cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

££ĨĈÃĹ~ⓜⓘⓝⓐ🔥🔥

●WELCOME-TO-OFFICAL~MINA ➾PICS 📷 ➾LOVE ❤❤ ➾VIDIO 🎬 ➾FUN 😃 ➾MUSIC 🎶🎼 ➾TIK TOK 😃 ➾VINE 😉 yagegnubtal feta yebelubt👌 @Creater- @minafaf Join 👇👇 @OFFICALMINA

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
143
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

sticker.webp0.26 KB
♥️የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ለሆናችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እንዲሁም ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን መልካም የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ኢድ ሙባረክ። #
Показать все...
data ተዘግቶ የካርድ ብር የቆጠበው ጀለሴ vitz ሊገዛ እየተከራከረ ነው😁😂😁
Показать все...
😭😭😭😭😭
Показать все...
3.81 MB
በሻሸመኔ ከተማ ሰሞኑን ተፈጥሮ በነበረው ሁከት እስካሁን ድረስ 553 ሰዎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ፡፡ ሸገር ከከተማዋ ፖሊስ እንደሰማው በቁጥጥር ስር ከዋሉት 553 ተጠርጣሪዎች ውስጥ 456ቱ ወንዶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 97ቱ ሴቶች ናቸው፡፡184ቱ ማስረጃ የቀረበባቸው መሆናቸውንም ሰምተናል፡፡ በሁከትና ብጥብጡ ወቅት የተዘረፉ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች፣ 29 የቤት እንስሳት፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ላፕቶፕ፣ ቴሌቪዥን እና ጀኔሬተር የመሳሰሉ እቃዎችን ፖሊስ እያስመለሰ መሆኑን ሰምተናል፡፡ በሻሸመኔ በሰሞኑ ሁከት የ3 ሰዎች ሕይወት ማለፉ የሚታወስ ሲሆን 78 ሆቴሎች፣ 20 ሱቆች፣ 196 መኖሪያ ቤቶች፣ 4 ባንኮች፣ 64 ተሽከርካሪዎች፣ 14 ሞተር ሳይክሎች፣ 9 ወፍጮ ቤቶች፣ 21 ህንፃዎች ተቃጥለዋል መባሉ ይታወሳል፡፡ ዘገባው የሸገር ኤፍኤም ነው። https://t.me/joinchat/AAAAAFimOg74HMibAQ0VAQ https://t.me/joinchat/AAAAAFimOg74HMibAQ0VAQ https://t.me/joinchat/AAAAAFimOg74HMibAQ0VAQ https://t.me/joinchat/AAAAAFimOg74HMibAQ0VAQ https://t.me/joinchat/AAAAAFimOg74HMibAQ0VAQ https://t.me/joinchat/AAAAAFimOg74HMibAQ0VAQ
Показать все...
🤣🤣🤣 Jᴏɪɴ 🔜 @Officalmina Jᴏɪɴ 🔜 @Officalmina Jᴏɪɴ 🔜 @Officalmina
Показать все...
2.13 KB
