𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂⏰
Открыть в Telegram
#Info Makes Chanege #አንድ_ላይ_ኾነን_ለውጥ_እንፈጥራለን! ማንኛውንም ቡልቡላ ነክ ወሬ፥ መረጃ እና ሃሳብ 👉 @Bulbula_bot ላይ ልታደርሱን አልያም ልትጠይቁን ትችላላችሁ። ለደላላ👉 @BDilela_bot
Больше2 437
Подписчики
+324 часа
+117 дней
+4830 день
Архив постов
2 437
⚠️Cyber Security Alert
‘Trust’ እና ‘Google TV’ የተባሉ መተግበሪያዎች የባንክ አካውንትን ለአደጋ እያጋለጡ ነው
በኢንተርኔት ማስፈንጠሪያዎች (links) አማካይነት ወደ ስልኮች በመግባት የባንክ ሂሳብን የሚያጠፉ “Trust”፣ “Google TV” እና “Known” የተባሉ አደገኛ የአንድሮይድ መተግበሪያዎች በስፋት እየተሰራጩ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።
እነዚህ መተግበሪያዎች በተለይ በGoogle Chrome፣ Telegram እና WhatsApp መድረኮች ላይ የሚጋሩ ሲሆን፥ ተጠቃሚዎች ሳያውቁ የገንዘብ ዝውውር በመፈጸም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ።
ይህ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሳይበር ጥቃት በስፋት እየተስተዋለ የመጣው ተጠቃሚዎች ከተላኩላቸው አጠራጣሪ ሊንኮች ላይ መተግበሪያዎቹን ሲያወርዱ መሆኑ ታውቋል። መተግበሪያዎቹ አንዴ ስልክ ላይ ከተጫኑ በኋላ ከሞባይል ባንኪንግ ጋር የተያያዙ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በመስረቅ ገንዘብ የመውሰድ አቅም እንዳላቸው ተገልጿል።
ህብረተሰቡ ከዚህ መሰሉ የሳይበር ዘረፋ ራሱን ለመጠበቅ መተግበሪያዎችን ከታመኑ ምንጮች (እንደ Play Store ወይም App Store) ብቻ ማውረድ እንዳለበት ባንኩ አሳስቧል።
ከተጠቀሱት የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች የሚላኩ አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመክፈት እና በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ላይ የባዮሜትሪክ (የፊት ወይም የአሻራ) እና የፒን (PIN) የደኅንነት ማረጋገጫዎችን አጣምሮ መጠቀም ለአደጋው የመጋለጥ እድልን በእጅጉ እንደሚቀንስ ተነግሯል።
#ሳይ_ቴክ
@BBN_info
2 437
🎉 REGISTRATION IS NOW OPEN! 🎉
Give your child a summer filled with creativity, confidence and fun!
🧸 Sew & Shine! Summer Kids Program
For children aged 8–12 years
Your child will learn to:
✂️ Hand & Machine Sewing
📐 Basic Pattern Concepts
📏 Measuring, Marking & Cutting
🧸 Make Their Own Plush Toy
🎨 Fashion Design & Creativity
🏆 Graduate with a Certificate
📅 Batch 1
July 7 – August 4, 2026
📅 Batch 2
August 5 – September 2, 2026
📍 Sweet Toys Workshop
Bole Bulbula 40/60 Condominium
Block 43
House No. 108
First Floor
Addis Ababa
💰 Training Fee
ETB 10,000
🎒 Kit
ETB 4,500
(includes apron & hair cover)
☎️ +251 911 410 975
☎️ +251 934 444 4408
📧 sweettoysethiopia@gmail.com
⚠️ Only 12 children per group!
Register early before seats fill.
