cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

መሳጭ መሳጭ ታሪኮች

ልብ አንጠልጣይ ታሪኮች አስቂና ቁም ነገር መማሪያ

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
252
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

" መቅደላዊት " ክፍል ፳፪ በአምባዬ ጌታነህ በዚህ ሁሉ መሀል ሜላት እያለቀሰች በስስት ትመለከተው ነበር። ልቧ ያለማቋረጥ ይመታል። የሚመታውን ልቧን ለማዳመጥ እጇን በሰደደች ጊዜ እንደ ጦር ይወጋታል። ለሷ ከደማሚት ልቆ የሚሰማትን የልብ ምቷን አጠገቧ ያሉት ሰወች የሚሰሙት መስሏት በሀፍረት ተሸማቀቀች። " ግን እኮ እሱ አይወደኝም ፣ በመጀመሪያ ቀን የራሱ እንዳደረገኝ አልተረዳም። ነፍሴን እንደሚያስጨንቃት አያውቅም። ለእኔ ግድ አይሰጠውም የሱ ግድ እራሱ ና አባቱ ነው።ምን ላደርግ እችላለሁ ? እንዴት ብየ የኔ አደርገዋለሁ እንዴት እንዲወደኝ ማድረግ ይቻለኛል? ሁሌም ቢሆን ይህ ነገር እኔ ላይ እንዳይደርስ እጨነቅ ነበር እሱን ላለማስከፋት ነው የጣርኩት አወ እሱ ልቤን ጠግኖ ሰብሮታል ያለምንም ማመንታት ራሴን ሰጠሁት ።እድለኛ አይደለሁም ። ሁሌም ቢሆን የሚያስበው እሱን ነው ከሱ ውጭ ሌላ ነገርን አያስብም ራስ ወዳድ ነው ። " አለች ሜላት በጉንጮቿ የሚወርዱትን እምባወቿን በግራ ና ቀኝ እጇ እያበሰች። አይኗ ሸልቷል ጉንጮቿ እምባዋን እንዲያብሱ የላከቻቸውን መዳፎች በማህተም ቀርፀዋቸዋል። " በቃኝ ስቃየን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቃህ ልለው ይገባል። ስለእሱ ማሰብ ማቆም አለመቻሌን እነግረዋለሁ። ሊረዳኝ ግድ ይለዋል። እንጅ በስቃይ መሞት አልፈልግም። " አለች እና የተቀመጠችበትን ታጣፊ ወንበር ስትነሳ ታዳሚ እንዳይረብሽ ቀስ አድርጋ ወደ ቦታው መልሳ የእግሮቿን ኮቴ በቀስታ በማራመድ ወደ አዳራሹ መናፈሻ መውጣቱን ትታ በዋናው በር ወጣች። ***** ከናሆም የመድርክ ቆይታ በኋላ ገጣሚ ኤልሳቤህ እና ደረበ በተከታታይ ስራቸውን አቅርበው መድረኩን ለመድረክ መሪው ለቀቁ። መድረክ መሪው ለሁለተኛው ዙር ሶስቱ ገጣሚያን አድናቆቱን ለግሶ የሶስተኛውን ዙር አቅራቢዎች ለታዳሚያን ማስተዋወቅ ጀመረ " ከአቅራቢወቹ የመጀመሪያው በብዙ አወዛጋቢ ድርጊቶቹ የምናውቀው ተወዳጁ ባሩክ እስጢፋኖስ ( ዲዮጋን ) "አለ ከኋላ የተቀመጡት ታዳሚ ወንዶች በአንድ ድምፅ" ዲዮጋን ዲዮጋን ዲዮጋን " አሉ። በጩኸት የማይደናገረው ባሩክ ወደ አትሮኖሱ ተጠጋ ማይኩን በቀስታ ካነሳ በኋላ " ለጥሪያችሁ አመሰግናለሁ። በዛሬው ቆይታየ ስለ ውሸት እናወራለን እውነትን ለተወሰነ ጊዚያት እንረሳለን " አለ እና ወደ ታዳሚው ፊቱን አዞረ። አዳራሹ በሳቅ ተጋባ ሳቁ ሊቆም አልቻለም " አትሳቁ! እስኪ ከመሀላችሁ በህይወት ዘመኑ ዋሽቶ የማያውቅ?" አለ ።አንዱ እጁን አውጥቶ "እኔ ዋሽቼ አላውቅም " የዋሸሁትም ዋሽቼ ለማስታረቅ ነው አለ" እና ቁጭ አለ ።ባሩክ በልጁ መልስ ሳቀ ።" እኔ የጠየኳችሁ ዋሽታችሁ ስለማስታረቃችሁ በኩራት እንድትነግሩኝ ሳይሆን ስለመዋሸታችሁ በራሳችሁ አንደበት እንድታረጋግጡልኝ ነው። ለማንኛውም የጥያቄ መልስ ከጥያቄየ ያገኛችሁት ይመስለኛል። የሰው ልጅ ይዋሻል። የሚዋሸው ግን ተፈጥሯዊ ሁኔታ አስገድዳው ሳይሆን ለቅንጦት ነው። እናም ጥቂቶቻችን ብቻ ሳንሆን ሁላችንም በየ አቅማችን፣ በየ ቁመታችን ልክ እንዋሻለን ግን የሚገርመው ከመዋሸታችን በፊት ስለምንዋሽበት አመክንዮ ሳይሆን ከዋሸን በኋላ ለምን እንደዋሸን ለምናቀርብበት አመክንዮ እንጨነቃለን። ይሄ ደግሞ ከውሸት ጋ ያለንን ቁርኝት ይበልጥ ያቆራኘዋል። .............. ስለ ውሸት ከፅሀፍት አንደበት እና ከመፅሐፍ ገፆች እያጣቀሰ ብዙ አለ ። በመጨረሻም " እኔ እዋሻለሁ የምዋሸው ግን ውሸታም እስኪታጣ ድረስ ነው" በማለት ዥረት ሀሳቡን ደመደመ። ከተጋባዥ የጥበብ አባቶች እስከ አዋቂ ሙህራን በዲዮጋን ሰፊ ገለፃ በመደነቅ ከመቀመጫቸው ተነሱ አጆቻቸውን አገናኙ። ገሚሱ ደግሞ እየሳቀ ያጨበጭባል። ዲዮጋን እንዲቀመጡ በቀኝ እጁ እያመለከተ ወደ ውጭ ወጣ። ***************** መቅደላዊት የአዳራሹ መናፈሻ በር ፊት ለፊት ካለው ደረጃ ላይ ተቀምጣ ታለቅሳለች። ያለ ማቋረጥ እምባዋን ታብሳለች ሜካፗን አበላሽቶባታል። ቀሚሷ አቧራ ስቧል ። መቅደላዊት አመድ ላይ የዋለች ቡሊትን መስላለች ። የተስፋ መቁረጥ ስሜት ይታይባታል ።ማንም ቢመጣ እየተፅናናች አይደለም። ናሆም ለመናፈስ ሲወጣ ማዶ ላይ መቅደላዊትን ሲያያት ግራ ተጋብቶ ቆመ። ሄዶ ሊጠይቃት አልፈለገም ግን ደግሞ ስሜቷ አስጨነቀው። እየሰረቀ ያያታል አልፎ አልፎ እሷም ስታየው እሱም ሲያያት ይገጣጠማሉ። ትቷት ወደ ውስጥ ገባ ።ማልቀሷን ቀጠለች ።ናሆም ውስጥ ሁኖ ወደ ውጭ አጮልቆ ሲያይ አሁንም እያለቀሰች ነው። የሆነ የማያውቀው ስሜት ተሰማው። እሱን የከፋው መሰለው ውስጡ ተረበሻ። ከራሱ ጋ በመሄድ እና ባለመሄድ ተከፈለ። ወደ ኋላ ሲዞር ማንም የለም ሁሉም ውስጥ እየታደሙ ነበር። " ለምን ብየ እሄዳለሁ? ምን አግብቶኝ በጭራሽ አልሄድም ለቅሶዋ ይውጣላት ምን አልባትም አልቀቅሳ ራሱ ላይወጣላት ይችላል።" አለ። ናሆም ማሰላሰል ጀመረ እሷ ጋ አይሂድ እንጅ ስለ እሷ ግን ማሰብ ማቆም አልቻለም።" ለምን ይሆን እንዲህ ስቅስቅ ብላ የምታለቅሰው? ማን ይሆን ያስከፋት ራሱን በተደጋጋሚ መጠየቅ "ጀመረ።" አዎ አንዳች ነገር አለ ይቺ ልጅ የምታለቅስበት 1000 ምክንያቶች ይኖሯታል። የመጀመሪያው ሴት መሆኗ በራሱ የለቅሶዋ ምንጭ ነው ። ሁለተኛው ተንኮላቸው ሳያውቁት ያስከፋየዋል ሶስተኛው እልህ እና ሽንፈት........ እያሉ መጥቀስ ይቻላል። ግን የእሷ ምንም ይሁን ምንም እንዲህ ለረጅም ስአት ያስከፋት ነገር ከባድ መሆን አለበት። " መምህር፣ ተማሪ፣ ሰራተኛ ........በነዚህ አይን ገብታለች ።ምን አልባት አንዱ በሴትነቷ እያስቸገራት ቢሆንስ?" ድንገት ለራሷ ያቀረበው ጥያቄ ነበር። ከእንደገና ኮስተር ብሎ ወደ ራሱ ተመለሰና " የፈለገ ቢሆንስ እኔ ምን አገባኝ? ራሷ ትወጣው እንጅ" አለ። ግን ደግሞ ይሄን ይበል እንጅ ህሊናው እየተረበሸ ነው። " ቆይ በህይወቴ የሴት ጣጣ መቼ ነው የሚያልቅልኝ?" አለ ራሱ ከመቅፅበት ሜላት ትዝ አለችው " ሜላት ልዩ ሴት ናት ሳልናገራት ምን ልላት እንደምችል ታውቃለች። ሲበዛ ለስሜቴ ትጨነቃለች። እንዲከፋኝ አታደርግም እሷ ላይ ሳልጨክን አልቀረሁም ያ አይገባትም አለ እና ስለ ሜላት ማሰብ ጀመረ። ቢሆንም ልሂድ እና ምን እንደተፈጠረ ልጠይቃት " አለ ናሆም ወደ መቅደላዊት ሄደ... ይቀጥላል
Показать все...
