cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Gospel of christ

❝ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።❞ —ሮሜ 1: 3-4 👉ለበለጠ መረጃና አስተያየት 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Mullergospel

Больше
Рекламные посты
210
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
የኪንታኪ ግዛት ነዋሪዎች 6300 አከባቢ ይጠጋሉ በአስበሪ ዩንቨርስቲ የተነሳው ሪቫይቫል ግን ከ 20000 በላይ ሰዎችን በቀን ያስተናግዳል!!!!!አስባችሁታል የእግዚአብሔር ጉብኝት ሲሆን የህዝብ ቁጥር ብዛት ትንሽ ይሆንና የእግዚአብሔር ጉብኝት የሚያመጣው ህዝብ ብልጫ ይኖረዋል  ወደምትኖሩበት ከተማ ይህ እንቅስቃሴ ቢመጣስ የሚኖረውን ተፅዕኖ አስቡት!!!!
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ይህቺ በስክሪኑ ላይ የምትመለከቷት እህት እሷ እና ባለቤቷ በቺሊ የሚገኙ የቤተክርስቲያን መጋቢዎች ናቸው። አስገራሚው ነገር በዚህ የአስበሪ ሪቫይቫል ለመካፈል ለበረራ ቲኬት የሚሆን በቂ ገንዘብ ስላልነበራቸው ሁለቱም መኪኖቻቸውን ሽጠው ወደስፍራው አቅንተዋል።😭😭 🔥🔥ወዳጆቼ ክብር ያስፈልገናል🔥🔥 #መለኮታዊ_ጉብኝት #ሪቫይቫል_ለምድሬ #asburyrevival2023 #asburyreviva
Показать все...
%E1%8A%AB%E1%88%88_%E1%88%9D%E1%8A%95%E1%88%9D_%E1%8A%90%E1%8C%88%E1%88%AD.m4a22.29 MB
 ⚡️ እንድርያስ ወደ ኢየሱስ አቅራቢዉ ደቀመዝሙር የምድረ በዳው ሰባኪ መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን አሻግሮ ተመለከተና አብረዉት ለነበሩት ሁለት ደቀመዛሙርት "የእግዚአብሔር በግ" ሲል ወደ ኢየሱስ አመለከታቸው ። ይህንን በሰሙ ጊዜ ሁለቱ ዮሀንስን በመተው ወደ አመለከታቸው ወደ ኢየሱስ ገሰገሱ።ኢየሱስ የሚከተሉትን ሁለት የመጥምቁ ዮሀንስ የቀድሞ ደቀመዛሙርት በተመለከተ ጊዜ ዞር ብሎ "ምን ትፈልጋላችሁ?" አላቸው ። እነርሱም "መምህር ሆይ ወዴት ትኖራለህ አሉት?" ሲሉ ጠየቁት ።ኢየሱስም "ኑና እዩ "ሲል መለሰላቸው። እነዚህ ሁለት የዩሀንስ ደቀመዛሙርት የነበሩ ሰዎች አላመኑበትም ነበር።ተከትለዉም በመሄድ የሚኖርበትን አዩ።በዚያም ከርሱ የመዳንን ወንጌል የሕይወትን ቃል ተቀበሉ።ኢየሱስም እንዲህ አይነት ሁኔታ ከተከሉት አንዱ የጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበር።እንድርያስም ኢየሱስ ጋር ያደረገው ቆይታ የህወቱን አቅጣጫ ያስለወጠው ነበር።በዚህ ጊዜ ነው መሲሁን አምኖ የተቀበለው። እንድሪያስ ህይወቱ እንደ ተለወጠ የመጀመሪያ ተግባሩ ያደረገው ወንድሙን ጴጥሮስን መፈለግ ነበር፤ ሲያገኘውም የምስራቹን ለማብሰር ጊዜ አልወሰደበትም ነበር። መሲሑን እንዳገኘዉ ነግሮት ወደ ኢየሱስ ይዞት መጣ። ኢየሱስም ጴጥሮስን በተመለከተው ጊዜ አወቀዉ "አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፥ ነገር ግን ኬፋ ትባላለህ" ሲል ተናገረዉ። እንድርያስ ጠሪዉ ደቀመዝሙር ለእግዚአብሔር መንግስት ስራ የሚሆንን ሊያመጣ ታላቅ ሰዉ ልያመጣ በቃ።  