cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

እውነትም አርነትያወጣችኋል አላቸው። ዮሐ 8 : 32📚

በዚህ ቻናል አስተማሪ ናቸው ያልናቸውን የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ መፅሐፍቶችን፣ መዝሙሮችን፣ ግጥሞችን፣ አጫጭር ቪዲዮዎችንና ሌሎችንም ያገኙበታልና ይቀላቀሉን🙏 👉 @EwunetmEyesusNw ✅ማስተላለፍ ምትፈልጓቸው ማንኛው አስተማሪ መልእክቶች ካሉ በራችን ክፍት ነው፤ @efkiye 👈በዚህ አድራሻ ያናግሩን፣ ይላኩልን፤ ጌታ ይባርካችሁ🙏

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
196
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

“ይህም ንጉሥ አካዝ በተጨነቀ ጊዜ እግዚአብሔርን መበደል አበዛ።” — 2 ዜና 28፥22 **** “ጽኑ፥ አይዞአችሁ ከኛም ጋር ያለ ከእርሱ ጋር ካለው ይበልጣና ከአሦር ንጉሥና ከእርሱ ጋር ካለው ጭፍራ ሁሉ አትፍሩ፥ አትደንግጡም።” — 2 ዜና 32፥7 **** በዚህ ለንፅጽር ባቀረብኩት ክፍል ላይ እንደምናየው ሁለቱም የመንገስ አጋጣውን አግኝተው የይሁዳ ንጉስ ሆነው ያለፉ ዎች ቢሆንም ሁለቱም በነበሩበት ወቅት ለገጠማቸው የመከበብ ችግር፣ በሌሎች ጠላቶች እጅ የመውደቅ ነገር የሰጡት ምላሽ ያለያያቸዋል፡፡ 😔 እንግዲህ የመጀመሪያው ስለመጨነቁ እግዚአብሔርን በመበደል በእግዚአብሔር ላይ ሌላ አማራጮችን ሲፈልግ እንዴት እንደወደቁ የሚያሳየን ሲሆን 👉 በአንጸሩ ደግሞ በመከበብ ውስጥ በጠላት ዛቻ ውስጥ ሆነው እግዚአብሔርን በማመስገን በጽድቅ ሲቆሙ በእግዚአብሔር ተዓምራት ድል ሲያደርጉ የምናይበት ይሆናል፡፡ ❤️‍🔥 ሰው በተጨነቀ ጊዜ አዳኝ መፈለጉ ምንም ጥርጥር የለውም 🗞 እኔ ግን ዛሬ እንደ እግዚአብሔር ቃል እውነት በጭንቀታቹ ውስጥ ሆናቹሁም ቢሆን በእግዚአብሔር ማዳን ታምናቹ በፅድቅ መንገድ እግዚአብሔርን በማመስገን ህይወት እንድቀጥሉ አላለው፡፡ 📍ድል ለእግዚአብሔር የመኖር ህይወት ነው፡፡ ምስቅልቅሎሽ በሆነባቹ ነገር ላይ በምርኮ በተያዘ ነገራቹ ላይ አማራጭ የሆነ 👉 ከጽድቅ ውጪ ሌላ መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር ጠብ ውስጥ የምትገቡበት እንጂ የድል መንገድ አይደለም። ስለሆነም እሱን በመታመን ብንወድቅ የሚያነሳውን እሱን በመታመን ብንሞት ትንሳኤ የሆነውን እርሱን... . . . በመታመን እና በማመስገን አንዘለቅ ባያድን እንኳን እንኖራልን እንበል . . “ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፦ አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።” ማቴዎስ 26፥39 🙌 በሞቱ እንኳን እንደምትወድ ይሁን አለ፡፡ 👇👇👇👇👇👇👇 📚 ቻናላችንን ይቀላቀሉ ብዙ አስተማሪ ነገር ያገኙበታል፤ እንዲሁም ወደዚህ ቻናል ሌሎችም ይመጡ ዘንድ ይህንን share ያድርጉ🙏 @EwunetmEyesusNw @EwunetmEyesusNw @EwunetmEyesusNw
Показать все...
