cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ዘ Gospel Light💥

"፤ እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።" (የማርቆስ ወንጌል 16: 15) "And he said to them, Go you into all the world, and preach the gospel to every creature."(AKJV-Mark 16:15) .

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
174
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

❤እግዚአብሔርን ማፍቀር❤ 💢እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በፍቅር የሚወድ አምላክ ነው 💥እግዚአብሔር የሚወዳቸው ፣ በመልኩ እና በምሳሌው የፈጠራቸው ሰዎች በኃጥያት ምክንያት ከእርሱ ተለዩ 😍ነገር ግን እግዚአብሔር ሰውን በፍቅር ስለሚወደው አንድያ ልጁን ክርስቶስ ኢየሱስን ለሞት አሳልፎ በመስጠት የኃጥያትን ዋጋ ክፍሏል ዩሐ3÷16 💯የተከፈለላቸውን የኃጥያት ዋጋ በማመን የእርሱ ልጆች የሆኑት ደግሞ እርሱን እንዲወዱት እንዲሁም እንዲያፈቅሩት ይፈልጋል ❤እግዚአብሔር እርሱን በፍጹም ልባችን በፍፁም ሃሳባችን በፍጹም ኃይላችን በፍፁም ሁለንተናችን እንድንወደው ይፈልጋል💯 ማር12÷30 💥ትርጉም ያለው ህይወት ያለው እግዚአብሔርን በማፍቀር ውስጥ ነው 🔥እግዚአብሔር እራሱን የሚገልጥላቸው እርሱ በእውነት ለሚወዱትና ለሚያፈቅሩት ነው 🥰እግዚአብሔር የሚወዱ በተገለጠ የእርሱ መገኘት ይመላለሳሉ ❤ፍቅር ከሁሉ ነገር ይበልጣል ደግሞም ከሁሉ ነገር ይቀድማል ❣ያለ ፍቅር የምናደርገው ነገር ሁሉ የእግዚአብሔርን ልብ አይስበውም አያስደስተውም 1ቆሮ13÷1-13 💯ከእግዚአብሔር በላይ የምንወደው ነገር እንዲኖር እግዚአብሔር አይፈልግም 💫ህይወታችን በእግዚአብሔር ፍቅር የተሞላ ሊሆን ይገባል 👌ህይወታችን የእግዚአብሔር ፍቅር የተቆጣጠረው ሊሆን ይገባል 🥰ሃሳባችን እግዚአብሔር በመውደድ የተሞላ ሊሆን ይገባል ‼️እግዚአብሔርን ወድዶ ወንድሙን የሚጠላ ማንም የለም። ስለዚህ እግዚአብሔርን መውደዳችን የሚታየው ወንድሞችን በመውደዳችን ነው።1ዩሐ4÷7-12 😍ሁለንተናችን እግዚአብሔርን በመውደድ ሊሞላ ያስፈልጋል ፤ በሁለንተናችን እርሱን ለመውደድ ተጠርተናል 💢በእርሱ ፍቅር የተነደፉ ትውልዶችን እግዚአብሔር በዘመናችን ያስነሳል💯 ❤አሜን❤
Показать все...
🏁ወንጌላዊው ቴዎፍሎሰ ተስፋዬ የተዘጋጀ ትምህርት ●በምድር ላይ የመኖራችን ዓላማ ምንድነው? በዓለማችን ሰዎች በምድር ላይ የመኖራቸውን ትርጉም ለማግኘት 5 መሠረታዊ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። (1) እኔ ማኝ ነኝ? (2) ከየት መጣሁ? (3) እዚህ ምን አደርጋለሁ? (4) ምን ማድረግ እችላለሁ? (5) ወዴት እሄዳለሁ? እነዚህን ጥያቄዎች ሊመልስ የቻለ ምድራዊ ፍልስፍናም ሆነ ሐይማኖት እስካሁን አልተገኘም። ሰዎች ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ሲሉ በራሳቸው መንገድ ሄደው ብዙ ችግር ውስጥ ውድቀዋል። እኔ ማን ነኝ? ለሚለው ጥያቄ መልሱን ከሰው ከራሱ ማግኘት መቼም ቢሆን አይቻልም። ምክንያቱም አንድ የተፈጠረ ነገር ማንነቱን የሚያገኘው ከራሱ ሳይሆን ከፈጣሪው ነውና። ስለዚህ ይህን መሠረታዊ ጥያቄ ከፍጥረት ለማግኘት መጣር ከንቱ ሙከራ ነው ማለት ነው። ለምሳሌ ስለ ሞባይል ሊናገር የሚችለው ሞባይልን አስቦ የፈጠረው ሰው እንጂ ሌላ አይደለም። በእጄ ላይ ያለው ይህ ሞባይል ነው እንበል። የሞባይልን ምንነት እና ዓላማ አገልግሎቱን እና ጥቅሙን ሊነግረን የሚችለው የፈጠረው ሰው ብቻ ነው። (1) ሞባይል ምንድነው? (2) ከየት ነው የመጣው? (3) ምን ይጠቅማል? (4) ሌላስ ምን ማድረግ ይችላል? ለእነዚህ ሌሎችም መሰል ጥያቄዎች ትክክለኛውን ምላሽ ሊሰጠን የሚችል ሞባይል የፈጠረው ሰው ብቻ ነው። የሚገርመው ነገር ሞባይልን የፈጠረው ሰው ሁልጊዜም ከሞባይሉ ጋር አሽጎ የሚሸጠው ማኑዋል የሚባል መጽሐፍ አለው። ●●●●●●●●ይቀጥላል●●●●●●●
Показать все...
