cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

አጋፔ የወጣቶች ህብረት

ሰላም ውድ ቤተሰቦች ይህ ቻናለ እርስ በእርስ እንድንተናነፅ አብረን እንድናገለግል የተከፈተ የእናንተው ቻናል ነው፡፡ አጋፔ፡- አንድ ሰው ሁሉንም ሰው ካለምንም ቅድመ ሁኔታ በእኩልነት የሚወድበት የፍቅር አይነት ነው። for any comment @Sami_series and @Bina_Music ተባርካችኋል፡፡

Больше
Рекламные посты
324
Подписчики
-124 часа
-47 дней
-1030 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

02:43
Видео недоступноПоказать в Telegram
✍ ሠርገኛ ነህ ወይስ ለቅስተኛ? **** ወዳጄ፦ ✍ ለአይሁድ ተሰጥቶ የነበረውን የሙሴ ሕግ ካልፈጸምኩ ብሎ መፍጨርጨር ለአሜሪካ መንግሥት ግብር ካልከፈልኩ ብሎ እንደመጨነቅ ነው!! ✍ ለአሜሪካ መንግሥት ግብር ክፈል እንዳልተባልክ ሁሉ የሙሴንም ሕግ ጠብቅ አልተባልክም!! ✍ የሙሴ ሕግ የተሰጠው ለአይሁዳውያን ብቻ እንጂ ለአለም ሁሉ አይደለም!! ✍ የሙሴ ሕግ በራሱ የተመሰረተው የሌዊ ክሕነት ላይ ነው!! ✍ በሙሴ ሕግ ሊቀካሕናቱ አሮን እንጂ ኢየሱስ አይደለም!! ✍ ኢየሱስን ካሕን አድርጎ ያልሾመን የሙሴ ሕግ ጠብቂ የተባለች ቤተክርስቲያን የለችም!! ✍ በሙሴ ሕግ ደመወዝ እንጂ ስጦታ የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ የራስ ጥረት እንጂ የጸጋ እርዳታ የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ መስራት እንጂ ማመን አይቻልም!! ✍ በሙሴ ሕግ ባርነት እንጂ ልጅነት የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ መርከስ እንጂ መጽደቅ አይታወቅም!! ✍ በሙሴ ሕግ ሞት እንጂ ሕይወት የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ ፍርሀት እንጂ ድፍረት የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ መቅሰፍት እንጂ ምህረት አይታወቅም!! ✍ በሙሴ ሕግ ኩነኔ እንጂ ሰላም የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ ሀዘን እንጂ ደስታ የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ ለቅሶኛ እንጂ ሠርገኛ የለም!! 📌 ጸጋ የተሰጠው ለአለም ሁሉ እንጂ ለአይሁዳውያን ብቻ አይደለም!! 📌 በጸጋ ሊቀካሕናቱ ኢየሱስ እንጂ አሮን አይደለም!! 📌 በጸጋ ጽድቅ እንጂ ኩነኔ የለም!! 📌 በጸጋ ሰላም እንጂ መታወክ የለም!! 📌 በጸጋ በረከት እንጂ እርግማን የለም!! 📌 በጸጋ ሕይወት እንጂ ሞት የለም!! 📌 በጸጋ ስጦታ እንጂ ደመወዝ የለም!! 📌 በጸጋ እረፍት እንጂ መባከን የለም!! 📌 በጸጋ መቻል እንጂ መዛል የለም!! 📌 በጸጋ መርካት እንጂ መጠማት የለም!! 📌 በጸጋ ልጅነት እንጂ ባርነት የለም!! 📌 በጸጋ ደስታ እንጂ ሀዘን የለም!! 📌 በጸጋ መቀደስ እንጂ መርከስ የለም!! 📌 በጸጋ ድፍረት እንጂ ፍርሀት የለም!! 📌 በጸጋ ድል እንጂ ሽንፈት የለም!! 📌 በጸጋ ሠርገኛ እንጂ ለቅሶኛ የለም!! 👉 እኔ በጸጋው አርፌአለሁና ሠርገኛ ነኝ!! አንተስ.....ሠርገኛ ነህ ወይስ ለቅስተኛ? #ሄኖክ_አሸብር
Показать все...
