cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Habesha🇪🇹 Daily

#Join & share our channel 💪 ይህ ቻናል ኢትዮጵያዊነት ጎልቶ የሚታይበት የተለያዩ ቴክኖሎጂ ስፖርት የትልልቅ ሰዎች ንግግሮች እና ሌሎችም መረጃዎች የሚዳሰሱበት ነው። Contact me 📩 @hailexo7 @miz10 Phone ~0912330800 ~0943520906

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
162
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ለዲሽ ባለሙያዎች ጠቃሚ ምክሮችን ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 1- ማንኛውንም ሳተላይት ስትሠሩ አሪፍ የሆነ LNB ተጠቀሙ የራሳችሁ የሆነ ይህም ሠው ቤት ስትሠሩ የቆየ ወይም በከፊል የተበላሸ ስለሚያጋጥም የራሳችሁ የሆነ Strong lnb ያስፈልጋል። ♨️ VARZISH ለመስራት Spartacus/Lifestar 0.2 db የምትጠቀሙ በvertical ስሩት በጣም ጥሩ ኳሊቲ ታገኛላችሁ ። Satcom LNB 0.1Db Lifestar LNB 0.2 Db ምርጥ የሆኑ Lnb ዎች ናቸው። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 2- ናይል ሳት የምትሠሩ በተለይ በ Analoge Finder ከሆነ 11938 H 27500 ወይም 12226 H 27500 በነኚህ ሪሲቨር ላይ እስከ 55-60% መምጣት አለበት ሁሉም ቻናሎች በጥራት እንዲሠሩ ከፈለጋችሁ ። ነገር ግን 11512 v 27500 በዚ መስራት ጥቅም የለውም እሱ 78 መቶ ሌሎቹ 40 ሊሆን ስለሚችል ማለት ነው። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 3- Yahsat /VARZISH የምትሠሩ ከሆነ ደግሞ በ11766 V 27500 ወይም 11881 V 27500 ስሩ ከዛን በነኚ እስከ60- 70 ሲመጣ varzish ይከፍትላችዋል። ሌላው ደግም ።Dstv እየገባ ስለምትቸገሩ በ11881 ስታገኙ search አርጉ ከዛን GEM LIFE,GEM CULTURE የሚሉ ቻናሎች ሲገቡ ትክክለኛውን ያህ ሳት ነው የፈየሠራችሁት ማለት ነው። ነገር ግን በ11785 H የምሠሩ ከሆነ ይህ ቁጥር Eutelsat 36° (DSTV),ላይ ስላለ ትቸገራላችሁ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 4- Varzish ለመስራት ጥሩ የሆነ ሠሀን ያልተጣመመ በተለይ ደግሞ LNB የምናስርበት ዘንግ ቀና ካለ ወይም ወደ ሠሀኑ ከተለጠጠ የፈለገ ቢሆን ከ40 ከፍ አይልላችሁም vARZISH ደግሞ አይታሠብም ስለዚህ ብዙ ከመልፋታችሁ በፊት ዘንጉን በደንብ ተመልከቱ። አጠገቡ ሌላ ሠሀን ካለይህ ነገር አዲስ ዲሽ ላይ ራሱ በብዛት ያጋጥማል። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 5- ከቅርብ ጊዜያት በተደጋጋሚ የሚከሠተው ነገር ደግሞ የዲሽ Coaxial (ገመድ) በጣም fake ሲሆን ይህም ኳሊቲ እየመረጠ ነው የሚገባብን ለምሳሌ 11512 እስከ 78 መቶ 12645 15-25 ሊመጣ ይችላል ስለዚህ ገመድ ስትገዙ በጣም ጥንቃቄ አድርጉ። ቻናላችንን ሸር በማድረግ ቤተሰብ ይጨምሩ። @habeshdaily
Показать все...