አንድ ጊዜ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ባህር ማዶ ሲሻገር አስቀድሞ ድንቅን ና ተዓምራትን አድርጎ ነበርና ብዙ ሰዎች ተከትለውት ነበር። ሲያስተምራቸው ውሎ በመሸ ጊዜ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው በመረዳቱ ሊመግባቸው ወደደ።በዚያ ስፍራ ምንም ነገር ባለመኖሩ ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ አንዱን ከሌላ ቦታ ምግብ መግዣ ምን ያህል ገንዘብ እንዳለ ጠየቀዉ።ይህም ደቀመዛሙር ያለው ገንዘብ በቂ አለመሆኑን በመግለፅ መለሰለት።በዚህ መካከል ከደቀመዛሙርቱ አንዱ የሆነው እንድሪያስ አምስት እንጀራና ሀለት ዓሳን የያዘ አንድ ብላቴና ይዞ ወደ ኢየሱስ ቀረበ።ኢየሱስም ያንን ዓሳና እንጀራ በባረከው ጊዜ ታላቅ ድንቅ ነገር ሆነ ፤ ብዙ ሺ ህዝብ ተመግቦና ተርፎ ለመመለስ በቃ።ሁሉንም ወደ ኢየሱስ ማምጣት የሚወደዉ እንድሪያስ ምንም ትንሽ ቢሆንም በስፍራው ያለዉን ይዞ ወደ ጌታው ቀረበ።በዚያም እርሱ የተሰበሰበውም ህዝብ ታላቅ ነገርን አየ።    ኢየሱስ ታጅቦ ወደ ኢየሩሳሌም በገባበት የፋሲካ ጊዜ የግሪክ ትውልድ የነበራቸው ሰዎች ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ነበር።ስለ ኢየሱስንም ዝና ሰምተው ነበርና ሊገናኙት ወደዱ፤ይህንንም ለማድረግ ከኢየሱስ ደቀመዛሙርት አንዱ ወደ ሆነው ወደ ፊሊጶስ መጡ።ፊሊጶስም ኢየሱስ ከአይሁድ ሌላ ማንንም ሲያነጋግር ባለማየቱ ግራ ተጋባ። እስከዚያ ጊዜ ድረስ እንደሚያዉቀዉ ኢየሱስ የመጣው ለአይሁዳውያን መሲህ በመሆን ነው። ታዲያ ከግሪክ ሰዎች ጋራ ምን ህብረት ሊኖረው ይችላል።ይህንን በአእምሮ እያሰላሰለ መፍትሔ ፍለጋ ወደ ሌላኛው ደቀመዝሙር እንድሪያስ ጋ አመራ። እንድሪያስ እነዚያን ሰዎች በተገናኘ ጊዜ ሳያመነታ ወደ ኢየሱስ ይዞአቸው መጣ።ምን ዓይነት ደስ የሚያሰኝ ህይወት ነዉ።ሁሉንም ወደ ኢየሱስ ማምጣት ።   በተለያዩ የአዲስ ኪዳን ክፍሎች ስሙ ከሐዋርያት ጋራ ከመጠቀሱ ሌላ ስለ እንድሪያስ የምናነበው በተመለከትናቸው ሶስት አጋጣሚዎች ብቻ ነው።በነዚህ ስፍራ የርሱ ተግባር ተመሳሳይ ነዉ።ያገኘውን ወደ ኢየሱስ ማምጣት ።እንድሪያስ ምንም የአዲስ ኪዳንን ክፍል አልፃፈም።በታላላቅ ስብሰባዎችም ላይ ቆሞ ወንጌል ለመስበኩ የሚታወቅ ነገር የለም።ነገር ግን ጴጥሮስን የመሰሉ የመዳንን ወንጌል በሀይል ና በስልጣን የሰበኩ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ጠርቶአል።ዛሬ ቤተክርስቲያን ብዙ እንድሪያሶች ያስፈልጎዋታል። እነኚህ ሰዎች በታላላቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤቶች ገብተዉ ያልተማሩ ለውስብስብ ጥያቄዎችም መልስ የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ይህ ሁሉ በጣም መሠረታዊ ነገር አይደለም።ተፈላጊው ነፍሳትን ለጥያቄ ሁሉ መልስ ወደ አለዉ ወደ ክርስቶስ ማምጣት ነዉ።በዚህች ምድር ደግሞ ይህንን እውነት ከመናገር የሚበልጥ ምንም ነገር የለም።  
Показать все...
