cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የመንፈስ ፍሬዎች ❤️ 🕊 🙏

👉በዚህ ቻናል በቅዱሱ መፅሐፋችን ለይ 📖ገላ 5÷22 ሰፍረው ስለ ምናገኛቸው የመንፈስ ፍሬዎች ማለትም ስለ :- ❤️ፍቅር 😁ደስታ 🕊ሰላም 🙏ትዕግሥት ✋ቸርነት 😍በጎነት ✝እምነት 🤗የውሃት፥ 🙊ራስን መግዛት በፅሁፍ እንደሁም ደግሞ በድምፅ እንማማራለን እንዲሁም :- 🗣በተለየ ሁኔታ በተለየ ቀን የበደላችሁን እንዱሁም የበደላችሁትን ሰው በይቅርታ ልባችሁን ከጥላቻ ወደ ፍቅር ከጨለማ ወደ

Больше
Рекламные посты
1 476
Подписчики
+124 часа
-17 дней
+430 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ወዳጆቼ ይነጋል 🥰 👉ለአንዳንዶቻችን መሽቶብናል፣ 👉 ለአንዳንዶቻችን ጀንበር አዘቅዝቃብናለች፣ 👉ለአንዳንዶቻችን በር ተዘግቶብናል፣ 👉 ለአንዳንዶቻችን ተስፋ መቁረጥ ጓዙን ጠቅልሎ እኛ ጋር ከትሞብናል፤ 👉 ለአንዳንዶቻችን በፀሐይ ጨልሞብን መሸሸጊያ አጥተናል ። 👉 ምናልባት የስራ ማመልከቻችሁ ተቀባይነት አጥቶ ይሆናል፣ 👉ምናልባት ፕሮሰሳችሁ አላለቀላችሁ ኢምባሲ ተቀባይነት አታችሁ ይሆናል፣ 👉 ምናልባት የጠየቃችሁት ይቅርታ ተቀባይነት እጥቶ ይሆናል ግን ወዳጆቼ አንዳች ልባችሁ አይሸበር አምላካችሁ አባታችሁ ፈጣሪያችሁ እግዚአብሄር ተቀብሏችኃል 🥰 ደግሞ እግዚአብሄር የተቀበለውን ማንም አይጥለውም ሰዎች ቢቀበሏችሁ ባሉበት ቦታ ነው እግዚአብሄር ግን ሲቀበላችሁ በሰማይና በምድር ነው በኢትዮጵያ ተቀባይነት ብታገኙ የኢትዮጵያ መንግስት ደብዳቤ የሚፅፍላችሁ እስከ ድንበሩ ነው ። እግዚአብሄር ግን ድንበር የለውም በሰማይና በምድር ነው። በእውነት እግዚአብሄር ተንከባክቦ አንከብክቦ በትከሻው አሰማርቶ ነው የያዘን።  የዓለም ውበቷ ይሄ ነው 😢       የእግዚአብሔር ቃል ግን "ማታም ሆነ ፤ ጠዋትም ሆነ" (ዘፍ 1፥13) ሰው ከጠላህ ጠላህ፣ ከጨከነ ጨከነ፣ ጥርሱን ከነከሰብህ ነከሰ ነው። እግዚአብሔር ብቻ ይራራልሃል። ጨለማውን በዛው አያስቀረውም ያነጋዋል ጠዋትን ያመጣልሃል። የሚጨልመው ላንተ ሊመስልህ ይችላል ለደከማቸው ማረፊያ ነው ላንተ ደግሞ የንጋት መምጫ ዋዜማ ነው። እግዚአብሔር ለአንተ ጨለማ ቀን የለውም  የሚነጋ ፣የሚያብብ ፣ የሚደምቅ፣ የሚያምር፣ የሚስብ ቀን ይወጣልሀል።     ሁሌም አስታውስ ወደ ጎን 360 ዲግሪ ብትዟዟር ካንተ በቀር የምታየው የሚረዳህ ላይኖር ይችላል፤ ቀና ስትል ግን የሰማይ ደጅ ላንተ ክፍት ነው። አባትህና የርሱ የሆነው ሁሉ ያንተ ነው።       አይዞህ ጨልሞ አይቀርም ይነጋል። እግዚአብሄርን አላልፍም ብሎ የሚገዳደር የትኛውም ሀይል የለም። አሳላፊው ስላለ ያልፋል። አልነጋም ብሎ ስታክ አርጎ የሚቀር የጨለማ ለሊትና የልብ ክረምት የለም። በጨለመብህ ጊዜም ቢሆን ጭለማ ውስጥ ጌታ ሊያሳይህ የፈለገውን ነገር ለማየት ሞክር።     ፀሐይዋ ወደመኝታዋ ስትሄድ ጥላዋን ትልክልናለች ጨለማው ሲደምቅ የሚያምሩ ከዋክብትን እናያለን። በጨለሙብን ነገሮች ውስጥም እንባችን የጋረዳቸው ከዋክብቶች ይኖራሉ እነሱን እያየህ ለሊቱ መንጋት ይሆንልሀል። አይዞህ ጨልሞ አይቀርም ይነጋል ዛሬ ባንተ ላይ የሆነው ካንተ በፊት ብዙ ሚልየን ሰዎች ላይ ደርሷል። አንተ መጀመሪያ አይደለህም መጨረሻ ግን ልትሆን ትችላለህ። ምንም ይሁን ምን ቢመሽም ይነጋል።     ┄┉┉✽»✨🌹✿🌹✨»✽┉┉┄                 #ፈጣሪ_ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን_ይባርክ ✍የአብስራ ተስፋዬ))   📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm Join and share 💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️ 💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️ 💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️   ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
Показать все...
👍 1
አረ ወገን እያስተዋልን 🤔 ሰው እንዴት እግዚአብሄር ይስጥልኝ ሲባል   ....አይ ምንም ችግር የለም እንዴት ይባላል 🙊 👉ይህ ቋንቋ ለርዕስ አይመች ለምንም አይመች ። 👉 አሁን ይሄ ምን ይባላል በወላዲቷ ? ባህል፣ እምነት ምንም አይገልፀውም እንደው ከንቱ ልማድ ካልሆነ በቀር  ሰዎች እግዚአብሄር ይስጥህ(ሽ) ሲሉን ሁልጊዜ መልሳችን ችግር የለውም የሚል ነው እስቲ ማን ይሙት 🙈 አሁን እኛ ችግር የለብንም ? 👉ያውም ተቆጥሮ ተሰፍሮ የማያልቅ ነዋ .....በችግር ያደግን ፣በችግር የተመረቅን፣ በችግር ወላፈን ተጠብሰን የኖርን የምንኖር አይደለንም ? እንዲህ ማለት በኛ አይምርም 🙅‍♂ ኑሮ ናላችንን አዙሮት ፣በበሽታ ጠውልገን፣ ሌቱ ጠሮብን፣ ህይወት እንቆቅልሽ ሆኖብን እግዜር ይስጥህ ስንባል ችግር የለም እንላለን ⁉️ አሜን🙏 ይሁንልኝ ይደረግልኝ ማለት ማንን ገደለ 🤔 እንደው የአምላክ እናት የአስራት ሀገር የብዙ ቅዱሳን መካናት መገኛ በቅዱሱ መፅሐፋችን ኢትዩጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የተሰኘች ደግሞ ኢትዩጵያ ሲባል ምድሪቷና ዛፎቹ ጋራ ሸንተረሩ ሳይሆን ህዝቦቿን መሆኑን አትዘንጉ እንኳን እኛ ብዙ የተባለልን ቀርተን 👉 ፈረንጆች እንኳ የእግዚአብሄር ስም ላልተጠራበት ምስጋና ቴንኪው ሲባሉ ዩ አር ዌልካም ነው የሚሉት እኛ በክርስቶስ ክርስቲያን ተብለን የተሰኘንስ እግዚአብሄር ይስጥልን ስንባል ችግር የለም ማለታችን ያሳፍራል ከዕርሱ ከቸር አምላካችን በላይ ማን አለ ማን ይስጠን 🤔 🌹 ወዳጆቼ በዛ በሰፊው እጁ እየሰፈረ የሚያኖረን መልካም አባት እርሱ ነው ። ከኛ አንደበት ይሄ ቃል ሲገኝ ያስነውራል ። ቅድስናችን በአንደበታችን ጭምር ነውና የምንናገረው ቃል ሁሉ የተቀመመና ማስተዋል ያለበት እንጂ ከንቱ ንግግር መናገር የለብንም ለማለት ነው ወዳጆቼ ። ከዚህ በኃላ መልሳችን  አሜን 🙏 ብቻ ነው ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ ወዳጆቼ 🙏  ┄┉┉✽»✨🌹✿🌹✨»✽┉┉┄                 #ፈጣሪ_ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን_ይባርክ ✍የአብስራ ተስፋዬ))   📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm           Join and share 💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️ 💚💛❤️ @Etelawyan3 💚💛❤️ 💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
Показать все...
