cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

Больше
Рекламные посты
1 952
Подписчики
Нет данных24 часа
+57 дней
-330 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

+• የእንባችን ዋጋ ምን ያህል ነው? •+                አንብቡት🙏 🥀አባ አንቶኒ ኮኒያሪስ የተሰኙ የግሪክ ኦርቶዶክስ ካህን በጻፉት "ፊሎካሊያ: የኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት ቅዱስ መጽሐፍ" (Philokalia: The Bible of Orthodox Spirituality) በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ለማስተማሪያነት ያሰፈሩት እንዲህ የሚል አንድ ጥንታዊ አፈታሪክ አለ:- 🥀እግዚአብሔር ከዕለታት በአንዱ ቀን ቅዱሳን መላእክቱን "ወደ ምድር ወርዳችሁ ከሁሉ ይልቅ እጅግ ብርቅዬ የሆነውን ነገር ይዛችሁልኝ ኑ" ብሎ ያዛቸዋል:: 🥀አንድ መልአክ ሌላ ሰው ለማዳን ብሎ ራሱን መስዋእት ያድረገን ሰው የደም ጠብታን ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔርም "መልአክ ሆይ ፥ በእርግጥ ይህ በእኔ ዓይን እጅግ የተወደደ ነው:: በዓለም ያለው እጅግ ብርቅዬ ነገር ግን አይደለም::" አለው:: 🥀ሌላኛው መልአክ ደግሞ ሌሎችን ስታስታምም በያዛት በሽታ ምክንያት ያረፈችን የአንዲት ነርስ የመጨረሻ እስትንፋስ ይዞ መጣ:: እግዚአብሔርም "መልአክ ሆይ ፥ በእርግጥ ስለሌሎች የሚከፈል መስዋእትነት በእኔ ዓይን እጅግ ታላቅ ዋጋ አለው:: ሆኖም ግን በዓለም ያለው እጅግ ብርቅዬው ነገር ይህ አይደለም" አለው:: 🥀በመጨረሻም አንድ መልአክ ንስሃ ገብቶ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰን ኃጢአተኛ አንድ ዘለላ እንባ ይዞ መጣ:: እግዚአብሔርም "መልአክ ሆይ ፥ በዓለም ላይ ያለውን እጅግ ብርቅዬ ነገር አመጣህ - ይኸውም የገነትን በር የሚከፍት የንስሃ እንባ ነው!" በማለት ተናገረ:: 🥀የጌታ ቃል “እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።"(ሉቃ 15:10) ብሎ ስለ ንስሃ ዋጋ ይነግረናል:: ንስሃ ደግሞ በተሰበረ ልብና በእንባ ሲሆን ይሰምራልና ፥ በዚህ መንገድ ሆነን ንስሃ ለመግባት እንፋጠን፤ እርሱ ይቅር ይለን ዘንድ ሁሌም ዝግጁ ነውና:: 🥀   አምላከ ቅዱሳን ለንስኃ የተዘጋጀ ልብ ይፍጠርልን   ለንስኃ ሞት ያብቃን🙏             ተቀላቀሉ ቴሌግራም https://t.me/dnhayilemikael
Показать все...
ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

"ነፍሳችን በስጋ ስንኖር ብዙ መከራ አለባት። እንዲሁም ከስጋችን ከተለየች በኋላ እንደሰራነው ስራ ጥሩ ወይም መጥፎ እጣፈንታዎች ይገጥሟታል። ታዲያ በህይወት ስንኖር ነፍሳችንን የምታሻግር አንድ መንገድ አለች ይህችም ቀጥተኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ናት። "