🇨. በመሳፍንት ዘመን የነበሩ ነፃ አውጪ መሪዎች መሳፍንት/Judges/ መሳፍንት፤ በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ ነገሥታት በእስራኤል ከመሾማቸው በፊት መስፍን የተባለው ከንጉሥ ዘር የሆነ ሰው ሳይሆን አገሪቱን ከጠላት ወራሪ ሀይል የሚያድን አዳኝ ጀግና ነበር። የእስራኤል ሕዝብ ወደ ርስት አገራቸው ከገቡና ኢያሱ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ትተው የአገሩን አማልክት በማምለክ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔር ተቈጣቸው፤ ወደ እርሱም ሊመልሳቸው ብሎ ለሚማርኩአቸው እርሱም ወራሪዎች አሳልፎ ይሰጣቸው ነበር። ወራሪ በመጣ ቊጥር እስራኤላውያን ተጨንቀው ተጸጽተውም ወደ እግዚአብሔር ይጮኹና ይጸልዩ ነበር። በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ይምራቸውና መስፍንንም አስነሥቶ ከሚማርኩአቸው እጅ ያድናቸው ነበር፤ መሳ.2፥11-19፤ 3፥9:15። እነዚህ የሚያድኑ መሳፍንት 14 ሲሆኑ ከኢያሱ መሞት ጀምሮ ሳኦል ንጉሥ ሆኖ እስኪሾም ድረስ 300 ዓመት ያህል አገሪቱን ጠበቁ። መሳፍንቱ የሚከተሉት ናቸው፦ ✔ ጎቶንያል (መሳ.3፥7-10) ✔ ግራኙ ናዖድ (መሳ.3፥12-30) ✔ ሰሜጋር (መሳ.3፥31) ✔ ነቢይት ዲቦራ እና ባርቅ (መሳ.4፥1-5፥31) ✔ ጌዴዎን (መሳ.6፥1-8፥35) ✔ አቤሜሌክ (መሳ.9፥1-57) ✔ ቶላ (መሳ.10፥1:2) ✔ ኢያዕር (መሳ.10፥3-5) ✔ ዮፍታሔ (መሳ.10፥6-12፥7) ✔ ኢብጻን (መሳ.12፥8-10) ✔ ኤሎም (መሳ.12፥11:12) ✔ ዓብዶን (መሳ.12፥13-15) ✔ ሶምሶን (መሳ.13፥1-16፥31) ከዚህ በላይ ያሉት መሳፍንት ለሁለት መክፈል ይቻላል፦ ታላላቅ መሳፍንት ታናናሽ መሳፍንት ➡ ጎቶንያል 1.ሴሜጋር ➡ ናዖድ 2.ቶላ ➡ ነቢይት ዲቦራ 3.ኢያዕር ➡ ጌዴዎን 4.ኢብጻን ➡ ሶምሶን 5.ኤሎም ➡ ዮፍታሔ 6.ዓብዶን ➡ ባርቅ ●●●●●●ይቀጥላል●●●●●●
Показать все...
