cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

Больше
Рекламные посты
985
Подписчики
-124 часа
+27 дней
+1930 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
✝️✝️✝️ ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ - - - ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን:: ✝️✝️✝️ ☞ከበዙ ተአምራቱ አንዱን፡- =>ጻድቁ #አባ_ዓቢየ_እግዚእ በገዳማቸው #ተንቤን (መረታ) ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ "አባቴ! የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?" አለቻቸው:: ጻድቁም በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው : በመስቀላቸው ባርከው ሰጧት:: +ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና "ልጠጣው" ብላ የተቀበለችውን ማይ (ጸበል) ልትጠመቅበት (ልትጸበልበት) ወሰነች:: ባልንጀራዋንም "በላዬ ላይ አፍሺልኝ" ስትል አዘዘቻት:: +ባልንጀራዋም "እሺ" ብላ ልታፈስላት (ልትጸብላት) በፋጋ (ግማሽ ቅል) ያለውን ጸበል አነሳች:: ልታፈሰው ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ 2ቱም ደነገጡ:: ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና:: +ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ:: ከውጭ ሆነውም "አባ! አባ! የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ" አሏቸው:: ጻድቁም እንዳላዋቂ "ምን አጠፋችሁ?" ሲሉ ጠየቁ:: +"አባታችን! ምንም አላጠፋንም:: ብቻ አፍሺልኝ ብየ ስሰጣት እንዲህ ሆነ" ስትል አንዷ መለሰች:: ጻድቁ ግን በየውሃት "ልጆቼ! ሁሌም : 'ምንም አላጠፋንም' አይባልም:: ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና:: + . . . አንቺም ልጄ! እኔን ያልሺኝ 'የምጠጣው ጸበል ስጠኝ' ነበር:: ግን ልትጸበይበት ወደድሽ:: ስሕተትሽ ከዚህ ይጀምራል:: (የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና) ¤በዚያ ላይ "አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . . ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም::" (ዮሐ. 8:44) + . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን 'አጥምቂኝ' አልሻት:: ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ ተለውጦባቹሃል" ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ:: "እፍ" ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ ተመለሰ:: ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው ለጻድቁ ሰገዱ:: =>ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን:: <<< በበዓሉም (ግንቦት 19 ቀን) ጐንደር በሚገኘው ቤተ መቅደሳቸው ተገኝተን እናክብራቸው ! >>> <<< ከጻድቁ በረከት አይለየን !! >>> ✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞ https://t.me/felegetibebmedia
Показать все...
ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