💔የድሀ ልጅ ፍቅር❣️ 🌺ምዕራፍ ሁለት ...........ክፍል 24 ሜላት የቅዱስን መኝታ ክፍል መግባት ተከትላ .ከእናትህ ቤትና ከእዚህ ቤት አንዱን ምረጥ ብላ ስትጮህብኝ ቅዱሴ የመኝታ ቤት በር ላይ ቆሞ ይሰማ ነበረ ...ሳየው ደነገጥኩ ...ሜላትም አየችው .ቅዱሴ ወደ መኝታ ክፍል ገብቶ ቁጭ አለ ተከትዬው ገባሁ .ሊያናግረኝ አልፈለገም... ሜላትም መጣች .እሷንም መልስ ሊሰጣት አልፈለገም.... ቅዱስ አኩርፏል ስንጨቃጨቅ አይቶን አያውቅም ሜላትም ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷት ስለነበር በደንብ ተቆጥታ ነበር የተናገረችኝ...መቼም የእናቴን ቤት መተው አልችልም እናቴ ናትና ...የሚስቴንም ቤት አልችልም ሚስቴ የልጄ እናት ናትና ከዛም በላይ አሁን ላለሁበት ትልቅ መሰዋአትነት ከፍላለችና ብቻ ግራ ገብቶኛል ምን እንደማደረግ አላውቅም.... እኔና ሜላት ከቀን ወደ ቀን ጭቅጭቃችን እየባሰ ቅዱስም እናቴጋ መዋል ማደረን ከመረጠ ሰነባበትን .. ቅዱስ ወደ ቤት እንሂድ ሲባል እናቴ እግር ላይ ተጠምጥሞ አልሄድም ይላል..ግራ ገብቶኛል ፍቅራችን እየተናደ እየተሸረሸረ ከመጣ ቀናቶች አለፉ...የተፈጠረውን እየተፈጠረ ያለውን ለእናቴ እነግራታለው.... ሜላት ሁሉን ነገር እርስት አድርጋው ጠጥታ አምሽታ ትመጣለች በጣም ሰለቸኝ በቃ ከአቅሜ በላይ ሆነችብኝ ምን ላድርጋት... ብመክራት ባስመክራት ምንም ልትስተካከል አልቻለችም ...አንድ ቀን አምሽታ በጣም ሰክራ መጣች ያን ቀን ግን በጣም በሽቄ ስለነበር በቃ እኔ ከዚህ በኃላ እኔና አንቺ አብረን መሆን አንችልም እናቴ ጋ እሄዳለው አልኳትና እናቴ ክፍል አድሬ ጠዋት ሻንጣዬን አዘጋጅቼ ወደ እናቴ ቤት ሄድኩ..... የእኔና የሜላትን እንደዚህ መሆን ሰው ሲሰማው እጅግ ልገረምበት ይችላል እንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ሲበረክት ፍቅር ይጨምራል ይላሉ ግን ውሽት ነው ገንዘብ ሲበረክት ፍቅር ይጠፋል....እኔና ሜላት በድህነቴ የነበረን ፍቅር እጅ በጣም ደስ ይል ነበር ገንዘብ ስናፈራ ብር ወደኛ ሲመጣ ግን ፍቅራችን ተሸረሸረ ...ልጃችንን እንኳን በፍቅር ማሳደግ አቅቶን ሁለታችንም በተለያየ መንገድ መጎዝ ጀመርን.... ብዙውን ጊዜ ቅዱስ እናቴ ጋ ነው የሚውለው ሜላትም ስትፈልግ ትወስደውና አሷ ጋ አድሮ ውሎ ይመጣል ... እኔና ሜላት አንድ ነገር ተነጋግረናል ከቤት ሰወጣ ...መጠጧን ትታ ወደራሷ ተመልሳ ...ትዳራችንን ለመቀጠልም ሆነ ለመፋታት እንደምንወስን ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ምንም ነገር መወሰን እንደማልችል ነግሪያት ነበር ... ሜላት ሁሉንም ነገር አየችው ለሳምንታት ያክል እኔ እየተደበቅሁ እያየኃት እሷ እንዳታየኝ እየተጠነቀቅሁ ስከታተላት ከረምክ ..በጣም ተጎሳቁላለች የሚገርመው የያዘቻቸው ጏደኞች እልም ያሉ ጠጪዎች ናቸው አብዛኞቹ እንደ ሹገር ማሚ ነገር ይሰራሉ ..የተረፍት ደግሞ አግብተው የፈቱ ናቸው...ከእነሱ ጋር ሆና ነው እንደዚህ ቅይርይር ያለችብኝ ... አንድ ቀን ማታ ከሰራ ስትወጣ ተከትያት ሄድኩኝ ሆቴል ውስጥ ስትገባ አብሪያት ገባሁ ...በጣም በብዛት ተሰብስበው ወደ ሚጠጡ ሴቶች ተደባልቃ ቁጭ አለች ...ብርጮቆ አምጥተው ቀዱላት ..በአንድ ትንፋሽ ጭልጥ አድርጋ ጠጣችው አጠጣጧ ያስፈራል ...ሳትሰክር ማናገር ስለነበረብኝ ...ተጠጋኃቸው ስታየኝ ደነገጠች ሁሉንም ሰላም አመሻችሁ አልኳቸው ...እዚህ ምን ትሰራለህ ብላ አፈጠጠችብኝ...ምንም አልሰራም መቼም መጠጥ እንደማልጠጣ ታውቂያለሽ ግን አንዳንድ ነገሮችን አንቺ ያላወቅሻቸውን ላሳውቅሽ ብዬ ነው አልኳት....ሴቶቹ ግራ ተጋቡ እሷም አይኗን አፈጠጠችብኝ..... ✍✍✍ይቀጥላል✍🏻......... ♥ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ እና ሼር ያድርጉ❤️🙏 :*:*••••••™🌸:*:*🌹:*:🌸™•••••••*:*: ••●◉Join us share @Officalmina @Officalmina ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Показать все...