" መቅደላዊት " ክፍል ፳፩ በአምባዬ ጌታነህ ሁሉም ታዳሚያን ዝግጅቱ ከመጀመሩ 30' በፊት ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል። ዝግጅቱ እስኪጀመር ደጄው አዳራሽ ያለውን ታዳሚ በሙዚቃ ፣ በግጥም እንዲሁም በአጫጭር ስላቅ ወጎች እየከፈተ ማዝናናቱን ይዟል። አስር ደቂቃ ሲቀረው ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዦች የተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ ተቀመጡ። መድረክ መሪው ማይኩን ጨበጠ " ክቡራትና ክቡራን የተወደዳችሁ የአንጋፋው እና የታሪካዊው አድዋ ዩኒቨርስቲ የስራ አመራሮች ፣ ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች እንኳን በደህና መጣችሁ" ጨብ ጨብ ጨብ ጨብ ጨብ ፣ አዳራሹ አስተጋባ መድረክ መሪው ከጭብጨባው በኋላ ማውራቱን ጀመረ። " እንግዲህ የዛሬው ምሽታችን በተወዳጅ እና በአዳዲስ ገጣሚያን እንዲሁም ተዋንያን የታጀበ ነው። አብራችሁን ስለሆናችሁ ክብረት ይስጥልን ብያለሁ። ይህ ዝግጅት በአምስት ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል ተወዳጇ ገጣሚ እንቁጳፂዮን " መውደዴ " ስትለን እሷን እንዳዳመጥን ደግሞ ሌላኛው ተወዳጅ ገጣሚ እዮሳፍጥ " ህይወት ማለት " ይለናል ሶስተኛዋ አቅራቢ ገጣሚ ልዕልት አለማየሁ" ከሸኘሁህ ወዲያ " ከዛ በዚህ ዙር የመጨረሻ አቅራቢ የሚሆነው ተዋናይ ዮሐናን ሞገስ ይሆናል የእነሱን ስራ ተመልክተን ከእኔ ጋር በድጋሚ እንገናኛለን መልካም ቆይታ ገጣሚ እንቁጳፂዮን ወደ መድረክ " አለ እና መድረክ መሪው ቦታውን ለቀቀ። ገጣሚ እንቁጳፂዮን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ግሩም በሆነ አቀራረብ ስራዋን አቀረበች።ሁሉም ታዳሚ ጭብጨባውን ቸራት ።ገጣሚ እዮሳፍጥ ፣ ገጣሚ ልዕልት ፣ ከዛ ተዋናይ ዮሐናን ሁሉም ስራቸውን በየተራ አቀረቡ። የመጀመሪያ ክፍል ተጠናቀቀ ። " እስኪ ለነዚህ የጥበብ ልጆች ጭብጨባ እንለግሳቸው። ሞራል አያንስም ? "አለ እና መድረክ መሪው የሁለተኛው ዙርን አቅራቢወች አስተዋወቀ። የመጀመሪያው አቅራቢ ገጣሚ ናሆም ነው ከሱ ቀጥሎ ገጣሚ ኤልሳቤህ ፣ ከዛ የመጨረሻ ወግ በደረበ መብራቱ ይቀርብልናል አሁንም መልካም ጊዜ በእኔ በኩል ገጣሚ ናሆም ወደ መድረክ " ብሎ ወረደ ።ገጣሚ ናሆም የማይኩን እጄታ ከተቀመጠበት ብድግ አርጎ " የግጥሜ ርዕስ " እምነት ወይስ እውነት " ይሰኛል አለና "ግጥሙን ረጋ ብሎ ማንበብ ጀመረ እምነት ወይስ እውነት? እኔ በዘመኔ፣ በዚች ቁንጥር እድሜ አባን ሲከፋው ነው የሚጨልም ህልሜ የሚሰበር ቅስሜ። አባቴ የዛሬየ ብሩህ ተስፋ፣ በእናት በኩል ለጎደልኩት የሆነልኝ ድርብ ካሳ። የፊቱ ወዝ ምጥጥ ብሎ፣ እኔ ስቀበጥ ተጎሳቁሎ፣ እጄን ይዞ አቦጊዳን ፊደል ሀሁን ያስቆጠረኝ፣ ለዚህ ስኬት ያደረሰኝ፣ አባባ ነው አባቴ ነው፣ ለእኔ ሻማ የቀለጠው። አባቴ ነው እውነት ሳጣ ያገኘሁት ትልቅ እምነት። ስለዚህ፦ እንዲህ ሚያደርግ አባት አያለ፣ ሰምና ወርቅ ቃላት ቢያጡ፣ እንዴት ወልዶ ጣይ እናቶች ለሙገሳ ከቤት ይውጡ። ፡ እናት እናት አትበሉኝ፣ ለማስመሰል አትደልሉኝ እናት እውነት አባት እምነት አትበሉኝ ለማስመሰል አትደልሉኝ። በደከመ ጉልበት አቅሙ ተራራውን እየናደ፣ ስንቱ ይሆን አርበኛ አባት ሚስቱ ጥላው እናት ሆኖ ልጁን ባክኖ ያሳደገ። ስንቱ የዋህ ባል በሚስቱ ወንድነቱ ጠወለገ። እናት እናት አትበሉኝ፣ ለማስመሰል አትደልሉኝ፣ አባየ ነው የኔ ድክመት፣ እድሜ ልኬን የማረሳው ቃልኪዳኑ ሆኖኝ እምነት፣ ከማንም ውጪ በእኔ ህይወት እሱ ብቻ የኔ ፊደል እሱ ብቻ የኔ እውነት! አባት ማለት ምስጢረኛ፣ ለጠላትህ ግልፍተኛ፣ እናት ላጣው እናት ሆኖ፣ እህት ላጣው እህት ሆኖ፣ ወንድም ላጣው ቀኝ እጅ ሆኖ፣ በእድሜው ሳይሆን በእድሜህ ሆኖ፣ የሚባዝን ለልጁ ሀሴት ዳገት ሜዳ ሁሉን ማክኖ! እምንት ሳይሆን አባት፣ ነው ለቃሉ ታማኝ... ኪዳን ያሰረ እውነት። ናሆም ርጋታን በተላበሰ ሁኔታ መሀል ላይ አረፍ እያለ እያንዳንዷን ስንኝ ዜማ እየሰጠ ካቀረበ በኋላ " አመሰግናለሁ" ብሎ ግጥሙን ቋጨ። የተለመደው ጭብጨባ ለናሆምም ተቸረው። ናሆም ከወገቡ ጎንበስ በማለት የጭብጨባውን አፀፋ ሰጥቶ ወደ ቦታው ሄደ። ሁሉም በሰመመን ውስጥ ነበር ሲያዳምጡት የነበረው በድንገት የጨረሰ መሰላቸው። የቃላቶቹ አደራደሩ ታዳሚን ሳይሰላች እስከ መጨረሻው ይዟል። አንዳንድ ታዳሚያን ሴቶች በፍርሀት ያዩት ነበር አንዳንዶቹ ደግሞ በፍቅር ሌላወቹ ደግሞ በአድናቆት፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በናሆም ግጥብ ጭብጥ ግራ የተጋቡ ይመስላሉ ።እርስ በርሳቸው ይተያያሉ ።በዚህ ሁሉ መሀል ሜላት እያለቀሰች በስስት፣ ትመለከተው ነበር። ይቀጥላል ..
Показать все...
" መቅደላዊት " ክፍል ፳ በአምባዬ ጌታነህ የአድዋ መንገድ ዳሮች በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ወረቀቶች ተንቆጥቁጠው አሸብርቀዋል። የምሽቱ የስነፅሁፍ ዝግጅት ባመረ ማስታወቂያ እየተካሄደ ነው። " ታላቅ የጥበብ ድግስ! በአድዋ ዩኒቨርስቲ ሁለገብ አዳራሽ ! ታዋቂ እና ጀማሪ ገጣሚያን የሚሳተፉበት ድንቅ ምሽት ሳያወጡ የሚያተርፉበት ውብ ማታ በእለቱ ፣ ወጎች ፣ መነባንብ ፣ ዲስኩር፣ ሙዚቃዊ ተውነት፣ እንዲሁም ስላቅ እና ሌሎቹም የመድረኩ ክዋኔወች የተካተቱበት በአይነቱ ለየት ያለ ምሽት ነው ።እንዳይቀሩ ተጋብዘዋል" ማስታወቂያው በየ አምስት ደቂቃ ልዩነት ይቀርባል። ሁሉም ሰው ጆሮወቹ እና ቀልቡ ማታ በሚዘጋጀው የስነፅሁፍ ምሽት ነው። እንደገና ማስታወቂያው በመሀል ይመለስና " ተወዳጁ ፈላስፋ ባሩክ እስጢፋኖስ ( ዲዮጋን ) በእለቱ ድንቅ ስራውን ያቀርባል በዲስኩሩ በኩል ዶክተር ኸንድማገኝ አስረስ እንዲሁም በተስፋ ጎህ የቲያትር ቡድን የሚቀርበው ሙዚቃዊ ተውኔት ሌላኛው የምሽቱ ድምቀት ናቸው። ብቻ እናንተ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ ወደ አድዋ ዩኒቨርስቲ ሁለ ገብ አዳራሽ ጎራ ይበሉ እንጅ ዘና ፈታ ብለው ይመለሳሉ ። ጋብዘው የማያፍሩበት እለት ነው ።ምሽት 1:00 " አለ ። " ሲያስጠላ ያነ ባሩክ ልጅ አለ " አለች ፀጉሯን ያንጨባረረች ሴት ያልታሰረ ፀጉሯን በእጇ እያፍተለተለች ጥቅርሻ የመሰለውን አፏን ከሩቅ ላየ የሲጋራ እና የጋንጃ መተርኮሻ ትመስላለች " ኧረ ባክሽ እሱ ከሌለማ ምሽቱ አያምርም አትሰሚውም ማስታወቂያው ራሱ እሱ እንዳለ ነው የሚደጋግመው ምክንያቱም ባሩክ በሁሉም ተማሪ ልብ በመጥፎም በጥሩም መልክ ተቀምጧል ።ለዚህም እሱን ብሎ የሚገባውን ሰው ስለሚያቁ ነው እንዲህ አሁንም አሁንም ዲዮጋን አለ የሚለው። የአንቺን መጥላት ሳይሆን ማየት ያለብሽ የአብዛኛውን ሰው ፍላጎት ነው ።ጠብቂ ስንት ተማሪ እንደሚሄድ ማንም አይቀርም ቦታ ሁሉ ይጠባል " አለች የጨበሬዋን ሀሳብ በመቃረን ጨበሬዋ ከተቀመጠችበት አግዳሚ ወንበር ማዶ ካለው የአንድ ሰው መቀመጫ ላይ የተቀመጠችው ባለ ጎራዳ አፍንጫዋ ሴት ።