#SweetToys
#SewAndShine
#SummerCamp
#KidsSewing
2 437
ከጠቀማችሁ!……
፩) ለአንድ ሰው ከሁለቴ በላይ አትደውሉ። ምናልባት የማያነሱ ከሆነ ወይ አላዩትም፣ ወይ ለማንሳት የሚመች ቦታ አይደሉም፣ ወይ ደግሞ ማንሳት አልፈለጉም። ስለዚህ መልሰው እስኪደውሉላችሁ ጠብቁ።
፪) የተበደራችሁትን ገንዘብ አዳሪው ከማስታወሱ ወይም ከመጠየቁ በፊት መልሱ። ይሄ የታማኘነታችሁ ወይም የመልካም ስብዕናችሁ መገለጫ ነው። ምናልባት ምልሰቱ ከእስክሪብቶ፣ ከእስርሳስ ሊጀምር ይችላል።
፫) አንድ ሰው ሆቴል ሲጋብዛችሁ ውድ ምግቦችን እና መጠጦችን ከማዘዝ ተቆጠቡ። ምክንያቱም ያስገምታችኋል።
፬) "እስካሁን ለምን አላገባህ/ሽም፤ ልጆች ለምን አልወለድክ/ሽም፤ አይነት በጣም ደባሪ ጥያቄዎችን አትጠይቁ። በፈጣሪ ስም! ይሄ የእናንተ ችግር አይደለም።
፭) ከኋላችሁ የሚመጣ ሰው ካለ ሁሌም በሩን ከፍታችሁ አስገቡት። ሴት ትሁን ወንድ፤ ታላቅ ይሁን ታናሽ ማተር አያደርግም። ሰዎችን በማክበር እናንተ አትዋረዱም።
፮) ጓደኛችሁ ዛሬ የታክሲ ከከፈለ፣ ነገ እናንተ ለመክፈል ሞክሩ።
፯) ልዩነቶችን አክብሩ። ለእናንተ 6 ቁጥር የመሰለው ለሌላው 9 ቁጥር ሊመስል ይችላልና ሐሳቡን እንደተቀናቃኝ ሳይሆን እንደአማራጭ ይውሰዱት።
፰) የሰዎችን ንግግር አታቋርጡ። እስኪጨርሱ በሚገባ አድምጠው የናንተን ቀጥሉ።
፱) ሰው ላይ አፊዛችሁ ደስተኛ ካልመሰለ በድጋሚ እንዳትቀልዱባቸው። ምክንያቱም የናንተ ሽንቁር ሌላውን ለማስገባት ትሞክራለች።
፲) በማንኛውም ነገር እርዳታ ስታገኙ "አመሰግናለሁ" ማለትን ልመዱ።
፲፩) ሰውን በሕዝብ ፊት ያወድሱ፣ ለብቻ ይገስፁ።
፲፪) የሰው መልክ፣ ቁመና፣ ፀባይ፣ ውፍረት… ላይ ምንም አስተያየት የመስጠት በቂ ምክንያት የላችሁም። የምትሏቸው ነገር ቢኖር "ውብ ናችሁ" ብቻ ነው። የምትናገሩት መልካም ካልሆነ ግን ዝምታን ልመዱ።
፲፫) ሰዎች አንድ ፎቶ ብቻ ሊያሳይዋችሁ ፈልገው ስልካቸውን ከሰጧችሁ ወደፊት፣ ወደኋላ አያድርጉ። ምክንያቱም ቀጣዩ ምን እንደሆነ አታውቁም!!