💔የድሀ ልጅ ፍቅር ❣️ 🌺🌺ምዕራፍ ሁለት ___🌸🌸ክፍል 23 ከስራ አምሽቼ እናቴ ጋ ሄጄ ማምሸት እያማረኝ ሜላቴ ቀድማኝ ከገባች ትናደድብኛለች ብዬ ቅር እያለኝ ወደ ቤት ሄድኩኝ ,...እቤት ስገባ ግን ማንም ሰው የለም ...ቤቱ ጠዋት ትቼው እንደወጣሁት ነው ምንም የተቀየረ ነገር የለውም,...እናቴ ክፍል ስገባ የተኛንበት አልተስተካከለም,..ልብሳችንን አነሳስቼ መኝታውን አነጠፍኩት.... ወደ እኔና ሜላት ክፍልም ስገባ አልተነጠፈም የቀየረችውን ልብስ እንኳን አላነሳችውም... እሱንም አስተካከልኩ ስልኬ ቻርጅ ስላልነበረው እሱን እያደረግሁ ቤቱን ማስተካከል ጀመርኩ.... ማታ እራት የተበላበት ሰአን አልታጠበም,...ብቻ በአጠቃላይ ቤቱ በጣም ያስጠላል ያስፈራል... እሪ ብዬ ብጮህ ደስ ይለኝ ነበር ግን አልችልም..... ስራውን ሰርቼ ጨረስኩ እራት መስራት ፈለግሁ ግን ቅድሚያ ሜላት ጋ ልደውል ብዬ ስልኬን ከፈትኩት ሜላት ደውላ ነበር ግን ባትሪ ዘግቶብኝ ስለሆነ አላየሁትም ...መልሼ ደወልኩ አታነሳም ትንሽ ልጠብቅ አልኩ ....ግን ማንም የመጣ ሰው አልነበረም ...በጣም ተበሳጨሁ ተናደድኩ ግን በቃ ትዕግስት ይኑርህ እያለች ነው እያቴ ያሳደገችኝ..... ጠብቄ ጠብቄ ሰው ሳይመጣ የሜላት ስልክ አልነሳ ሲለኝ እናቴ ጋ ደወልኩ ሰላም አልኳት እቤት ማንም እንደሌለ ነገርኳት እራት ቀርቧል ና አለችኝ ...ተነስቼ እናቴ ጋ ሄድኩ .... እናቴ ጋ እራት በልቼ ትንሽ ተጫውቼ ወደ ቤት ተመለስኩ ... እቤት ስመለስ ሜላት ተኝታ አገኝኃት ቅዱስም ተኝቷል ..... ወደ ሜላት ተጠግቼ ሜላት አልኳት ምን ላድርግህ ?አለችኝ በጣም ደነገጥሁ....ስልክ ስደውልልሽ አታነሽም ስጠብቃችሁ ስትቀሩብኝ እናቴ ጋ ሄድኩ አልኳት ...አሪፍ ነው ደክሞኛል ማረፍ እፈልጋለው አለች....ሜላት እየጠየቅሁሽ ነው ስደውልልሽ ስልክ አታነሽም ለምንድነው? አልኳት.... ሜላት በጣም በመቆጣት ከመኝታዋ ተነስታ ቁጭ አለችና በመጀመርያ ስደውል ለምን አላነሳህም አለችኝ.... ስልኬ ባትሪ ዘግቶ ነበር እንደከፈትኩ ስደውልልሽ አታነሺም ሲጨንቀኝ እናቴ ጋር ሄድኩ አልኳት.... አሪፍ ነው እኔም ስልኬን መኪና ውስጥ እርስቼው ስለነበር ነው አሁን ደክሞኛል ደህና እደር ብላኝ ትታኝ ተኛች..... ነገሩን ላለማክረር ብዬ እኔም ዝም አልኩ ልብሴን ቀይሬ ተኛሁ .....ጠዋት ስነሳ ሜላት ተኝታ ነበር እስከዛሬ እናቴ ነበረች በጠዋት ተነስታ ቁርስ ሰርታ ቅዱስን አልብሳ እኛን የምትቀሰቅሰን አሁን ግን ያ የለም..... እኔም ተነስቼ ቅዱስን ቀስቅሼ ሜላትን ቀሰቀስኳት .... ቅዱስን ልብሱን አልብሼው እኔም ለበስኩ ...ድንገት ቅዱስ አባቢ አባቢ እንደ ትላንትናው እነ እቴቴ ጋ ቁርስ እንበላለን አለኝ?..... በጣም ደነገጥኩ ሜላት አፈጠጠችብኝ ... አይ ቅዱሴ ዛሬ ማሚ የሰራችውን ቁርስ ነው የምንበላው እሽ አልኩትና ወደ መኝታ ክፍል ገባሁ...