አፍንጫ የሰራላት አይመስልም እግዜር አፍንጫዋ ላይ ምን እኔደነዳበት ባይታወቅም "ከቅላቷ ቀንሷ ምን አለ ትንሽ አፍንጫ ቢጨምርላት " እየየተባለች የምትታማዋ መካከለኛዋ ሴት ። ***** መቅደላዊት ረጅም የሐበሻ ቀሚሷን ለብሳ ሁለት ስአት ከፈጀው የመካፕ ቆይታዋ በኋላ አግድሙን ወደ አድዋ ሁለገብ አዳራሽ የሚወስደውን መንገድ በመያዝ እየሄደች ነው። በአካሄዷ ፣ በአለባበሷ ፣ እና በውበቷ ውህደት የተደመሙ ወንዶች የመንገዱን ጠርዝ ይዘው ይመለከቷታል። መቅደላዊት መላልክ መስላለች ። *** ናሆም የሚያነበውን በአዳም ረታ የተፃፈውን "የስንብት ቀለማት" የተሰኘውን መፅሐፍ ከድኖ ተነሳና የሎከሩን ቁልፍ ከፈተ። ሎከሩ ባልታጠፉ እና ባልታጠቡ ልብሶቹ ተዝረክርኮ ተሞልቷል። የትኛውን መልበስ ግራ ገብቶት ቆመ። ሁሉንም ልብሶቹን አንድ በአንድ አወጣቸው እና አልጋው ላይ አስቀመጣቸው። ሁሉንም አንድ በአንድ ካነሳቸው እና ከለያያቸው በኋላ አስረኛ ክፍል እያለ አባቱ ወደ ላሊበላ ሄዶ የበረከት ስጦታ የገዛለትን ከኋላው እና ከፊቱ የአፍሮ አይገባ መስቀል የተገለፈበትን ሸሚዝ አገኘው ።ብድግ አድርጎ ወደ አፍንጫው አስጠጋው ምንም የመጥፎ ሽታ የለውም።እንደውም የአባቱን ጠረን ያሸተተው መሰለው።" አባ የእኔ እናት የእኔ ሁሉ ነገር ምን አለ አሁን ብትኖርልኝ? ግን ምን አድርጌህ ነው ትተከኝ የሄድከው" አለና የሱን አላባሽ ሱሪ እና ጫማ አውጥቶ አልጋው ላይ ያሉትን ልብሶቹን ከእንደገና በስርዓት እያጠፈ ያልታጠቡ ልብሶቹን ከሚያስቀምጥበት ሻንጣ ላይ ካስገባ በኋላ አልጋው ላይ ተቀምጦ ልብሱን በትክክል ለበሰ እና የሁለቱም ክንዶች ብብት እና አንገቱ አካባቢ ላይ ዶዶራንቱን በመጠኑ ከረጨ በኋላ ዶርሙን ቆልፎ ብሎኩን ሲወርድ። በሀሉም አቅጣጫዎች የሚኒሚዲያ ክበብ ስፒከሮች ስለ ምሽቱ የጥበብ ሻማ ክብሪት የሆኑ ሀሳቦቻቸውን እየለኮሱ ይሰማሉ። * ናታኔም በተለምዶ አምበሳ ጊቢ እየተባለ ከሚጠራው የዩኒቨርስቲው ፓርክ ውስጥ ሆኖ እያነበበ ቢሆንም ነገር ግን የሚኒሚዲያ ስፒከሮች የረቡሹት ይመስላሉ። ትንሽ ካነበበ በኋላ ተነስቶ ወደ ወደ ወይዘሮ ስህን የሴቶች ብሎክ የሚወስደውን መንገድ በግራ በመተው ዋናውን አውራ መንገድ በመያዝ ወደ ስነፅሁፍ መግቢያ አዳራሹ ሄደ። ነገር ግን አዳራሹ ውስጥ ዝግጅት ለማቅረብ ከሚለማመዱ የትያትር ቡድን አባላት ውጪ የተገኘ ሰው አልነበረም።አዳራሹን እየተዟዟረ ከተመለከተ በኋላ ከፊት ወንበር ሶስተኛ ረድፍ ላይ ተቀመጠ። በሶስቱም የአዳራሹ ረድፍ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ከለርን የያዙ ወረቀቶች በውስጣቸው በተለኮሰ ሻማ አሸብርቋል በአራቱም ኮሪደሮች አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራ ተሰቅሏል። ናታኔም ስልኩን አውጥቶ የአዳራሹን ትዕይንት በስልኩ ለማስቀረት እየተዟዟረ አንስቶ ከጨረሰ ኋላ ርግረ መንገዱን ለመቅደላዊት ደወለ ።ነገር እሷ ስልክ እያነሳች አልነበረም። በመጨረሻም ስልኩን ዘግቶ ወደ ኪሱ ከቶ እጁን ከኪሱ አስገብቶ ቁጭ አለ። ይቀጥላል ....
Показать все...
" መቅደላዊት " ክፍል ፲፱ በአምባዬ ጌታነህ ምን ያልገባሽ ነገር አለ ? ከጣፍኩልሽ ውስጥ? " ዝምታውን ለመስበር እና የውይይት መጀመሪያ እንዲሆን አስቦ ባሩክ የጠየቀው ጥያቄ ነበር። " ሀሳብህ በጣም ከባድ ነው እኔ ያን ማድረግ አልችልም እዚህ እኔን የሚያውቁኝ ብዙ ናቸው ። ቤተሰቦቸንም የሚያውቋቸው ተማሪዎች አሉ። አንተ ያልከውን ባደርግ እና ብል ያለ ጥርጥር ቤተሰቦቼ ጋር እቀያየማለሁ በስስት የሚያየኝን እና የሚወደኝን አባቴን እስከመጨረሻው አጣዋለሁ። እናም በጭራሽ አልችልም። ወይ ለዚህ ሀሳብህ ሌላ ሴት መፈለግ ሳይኖርብህ አይቀርም ።" አለች " የሀሳቡ አመንጪ እኮ እኔ አይደለሁም ይሄን የስነልቦና ህክምና የጀመራችሁት አንቺ እና ናታኔም ናችሁ። እኔን በተወሰነ መልኩ እንድረዳችሁ ጠይቆኝ ነው። እናም በዚህ ምክንያት የዚህ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጇ አንቺ ስለሆንሽ ነው ይሄን ሀሳብ የሰጠሁሽ እንጂ አንቺ እምቢ ብለሽ ለሌላ ልሰጠው የምችለው የፊልም ስክሪፕት አይደለም። " አለ ባሩክ " አይ እኔ እኮ እምቢ ያልኩት ሀሳብህ ከባድ ስለሆነ ነው ። " አለች " ምን መሰለሽ መቅደላዊት ለከባድ ገጠመኞች ለከባድ ችግሮች ከባድ ውሳኔ ያስፈልጋል። ለዚህም አሁን ከባዱን ነገር ታደርጊያለሽ።እመኚኝ ስኬታማ ትሆኛለሽ። አውቃለሁ ብዙ ነገር ሊደርስብሽ ይችላል ግን ለዛም መፍትሔ እናስቀምጣለን።" አለ ባሩክ እጆቿን እየጨበጠ " እንደ እውነቱ ከሆነ ጥሩ ልብ አለሽ ከቅንነት ጋ ከውብ ቁንጅና ጋ ይሄን ባለኝ መረጃ እና በደቂቃዎች ለመረዳት ችያለሁ ።ሰወች ደግሞ ትክክለኛ ነገር አስበው ከሄዱ ከሚጓዙበት የእውነት መንገድ ማንም ሊመልሳቸው ሊያሰናክላቸው አይችልም ይህ የተፈጥሮ እውነት ነው።መጨረሻው መጨረሻ መሆን እንዳለበት ይሆናል። ናሆም ላይ ለእንዲህ አይነት የስነልቦና ችግር በመጋለጡ እኔ በጣም ነው ያዘንኩት ማንም ሰው እንዲህ አይነት ችግር እንዲደርስበት የሚፈልግ የለም እስከማቀው ድረስ አትጠራጠሪ እሱ ላይ የደረሰበት ችግር እኔ ላይ አለያም አንቺ ላይ ቢደርስ የምናደርገው እሱ ከሚያደርገው ቢበልጥ እንጅ አያንስም ። እሱስ ባይሆን ከላይም ቢሆን እናቱን ያወራታል እሷ ጋ ይኖራል ከዚህ በላይ እኮ ምህረት የለም። ግን ደግሞ እናቱ ነች ስለዚህ ለጥላቻው ገደብ ልናበጅበት ይገባል ይቅር ማለትን ልናስተምረው ይገባል። አለዚያ ከባድ ነው"አለ ባሩክ። " ካልክ እሽ ግን ውስጤን ልክ አይደለም እየተሰማኝ ያለው።" አለች መቅደላዊት " አሁን ለስነፅሁፍ ምሽቱ ተዘጋጅ እኔም ወግ ነገር ስለማወጋ መለማመድ አለብኝ በይ ተነሽ ልሸኝሽ አለ እና ቀድሞ ብድግ አለ ። **** ናሆም አቢሲኒያ ስታዲየም በክቡር አቶ ይድነቃቸው መቀመጫ በኩል ጫፍ ላይ ከአንዲት ግራር ዛፍ ስር ሆኖ በየደቂቃው ይጥፋል ፣ይቀደዳል ፣ ይጥላል። ቀዶ በጣላቸው ወረቀቶቹ ተከቦ ራሱን ይዞ ቁጭ ብሏል። ከእንደገና ራሱን ለቀቅ አድርጎ ዙሪያውን ሲመለከት ከአንዲት ቁራጭ ወረቀት ላይ ያፈጣል። ወረቀቱ ላይ የተጀመሩ ቃላቶች አሉ። "የዘራውን ሲያጭድ ይኖራል አለሜ፣ እማ ነች ቅኝቴ እናቴ ናት ህልሜ" ስንኟን ደጋግሞ አነበባት ማን ይሆን ማን ትሆን ይሄን ስንኝ የሰደረችው የሰደረው? ስንኟ የተፃፈችባትን ወረቀት ኪሱ ውስጥ አስገባት። ይሄን የፃፈው ሰው በምን አይነት ጥልቅ የእናት ፍቅር ውስጥ ይሆን? ምን አለ እኔም እናቴ እንዲህ እንዳደርግ ብትፈቅድልኝ ለምን አባየን ለምን እኔን ትታኝ ሄደች? ምን አድርጊያት ነው ገና በልጅነቴ የጨከነችብኝ? " ብሎ ራሱን ይጠይቃል። ትዝ አለው አንድ ቀን ትምህርት ቤት የተቋጠረላቸውን ምሳ ተሰብስበው ሲበሉ ሁሉም ጓደኞቹ እናታቸው እንደሰራችላቸው እየተናገሩ ናሆም ግን አባቴ ነው የሰራልኝ ሲላቸው በጣም ተገረሙ ።ነገር ግን ናሆም ከትምህርት ቤት ሲመለስ አባቱን ጠየቀ እናቴ ለምንድነው ትታን የሄደችው? ብሎ ሲጠይቀው ልጄ እኔን ትታ ለመሄድ ምክንያት ሊኖራት ይችላል አንተን ትታ ለመሄዷ ግን ምክንያት ያላት አይመስለኝም ቢሆንም ምክንያት ካላት ደግሞ አንተ ትልቅ ልጅ ስትሆን እናትህ ጋ ሄደህ እማ ምን አድርጌሽ ነው? ትተሽኝ የሄድሽው?"ብለህ ትጠይቃታለህ " አሁን ግን ጥያቄወችህን በሙሉ ተዋቸው እኔ ለአንተ ሁሉ ነገሬን እሰጣለሁ የእኔ ትልቁ ህልም የአንተ ትልቅ መሆን ነው። ስለዚህ በትምህርትህ በርትተህ ወደፊት እኔን እንድታኮራኝ ነው የምፈልገው ።እሽ የኔ ልጅ ደግሞ እኮራብሀለሁ " አለና እያገላበጠ ሳመው። ናሆም ከትዝታ ማዕበል ወጥቶ ጉንጩን ተደገፈ ።ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ " አባቱ እንደነገረው እናቱ ለምን ጥላው እንደሄደች አልጠየቃትም ። ግን ደግሞ መጠየቅ የምችለው አሁን አይደለም ብሎ ያስባል። ይህን እያሰበ እያለ ሀሳብ መጣለት እና ወረቀቱን አውጥቶ መፃፍ ጀመረ። ለስአታት ቀና ሳይል ከፃፈ በኋላ ። ጨርሶ በደስታ ፈገግ አለ ደግሞ ደጋግሞ አነበበው። " "ሸጋ ግጥም" አለ በለሆሳስ! ይቀጥላል .....