🙏 2👍 1
​​ወዳጆቼ 🥰 ማፍቀርም ሆነ መፈቀር የማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ባህሪ ነው 🌹ፍቅር መስዋትነት ነው ላፈቀሩት ሰው ደስታ ፣ሰላም ፣ምቾት፣እረፍት ሲሉ የራስን ደስታ አቶ ራስን አሳልፎ እስከመስጠት ድረስ የሚከፈለውን ዋጋ ነው። 🌹የእውነት ያፈቀረ ሰው ለኔለኔ ከሚል ስሜት የፀዳ ፥ ለኔ ከማለት ይልቅ ለወደደው ሰው ራሱን ሳይሰስት መስጠት ነው ለኔ። 👉ፍቅር የማንነት... የዘር... ወይንም የገንዘብ ጥያቄ አይደለም.......የህሊና የነብስ እና ራስን አሳልፎ የመስጠት 😍ጥያቄ እንጂ.....💖 ፍቅር እኔ....እኔ...ለኔ....ለኔ ከሚል የራስ ወዳድነት ቀንበር የፀዳ ነው፡፡ ❣እውነተኛ ፍ...ቅ...ር በእድሜ የማይለካ...በችግሮች የማይገታ በማግኘት ያልተጀመረ በማጣትም የማይቀየር የሰብአዊነት ጥምረት ነው::❤ 👉 ከባዱ ነገር ፍቅር መጀመር ሳይሆን በፍቅር መቆየት ነው:: 👉ስለ ፍቅር ቢያወሩ የሚያምርባቸው ፍቅርን በፊልም የተማሩት ሳይሆን በፍቅር የኖሩት ናቸው ፡፡😘 👉ፍቅር ማለት😘 እወድሻለው እወድሀለው ከመባባል በላይ በተግባር የሚፈተን....በመተማመን የሚፀና...በመደማመጥ 😍የሚሆን...በመከባበር❤ የሚሰምር ...የህይወት ማጣፈጫ ቅመም የሆነ የፈጣሪ የፀጋ ስጦታ ነው፡፡ ማፍቀር መፈቀርም መታደል ነው፡፡ሁለቱንም ማግኘት ደግሞ መመረጥም መባረክም ነው፡፡😍 ፈጣሪ "ፍቅርን" ያብዛልን!!!😜አምላካችን የሚያከብረን የሚያምነን አጠፋህ ብቻ ሳይሆን አጥፍቻለሁንም የሚያውቅ ፈጣሪው ይቅር ሲል ይቅር እንደሚለው አውቆ ይቅርታን በልቡ ያተመ እዉነተኛ አፍቃሪ ይስጠን ❤️😘  ┄┉┉✽»✨🌹✿🌹✨»✽┉┉┄                 #ፈጣሪ_ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን_ይባርክ ✍የአብስራ ተስፋዬ)) 📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm Join and share 💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️ 💚💛❤️ @Etelawyan3 💚💛❤️ 💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️   ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
Показать все...
👏 3
ስለ አጉል ፍቅር...ሳምሶንን ጠየቁት ☺️ ስለ አጉል ፍቅር መዘዝ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ከሳምሶን በላይ ሊያስተምረን የሚችል ሰው ማግኘት ይከብዳል.... ሳምሶን የእግዚአብሔርን ክብር የተሸከመ ትልቅ የእግዚአብሔር ሰው እንደነበር ሁላችንም እናውቃለን ነገር ግን በአንዲት ደሊላ በምትባል ሴት ልቡ ተይዞ ያንን ትልቅ ክብር ከላዩ ላይ አሶስዷል ፤ በዚህም ዘመንም ልክ እንደ ሳምሶን  ብዙ ልጆች በ Relationship ጉዳይ ላይ ማንን ወደ ህይወታቸው ማስገባት እንዳለባቸው አያውቁም  ለዚህም ይመስለኛል 🤔 በዚህ ጉዳይ ላይ ቶሎ የሚጎዱት...የተወደዳቹ ልባም እህቶቼ እና ወዳጆቼ 🥰 እናንተ የያዛቹትን ለማስለቀቅ የእናንተን ቀልብ የሚስቡ ወንድና ሴት ልጆችን ማምጣት ለሰይጣን  በጣም ቀላል እንደሆነ አትርሱ፤ ትናንት ላይ ሳምሶን አጥፍቶ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ትልቅ ትምህርት ትቶልን አልፎአል እናንተ ግን ዛሬ ላይ የሳምሶንን ህይወት መድገም የለባቹም... ማሰብ ባለባቹ ጉዳይ ላይ ቆም ብላቹ አስቡ ካለዚያ በዚህ ዘመን ደሊላዎች የከበረውን ነገራቹን ታጣላቹ ። 🙏ሰናይ ምሽት💚💛❤️🕊️🕊️🕊️ 🙌ምሽታችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን የሰላም ባለቤትም አንተ ነህና ለሀገራችንም የቀደመ የማይናወፅ ሰላሟን አንተ አድላት ሰናይ ምሽት ወዳጆቼ🙌 ✍የአብስራ ተስፋዬ  @yeabm 💚  •✥• @Etelawyan •✥•  💚 💛  •✥• @Etelawyan3 •✥•💛 ❤️  •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
Показать все...
👏 1
ምን አይነት ፍቅር ነው 🙆 መግደላዊት ማርያም ትባላለች ፈጣሪዋን በጣም ከመውደዷ የተነሳ " በቃ  ጌታሽ እኮ ሞቷል " ተብላ እንኳን  ሽቶ ልቀባው  ነው በሚል ሰበብ የሞተ ስጋውን  ለማየት ለሊቱ እስኪነጋላት አጠብቅም ፤  ባይገርማቹ  ሌሎቹ ደቀ መዛሙርቶች ኢየሱስ በህይወት እያለ " አንተ ጌታችን ነህ " ብለውት ነበር ነገር ግን ኃላ ላይ እንደ ሰው ሲሞት ሀሳብ ቀይረው ሁሉም ወደ ኋላ ተመለሱ ይቺ ድንቅ ሴት ግን በህይወት እያለ በራሷ ላይ ብቸኛ ጌታ ያረገችውን  ኢየሱስን ሞቶም እንኳን ልትቀይረው አልፈለገችም፤ ምን አይነት ፍቅር ነው 😭  ምን አይነት መረዳት ቢኖራት ነው ኢየሱስ ሞቶም እንኳን ለእርሱ ያላት ፍቅር አልቀዘቅዝ ያለው  እናንተዬ ለካስ ፈጣሪ እንዲም ይወደዳል....ትዝ ካላቹ  ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን የገለጠው ለዚች ድንቅ ሴት ነበር 🔥 የተወደዳቹ እህቶቼ ትናንት ላይ ይህቺን ልባም ሴት 😍 የነካት ይሄ ታላቅ ፍቅር ዛሬ ላይ  ሁላችንንም ይንካን የእርሷን የልብ ማስተዋል ለእኛም ያድለን 🔥🔥 🙏ሰናይ ቀን💚💛❤️🕊️🕊️🕊️ 🙌ቀናችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን የሰላም ባለቤትም አንተ ነህና ለሀገራችንም የቀደመ የማይናወፅ ሰላሟን አንተ አድላት ሰናይ ቀን ወዳጆቼ🙌 ✍የአብስራ ተስፋዬ  @yeabm 💚  •✥• @Etelawyan •✥•  💚 💛  •✥• @Etelawyan3 •✥•💛 ❤️  •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
Показать все...