#አምስቱ_የፍርድ_አይነቶች❤    2 ጢሞቴዎስ 2:15   የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ። ✍️ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በአዲስ ኪዳን አምስት( 5 ) የተለያዩ ፍርዶች ይገኛሉ። ይህን በአግባቡ መረዳት ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት እንዲኖረን ከማስቻሉ በተጨማሪ ፍርድን በተመለከተ በቅዱሳን ዘንድ ያለውን ግራ መጋባት ያስተካክልልናል ብለን እናምናለን። ✍️ ሀይማኖቶች ስለ ፍርድ የሚያስተምሩት እና የሚያምኑት ሰው ሁሉ ያመነም ሆነ ያላመነ አንድ ላይ ከሙታን ተነስተው እግዚአብሔር ፍርድን ያስተላልፋል ይላሉ። ይህ የሐይማኖቶች አስተምህሮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ስለሌለው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት በትህትና ልብ እንመለስ። ይሁዳ 1፡17 ይሁዳ 1 (Jude) 17፤ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤ ❤ የፍርዶችን ልዩነት ለመረዳት ፦ 1) የፍርዱ ዓይነት/ምክንያት ? 2) ፍርዱ የሚፈረደው በማን ላይ ነው? 3) ፍርዱ የሚፈረድበት ጊዜ? 4) ፍርዱ የሚፈረድበት ቦታ? 5) የፍርዱ ውጤት? 1,#የመጀመሪያው_ፍርድ ================== 📌1)#የፍርዱ_አይነት ፦በአማኝ የእድሜ ዘመን ሀጥያት  ላይ ነው ============================ 👉#ምክንያት፦ የአማኙ ሀጥያት 👉#ጊዜው ፦ በ30 ዓ.ም የዛሬ ሁለት                      ሺህ አመት 👉#ቦታ ፦ በቀራንዮ( በጎልጎታ)             መስቀል ላይ 👉#ፍርዱን የተቀበለልን ኢየሱስ ነው  👉#የፍርዱ ውጤት ለእኛ ከእግዚአብሄር ቁጣ መዳን  እና የዘላለም ሕይወት ማግኝት። ዮሐ 5:24 (ሕያው ቃል) እውነቱን ልንገራችሁ ቃሌን የሚሰማ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው ከሞት ወደ ሕየወት ተሻግሯልና በኃጥያቱ ምክንያት ለፍርድ አይቀርብም። ✍️እግዚአብሔር ክርስቶስን ኢየሱስን በቀጣበት ነገር ዳግመኛ እኛን አይቀጣንም። ማንኛው ሰው በተቀጣበት ወንጀል ዳግመኛ እንደማይቀጣ የሚደነግግ በእንግሊዘኛው Double Jeopardy በመባል የሚጠራ የሰው ሕግ አለ። ይህም ሲባል አንድ ሰው አጥፍቶ በተቀጣበት ወንጀል ዳግመኛ አይጠየቅበትም ማለት ነው። ይህ ሕግ በእግዚአብሔር ዘንድም የሚሰራነው። ስለ ኃጢአታችን እና ስለ መተላለፋችን የሚገባንን ቅጣት ሁሉ በእኛ ፈንታ ሆኖ በምትክነት በመሞት ኢየሱስ ወስዶታል። እርሱም በመስቀል ላይ ሆኖ ሁሉ እንዳለቀ አይቶ “ተፈጸመ!” ብሎ በታላቅ ድምጽ በመጮህ ለእኛ ያስተረፈልን የጽዋ ጭላጭ፣ የፍርድ እንጥፍጣፊ እንደሌለ አብስሮናል። 2)#ሁለተኛው_የፍርድ_አይነት #በአማኝ #ስጋ ላይ 👉#ምክንያት_የተገለጠ_ሀጥያት 👉#ቦታ፦ በምድር ላይ 👉#ጊዜ፦ አማኙ በህይወት በምድር ሲኖር 👉#ውጤት፦ አማኙ በተለያየ መንገድ #በስጋው ያሰለጥነዋል፣ ይገሰጻል በእንቅልፍ (በመበስበስ በሞት) ሊቀጣ ይችላል ይህም ለአማኙ ጥቅም ነው 3ኛ #በአማኝ_ሥራ ላይ የሚፈረድ ፍርድ ነው። ================================ 👉ፍርዱ ፦በአማኝ ሥራ ላይ ነው 👉ምክንያት አማኙ የሰራው ስራ 👉ጊዜው፦ ቅዱሳን ሁሉ ስንነጠቅ (በመነጠቅ) 👉የፍርዱ ቦታ፦ የክርስቶስ የፍርድ ወንበር(Bema) 👉የፍርዱ ውጤት ፦#ሽልማት_መቀበል ወይም                             #ሽልማት_አለመቀበል 4) #ባልተነጠቁ_በምድር_በሚኖሩ _ላይ_ነው። --------------------------------- #ምክንያት፦ የመንግስት ወንጌልን ባለማመን እና         እስራኤላውያንን የማጥፋት ሙከራ #ጊዜ፦ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በክብር ሲገለጥ ማቴ 25:31-33, ዘካ 14:5 #ቦታ፦ በኢዮሳፍጥ ሸለቆ ( አርማጌዶን)  ኢዮኤል 3:2,12...,ራዕ 16:16 #ውጤት፦  ♦️የመንግስት ወንጌልን ያመኑ ወደ ሺው አመት  በረከት ይገባሉ ። ማቴ 25:31-32 ♦️ የመንግስት ወንጌልን አናምንም እስራኤላውያንን እናጠፍለን የሚሉት ፍርድ ይቀበላሉ =    ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ ።      ራዕ 19:21, ዘካ14 :12-13 ✍️ ይህ  ፍርድ ከአማኞች ጋር ግንኙነት የሌለው እና አማኞች ከተነጠቁ ከ ሰባት(7) አመት በኃላ የሚፈፀም ፍርድ ነው። 5) #በኢየሱስ_ባላመኑ_ሙታን #ላይ_የሚፈረድ_ነው። 👉ፍርዱ በኢየሱስ ክርስቶስ #ባላመኑ ላይ ነው 👉የፍርዱ አይነት #ሁለተኛው_ሞት ነው 👉ጊዜው የሺው አመት መንግስት ፍፃሜ ላይ 👉ቦታው #ታላቁ_ነጭ_ዙፋን ፊት ነው (የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 20) ---------- 11፤ 👉ታላቅና ነጭ ዙፋንን👈 በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፥ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ ስፍራም አልተገኘላቸውም
Показать все...