Показать все...
" መቅደላዊት " ክፍል ፲፰ በአምባዬ ጌታነህ ማን ነው ስራህን ያቀለለልህ? ምን አይነት ስራ ነበር የነበረህ? " ናሆም ጥያቄወቹን አከታተለበት ። " አሳይመንት ነበረኝ እሱን ሰርቶልኝ ነው " አለ ናታኔም በድንጋጤ " ታዲያ ምነው ደነገጥክ? " " በድንገት ስለገባህብኝ ነዋ " " እንደዛ ከሆነ ጥሩ ግን..... ምን አሳይመንት ነበር? እንዴት ስታወራ አልሰማህም?" አለ ናሆም " አየ ወንድሜ ለዚህ እኮ ነው እኔ እና አንተ ተጠፋፍተናል የምልህ ።ግን የስነፅሁፍ ዝግጅት አለብኝ ምናምን ብለኸኝ ነበር እኮ እንዴት ታዲያ ተመለስክ?" " ባክህ ያቺ መቅደላዊትን ከሩቅ አይቻት የሁሉም ነገር ፍላጎቴ ጠፋ " " ቆይ ግን ይቺ ልጅ ምን አድርጋህ ነው እንዲህ ጠምደህ የያዝካት?" ምን እኔ ጠምጀ እይዛታለሁ እሷ ነች እንጅ " እኮ እሷ ምን አድርጋህ ነው?" " ከንፈሩን ነከሰ ባውቅማ ኖሮ ጥሩ ነበር የማደርገውን አውቅ ነበር። ነገር ግን ልጅቱ አስመሳይ ነች በጭራሽ የሆነ ነገር እየሰራች ነው እስካሁን አላወኩም ግን ግዴለም እደርስበታለሁ።" አለ ናሆም " * መቅደላዊት ፖስታውን እያየች ይሄ ደግሞ ምን ለማድረግ አስቦ ነው? " ራሱን እንዴት ነው የሚያየው? ሲያስጠላ " አለች እየተመናጨቀች ፖስታውን በዝግታ አንስታ ከከፈተች በኋላ በጥሞና አምብባ ከጨረሰች በኋላ ፊቷ ሁሉ ተለዋወጠ። ስልኳን አንስታ ደወለች " አቤት መቅደላዊት " ከወዲኛው የስልክ ድምፅ የተሰማው የናታኔም ድምፅ ነበር። " ቆይ ጓደኛህ ምን አይነት ጅል ነው ያመዋል ልበል? ሰውን ሳያውቅ " አለች መቅደላዊት " ቆይ መቅዲ ተረጋጊና ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ " አለ ናታኔም ።መቅደላዊት አንድም ሳታስቀር ሁሉም በስልክ ነገረችው እና በመጨረሻ" አሁን ላገኘው እፈልጋለሁ ስልኩን ስጠኝ " አለች " እሽ 0910..........ባሩክ እስጢፋኖስ ከፈለግሽ ዲዮጋንም ማለት ትችያለሽ ።ነፃ ሁኝ ግን መቅዲ አደራሽን ባሩክ ላይ ብስጭት መቆጣት መጮህ አይሰራም ።በእርጋታ የአንቺን ሀሳብ ትነግሪዋለሽ ።ለምን የእሱን ሀሳብ በአንቺ ሀሳብ ላይ እንደመዘንሽ ይገባዋል።ወይም ለምን እንደዛ እንዳለሽ ያብራራልሻል። ይህ ካልሆነ ግን በእውነት ትቶሽ ይሄዳል ።" አለ ናታኔም በልመናም በማስጠንቀቂያም አዘል ንግግር በተወሰነም መልኩ ስለ ባሩክ ግብአት " እና መሄድ ይችላል ለእኔ ብሎ አይቀመጥ " አለች መቅደላዊት " መቅዲ ምን ሆነሻል? ናታኔም በስልክ አምባረቀ " በዚህ ጉዳይ ላይ እኮ አንቺ ነሽ ትልቁን ስራ እየሰራሽ ያለሽው ለምንድነው የምትቀልጅው?" ናታኔም እየተቆጣ ተናገራት። " እሽ ናቲ በቃ አትቆጣ እንዳልከኝ አደርጋለሁ " አለች " ጥሩ አመሰግናለሁ ስትጨርሽ ደውይልኝ " እሽ እደውልልሀለሁ ። ************* ባሩክ " አክሱም የተማሪወች መናፈሻ " መጨረሻ ፎቅ ላይ ሆኖ " መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ" የተሰኘውን የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ን መፅሀፍ ማንበቡን ገታ አድርጎ ያዘዛትን ወተት አንስቶ ፉት ሲል ስልኩ ጠራ። ያነሳትን ወተት አንድ ጊዜ ስቦ ወደ ነበረችበት ጠረምጴዛ መለሳትና ስልኩን ከኪሱ አወጣ ። አዲስ ቁጥር ነው ላለማንሳት ካመነታ በኋላ አንስቶ "ሀሎ" አለ ። " ሰላም ነው ባሩክ? አወከኝ?" " አላወኩሽም ወይዘሪት " አለ። " መቅደላዊት ነኝ " አለች " እሽ መቅደላዊት በጣም ነው የሚገርመው አሁን ስለ አንቺ እያሰብኩ ነበር።" " እንዴ ስለምንድን ነው ስለ እኔ እምታስበው?" የዋህነትሽን ፣ ቁጡነትሽን ፣..... ሌላም ሌላም እሱን አለማሰብ አይቻልም በዛ ላይ ........" ብሎ ዝም አለ ።" እህ በዛ ላይ .........ጨርሰው እንጅ " አለች ግን ለምንድነው ሴቶች ተጀምሮ ላልተጨረሰ ሀሳብ የምትሞቱት? ውይ ሁሉንም ማወቅ የሚፈልጉ ፍጥረቶች ቢኖሩ ሴቶች ናቸው ሊፈነዱ እኮ ነው የሚደርሱት። ምን እንደሚሻላቸው አሁን ይሄን ሳልጨርስላት ብቀር ሌቱንም ቀኑንም ስለዚህ ጀምር ሀሳብ ነው ቁማ የምታድረው ጉድ እኮ ነው። " አለ በውስጡ " እየጠበኩህ እኮ ነው "አለች ።መቅደላዊት እንዳልተፋታችው ሲረዳ " በዛ ላይ ቆንጆ ነሽ ለማለት ፈልጌ ነው።" አላት በተቻለው መጠን ግንኙነታቸውን ጤናማ አድርጎ ለመሞከር አስቧል። " ኧረ ባክህ ቆንጆ ነኝ እንዴ? አላወኩም ነበር።" አለች መቅደላዊት ምፀታዊ ንግግር ነበር። ባሩክ ገብቶታል ግን እንዳልገባው ለመምሰል " አባቴ ይሙት እውነቴን ነው " አለ ባሩክ እየሳቀ ። መቅደላዊት በሱ በኩል ያላትን የተቃረነ አመለካከት የማስተካከል አይደለም ዋና እቅዱ ናሆም ነው መቅደላዊት ጋር ያለው ጓደኝነት ጤናማ እና አሪፍ ከሆነ ናሆምን ካለበት የስነልቦና ችግር ማውጣት ይቻላል ብሎ ስላመነ ነው።እንዲህ ውድ ጊዜውን የሚያባክነው። ባሩክ ህይወቱ ማንበብ ብቻ ነው።መቅደላዊት ትንሽ ፈገግ ካለች በኋላ " ፈልጌህ ነበር " አለች " ለምንድነው ነው ልታገኚኝ የፈለግሽው?" አለ ባሩክ በደብዳቤው የተነሳ እንደሆነ ገምቷል።" እሱን ስንገናኝ እነግርሃለሁ " " ጥሩ መምጣት ከቻልሽ አክሱም ነኝ ጣራው ላይ " እሽ በቃ መጣሁ " ብላ ስልኩን ዘጋችው። * * መቅደላዊት አክሱም መናፈሻ ጣራው ላይ ስትወጣ ሽቅብ የሚነፍሰው ነፋስ አንዳች ነገር የፈለገ ይመስል ቀሚሷን ለመግለብ ይጥራል ። ቅንዝራም የሆነ ነፋስ እሷ ዝቅ ስታደርግ እሱ ደግሞ ከእንደገና ይገልበዋል በስተመጨረሻ እጇን ከቀሚሷ ላይ ሳታነሳ በሁሉም አቅጣጫ ስታማትር ባሩክ በመናፈሻው ደቡብ አቅጣጫ ጥግ ላይ ሆኖ በጥሞና ሲያነብ ተመለከተችው። ለተወሰነ ደቂቃ ቆማ ብትመለከተው እሱ ግን ከሚያነበው መፅሀፍ ውጭ ሌላ የትኛውንም አቅጣጫ ለማየት የፈለገ አይመስልም ። " ባይፈላሰፍ ቆንጆ ወንድ ነበር " አለችና ባሩክ ወደተቀመጠበት ቦታ ሄደች ባሩክ ወደ እሱ የቀረበ የእግር ኮቴ እንደሰማ ቀና ሲል መቅደላዊት ደርሳለች። ሰለም ብያለሁ እንዴት ነሽ ? እጁን ለሰላምታ ዘረጋ ጨበጠችው ጨበጣት እና ፈጠን ብሎ የምትቀመጥበትን ወንበር ስቦ አስቀመጣት። መቅደላዊት በአድራጎቱ የተገረመች ትመስላለች ። የአክሱም ሀውልት ምስል ያለበትን ቲሸርት የለበሰ አስተናጋጅ መጣ እና የተለመደውን ጥያቄ ጠየቀ የመቅደላዊትን የስፕራይት ትዕዛዝ ተቀብሎ አስተናጋጁ ሄደ። " ፈጥነሽ ገው የመጣሽው " አለ " የእውነት? እኔ ደግሞ የቆየሁ መስሎኝ ነበር " አይ በጭራሽ ጥሩ ስአት ላይ ነው ቢያንስ ከዘገየሽ ራሱ የዘገየሽው ካለሽበት እስከዚህ ድረስ ለመድረስ የፈጀብሽ መንገድ ነው " አለና ምቾት እንዲሰማት አደረገ። አስተናጋጁ አንድ የውሀ ብርጭቆ ከአንድ ሎሚ ጋር የታዘዘውን ስፕራይት አስቀመጠ እና ወደ ሌላኛው አካባቢ ተሰወረ። ይቀጥላል
Показать все...