ከፌስቡክ የተወሰደ ትምህርት ከእግዚአብሔር ሴት ነቢያት ዮዲት ተስፋዬ መልዕክት 🏁ክፍል-ሁለት ወንጌላት ስለ ኢየሱስ ስብዕና ምን ይላሉ? #.2ተኛ ኢየሱስ ሰው ልጆች ወዳጅ እና አፍቃሪ ነው። ኢየሱስ ሰዎች አጣርቶ መዝነው በሚወዱበት መንገድ አይደለም የሰው ልጆች የወደደው። ●የእርሱ ፍቅር ከሰዎች ምግባር ተነስቶ ሳይሆን አፍቃሪ ከሆነው ማንነቱ የጀመረ ነው። ኢየሱስ በሰው ልጆች ምላሽ ላይ ያልተመረኮዘ ፍቅር ነው ለሰው ልጆች ያለው፤ ሉቃ.15፥20። 1 ዮሐንስ.4 (1 John.4) 10፤“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” — 1ኛ ዮሐንስ 4፥10 ሰው ቅዱስ ከሆነው እግዚአብሔር ጋር ለመኖር አቅም የሰጠው የእግዚአብሔር አፍቃሪ የሆነ ማንነቱ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ያኖረን ፅድቃችን ሳይሆን ከምንም ያልተጀመረ ፍቅሩ ነው። ●ኢየሱስ በምድር ሰዎችን ያፀናናው የሀጢአትን ስርዓት የሰጠው ሰዎችን ይወድ ስለነበር በአርነታቸው ደስ ይሰኝ ስለነበረ ነው፤ ማቴ.1፥40። #.3ኛ በተቃውሞ ብዛት አልቆመም። ኢየሱስ ብዙ ትችቶች የደረሱበት ቢሆንም በደረሰበት ችግር እና ተቃውሞ በመፅናት እውነተኛነቱን አሳይቶናል። ●ኢየሱስ ተቃውሞ ብዙ ደጋፊዎች እና ተከታዮች በነበሩት ሰዓት ብቻ ሳይሆን አብረውት ያሉት ሁሉ ተበትነው የሞትን ጽዋ እየወሰደ ባለበት ሰዓት በተቃውሞ ውስጥ የአብን ፈቃድ ገልጦዋል፤ ሉቃስ 23፥39-43። ●ኢየሱስ ተቃውሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ ለመግለጥ በምንሄድበት ጊዜ የመንገዱ አንድ ባህሪ መሆኑን አሳይቶናል፤ ማቴ.12፥30። ●ተቃውሞ የአብን ፈቃድ ፈፅሞ አብን ማክበሪያ እንደሆነ አስተምሯል። ኢየሱስ በብዙ ተቃውሞ ስራውን በመፈጸም የላከውን አብን አክብሯል፤ዮሐንስ ምዕ.17፥4። #.4ኛ ተመሳስሎ አልኖረም። ኢየሱስ ተመሳስሎ ለመኖር ሳይሆን ትክክለኛ የሆነውን የአብን ፈቃድ ለማድረግ የቆረጠ ነው። ይህች አለም ተመሳስሎ ለሚኖርባት ተቃውሞ የሌላት እውነትን ብቻ ገልጦ ሊኖር ለሚወድ ምንም ስፍራ የሌላት ነች፤ ዮሐ.5፥40-44። #.5ኛ ኢየሱስ በብዙ ነቃፊዎች መሀል ያለ ነቀፋ ኖሯአል። ኢየሱስ በያዘው እውነት ውስጥ ብዙ ነቃፊዎች ቢኖሩበትን በግል ህይወቱ ግን የሚነቀፍበት የሚከሰስበት ለእውነቱ የማይመጥን ስብዕናን የያዘ አይደለም። ኢየሱስ የያዘውን አላማ የሚመጥን መልካም ስብዕና ነበረው፤ ማቴ.27፥24፤ ሉቃስ 24፥19። ከዚህ ምን እንማር? 1. እግዚአብሔር ፍቅሩን ባሳየን መንገድ ሌሎችንን እንውደድ። 2. በያዝነው እውነት በደረሰብን መከራ እንፅና። 3. ተመሳስሎ ሳይሆን ከእውነት ጋር ወግነን እንኑር። 4. በያዝነው እውነት እንጂ በስብዕናችን የምንነቀፍ እንዳንሆን እራሳችን በእግዚአብሔር ባህሪ እናሳድስ።
Показать все...