❤️በልጄ ሞት❤️ እንካ ብላ ያልከው ሰውን ለሀጢአቱ የልጅህ ስጋ ነው የሞት መድሀኒቱ በልጄ ሞት ብለህ አንተው ተዛመድከኝ ቃልህን ስጋ አርገህ ስጋህ አደረከኝ ያብራክህ ክፋይ ነኝ ላድግ አልመጣሁም የራስህ ዘር እንጂ ማደጎ አይደለሁም🙏 ✍ተፃፈ በሄኖክ አሸብር✍
Показать все...
የወንጌል እውነት አገልግሎት ጅማ Gospel Truth Ministry Jimma
Показать все...
#አምስቱ_የፍርድ_አይነቶች❤    #ክፍል_አንድ (፩) ==================== 2 ጢሞቴዎስ 2:15   የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ። ✍️ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በአዲስ ኪዳን አምስት( 5 ) የተለያዩ ፍርዶች ይገኛሉ። ይህን በአግባቡ መረዳት ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት እንዲኖረን ከማስቻሉ በተጨማሪ ፍርድን በተመለከተ በቅዱሳን ዘንድ ያለውን ግራ መጋባት ያስተካክልልናል ብለን እናምናለን። ✍️ ሀይማኖቶች ስለ ፍርድ የሚያስተምሩት እና የሚያምኑት ሰው ሁሉ ያመነም ሆነ ያላመነ አንድ ላይ ከሙታን ተነስተው እግዚአብሔር ፍርድን ያስተላልፋል ይላሉ። ይህ የሐይማኖቶች አስተምህሮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ስለሌለው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት በትህትና ልብ እንመለስ። ይሁዳ 1፡17 ይሁዳ 1 (Jude) 17፤ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤ ❤ የፍርዶችን ልዩነት ለመረዳት ፦ 1) የፍርዱ ዓይነት/ምክንያት ? 2) ፍርዱ የሚፈረደው በማን ላይ ነው? 3) ፍርዱ የሚፈረድበት ጊዜ? 4) ፍርዱ የሚፈረድበት ቦታ? 5) የፍርዱ ውጤት? 1,#የመጀመሪያው_ፍርድ ================== 📌1)#የፍርዱ_አይነት ፦በአማኝ የእድሜ ዘመን ሀጥያት  ላይ ነው ============================ 👉#ምክንያት፦ የአማኙ ሀጥያት 👉#ጊዜው ፦ በ30 ዓ.ም የዛሬ ሁለት                      ሺህ አመት 👉#ቦታ ፦ በቀራንዮ( በጎልጎታ)             መስቀል ላይ 👉#ፍርዱን የተቀበለልን ኢየሱስ ነው  👉#የፍርዱ ውጤት ለእኛ ከእግዚአብሄር ቁጣ መዳን  እና የዘላለም ሕይወት ማግኝት። ዮሐ 5:24 (ሕያው ቃል) እውነቱን ልንገራችሁ ቃሌን የሚሰማ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው ከሞት ወደ ሕየወት ተሻግሯልና በኃጥያቱ ምክንያት ለፍርድ አይቀርብም። ✍️እግዚአብሔር ክርስቶስን ኢየሱስን በቀጣበት ነገር ዳግመኛ እኛን አይቀጣንም። ማንኛው ሰው በተቀጣበት ወንጀል ዳግመኛ እንደማይቀጣ የሚደነግግ በእንግሊዘኛው Double Jeopardy በመባል የሚጠራ የሰው ሕግ አለ። ይህም ሲባል አንድ ሰው አጥፍቶ በተቀጣበት ወንጀል ዳግመኛ አይጠየቅበትም ማለት ነው። ይህ ሕግ በእግዚአብሔር ዘንድም የሚሰራነው። ስለ ኃጢአታችን እና ስለ መተላለፋችን የሚገባንን ቅጣት ሁሉ በእኛ ፈንታ ሆኖ በምትክነት በመሞት ኢየሱስ ወስዶታል። እርሱም በመስቀል ላይ ሆኖ ሁሉ እንዳለቀ አይቶ “ተፈጸመ!” ብሎ በታላቅ ድምጽ በመጮህ ለእኛ ያስተረፈልን የጽዋ ጭላጭ፣ የፍርድ እንጥፍጣፊ እንደሌለ አብስሮናል። ✍️ ዮሐንስ 19 (John) 17፤ ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ። 18፤ በዚያም ሰቀሉት፥ ✍️ 1 ጴጥሮስ 2 (1 Peter) 24፤ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ ✍️ 1 ጴጥሮስ 3 (1 Peter) 18፤ ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ ✍️ ገላትያ 3 (Galatians) 13፤ በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤ ✍️ ዕብራውያን 10 (Hebrews) 10፤ በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።........ 14፤ አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና። ✍️ ሮሜ 4 (Romans) 7፤ ዓመፃቸው የተሰረየላቸው ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፤ 8፤ ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው። ✍️ ዕብራውያን 10 (Hebrews) 18፤ የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም። ✍️ መዝሙር 103 (Psalms) 10፤ እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።...... 