Фото недоступноПоказать в Telegram
✞✝️✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✝️✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +✝️+ አባ ዓቢየ እግዚእ +✝️+ ❖ጐንደር ከተማ ነዋሪ ከሆኑ: ወይም ከተማዋን የሚያውቁዋት ከሆነ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎ:: (እንደ ወትሮው ሁሉ) ከተማዋ ውስጥ ጅብና እባብን የመሠሉ አራዊት ነዋሪውን ሲገድሉ: ወይም ሲያቆስሉ ተመልክተው: ካልሆነም በታሪክ ሰምተው ያውቃሉ? ☞ መልስዎ "በጭራሽ አላውቅም" እንደሚሆን እገምታለሁ:: (ምክንያቱም ሆኖ አያውቅማ!) +ነገሬን እንዲረዱኝ ሌሎች የሃገራችን ዋና ዋና ከተሞችን ልብ ይበሉልኝ:: እንኳን በሌሊት በቀንም አራዊቱ አይጠፉባቸውም:: "ታዲያ ጐንደር ከተማ ውስጥ ጅብ የማይገባው: እባብና ጊንጥ ሰው የማይገድለው ግን ለምን?" ካሉ በጻድቁ በአባ ዓቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን ምክንያት ነው:: (ሁሉም የሃገራችን ከተሞች የተባረኩ መሆናቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው) +ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- +አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው 'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጉመ መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው" ማለት ነው:: +ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ:: ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኩሰዋል:: +በገዳሙ በጾም: በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል:: በጊዜው በ40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር:: +ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል:: ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ ስብከታቸው ነው:: +አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ 10 ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ3 ቀናት ባለመጉደሉ ከ1,000 በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ- አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ:: +ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከ1,000 በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይሕም ዘወትር ነሐሴ 10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል:: +ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: +በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሠል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይሕንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ:: +የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም:: በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጓል:: +ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል:: ይሔው እኛ ምን ብንከፋ: ጻድቁንም ብንረሳቸው እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ ይኖራል:: ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ (ጎንደር ቀበሌ 09 ኪዳነ ምሕረት) ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ ነው:: እንኳን በወርሃዊ በዓላቸው (በ19) ይቅርና በዓመታዊ በዓላቸው (ግንቦት 19) ለንግስ የሚመጣው ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል:: +አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው: 3 ሙታንን አስነስተው: ብዙ ድውያንን ፈውሰው: ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው: የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው: በ140 ዓመታቸው ግንቦት 19 ቀን አርፈዋል:: የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው:: +<< ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ - - - ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን:: >>+ +<< ከበዙ ተአምራቱ አንዱን >>+ =>ጻድቁ አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው #ተንቤን (መረታ) ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ "አባቴ! የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?" አለቻቸው:: ጻድቁም በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው : በመስቀላቸው ባርከው ሰጧት:: +ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና "ልጠጣው" ብላ የተቀበለችውን ማይ (ጸበል) ልትጠመቅበት (ልትጸበልበት) ወሰነች:: ባልንጀራዋንም "በላዬ ላይ አፍሺልኝ" ስትል አዘዘቻት:: +ባልንጀራዋም "እሺ" ብላ ልታፈስላት (ልትጸብላት) በፋጋ (ግማሽ ቅል) ያለውን ጸበል አነሳች:: ልታፈሰው ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ 2ቱም ደነገጡ:: ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና:: +ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ:: ከውጭ ሆነውም "አባ! አባ! የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ" አሏቸው:: ጻድቁም እንዳላዋቂ "ምን አጠፋችሁ?" ሲሉ ጠየቁ:: +"አባታችን! ምንም አላጠፋንም:: ብቻ አፍሺልኝ ብየ ስሰጣት እንዲህ ሆነ" ስትል አንዷ መለሰች:: ጻድቁ ግን በየውሃት "ልጆቼ! ሁሌም : 'ምንም አላጠፋንም' አይባልም:: ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና:: + . . . አንቺም ልጄ! እኔን ያልሺኝ 'የምጠጣው ጸበል ስጠኝ' ነበር:: ግን ልትጸበይበት ወደድሽ:: ስሕተትሽ ከዚህ ይጀምራል:: (የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና) ¤በዚያ ላይ "አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . . ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም::" (ዮሐ. 8:44) + . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን 'አጥምቂኝ' አልሻት:: ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ ተለውጦባቹሃል" ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ:: "እፍ" ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ ተመለሰ:: ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው ለጻድቁ ሰገዱ:: =>ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን:: ❖አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይሠውርልን:: ❖ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) 2.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም (የ12ቱ ሐዋርያት መቃብር ከጌታ የተገለጠላቸው ኢትዮዽያዊ) 3.አቡነ ብስጣውሮስ ዘሐይቅ እስጢፋኖስ (ኢትዮዽያዊ) 4.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ታላቁ (7 ጊዜ ሙቶ የተነሳ) 5."805,007" ሰማዕታት (በአንድ ቀን ብቻ የተገደሉ) 6.አባ ይስሐቅ ገዳማዊ ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት 2፡ ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት 3፡ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ 4፡ አባ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ
Показать все...