ከፌስቡክ የተወሰደ ትምህርት ከእግዚአብሔር ሴት ነቢያት ዮዲት ተስፋዬ መልዕክት 🏁ክፍል አንድ ፨ወንጌላት ስለ ኢየሱስ ስብዕና ምን ይላሉ??? 1 ጴጥሮስ 2(1 Peter) 21፤“የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።” — 1ኛ ጴጥሮስ 2፥21 አንድ ሰው የኢየሱስ ደቀ-መዝሙር ሲሆን የእርሱ ፍለጋውን መፈለግ እና የተገለጠውን የህይወት ምሳሌውን መከተል አለበት። እንደዚህ ከሆነ የኢየሱስ ፍለጋ በወንጌላት ውስጥ ምን ነበር?? #.1ኛ-የእውነት ወዳጅ እና ፈላጊ ነው። “ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” — ዮሐንስ 14፥6 ●ኢየሱስ ሲገልጠው የነበረው እውነት በእግዚአብሔር አብ ዘንድ የነበረው ዘላለማዊውን እቅድ ነው። ዮሐንስ 8 14፤“ኢየሱስ መለሰ አላቸውም፦ እኔ ስለ ራሴ ምንም እንኳ ብመሰክር ከወዴት እንደመጣሁ ወዴትም እንድሄድ አውቃለሁና ምስክርነቴ እውነት ነው፤ እናንተ ግን ከወዴት እንደ መጣሁ ወዴትም እንድሄድ አታውቁም።” — ዮሐንስ 8፥14 እግዚአብሔር አብ በምድር እንዲገልጥበት ኢየሱስን እውነት እና መንገድ ደግሞም የሌሎች የህይወት ብርሃን እንዳደረገው ምስክሩን የላከውን አብ አድርጎ እውነት በሁሉ አጋጣሚ ይነገር ነበር። የኢየሱስ ደቀመዝሙር በሁሉ አጋጣሚ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሆነው እውነት የሚገልጥ መሆን አለበት። ኢየሱስ ለእውነት የሚገባውን ዋጋ ከፍሎአል። ዮሐንስ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵⁸ ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ⁵⁹ ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ። ኢየሱስ ከፈሪሳውያን ብሎም ከአይሁድ ማህበረሰብ ጋር እውነት በመግለጥ ከብዙሃኑ ጋር በተቃራኒ ቆሞዋል። እናም የሆንከውን ማውራት በትውልድ መሀል ድንጋይ ቢያስነሳም በክርስቶስ የተቀበልከውን እውነት ከመግለጥ ወደ ኋላ አትበል። ምክንያቱም ኢየሱስን እውነትን የፈለገው ሊያስወግረው በሚችል በአደባባይ ነው። እውነት ሁሌ የምታሸልም ብቻ ሳትሆን የምታስወግርም ነች። ስለዚህ የኢየሱስ ደቀመዝሙር ለመሆን የሚወድ ሁሉ ለእውነት የሚከፈለውን ዋጋ ከመጀመሪያ የተመነ መሆን አለበት። ●እውነትን በመኖር ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ህይወት አኑሮአል። ዮሐንስ 18 (John) 18፤“ጲላጦስም፦ እንግዲያ ንጉሥ ነህን? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው።” — ዮሐንስ 18፥37 ኢየሱስ ስለ እውነት በቃላት ብቻ ሳይሆን ነፍሱን አሳልፎ እስከ መስጠት ድረስ በማህበረሰቡ፣ በካህናት፣ በፈሪሳውያን፣ በአለቆች፣ በነገሥታት ዘንድ ባልተቀረየ ስብዕና የህይወት ምሳሌነት አስቀምጧል። ለዚህም አለም ሰዎች እውነት ርካሽ ናት፤ እውነት ውድ የምትሆነው ውድ አድርገው በያዙዋት እጅ ነው ብሎ ያምናሉ። በህይወት ምሳሌ ያለው እውነትን መግለጥ ያቃተን ለመኖር ካለን ጉጉት የተነሳ ነው። እውነተኛ የኢየሱስ ደቀመዝሙር በህይወት የተገለጠ እውነትን ገልጦ ለሌሎች የእውነት ህይወት ምሳሌ የሚያኖር ነው። ስለዚህ ሁላችን እንደ ኢየሱስ ስብዕና የእውነት ወዳጅ፣ ለእውነት የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈል እና ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ህይወት ለመኖርን በዚህ የክርስቶስ ፍለጋ ውስጥ እራሳችንን አማጥነን እንኑር።
Показать все...