" መቅደላዊት " ክፍል ፲፯ በአምባዬ ጌታነህ ናሆም ዶርም ሲገባ ናታኔም አልሰማውም ። ምክንያቱም ናታኔም በረንዳ ላይ ጀርባውን ለዶርሙ በር ሰጥቶ እያነበበ ነበር። ናሆም የሚቀይረውን ልብስ ቀይሮ ሊወጣ ሲል ናታኔም ደግሞ ቀና ሲል አይን ለአይን ይገጣጠማሉ ። ናታኔም ብድግ ብሎ "እንዴ ናሆም ደህና ነህ አሁንማ ተጠፋፋን እኮ ወንድሜ " አለ " በጣም ደህና ነኝ ወንድሜ ልክ ነህ በጣም ነው የተጠፋፋነው ግን ደግሞ ያው አንተም ስታነብ ነው የምትውለው እኔም ማንበብ ስለጀመርኩ ነው ።በል አሁን ቶሎ መውጣት አለብኝ " " ናሆም ወደየት ነው እንዲህ የምትቻኮለው? ቀስ በል እንጅ" አለ ናታኔም ወደ ናሆም እየተጠጋ " እየውልህ ወንድሜ ቶሎ መሄድ አለብኝ ቀጣይ ሳምንት የሚዘጋጅ የስነፅሁፍ ምሽት አለ ስለዚህ መዘጋጀት አለብኝ ለዛ ነው ወንድሜ " " ታቀርባለህ ?" አለ ናታኔም " አወ አቀርባለሁ " አለና ናሆም ትቶት ወጣ። መቅደላዊት በንዴትም በእልህም ወዲያና ወዲህ ትንጎራደዳለች። ጨይኖቿ ፀሀይ ለመሞቅ ወጥተው የተቀመጡ ይመስላሉ" ናሆም እንኳንም መረቤ ላይ ተጠመድክ ይሄን ነበር የምፈልገው ።አሁን የጨዋታው አሸናፊ ማን እንደሚሆን እናያለን ። አታስብ ቃል እገባልሀለሁ ትክክለኛዋን መቅደላዊት ታያለህ። አወ " አለች ራሷን አያወዛወዘች ስለዚህ ቀጣይ ማድረግ ያለብኝ ነገር ቢኖር ይሄ ነው " አለችና ጠረምጴዛው ላይ የተወሰነ ፅሁፍ የማይመስል ደግሞም ስዕልም የማይመስል ነገር ሞነጫጨረች እና በአንድ እጇ ወገቧን ይዛ አውራ ጣቷን ከንፈሯ ላይ አስጠጋችው። ባሩክ ሰባ ደረጃ አለፍ ብሎ ከበቀለች አንዲት ትንሽየ ዛፍ ስር ተቀምጦ ወጭ ወራጁን ይመለከታል ። kissing square በመባል የሚታወቅ ቦታ ነው። አንዳንድ ካፕሎች እየመጡ እዚህ ቦታ የሆድ የሆዳቸውን ሲጫወቱ ያመሹና "ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ፣ አቤት የአንቺ ፍቅር ሲበረታ " ብሎ ድምፃዊ ቴወድሮስ ካሳሁን እንደዘፈነው ።እነዚህ ካፕሎችም ደንገዝገዝ ሲል ጨለማው ለአይን ሲነሳ ከንፈር ለከንፈር ይያያዛሉ። ከዚያ ለያዥ ለገናዥ ያስቸግራሉ።በዙ ቆነጃጅት የከንፈር ድንግልናቸው የሚወሰደው እዚህ አካባቢ ነው። አንዳንድ ቦዘኔ እና በሰው ደስታ የሚደሰቱ ስራየ ብለው እዚህ አካባቢ በመምጣት የማታ ትዕይንትን ያለ ገቢር ክፋይ ይመለከታሉ ።ያለ ክፍያ ሲኒማን እንደማየት ይቆጥሩታል። ሰባ ደረጃ ደግሞ ስንቱን ደምበር እየሆነ ያስመልሰዋል ።ከሁሉም ብሎኮች ያሉት ወንዶች በመንገዳቸው ባይገናኝም እንኳ ሰባ ደረጃን ሳይሳለሙ አይሄዱም ።አንዳንዶች በዚህ ደረጃ ላይ ሲወጡ ሲወርዱ ከየካቲት ወይም ከስድስት ኪሎ ወደ ፒያሳ የሚወርዱበት ትክክለኛው ሰባ ደረጃ ይመስላቸዋል። በርግጥ ይሄን አካባቢ ለሚያዘወትር ሰው እና ለሚመሰጥበት ሰው ተነቦ የማያልቅ መፅሐፍ መፃፍ ይችላል።ባሩክ ከወዲያኛው መስመር መቅደላዊት ስትመጣ ሲያይ ከተቀመጠበት ይነሳ እና ወደ እሷ ይሄዳል። መቅደላዊት ስለ ባሩክ ሰምታለች ለሴት ባለው ከልክ ያልፈ ድፍረት እና ንቀት ትናደዳለች።ወደ እሷ አቅጣጫ እየመጣ እንደሆነ ስታይ ጉዞዋን ገታ አድርጋ ባለችበት ቆመች ባሩክ እየተጠጋት መጣ ። " ሰላም እንዴት ነሽ መቅደላዊት ባልሳሳት አንቺ ነሽ?" አልተሳሳትክም ፈላስፋው ባሩክ እስጢፋኖስ " አለች መቅደላዊት በጥላቻ አይን እየተመለከተችው " ወይ ይቺ አለም ምን አይነት ሰወች ነን የምንኖርባት ግን? ብሎ ከራሱ ጋ አወራ እና "መቅደላዊት የአንቺ እንዲህ መሆን የኔ ጉዳዬ አይደለም እንኳን አንቺ በህይወቴ ላይ ቅንጣት ታህል ቦታ የሌለሽ ሴት ይቅርና በህይወቴ ውስጥ ሰፊ ቦታ ያላቸው ሰወች እንኳ ምንም ቢሉ ግድ አይሰጠኝም ።እዚህ የመጣሁት የአንቺን የተዘፈዘፈ ፊት ለማየት አይደለም ለዚህም ብየ የምጠቀምበትን ጊዜየን አላጠፋም ።አውቃለሁ የዚህ ጊቢ ሴቶች በእኔ በኩል ጤናማ አመለካከት የላችሁም።እሱ ለእኔ ምይም ነው ሰው እንዲወደኝ አለያም እንዳይጠላኝ ሀሰት የምሸርብ ሰው አይደለሁም።እስከሚገባኝ እና እስከማውቀው አንቺ በእኔ ላይ የምትናደጅበት አመክንዮ አለ ብየ አላስብም ።ምን አልባት በሌሎቹ ጓደኞችሽ ካልሆነ። አሁን እሱን ልተወውና የመጣሁበትን ብየሽ ልሂድ ምን አልባት በሀሳብ ላንግባባ እንችላለን በሚል እሳቤ የምታደርጊውንና የምታደርጊውን ምክንያት ፣ ውጤት በተገቢው ሁኔታ እዚህ ደብዳቤ ላይ አስፍሬልሻለሁ። እኔ እና አንቺ የተለያየን አመለካከት እንዳለን አውቃለሁ ግን በናሆም ጉዳይ አንድ ነን ።እርዳታየን የጠየቀኝ ናታኔም ነው። ፖስታውን ስታነቢ ማንም እንዳያይሽ ተጠንቀቂ በተረፈ ቀጣይ እሁድ ናሆም የሚሳተፍበት የስነፅሁፍ ምሽተሰ አለ ከፈለግሽም ሀሙስ የሂስ ምሽት አለ መምጣት ትችያለሽ " አለ እና ባሩክ ትቷት ሄደ ። መቅደላዊት ለተወሰነ ርቀት እስኪሄድ በአይኗ ከሸኘችው በኋላ ስልኳን አውጥታ ወደ ናታኔም ደወለች " አቤት መቅዲ " አለ ናታኔም " አልገባኝም ናታኔም ምን እያሰብክ እንደሆነ ለምንድነው በዚህ ጉዳይ ላይ ባሩክን ያስገባኸው? በእኔ ስለማትተማመን ነው? ወይስ ሌላ ያሰብከው ነገር አለ? " አለች " ለዛ አይደለም አንቺ እንዳሰብሽው አይደለም። ታቂያለሽ አንቺ በዚህ ጉዳይ ላይ ተዋናይ እንጅ ፀሀፊም ዳይሬክተርም ተዋናይም እንዳትሆኚ ብየ ነው። ጊዜሽን እንዳይወስድብሽ ከትምህርትሽ እንዳትዘናጊ በዛ ላይ ባሩክ አሪፍ ነማንበብ ልምድ እና የማስተዋል አቅም ስላለው ናሆምን በቀላሉ ለማጥመድ ይቀለናል ። ከዚህ በኋላ ባሩክ የሚሰጥሽን ስክሪፕት ናሆም ላይ መተወን ብቻ ነው የሚጠበቅብሽ ። ገባሽ አይደል መቅዲ? " አለ አወ ገብቶኛል ጥሩ ያሰብክ ይመስለኛል ። ባሩክ ግን ደስ ስለማይለኝ ነው " አለች " አውቃለሁ መቅደላዊት ስለ ባሩክ ጥሩ ያልሆነ አመለካከት እንዳላችሁ አውቃለሁ ግን ባሩክን አውቀዋለሁ የሰፈሬ ልጅ ነው የዚህን አላማም እንደነገርኩት ሳያቅማማ ስለተቀበለኝ ነው።" አለ " እሽ በቃ የሆነ ፖስታ ነገር ሰጥቶኛል ከአነበብኩት በኋላ እናወራለን ደግሞ እረስቼው ናሆም እሁድ የስነፅሁፍ ምሽት ላይ ግጥም ያቀርባል።" " ማን ነገረሽ? " " ይሄ ባሩክ ተብየህ ነዋ መረጃው እውነት ይሁን አይሁን የማውበው ነገር የለኝም " አለች " ባሩክ ባሩክ ካሰብኩህ በላይ ስራየን እያቃለልክልኝ ነው " አለ ናታኔም ጮሆ። " ማንነው ስራህን የሚያቃልልልህ? አለ በሩን ከፍቶ እየገባ። ናታኔም ደንግጦ ቆመ። ይቀጥላል
Показать все...