“ከሞተ አንበሳ በህይወት ያለ ውሻ ይሻላል” በዚህ ቃል ውስጥ ብዙ የሞቱ በህይወት የሌሉ ነገሮችን እያወዳደርኩ በርግጥም ይሻላሉ እያልኩ በልቦናዬ በህይወት ያሉ ነገሮች ላይ ስለማተኮር እያሰብኩ እየወሰንኩ የፃፍኩት ነው፡፡ በርግጥ የመክብብ መፅሐፍ ክፍለ ምንባብ ነው፡፡ የሀሳቡም አውድ ሞት ድምዳሜ መሆኑን የሚናገር ከሞት በሃላ ምንስ ዋጋ አለው የሚል ሃሳብ ስር ነው የምናገኝው፡፡ የመክብብ መጽሐፍ ዋና ሃሳብ ሰዎችን ከእግዚአብሔር ውጪ ሆነው ማግኘት ቢባል ማጣት ብቻ ሁሉ ከንቱ መሆኑን ነገሮ እና አሳስቦ በእግዚአብሔር ፊት በህጉ ስርዓት ከመኖር ውጪ ባሉ በሁሉ ነገር ተስፋ እንዲቆርጡ የሚዘግብ መጽሐፍ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ውጪ ተስፋ ቁረጥ የሃሳቡ ጡዘት ነው፡፡ ሆኖም በተነሳበት ክፍለ ምንባብ ውስጥ መሞትን እና በህይወት መኖርን ያወዳድራል፡፡ ከሞት አንበሳ ምናልባት በህይወት እያለ ድምፁ፣ ግርማ ሞገሱ፣ ጉልበቱ ማስፈራቱ ምናምን ከሚባልለት አንበሳ ይልቅ ለማባረር ድንጋይ ምናነሳለት በህይወት ያለ ውሻ ይሻላል የሚል ነው፡፡ በህይወት መኖር ከመሞት የሚስጠውን ዕድል ሲያነፃፅር ልኬት ቢያጣ እዚ እና እዛ ቢሆንበት ነው እንግዲ በህይወት የሌለውን የጫካውን ንጉስ እና በህይወት ያለ ውሻን የሚያነሳው፡፡ በዚህ ውስጥ ስለሞቱ ትላልቅ ዕድሎች አሁን በህይወት ካሉ ትናንሽ ዕድሎች እንደማይሻሉ እንድናስብ በማሰብ ነው ወደዚህ የመጣውት፡፡ ዕድሎች ይሞታሉ ወይ ብትሉኝ እኔው እናንተን ልጠይቃቹ ወደኃላ ለማስተካከል ምትመኙት ችላችሉ ያልቻላቹት ነገር የሉም ወይ? ለመሆን አንዳች እንዳልጎደላቹሁ አሁን ሲገባቹ በትላትናውስጥ የተቀበረ የሞተ በጊዜ ማለፍ የተገባደዱ አንድስ ነገር የላችሁም ወይ እኔም የምለው እሱን ነው፡፡ ትላንት ውስጥ የነበረ ዛሬ የሌለን ነገር እያሰቡ ዛሬን መበደል ማለት ነገን መግደል በዛሬም ላይ መሳለቅ ነው፡፡ የሚሻለው በህይወት ስላለው ነገር መኖር ነው፡፡ የሞተ ነገር እኮ የሞተ ነው ዋጋው ምንም ነው፡፡ የትላንት ቁጭት ለዛሬው ህይወትን ካልስጠ በትላንት ሀዘን መከፋት ሲያይል የዛሬውን ህይወት የሚያጨልም ነው የሚሆነው፡፡ በእውነትም ምን ቢሆን አንበሳ ከሞተ ከሌለ በህይወት ከውሻ አይሻልም፡፡ ስለሆነም ትኩረታችን አሁን ካሉ ወደፊት ከሚኖሩ ህያዋን ጋር ይሆን፡፡ ስለሞተው በህይወት ያለውን አንበድል፡፡ ትላንት ያላረግነው ነገር ዛሬን እንዳይበድል የትላቱ 20 ዓመት የዛሬውን የነገውን እንዳያጉድል፡፡ ለሞተው ኖረን በህይወት ያለውን ዛሬን ደገሞ ነጋችንን እንዳንከስር፡፡ “ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና ሰው ከሕያዋን ሁሉ ጋር በአንድነት ቢኖር ተስፋ አለው።” መክብብ 9፥4
Показать все...