፲፬) ጓደኛችሁ የሕክምና ቀጠሮ እንዳላቸው ከነገሯችሁ ምን እንደሆነ በፍፁም እንዳትጠይቋቸው። "እንደሚሻልህ/ሽ ተስፋ አደርጋለው" ብቻ በሉ። የጤና እክላቸውን ተናግረው የሚረብሽ ኹኔታ ውስጥ እንዳትከቷቸው ተጠንቀቁ። እነሱ መንገር ከፈለጉ ያለናንተ ጥያቄ ይነግሯችኋል።
፲፭) ለዶክተር፣ ለባለስልጣን፣ ለባለፀጋ ክብር በምትሰጡት ልክ ለፅዳት ሰራተኛም፣ ለተራው ዜጋም፣ ለነዳዲያንም ስጡ። ሰውን መናቅ ብልግናችሁን ቢሆን እንጂ ሌላ ምንም አያሳይም። ሁሉንም ሰው በእኩል አይን ማክብር ትልቅነት ነው።
፲፮) ሰዎች ፊት ለፊት እየተመለከቱ ሲያናግሯችሁ ሞባይል፣ ኮምፒተር ወይም መጻሕፍትም ቢሆኑ ተተክላችሁ አትመልሱ። ተገቢ አይደለም። በወቅቱ ቀዳሚው መሆን የሚገባው ሰዎቹ እንጂ ቁስ አይደለም።
፲፯) ከረጅም ጊዜ በኋላ ጓደኛችሁን ወይም ወዳጃችሁን ካገኟችኋቸው እነሱ ለመናገር ካልፈቀዱ በስቀር ስለኑሯቸው፣ ስለሕይወታቸው ከመጠየቅ ተቆጠቡ።
፲፰) በቀጥታ ካልተመለከታችሁ በስተቀር በማያገባችሁ ጉዳይ አትግቡ።
፲፱) ሰዎች መንገድ ሲያናግሯችሁ የአክብሮት ምልክት በመሆኑ የፀሐይ መነፅራችሁን የማውለቅ ልምድ ይኑራችሁ። ከቃላት እኩል የአይን ግንኙነት ጠቃሚ ነው።
፳) ስለባለፀግነታችሁ በነዳዲያን ፊት ከመለፍለፍ ይቆጠቡ። በተመሳሳይ ስለልጆች በመሃኖች ፊት አያንሱ።
፳፩) ካልተጠየቃችሁ በስተቀር ለማንም ምክር ለመስጠት እትሞክሩ። "ባንተው ምክር ሄጄ፣ ባንተው አስጨከነኝ" እንዳለው ድምፃዊው አንተስ ምን እያደረክ ነው ካላችሁኝ ምናልባት ይሄ በጥቆማ ደረጃ ከተወሰደ ቢሆን እንጂ ምክር መሆን የሚችል አይመስለኝም።
መልካም ቀን ❤
@BBN_info
2 437
+1
አሁንም የተወሰኑ ቦታዎች ስላሉን ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆችዎን እየመዘገብን እንገኛለን ።
የዘንድሮ የ12ተኛ ክፍል ተፈታኞች እንዲሁም የ2018 የ11ኛ ክፍል የክረምት ተማሪዎች
ውድ ወላጆች እና አሳዳጊዎች 👇
በጥያቄያችሁ መሠረት የክረምት ትምህርታችሁን በማይነካ መልኩ የከሰዓት ልዩ የስልጠና ፖኬጅ ያዘጋጀን መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው ፡፡
📞 0910215400
በመጪው የክረምት ወቅት ለሁሉም ሰልጣኞች እና ቤተሰቦች የተሻለ የስልጠና አካባቢ ለመፍጠር ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ ነን ።
ለቀጣይ እምነታችሁ እና አጋርነታችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር፣
የተቋሙ አስተዳደር
📞 አሁኑኑ ይደውሉ/ ያግኙን፤ ይመዝገቡ 👇
Bulbula branch representative
• ስልክ፡ 0945562429 (SMS)
0910215400 / call
• የቪዲዮ ለማየት ሊንኩን ይጫኑ👇❤️
https://vt.tiktok.com/ZSCJbEMtp/
2 437
#ቅድሚያ_መስጠት_ላለብህ_ብቻ
… ቅድሚያ ስጥ
ታዋቂው አሜሪካዊ ኮሜድያንና የፊልም ዳይሬክቴር ውዲ አለን በአንድ ወቅት በተጋበዘበት ዩኒቨርስቲ ለፍልስፍና ተማሪዎች..... ተሞክሮውን እንዲህ ባለ ምሳሌ አካፍሏቸዋል.....