የተወደዳችሁ #ንቁ_የሆነ_ክርስቲያን። 1ኛ ቆሮንቶስ 16 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹³ ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ። ¹⁴ በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን። 👉ንቁ። 👉በእምነት ፀንታችሁ ቁሙ። 👉ጎልምሱ። 👉ጠንክሩ። ኤፌሶን 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵ እንግዲህ እንደ #ጥበበኞች እንጂ #ጥበብ #እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት #እንድትመላለሱ #በጥንቃቄ_ተጠበቁ፤ ¹⁶ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና #ዘመኑን_ዋጁ። ¹⁷ ስለዚህ #የጌታ_ፈቃድ_ምን_እንደ_ሆነ #አስተውሉ እንጂ #ሞኞች አትሁኑ። #ሞኝ_ክርስቲያን _ምንአይነት_ነው? 👉ጥበበኛ ሁኖ ሳለ ነገር ግን ጥበበኛ እንዳልሆነ ሰው ሁኖ ሲመላለስ። 👉ቀኖቹ ክፉዎች ሁነው ሳለ ፣ዘመኑን መዋጀት እየቻለ ነገር ግን የቀኑ ክፋት የሚሰለጥንበት ማለትም እንደቀኑ እንጂ እንደቃሉ የማይመላለስ፣ 👉በዚህ ክፉ በሆነው ቀን ውስጥ የጌታ ፍቃድን የማያስተውል ፣ ይሄንንም ያንንም የሚያግበሰብስ በሂወቱ የመጣውን ሁሉ የሚያስተናግድ፣ 👉የጌታን ፍቃድ ከማስተዋል ይልቅ በስሜቱ ብቻ የሚነዳ፣ ኤፌሶን 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁸ መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤ ¹⁹ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤ 👉ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ቃል እና በመንፈሱ ተሞልቶ ከመስከር ይልቅ በማይሆን ነገር ሰክሮ ጊዜውን ያባከነ፣ 👉በዝማሬ፣በመንፈሳዊ ቅኔ እርስ በርሳችንን ከመነጋገር ይልቅ የማያሳድግ ወሬ ስር የተጠመደ፣ 👉ስለክርስቶስ ሞኞች ነን ማለትም ስለ ክርስቶስ የሚመጣብን መከራ ሁሉ ሞኞች ልንባል እንችላለን፣ በክርስቶስ ደግሞ ልባሞች ነን 👉ስለክርስቶስ ሞኞች ብንሆን ዘመኑን ፣ቀኖችን በተመለከተ ግን ክርስቲያን ሁልጊዜ ንቁ፣ጠንካራ፣ በእምነቱ የፀና ፣ በእግዚአብሔር ቃል፣በመንፈሱ የሚሞላ፣ዘመኑን የሚዋጅ፣የጌታን ፍቃድ የሚያስተውል ነው። ሞኝ ክርስቲያን ሳይሆን ንቁ፣አስተዋይ፣ጠንካራ ክርስቲያ መሆን አለብን የዛሬ መልዕክቴ ነው ተባርካችኋል። 👉ያዳነን ያው ፀጋ ደግሞ እንዴት እንደምንኖር ያስተምረናል እና ከፀጋው ለመማር የተዘጋጀን እንሁን። #ፀጋ ይብዛላችሁ።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
“ከብዙ ውኆች ድምፅ ከባሕርም ታላቅ ሞገድ ይልቅ እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው።” — መዝሙር 93፥4
Показать все...