3👍 2
እግዚአብሔር ዝም ሲል 😢 አስተውላቹ ከሆነ እግዚአብሔር ዝም ሲል ተናጋሪ ይበዛል ኢዮብ ትዝ ይላቿል ምንም በማያውቀው ጉዳይ ምክንያት ያለው ንብረት ሁሉ አንድ በአንድ ሲጠፋበት፣ የገዛ ሚስቱ እንኳን ስትክደው ፣ ሰውነቱም በገል ብረት ሲቆሳስል እግዚአብሔር ግን በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ዝም ሲለው ነበር ፤ ነገር ግን ኃላ ላይ እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ የነበረውን ሀሳብ ሲጨርስ በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ እንደ ገና እንዳሰበው ቅዱሱ መጽሐፍ 📖 ይነግረናል ። ወዳጆቼ አስቸውሉ የእግዚአብሔር ድምጽ በጣም አስፈልጓቹ ድምጹን ግን ሳትሰሙት ስትቀሩ  እግዚአብሔር በህይወታቹ ላይ እናንተ ሳታውቁ የሆነ ትልቅ ስራ እየሰራ እንደሆነ አስቡ፤ አንዳንዴ ደግሞ በእግዚአብሔር ዝም ውስጥ እናንተ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ልታልፉ ትችላላቹ ነገር ግን ከብዙ ዝምታዎች በኋላ የሚመጣውን የእግዚአብሔርን ድምፅ ስትሰሙ የቀድሞ ዝምታው ለምን እንደነበር ይገባቿል። ዝምታው ውስጥ ክብር አለ 🔥 🙏ሰናይ ቀን💚💛❤️🕊️🕊️🕊️ 🙌ቀናችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን የሰላም ባለቤትም አንተ ነህና ለሀገራችንም የቀደመ የማይናወፅ ሰላሟን አንተ አድላት ሰናይ ቀን ወዳጆቼ🙌 ✍የአብስራ ተስፋዬ  @yeabm 💚  •✥• @Etelawyan •✥•  💚 💛  •✥• @Etelawyan3 •✥•💛 ❤️  •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
Показать все...
👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ይቅር__በለኝ🙏 #ከኃጢያታችን የበለጠ እግዚአብሔርን እጅግ የሚያሳዝነው ይቅር አይለንም ብለን ማሰባችን ነው። በደል የሌለበት አምላክ ከእኛ ከትቢያዎቹ ጋር ራሱን አቻ አድርጎ "ኑና እንዋቀስ፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዛቶ ትጠራለች" ብሎ የምሕርት ጥሪ እያቀረበ ይቅር አይለኝም ሰንል ሲሰማን ያዝናል። (ኢሳ,፩፥፲፰) አንተ በክፉ ሥራህ ራስህን ብትጠላውም እንኳን #እግዚአብሔር ግን አይጠላህም፤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለው #እግዚአብሔር ለአንተ ያለው ፍቅር አንተ #ለራስህ ካለህ ፍቅር ይበልጣል» እንደ ይሁዳ ብትክደው ፣ ወዳጅህን ብትሸጥ፣ ንጹሕ ደም በግፍ ብታፈስስ፣ ሙዳየ ምጽዋቱን ብትዘርፍ፣ እንደ ይሁዳ በአምላክነቱም ጨርሶ ባታምን እንኳን ፈጣሪ የሚጠብቀው የምትሞትበትን ሳይሆን #የምትጸጸትበትንና የምትመለስበትን ቀን ብቻ ነው። በወንጌሉ «እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት» እንደሚል #እግዚአብሔር ከእርሱ እጅግ በጣም ርቀህ እያለህ እንኳን እያየ ያዝንልሃል እንጅ አያዝንብህም። (ሉቃ. ፲፭፥፳)              #_ሰናይ__ቀን🙏
Показать все...