"....አሁን አንድ ቀላል ምሳሌ አሳያችኋለሁ፤ ይኽ የምታዩት የማርማላት ጠርሙስ ባዶ ነው ወይስ አይደለም?" አላቸው። ተማሪዎቹም በአንድ ቃል
"ባዶ ነው" አሉት።
የተማሪዎቹን መልስ እንደሰማ የጠረጴዛ ቴኒስ ኳስ በማንሳት ጠርሙሱን ይሞላው ጀመር። ኳሷቹ የጠርሙሱ አፍ ሲደርሱ....."አሁንስ?" በማለት ጠየቃቸው።
"አሁን ሞልቷል!".....አሉት ተማሪዎቹ በአንድ ቃል።
አለን ግን ብዮች እንስቶ በጠርሙሱ ውስጥ መክተት ጀመረ። ብዮቹም በኳሶቹ መሀል እየገቡ ቦታቸውን መያዝ ጀመሩ።
"አሁንስ?" አላቸው። ተማሪዎቹ በድጋሚ በአንድ ቃል " አሁን ሞልቷል!" አሉት ።
አለን አሁንም ደቃቅ አሸዋ ዘግኖ ጠርሙሱ ውስጥ መክተት ጀመረ። አሸዋውም ገብቶ ቦታውን ያዘ " አሁንስ?" አላቸው። ተማሪዎቹም በእርግጠኝነት "አሁን ሞልቷል!"አሉት። አንድ ጠርሙስ ቢራ ከፈተና ማንቆርቆር ጀመረ። ቢራውም ገብቶ ቦታውን መያዝ ጀመረ። ይኽን ጊዜ ተማሪዎቹ በመገረም መሳቅ ጀመሩ።
".....አሁን" አለ ውዲ አለን የተማሪዎቹ ሳቅ ረገብ ሲል ጠብቆ "......ይኽ የማርማላት ጠርሙስ የእናንተን ሕይወት የሚወክል ነው......የጠረጴዛ ቴኒስ ኳሱ በሕይወታችሁ ውስጥ እጅግ አስፈላጊውን ክፍል የሚይዝ ነው። ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ፣ ጤንነት ፣ ልጆች በአጠቃላይ የምትወዱት ነገር ሊሆን ይችላል...
".....ብዮቹ ደግሞ ሁለተኛው የሕይወታችሁ ጉዳይ ሲሆኑ ይኸውም ሥራችሁ ፣ ቤታችሁ ፣ መኪናችሁ ሊሆን ይችላል። አሸዋው ደግሞ በሦስተኛ ደረጃ የሚያስፈልጋችሁና ጥቃቅኑ ነገር ነው ።
"......ነገር ግን በሕይወታችሁ ውስጥ አስቀድማችሁ አሸዋውን ብትከቱ ለጠረጴዛ ቴኒስ ኳስና ለብዮቹ ቦታ አይኖራችሁም ነበር። ሕይወታችሁም እንዲሁ ይመስላል። ጊዜአችሁንና ጉልበታችሁን ለጥቃቅኑ ጉዳይ ቅድሚያ ከሰጣችሁ በሕይወት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ለሆነው ጉዳይ የሚሆም ቦታ አይኖራችሁም ። ዋነኛ አትኩሮታችሁ ለሕይወት የሚጠቅማችሁ ጉዳይ ላይ ብቻ ይሁን ።
መልካም ቀን🌞
@BBN_info
2 437
📍አድራሻ፡ ቦሌ ቡልቡላ ከአባሳሙኤል ቤ/ክ 150ሜትር ከፍ ብሎ ከሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ ጐን ያገኙናል።
☎️ +2519-04-77-44-77
Telegram:@DyAKG
dynamicaddis@gmail.com
2 437
Repost from 𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙱𝚁𝙾𝙺𝙴𝚁𝚂🤝
📌የሥራ ማስታወቂያ
ከ ኦፓል የውበት ሳሎን፡
የሥራው ዓይነት፡ የሳሎን ሪሴፕሽኒስት (Receptionist)
የእኛ የውበት ሳሎን ተጫዋች፣ ቀልጣፋ እና በሥራዋ ፕሮፌሽናል የሆነች የሪሴፕሽን ባለሙያ አጋር አድርጎ መቅጠር ይፈልጋል።
🚨 ዋና መስፈርት (Mandatory Requirement)
• ለሶሻል ሚዲያ የሚሆኑ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ፎቶዎች ማንሳት እና ቪዲዮዎችን መቅረጽ መቻል ግዴታ (Mandatory) ነው!