https://t.me/MoaeTewahedoB

አስተያየት ና ጥያቄ ያለው ብቻ‼️ @sosi5555 ይህ ፔጅ ታህሳስ 30/4/2014

👍 2👎 1
አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ  "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል። ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው ቤት አለ። "የምን ቤት?" ብለህ ብትጠይቀኝ "ልብህ ነዋ" ብዬ እመልስልሃለሁ፤ "ማን ይኖርበታል?" ካልኸኝም "እግዚአብሔር ነዋ" እልሃለሁ። አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም? እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል? (Dn Abel Kassahun Mekuria ) @MoaeTewahedoB
Показать все...
4
እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ (በዓለ ሃምሳ ) በሰላም አደረሳችሁ ። በዓለ ጰራቅሊጦስ ወይም በዓለ ጰንጠቆስጤ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደበትን ቀን የምናስብበት በዓል ነው። ጰራቅሊጦስ፡- ቃሉ የግሪክ ነው። “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስሙ ሲኾን፣ ትርጕሙም 👉መጽንኢ (በእምነት የሚያጸና)፣ ❖መንጽሒ (ከኃጢአት የሚያነጻ)፣ ❖ናዛዚ (ያዘኑትን የሚያረጋጋ)፣ ❖መስተፍስሒ (የተጨነቁትን የሚያስደስት)፣ ❖ከሣቲ (ምስጢርን የሚገልጽ) ማለት ነው ከበዓሉ በረከት ረድኤት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያሳትፈን። https://t.me/dnhayilemikael
Показать все...
ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

2ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፈ 5 6 እንግዲህ ሁልጊዜ እመኑ ጨክኑሞ በዚህ ሥጋ ሳላችሁም እናንተ እንግዶች እንደ ሆናችሁ ታውቃላችሁ ከሥጋችሁ ተለይታችሁ በሄዳችሁ ጊዜ ወደ ጌተችን ትሄዳላችሁ ። 7 በእምነት እንሄዳለን በማየትም አይደለም 8 ታምነናል ይልቁንም ከሥጋችን ተለይተን ወደ ጌታችን እንሄዳለንና ደስ ይለናል ። 9 አሁንም ብንኖርም ብንሞትም እርሱን ደስ ለማሰኘት እንጥራለን ። 10 መልካም ቢሆን ክፉም ቢሆን በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን እንቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንሰማለንና
Показать все...
3
*በዓለ ጰራቅሊጦስ* ❖ጰንጠቆስጤ ቃሉ የግሪክ ቃል ነው፡፡ ትርጓሜውም ሃምሳኛ ማለት ነው፡፡ ❖ ጰራቅሊጦስ ማለትም የሚረዳ፤ የሚያጽናና ማለት ነው፡፡ ❖በብሉይ ኪዳን በዓላት ለምሳሌ የአይሁድ የፋሲካ በዓላቸውን ካከበሩ በኋላ አምሳውን ቀን የነጻነት በዓላቸው አድርገው ከሰነበቱ በኋላ ኃምሳኛውን ቀን በተለየ ሁኔታ በዓለ ሰዊት ብለው ያከብራሉ፡፡ ❖ በእነርሱ ሀገር ከመጋቢት እስከ ግንቦት ያለው ወቅት ጸደይ /የእሸት ወራት/ ነው፡፡ ጌታችን እርሱ ባወቀ ይህን በዓል /በዓለ ሠዊትን/ ለሐዲስ ኪዳን በዓላችን ፪ ጥቅሞችን እንዲያስገኝ አድርጓል”” ✢ የመጀመሪያ ለበዐለ ጰራቅሊጦስ ምሳሌ መንገድ ጠራጊ፤ መተርጐሚያ ፤ ማሳመኛ መሆኑ ነው፡፡ ✢ ሁለተኛው በዓሉ እንዲከበር ምክንያት የሆነው ርደተ-መንፈስ ቅዱስ /የመንፈስ ቅዱስ መውረድ/ ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን በተነሳ በአምሳኛው ቀን በወረደበት ዕለት በዝርዎት የነበሩ አይሁድ ሁሉ ለበዓለ ፋሲካና ከዚሁ ተያይዞ ለሚከበረው ለበዓለ ሠዊት እንደተሰበሰቡ የተፈጸመ መሆኑ ነው፡፡ ❖ ሰዎቹም በጸሎት የተጉ መሆናቸውና ከእግዚአብሔር የሆነውን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸው በክርስቶስ አምላክነት አምነው የቤተክርስቲያን መሠረት እንዲጣል ምክንያት ሆኖአል፡፡ ማስረጃ፡- ሐዋ.