🌿እንኩዋን ለጥንተ በዓለ ዸራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) እና ለጻድቁ አባ ገዐርጊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝በዓለ ዸራቅሊጦስ 📖ከዚሕ በፊት እንደተመለከትነው የጌታችን ዓበይት በዓላቱ 2 ጊዜ (ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው) ይከበራሉ:: ዛሬም ከ1,978 ዓመታት በፊት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን እናስባለን:: ♱ ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- 📝ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል *ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ: *በማሕጸነ ድንግል ተጸንሶ: *በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: *ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕጻናት አድጐ: *በ30 ዘመኑ ተጠምቆ: *ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ: *በፈቃዱ ሙቶ: *በባሕርይ ስልጣኑ ተነስቶ: *በአርባኛው ቀን ያርጋል:: +ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው ነበርና በተነሳ በ50ኛው ቀን: በዐረገ በ10 ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው:: +እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች:: 120ው ቤተሰብ ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ በአምሳለ እሳት አደረባቸው:: +ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች: አሮጌ ሕሊና የነበራቸው ሐዲሶች ሆኑ:: በአዕምሮ ጐለመሱ: ቁዋንቁዋ ተናገሩ: ምሥጢርም ተረጐሙ:: በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ:: +ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሰዋል:: አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል:: ሳይሳሱም አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል:: "ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ: ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ: ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ::" እንዳለ ደራሲ:: +በዚህ ቀን 2 ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ:- 1."የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት:-" *እርሱ ከአብ የሠረጸ: ቅድመ ዓለም የነበረ: በባሕርይ ስልጣኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል የሆነ: የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን ነውና:: 2."ቅድስት ቤተ ክርስቲያን:-" *አብ ያሰባት: ወልድ በደሙ የቀደሳት: መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት: አንድም ቤት ናትና:: ዛሬ በጉባዔ ተመስርታለች:: ♱ አባ ገዐርጊ =>በዚችም ዕለት የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ አባ ገዐርጊ አረፈ።ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገን ነው ወላጆቹ ደጎች ጻድቃን ናቸው።በአደገም ጊዜ የወላጆቹን ከብቶች የሚጠብቅ እረኛ ሆነ።ሁል ጊዜም የምንኵስና ልብስ ይለብስ ዘንድ በልቡ ይመኝ ነበር። ዐሥራ አራት ዓመትም በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ አነሣሳችው በጎቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ።እየተጓዘም ሳለ ከሩቅ የብርሃን ምሰሶ አየ ወደ ወንዝ እስከ ደረሰ ድረስ ወደ ርሱ ሔደ ከዚህም በኃላ ያ የብርሃን ምሰሶ ከእርሱ ተሰወረ። ያንንም ወንዝ በተሻገረ ጊዜ በሽማግሌ አምሳል ሰይጣን ተገለጠለትና ልጄ ሆይ ዕወቅ ስለ አንተ ልብሱን ቀዶ አባትህን አየሁት እርሱም ያዝናል ያለቅሳል ተመልሰህ የአባትህን ልብ ልትአጽናና ይገባሃል።የዱር አውሬ ነጥቆ የበላህ መስሎታልና አለው። አባ ገዐርጊም ደንግጦ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ከዚህም በኃላ የከበረ ወንጌል ከእኔ ሊሆን አይገባውም ደቀ መዝሙሬም ሊሆን አይችልም ብሏል ብሎ አሰበ።ይህንንም በአለ ጊዜ ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ።አባ ገዐርጊም ሰይጣን እንደ ሆነ አወቀ በዚያን ጊዜም ያ የብርሃን ምሰሶ ደግሞ ተገለጠለት የእግዚአብሔርም መልአክ በመነኵሴ አምሳል አብሮት ተጓዘ ቅዱሱም መልአኩን ተከተለው እርሱም ከአባ አርዮን ገዳም አደረሰው።አባ ገዐርጊም ከአንድ ጻድቅ ሰው መነኵሴ ጋራ በዚያ ዐሥራ አራት ዓመት ወጥሳይቀምስ ወይን ሳይጠጣ የአትክልት ፍሬም ቢሆን በዚህ በዐሥራ አራት ዓመት ያህል ከሚቀመጥ በቀር አልተኛም። ተጋድሎውንም በጨመረ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ሥጋህ እንዳይደክም በመካከለኛ ገድል ተጋደል ብሎሃል ጌታ።ከዚህም በኃላ ሊሠራው የሚገባውን ሥርዓት ሠራለት ።ሁል ጊዜም እስከሚመሽ እንዲጾም ትንሽም እንጀራን እንዲበላ ከአራት ሰዓት እስከ መንፈቀ ሌሊት ስለ ሥጋው ዕረፍት እንዲተኛ በቀረው ሌሊት እስቲነጋ ተግቶ እንዲጸልይ። በዚህም ተጋድሎ ብዙ ዘመናት እየተጋደለ በኖረ ጊዜ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ሊኖር ወዶ በጫካ ውስጥ እየተመላለሰ ሁለት ዓመት ኖረ።ከዚህም በኃላ ጌታ ተገለጾለት ወደ ቦታው እንዲመለስ አዘዘው።ያን ጊዜም አምላካዊት ኃይል ከከበሩ መክሲሞስና ደማቴዎስ ገዳም አደረሰችው እርሷም ለደብሩ አቅራቢያ ናት። ወደ ደብሩም በተመለሰ ጊዜ በዚያን ወቅት አብርሃም ከዓለም ወደዚያ ገዳም መጥቶ ሁለቱም ተገናኙና በአንድነት ተስማምተው የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ወደ ሆነ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሱ።እርሱም ቦታ ሰጥቷቸው በውስጡ ኖሩ ያ ቦታም እስከ ዛሬ ታውቆ ይኖራል ። ያቺም ዋሻ በግቢግ ትባላለች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐለት የሆነ ጣሪያዋን ሠንጥቆ ወደ እነርሱ የወረዳበት ናት ።እነርሱም ሰገዱለት ሰላምታም ሰጥቷቸው አጽናንቷቸው ከእርሳቸው ዘንድ ዐረገ።በዚያችም ጌታችን በወረደበት መስኮት ብርሃንን አዩ እስከ ዛሬም የተከፈተች ሁና ትኖራለች። እሊህ ቅድሳንም ለመነኰሰኘሳት የሚሆን ብዙ ድርሳናትንና ብዙ ተግሣጻትን ደረሱ።ለአባቶቹ የሚታዘዘውንና የሚገዛውን አመሰገኑት።ከዚህም በኃላ አባ አብርሃም ጥር ሁለት ቀን አረፈ።ከእርሱ በኃላም የከበረ አባ ገዐርጊ በዚች በግንቦት ወር በዐሥራ ስምንት ቀን አረፈ።መላ ዕድሜውም ሰባ ሁለት ዓመት ሆነ።በዓለም ዐሥራ አራት ዓመት በምንኩስና ኃምሳ ስምንት ዓመት ነው።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትሁን አሜን። =>በዚችም ዕለት የሰማዕት ሲኖዳ መታሰቢያው ነው በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። =>አምላከ ገዐርጊ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ለኃጥአን ባሮቹ ያድለን:: =>ግንቦት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን ሐዋርያት ወአርድእት 2.አባ ገዐርጊ ገዳማዊ 3.ቅዱስ ሲኖዳ ሰማዕት =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን) 3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ 4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ =>+"+ በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ:: ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው:: እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው:: በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው:: በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው:: መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር:: +"+ (ሐዋ. 2:1-4) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/felegetibebmedia
Показать все...
ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

