cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

አል መእዋ የበጎ አድራጎት ግሩፕ ( المأوى)

ففروا إلى الله "The best of mankind are those who benefit mankind." Prophet Muhammad -peace be upon Him-

Больше
Рекламные посты
2 890
Подписчики
+624 часа
-27 дней
+1730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

https://surveyheart.com/form/664272b2da06d43cc45b4ec7 ውድ እና የተከበራችሁ የአል―መእዋ አባሎቻችን ለአል―መእዋ በቋሚ አባልነት ያልተመዘገባችሁ👆ከላይ ባለው ሊንክ በመግባት እንድትመዘገቡና ሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሊንኩን Share በማድረግ እንድታስመዘግቡ በአክብሮት እንጠይቃለን🙏 ውዶቼ ሊንኩን Share Share Share በማድረግ የዚህን ኸይር ተካፋይ እንሁን።
Показать все...
አል-መእዋ ኢስላማዊ ድርጅት

👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ከተፈቃሪያችን [ﷺ] ጋር የተሰጠን ትልቁ የአላህ ፀጋ ከርሳቸው ጋር የተፈቀደልን ቅርበት ነው። ሶለዋት እና ሰላምታ ስናቀርብላቸው ይደርሳቸዋል። እርሳቸው ናፍቀናቸው አንብተዋል። እኛ የርሳቸው እጣ እርሳቸውም የኛ እድል እንደሆኑ ነግረውናል። የህይወት ውሏቸው፣ የአካል ገፅታቸው እና የቤተሰብ ግንኙነታቸው ሳይቀር ተሰንዶ ተዘግቦልናል። ከህይወታቸው ገፅታ እኛ ዘንድ ሳይደርስ ተዳፍኖ የቀረ የለም! ስለዚህ ፍቅር ያለው ወዳጃቸው ከእቅፋቸው ሳይወጣ፣ ተዝካራቸው ከህይወት ማእዱ ሳይርቅ ይመላለስበታል። እነሆ ዛሬ ዝክረ ሂጅራቸው ድምቀታችን ይሆን ዘንድ አላህ አድርሶናል! አልሐምዱሊላህ! እናም አደራ የምላችሁ!… ስለ ሂጅራቸው እናውራ ለልጆቻቸን እንንገር። እለቱን ከታሪክ ዐውዱ ጋር አቆራኝተን ደማቅ ወጋችን እናድርገው። የመድረሳ ባለቤቶች፣ የመስጂድ አስተዳዳሪዎች፣ ዳዒዎች፣ የረሱልን ፍቅር በትውልድ ልብ ውስጥ መዝራት የሚሻ ሁሉ ዓመቱን ሁሉ ከህይወታቸው ክስተት እየቀዳ ይጠጣ። ለሌላውም ያጋራ። ከህይወት ቅኝታቸው የሚገኘውን አስተምህሮና ለዛ ይቋደስ! እንኳን ለ1446 ኛው ዓመተ ሂጅራ አደረሳችሁ! የከርሞ ሰው ይበለን!
Показать все...
🥰 6
ማስታወሻ ======= ነቢያዊው ሂጅራ የኢስላማዊው ቀን መቁጠሪያ በሚጀምርበት ወርሀ ሙሐር‐ረም አልተከሰተም! ሂጅራው የሆነው በወርሀ ረቢዕ አል‐አወል ነው። ነገርግን የሂጅራው የቀን አቆጣጠር የዓመት መጀመሪያው የተከበረው የሙሐር‐ረም ወር እንዲሆን ተደርጓል። ይኸውም ሰዎች ከሐጅ ጉዞ ተመልሰው በቀዬኣቸው ተረጋግተው ኑሮ የሚጀምሩት በሙሐረም ስለሆነ ነው። የሂጅራ አቆጣጠርን አሁን ባለበት ሁኔታ እንዲሆን ያደረጉት ኸሊፋው ሰይድ ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] ናቸው። ያው ከሌሎች ከሶሓቦች ጋር ተማክረው ማለት ነው። : ኢማም ኢብኑ ሐጀር "ፈትሕ" በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ ሌላ ምክንያት ይጠቅሳሉ: ‐ «ሂጅራን ከረቢዕ አል‐አወል ወደ ሙሐረም አዘግይተው የቀን መቁጠሪያ ያደረጉት ሂጅራ ለማድረግ ውሳኔ የተወሰነበት ወር ስለሆነ ነው። ምክንያቱም በይዐህ (ቃልኪዳን) የተካሄደው በዙል‐ሒጅ‐ጃ ወር አጋማሽ ነበር። በይዐህ ደግሞ የሂጅራ መቅድም እንደሆነ ይታወቃል። ከቃልኪዳኑ በኋላ የተቀለደው የመጀመሪያው ጨረቃ ደግሞ የሙሐረም ወር ጨረቃ ነው። ስለዚህ ሙሐረም [የኢስላማዊው] ቀን መቁጠሪያ የመጀመሪያ ወር ሆነ። ቀን መቁጠሪያው ከሙሐረም ወር የጀመረበትን ምክንያት ከሚያስረዱ አስተያየቶች ሁሉ ጠንካራ ሆኖ ያገኘሁት ሃሳብ ይህኛው ነው።» አላሁ አዕለም!
Показать все...
👍 6 1🥰 1
«ወላሂ! ከዚያን ቀን በፊት አንድ ሰው ከደስታ ብዛት እንደሚያለቅስ አላውቅም ነበር። አቡበክርን በዚያ ቀን ሲያለቅሱ አየሁ!» እናታችን ሰይዳ ዓኢሻ አባታቸው ሲዲቅ [ረዲየላሁ ዐንሁማ] የተፈቃሪያችን [ﷺ] ሂጅራ ባልደረባ እንዲሆኑ መመረጣቸውን የሰሙ ጊዜ የነበሩበትን ስሜት የገለፁበት መንገድ ነው! በእርግጥም ለዚህ ታላቅ እድል መታጨት ያስለቅሳል!
Показать все...
دعاء آخر السنة مخرج 1.pdf3.76 KB
دعاء أول السنة 2.pdf3.36 KB
የሰይዲና ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] ለቅሶ: ‐ «አንድ ሰውዬ ከሀገረ ሻም ሰይዲና [ረዲየላሁ ዐንሁ] ዑመር ዘንድ መጣ። ሰይዲና ፋሩቅ ጠየቁት «ከሩቅ ሀገር እዚህ ድረስ ለምን መጣህ?» ሰውየውም: ‐ «ተሸሁድ ለመማር ፈልጌ።» አለ። ሰይድ ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] ፂማቸው እስኪረጥብ ድረስ አለቀሱና እንዲህ አሉ: ‐ «ወላሂ! እኔ በበኩሌ አላህ መቼም ይቀጣሃል ብዬ አላስብም!» : ሰውየው ከሻም መዲና ከአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የተጓዘው እዚህ ኢንተርኔት ላይ ልንማረው የናቅነውን [የተጠየፍነውን ላለማለት ነው] ተሸሁድን ብቻ ለመማር ነው። አጎራባች መስጂድ ሄደን በተማሪ እጦት ስራ ፈት የሆኑ ሸይኾቻችንን ዒልም መቅሰም ስለምን ከበደን ግን?በተለይ የእኛ ነገር ግርም ይለኛል🤔
Показать все...
5😢 3
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.