12፤ ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፥ እንዲሁ ኃጢአታችንን ከእኛ አራቀ። ✍️ 2 ቆሮንቶስ 5 (2 Corinthians) 21፤ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። ✍️ ሮሜ 8 (Romans) 1፤ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። ✍️ ሮሜ 8 (Romans) 33፤ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? ✍️ የዮሐንስ ወንጌል 5:24) " እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ 👉ወደ ፍርድ አይመጣም👈።" ✍️ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ይቀጥላል...... የወንጌል እውነት አገልግሎት ጅማ Gospel Truth Ministry Jimma
Показать все...
የእውነትን ቃል በአግባቡ መለየትCONTACT & MORE chrome_reader_mode CHAPTER 2/11 personScofield, C. I. expand_moreMORE lightbulb_outlineMODE shopping_cartORDER shareSHARE text_fields star_borderMARKED tab NEW TAB hearingREAD chrome_reader_mode CHAPTERS arrow_backBACK NEXTarrow_forward Book content2/11 መግቢያ 1. አይሁድ፣ አሕዛብ፣ እና የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ዓቢይ ምንባብ፣ 1ቆሮ.10፡32 2. ሰባቱ ዘመናተ-መግቦት (Dispensations) 3. ሁለቱ የክርስቶስ ምጽአቶች ዐቢይ ምንባብ፣ 1ጴጥ1፡11 4. ሁለቱ ትንሣኤዎች 5. አምስቱ የፍርድ ዓይነቶች 6. ሕግ እና ጸጋ 7. ሁለቱ የአማኝ ባሕርያት 8. የአማኝ ስፍራ እና ገሀዳዊ ሁኔታው 9. ደኅንነት እና ሽልማት (ዋጋ) 10. አማኞች እና የአፍ-አማኞች 1. አይሁድ፣ አሕዛብ፣ እና የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ዓቢይ ምንባብ፣ 1ቆሮ.10፡32 የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ የሆነ አንድ ሰው፣ ከመጽሐፉ እኩሌታ በላይ ይዘቱ የሚመለከተው አንድን ሕዝብ - ማለት  እስራኤላውያንን - መሆኑን ማስተዋል አይሣነውም፡፡ ደግሞም፣ ይኸው ሰው እነርሱ በእግዚአብሔር ዕቅድና ምክር ውስጥ በጣም ለየት ያለ ስፍራ እንዳላቸው ይገነዘባል፡፡ ከብዙኃኑ የሰው ዘር ተለይተው በያህዌ ቃል ኪዳን ውስጥ እንዲገቡ ተደርገዋል፣ እርሱም ለእነርሱ ብቻ የሆኑና ሌሎችን ሕዝቦች የማይመለከቱ ተስፋዎች ሰጥቷቸዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን ትረካዎችና ትንቢቶች ውስጥ የተነገረው የአይሁድ ታሪክ ብቻ ነው፤ ሌሎች ሕዝቦች የተጠቀሱት ከእነርሱ ጋር ባላቸው የተያያዘ ነገር አንጻር ብቻ ነው፡፡ እንዲያውም እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር እንደ ሕዝብ ያደረጋቸው ግንኙነቶች ምድርን ባጠቃላይ የሚመለከቱ ይመስላል፡፡ በቀደመው ኪዳን ውስጥ፣ እነሱ ታማኝና ታዛዥ ቢሆኑ፣ ምድራዊ ታላቅነት፣ ባለጠግነትና ኃይል እንደሚሆንላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል፤ ባይታመኑና ታዛዥ ባይሆኑ ደግሞ፣ «ከምድር ዳር እሰከ ዳርቻዋ ድረስ ወዳሉ አሕዛብ ሁሉ» (ዘዳ.28፡64) እንደሚበተኑ ተገልጾአል፡፡ እንደ ሥጋ ትውልድም ከእነርሱ ወገን እንደሚመጣ የተነገረው የመሢሑ ተስፋም ለ«ምድር ነገዶችም ሁሉ» በረከት የሚሆን ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱሱ ተማሪ ምርመራውን ሲቀጥል፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በብዛት የተጠቀሰች ሌላ ለየት ያለች አካል ያገኛል፡- እርሷም የእግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን ተብላ     ተጠርታለች፡፡ ይህችም አካል ከእግዚአብሔር ጋር በዓይነቱ የተለየ ግንኙነት አላት፤ እንዲሁም እንደ እስራኤል ሁሉ፣ ለእርሷ ብቻ የሆኑ ተስፋዎችን ከእርሱ ተቀብላለች፡፡ ነገር ግን ከእስራኤል ጋር ያላቸው ተመሳሳይነት በዚሁ ብቻ ያበቃና፣ ጉልህ የሆነው ልዩነታቸው ይጀምራል፡፡ ይህች አካል ከአብርሃም የሥጋ ተወላጆች (ዝርያዎች) ብቻ የተመሠረተች ከመሆን ይልቅ፣ እንዲያውም በእርሷ ውስጥ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ያለው ልዩነት አክትሟል፡፡ ግንኙነቱ በቃል ኪዳን ላይ ብቻ የተመሠረተ ሳይሆን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝና ጌታ በመቀበል በሚገኘው በዳግም ልደት ላይ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን፣ በመታዘዝ ምድራዊ ታላቅነትንና የሀብትን ብድራት ከማግኘት ይልቅ፣ ምግብና ልብስ ካገኘች ኑሮዬ ይበቃኛል እንድትልና፣ ስደትንና መጠላትን እንድትጠብቅ ትምህርት ተሰጥቹታል፤ እንዲሁም እስራኤል በልዩ ሁኔታ ከምድራዊና ጊዜያዊ ነገሮች ጋር እንደተያያዘች ሁሉ፣ ቤተክርስቲያንም እንዲሁ ከመንፈሳዊና ከሰማያዊ ነገሮች ጋር በልዩ ሁኔታ ተያይዛለች፡፡ በተጨማሪም፣ መጽሐፍ ቅዱስ እስራኤልም ሆነች ቤተክርስቲያን ከዘላለም ጀምሮ ሕልውና እንዳልነበራቸው ለአንባቢው ያሳየዋል፡፡ ሁለቱም በውል የሚታወቅ ጅማሬ አላቸው፡፡ አንባቢው መጽሐፍቅዱስን ሲያጠና የእስራኤል ሕልውና የሚጀምረው በአብርሃም መጠራት መሆኑን የሚረዳ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያንን የልደት ቀን ሲያፈላልግ ደግሞ፣ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ምድራዊ ሕይወት ወቅትም ሆነ ከዚያ በፊት እንዳልነበረች ይረዳል፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ስለ ቤተክርስቲያኑ ገና ወደፊት እንደምትሆን አድርጐ ሲናገር ይገኛልና(ማቴ16፡18(፡- «በዚችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለሁ፡፡» ይላል፡፡ «ሠርቻለሁ፣» አሊያም «እየሠራሁ ነው፣» አይደለም የሚለው፤ ነገር ግን «እሠራለሁ፣» ነው፡፡ በመቀጠልም ከኤፌሶን 3፡5-10 ውስጥ ቤተክርስቲያን በብሉይ ኪዳን ትንቢት ውስጥ አንድም ጊዜ እንኳ እንዳልተጠቀሰች፣ ይልቁኑም በእነዚያ ዘመናት «በእግዚአብሔር ... የተሰወረች» እንደነበር ይገነዘባል፡፡ (አንዳንድ ሰዎች በተሳሳተ ሁኔታ አዳምና ሌሎቹ የብሉይ ኪዳን አበው በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳሉ ይናገራሉ፤ ይህ ግን ስሕተት ነው፡፡) ከመጽሐፍ ቅዱስ አኳያም የቤተክርስቲያን ልደት በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ውስጥ (መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ)፣ በምድር ላይ ያላትን ፍጻሜዋን ደግሞ በተሰሎንቄ መልእክት ምዕራፍ 4 ውስጥ (የመነጠቅ ጊዜን ይመለከታል) ያገኘዋል፡፡ ደግሞም ተማሪው፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሰው ዘር ክፍፍል አንጻር፣ በመጠኑ   የተጠቀሰና በሁሉም መልክ ከእስራኤልም ሆነ ከቤተክርሰቲያን ልዩ የሆነ ሌላ ወገን ያገኛል - ይህም አሕዛብ ነው፡፡ የአይሁድ፣ የአሕዛብ እና የቤተክርስቲያን አንጻራዊ ስፍራ አጠር ባለ መልክ በሚከተሉት ምንባባት ውስጥ ይገኛል፡፡ አይሁድ - ሮሜ.9፡4-5፤ ዮሐ.4፡22፤ ሮሜ3፡1-2 አሕዛብ - ኤፌ.2፡11-12፤ C:\Users\johannes\AppData\Local\Microsoft\Windows\INetCache\Content.Outlook\BL2V4NXT\ኝመቷፀለተጸዕኤፌ.4፡17-18ኝማር.7፡27-28 ቤተክርስቲያንC:\Users\johannes\AppData\Local\Microsoft\Windows\INetCache\Content.Outlook\BL2V4NXT\ኝመቷፀለተጸዕኤፌ.1Ý22-23ኝ - C:\Users\johannes\AppData\Local\Microsoft\Windows\INetCache\Content.Outlook\BL2V4NXT\መቷፀለተጸዕኤØ.5Ý29(33ኤፌ5፡29-33፤ 1ጴጥ.2፡9 ስለ እስራኤልና ስለ ቤተክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተባለውን ሲያነጻጽር፣ በአጀማመር፣ በጥሪ፣ በተስፋ፣ በአምልኮ፣ በሥነ-ምግባር መመሪያ እና በወደፊት ግባቸው የተለያዩ ሆነው ያገኛቸዋል፡፡   በጥሪ እስራኤል እግዚአብሔር አብራምን አለው፡- ከአገርህ፣ ከዘመዶችም፣ ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ፡፡  ዘፍ12፡1፡፡ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መልካም ምድር፣ ከሸለቆና ከኮረብታ የሚመነጩ የውሃ ጅረቶችና ፈሳሾች ምንጮችም ወዳሉበት ምድር ስንዴ ገብስም ወይንም በለስም ሮማንም ወይራም ማርም ወደ ሞሉባት ምድር፡-... ያገባሃል፡፡ ዘዳ.8፡7-9፡፡ እርሱም አለ፡- እኔ የአብርሃም ሎሌ ነኝ፡፡ እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው አገነነውም፤ በጎችንና፣ ላሞችን፣ ብርንም፣ ወርቅንም ወንዶች ባሪያዎችን፣ ሴቶች ባሪያዎችን፣ ግመሎችንም አህዮችንም ሰጠው፡፡ ዘፍ.24፡34-35፡፡
Показать все...