🇧.ስለ ኢያሱ መሪነት ታሪክ ኢያሱ ትርጉም <<እግዚአብሔር አዳኝ>> ማለት ነው። የነዌ ልጅ ኢያሱ ከሙሴ በኋላ የእስራኤል መሪ ሆኖ በራሱ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው ሕዝቡን ወደ ከነዓን አሻግሮ ምድሩን አወረሳቸው። አያቱ ኤሊሳማ የኤፍሬም ነገድ አለቃ ነበረ፤ 1ዜና 7፥26:27፤ ዘኊ.1፥4-10። ብላቴና ሆኖ ከግብፅ ወጣ፤ ሙሴም ከአማሌቅ ጋር እንዲዋጋ አዘዘው፤ አሸነፈው፤ ዘፀ.17፥8-13። ከእግዚአብሔር ቤት የማይጠፋ ከቀድሞው ከሙሴ የሚማርና የተማረ ሎሌ ነበር፤ ዘፀ.24፥13፤ 32፥17፤ 33፥11፤ ዘኊ.11፥28። ከነዓንን ሊሰልሉ ከቃዴስ ከወጡት 12 ሰላዮች መካከል አንዱ ነበረ። እርሱ እና ካሌብ በእምነት እንወጣ ስላሉ ወደ ከነዓን እንደሚገቡ ተስፋ ተሰጣቸው፤ ዘኊ.13 እና 14። በዘኊ.13፥8 ላይ የኢያሱ የቀድሞ ስም <<አውሴ>> ነበር። ከሙሴ በኋላ መሪ እንዲሆን ተመረጠ፤ ዘኊ.27፥15-23፤ ዘዳ.3፥28፤ 31፥23። ከእግዚአብሔር ጋር ጠንካራ ህብረት ነበረው፤ በእግዚአብሔር ላይ በሙላት የተደገፈ እና ጠንካራ የእምነት መሪ ነበር። እግዚአብሔርም ቃል በቃል እና በራዕይ አደፋፈረው፤ ኢያሱ 1፥1-9፤ 5፥13-15። የእስራኤል ሕዝብ በኢያሱ መሪነት ዮርዳኖስን ተሻግረው ኢያሪኮን ያዙ፣ ዋና ሰፈራቸው ጌልገላ ሆነ። ከዚያም እየዘመቱ የከነዓን ነገሥታት አሸነፉ። እግዚአብሔር ቀኑን በማስረዘም፣ በረዶ በማዝነብ ረዳቸው፤ ኢያሱ 10፥11-14። አገሩን ከያዙ በኋላ ኢያሱ መሬቱን ለእስራኤል ነገዶች አከፋፈለ። የመሞቱ ጊዜ ሲቀርብ ሕዝቡን ሰብስቦ እግዚአብሔር ስላደረገላቸው ሁሉ አሳሰባቸው። ከሕዝቡም ጋር ቃል ኪዳን ተጋብቶ ለመታሰቢያ ታላቅ ድንጋይ በሴኬም አቆመ፤ ኢያሱ 24፥25-28። ከኢያሱ ጠንካራ ከየሚያስብለው ነገር ሁሉ ከቤተሰቡን ጋር ጠንካራ አቋም ያላቸው ሰዎች ሲሆን እግዚአብሔርን የማምለክ ህይወት እንዲኖራቸው እና እንዲሁም የሚመራው ህዝብ ጠንካራ የአምልኮ ህይወት እንዲኖራቸው የአቋም መግለጫ የሰጠ መሪ ነበር። ኢያሱ በ110 ዓመቱ ሞተ፤ በርስቱ በኤፍሬም ነገድ እንደተቀበረ መጽሐፍ ይናገራል፤ ኢያሱ 24፥29-31።
Показать все...
