше
Рекламные посты
3 610
Подписчики
Нет данных24 часа
+67 дней
+2830 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Показать все...
እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 35)

ክርስቶስ በገዛ ደሙ ወደ መቅደስ በመግባቱ ክርስቶስና ደሙ የተነጣጠሉ አድርገን ማሰብ ግን የለብንም። ክርስቶስ ሊቀ ካህንም መሥዋዕትም ነውና። ይህም ከብሉይ ኪዳኑ ጥላ በእጅጉ ይልቃል። ምክንያቱም የብሉይ ኪዳን ጥላዎች ሊቀ ካህናቱ ስለ ሕዝቡ መሥዋዕት ማቅረቡን እንጂ ሊቀ ካህናቱ ራሱን በመሥዋዕትነት ማቅረቡን አይናገሩም። በብሉይ ኪዳን የኀጢአት መሥዋዕት ሲቀርብ፣ ኀጢአተኛውን የሚወክለውና በኀጢአተኛው ምትክ የሚቀርበው የታረደው በግ ወይም ፍየል እንጂ መሥዋዕት አቅራቢው ካህን አይደለም። መሥዋዕቱ ያለ ካህኑ ኀጢአተኛውን ሊወክል በቂ ነው። ታዲያ የካህኑ ሥራ ምንድን ነው? በብሉይ ኪዳን በስርየት ቀን መሥዋዕት የሚያቀርበው ሊቀ ካህናቱ ነው። መሥዋዕቱ ኀጢአተኛውን ሊወክል በቂ ቢሆንም፣ ካህኑ በሌለበት በጉ ወይም ፍየሉ በመሥዋዕትነት ወደ እግዚአብሔር አይቀርብም። መሥዋዕቱ ራሱን በመሥዋዕትነት ለመሥዋዕት ተቀባዩ ለማቅረብ አይቻለውምና። ሊቀ ካህናቱ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜም የመሥዋዕቱን ደም በመሠዊያው ላይ በመርጨት ሕዝቡንና ቤተ መቅደሱን (የመገናኛ ድንኳኑን) ከርኩሰት ያነጻል (ዘሌ. 16፥15-19)። በዚህም እግዚአብሔር በኪዳኑ መሠረት ከሕዝቡ ጋር እንዲኖር ለማመቻቸት መሠዊያውን ያበጃጃል። ስለዚህ መሥዋዕቱ ራሱን በራሱ ለእግዚአብሔር ሊያቀርብ አይቻለውም። ያለ ካህን መሥዋዕት የለም። ይህን በልቡናችን ስንጨብጥ ነው በትእምርቶችና በተምሳሌቶች የታጨቀውን የዕብራውያን መልእክት ጭብጥ የምናስተውለው። በኀጢአተኞች ምትክ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እግዚአብሔር አስቀድሞ በመሠዊያው ላይ እንዲደረግ የፈለገው ሁሉ በመስቀሉ ላይ ሆኗል። የኢየሱስ መሥዋዕትነት ለሁሉ ይበቃል። ነገር ግን ይህ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር መቅረብ አለበት። እናም በሰማያዊ ስፍራ ይህን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረበው፣ ደሙን ይዞ ወደ ሰማያዊቱ መቅደስ የገባውም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዕብ. 9፥12)። እንከን የለሹ ካህን፣ እንከን የለሹን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ። ቅዱሱ ካህን የገዛ ደሙን ይዞ ወደ ቅድስት ገባ። ከሁሉ የሚሻለው ካህን፣ ከሁሉ የተሻለውን መሥዋዕት፣ በምትሻለው መቅደስ ውስጥ አቀረበ። ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስ፣ መሥዋዕቱም ኢየሱስ። ምንኛ ድንቅ ነው!