(ለማርያም ከተሰጡት ከእነዚህ ሰባት ተስፋዎች መካከል፣ የመጀመሪያዎቹ አምስቱ ቃል በቃል ተፈጽመዋል፡፡ ታዲያ ቀሪዎቹ ሁለቱ አይፈጸሙም ልንል የምንችለው፣ የትኛው የአተረጓጐም ሕግ በሚሰጠን ሥልጣን ነው?) እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደጐበኘ ስምዖን ተርኮአል፡፡ ከዚህም ጋር የነቢያት ቃል ይስማማል እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፡ ከዚህ በኊላ ... እመለሳለሁ የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን እንደገና እሠራታለሁ እንደገናም አቆማታለሁ ...» የሐዋ.ሥ.15፡14-16፡፡ እንግዲህ፡- እግዚአብሔር ሕዝቡን ጣላቸውን? እላለሁ አይደለም እኔ ደግሞ እስራኤላዊና ከአብርሃም ዘር ከብንያምም ወገን ነኝና ... እንግዲህ፡- የተሰናከሉ እስኪወድቁ ድረስ ነውን? እላለሁ፡፡ አይደለም ነገር ግን እነርሱን ያስቀናቸው ዘንድ በእነርሱ በደል መዳን ለአሕዛብ ሆነ፡፡ ... አንተ በፍጥረቱ የበረሀ ከነበረ ወይራ ተቈርጠህ እንደ ፍጥረትህ ሳትሆን በመልካም ወይራ ከገባህ ይልቁኑስ እነዚያ በፍጥረታቸው ያሉት ቅርንጫፎች በራሳቸው ወይራ እንዴት አይገቡም? ወንድሞች ሆይ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤ እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል፡፡ ሮሜ11፡1፣ 11፣ 24-26፡፡ በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ... ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደገና እጁን ይገልጣል፡፡ ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል ከእስራኤልም የተጣሉትን ይሰበስባል ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱም የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል፡፡ ኢሳ11፡11፣12፡፡ እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል በአገራቸውም ያኖራቸዋል መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃል፡፡ ኢሳ14፡1፡፡   ስለዚህ እነሆ፡- የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን፡- የእስራኤልን ልጆች ከሰሜን ምድር ካሳደዳቸውም ምድር ሁሉ ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኊት ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ፡፡ ኤር16፡14-15፡፡   እነሆ ለዳዊት ጻድቅ ቊጥቋጥ የማስነሣለት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል ይከናወንለታልም በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል፡፡ በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል  የሚጠራበትም ስም፡- እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው፡፡ ኤር.23፡5-6፡፡ እነሆ በቊጣዬ በመዓቴ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት አገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፣ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፡፡ ኤር32፡37-38፡፡ የጽዮን ልጅ ሆይ ዘምሪ እስራኤል ሆይ እልል በይ፣ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ በፍጹም ልብሽ ሐሤት አድርጊ ደስም ይበልሽ፡፡ እግዚአብሔር ፍርድሽን አስወግዶአል ጠላትሽንም ጥሎአል የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ ነገርን አታዪም ሶፎ3፡14-15፡፡ የቤተክርስቲያንን እድገት ከማጓተት፣ ተልዕኮዋን ከመበረዝ እንዲሁም መንፈሳዊ ነገሯን ከማጥፋት አንጻር፣ ሌሎች ምክንያቶች በአንድ ላይ ተደምረው ካደረሱባት ጥፋት ይልቅ፣ ለእርስዋ አይሁዳዊ ጠባይ መስጠቱ (የእስራኤል ምትክ አድርጎ መውሰዱ) የከፋ ጉዳት አድርሶባታል፡፡ አሁን «ቤተ ክርስቲያን» ነን እያሉ እራሳቸውን የሚጠሩት የተለያዩ አካላት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የተሰጣትን የመለየት (Separation)፣ የመሰደድ፣ በዓለም የመጠላት፣ የድህነት እና አፀፋን ያለመመለስ መንገድ ፈጽሞ እየተከተሉ አይደለም፤ ነገር ግን እነርሱ፣ ለአይሁድ ማለትም ለእስራኤል የተሰጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ለቤተክርስቲያን