፪÷፭-፮ “ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤ ይህም ድምጽ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ ….” ሕዝቡም እንደተጻፈውም ነገሩ ከእግዚአብሔር መሆኑን ለመመርመር ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ሐዋ.፪÷፯-፲፩ “ ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ፡- ❖እነሆ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? ❖እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን?... እግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን፡፡” ❖ተገርመው ተደንቀውም አልቀሩም - 👉አለ -የቅ/ጴጥሮስን ስብከትሰምተው አምነው የተጠመቁ ብዙዎች ናቸውና ይህንን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ሐዋ.፪÷፵፩-፵፪ “ ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤በሐዋርያትም ትምህርትና በኀበራት እንጀራውንም በመቁረስ በጸሎትም ይተጉ ነበር” ❖ ይህዊ ዕለት፤ የቤተክርስቲያን የልደት ቀን የምትባለውም ለዚህ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የወረደበት፤ በሦስት ሺህ ✢ሰዎች ጥምቀት መስፋፋት የጀመረችበት፤ ሐዋርያትም ፍሩሃኑ ጥቡዓን /ደፋሮች/ ሆነው፤ በዕውቀት በልጽገው፣በአእምሮ ታድሰው ዓለሙን ለመለወጥ ኃይል ያገኙባት ዕለት ናት፡፡ ❖ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ እነዚህን ነገሮች አስታውጦ ሲናገር “መንፈስ ቅዱስ ባይወርድላት ኑሮ የቤተክርስቲያን ሕልውና ከስሞኖ ቀጭጮ ይቀር ነበር፤ ስለዚህም በሚገባ አነጋገር ይህች ዕለት የቤተክርስቲያን የልደት ቀን ትባላለች” ብሎአል፡፡ 👉ከዚህም የተነሳ ሌሎች ሊቃውንትም ዕለቲቱን የበዓላት ሁሉ እመቤት እንደሚሏት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ገልጸውታል፡፡ በዓሉ ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው ለቤተክርስቲያን “ ከእናንተ ጋር ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ፤ እኮ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፤ እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል” እና “ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤በስሜ አጋንንትን ያወጣኑ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤…” ሲል የገባው ኪዳን የተፈጸመበት ተደርጎም ይከበራል፡፡ 👉 በእኛ በቤተክርስቲያን ሊቃውንት በፍትሐነገሥት የገለጹትን በማሰብ ለመንፈሳዊ ሐሴት በቃለ -እግዚአብሔር ይከበራል ፡፡ ፍትሐ ነገሥታችን “ ትንሣኤን በአከበራችሁ በአምሳኛው ቀን ዕርገቱን በአከበራችሁ በዐሥረኛው ቀን በዓለ ጰራቅሊጦስን አክብሩ በዓል ይሁንላችሁ" እንዳለ ቤ/ክ ታከብራለች! ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ    ╭═https://t.me/dnhayilemikael
Показать все...
ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

ይህ የሀገረ ማርያም ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሠረተ ተዋሕዶ ሰንበት ት/ት ቤት አባላት መማሪያና መልእክት መጋሪያ ብቻ ይሆን ዘንድ የተዘጋጀ አውታር ነው።

መጽሐፍ : ቅዱስ : እንዲህ : ይላል :- «በጥቂቱ : ታምነሃል : በብዙ : እሾምሃለሁ፤..." (ማቴ. 25 ፥ 2።) ይህም ፡ ማለት ፡ በምድራዊ ፡ ነገሮች ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ስትገኝ ፡ በሰማያዊ ፡ ነገሮች ፡ ላይ ፡ እሾምሃለሁ ፡ ማለት ፡ ነው። በዚህኛው ፡ ዓለም ፡ ውስጥ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከቆየህ ፡ በዘላለማዊነት ፡ ውስጥ ፡ እሾምሃለህ ፡ ማለትም ፡ ነው። ይህ ፡ መመሪያ ፡ በብዙ ፡ መስኮች ፡ ላይ ፡ ተግባራዊ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል . . . ༒ ዘመዶችህን ፡ በመውደድ ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከተገኘህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጠላቶችህንም ፡ በመውደድ ፡ ላይ ፡ ይሾምሃል፡፡ ጠላትህን ፡ የምትወድበትን ፡ ጸጋ ፡ ያድልሃል ፡ ማለት ፡ ነው፡፡ ༒ በትርፍ ፡ ጊዜዎችህ ፡ እግዚአብሔርን ፡ የምታገለግል ፡ ከሆንህ ፡ በሕይወትህ ፡ ጊዜ ፡ ሙሉ ፡በእርሱ ፡ ላይ ፡ ትኵረት ፡ የምታደርግበትን ፡ ፍቅር ፡ ያድልሃል፡፡ ༒ የፈቃድ ፡ ኃጢአቶችን ፡ ከአንተ ፡ በማስወገድ ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከተገኘህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ፈቃድህ ፡ ከሚመጡ ፡ ኃጢአቶች ፡ ነጻ ፡ ያወጣሃል። ༒ ንቁ ፡ ኅሊናህን ፡ ከክፉ ፡ ሀሳቦች ፡ የምትጠብቅ ፡ ከሆንህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ንቁ ፡ ያልሆነው ፡ ኅሊናህን ፡ ንጽሕና ፡ ይጠብቅልሀል። ከዚህ ፡ በተጨማሪ ፡ የሕልሞችህን ፡ ንጽሕናም ፡ ይጠብቅልሀል። ༒ ልጅ ፡ እያለህ ፡ ታማኝ ፡ ከሆንህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ውጊያዎች ፡ በሚበዙበት ፡ በወጣትነት ፡ ዘመንህ ፡ ውስጥም ፡ ታማኝነትን ፡ ያድልሃል፡፡ ༒ ሌሎች ፡ ሰዎች ፡ ላይ ፡ በቃላት ፡ ብቻ ፡ የማትፈርድባቸው ፡ ሆነህ ፡ ለመገኘት ፡ ታማኝ ፡ ከሆንህ ፡ ይበልጥ ፡ አስቸጋሪ ፡ በሆነው ፡ በሀሳብ ፡ እንዳትፈርድባቸው ፡ ያስችልሃል፡፡ ༒ ልክ ፡ እንደዚሁ ፡ ራስህን ፡ ከውጪያዊ ፡ ንዴት ፡ በመጠበቅ ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከተገኘህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከውስጣዊ ፡ ቁጣ፣ ንዴትና ቅናት ፡ ነጻ ፡ ያወጣሃል። ༒ በተለመዱ ፡ መንፈሳዊነቶች (በመንፈስ ፡ ፍሬዎች) ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ከተገኘህ ፡ እግዚአብሔር ፡ የመንፈስ ፡ ስጦታዎችን ፡ ያድልሃል! በመጀመሪያው ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ ሆነህ ፡ ካልተገኘህ ፡ ሁለተኛውን ፡ ፈጽሞ ፡ ልታገኘው ፡ አትችልምና፡፡ እግዚአብሔር ፡ በመጀመሪያ ፡ የሚፈትሽህ ፡ በጥቂት ፡ ነገር ፡ ነው:: በዚህች ፡ በጥቂቷ ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ታማኝ ፡ መሆንህን ፡ ካረጋገጥህ ፡ እርሱ ፡ በሚበልጠው ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ይሾምሃል፡፡ ውድቀትህንና ፡  አለመታመንህን ፡ በጥቂቷ ፡ ነገር ፡ ላይ ፡  ከገለጽህ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ በሚበልጠው ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ አይሾምህም። መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ እንዲህ ፡ ይላልና:- «ከእግረኞች ፡ ጋር ፡ በሮጥህ ፡ ጊዜ ፡ እነርሱ ፡ ቢያደክሙህ ፡ ከፈረሶች ፡ ጋር ፡ መታገል ፡ እንዴት ፡ ትችላለህ?» (ኤር. 12 ፥ 5።) ብዙ ፡  ሰዎች ፡ ዝቅተኛውን ፡ ኃላፊነት ፡ መወጣት ፡ ሳይችሉ ፡ ከፍተኛውን ፡ ኃላፊነት ፡ ለመቀበል ፡ ማሰባቸው ፡ እጅግ ፡ አስደናቂ ፡ ነገር ፡ ነው። እነዚህ ፡ ሰዎች ፡ በተሰጣቸው ፡ ጸጋ ፡ ሳይጠቀሙ ፡ ተጨማሪ ፡ ጸጋ ፡ እንዲሰጣቸው ፡ የሚጠይቁ ፡ ናቸው። ይህን ፡ ሲያደርጉም ፡ «በጥቂቱ ፡ ታምነሃል ፡ በብዙ ፡ እሾምሃላሁ፤...» የሚለውን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ በመዘንጋት ፡ ነው። ይህ ፡ ቃል ፡ ለእነርሱ ፡ እንደ ፡ ሁኔታው ፡ የሚወሰንበት ፡ ነው ፡ የሚሆነው፡፡ ════•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ════   ✞❀ https://t.me/dnhayilemikael ❀✞ ════•ೋ•✧๑♡๑✧•  ════
Показать все...
ኑ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @zearsema_dn