ሜላት ተከትላኝ መጣች ...ትላንት በጠዋት ልጄን ይዘህ የሄድከው የት ነው አለችኝ ... እናቴ ጋ.. አልኳት ...በጣም ተበሳጨች ግን እናቴን እንደምወዳት ስለምታውቅ ምንም ማለት አልፈለገችም ነበር..... ሜላት ቁርስ እስከምትሰራ እኔ መኝታችንን አነጠፍኩ የሚስተካከለእን አስተካከልኩ ...ቁርስ ደርሶ በልተን ቅዱስን ይዜ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ በዛውስራዬ ገባሁ ....ስራ ውዬ ቅዱስን ወንድሜ ከትምህርት ቤት አውጥቶት ስለነበር ቅዱስን ላመጣ ሄድኩ ...በዛውም እራት ሳትበላ አትሄድም በለውኝ እራት በልቼ ወደ ቤት ሄድኩ .... እቤት ስንደርስ ሜላት እራት አዘጋጅታ ጠበቀችን ቅዱስ ጠግቧል እኔም ጠግቤያለው ግን በቃኝ ማለት ስላልፈለግሁ ቁጭ አልኩ..... ቅዱስ ወደ መኝታ ክፍል ሲገባ .. ሜላት በጣም ተቆጥታ ከዚህ በኃላ አንዱን ቤት ምረጥ እሺ ወይ እዚህ ወይ እናትህ ቤት ... ስትል ድንገት ቅዱስ መኝታ ቤት በር ላይ ሆኖ ሲሰማ አየሁት........ ✍✍✍ይቀጥላል✍🏻......... ♥ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ እና ሼር ያድርጉ❤️🙏 :*:*••••••™🌸:*:*🌹:*:🌸™•••••••*:*: ••●◉Join us share @Officalmina @Officalmina ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Показать все...
💔የድሀ ልጅ ፍቅር❣️ 🌺🌺ምዕራፍ ሁለት .....,,,🌸🌸ክፍል 22 እኔና ቅዱስ ወደ ቤት ተመለስን እቤት ስደርስ ያጋጠመኝ ነገር ግን ያልጠበቅሁት ነገር ነበር ...እናቴ እራት ሰርታ ጠረቤዛው ላይ አስቀምጣ በትንሽዬ ወረቀት ይቅርታ ልጄ,,ብላ ፀፉልኝ አገኝሁት በጣም ደነገጥኩ,...እናቴ ክፍል ተንደርድሬ ስገባ የእናቴም የወንድሜም ልብስ የለም,.እናቴ ቤቱን ትታ ሄዳለች ...በጣም ተበሳጨሁ እንባ ተናነቀኝ ቅዱስ ዝም ብሎ ቆሞ ያየኛል ..... በዛው ቅፅበት ሜላት መጣች ቤቱ እርጭ ብሏል ግራ ገባት የደነገጠች ትመስላለች ደህና ዋላችሁ አለች...ካጎነበርኩበት እንባዬን ጠርጌ ቀና በማለት ሰልይምታ ሰጠኃት ...ውዱሴም ማሚ ብሎ ሄዶ ተጠመጠመባት አቅፋ ሳመችው ...እንዴት በጊዜ እንደመጣች ገርሞኛል ግን ልጠይቃት አልፈለግሁም ..እንዳቀተቀርኩ ዝም አልኳት... ሜላት ዝምታው ስለጨነቃት ምን እንደተፈጠረ ጠየቀችኝ እኔ ሳልሆን ቅዱስ እቴቴ ሌላ ቤት ሄደች..ስትናፍቀኝ መጥቼ አይሀለው ስናፍቅህ ና እሽ ብላኝ ሄደች አላት....እኔ ምንም አልተነፈስኩም..ሜላት ደነገጠች ..