• በነጻነት እና በተሻለ ሁኔታ እንግሊዘኛ እና አማርኛ መናገር/መጻፍ የምትችል
•መሠረታዊ የኮምፒውተር ችሎታ እና የማይክሮሶፍት ኤክሴል (Microsoft Excel) እውቀት ያላት
•የደንበኞችን ቀጠሮ እና ቡኪንግ በሥርዓት መያዝ የምትችል
•እጅግ በጣም ጥሩ የደንበኛ አያያዝ እና የኮሚዩኒኬሽን ክህሎት ያላት
•በሥራዋ ንቁ፣ ኃላፊነት የሚሰማት እና ሰዓት አክባሪ የሆነች
•ማራኪ የውጫዊ ገጽታ (አለባበስ) እና በጎ አመለካከት ያላት
•በውበት ሳሎን ውስጥ ከዚህ ቀደም የሥራ ልምድ ያላት
•ደንበኞችን በደስታና በአክብሮት መቀበል እንዲሁም ማስተናገድ
•የደንበኞችን የሳሎን አገልግሎት ቀጠሮዎች ማስተካከል እና መምራት
•ለስልክ ጥሪዎች እና ለሶሻል ሚዲያ መልእክቶች ፈጣን ምላሽ መስጠት
•በሳሎኑ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ፎቶ ማንሳት እና ቪዲዮ መቅረጽ
•የደንበኞችን መረጃ እና የዕለት ተዕለት ሪፖርቶችን መያዝ
•የሳሎኑ አጠቃላይ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲሄድ መደገፍ
የሥራ ሰዓት፡ በፈረቃ
👉ጠዋት 2:30 - ምሽት 1 ሰአት
👉 ረፋድ 4:30 -ምሽት 3:30
📍 አድራሻ ፡ ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ
📲 ለመቀጠር፡ ሲቪሽን (CV) በ @anali2378 ላኪልን።
2 437
📌አስቸኳይ የሥራ ማስታወቂያ
የድርጅቱ ስም፡ ሶማ - SOMA ሬስቶራንትና ካፌ
1. ባርማን - ኮክቴል መጠጦችን የማዘጋጀት ልምድ ያለው/ያላት
2. ባሪስታ ፡ ተኩስ እና ቀዘቃዛ መጠጦችን የማዘጋጀት ልምድ ያለው/ያላት። (ሥልጠና የወሰደ/ች ቢኾን ይመረጣል)
3. ገንዘብ ተቀባይ / ካሸር፡ ቢያንስ የ 2 አመት በፖስ ማሽን የመስራት ልምድ ያላት
4. መስተንግዶ ሱፐርቫይዘር: በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ የሰለጠነ/ች እና ቢያንስ የ2 አመት ልምድ ያለው / ያላት
5. ስቴዋርድ (ዕቃ አጣቢ) ፡ በተመሳሳይ ዘርፍ ልምድ ያላት
6. ጋጋሪ ፡ አርቲሲያን ሳወር ዶው ዳቦዎችን የመጋገር ልምድ ያለው
ለማመልከት የሥራ ዘርፉን፣ የስልክ ቁጥር፣ የትምህርት እና የስራ ልምድ በዚህ ቴሌግራም አካውንት ይላኩልን @MHElban
📌አድራሻ፡ ቦሌ ቡልቡላ--> ማሪያም ማዞሪያ
2 437
ዘንድሮ ከምንግዜውም በላይ ለተማሪዎች የክረምት ማሳለፊያ የኾኑ አማራጮች በዝተዋል።