ስለ WIFI ROUTER ምን ያህል ያውቃሉ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ WIFI ROUTER ማለት የኤሌክትሮኒስ እቃ ሲሆን ከኢንተርኔት ያገኘውን ዳታ ወደ ምንፈልጋቸው እቃዎች እንደ Reciver ,computer,Mobile የመሣሠሉት ሲሆን ከኢንተርኔት ያገኘውን ዳታ ወደ ራዲዮ ሲግናል የሚቀይርልን መሣርያ ነው ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ በአሁኑ ሠአት ሁለት አይነት ራውተሮች ሲገኙ የቅርቡ 802.11Ac የሚባለው 5GHZ ሲሆን በቀላሉ 50 YOUTUBER VIDEO በተመሣሣይ ሠአት በተለያዩ እቃዎች እንደማጫወት ይቆጠራል። የፍሪኩዌንሲው መጠን ሲጨምር ፍጥነቱ ይጨምራል ነገር ግን ረዥም መንገድ መጓዝ አይችልም ። የምታውቁ ከሆነ ሀገራችን ባይገባም የ5G ኔትዎርክ የጀመሩ የውጪ ሀገራት አሉ።ታድያ 5G ማለት ፍጥነቱ በቀላሉ 2Gb ፋይል ለማውረድ ደቂቃ ብቻ ነው የሚወስድብን ይህም ፍጥነቱ በጣም የሚገርም ሲሆን ነገር ግን 5G የራሱ የሆነ ደካማ ጎን አለው። ይህም ኔትዎርኩ በግንብ በዛፍ በመስታወት ምናምን ይሸፈናል። በቀላል አማርኛ 5g tower ያለበት ቦታ ላይ ከፊትለፊቱ ረዥም የሆነ ህንፃ ቢኖር ኔቴዎርኩን በጣም የመቀነስ ባህሪ አለው። ሌላው 5g ኔትዎርክ ሀገራችን ለመዘርጋት ከላይ የጠቀስኩትን ችግሮች ለመቅረፍ ቢያንስ በ10 m ርቀት Tower ሊኖር ያስፈልጋል። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ MODEM ማለት ኢንተርኔት Connect እንድናደርግ የሚጋብዘን Gate way ሲሆን Router ደግሞ የሚያከፋፍልንን ኤሌክትሮኒስ መሣርያ ነው። ROUTER ላይ የሚገኙ LED INDICATOR [ የሚበሩ 3 መብራቶች አሉ እነሱ 1-POWER LIGHT ይባላል። ራውተራችን power ሲያገኝ የሚበራው ነው። 2- ADSL light ይህ ደግሞ ሁሌም Constantly መብራት አለበት ይህም ከውጪ ከTerminal ሉ የተሳበው phone cable በትክክል መስራት አለበት።በተጨማሪም ከrouter ችን ጀርባ ADSL የሚለው port ላይ የተሠካው CORD ትክክል የሆነ ወይም Short ያልሆነ መሆን አለበት። 3- Connection/Internet Light ይህ መብራት የሚጀምረው Router ችን በትክክል Configure ከተደረገ ብቻ ሲሆን ልክ ሲበራ የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት እንችላለን ማለት ነው። Light blink የሚያረግ [ የሚርገበገብ ሲሆን] በትክክል እየተጠቀምን / እየሠራ ነው ለማለት ሲሆን የማይርገበገብ ከሆነ Configuration ወይም Server ላይ ችግር አለ ማለት ነው። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ መረጃዎቹን Share በማድረግ ይተባበሩን። @habeshdaily
Показать все...
