ሱረቱል አንፋል(የጦር ዘረፋዎች ምዕራፍ)
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
የጦር ዘረፋ ማለት ምርኮ ማለት ሲሆን።ዘረፋ የምትለዋ ቃል መውሰድን ማግኘትን ይገልፃል።ቃሉ ሁል ጊዜ Negative/አሉታዊ ትርጉም የለውም።ስለ ምርኮ ይህን መጣጥፍ አንብቡ
https://t.me/Wahidcom/1349
ስለ ምርኮ የወረደ ከሆነ የምርኮ ምዕራፍ ተብሎ መሰየም ስለሚገባው በዚያ ተጠርቷል።
8:1 *ከምርኮ* الْأَنفَالِ ይጠይቁሃል፡፡ «የዘረፋ ገንዘቦች የአላህና የመልክተኛው ናቸው፡፡» ስለዚህ አላህን ፍሩ፡፡ በመካከላችሁ ያለችውንም ኹኔታ አሳምሩ፡፡ አማኞችም እንደኾናችሁ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ በላቸው፡፡
ሱረቱ ተውባህ(የንስሃ ምዕራፍ)
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
2፥102 ሌሎችም በኃጢአቶቻቸው የተናዘዙ መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ አልሉ፡፡ አላህ “ከእነሱ ጸጸታቸውን” يَتُوبَ عَلَيْهِمْ ሊቀበል ይከጀላል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
ሱረቱ ዩኑስ(የዮናስ ምዕራፍ)
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
በነብዩ ዩኑስ(ዮናስ)ስም የተሰየመ ምዕራፍ ነው።ቃሉ በ አንቀፅ98 ተጠቅሷል።
10:98 ያመነችና እምነትዋ የጠቀማት ከተማ ለምን አልኖረችም ግን *የዩኑስ* يُونُسَ ሕዝቦች ባመኑ ጊዜ በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ከእነሱ ላይ አነሳንላቸው፡፡ እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው፡፡
ሱረቱል ሁድ(የሁድ ምዕራፍ)
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
ሁድ የአሏህ ነብይ ነው። በሃዲስ ከተጠቀሱት 4የዓረብ ነብያት(ሁድ ሷሊህ ሹዓይብና ነብዩ ሙሀመድ) መካከል ናቸው።
11:53 አሉ፡- «*ሁድ* هُودُ ሆይ! በአስረጅ አልመጣህልንም…
ሱረቱ ዩሱፍ(የዮሴፍ ምዕራፍ)
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
ዩሱፍ የአላህ ነብይ ሲሆን አስራ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
12:4 *ዩሱፍ* يُوسُفُ ለአባቱ፡- «አባቴ ሆይ! እኔ ዐስራ አንድ ከዋክብትን ፀሐይንና ጨረቃንም በሕልሜ አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው» ባለ ጊዜ አስታውስ።
ሱረቱ ረዕድ (የነጎድጓድ ምዕራፍ)
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
“ረዕድ” الرَّعْدُ ማለት ነጎድጓድ ማለት ሲሆን ስያሜው በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
13 ፣13 *ነጎድጓድም* الرَّعْدُ አላህን በማመስገን ያጠራል፡፡ መላእክትም እርሱን ለመፍራት ያጠሩታል፡፡
ነጎድጓድ አንኳ አሏህን የሚያመልክና የሚያመሰግን መሆኑን በደንብ እንድናተኩር ይመስላል ስያሜው የተሰጠው
ሱረቱ ኢብራሂም
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
“ኢብራሂም” إِبْرَاهِيمُ ማለት የአላህ ነብይ ሲሆን አስራ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
14፣35 *ኢብራሂምም* إِبْرَاهِيمُ ባለ ጊዜ አስታውስ «ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን፡፡
ሱረቱል ሒጅር(የሒጅር ምዕራፍ)
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
“ሂጅር” الْحِجْرِ የሸለቆ ስም ነው። በመዲናና በሻም መካከል የሚገኝ ቦታ ሲሆን
15: 80 *የሒጅርም* الْحِجْرِ ሰዎች መልክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ፡፡
በሚለው ላይ ስያሜው ተጠቅሷል።መልክተኛን ነብይን መቃወም ከባድ ቅጣት እንዳለው አሏህ ስለ ስያሜው ስናጠና እንድናስተነትን አድርጓል።
@Albeyan_channal