👍 7 4🔥 1
01:14
Видео недоступноПоказать в Telegram
5.94 MB
🙏 33👍 20 15🥰 7🤔 6
“የእግዚአብሔር ምርጫ conditional ነው” እና “የእግዚአብሔር ምርጫ unconditional ነው” የሚሉና ጎራ ለይተው የሚያቆራቁሱ ነገረ መለኮታዊ ሙግቶች በወንጌላውያኑ ጎራ መኖራቸውን አውቃለሁ። እኔ ግን ይህ አካሄድ ታውቆ የማይጨረሰውን እግዚአብሔርን እኛ ባበጀነው ሳጥን ውስጥ ለመክተት የሚደረግ ከንቱ ጥረት ከመሰለኝ ከራርሟል። ከሰሞነኛ ንባቤ ልነሣ፦ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ያዕቆብ መመረጥና ስለ ኤሳው አለመመረጥ ሲናገር፣ “ልጆቹ ገና ሳይወለዱ፥ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ፥ ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ” በማለት ያስረዳል (ሮሜ 9፥11)። ይህ ምርጫ ያዕቆብና ዘሮቹ ለኪዳን ወራሽነት መመረጣቸውን ታሳቢ የሚያደርግ ነው። በነገረ መለኮት ትምህርት ስለ እግዚአብሔር እንደሚታወቀው እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል። ስለዚህ በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን ያውቃል። እናም ያዕቆብና ኤሳው ምን ዐይነት ሰዎች እንደሚሆኑና የሕይወት መንገዳቸው ምን እንደሚመስል ለማወቅ እስኪወለዱና ሕይወታቸውን እንዲኖሩ መጠበቅ አያስፈልገውም። ዳዊት፣ “የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ” ያለው ለዚህ ነው (139፥16)። ታዲያ ሁሉን የሚያውቀው እግዚአብሔር ያዕቆብና ኤሳው ምን ዐይነት ሰዎች እንደሆኑና ሥራቸው ምን ዐይነት እንደሚሆን እያወቀ ነው የመረጣቸው ማለት ነው? ስለዚህ ከሁለቱ ማንኛቸውን መምረጥ እንዳለበት መዝኖ የተሻለውን ነው የመረጠው? ወይስ እግዚአብሔር ሁሉን ዐዋቂነቱን ወደ ጎን አድርጎ፣ ምንም እንደማያውቅ ሆኖ መርጧቸዋል ማለት ነው? ለመሆኑ እግዚአብሔር በዚህ መልኩ አንድ ነገር የማያውቅ መሆን ይችላል? ወይስ ምን?
Показать все...
51🤔 25👍 15👎 3
Показать все...

👍 8 1
ኢሳይያስ 6 ላይ መላእክቱ እግዚአብሔርን ላለማየት ፊታቸውን የሸፈኑት ኀጢአተኞች ስለሆኑ አይደለም፤ ፍጡራን ስለሆኑ ነው።
Показать все...
83👍 29🤔 13
Показать все...

13👍 4🙏 2
Показать все...
Aster Abebe - New Gospel Song - Litarekegn Wedo (ሊታረቀኝ ወዶ)

#asterabebe #Litarekegn wedo #Bezemeneayalehu #newamharicgospelsong #መዝሙር #mezmur #worship Unauthorized distribution and reupload of this content is strictly prohibited Get on 📲APP STOR

https://itunes.apple.com/us/album/ክብር-የበቃህ-ነህ-vol-1/id1227931133

Get on 📲 TUNES

https://play.google.com/store/music/album/Aster_Abebe_ክብር_የበቃህ_ነህ_Vol_1?id=B2qof75mhvvzfc2erabr7ojzwby

Copyright © Aster Abebe

https://youtu.be/6s-xG7PDJLU

Song Written by Aster Abebe Music Arrangement Fikadu Betela Mixing and Mastering Robel Dagne Lyrics የመራቄ ርቀት ከኣብ መለያየቴ ማን ግድ ብሎት ነበር የመንከራተቴ ክብሩ በጎደለው ህይወት ስመላለስ ርቄ ከፈቃዱ መታደሴ እስኪደርስ ከመላዕክት መካከል ወይም ከሰማዕታት ቀድመው ከነበሩት ከተባሉት አባት ማን በጥቂት ጣረ ወደ አብ ሊያስጠጋኝ ህጉስ ምን ፈየደኝ ይብሱን አጣላኝ አብ አባት ራርቶልኝ ሊታረቀኝ ወዶ በእቅፉ ያለውን አንድ ልጁን ልኮ ሃጥያት የማያውቀውን ሃጥያት አደረገው ከድምፁ ያራቀኝን የዕዳ ጽህፈቴን በደሙ ገሰሰው ማነው ያለው ተገዳ ነው? የራሱ ያደረገኝ መውደዱ ማርኮኝ ነው ማነው ያለው ቸግሯት ነው? ርስቱ ያደረገኝ ፍቅሩ ገዝቶኝ ነው መች አጠረች እጁ ከማዳን መች ተሳናት ጆሮው ልትሰማን እውነት ስፍራን አጥቶ ጽድቅ ርቆ ቆሞ ህያው ነፍስ በሙሉ ለሃጥያት ታድሞ ማላጅ እንደሌለ ምድርን አየች አይኑ ጽድቁም አገዘችው ፈጠነች ማዳኑ በገዛ ክንዶቹ መድሃኒት ሆነልን ፍጥረቱ ታደሰ በስላሴ ምክር

35👍 9🙏 6🔥 1🥰 1
Показать все...

12👍 5🥰 2
Показать все...
SOPHOS AFRICA UK (SAUK)

Project: SAUK Community Harmony Project (Project Harmony) Purpose of the Project: Project Harmony exists to serve the Ethiopian Diaspora in England through facilitating a platform towards communal harmony and collective wellbeing characterised by understanding and trust. Survey Questionnaire: The questions are designed to gather basic information about personal experiences, perceptions of community dynamics, and the impacts of broader social and political issues on interpersonal relationships within the Ethiopian community in England. Purpose of the Survey: To gather basic data that will inform our attempt to create and sustain an inclusive platform of conversation, organise meetings and workshops, and foster inter-communal relations based on understanding and trust.

👍 4 1
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.