🏁🏁ክፍል=አንድ🏁🏁 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መሪዎች ታሪክ 🅰 የብሉይ ኪዳን መሪዎች ታሪክ 🇦. ስለ ሙሴ መሪነት ታሪክ ሙሴ፤ እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብፅ ባርነት አውጥቶ እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ለማድረስ የተጠቀመበት የእስራኤል መሪ ነበር። ይህንንም ሲያደርግ ሙሴ ሰፊ የሆነ አገልግሎት ነበረው። 🏁 ስለ ሙሴ መሪነት ምን እንደሚመስል ከዚህ በታች ያለው ሀሳብ በዝርዝር እንመለከታለን። ✔.1 በእግዚአብሔር የተመረጠ መሪ ነበር ሲሆን የሕዝብ መሪ እና ፈራጅ ነበር፤ ዘፀ.18፥13:26። ✔.2 ለተጠራሁበት አገልግሎት ብቁ አይደለሁም ብሎ እግዚአብሔርን የሞገተ መሪ ነበር፤ ዘጸ.4፥10-17። ✔.3 እግዚአብሔር በሲና ሕግን ሰጥቶ ከእስራኤል ጋር ላደረገው ቃል ኪዳን ሙሴ መካከለኛ ነበረ፤ ዘፀ.19፥7፤ ዘፀ.ምዕ.24፤ ገላ.3፥19። ➢“ታዲያ ሕግ የተሰጠበት ምክንያት ምንድን ነው? ሕግ የተጨመረው ከመተላለፍ የተነሣ ተስፋው ያመለከተው ዘር እስኪመጣ ድረስ ነበር፤ ሕጉም የመጣው በመላእክት በኩል፣ በአንድ መካከለኛ እጅ ነበር።” — ገላትያ 3፥19 (አዲሱ መ.ት) ✔.4 እንደ ተገለጠለትም ምሳሌ የመገናኛውን የድንኳን መቅደስ አሠራ፤ ዘፀ.ምዕ.25-31፤ ምዕ.35-40። ✔.5 ከእግዚአብሔር ጋር ጠንካራ ግንኙነት የነበረው መሪ ነበር ሲሆን ለጽድቅ፣ ለእውነት፣ ለቅድስና ትልቅ ስፍራ የሚሰጥ እና ትሕትና የተላበሰ መሪ ነበር (ዘኊ.12፥3)። ✔.6 እግዚአብሔር <<አፍ ለአፍ በግልጥ>> ያናገረው እግዚአብሔርም <<ፊት ለፊት>> ያወቀ ነቢይ ነበረ፤ ዘኊ.12፥6-8፤ ዘዳ.34፥10-12። ✔.8 አብዛኛዎቹ በእጁ ስለ ተጻፉ ዐምስቱ የኦሪት መጻሕፍት <<የሙሴ>> ተብለው ይጠራሉ፤ ሉቃ.24፥27። ✔.9 ሙሴ በአገልግሎቱ ሰፊ ቢሆንም እንኳ ሙሴ የእስራኤል ሕዝብ ጉዳይ ለመፍታት በእንዲህ ብሎ ተናግሮ ነበር። ዘጸአት 18 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹³ በማግሥቱ ሙሴ ሕዝቡን ለመዳኘት ተቀመጠ፤ እነርሱም በዙሪያው ከጧት እስከ ማታ ድረስ ቆሙ። ¹⁴ አማቱም ሙሴ ለሕዝቡ የሚያደርገውን ሁሉ ባየ ጊዜ፣ “ምን ማድረግህ ነው? እነዚህ ሁሉ ሰዎች ከጧት እስከ ማታ በዙሪያህ ቆመው ሳለ፣ ብቻህን በፍርድ ወንበር ላይ ለምን ትቀመጣለህ?” አለው። ¹⁵ ሙሴም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ “ምክንያቱም ሰዎቹ የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም) ፈቃድ በመፈለግ ወደ እኔ ይመጣሉ። ¹⁶ ክርክር በኖራቸው ቍጥር ጒዳያቸው ወደ እኔ ይመጣል፤ ለግራና ለቀኙ የሚሆነውን እኔ ወስኜ የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም) ሥርዐትና ሕጎች እነግራቸዋለሁ።” ይህንን ምላሽ በሚሰጥበት ጊዜ ዮቶር ለሙሴ በተናገረው ሀሳብ ላይ አልተስማማም ነበር። ዮቶር ለሙሴ የአንድ ምክረ-ሀሳብ በሚሰጥበት ጊዜ የሕዝብ ጉዳይ በራሱ መንገድ ብቻ መፍታት እንደማይችል ሲገልጽ እንመለከታለን። ከዚህም በኋላ ደግሞ አንድ መፍትሔ ለሙሴ ሲያብጅለት የእስራኤል ሕዝብ ጉዳይ በተመለከተ ከሙሴ ጋር የሚተባበር እና የሚያግዝ ሰው ያስፈልጋል ብሎ አቅጣጫ ሲያስቀምጥ እንመለከታለን። የእስራኤል ህዝብን የማስተዳደር የሚችል ሰው እንድትመርጥ እና የእስራኤል ሕዝብ ጉዳይ በተመለከተ ደግሞ ቀላል የሆኑ ጉዳዮች በአለቆች በኩል የሚፈታ ሲሆን ከአለቆች አቅም በላይ የሆነ ከባድ እና ውስብስብ ሀሳብ የሆኑ ጉዳዮች ሙሴ እንዲፈታ ምክረ ሀሳብ ሲሰጥ እንመለከታለን። ሙሴ ደግሞ የዮቶር ምክረ ሀሳብ ከተቀበለ በኋላ የአስተዳደር ስርዓቱ መስመር እንዳስያዘ እና እንዳስተካክለ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ይናገራል፤ ለተጨማሪ ደግሞ ዘጸ.18፥1-27 ያለው ማንበብ ይቻላል። ✔.10 ለክርስቶስ ምሳሌ ሆነ፤ ነቢይ መሆኑን (ዘዳ.18፥15-19፤ ሐ.