የአንድ ሰው ብዕር....✍️ እምነትስ ከየት ይገኝ ፍቅርስ ከየት ይምጣ ፍንጣቂ ተስፋ በየት በኩል ያብራ . . . መዝገቡ ልቦና መች ተገለጠና፡፡ 2ኛ ቆሮ 4፡4 ንጋት ውስጥ ጭለማ አይታች ታቁ ይሆን…? ያ ማለት ጨፍናችኋል ውይም አይናቹ እያየላቹህ አይደለም ማለት ነው፡፡ ይህ ጭለማ ውስጥ ያሰነብተናል አደኝ ፊት በሽተኛነታችንን ያፀናል። ስለሆነም የተገለጠውን ያለውን የከበረውን ለማየት የልቦና አይናችን ይብራ። “ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤” — ኤፌሶን 1፥18-19 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Показать все...
የአንድ ሰው ብዕር በትዝበት አይን ወደ ልቤ ያጋበስኩት ነገር በልቤም የከበደኝን በአይምሮዬ በምናቤ ውስጥ ወዲህ እና ወዲያ ማንከላውሰውን ነገር እንዲህ በበዕሬ መተንፈስ ያው መተንፈስ ነው፡፡ የዘመኗ ቤተ-ክርስቲያ መልኳን በብዙ ነገሮች አዠጎርግራ ትክክል እና ሀሰተኛ ለማለት አዳጋች እየሆነ ነው፡፡ ሁሉም ለይስሙላ ፈርሃ እግዚአብሔር ያላቸው ይመስላሉ፡፡ ማየስግዱለትን ጌታ ማይታዘዙትን አምላክ ሰባኪዎች ናቸው፡፡ ብቻ ምን አለፋቹኁ አብዛኞቹ ትርፍ መሰበሰቢያ ወንጌልን ጎተራ መሙያ ስምን ዝና መስቀያ አድረገውቷል፡፡ እኔ ማንም ምንም ሆኜ አይድለም ግን እንዲህ ያለው ነገር ቃለ እግዚአብሔር ልክ ማይለው መንገድ መሆኑን ቃለ እግዚአብሔር የሚገልጠው እውነት መሆኑን መናገሬ ነው፡፡ መቼም የእኔን ልክነት ማረጋገጫ አድርጌ አለማቅረቤን ያሳይልኛል፡፡ በእኔ በሸውራራው አይን አይደለም ልክ አይደሉም ምለው ቃለ እግዚአብሔር ነው በወንጌል የሚሸቃቅጡ የሚላቸው…ትርፍ ነው ጉዳያቸው አገለጋይ የሚለው ስምን ከስማቸው ፊት ያስቀደሙትን ሁሉ ይመለከታል... ❓ለምንድነው ምናግልግለው ❓ከአገልግሎታችን ጀርባ ያለው ፍላጎታችንስ ምንድነው ብዙ መልሶችን አስባለው🤔 አገለግሎት የከበረ ጥሪ ነው ይህንን እረዳለው፡፡ መፅሐፍ እንደሚል“ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው?” 2ኛ ቆሮ 2፥16 ለዚህ ጥሪ ዕድል ማግኘት ይበል ይበጅ የሚያሰኝ ነው፡፡ ነገር ግን አሁን በሀገራችን ብሉም በተለያዩ ሀገራት እየበዛ ያለው ''የቤተክርስቲያን (ዓለም አቀፍ)'' ብዛት የማንን ፍላጎት እና ሀሳብ ለማገልገል የወጡ ሰዎች እንደሆኑ ለመገመት ሚዲያውን ማየት በቂ ነው፡፡ 🙇‍♂ ወንጌልን መጠቀሚያ ያደረጉ ትርፋቸው ከሆነ በኢየሱስ ስም በተፀለየበት ስም የሚሸጡ የሚሸቅጡ…ትዝብት ነው ትርፉ፡፡ በስተመጨረሻ ወንጌል የሚኖርለት ካልሆነም የሚሞትለት ጉዳይ ነው፡፡ በወንጌል ስም ለትርፋቹ ለዝናችሁ ለስማችሁ ብላቹ ኖራቹሁ አንደሆነ የሰማ መዝገብ ዋጋቢስ ነው ሚላችሁ በአንፃሩ ግን ለወንጌል የተከሰከሰ የተሰባበረ የተከፈለ ህይወት ኖራቹ ከሆነ የሰማይ መዝገብ ዋጋ አላቹ ይላችኃል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራን 2ኛ ቆሮ 2፡17 ነገር ግን የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናልና በተንኮል አንመላስም የእግዚአብሔር ቃል በውሸት አንቀላቀልም እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራችንን እናመሰግናለን፡፡ 2ኛ ቆሮ 4፡2
Показать все...
Watch "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።ዮሐ 15:13" on YouTube https://youtu.be/UN37Q0vUpXA
Показать все...
ፍቅሮች አነሱ

Singer ZELALEM BEYERO

“ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል።” — ምሳሌ 16፥32 ይህን እውነታ በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ በእኔ በግለሰቡ ብዕር ውስጥ ለማሰብ ለማካፈልም ወደድኩ፡፡ የምሳሌ መፅሐፍ ከሌሎች መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ መፅሐፍ የሚጠናበት መንገድ የተለየነ ነው፡፡ ይህም ልዩነት ቁጥሮች እራሳቸውን ችለው ትርጉም የሚሸከሙበት ሁኔታ መኖሩ ነው፡፡ ይህ ማለት አንድ ቁጥር ቀጥሎ ካለው ቁጥር ጋር ምንም አይነት ቁርኝነት ሳይኖረው እራሱን ችሎ ትርጉም ሲኖረው ምናይበት ቁጥሮች በርካታ ናቸው፡፡ ይህንን ማንሳታችን ለቆምንበት ቁጥር ትርጋሜ ለመስጠት ቁጥሩ በራሱ መተርጎም የሚችል እንደሆነ ለመጠቆም ይረዳን ዘንድ ነው፡፡ በዚህ ቁጥር ውስጥ ንግርቱ ወይም ፅሑፉ ለንፅፅር የሚያቀርባቸው ነገሮች አሉ፡፡ - ትዕግስተኛ ሰው ወይም ታጋሽ ሰው - ስሜቱን የሚገዛ ወይም በመንፈሱ ላይ የሚገዛ * ከኃይለኛ ሰው ወይም ከጦረኛ ይሻላል * ከተማን በጉልበቱ ከሚይዝ ይብለጣል ወይም ከተማን ከሚወስድ ይበልጣል በንፅፅር ላይ ያቀረብካቸው 1954 እና አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሆኑት የአማርኛ የመፅሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ነው፡፡ በእውነቱ እራስን የመግዛት ክብደቱ ምን ያህል ይሆን ብዬ ውስጤ ብጠይቀው ምንም ሳያንገራግር ግዝፈቱን አተልቁ እንደ ተራራ ለመሸከም ከሚከብድ በላይ አድርጎ ቁልብጭ አድርጎ ያሳየኛል፡፡ ይህን እውነት ደግሞ በዚህ ቁጥር ውስጥ ስንፈትሸው ከኀይለኝነት ከተማን ከመግዛት በላይ የሚሻል የሚበልጥ ክብደት አኑሮ ያሳየናል፡፡ እነዚህን ወደዚህ ክፍል ለመምጣት ደግሞ ክፍሉን ለማሰላሰል ምክንያት የሆነ እውነታዎች እንደሆኑ አድርገን እንያቸውና ክፍሉ ውስጡ የተሸከመውን ነገር በዚህ በአንድ ሰው ብዕር ለማየሳየት እሞክራለው፡፡ ትዕግስት ወይም ታጋሽ መሆን፡- በትክክለኛ ሰዓት መሆንን ለመሆን ትክክለኛ ባልሆነ ሰዓት አለመሆንን መሆን ነው፡፡ ለመነሻነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚህ ነገር ምሳሌ እንዲሆን የምድር ላይ ቆይታውን ብናነሳ፡፡ ትዕግሰቱ እሰከ መስቀል ሞት የታገሰ ብሎ የተገለጠ ነገር ነው፡፡ በእጁ የተበጀው ሰው ሲተፋ ሲገርፈው ሲሳለቅበት ቢሆን ሊያጠፋው አንዳች አቅም ሳይጎለው በበቀል ልብን ሳያነሳሳ በሌላ ዕድል ሲያግኛቸው ድምጥመታቸውን ሊያጠፍ ጥርስ ነክሶ ሳያቄምባቸው የሚያደርጉትን አያቁምና ይቅር በላቸው በማለት የትእግስትን ልክ የገለጠ ነው፡፡ ትዕግስት የማንችለውን ነገር መሆን አይደልም፡፡ ምን ብንጠራራ ምን ብንሮጥ የማንደርስበትን ነገር ለመሆን የተገደድንበት እውነት የምንቀበለበት ነገር አይደለም፡፡ ትእግስት መቻል እና መሆንን ይዘን አለመሆንን በምርጫችን የምንወስነው ውሳኔ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ንፅፅር ላይ እንደ ቀረበው ሌላን ሰው በኃይል ከማሸነፍ በሃይለኝነት ሀገርን ከመግዛት ሁላ በላይ እራስን መግዛት የበልጣል ይለናል፡፡ 🙄 እንዴት ሆኖ ይህ እውነት ይሁን? ከተመን ከመግዛት በላይ እራስን መግዛት እንዴት ይልቃል? ከተማን መግዛት ኃይል ላይ ያለ በጉልበት ልክ በአቅም ልክ መኖርን የሚያበረታታ እውነት ነው፡፡ ይሁን ይደረግ ያልነውን ለማድረግ ለመሆን አቅማችንን እንጠቀማለን፡፡ እራስን መግዛት ግን የምንጠቀመው ኃይል ሌሎችን የሚያንበረክክ ሳይሆን እኛን የሚስበረክክ ነው፡፡ ከመቻል ይልቅ በትክክለኛ ነገር ላይ ነገሮችን ለማሳረፍ ያለ ፈተና ነው፡፡ እንዴ አድርገህ ትታገሳለህ ? እንዴት አድርገህ ስሜትህን ትገዛለህ ? በመሆን መካከል እየኖርን በመቻል ልክ አቅም እያለን አለቻሉምን አላሸነፉንም አላገኙንም አልተደሰቱምን እንዴት እንታገስ እንዴት ስሜታችንን እንግዛ? የአንድ ሰው ብዕር ✍
Показать все...
“ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል።” — ምሳሌ 16፥32 ይህን እውነታ በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ በእኔ በግለሰቡ ብዕር ውስጥ ለማሰብ ለማካፈልም ወደድኩ፡፡ የምሳሌ መፅሐፍ ከሌሎች መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ መፅሐፍ የሚጠናበት መንገድ የተለየነ ነው፡፡ ይህም ልዩነት ቁጥሮች እራሳቸውን ችለው ትርጉም የሚሸከሙበት ሁኔታ መኖሩ ነው፡፡ ይህ ማለት አንድ ቁጥር ቀጥሎ ካለው ቁጥር ጋር ምንም አይነት ቁርኝነት ሳይኖረው እራሱን ችሎ ትርጉም ሲኖረው ምናይበት ቁጥሮች በርካታ ናቸው፡፡ ይህንን ማንሳታችን ለቆምንበት ቁጥር ትርጋሜ ለመስጠት ቁጥሩ በራሱ መተርጎም የሚችል እንደሆነ ለመጠቆም ይረዳን ዘንድ ነው፡፡ በዚህ ቁጥር ውስጥ ንግርቱ ወይም ፅሑፉ ለንፅፅር የሚያቀርባቸው ነገሮች አሉ፡፡ - ትዕግስተኛ ሰው ወይም ታጋሽ ሰው - ስሜቱን የሚገዛ ወይም በመንፈሱ ላይ የሚገዛ * ከኃይለኛ ሰው ወይም ከጦረኛ ይሻላል * ከተማን በጉልበቱ ከሚይዝ ይብለጣል ወይም ከተማን ከሚወስድ ይበልጣል በንፅፅር ላይ ያቀረብካቸው 1954 እና አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሆኑት የአማርኛ የመፅሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ነው፡፡ በእውነቱ እራስን የመግዛት ክብደቱ ምን ያህል ይሆን ብዬ ውስጤ ብጠይቀው ምንም ሳያንገራግር ግዝፈቱን አተልቆ እንደ ተራራ ለመሸከም ከሚከብድ በላይ አድርጎ ቁልብጭ አድርጎ ያሳየኛል፡፡ ይህን እውነት ደግሞ በዚህ ቁጥር ውስጥ ስንፈትሸው ከኀይለኝነት ከተማን ከመግዛት በላይ የሚሻል የሚበልጥ ክብደት አኑሮ ያሳየናል፡፡ እነዚህን ወደዚህ ክፍል ለመምጣት ደግሞ ክፍሉን ለማሰላሰል ምክንያት የሆነ እውነታዎች እንደሆኑ አድርገን እንያቸውና ክፍሉ ውስጡ የተሸከመውን ነገር በዚህ በአንድ ሰው ብዕር ለማየሳየት እሞክራለው፡፡ ትዕግስት ወይም ታጋሽ መሆን፡- በትክክለኛ ሰዓት መሆንን ለመሆን ትክክለኛ ባልሆነ ሰዓት አለመሆንን መሆን ነው፡፡ ለመነሻነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚህ ነገር ምሳሌ እንዲሆን የምድር ላይ ቆይታውን ብናነሳ፡፡ ትዕግሰቱ እሰከ መስቀል ሞት የታገሰ ብሎ የተገለጠ ነገር ነው፡፡ በእጁ የተበጀው ሰው ሲተፋ ሲገርፈው ሲሳለቅበት ቢሆን ሊያጠፋው አንዳች አቅም ሳይጎለው በበቀል ልብን ሳያነሳሳ በሌላ ዕድል ሲያግኛቸው ድምጥመታቸውን ሊያጠፍ ጥርስ ነክሶ ሳያቄምባቸው የሚያደርጉትን አያቁምና ይቅር በላቸው በማለት የትእግስትን ልክ የገለጠ ነው፡፡ ትዕግስት የማንችለውን ነገር መሆን አይደልም፡፡ ምን ብንጠራራ ምን ብንሮጥ የማንደርስበትን ነገር ለመሆን የተገደድንበት እውነት የምንቀበለበት ነገር አይደለም፡፡ ትእግስት መቻል እና መሆንን ይዘን አለመሆንን በምርጫችን የምንወስነው ውሳኔ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ንፅፅር ላይ እንደ ቀረበው ሌላን ሰው በኃይል ከማሸነፍ በሃይለኝነት ሀገርን ከመግዛት ሁላ በላይ እራስን መግዛት የበልጣል ይለናል፡፡ 🙄 እንዴት ሆኖ ይህ እውነት ይሁን? ከተመን ከመግዛት በላይ እራስን መግዛት እንዴት ይልቃል? ከተማን መግዛት ኃይል ላይ ያለ በጉልበት ልክ በአቅም ልክ መኖርን የሚያበረታታ እውነት ነው፡፡ ይሁን ይደረግ ያልነውን ለማድረግ ለመሆን አቅማችንን እንጠቀማለን፡፡ እራስን መግዛት ግን የምንጠቀመው ኃይል ሌሎችን የሚያንበረክክ ሳይሆን እኛን የሚስበረክክ ነው፡፡ ከመቻል ይልቅ በትክክለኛ ነገር ላይ ነገሮችን ለማሳረፍ ያለ ፈተና ነው፡፡ እንዴ አድርገህ ትታገሳለህ ? እንዴት አድርገህ ስሜትህን ትገዛለህ ? በመሆን መካከል እየኖርን በመቻል ልክ አቅም እያለን አለቻሉምን አላሸነፉንም አላገኙንም አልተደሰቱምን እንዴት እንታገስ እንዴት ስሜታችንን እንግዛ? የአንድ ሰው ብዕር ✍
Показать все...