👑👑 #የዘላለም_ወዜ 👑👑 የተሰጠኝ አንዱ አይደለም የዋዛ                            ሲተረጎም በዛ በተሰጠኝ በአንዱ በበዛልኝ በእሱ                              ዘላለሜ ወዛ። ኢየሱስ❤
Показать все...
#ጥምቀት ምንድነዉ? 👉ለአንዳንዶቻችሁ #ሎሚ መወርወር ሊመስላችሁ ይችላል 👉ለአንዳንዶቻችሁ ደግሞ በሚያማምር አልባሳት አሸብርቆ ታቦትን መከተል ሊመስላችሁ ይችላል እንዲሁም ደግሞ ወንድና ሴት ሆኖ በየድራፍት ቤቱ እና በየጭፈራ ቤቱ አዳር መጨፈር የሚመስላቸዉም ሰዎች አሉ ነገር ግን #ጥምቀት ይህን ሁሉ ማድረግ አይደለም ።        #ጥምቀት ማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እዚህ ምድር በመጣበት ጊዜ እኛም አብረን #ሞቱን በሚመስል ሞት አብረን ወደ ዉሀዉ የምንጠመቅበት ለሀጥያት ለክፋት ፣ ለዝሙት ፣ ለመስከር ለዘፈን ፣ ለመዳራት ፣ ለጣኦት አምልኮ ፣ ለተለያየ የሀጥያት ጥፋት ውሀው ዉስጥ ጥለን #ለፅድቅ_ለቅድስና_ክርስቶስን_ለሚመስል_ማንነት ደግሞ ከዉሀዉ ዉሰጥ የምንዉጣበት ድንቅ #ባርኩት ነዉ ።    ስለዚህ ይህ ቀን ሀጥያትን እንደዉሀ #የምንጨልጥበት ሳይሆን #ለሀጥያት_የምንሞትበትና #ለፅድቅ_የምንነሳበት ቀን ነዉ። ስለዚህ በዚህ እዉነት በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ይሁንላችሁ።
Показать все...
#ጥምቀት ምንድነዉ? 👉ለአንዳንዶቻችሁ #ሎሚ መወርወር ሊመሰላችሁ ይችላል 👉ለአንዳንዶቻችሁ ደግም በሚያማምር አልባሳት አሸብርቆ ታቦትን መከተል ሊመስላችሁ ይችላል እንዲሆም ደግም ወንድና ሴት ሆኖ በየድራፍት ቤቱ እና በየጭፈራ ቤቱ አዳር መጨፈር የሚመሰላቸዉም ሰዉች አሉ ነገር ግን #ጥምቀት ይህን ሁሉ ማድርግ አይደለም ።        #ጥምቀት ማለት ጌታችን ኢየሱሰ ክርሰቶሰ ወደ እዚህ ምድር በመጣበት ጊዜ እኛም አብረን #ሞቱን በሚመሰል ሞት አብረን ወደ ዉሀዉ የምንጠመቅበት ለሀጥያት ለክፋት ፣ ለዝሙት ፣ ለመስከር ለዘፈን ፣ ለመዳራት ፣ ለጣኦት አምልኮ ፣ ለተለያየ የሀጥያት ጥፋት ውሀው ዉሰጥ ጥለን #ለፅድቅ_ለቅድሰና_ክርሰቶሰን_ለሚመሰል_ማንነት ደግም ከዉሀዉ ዉሰጥ የምንዉጣበት ድንቅ #ባርኩት ነዉ ።    ስለዚህ ይህ ቀን ሀጥያትን እንደዉሀ #የምንጨልጥበት ሳይሆን #ለሀጥያት_የምንሞትበትና #ለፅድቅ_የምንነሳበት ቀን ነዉ ስለዚህ በዝህ እዉነት በክርሰቶሰ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ይሁንላችሁ።
Показать все...