Показать все...
ለነብሴ ነብሷነሽ በዘማሪ ዲ/ን አስማማው#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ @felegetibebmedia

እንኳን ወደ ፈለገ ጥበብ ሚዲያ በሰላም መጣችሁ ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች፣ መዝሙራት፣ ምክረ አበው፣ ብሒለ አበው፣ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች፣ ሃይማኖታዊ ጥቅሶችና አባባሎች እንዲሁም ትምህርታዊ የቀጥታ ሥርጭቶች የሚቀርቡበት መድረክ ነው። ማንኛውንም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን የተመለከተ ቁም ነገር ሲፈልጉ የመጀመሪያ መድረሻዎን ፈለገ ጥበብ ሚዲያ ቢያደርጉ ይጠቀማሉ። የቤተ ክርስቲያናችንን መሠረተ እምነት፣ ሥርዓት፣ ትውፊትና ታሪክ መማሪያና ማስተማሪያ ወደሆነው የኢንተርኔት ዐውደ ምሕረት እንኳን ደህና መጡ። የፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርትቤት ሾሻል ሚዲያን ይቀላቀሉ YOUTUBE :

https://youtube.com/@felegetibebmedia

TikTok :

https://www.tiktok.com/@felegetibeb?_t=8YPpcRvvdGY&_r=1

Facebook :

https://www.facebook.com/felegetbe?mibextid=ZbWKwL

Instagram :

https://www.instagram.com/invites/contact/?i=n5xks7h4rx64&utm_content=ohboikq

Telegram channel :

https://t.me/felegetibebmedia

             #Telegram ፈለገ ጥበብ photography(የፎቶ ማህደር)( ፎቶ  ብቻ የሚለቀቅበት  ቻናል)

https://t.me/felegetibebimage

https://t.me/felegetibebimage

youtube channel;

https://www.youtube.com/channel/UC6naKn4aOxVEht6lW-whftA

Welcome to Arts Media. This channel is orthodox and offers live lessons, songs, arts and various programs for Tewahedo children. Congratulations on joining our channel.