ትላንት ለተናገርኳቸው ነገር ይቅርታ ልጠይቃቸው ነበር በጊዜ የመጣሁ በጣም አዝናለው አለች,.ምንም ሳልላት ተነስቼ መኝታ ክፍላችን ገባሁ... ልብሴን ቀይሬ እናቴ መኝታ ላይ ጋደም አልኩ,... ቅዱስ አባቢ ተነሳ እርቦኛል እራታችንን እንብላ አለኝ ....እንቢ ማለት ስላልፈለግሁ ተነስቼ ወደ ምግብ ጠረቤዛው ሄድኩ የቤቱ ቅዝቃዜ በጣም ያስፈራል ለመጀመርያ ጊዜ ነው እንደዚህ ቅዝቅዝ አለ ቤት ውስጥ ስናመሽ ሜላትም ጨንቋታል እንዳታንይግረኝ ምን ትበለኝ ዝም እንዳትል ዝም ማለት አልቻለችም...እሽ ግን የት ነው የሄዱት እኛ እንውጣ እንጂ መቼ እነሱ ይውጥ አልኩ አለች..... ልጎእስ በእጄ የጠቀለልኩትን ትቼ ምንም ሳልል ከመቀመጫዬ ተነስቼ እጄን ታጠብኩና ደህና እደሩ ብዬ እናቴ ክፍል ገብቼ ተኛሁ..... ሜላት የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፍቷታል ቅዱስም አባቢ ካንተ ጋር መተኛት እፈልጋለው ብሎኝ አጠገቤ መጥቶ ተኛ,.....ሜላት የበላንበትን አንስታ ክፍላችን ገብታ ተኛች,በአይኔ እንቅልፍ ሳይዞር ነጋ ....እናቴ ጋ ያልደወልኩት ምንም የምለው ነገር ስለሌለኝ ነበር ምክንያቱም እናቴ ቅር ብሏታል ስለዚህ ደውዬ ምንም አልላትም... ዝም ብዬ አደርኩ,ጠዋት ከመኝታዬ ተነስቼ ቅዱስን አስነስቼ ልብሳችንን ቀያይረን ልንወጣ ስንል ሜላት ነቃች ... ወዴት ልትሄዱ ነው ቁርስ ልስራ ስትል አይ ተይው ውጪ እንበላለን ስራ እንዳይረፍድብሽ ብያት .ቅዱስን ይዝኡ ወጥይሁ...ወንድሜ ጋ ደውዬ የቤታቸውን አድራሻ ተቀብዬ እናቴ ጋ ሄድኩ..እናቴ ጋ ደርሰን ገና እናቴን ሳያት ቅዱስ ከመኪናው ወርዶ እየሮጠ እቴቴ ቁርስ ደርሷል እርቦኛል አላት ,...ና ልጄ ቁርስ ደርሷል ብላ እኔን ሰላም ብላኝ ወደ ውስጥ ገባን ....እናቴን ሳያት እንባ ተናንቆኛል ግን በፍፁም ማልቀስ አልፈለግሁም ምክንያቱም እናቴ ሳለቅስ ማየት እንደማትወድ ስለማውቅ..... እናቴ የፊቷ ፈገግታ ምንም አልቀነሰ ...ገብተን የተዘጋጀውን ቁርስ በላን ወንድሜ ጎበዝ ነው ቤቱን አሟልቶታል,...ቁርስ በልተን ቅዱስን ይዜ ልወጣ ስል ሜላት ደወለች.ቅዱስ ከትምህርት ሲወጣ እኔ አወጣዋለው አለችኝ እሽ ብያት ቅዱስን ትምህርት ቤት አስገብቼ እኔም ወደ ስራዬ ገባሁ,..ስራዬን እንደምንም ስሰራ ዋልኩኝ .....ማታም ወደ ቤት ሄድኩ እቤት ስደርስ ግን ማንም ሰው አልነበረም...... ✍✍✍ይቀጥላል✍🏻......... ♥ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ እና ሼር ያድርጉ❤️🙏 :*:*••••••™🌸:*:*🌹:*:🌸™•••••••*:*: ••●◉Join us share @Officalmina @Officalmina ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.