cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

አዲስ🎧music & Cast Of Mind

WEL COME to ADDISEMUSIC7 I'm FahmiSeven 👍new music 👍Trening hit 👍hip hop 👍Reggee 👍dancehall ሙዚቃ የአለምቋንቋ እዚህ ታገኛላችሁ!!!!! እንዲሁም መልካም አስተሳሰብ ለምትሹ አሁንም በዚህ channal ብቻ For any promotion contact With me @FAHMI_SEVEN

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
306
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​👤 • Xidding Dayax X Aman Mussie 🔊 • ምነው 💵 • 1.16 Birr on data packages 💵 • 1.77 Birr on mobile data To Download Mp3 Song 👇👇👇👇👇 #ADDISEMUSIC7 @ADDISEMUSIC7
Показать все...

🎙 • Xidding Dayax X Aman Mussie 🔊 • ምነው #ADDISEMUSIC7 @ADDISEMUSIC7
Показать все...
አመለካከት ! በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብትሆን አመለካከትህን በመቀየር ማሸነፍ ትችላለህ ። እስቲ ራስህን ጠይቅ ችግሩ ከባድ ሆኖ ነው ወይስ አንተ በምን አይን አይተኸው ነው ? አንተ የገባህበት ሁኔታ ውስጥ የገቡ ያሸነፉ አሉ እነሱ እንዴት አለፉ ? አንተም ማለፍ የምትችል መሆንህን ማረጋገጫ ነው ። ምርጡን ቅዳሜ ተመኘን 🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ብዙ ሰው ወዷችሁ አንድ ሰው ጠልቷችሁ ሊሆን ይችላል፣ ብዙ ነገር አግኝታችሁም አንድ ነገር አጥታችሁ ይሆናል፣ ብዙ ነገር ተሳክቶላችሁም አንዱ ከሽፎባችሁ ሊሆንም ይችላል ወይም ብዙ ነገር አስደስቷችሁ አንድ ነገር አሳዝኗችሁ ሊሆን ይችላል። ታዲያ በምን ስሌት ነው አንዱ ከብዙ በልጦ በህይወታችሁ ጭንቀትና ሃሳብ እንዲያመጣ የምትፈቅዱለት?!! ብዙውን የእኛ እንዲሆን ላደረገና ብዙውን ለእኛ የሰጠ እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይድረሰው!! 🙌 🙌 🙌
Показать все...
ዕንቁዎችህን የምትሰጣቸውን ሰዎች ምረጥ!! "..በታክሲ ውስጥ ስትሄድ አንድ ጋጠወጥ ሰው ቢያጋጥምህና የማይሆን ቃል ቢናገርህ ለእርሱ ቦታ አትስጠው። አንዱ ፌርማታ ላይ ይወርዳል፤ ከዚያ በኋላ አታገኘውም። አንተን ግን ቀኑን ሙሉ ሲበጠብጥህ ይውላል። "ቁንጫ የጠረጉት ባለጌም የመከሩት ዕለት ይብሰዋል" እንዲሉ ምክር ለሁሉ አይሰጥም፣ መልስ ለሁሉም አይመለስም ፣ ክርክር ከሁሉም ጋር አይደረግም። ዕንቁዎችህን የምትሰጣቸውን ሰዎች ለይ። እንቁላል የምታስታቅፋቸውን ዶሮዎችም ምረጥ።" #መጋቢ_ሀዲስ_እሸቱ_አለማየሁ😍 #ADDISEMUSIC7 @ADDISEMUSIC7 #share_with_love ❤️ የchannalu ተከታታዮች እየቀነሱ ነው!!!!!!!!
Показать все...