ሥ.3፥22:23)፣ በታማኝነቱ (ዕብ.3፥1-6)፣ የማደሪያውን ድንኳን በመትከሉ እና በማገልገል (ዕብ.8 & 9)፣ በደረሰበትም ተቃውሞ እንደገጠመው ይናገራል፤ ሐ.ሥ.7፥35-40:52:53። ✔.11 በኮሬብ በተገለጠው ክብር ፊቱ የበራ የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ፣ በደብረ ታቦር የክርስቶስን የክብር መገለጥ አየ። ሙሴ አስቀድሞ በትንቢት እና በምሳሌ ስለ ክርስቶስ እና ስለ ሞቱ ጻፈ (ዮሐ.5፥46፤ 3፥15)፣ ስለ ትንቢቱም መፈጸም በታቦር ከክርስቶስ ጋር እንዲነጋገር ዕድል አገኘ፤ ሉቃ.9፥30:31፤ ዘፀ.34፥29-35፤ 2ቆሮ.3፥7-18። ስለ ሙሴ መሪነት ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም ሰፊ አገልግሎት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ስለ ሙሴ መሪነት ታሪክ ውስጥ ጠንካራ ጎኖች እና ደካማ ጎኖች ማየት አስፈላጊ ነው። ስለ ሙሴ መሪነት ታሪክ ውስጥ ጠንካራ ጎኖች ምንድናቸው? ✔ ሙሴ እጅግ ትሑት መሪ እንደ ነበር መጽሐፍ ይናገራል፤ ዘኊ.12፥4። ✔ ሙሴ ለእግዚአብሔር አገልግሎት እና ለቤቱ ታማኝ እንደነበረ መጽሐፍ ይናገራል፤ ዘኊ.12፥6-8። ✔ ሙሴ የእስራኤል መቃወም እና ማጒረምረም በብዙ ነገር የታገሠ ሰው ሲሆን ራሱንም ለእነርሱ አሳልፎ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን በጸሎቱ በመግለፅ፣ እግዚአብሔር እንዳያጠፋቸው ለመነ መሪ ነበር፤ ዘፀ.32፥11-14፤ ዘኊ.11፥1-15፤ 12፥1-16፤ 14፥10-19፤ 21፥4-9። ✔ ሙሴ በእግዚአብሔር አገልግሎት እና በቤቱ የነበረው አገልግሎት ደከመኝ እና ሰለቸኝ ሳይል የማደሪያውን ድንኳን በመትከሉ እና በማገልገሉ የታወቀ መሪ ነበር፤ ዕብ.8፥5፣ ዕብ ምዕ.9። የሙሴ መሪነት ታሪክ ውስጥ ደካማ ጎኖ ምንድነው? እስራኤላውያን በምድረ በዳ በሚንከራተቱባቸው ዓመታት መጨረሻ ላይ ግን አንድ ጊዜ ሙሴ ተቈጥቶ እግዚአብሔር አላከበረምና ወደ ከነዓን እንዳይገባ ተከለከለ፤ ዘኊ.20፥1-13፤ መዝ.106፥32:33። 🏁የሙሴ የመጨረሻ ተግባራት ሙሴ በኤዶምና በሞዓብ ዳርቻ በኩል እስራኤልን አዞራቸው፤ የአሞራውያንን ነገሥታትም በማሸነፍ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ወዳለው ሰፊ ምድር አገባቸው፤ ዘኊ.21-32። የሁለተኛው ትውልድ አባላት ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን እንዲያድሱ እና ሕጉን እንዲጠብቁ በማለት፣ እርሱ ያደረገላቸውን ምሕረት አሳስቦ ለሕዝቡ ተናገረ (ኦሪት ዘዳግም)። በራስ ምትክ ኢያሱ መሪ እንዲሆን አደረገ፤ ዘኊ.27፥12-23። ሙሴ በግጥም ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ (ዘዳ.32)፣ የእስራኤልን ነገዶች ባረከ፤ ዘዳ.33። ከዚያም በኋላ ፈስጋ በተባለው ተራራ ራስ ላይ ሆኖ የከነዓንን ምድር ካየ በኋላ በ120 ዓመቱ ህይወቱ አረፈ።
Показать все...