እንደተሰጡ አድርገው በመውሰድ፣ ዓላማቸውን ወደ ዓለም ሥልጣኔ፣ ሀብት (ንዋይ) ወደ ማጋበስ፣ ሥርዓቶችን ወደ መደንገግ፣ ትላልቅ «የአብያተ ክርስቲያናት» ሕንጻዎችን ወደ መገንባት፣ የእግዚአብሔርን ቡራኬ በአገሮች መካከል በሚከሰቱ የጦርነት ግጭቶች ላይ ወደ መጋበዝ፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ፊት እኩል የሆኑ ወንድማማቾችን «ካህን» እና «ምዕመን» ብሎ ወደ መለያየት ዝቅ ለማድረግ እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ፡፡ About the book Title: የእውነትን ቃል በአግባቡ መለየት Subtitle: - English title: Rightly Dividing The Word of Truth Item number: 1150001 ISBN: No Language: Amharic More picture_as_pdf Download BOOK-PDF comment Make a text correction arrow_upward
Показать все...
እግዚአብሔር በላይህ የሚቆሙትን  ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል፤  በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፣ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ፡፡ ዘዳ.28፡7፡፡ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁል ጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም፡፡ ዘዳ.28፡13፡፡   ቤተክርስቲያን ... ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ....፡፡ ዕብ3፡1፡፡ እኛ አገራችን በሰማይ ነውና ...፡፡ ፊል3፡20፡፡ ኢየሱስም፡- ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው፡፡ ማቴ8፡20፡፡ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ እድፈትም ለሌለበት፡- ለማያልፍም ርስት... ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል፡፡ 1ጴጥ1፡4፡፡ እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፣ እንጠማለን፣ እንራቆታለን፣ እንጐሰማለን፣ እንከራተታለን ... ፡፡ 1ቆሮ4፡11፡፡ እግዚአብሔር በእምነት ባለጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድሆች አልመረጠምን? ያዕ.2፡5፡፡ ከምኩራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ዮሐ16፡2፡፡ እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው፡፡ ማቴ18፡4፡፡ በእርግጥ እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ የሚኖር አይሁድ በሞት ሲለይ ወደ ሰማይ(ገነት አይሄድም አልተባለም፡፡ ልዩነቱ፣ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ማለትም እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ መኖር ለአይሁድ የነበረው ብድራት፣ ምድራዊ እንጂ ሰማያዊ ሽልማት አለመሆኑ ላይ ነው፡፡ አሁን በያዝነው የጸጋ ዘመነ-መግቦት አይሁድም ሆኑ አሕዛብ የሚድኑት፣ ዳግመኛ በሚወለዱበት (ዮሐ.3፡3-16) እና «ቤተ-ክርስቲያን» (ኤፌ.1፡22-23) በምትሆን በዚያች «አንድ አካል» (1ቆሮ.12፡13) ውስጥ በሚጨመሩበት፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለ እምነት ብቻ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ያለው ልዩነት ይጠፋል (1ቆሮ12፡13፣ ገላ3፡28፣ ኤፌ2፡14፣ ኤፌ2፡11) «አስቀድሞ አሕዛብ የነበራችሁ»፣ (1ቆሮ.12፡2) «አሕዛብ ሳላችሁ ... »፣ የሚሉት አባባሎች የሚያስረዱን በትውልዳቸው አሕዛብም ሆነ አይሁድ የነበሩ ሰዎች፣ ወደ ቤተክርሰቲያን ሲመጡ፣ በመካከላቸው ያለው ልዩነት ጠፍቶ ሁለቱም በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት የሆኑ ክርስቲያኖች ብቻ እንደሚሆኑ ነው፡፡   በእስራኤልና በቤተክርስቲያን መካከል ያለው ልዩነት፤ ለእያንዳንዳቸው በተሰጣቸው የሥነ-ምግባር መመሪያዎች ውስጥም በተጨማሪ ይታያል፡፡ የሚከተለውን አነጻጽር፡-   በሥነ ምግባር እስራኤል                  አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን፣... በመታሃቸውም ጊዜ፣ ፈጽመህ አጥፋቸው ከእነርሱም ጋር ቃል-ኪዳን አታድርግ አትማራቸውም፡፡ ዘዳ.7፡1-2፡፡ ዓይን በዓይን ጥርስ በጥርስ እጅ በእጅ እግር በእግር መቃጠል በመቃጠል ቁስል በቁስል ግርፋት በግርፋት ይከፈል፡፡ ዘጸ.21፡ 24-25፡፡ እንዲሁም፣ ዘዳ21፡18-21፡፡   ቤተክርስቲያን ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፣ ለሚጠሉአቸሁም መልካም አድርጉ ስለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ፡፡(ማቴ5፡44) ሲሰድቡን እንመርቃለን፣ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፣ ክፋ ሲናገሩን እንማልዳለን፡፡ 1ቆሮ 4፡12፡13፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ ክፋውን አትቃወሙ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፡፡ ማቴ5፡39፡፡ ሉቃ15፡20-23፡፡ በአምልኮ ሁኔታዎች ውስጥም ልዩነት እናያለን፡፡ እስራኤላውያን ማምለክ የሚችሉት በአንድ ስፍራ እና ከእግዚአብሔር ራቅ ብለው ብቻ ነበር፤ ወደ እርሱ የሚቀርቡትም በካህን አማካኝነት ብቻ ነበር (ማለትም፣ ሁሉም ሕዝበ እስራኤል ካህን ስላልነበር ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚችሉት በተለዩ የካህናት ወገኖች አማካኝነት ብቻ ነበር) ቤተክርስቲያን ግን ሁለት ወይም ሦስት በሚሰበሰቡት በማንኛውም ስፍራ ማምለክ ትችላለች፤ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የመግባት ድፍረት አላት፤ እንዲሁም ሁሉም አባላት (አማኞች) ካህናት ናቸው፡፡ እነዚህን አነጻጻር፡-   ዘሌ.17፡8-9ን        ከማቴ.18፡20) ጋር ሉቃ.1፡10ን         ከዕብ.10፡19-20 ጋር ዘኁ.3፡10ን          ከ1ጴጥ.2፡5 ጋር   በተስፋ የእስራኤልና የቤተክርስቲያንን የወደፊት ሁኔታዎች አስመልክቶ በተነገሩ ትንበያዎች (ትንቢቶች) ውስጥም ያለው ልዩነት አስደናቂ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ከምድር ወደ ሰማይ የምትወሰድ ሲሆን፣ ወደ ቀድሞ ስፍራዋ የምትመለሰው እስራኤል ግን ገና እጅግ ታላቅ ምድራዊ ባለጠግነትና ኃይል ይጠብቃታል፡፡ ይህን ተመልከት፤ ቤተክርስቲያን በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፣ እንዲህስ ባይሆን ባልኊችሁ ነበር ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኊለሁ፡፡ ዮሐ.14፡2-3፡፡ በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድምም፤ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ ከዚያም በኊላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን፡፡ 1ተሰ4፡15-17፡፡ እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፣ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስን እንጠባበቃለን፤ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል፡፡  ፊል3፡20-21፡፡ ወዳጆች ሆይ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፡- ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፡፡ ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን፡፡ 1ዮሐ3፡2፡፡ የበጉ ሠርግ ስለደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሴትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ ... ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል፡፡ ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና፡፡ እርሱም ወደ በጉ ሠርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው ብለህ ጻፍ አለኝ፡፡ ራእ19፡7-9፡፡ በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፡፡ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ፡፡ ራእ20፡6፡፡   እስራኤል እነሆም ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ፡፡ እርሱም ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፤ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ይነግሣል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም፡፡ ሉቃ1፡31-33፡፡
Показать все...