👍 3
እህቴ 👸 ሆይ አርአያሽ (ሮል ሞዴልሽ) ማነች ⁉️ 👉አስተዋይ ሴት እንድትሆኝ ሁሌ ፀልይ አንች የ ቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም ልጅ ነሽ😘 💖ድንግል ሆይ ልደትሽ በረከታችን ነው!!! 💖ድንግል ሆይ የልደትሽ ቀን ሙላታችን ነው!!! 💖የእመቤታችን የልደቷ በረከት ይደርብን! \ ምልጃዋ ሀገራችንን ይጠብቅልን ሕሙማንን ይፈውስልን!!! 🌹የተወለድንበትን ቀን ከምንረግምበት ፈተና ሁሉ እግዚአብሔር ይሠውረን! 🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን። 🙏ሰናይ ቀን💚💛❤️🕊️🕊️🕊️ 🙌ቀናችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን የሰላም ባለቤትም አንተ ነህና ለሀገራችንም የቀደመ የማይናወፅ ሰላሟን አንተ አድላት ሰናይ ቀን ወዳጆቼ🙌 ✍የአብስራ ተስፋዬ @yeabm 💚  •✥• @Etelawyan •✥•  💚 💛  •✥• @Etelawyan3 •✥•💛 ❤️  •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
Показать все...
8.10 MB
👍 3 3
አይዞሽ              አንቺ ከመኖሪያሽ ተነስተሽ ወደ አንድ ከተማ በመኪና ስትጓዢ ለዓይን ያማረሽን ለምላስ የጣመሽን ምግብ ቋጥረሽ ትጓዣለሽ። እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ወጥተው የሲና ምድረ በዳን ሲያልፉ የቋጠሩት ምሳና እራት አልነበረም። በማያርሱበት በማይዘሩበት በማያጭዱበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው፣ ጎራ ብለው የሚበሉበት ሬስቶራንት በሌለበት፣ የታሸገ ምግብ የሚገዙበት ሱፐርማርኬት ባልኖረበት ምድረ በዳ ላይ እግዚአብሔር መናና ድርጭት እየመገበ መራቸው። ከመሀላቸው አንዳች የተራበ አልነበረም። እግዚአብሔር መሪ የሆነበት ህይወትና ጉዞ በጉድለት ሳይሆን በበረከትና በጠል የተመላ ነው። ወዳጄ አምላክሽ እስራኤልን በምድረ በዳ የመገበ፣ እውር አሞራን የሚቀልብ፣ ድንጋይ የተጫነውን ትል የማይረሳ፣ ትንሿን ትንኝ ሳይዘነጋ የሚመግባት ጌታ ነው።  አንቺንማ ሞቶልሽ እንዴት ይረሳሻል ርቦሽ እንዴት ይጨክንብሻል በፍፁም!        ምድረ በዳ በሆነ የህይወት ቀጠና ብታልፊ፣ ዘርተሽ የማታጭጂበት ሰርተሽ የማታተርፊበት፣ ቀድተሽ የማትጎነጪበት ሁኔታ ላይ ብትሆኚ እንኳ በሚያስፈልግሽ ሁሉ መለኮታዊ እጁን ይገልጥልሻል።            ምድረ በዳ ነው ብሎ ሰው ሲጨነቅ በምድረ በዳ አንቺን ለመርዳት የማይከለክለው ጌታ የበረከቱን ጠል ያዘንምልሻል። በሲና ምድር እስራኤላውያን ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ሰዎች ለጉብኝት አልፈዋል፣ ሀገር አቋርጠው ሄደዋል ያቋርጡ እንጂ መና አልበሉም ከአለት ውኃ አልጠጡም የጠጡት በእግዚአብሔር ያመኑት እስራኤላውያን ብቻ ናቸው። አንቺ ግን ሰው በሚራብበት ዘመን ትጠግቢያለሽ፣ ሰው በሚጠማው ዘመን ትረኪያለሽ፣ በሚሞትበት ዘመን በህይወት ትኖሪያለሽ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ያዘጋጃል!    "እናት ከእንቅልፍ ቀስቅሳ ታበላለች እግዚአብሔር ግን ከሞትም ቀስቅሶ ይመግብሻል።" በአንዳች አትጨነቂ እግዚአብሔር ያዘጋጃል።   🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊 መልዕክት፣አስተያየት፣ ጥያቄ፣ ጥቆማ በ  @Yeabm 🕊//ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር //🇪🇹 @Etelawyan 🇪🇹 @Etelawyan3 🇪🇹 @Etelawyan 🇪🇹                  
Показать все...
👍 3
ያሰባችሁት ባይሆንም ያሰበላችሁ ሆኗል ይደመጥ 🦻🦻🦻‼️ 🎤የአብስራ ተስፋዬ @Yeabm
Показать все...
1.24 MB
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.