ስለ ስማርት ስልኮች ጠቃሚ መረጃዎችን ለናንተ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ Refresh rate ይህ ማለት ስክሪኑ የስልካችን ራሱን ነፃ የሚያረግበት ሠአት ሲሆን just ኮምፒውተር ላይ F5 የምንጫነው ኮምፒውተራችን እንዳይጨናነቅ ወይንም ከተጨናነቀ ራም ሚሞሪን Free ለማደድረግ የምንጫነው በተን ሲሆን ስልክም ላይ እንዲ ነው። ነገር ግን High refresh rate ያለው ስልክ ማለት ስክሪኑ በጣም አክቲቭ ነው።ትላልቅ ጌሞችን ስንጫወት ድንዝዝ አይልብንም ማለት ነው። 💢 በአሁኑ ሠአት የሚሠሩት ምርጥ የሚባሉት ስልኮች 90እና 120 HZ ናቸው።ከዚህ በታች ያሉት 60 HZ የሚባሉ ስልኮች ሲሆኑ High refresh rate ተብለው አይጠሩም። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ Screen protection ስልካችን ወድቆ ሲሰበር የላይኛው ብቻ ተሠብሮ ነገር ግን ይሠራል ይህ ማለት screen protection የሚባለው ይህ glass ሲሆን ጥሩ የሚባሉ በአሁን ሠአት የሚሠሩ ስልኮች Gorilla Glass 5 እና 6 ናቸው። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ Multi touch ስልካችን multi touch Support ያረጋል የሚባለው በተመሳሳይ ሠአት ሁለት ነገር ወይም ከዛ በላይ Select የምናረግ ከሆነ ነው። ለምሳሌ ሙዚቃ ለመላክ አንድ በአንድ ሲሆን የምንመርጠው support የሚያረግ ስልክ ከሆነ ግን በአራትም ሦስት ጣታችንም ስንመርጥ mark ያረገዋል። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ PROCESSOR Snapdragon ይህ ደግሞ በጣም ምርጡ የ processor አይነት ሲሆን ይህንን የሚጠቀሙ ስልኮች በተሻለ ሁኔታ process ያረጋሉ። ግን ሁሉም በየጊዜው የተለያየ Version ይወጣለታል። ጥሩ አቅም እንዲኖረው ከበፊቱ ባትሪ ፍጆታው እንዲቀንስ image ጥራቱ እየጨመረ እንዲመጣ ተብሎ ነው የሚሠራው። Snapdragon 660,720G 855,865 እየተባለ ሲሆን ምርጦቹ 855 እና 865 ናቸው። Samsung s20 ultra ላይ ሁለት አይነት ቺፕ ተጠቅመው ለሀገራቸው ኮርያ እና ለEurope ሀገራት የSnapdragon ን ሲሆን ወደ ሌላ ሀገራት ደግሞ Exynos ን ተጠቅመዋል። ይህም Exynos ቺብ ከsnapdragon በላይ ባትሪ ይጨርሳል እናም ሳምሠንግ ብዙ ትቺቾችን አስተናግዷል። በተመሣሣይ ብር ለምን ሁለት አይነት ነገር ሆነ ተብሎ። ♨️ ሳምሠንግ በአዲሱ Note 20 ላይ የExynos chip እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል።Exynos 990 ስለዚህ የNote 20 ስልክ ዋጋው የተጋነነ እንደማይሆን ይጠበቃል። ♨️ Apple ደግሞ A13 ሲሆን አሁን ላይ እየተጠቀመ ያለው Iphone 12 በቅርቡ የሚወጣው ላይ A14 ን chip ይጠቀማል የሚሉ ዜናዎች አሉ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ Screen type የተለያዩ የስልክ አምራቾች የተለያየ አይነት ስክሪን የሚጠቀሙ ሲሆን ሳምሠንግ አዲስ የDisplay አይነት ያለው ስክሪን Note 20 ላይ እንደሚጠቀም ተናግሯል። ይህም ከs20 በላይ ራሱ refresh rate ን የሚቀያይር የስክሪን አይነት ነው። ስልኩን ትላልቅ ነገሮችን ስንጠቀምበት በ120Hz ሲሠራ ነገር ግን Always on display እና ትናንሽ ነገሮችን Process ስናረግ በትንሽ Refresh rate ይሠራል። ⚠️ refresh rate በጨመረ ቁጥር ባትሪ ፍጆታው ይጨምራል።ያው ስልካችንን smooth ቢያረግልንም ማለት ነው። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ መልካም ምሸት @habeshdaily
Показать все...