ከአምና አንጻር በርካታ የSummer Camp ማስታወቂያዎችን እያየን ነው።
በሰለጠነው ዓለም በተለይ በአሜሪካ ተማሪዎች በትምህርት ቤታቸው አማካኝነት ከከተማ ወጥተው የተዘጋጀ ካምፕ ላይ አርፈው ስፖርት፣ ሙዚቃ፣ ትያትር የመሳሰሉ ነገሮችን እየተማሩ እየተዝናኑ ያሳልፋሉ።
ከካምፑ ወደቤት ሲመለሱ ንፁሕ አዕምሮ ይዘው ስለሚመለሱ በጋውን በተሻለ አቅም የሚማሩበት ኃይል ሰብስበው ይመለሳሉ።
እኛም አገር ተስፋዎች እንዳሉ ከዘንድሮ የሰመርካምፕ ማስታወቂያዎች እያየን ነው።
እስከዛሬ የነበረው ልጅን የክረምት ትምህርት ማስገባት አይመከርም። ከትምህርት ወደትምህርት ከሚኾን ልጅ እየተዝናና ሕይወትን የሚገነዘብባቸው ሌሎች አማራጮች መኖር አለባቸው።
አኹንም ይቀራል
✔️ባሕላዊ ውዝዋዜ
✔️ ፈረንሳይኛ
✔️ትያትር
✔️ቼዝ
✔️ኮዲንግ የመሳሰሉ cover ያልተደረጉ ሥልጠናዎች አሉ። እዙኹ ቡልቡላ ውስጥ እነዚኽ ሥልጠናዎች መኖራቸው ወላጆች ስለትራንስፖርት እና ስለልጆቻቸው ደኅንነት ሳይጨነቁ መልካም ጊዜ እንዲያሳልፉላቸው ይረዳል።
መጪዎን ጊዜ ለታዳጊዎች አስጊ ሳይኾን አጓጊ እንዲኾን ድርሻችንን እንወጣ
2 437
የክረምት የስዕል ስልጠና ! 🎨
ስዕል መማር ፈልገው ነገር ግን ያልቻላችሁ ይሔ ዕድል ለእናንተ ነውበአጭር ጊዜ ውስጥ ከመሰረታዊ ስዕል አሳሳል ጀምሮ እስከ ተጨባጭ ስዕሎች አሳሳል ዘዴ የሚማሩበትን ይህን ስልጠና እኛ ጋር በመመዝገብ መማር ይችላሉ። በስልጠናው፡-
-የስዕል ማቴሪያል አጠቃቀም ዘዴ - ስለ ስዕል ተግባራዊ የሆነ ትምህርት - የእርሳስ ፣ የከለር እና የቀለም ስዕል አሳሳል ዘዴዎች -ሃሳብን በስዕል የመግለፅ ችሎታ እና ሌሎችምምዝገባ እስከ ሐምሌ 10 ድረስ 📍 ቦታ: ቦሌ ቡልቡላ፣ ቢጫ ፎቅ 1ኛ ወለል ላይ ለመመዝገብ በአካል ወይም በነዚህ ስልኮች ይደውሉ 📞 ስልክ: 0933548302 📞 ስልክ: 0942746078
2 437
ኦቲዝም
🩺 ኦቲዝም ምንድነው?
ኦቲዝም ማለት የአንጎል ዕድገት ዉስንነት ተብለዉ ከሚታወቁ ህመሞች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡
ኦቲዝም በአንጎል እና በአእምሮ የነርቭ ሥርዓት ዕድገት ዉስንነት የተነሳ በሚፈጠር የጎላ የማህበራዊ ተግባቦት ችግር ከሌሎች ጋር ለመግባባትና አብሮ ለመሆን የመቸገር ህመም ነዉ፡፡
የኦቲዝም ህመም ያለባችዉ ልጆች ከጤናማ ልጆች በተለየ መልኩ ተደጋጋሚ ነገሮችን የማድረግ ልምድ እና በጣም ዉስን የሆኑ ፍላጎቶች አላቸዉ።
🩺 ለኦቲዝም አጋላጭ የሆኑ ሁኔታዎች ምንድናቸው?