Фото недоступноПоказать в Telegram
🌿እንኳን ለታላቁ የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✝በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ♱ቅዱስ ኤዺፋንዮስ 📝ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ጽድቅ ከቅድስና : ድርሰት ከጥብቅና የተሳካለት አባት ነው:: "ኤዺፋንያ" ማለት የመለኮት መገለጥ ሲሆን "ኤዺፋንዮስ" ማለት ደግሞ ምሥጢረ መለኮት የተገለጠለት ማለት ነው። 💡ቅዱስ ኤዺፋንዮስ የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ አይሁዳውያን ቤተሰቦች ቤተ ገብርኤል ውስጥ ነው። ቤተሰቦቹ ከአንድ አህያ በቀር ምንም የሌላቸው ድሆች ነበሩ። በዚያ ላይ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እህቱ ጋር በረሃብ ሊያልቁ ሆነ። ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ አህያው ክፉ ነበርና ሊሸጠው ገበያ አወጣው። 📝ፊላታዎስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ለግዢ ሲደራደሩ አህያው የኤዺፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው:: በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ክርስቲያኑ በትእምርተ መስቀል አማትቦ አዳነው:: በፈንታው ግን አህያው ሞተ:: ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ እያደነቀ ሔደ። 📝ከቆይታ በኋላ ሀብታም አጎቱ ገንዘቡን አውርሶት በመሞቱ ገና በ16 ዓመቱ ባለጠጋ ሆነ:: ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር። 💡አንድ ቀን ደግሞ ሉክያኖስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ሲሔዱ ነዳይ አገኙ:: ባለጠጋው ኤዺፋንዮስ አለፈው:: ያ ድሃ ክርስቲያን ግን የለበሳትን አውልቆ መጸወተው:: በዚሕ ጊዜ መልዐኩ መጥቶ የብርሃን ልብስ ሲያለብሰው ኤዺፋንዮስ ተመለከተ። 📝ኤዺፋንዮስ ጊዜ አላጠፋም:: ከእህቱ ጋር በክርስቶስ አምኖ ተጠመቀ:: ሃብት ንበረቱን ግማሹን መጸወተ:: በተረፈው ደግሞ መጻሕፍትን ገዝቶ ወደ አባ ኢላርዮን ገዳም ገባ:: በዚያም መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስ በፍጹም ትጋትና ቅድስና ተጋደለ። በጸሎቱ ዝናም አዘነመ : ድውያንን ፈወሰ : ብዙ ተአምራትንም አደረገ። 📝 እግዚአብሔርም ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ሽቶታልና በቆዽሮስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ:: ብሉይ ከሐዲስ የወሰነ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ:: በሺሕ የሚቆጠሩ ድርሳናትን ደረሰ:: በአፍም በመጽሐፍም ብሎ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ቤተ ክርስቲያን "ጠበቃየ" ትለዋለች። 📝ከደረሳቸው መጻሕፍት መካከል "ሃይማኖተ አበው ዘኤዺፋንዮስ : መጽሐፈ ቅዳሴውና አክሲማሮስ (ስነ ፍጥረት)" ዛሬም በቅርብ ይገኛሉ:: ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ተመላልሶ በ406 ዓ.ም. ዐርፏል:: እድሜውም 96 ዓመት ያህል ነበር። 🤲አምላካችን ከቅዱሱ ሊቅ በረከት ያድለን! 🗓 ግንቦት 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ) 2. ቅዱስ ኢላርዮን ገዳማዊ 3. አባ ሉክያኖስ ጻድቅ 4. ቅዱስ ፊላታዎስ ክርስቲያናዊ 🗓 ወርኀዊ በዓላት 1. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት) 2. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ) 3. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ 4. አባ ገሪማ ዘመደራ 5. አባ ዸላሞን ፈላሢ 6. አባ ለትጹን የዋህ 📖"የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል። እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው። እኛ ግን የማይጠፋውን። ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም። ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም። ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጐሰምሁ አስገዛዋለሁ።'' (1ቆሮ. 9:25) ✨ወስብሐት ለእግዚአብሔር✨
Показать все...