የተቃውሞ ውበት “ስኬታማ ሰው ማለት ሰዎች የሚወረውሩበትን የተቃውሞ ድንጋይ መሰረት ለመጣል የሚጠቀምበት ሰው ነው” - David Brinkley የማይንቀሳቀስንና የማይሰራን ሰው ብዙም ተቃውሞ ሲገጥመው አይታይም፡፡ የሚያልምን፣ የሚሰራን፣ ለውጥን ለማምጣት የሚነሳሳንና ውጤትን የሚያስመዘግብን ሰው ግን ለመቃወም ሃሳብ ሰጪው ብዙ ነው፡፡ በሕይወትህ የመጀመሪያውን የስኬት ጣእም አጣጥመህ ሳትጨርስ የመጀመሪያውን የተቃውሞ ድንጋይ ወደ አንተ ሲወረወር ማየትህ የማይቀር ነው፡፡ ሆኖም፣ አንድ እውነታ መዘንጋት የለብህም፣ ለስኬታማነትህ መዋጮ የሚያደርጉት የሚደግፉህና የሚያደንቁህ ሰዎች ብቻ አይደሉም፤ የሚቃወሙህና የማይቀበሉህም ሰዎች ጭምር እንጂ፡፡ የሚጋፉህና የሚቃወሙህም ሰዎች በሕይወትህ ትልቅ ስፍራ እንዳላቸው መዘንጋት የለብህም፡፡ ሰው በተቀባይነት ውስጥ ይነሳሳል፣ በተቃውሞ ውስጥ ደግሞ ይጠነክራል፡፡ ተቃውሞ ራስህን ካለማቋረጥ እንድትመለከትና እንድትፈትሽ ያስታውስሃል፡፡ ተቃውሞ ነገ የተሻለ ስኬት በእጅህ ሲገባ ከተከፈለበት መስዋትነት አንጻር ለስኬቱ እንድትጠነቀቅ ይረዳሃል፡፡ ተቃውሞ ነገ የስኬት ከፍታ ላይ ስትደርስ ስኬቱን በጨዋነት እንድትይዘው የሚስችልህን ባህሪይ ይገነባልሃል፡፡ መለስ ብለህ ታሪክን አንብብና ለአለምም ሆነ ለሕብረተሰባችን መልካም ፈርን ቀድደው ያለፉ ሰዎችን ጎዳና አጢን፣ ምናልባት ለማመን የሚያስቸግርህን ውጣ ውረድና ተቃውሞ አሸንፈው እንዳለፉ ትደርስበታለህ ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡ አየህ፣ ብዙ ሰዎች የሚቃወሙትን እንጂ የሚደግፉትን አያውቁም … የሚያፈርሱትን እንጂ የሚገነቡትን አያውቁም … የሚጠሉትን እንጂ የመወዱትን አያውቁትም፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ከላይ የተዘረዘሩትን አሉታዊ እርምጃዎች ከወሰዱና የተመኙትን አሉታዊ ውጤት ካገኙ በኋላ አዎንታዊ እቅድ ስለሌላቸው ሌላ የሚቃወሙትን፣ የሚያፈርሱትንና የሚጠሉትን ፍለጋ ይቅበዘበዛሉ፡፡ አንተ ግን ዝም ብለህ ዓላማህ ላይ አተኩር፡፡ ዶ/ር ምህረት ደበበ @habeshdaily
Показать все...
የተቆለፈ ኮምፒውተር እንዴት በቀላሉ መክፈት እንችላለን ? ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ የኮምፒውተራችንን Password በድንገት ብንረሳው በቀላሉ እንዴት መክፈት እንደምንችል ለናንተ ልክ ስልካችንን Passowrd ወይም Pattern ከረሳን ስልካችንን በሁለት አይነት መንገድ መክፈት እንደምንችለው ሁሉ የኮምፒውተራችንንም መክፈት እንችላለን። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ የሚያስፈልጉን ነገሮች 1 Window installation Media ይህ ምንድነው Window 8 ወይም 10 የተጫነበት Cd ወይም boot የተደረገ ፍላሽ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ከዛን ኮምፒውተራችንን ላይ Cd እንጨምራለን። ፍላሽ ከሆነ ደግሞ እንሰካና ኮምፒውተራችንን እናጠፋለን ከዛ boot ማምጫ የኮምፒውተሮች F2,F4,F8,F10,F12 ሊሆን ይችላል ከነኚ በአንዱ ወደ boot device ሲወስደን F10 እንጫናለን ከዛ Cmd[ Command promote ] ይከፍትልናል። ካልከፈተ ለአንዳንድ ኮምፒውተሮች Shift +Fn +F10 ነው ከዛን ከታች ያሉትን መተግበሪያዎች እንፅፋለን ➡️ Type “cd c:” without quotation then hit enter ➡️ Type “dir” ከዛን Enter ➡️ Windows የሚለው ዝርዝር እስከሚመጣ ድረስ ፊደሉን እየቀያየሩ መሞከር Eg. “D:” hit enter then “dir” hit enter then check “windows” “E:” hit