1. ዘረመል/ተፈጥሯዊ
🔹በቤተሰብ/ቅርብ ዘመድ የኦቲዝም ህመም ተጠቂ ካለ
🔹ዕድሜ ከገፋ በኃላ ልጅ መዉለድ (አባት ከ40 ዓመት በላይ ፤ እናት ከ35 ዓመት ሲበልጡ)
🔹ልጆችን በጣም አቀራርቦ መዉለድ (ከሁለት አመት በታች በሆነ ልዩነት የተወለዱ ህፃናቶች ይበልጥ ተጋላጭ ይሆናሉ)
🔹የመጀመሪያ ልጅና ወንድ ልጅ ይበልጥ ተጋላጭ ይሆናሉ
2. አካባቢያዊ/አስተዳደጋዊ ምክንያቶች
🔹በእርግዝና ወቅት
➛ እናት የአካላዊም ሆነ የእእምሮ ህመም ተጠቂ ከሆነች
➛ ከመጠን በላይ ዉፍረት
➛ የተለያዩ መድሀኒቶችን መዉሰድ
➛ ለኬሚካሎች ተጋላጭ መሆን
➛ የአልኮል መጠጦችን ደጋግሞ መዉሰድ
🔹በወሊድ ወቅት
➛ መወለድ ካለበት ግዜ ቀድሞ የተወለደ ልጅ
➛ አነስተኛ ክብደት
🔹ህፃናት ከተወለዱ በኃላ
➛ በወሊድ ግዜ የሚከሰቱ ማንኛዉም ጉዳቶች
➛ ደም መፍሰስ
➛ የተራዘመ ምጥ
➛ የማጅራት ገትር ህመም
➛ የሚጥል ህመም
➛ የምግብ እጥረት
🩺 የኦቲዝም ምልክቶች
🔸ከሰዎች ጋር አብሮ መሆን አለመፈለግ/ለብቻ መሆንን መምረጥ
🔸ለሰዎች ምንም አይነት ፈገግታ እና አካላዊ እንቅስቃሴዎችን አለማሳየት
🔸ከሰዉ ይልቅ ለመጫወቻና ለሌሎች ቁሳቁሶች ፍላጎት ማሳየት
🔸ቃል ለማዉጣት እና በንግግር ለመግባባት አለመቻል
🩺 የኦቲዝም ምልክት ደረጃዎች
1. አነስተኛ/ዝቅተኛ ደረጃ
➨ ዕድሜቸዉ እስከሚገፋ / እስከ 6 ዓመት ድረስ ላይታወቅ ይችላል፡፡
2. መካከለኛ ደረጃ
➨ ከ4-6 ዓመት ዉስጥ ሊታወቅ ይችላል፡፡
3. ከፍተኛ ደረጃ
➨ ከ1 ዓመት ጀምሮ ሊታወቅ ይችላል፡፡
🩺 የኦቲዝም የህክምና አማራጮች
የኦቲዝም ህመም ህክምና ዓላማ ማህበራዊ ግንኙነትን/ መስተጋብርን ማሻሻልና የህመሙ ተጠቂዎች ከሰዎች ጋር ግዜ እንዲያሳልፉ ማድረግ ፣ የቃላትና የምልክት ተግባቦትን ማዳበር ፣ ወደ ትምህርት ቤት እንዲቀላቀሉ እና እንዲማሩ ማድረግ ነው።
የኦቲዝም ህመም የህክምና አማራጮች ፦
1. የመድሃኒት ህክምና
➨ የመድሀኒት ህክምና በታማሚው ላይ አስቸጋሪ ባህሪ ሲኖር ፣ የምግብ ፍላጎት ሲቀንስ እና የእንቅልፍ ችግር ሲኖር የሚሰጥ ነው፡፡
2. የስነ-ልቦና ፣ የማህበራዊ እናና የባህሪ ህክምና
➨ ይህ ህክምና ከፍተኛ ለዉጥ የሚገኝበት ሲሆን ትዕግስት እና ከፍተኛ ክትትል የሚጠይቅ ነው፡፡
ያስታውሱ ፦ ሁሉም ወላጅ ልጆቹን ማዳመጥና በተለያዩ ማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
✍️ በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል የጤና ትምህርት እና የስነ-አእምሮ ክፍል የተዘጋጀ ©
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ምንጭ: ኢትዮ ሳይካትሪ
@BBN_imfo
2 437
የክረምት የስዕል ስልጠና ! 🎨
ስዕል መማር ፈልገው ነገር ግን ያልቻላችሁ ይሔ ዕድል ለእናንተ ነውበአጭር ጊዜ ውስጥ ከመሰረታዊ ስዕል አሳሳል ጀምሮ እስከ ተጨባጭ ስዕሎች አሳሳል ዘዴ የሚማሩበትን ይህን ስልጠና እኛ ጋር በመመዝገብ መማር ይችላሉ። በስልጠናው፡-
-የስዕል ማቴሪያል አጠቃቀም ዘዴ - ስለ ስዕል ተግባራዊ የሆነ ትምህርት - የእርሳስ ፣ የከለር እና የቀለም ስዕል አሳሳል ዘዴዎች -ሃሳብን በስዕል የመግለፅ ችሎታ እና ሌሎችምምዝገባ እስከ ሐምሌ 10 ድረስ 📍 ቦታ: ቦሌ ቡልቡላ፣ ቢጫ ፎቅ 1ኛ ወለል ላይ ለመመዝገብ በአካል ወይም በነዚህ ስልኮች ይደውሉ 📞 ስልክ: 0933548302 📞 ስልክ: 0942746078