በሩን ዝጋ! "አንዳንድ በሮችን ጥርቅም አርገህ ዝጋ፤ ስለማትችል አይደለም...በንቀትም አይደለም...በኩራትም አይደለም ግን በአጭሩ የምትዘጋቸው የትም ስለማያደርሱህ ብቻ ነው" ይለናል ደራሲ ፖውሎ ኮሊዮ። ከማይጠቅሙን ሰዎች ጋር የምንውል ከሆነ እሱን በር መዝጋት አለብን! ወዴትም የማያደርስ ነገ የሌለው የፍቅር ግንኙነት ውስጥም ካለን በሩን መዝጋት ግድ ነው! ህይወታችንን ወዴትም ለማያደርሱ ነገሮች ቦታ መስጠት ማቆም አለብን። ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @Inspire_Ethiopia✊ የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
Показать все...
#አንተ_ነህ_የገደልከኝ!!! ▶በአንድ ወቅት ባል ጥዋት ተነስቶ ወደ ስራው ሊሄድ እየተሰናዳ ሳለ ሚስት ትመጣና ውዴ ሆይ ምነው ፊትህ ላይ ጥሩ ስሜት አይታየኝም ምን ሆነክብኝ ነው ብላ ትጠይቀዋለች?? ▶ባልም፦ እንጃልኝ ማሬ ዛሬ ለሊቱን ሙሉ ሲያቃዠኝ ፡ እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር ነው ያደርኩት። ድሮ ልጅ እያለው እናቴ በመኪና አደጋ ከመሞቷ አንድ ቀን በፊት ልክ እንደዛሬው ለሊት ሲያደርገኝ ስለነበር አሳስቦኝ ነውና ዛሬም ጥሩ ነገር ስለማይሸተኝ እባክሽ አንችም አንድ ነገር እንዳትሆኚብኝ ከስራ ቀርቼ አብሬሽ ልዋል ይላታል?? ▶ሚስትም፦ ውዴ ሆይ አታስብ አትጨነቅ አንተ አብረሀኝ ዋልክም አልዋልክም ዛሬ ቀኔ ከሆነ ምንም የሚለወጥ ነገር አይኖርም ስለዚህ በቃ ወደስራህ ሂድ ትለዋለች። ▶ባልም፦ እየከበደውም ቢሆን በሚስቱ ሀሳብ ተስማምቶ ወደስራው ሄደ። እኩለ ቀን ላይም ምሳ ለመብላት ወደ ክበብ ሄደ ምሳውንም ለመብላት ሲሰናዳ ክበብ ውስጥ ካለው ቴሌቪዥን ውስጥ አንድ #ሰበር ዜና ጆሮውን ገረፈው!!! ▶ዜናውም እንዲህ ይል ነበር፦ እሱ የሚኖርበት የጋራ መኖሪያ ሰፈር በከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ መመታቱን ያትታል። ▶በዚ ጊዜ ባል በከፍተኛ መሸበር እና መደናገጥ በፍጥነት ወደ ሰፈሩ በሩጫ አቀና። ▶አከባቢው ላይም ሲደርስ መንደሩ በፖሊሶች እና በነብስ አድን ሰራተኞች ተከቦ ያገኘዋል። ወደ ውስጥም ዘልቆ ሊገባ ሲል ባከባቢው የነበሩ ፖሊሶች እንዳይገባ ይከለክሉታል። እባካቹ አሳልፉኝ የልጅነት ፍቅሬ(ሚስቴ) ከውስጥ ነው ያለችው እያለ መማፀን ጀመረ?? ▶ ፖሊሶቹም ፦አፓርታማው በጣም ስለተጎዳና ሙሉ ለሙሉ ሊፈርስ ስለሚችል ለህይወትህ አደጋ ነው ስለዚህ ማለፍ አትችልም ይሉታል። ▶ በዚ ጊዜ ባልም ከፈለጋቹ ተኩሳቹ ግደለኝ ይልና ፖሊሶቹን ጥሶ በከፊል ወደፈራረሰው አፓርታማ ዘልቆ ይገባል ። ▶ከብዙ ፍለጋና ልፋት በኋላም ሚስቱ በፍርስራሽ ተሸፍና ለመሞት እያጣጣረች ያገኛታል። ሊያወጣት ቢሞክርም በላያ ላይ ያለውየብሎኬት እና የሲሚንቶ ፍርስራሽ ብዙ ስለነበር ሊያወጣት አልቻለም። ▶ሚስትም፦ እያቃሰተች የመጨረሻ ቃሏን እንዲህ ስትል ነገረችው፦ ውዴ አንተ የመኖሬ ምክንያት ዛሬ አንተ እውነተኛ አፍቃሪ እንደሆንክ በቃላት ድርደራ ሳይሆን በተጨባጭ በተግባር አሳይተህኛል። ዛሬ አንተ ባትመጣ ኖሮ ሁለት ሞት እሞት ነበር። አንድም በ#አካል_ ሁለትም #በመንፈስ ። ነገር ግን አሁን አንተ ስለኔ ስትል ህይወትህን አደጋ ላይ ጥለህ ስለመጣህልኝ በመንፈስ ከመሞት ተርፌ በአካል ብቻ እሞታለው። ▶ውዴ፦ ጥዋት እንደነገርኩህ የፈጣሪ ትእዛዝ እስከሆነ ድረስ የመጣውን ሁሉ በፀጋ አለመቀበል ፈጣሪን መፈታተን ነው። ስለዚህ የእውነት የምትወደኝ ከሆነ ቀጥሎ የምልህን ነገር እህህህ ብለህ ስማኝ፦ እኔ ቀኔ ስለሆነ ለዘላለሙ ልሄድ ነው። አንተ ግን ሌላ ሚስት አግባ ልጆችም ውለድ። ነገር ግን ይሄን ቃሌን ጥሰህ በኔ ሀዘን ተቆራምተህና እኔን እያሰብክ ቀሪ ህይወትህን የምታበላሽ ከሆነ ዛሬ እኔን የገደለኝ የመሬት መንቀጥቀጡ አደጋ ሳይሆን #አንተ ነህ ብላ የዘላለም እንቅልፍ አሸለበች። * ተ ፡ ፈ ፡ ፀ ፡ መ *** ❤እውነተኛ ፍቅር መስዋእትነትን ይጠይቃል። ❤ጊዜና ሁኔታ(ደስታና መከራ) የማያናውጠው ፍቅር ይስጠን። #ADDISEMUSIC7 @ADDISEMUSIC7
Показать все...
​​ዶክተሯ ከስራ ደክሟት ከጓደኛዋ ጋር ወደ ቤት እየተመለሰች ነው፤ በድንገት ግን መንገድ ላይ እራሱን ስቶ የወደቀን ሰው ሰዎች ከበውት ተመለከተች፡፡ በጣም ደክሟታል፤ ማረፍ ፈልጋለች፤ ነገር ግን ድካሟን ሁሉ ተቋቁማ ይህን ሰው ለመርዳት ወደ ወደቀበት አመራች፡፡ በቦታው ስትደርስ ታማሚው ሙሉ በሙሉ እሩሱን ወደ ማያውቅበት ደረጃ በመድረሱ የግድ ሆስፒታል መሄድ እንዳለበት ተረዳች፡፡ እናም ይዘውት ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ ጓደኛዋን ጠየቀቻት፡፡ ጓደኛዋ ግን "ደክሞኛል፤ አንቺም ደክሞሻል ገብተን እንረፍ፤ ይሄ ሁሉ ሰው ምን ያረጋል? እነሱ ይወስዱታል" አለቻት፡፡ ይቺ ዶክተር ጓደኛዋን "አንቺ ሂጂ በቃ እኔ ከሌላ ሰው ጋር እወስደዋለው" ብላት ወደ ታማሚው ተመለሰች፡፡ ጓደኛዋ ዶክተሯን ጥሎ መሄድ ስለከበዳት እየደበራትም ቢሆን አብራት ታማሚውን ወደ ሆስፒታል ለመውሰድ ተስማማች፡፡ ታማሚውን ሆስፒታል ወስደው ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ ካደረጉ በኀላ በትራንስፖርት ወደ ቤት መመለስ ጀመሩ፡፡ በመሀል ጓደኛዋ "እንደዛ በጣም ደክሞሽ፤ በዛ ላይ የማታውቂውንና መንገድ ላይ ወድቆ ያገኘሽውን ሰው የዕረፍት ሰዓትሽን መሰዋት አርገሽ ለመርዳት ምክንያት የሆነሽ ምንድን ነው?" ስትል ዶክተሯን ጠየቀቻት፡፡ ይቺ ቅን ዶክተርም "እስቲ ተመልከቺ፤ በዚህ አለም እኮ ቢገባን ሁሉም ለሌላው ነው መኖር ያለበት፡፡ ተመልከች ወንዞችን የያዙትን ውሃ እነሱ አይጠቀሙትም፤ ሌላ ነው የሚጠቀመው፡፡ ዛፎች የሚያፈሩትን ፍራፍሬ እነሱ አይበሉትም፤ ሌላ ነው የሚመገበው፡፡ ፀሀይ ያን ደስ የሚል ብርሀንና ሙቀቷን እሷ አትምቀውም፤ ሌላ እንጂ፡፡ እነዚህ ሁሉ ፍጥረቶች እኔ ስለማልጠቀምበት ብለው ያላቸውን ከመስጠት አልተቆጠቡም፡፡ ታዲያ እኛስ ከእነሱ ብንበልጥ እንጂ አናንስ፡፡ ስለዚህ አንዳንዴም የእኛን ትተን ለሌሎች መኖር ይገባናል፡፡ ታማሚው በሰዓቱ የግድ ህመሙን የሚያውቅና የሚረዳው ስው ያስፈልገው ስለነበር ነው እንደዛ ያደረኩት" ስትል መለሰችላት፡፡ ✍ግን እውነት እስቲ እራሳችንን እንታዘበው፡፡ እያንዳንዷን ነገር የምናረገው እኮ ከእራሳችን ጥቅም ጋር እያገናዘብን ነው፡፡ ሀሌም እላችኀለው፤ ዛሬም እደግመዋለው፡፡ እመኑኝ ደግነት መልሶ ይከፍላል፡፡ መልካም እናድርግ፡፡ #መልካም_አመሻሽ 🌙🌙🌙 share with love ❤️ 💚💛❤️🇪🇹 @motiv068
Показать все...
የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል፤ ራስህን ከሰዎች ጋር የምታወዳድር ከሆነ መቼም አትደሰትም፤ ደስ ቢልህ እንኳን ደስታህ ብዙ አይቆይም! ከራሱ ጋር የሚወዳደር ሰውን ግን ማንም አያቆመውም። በራስህ ለውጥ ደስ ይበልህ፤ ዛፎች ሁሉ እኩል አያድጉም ግን ማደግ እስከሚችሉት ከፍ ይላሉ። ወዳጄ አይንህን ከሌሎች ላይ ነቅለህ ወደ ራስህ ባየህ ቁጥር እድገትህ ፈጣን ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ የአይምሮ ሰላም አለህ!
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
አይምሯችን መሬት ነው፤ የተዘራበትን ማብቀል ነው ስራው። መልካም ነገር ከነገርነው፣ መልካም ነገር ካየ የህይወት መንገዳችን ያማረና ደስተኛ እንሆናለን። ለሆዳችን እኮ በጣም ጥንቃቄ እናደርጋለን፤ በፍፁም የቆሸሸ ምግብ አንበላም። ታዲያ የነገ መድረሻችንን ለሚወስነው አይምሯችን ምንድነው የምንመግበው? መጥፎ ዜና ነው ወይስ መንፈሳዊ ሀሳብ? ስለ ሰው አሉባልታ ነው የምናስበው ወይስ ስለ ነገ መድረሻችን? ምርጫው የኛ ነው!
Показать все...