" መቅደላዊት " ክፍል ፲፮ በአምባዬ ጌታነህ ነፋሱ ያለ ማቋረጥ ዝቅዝቅ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ይነፍሳል በዛፎች ዳር እና ዳር የታጀበው አስፓልት በወጀቡ ነፋስ በረገፉ አበባወች ተንቆጥቁጦ አንድ ሀፍታም ለአንዲት ሚስቱ ስጦታ ያነጠፈው መስሎ ሊረግጡት ያሳሳል። ከትንሽ ወጀብ ነፋስ በኋላ ያለ ምንም ግምግምታ ዝናቡ ጣለ ።መቅደላዊት ፀጉሯን በእጇ ሸፍና ወደ ራስ ተፈሪ ህንፃ ስትገባ ናሆም ያያት እና እሱም ወደ ህንፃው ተከታትሏት ገባ። መቅደላዊት ከመግባቷ እዛ የተጠለሉት ተማሪወች አይናቸውን ይጥሉባታል። አንደኛው " ይቺን ልጅ ላወራት ነው!" አለ ሌላኛው ቀበል አድርጎ" ሰው ይዘህ ነው ወይስ ራስህን ችለህ?" ሲለው "ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ራሴን ችየ ነው የማውራት አውርቼ ስልኳን ተቀብየ ካልመጣሁ እኔ አይደለሁም" አለ ሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀ ኧረ ሞራልህ በለው ጀግና ነህ አለ ሌላኛው እየሳቀ " ትቷቸው ወደ እሷ ሄደ ይሄኔ እንዴት ነው? ምታናግረው ገና እንዳየችው ደንግጣ የምትሮጥ ይመስለኛል ።ሰይጣን ራሱ የሱን ያህል የሚጠቁር አይመስለኝም "አለ ይሄን እያለ ይከታተለዋል ።ተገረመ ፍፁም ተቃራኒ ሆነበት መቅደላዊት በስርአት እያወራችው ነው። ተመልሶ መጥቶ የሆነውን ሁሉ እስኪነግራቸው ጓጉ ፣ ኮስታራዋ ፣ እና ማንም የማይደፍራት ቆንጆዋ መቅደላዊት አሁን ከሰል ከመሰለ ሰው እየተሳሳቀች ነው። * መቅደላዊት ልጁ በሚያወራት ሳይሆን የምትስቀው በናሆም እቅድ ነው። እሷን እንዲፈትን በላከው ሰው ላይ አንዳንዴ ልጁ አውርቶ ሳይጨርስ አቋርጣው ትስቃለች ።ስትስቅ ጠፈርን የምታደምቅ ፀሀይ ትመስላለች።የውበቷ ጥግ በሳቋም አላምን ያዳርሳል ያ ማነው ናትናኤል ነው? እግዜር ስድስቱንም ቀን ሲሰራት የኖረ ያለው።እውነቱን ሳይሆን አይቀርም።ፍፁም ሀዘን የነካት አትመስልም ።አወ መቅደላዊት በተንደላቀቀ ሁኔታ ነው ያደገችው። ሁሌም እናትና አባቷ አይተው አይጠግቧትም።በዚህም በተለየ አስተዳደግ ነው ያደገችው። ይሄን የህይወቷን ሙሉ የአንዲት ፈገግታዋ ማንፀባረቅ ይችላል ። ረጅም ሳቋን በመሀል አቋረጠውና " በነገራችን ላይ ስትስቂ ይበልጥ ቆንጆ ነሽ " አለ " ኧረ ባክህ ሀሀሀሀሀሀሀሀ አላውቅም ነበር " አለች በቃ ከዚህ በኋላ እወቂ አላት " እሽ አውቂያለሁ በጣም አመሰግናለሁ ግን እስካሁን ስምህን አልነገርከኝም "አለች" ስሜ ኦኪዮ ይባላል " አለ ስምህ በጣም ደስ ይላል ። ስላወኩህ ደስ ብሎኛል ። አሁን ግን መሄድ አለብኝ ዝናቡ እያቆመ ስለሆነ " አለች እሽ መቅደላዊት ሌላ ጊዜ እንገናኛለን " አለ እና ወደ ጓደኞቹ ተመለሰ። መቅደላዊት ዝናብ የማታው ፀጉሯን አራግፋ ቀና አለች እና " ለራሷ ፈገግ ብላ ለምን ግን እኔን ይሄን ያህል ማወቅ ፈለገ ለምን ስለ ባህሪየ ግድ ሰጠው። ነው እሱም ከእኔ ፍቅር ይዞት ይሆን? ማን ያውቃል እልህ እና ንዴት ወደ ፍቅር ይቀየራል። እንደዛ ካልሆነ ለምን ታዲያ ይሄን ልጅ ለመፈተን ይልክብኛል? ናታኔም ልክ ነው ።በጭራሽ ዝም ብሎ የሚተኛ አይነት ልጅ አይደለም። ለማንኛውም የመጀመሪያ ፈተናውን በድል ተወጥቻለሁ ።ቀጣዩንም በኩራት የማልፈው ይሆናል።" አለች እና በዝናቡ የተቋተውን ውሀ እየዘለለች ወደ ብሎኳ ሄደች። #### ናሆም ልጁን በስርአት እና በፈገግታ በማውራቷ የተደሰተ ቢመስልም ግን ደግሞ "የሆነ ያሰበችው ነገር እንዳለ ግልፅ ነው" አለ እና ከህንፃው ወጥቶ የ ደጃዝማች በላይ ዘለቀን ሀውልት አልፎ ወደ አሉላ አባ ነጋ ብሎክ ቀጥ ብሎ ያልፋል። በዚህ ሁሉ የሀሳብ ጉዞ የመቅደላዊት ስራ እየመጣበት ነው።አብዛኛውን ጊዜ ስትስቅ የነበረው እሱ እያወራ ነው በድንገት እንደውም አልፎ አልፎ የሚያወራውን ነገር አቋርጦ ይመለከታት ነበር። የሆነ ተንኮልማ ሸርባለች። ዋ መቅደላዊት እኔ ላይ እየተጫወትሽ ከሆነ እኔ አንቺን አያርገኝ።" አለ ናሆም ።ከዚህ ሁሉ ሀሳብ ያባነነው ስልኩ ሲጠራ ነበር። ስልኩ የሚያውቀው ስልክ ነው" እሽ በርና ሰላም ነው " " ደህና ነኝ ናሆም አንተ እንዴት ነህ?" " አለሁ ወዳጄ አንድ ጎኔ ተሰብሮ " ደግሞ ምን ሆንክ? ችግር አለ ናሆም? " እኔ እስካለሁ ድረስ ችግር አይጠፋም ሰወች በምሄድበት መንገድ ሁሉ እየተከተሉ ነገረኛ ሳያደርጉኝ አይቀሩም።" አለና ናሆም በረጅሙ ተነፈሰ ለማንኛውም እሱን ለእኔ ተወው በማስተካክልበት መንገድ አስተካክለዋለሁ አንተ ግን ዛሬ እንዴት ትዝ አልኩህ?" አለ ናሆም " ያው እኔማ የደወልኩልህ የሚቀጥለው እሁድ ማታ ግሩም የግጥም ምሽት አዘጋጅተናል እና ስራ ካለህ ብየ ነው።" አለ በርና " በጣም ነው የማመሰግነው ወዳጄ በቃ ይዤ እመጣለሁ "አለ ናሆም ኧረ ችግር የለውም በቃ ሀሙስ የሂስ ምሽት አለን እዛ ይዘኸው ና " " መልካም በርናየ ይዤ እመጣለሁ መልካም ጊዜ " ስልኩን ዘግቶ በነገረው የስነፅሁፍ ምሽት ላይ ለማሰብ የሆነ ቦታ መሄድ እንዳለበት አምኗል ግን መጀመሪያ ዶርም መድረስ አለበት። ይቀጥላል .....................
Показать все...
" መቅደላዊት " ክፍል ፲፭ በአምባዬ ጌታነህ ዲዮጋን እና ናታኔም የአንድ ሰፈር ልጆች ናቸው ዲዮጋን የአራተኛ አመት የ electrical engineering ተማሪ ነው። ዲዮጋን የአራተኛ አመት electrical engineering department ሁለተኛ ሰቃይ ነው። "ህይወት እና ጥበብ ያበሰለችው፤ ልቦለዱን ከገሀዱ መንዝሮ በብልሀት የሚኖር ፤ የፍልስፍናው ቀበኛ ፣ ሰው ቢኖር እሱ ዲዮጋን ብቻ ነው "ይላል ናታኔም ሁልጊዜም ስለ ዲዮጋን ( ባሩክ ስስጢፋኖስ ) ሲናገር። " ባሩክ ዛሬ አንድ የምነግርህ ትልቅ ነገር አለ እና በረቀቀ ሀሳብ ልትደግፈኝ ይገባል " አለ ናታኔም " እሽ አለ ባሩክ ( ዲዮጋን ) ከንፈሩን እያሸራመጠ እየውልህ ባሩክ ናሆም ከእናቱ ጋ አስተዋውቆኝ ነበር እናም አንድ ቀን ስልኬን ከናሆም ተቀበላ ደወለችልኝ ደውላ ያለችኝ እጅግ አስገራሚ ነገር ነው። ናሆም ጣም ትልቅ በሽታ አለበት የናሆም እናት ደወለችልኝ " ናሆም ከባድ የስነልቦና ችግር አለበት። እኔ በልጅነቱ ከአባቱ ጋር ተጣልቼ ሌላ ባል አግብቼ ናሆምን ከአባቱ ጋር ትቼው ሄድኩ። አባቱ በውል እንኳ ያላደገ ልጅ ሰጥቼው ስለሄድኩ አባቱ በጣም አዘኖ ነበር። እኔ በወቅቱ ከእሱ ጋ መጣላቴን እንጅ ስለ ልጅ ግድ ሳይሰጠኝ በስስት የወለድኩትን ባሌን የጎዳሁ መስሎኝ ልጄን ትቼው ወጣሁ። አባቱ ግን እንደኔ ሊተወው አልቻለም እንደ እናትም እንደአባትም ሆኖ አሳደገው ትምህርት ቤት አስገብቶ ራሱ እየሰራ ሚስት ሳያገባ ናሆምን አስተማረው ናሆምም አባቱን እጅግ በጣም ይወደው ነበር እና በትምህርቱ ጎበዝ በመሆን አባቱን ማስደሰት ቻለ። አባቱ ናሆምን ምንም ሳይጎልበት ነው ያሳደገው ሁልጊዜም ትምህርት ቤቱ ድረስ ሸኝቶት ይመለሳል ታዲያ ናሆም 11 ኛ ክፍል እያለ ወደ ሁለተኛ ሲሚስተር ገደማ አባቱ ከስራ ሲመለስ በመኪና አደጋ ይሞታል። ናሆም ሁሉ ነገር ተቀያየረበት ነገሮችን መቋቋም አቃተው። ሀዘኑ መሪር ሆነ ይህን ጊዜ እኔ ጋር እንዲመጣ አደረኩ አልተቃወመኝም።ግን ከመጣ በኋላ በሚያደርጋቸው ነገሮች ውስጤ ተነካ እኔን እና ከአሁኑ ባሌ የወለድኳትን ሴት ልጀን እጅግ ይፀየፈናል። በጭራሽ አንድ ቀን እንኳ እንደ እናት እና ልጅ ሆነን አናውቀም በጣም ብዙ ጊዜ ሞክሪያለሁ ግን አልቻልኩም ።ልጄም እየተሰቃየች ነው የናሆም ክፋቱ እኔ ላይ መጨከኑ ሳይሆን ምንም ከማታቀው እህቱ ጋር መጣላቱ አንድ ቀን ለጀሮ የሚከብድ ንግግር ልጄን ተናገራት " አንቺ በእናትሽ ነው እኔ ደግሞ አባቴን ነው መሆን የምፈልገው ለዚህም ደግሞ ያለ ሴት ያለ ሚስት እንዴት መኖር እንደሚቻል አባቴ አሳይቶኛል ነፍሱን ይማረው እና " አላት ያኔ ውስጤ ተጎዳ መቋቋም አልቻልኩም ልጄን አጥቸዋለሁ " ሲቃዋ በስልክ ይሰማ ነበር። ልጄ ሴትን ልጅ በጣም ይፀየፋል ይሄን አመለካከቱን እንዲቀይር እፈልጋለሁ እና የቻልከውን አድርግልኝ ምን አልባት እሽ ካለህ!" አለችኝ ልቧ በጣም ተሰብሯል እናም እሷ እንዳለችው የግድ ልንቀይረው ይገባል እና ለዚህ ስራ ደግሞ አንዲት ሴት ልጅ አግኝቻለሁ። በሀሳቤ ተስማምታ እያገዘችኝ ነው። "እሷ ማን ናት?" አለ ባሩክ በጥሞና ሲያዳምጠው ከቆየ በኋላ "መቅደላዊት "አለ ናታኔም " ጥሩ በእኔ በኩል አታስብ ከእሷ ጋ ታስተዋውቀኝ እና ምን ማድረግ እንዳለባት እንመካከራለን ይሄን በእኔ ጣለው " አለ ባሩክ (ዲዮጋን )በፍጹም በራስ መተማመን "" ግን ባሩኬ እንደምታስበው ቀላል አይደለም ሁሌም ንቁ እና ሲበዛ ተጠራጣሪ ነው በጣም መጠንቀቅ እና ከእሱ በላይ ማሰብ ይጠበቅብሀል" አለ ናታኔም " አታስብ "እኔ ያልፈሳሁበት ዳገት የለም አለች አህያ አለና ስቆ ምን ሆነሀል በእኔማ ተማመን እንጅ " አለና የናታኔምን ተከሻ ቸብ ቸብ አደረገው እሽ ተስፋ አደርጋለሁ ወንድሜ በቃ አሁን ልሂድ " ብሎ ባሩክን ከተቀመጠበት ትቶት ሄደ ባሩክ ስለ ናሆም በጣም አዝኗል በእናቱ የተናደደ እንዴት በውል እንኳ ያልበሰለ ልጅ ትታ ትኮበልላለች ። ፅፅፅፅፅ መሆን አልነበረበትም ግን ሆኗል። ይቀጥላል
Показать все...