👍 1
‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ››
Показать все...
2
✝ስለ ምሥጢራተ ቅድሳት ✝ ✝✝✝ ከኢትዮዽያ #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ ምዕመናን አብዛኛው #ከቅዱስ_ሥጋውና_ክቡር_ደሙ የራቀ መሆኑን ሳስብ በጣም አዝናለሁ! ✝✝✝ ✝ ግን ለምን ??? ✝ ✝ ለምን ብዙዎቻችን #ሕይወት_መድኃኒት ከሆነው ማዕድ ተለየን ??? ✝ ✝ ከቅዱስ ሥጋው ሳይበሉ: ከክቡር ደሙ ሳይጠጡ መዳን ይኖር ይሆን ??? ✝ ✝ በሰማያዊው ዙፋን #በዘለዓለም_አምላክ_በክርስቶስ ፊትስ በቂ መልስ ይኖረን ይሆን ??? ✝ ✝ሁልጊዜ ባልረባ ምክንያት ሕይወት ከሆነው #ማዕደ_ክርስቶስ እስከ መቼ እንርቃለን ??? +እርሱ ግን አሰምቶ ይጠራናል:: "ኑ! ሥጋየን ብሉ: ደሜንም ጠጡ" ይለናል:: "ሥጋየን የሚበላ: ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው:: እኔም በእርሱ አድሬበት እኖራለሁ" ይለናል:: (ዮሐ. 6:56) +ሌላ መንገድ አለ እንዳይመስለን ደግሞ "የሰውን ልጅ (የክርስቶስን) ሥጋውን ካልበላችሁ: ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም" (ዮሐ. 6:53) የሚል ተግሣጽን ልኮልናል:: +ቤተ ክርስቲያን እኛን ወደ #ምስጢረ_ቁርባን ለማድረስ ከእነዚህ የተረፈ ነገር አልጫነችብንምኮ! ¤በሃይማኖት መኖር (መመላለስ) ¤ከክርስቶስ (ከጌታችን) ጋር ለመኖር ቁርጥ ውሳኔ ¤በመምሕረ ንስሃ ሥር መጠለል ¤በንስሃ ሕይወት መመላለስና ¤ቀዋሚ የሕይወት መሥመር (ጋብቻ ወይ ምናኔ) መያዝን ትሻለች እንጂ መቼ ሌላ ቀንበር ጫነችብን! +እናም የመንፈስ ወንድሞቼና እህቶቼ . . . ¤የራቅን እንቅረብ! ¤የቀረብንም እንበርታ! ¤የበረታንም እንጽና! ¤የጸናንም ደካሞቹን እንርዳ! (ይህ በጌታ ዘንድ ዋጋው ትልቅ ነውና!) ☞#የምሕረት_ጌታ #ለምሥጢራተ_ቅድሳት የምንበቃበትን የምሕረት ዘመን ያምጣልን:: ☞ግን እናስብበት!!! <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> . Dn Yordanos Abebe https://t.me/Meseretemedia
Показать все...
ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

ይህ የሀገረ ማርያም ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሠረተ ተዋሕዶ ሰንበት ት/ት ቤት አባላት መማሪያና መልእክት መጋሪያ ብቻ ይሆን ዘንድ የተዘጋጀ አውታር ነው።

👍 1
Показать все...
ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

ይህ የሀገረ ማርያም ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሠረተ ተዋሕዶ ሰንበት ት/ት ቤት አባላት መማሪያና መልእክት መጋሪያ ብቻ ይሆን ዘንድ የተዘጋጀ አውታር ነው።

Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.