2 437
ቁልፍ የዱባ ጤና ጥቅሞች
1. ዱባ በቫይታሚን ኤ እና ሲ የበለፀገ ነው። የዓይን ጤና;፣ ከእድሜ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ማኩላር ዲጄኔሬሽን እና የዓይን ሞራ ግርዶሾችን ለመከላከል የሚረዱ ሉቲን እና ዜአክሳንቲን የተባሉ ፀረ-አንቲኦክሲዳንቶችን ይዟል።
በዱባ ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኤ ቆዳን ከመበከል እና ለፀሀይ ከመጋለጥ ለመከላከል ወሳኝ ነው።
2.ዱባ የካሎሪ ይዘት ያለው እና ከፍተኛ ፋይበር ያለው ሲሆን ይህም ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል። ዱባ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚረዳ ጥሩ የፖታስየም ምንጭ ነው።
3. በዱባ ውስጥ ያለው ፋይበር ወደ ደም ውስጥ የሚገባውን የስኳር መጠን እንዲቀንስ ይረዳል፣ ይህም የደም ስኳር መጠን ለመቆጣጠር ጠቃሚ ነው።
4. ዱባ ቫይታሚን ኬ እና ካልሲየም ይዟል። ሁለቱም ጠንካራ አጥንትን ለመጠበቅ ጠቃሚ ናቸው።
5. ለልብ ጤና ጠቃሚ ነው። በዱባ ውስጥ የሚገኙት ፋይበር፣ ፖታሲየም እና ማግኒዚየም የደም ግፊትን እና የኮሌስትሮል መጠንን በመቀነስ ለልብ ጤና አስተዋፅዖ ያደርጋሉ።
6.ዱባ ቤታ ካሮቲንን ጨምሮ ሥር የሰደዱ በሽታዎችን ለመከላከል እና እብጠትን ለመቀነስ የሚረዳ ጥሩ የፀረ-ኦክሲዳንት ምንጭ ነው።
7. ለአንጀት ጤናጥሩ ነው። ዱባ፣ በተለይም ልጣጩ፣ የአንጀት ጤናን የሚያሻሽሉ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይዟል።
@BBN_info
2 437
+1
የዘንድሮ የ12ተኛ ክፍል ተፈታኞች እንዲሁም የ2018 የ11ኛ ክፍል የክረምት ተማሪዎች
ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (June 30, 2026)
ውድ ወላጆች እና አሳዳጊዎች 👇
በጥያቄያችሁ መሠረት የክረምት ትምህርታችሁን በማይነካ መልኩ የከሰዓት ልዩ የስልጠና ፖኬጅ ያዘጋጀን መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው ፡፡
📞 0910215400
በመጪው የክረምት ወቅት ለሁሉም ሰልጣኞች እና ቤተሰቦች የተሻለ የስልጠና አካባቢ ለመፍጠር ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ ነን ።
ለቀጣይ እምነታችሁ እና አጋርነታችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር፣
የተቋሙ አስተዳደር
📞 አሁኑኑ ይደውሉ/ ያግኙን፤ ይመዝገቡ 👇
Bulbula branch representative
• ስልክ፡ 0945562429 (SMS)
0910215400 / call
• የቪዲዮ ለማየት ሊንኩን ይጫኑ👇❤️
https://vt.tiktok.com/ZSCJbEMtp/
2 437
📍አድራሻ፡ ቦሌ ቡልቡላ ከአባሳሙኤል ቤ/ክ 150ሜትር ከፍ ብሎ ከሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ ጐን ያገኙናል።
☎️ +2519-04-77-44-77
Telegram:@DyAKG
dynamicaddis@gmail.com
Уже доступно! Исследование Telegram 2025 — ключевые инсайты года 