🔺🔻መክብብ 2፡1🔺🔻 በዚህ ክፍል ውስጥ የዚህ መፅሐፍ ፀሐፊ በመጀመሪያው ምዕራፍ በመጀመሪያው ቁጥሮች ላይ ከፀሐይ በታች ያሉ ነገሮች ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው የሚለውን አገላለፀ እናገኛለን፡፡ ይህም የመፅሐፉ ገዢ ሃሳብ ሆኖ እከመጨረሻም ይዘልቃል፡፡ ይህንንም ተጨባጭ በሆነ መልኩ ማግኘትን፣ ጥበብን ቢሆን፣ ደስታን ቢሆን ሌሎች ሌሎች ነገሮችን በማንሳት ወጋቢስ ሲያደርጋቸው የምናይበት መፅሐፍ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ድምዳሜው ግን ሰዎች ለሰማይ ሥርዓት ይገዙ ዘንድ የምድሩን ሁሉ ከንቱ ማድረግ ነው፡፡ 💠 እንግዲህ ይህን ያህል አጠቃላይ መፅሐፍን በተመለከተ ለማለት ከሞከረን ቀጥለን ከዚህ መፅሐፍ ውስጥ በተወሰደው ጥቅስ ክፍል ያለውን እውነታ እንደሚከተለው ለመፈተሽ እንሞክራለን፡፡ ❇️እኔም በልቤ‹‹መልካም የሆነውን ለማወቅ በተድላ ደስታ እፈትንሃለሁ›› አልሁ፡፡ በዚህ ክፍል ጥቀስ ውስጥ የምናያቸው ነገሮች በዚህ ጥቅስ ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው፡፡ ይህም መልካም የሆነውን ለማወቅ በተድላ ደስታ መፈተን የሚል ነው፡፡ በተድላ ደስታ ፈገግ ማለት ከቻለን መልካም ነገሮችን አገኘን ማለት እንችላለን የሚል ጥያቄያዊ ዐ.ነገር ማውጣጥ ይቻለናል፡፡ እንግዲህ ክፍሉ እንደሚነግረን በተድላ ደስታን ፍለጋ የተለያዩ መውጣት መውረዶች፣ የተለያዩ ማከማቸቶች እንደውም የዐይን አምሮቴን ሁሉ ያለአንዳች መከላከል አገኘው ይለን እና በዚህም በሰራውት ሁሉ ደስ አለኝ፡፡ (የሰራውት ከሚላቸው ጥቂት ነገሮች መካከል…ቤቶችን ሰራው፣ ወይንንም ተከልሁ፣ የመዝናኛ ስፍራዎችን አዘጋጀው…2፡4-9) በዚህ ሁሉ ማግኘት ውስጥ እንግዲህ ያለው ነገር ያስከፈለውን ነገር መለስ ብሎ ሲያስተያየው የደከመውን ድካም ሁሉ ሲያስብ ሁሉም ከንቱ ንፋስ እንደመከተል ነው ይለናል፡፡(2፡11) ስለዚህም መልካም የመንላቸው ነገሮች መዳረሻ ደስታ እና ተድላ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ እርግጥ ነው ሰው ደስታውን ለመፍጠር ተድላን ለማግኘት በበዙ ይጥር ይሆናል፡፡ ይህ ግን ግባችን ሆኖ ሳለ በሳቃችን ውስጥ ብዙ የተደበቁ የለቀሶ ሲቃዎች እንዳይኖሩ ስጋቴ ነው፡፡ በጣም ጮክ አድርገን መሳቃችን ምናለባት የለቅሶውን ሲቃ እንዳንሰማ አድርጎን ሊሆን የችላል፡፡ ይህ ማለት ግን የለቅሶው ሲቃ የለም ማለት አይደለም እርግጥ ነው የሳቁ ጩኀት ደብቆልን ሊሆን ይችላል፡፡ ማግኘት ማትረፍ ከሆነ ስሌቱም መሆን ያለበት ምን ከፍለን ምን ገዛን ነው፡፡ ሰው ብዙ ነገሩን ሸጦ የሚገዛውን ነገር ዋጋ ካላስተዋለ ኪሳራ በራሱ ላይ እየሰራ እያከማቸ ነው፡፡ ሰው ጤንነቱን ገበሮ ሊስቅ ሊደሰት ይችላል፣ ሰው ነገውን ሰውቶ ለዛሬው ሊደሰት ሊፈነድቅ ይቻለዋል…እኚ ሁላ ደስታዎች ግን የገበርንላቸውን ነገር ብናስተውል ከንቱ የከንቱም ከንቱ ናቸው እንላን፡፡ ዛሬን ስቀን በዘላለሙ ፍርድ ፊት የዛሬው ሳቃችን ለዘላለሙ ለቅሶ ምክንያት እንዳይሆን ማሰብ ግድ የለናል፡፡ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 📚 ቻናላችንን ይቀላቀሉ ብዙ አስተማሪ ነገር ያገኙበታል፤ እንዲሁም ወደዚህ ቻናል ሌሎችም ይመጡ ዘንድ ይህንን share ያድርጉ🙏 @EwunetmEyesusNw @EwunetmEyesusNw @EwunetmEyesusNw
Показать все...
/////> ብዙ የተተወለት ብዙ ይሆናል ለተወለት... እግዚብሔርን አምነን ስንከተለው የትዬለሌ ተስፋዎችን ከፊታችንን ስለን ሊሆን ይችላል፡፡ . ይህ በእርግጥ መፅሐፍ ቅዱሳዊም ማረጋገጫዎች ያሉት እውነታ ነው፡፡ . ተስፋን ስናስብ የክርስትናን ህይወት እሰከፍፃሜው ለመድረስ የምናልፋቸው ቀላል የማይባሉ መንገዶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ለዚህም የመፅሐፍ ቅዱስን ምስክርነት መጥራት ቢያሻን ሮሜ 8፡18 ምስክር ነው፡፡ ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ስቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ፡፡ . ስለዚህ ከፊት ያለውን ተስፋ በማሰብ ብቻ የምናልፋቸው ጎዳናዎች ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ ግን ወደ ኃላም ዞር ብለን ያነሳንን የረዱንን እጆች ውለታ እንድናይ እድል ይሰጠናል፡፡ እነዚህም ያነሳንን የታደገንን ህይወት የሆነንን ጌታን አይተን በእርሱ መንገድ እንድንቀጥል ያደርገን ዘንድ ነው፡፡ ምንም እንኳ ብዙ ተስፋ ቢኖረኝ በቤቱ ህይወቴን ሊገዛ የሚያስችል ብዙ ምህረትን ቀምሻለው….🙏🙏🙏 ሉቃ 7፡41-47 👇👇👇👇👇👇👇 📚 ቻናላችንን ይቀላቀሉ ብዙ አስተማሪ ነገር ያገኙበታል፤ እንዲሁም ወደዚህ ቻናል ሌሎችም ይመጡ ዘንድ ይህንን share ያድርጉ🙏 @EwunetmEyesusNw @EwunetmEyesusNw @EwunetmEyesusNw
Показать все...
ዕብራውያን 11 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁴ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ³⁵ ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ³⁶ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ ³⁷ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ³⁸ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ።
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.