" መቅደላዊት " ክፍል ፲፭ በአምባዬ ጌታነህ ዲዮጋን እና ናታኔም የአንድ ሰፈር ልጆች ናቸው ዲዮጋን የአራተኛ አመት የ electrical engineering ተማሪ ነው። ዲዮጋን የአራተኛ አመት electrical engineering department ሁለተኛ ሰቃይ ነው። "ህይወት እና ጥበብ ያበሰለችው፤ ልቦለዱን ከገሀዱ መንዝሮ በብልሀት የሚኖር ፤ የፍልስፍናው ቀበኛ ፣ ሰው ቢኖር እሱ ዲዮጋን ብቻ ነው "ይላል ናታኔም ሁልጊዜም ስለ ዲዮጋን ( ባሩክ ስስጢፋኖስ ) ሲናገር። " ባሩክ ዛሬ አንድ የምነግርህ ትልቅ ነገር አለ እና በረቀቀ ሀሳብ ልትደግፈኝ ይገባል " አለ ናታኔም " እሽ አለ ባሩክ ( ዲዮጋን ) ከንፈሩን እያሸራመጠ እየውልህ ባሩክ ናሆም ከእናቱ ጋ አስተዋውቆኝ ነበር እናም አንድ ቀን ስልኬን ከናሆም ተቀበላ ደወለችልኝ ደውላ ያለችኝ እጅግ አስገራሚ ነገር ነው። ናሆም ጣም ትልቅ በሽታ አለበት የናሆም እናት ደወለችልኝ " ናሆም ከባድ የስነልቦና ችግር አለበት። እኔ በልጅነቱ ከአባቱ ጋር ተጣልቼ ሌላ ባል አግብቼ ናሆምን ከአባቱ ጋር ትቼው ሄድኩ። አባቱ በውል እንኳ ያላደገ ልጅ ሰጥቼው ስለሄድኩ አባቱ በጣም አዘኖ ነበር። እኔ በወቅቱ ከእሱ ጋ መጣላቴን እንጅ ስለ ልጅ ግድ ሳይሰጠኝ በስስት የወለድኩትን ባሌን የጎዳሁ መስሎኝ ልጄን ትቼው ወጣሁ። አባቱ ግን እንደኔ ሊተወው አልቻለም እንደ እናትም እንደአባትም ሆኖ አሳደገው ትምህርት ቤት አስገብቶ ራሱ እየሰራ ሚስት ሳያገባ ናሆምን አስተማረው ናሆምም አባቱን እጅግ በጣም ይወደው ነበር እና በትምህርቱ ጎበዝ በመሆን አባቱን ማስደሰት ቻለ። አባቱ ናሆምን ምንም ሳይጎልበት ነው ያሳደገው ሁልጊዜም ትምህርት ቤቱ ድረስ ሸኝቶት ይመለሳል ታዲያ ናሆም 11 ኛ ክፍል እያለ ወደ ሁለተኛ ሲሚስተር ገደማ አባቱ ከስራ ሲመለስ በመኪና አደጋ ይሞታል። ናሆም ሁሉ ነገር ተቀያየረበት ነገሮችን መቋቋም አቃተው። ሀዘኑ መሪር ሆነ ይህን ጊዜ እኔ ጋር እንዲመጣ አደረኩ አልተቃወመኝም።ግን ከመጣ በኋላ በሚያደርጋቸው ነገሮች ውስጤ ተነካ እኔን እና ከአሁኑ ባሌ የወለድኳትን ሴት ልጀን እጅግ ይፀየፈናል። በጭራሽ አንድ ቀን እንኳ እንደ እናት እና ልጅ ሆነን አናውቀም በጣም ብዙ ጊዜ ሞክሪያለሁ ግን አልቻልኩም ።ልጄም እየተሰቃየች ነው የናሆም ክፋቱ እኔ ላይ መጨከኑ ሳይሆን ምንም ከማታቀው እህቱ ጋር መጣላቱ አንድ ቀን ለጀሮ የሚከብድ ንግግር ልጄን ተናገራት " አንቺ በእናትሽ ነው እኔ ደግሞ አባቴን ነው መሆን የምፈልገው ለዚህም ደግሞ ያለ ሴት ያለ ሚስት እንዴት መኖር እንደሚቻል አባቴ አሳይቶኛል ነፍሱን ይማረው እና " አላት ያኔ ውስጤ ተጎዳ መቋቋም አልቻልኩም ልጄን አጥቸዋለሁ " ሲቃዋ በስልክ ይሰማ ነበር። ልጄ ሴትን ልጅ በጣም ይፀየፋል ይሄን አመለካከቱን እንዲቀይር እፈልጋለሁ እና የቻልከውን አድርግልኝ ምን አልባት እሽ ካለህ!" አለችኝ ልቧ በጣም ተሰብሯል እናም እሷ እንዳለችው የግድ ልንቀይረው ይገባል እና ለዚህ ስራ ደግሞ አንዲት ሴት ልጅ አግኝቻለሁ። በሀሳቤ ተስማምታ እያገዘችኝ ነው። "እሷ ማን ናት?" አለ ባሩክ በጥሞና ሲያዳምጠው ከቆየ በኋላ "መቅደላዊት "አለ ናታኔም " ጥሩ በእኔ በኩል አታስብ ከእሷ ጋ ታስተዋውቀኝ እና ምን ማድረግ እንዳለባት እንመካከራለን ይሄን በእኔ ጣለው " አለ ባሩክ (ዲዮጋን )በፍጹም በራስ መተማመን "" ግን ባሩኬ እንደምታስበው ቀላል አይደለም ሁሌም ንቁ እና ሲበዛ ተጠራጣሪ ነው በጣም መጠንቀቅ እና ከእሱ በላይ ማሰብ ይጠበቅብሀል" አለ ናታኔም " አታስብ "እኔ ያልፈሳሁበት ዳገት የለም አለች አህያ አለና ስቆ ምን ሆነሀል በእኔማ ተማመን እንጅ " አለና የናታኔምን ተከሻ ቸብ ቸብ አደረገው እሽ ተስፋ አደርጋለሁ ወንድሜ በቃ አሁን ልሂድ " ብሎ ባሩክን ከተቀመጠበት ትቶት ሄደ ባሩክ ስለ ናሆም በጣም አዝኗል በእናቱ የተናደደ እንዴት በውል እንኳ ያልበሰለ ልጅ ትታ ትኮበልላለች ። ፅፅፅፅፅ መሆን አልነበረበትም ግን ሆኗል።
Показать все...