enter then “dir” hit enter then check “windows” ➡️ ከዛ በ ስእሉ ላይ የሚታየዉን በትክክል ይጻፉ ➡️ “cd windows/system32” hit enter ➡️ Type “rename osk.exe osk.old” hit enter ➡️ Type “rename cmd.exe osk.exe” hit enter ➡️ አሁን 75% ሚሆነዉን ስራ ጨርሰናል ከዚ ቀጥሎ computerun restart ማድረግ ➡️ ከስር በግራ በኩል የሚታየዉን icon መጫን ➡️ On-Screen Keyboard የሚለዉን መምረጥ ➡️ command promote display ሲሆን ስእሉ ላይ ያለዉን command ማስገባት ➡️ Type ”net user” hit enter ➡️ Type ”net user help *” hit enter —---- help ማለት የ computeru ስም ነው ከዛ ምትፈልጉትን password ማስገባት ትችላላችሁ ነገር ግን Password እንድይኖረው ከፈለጋቹ ደሞ hit enter ሁለቴ አሁን የComputer ቹ የይለፍ ቃል ተቀይሯል ማለት ነው። ከዛን Log in በቀየራችሁት Password መሆን ትችላላችሁ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ መልካም ምሽት @habeshdaily
Показать все...
እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም .. የኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው..ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው ብዬህ ብከራከርህ ቂል..... ነኝ.... እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ነው .... እንደ እኔ ደግሞ የእኔ እውነት ይሆናል .... ባንተ እውነት ለማመን ... ያንተን ጫማ .... መሆን የለብኝም የቆምኩበትን ሆኜ ለስህተትህ ሂሣብ እየሠራሁ ስዳኝህ እቀሽማለሁ (የራሣችንን እውነት እንኑር) ጠበኛ እውነቶች በሜሪ ፈለቀ
Показать все...
እውነት በሌለበት አለም ለመኖር ...... አልወለድም...... እውነት ነፍሳችን ውስጥ ትዘምራለች እና እሷን በመኖር እናድምቃት ………
Показать все...
ስኬትን ፍለጋ “ስኬትን ከፈለክ ስኬትን ዓላማህ አድርገህ አትያዝ፡፡ የምታምንበትንና የምትወደውን ነገር ከልብህ ስታደርግ ስኬት ራሱ ይመጣል” - David Frost ለትክክለኛ አላማ መቆም ስኬትን ይቀድማል እንጂ ስኬት አላማን አይቀድምም፡፡ አንዳንድ ሰዎች፣ “ቢሳካልኝ ኖሮ ይህንና ያንን አደርግ ነበር” በማለት በገንዘብና በተለያዩ አቅጣጫዎች “ቢሳካላቸው” ሊያደርጉ ስለሚፈልጉት የወደፊት አላማ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ አንድ ማስታወስ ያለባቸው እውነታ ግን አንድን አላማ ይዘው መስራታቸው ወደ ስኬት እንደሚወስዳቸው ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ ተሳካላቸው በመባል የሚታወቁ ሰዎች ለስኬት የኖሩ ሰዎች ሳይሆኑ ለአንድ አላማ በጽንአት የኖሩ ናቸው፤ ያንን ሲያደርጉ ስኬት ተከተላቸው፡፡ ለስኬት የሚኖር ሰው ስኬት ያጣ ሲመስለው ያቆማል፡፡ ለአላማ የሚኖር ሰው ግን ስኬት ያላገኘ ቢመስለውም እንኳ ጉዞውን ይቀጥላል፣ ምክንያቱም አላማ የተሰኘውን የስኬቶችን ሁሉ ስኬት በእጁ ጨብጧልና ነው፡፡ “የምትወደውንና መልካም የሆነውን ነገር አድርግ፣ ያንን የምታደርገውን ነገር ደግሞ ውደደው” የሚለው አባባል እውነት ነው፡፡ ስኬትን ፍለጋ ከአላማህ ውጪ የሆነን “ታላቅ” ነገር ከማድረግ፣ አላማን በመከተል አስቸጋሪ ጎዳና መጓዝ ይመረጣል፡፡ በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ
Показать все...