" መቅደላዊት " ክፍል ፲፬ በአምባዬ ጌታነህ የጠዋቷ ፀሀይ ገና ከመውጣቷ በጉም ተሸፍና ልውጣ አልውጣ ትላለች ከአድማስ ማዶ የሚታየው የፅሀይ ብርሀን ዶርሙን በፈገግታ ሞልቶታል አይኖቹን እያሻሸ ከእንቅልፉ ተነሳ እና እራሱን ከአልጋው ሳይወርድ ማነቃቃት ጀመረ።ናታኔም በተደጋጋሚ በቀኝ እጁ መዳፍ የቀኝ አይኑን ያሻል። አጭር ቁምጣ በቲሸርት በነጠላ ጫማ ተጫምቶ ከዶርሙ ወጣ ።ታች ሲደርስ ተማሪዎች ስለ ናሆም እያወሩ ይሰማ እና ጆሮውን በደምብ ሰጥቶ ያዳምጣል ።እንደው ይሄ ልጅ ምን አድርጎ ይሆን " አለ ። አንደኛው ተማሪ ደግ አድርጎታል ይሄ ቆሻሻ መምህር እሱን ቢሉ አዋቂ ጭራሽ ከእሱ በላይ ሰው ያለ አይመስለውም እንደው ገና ሳንጀምረው ምን አይነት ጠማማ መምህር ገጠመን ናሆም እማ ልክልኩን ነገረው ።ጀግና ነው አቦ እኔ ልጁ ከመጀመሪያው ይመቸኛል ቆራጥ ነው።" አለ አንደኛው ተማሪ ሌላኛው ተቀበለና ናሆም ግን በጣም አበዛው ብዙ ጊዜ ለችግር ይጋለጣል ደግሞ ዩኒቨርስቲ ላይ መምህር ከጠመደህ " F " ነው የሚሰጥህ አጉል ከመምህር ጋር ሰፋጣ ለእኔ ጥሩ አይደለም ህይወቱን ነው የሚያበላሽበት ደግሞ ጊቢው ላይ በጣም ስሙ የገነነ መምህር ነው ።ከሲኒየር እስከ ተመራቂ ተማሪዎች የማይፈራው የለም ሰውየው በጣም ክፉ ነው ኧረ እንደውም መምህራን እና ሌሎች ሰራተኞች ሁሉ ይፈሩታል አሉ ህህ ሰውየው እኮ ብርሃኑ ነው።"አለ እና ዝም አለ " ባክህ ምንም አያደርገውም እንዳይመስልህ መምህራን እንዲህ አይነቱን ደፋር ተማሪ በጣም ነው የሚፈሩት " አለ ሌላኛው። ይሄን ሁሉ በጥሞና ከሰማ በኋላ ናታኔም " ደግሞ ዛሬ የትኛውን ጀብድ ሰርተህ ይሆን? " አለና ናታኔም ጉዞውን ቀጠለና ወደ ወንዶች እና ሴቶች ብሎክ መገነጣጠያ ሲደርስ የሴቶቹን መግቢያ ብሎክ ወደ ቀኝ በመተው በግራ በኩል ወደ ቻሪቲ ክበብ ቢሮ የሚያስኬደውን መንገድ ይዞ ትንሽ እንደሄደ ዲዮጋንን ያገኘዋል። ዲዮጋን ቅፅል ስሙ ነው ዲዮጋን የተባለው በአንድ የኪነጥበብ ምሽት የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ሰራተኞች ከፍተኛ አመራሮች መምህራኖች ተማሪወች በታደሙበት ትልቅ የጥበብ ምሽት ፊቱን ወደግድግዳው አዙሮ ያዘጋጀውን ፅሁፍ ሲያቀርብ የመድረክ መሪው " ፊትህን ወደዚህ አዙረህ አቅርብ እንጅ ወደ ታዳሚ" ቢለው " ታዳሚ መኖሩን በምን አወክ? አንተ ነፋስ ዝም በል እኔ የማደርገውን የማውቅ ሰው ነኝ ዝም ብለህ አታሽቃብጥ " ብሎት ፅሁፉን ያቀርብ እና ከመድረክ ሲወርድ ሁሉም ከመቀመጫው ተነስቶ አጨበጨበለት ። ብዙውን ጊዜ ስለ ዲዮጋን ፍልስፍና አውርቶ አይጠግብም የተወሰኑትን የዲዮጋንን ፍልስፍናወች እንደወረደ ሲጠቀም የተወሰኑትን ደግሞ በእራሱ አሻሽሎ ያወርዳቸዋል ። ዲዮጋን ትክክለኛ ስሙ " ባሩክ " ነው ትርጉሙም የተባረከ ብሩክ ማለት ነው። ጠይም ዘለግ ያለ መልከመልካም ወጣት ነው። ባሩክ (ዲዮጋን )የሰው መፅሐፍ ነው። ለአፍታ እሱ ጋር የቆመ ሰው ብዙ ነገር ያውቃል ።ከአገር አቀፍ እስከ አለም አቀፍ መፅሃፍትን ያገላብጣል። ብዙ ጊዜ ዲዮጋን ( ባሩክ )ሲናገር አይፈጥንም ነገር ግን ዘግይቶ የሚናገራቸው ቃላቶች ወስጠ ወይራ ሀሳብ ናቸው። ለእያንዳንዷ ነገር ትንታኔ ይሰጥባታል። አንድ ጊዜ ታዲያ በሁሉም ተማሪ አይን እና ጀሮ የገባው የጊቢውን ሴቶች ለአራት በመክፈሉ ነው። የጊቢውን ሴቶች በፐርሰንት አስቀመጧቸው ከስር የእሱን ስም ከነፊርማው አኑሮ በየቦታው ይለጥፋል።እንዲህ ይል ነበር፦ "የታደላችሁ በዚህ በጀግኖች አያቶቻችን አጥንታቸውን ለእኛ ነፃነት በከሰከሱበት ምድር አድዋ አድዋ ዩኒቨርስቲ የምትማሩ ተማሪወች እኔ ባሩክ እስጢፋኖስ በጊቢያችን የሚገኙትን ሴቶች መረጃ በመውሰድ እና ተገቢውን ጥናት በማድረግ ተከታዩን ለጥፊያለሁ ።በዚህም በአጠቃላይ የጊቢያችንን ሴቶች በአራት ዘርፍ መድቢያቸዋለሁ ፦ 1, እምቢ ለምኔ ( ከፍቶ እንካ ) 2, ወጨጌ 3, ሱሴ 4, ወሴ ሲሆኑ እስኪ ደግሞ እያንዳንዳቸውን በመረጃ እንመልከት! 1,እምቢ ለምኔ ( ከፍቶ እንካ )፦ እኒህ ሴቶች በምንም ታዕምር እምቢን የማያውቁ ለጠየቃቸው ሁሉ እሽ እያሉ ማንንም ላለማስከፋት ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚታትሩ ትጉህ የጊቢያችን ሴቶች ናቸው።ለዚህም ግብራቸው ተመሳሳይ መገለጫ እንዲሆናቸው "እምቢ ለምኔ ወይም ፣ከፍቶ እንካ፣ አይክፋህ ብያቸዋለሁ። በዚህም 52% ናቸው። 2, ወጨጌ ፦ አኒህ ወጨጌ የሚባሉት የዩኒቨርስቲያችን ሴት ተማሪዎች ሲበዛ ትሁት ትዕግስተኛ እና አክራሪ የሀይማኖት ሰወች ሲሆኑ በጭራሽ ለቧልት ጊዚያቸውን የማያባክኑ እንስቶች ሲሆኑ ፣ እንትን የሚጠይቃቸውን ወንድ ደግሞ" ከትዳር በኋላ፤ ከምረቃ በኋላ" እያሉ ወንዶችን ከአጠገባቸው የሚያባርሩ ጠንካራ ሴቶች ሲሆኑ በትምህርታቸው ላይም ተፅዕኖ የሚፍጥሩ ጀግኖች ናቸው።በፐርሰንት ሳስቀምጣቸውም 23% ናቸው። 3, ሱሴ ፦ እነዚህ ሱሴ የሚባሉት ደግሞ ሁልጊዜም በጭስ ታፍነው በተለያዩ ሱሶች ተዘፍቀው መውጫው የጠፋባቸውም መውጫውን እያወቁት ላለመውጣት ያሉትም ጭምር በዚህ አለም የሚኖሩ ሴቶች ናቸው። እነዚህ ሴቶች ብዙውን ጊዜ ሲጋራ ፣ ሀሺሽ ፣ ጋንጃ ፣ የሚጠቀሙ ሲበዛ ሱሱ በላናቸው የዞረ አሳዛኝ ፍጡር ናቸው። እነዚህን ደግሞ በፐርሰንት ሳስቀምጣቸው 15% ናቸው። 4, ወሴ ፦ እነዚህ ሴቶች ደግሞ ከሴቶች ሆነው ነገር ግን ሴትነታቸውን ያልወደዱ ከተፈጥሮ ጋር የተጣሉ ሁሉ ስራቸው ከሴት ወጭ ድርጊታቸው ምግባራቸው ሁሉ ነገራቸው በራሳቸው ራሳቸውን ወደ ወንድነት የቀየሩ ሴቶች ሲሆኑ እኔም ይህንን በማየት አዲስ ፆታ ከወንድ " ወ " ን ከሴት ደግሞ " ሴ " ን በመውሰድ "ወሴ" የሚል ስያሜ ሰጥቻቸዋለሁ ። እነዚህ ሴቶች ልብሳቸው የፀጉር ቁርጣቸው በሙሉ የወንድ ቢሆንም ያው ግን በተፈጥሮ ሴት ናቸው በዚህም በፐርሰንት ሳስቀምጣቸው 10% ናቸው። ባሩክ እስጢፋኖስ የማይነበብ ፊርማ........." የሚል ማስታወቂያ ለጥፎ የጊቢውን ተማሪ አስደመመው በወንድ ተማሪዎች በኩል አድናቆትን ተቸረው እንደ ጉድ ተወራ ስሙ በአንድ ጊዜ ገነነ በሴቶች በኩል ደግሞ ጥላቻ እና እልህ የታዘሉባቸውን መልዕክቶች ለባሩክ መወንጨፍ ጀመሩ የተወሰኑት ሴቶች በድርጊቱ ተደመሙ! ግን የሁሉንም አፍ ያስከፈተው እና ሁሉንም በሳቅ ያስፈነደቀው ይሄን ማስታወቂያ ከለጠፈ በኋላ ባሩክ ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ ራስ መንገሻ አደባባይ ቁጭ ብለው ሳለ አንዲት ሴት እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ወደ እሱ መጣች እና ዘላ ሸሚዙን አንቃ " አንተ ማን ሆነህ ነው እንዲህ አይነት ድፍረት የምትዳፈረው?" ባለችው ጊዜ እሱ ከቁብ ሳይቆጥራት ምንም አይነት አፀፋ ሳይመልስ" ለመሆኑ አንቺ ማንኛይቱ ሴት ነሽ?" ብሎ የጠየቃት ጊዜ ጓደኞቹ በሳቅ ወደቁ በባሩክ ጥያቄ እና በባሩክ ጥያቄ ግራ በተጋባችው ልጅ የደከሙ ይመስላሉ የያዘችውን ኳሊታ ለቀቅ እያረገች ወደ ውሀነት እየተቀየረች " ለመሆኑ አንቺ ማንኛይቱ ነሽ? " ስትል ምን ለማለት ፈልገህ ነው?" አለችው መልሳ አንደኛው ቀበል አደረገ እና" ምን ይሄ ጠፍቶሽ ነው? ከፍቶ እንካ ነሽ? ወሴ ነሽ ወይስ ሱሴ ነሽ ለማለት ነው እንጅ መቼም ወጨጌ አይደለሽም" አለና ከት ብሎ ሲስቅ ጓደኞቹ ተከትለውት አብረው ሳቁ። ይሄኔ እያለቀሰች ከአጠገባቸው እየሮጠች ሄደች። ከዚህ በኋላ ባሩክ እና ሴቶች አይን እና አፈር ሆኑ። በጣም ነው የሚጠሉት በጣም ነው የሚያፍሩት፣ በጣም ነው የሚፈሩት ። ናታኔም ዲዮጋንን በጣም ነው የሚወደው ናታኔምን ተቀብሎ ጊቢውን ያሳየው ያላመደው ዲዮጋን ነው። ይቀጥላል .........
Показать все...