🏁መሪነት/Leadership/ መሪነት ምን ማለት ነው? ስለ መሪነት መማር ካስፈለገ በማቴ.20፥20-28 ድረስ ያለው ቃል መሠረት አድርጎ መነሳት ይቻላል። ማቴዎስ 20 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁰ ከዚያም፣ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆቿ ጋር ወደ ኢየሱስ ቀርባ በፊቱ ተንበርክካ እየሰገደች፣ አንድ ነገር እንዲያደርግላት ለመነችው። ²¹ እርሱም፣ “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርሷም፣ “እነዚህ ሁለት ልጆቼ፣ በመንግሥትህ አንዱ በቀኝህ፣ አንዱ በግራህ እንዲቀመጡ ፍቀድ” አለችው። ²² ኢየሱስም፣ “የምትለምኑትን አታውቁም፤ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ ትችላላችሁን?” አላቸው። እነርሱም፣ “እንችላለን” አሉት። ²³ እርሱም፣ “ከጽዋዬ በርግጥ ትጠጣላችሁ፤ ነገር ግን በቀኜና በግራዬ መቀመጥ አባቴ ላዘጋጀላቸው ነው እንጂ እኔ የምፈቅደው ነገር አይደለም” አላቸው። ²⁴ ዐሥሩም ይህንን በሰሙ ጊዜ፣ ሁለቱን ወንድማማቾች ተቈጧቸው። ²⁵ ኢየሱስም አንድ ላይ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “የአሕዛብ ገዢዎች በሕዝባቸው ላይ ጌቶች እንደሚሆኑ፣ ባለ ሥልጣኖቻቸውም በኀይል እንደሚገዟቸው ታውቃላችሁ፤ ²⁶ በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም። ከእናንተ ትልቅ መሆን የሚፈልግ አገልጋያችሁ ይሁን፤ ²⁷ የበላይ ለመሆን የሚሻም የእናንተ የበታች ይሁን፤ ²⁸ የሰው ልጅ እንዲያገለግሉት ሳይሆን፣ ለማገልገልና ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ለመስጠት መጥቶአልና።” ስለ መሪነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተለያዩ ሀሳቦች ማግኘት ይቻላል። ከዚህ በላይ ያለው ሀሳብ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ መሪነት ሁለት ነገሮች ለደቀመዛሙርቱ ግንዛቤ ሲሰጥ እንመለከታለን። አንደኛ ነጥብ የሚያወራው ስለ አለም መንግሥት አመራርነት ሲሆን ሁለተኛ ነጥብ የሚያወራው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አመራርነት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ መሪነት ምን አይደለም ብለን መነሳት ያስፈልጋል። ✔.1 መሪነት አለቃ መሆን አይደለም። ✔.2 መሪነት አምባገነን መሆን አይደለም። ✔.3 መሪነት ከሁሉም የበላይ መሆን አይደለም። ✔.4 መሪነት ሀይለኛ ወይም ከሌሎች ሰዎች ትልቅ መሆን አይደለም። ✔.5 መሪነት ስልጣን ላይ መቀመጥ አይደለም። ✔.6 መሪነት ትልቅ ቦታ ላይ መቀመጥ አይደለም። ✔.7 መሪነት ለጥቂት ግለሰቦች የተሰጠ አይደለም። ከዚህ በላይ በዝርዝር ያየናቸው ሰባት ነጥቦች መሪነት ሊሆኑ ካልቻሉ መሪነት ምንድነው የሚለው ነገር በደንብ መረዳት ያስፈልጋል። ❖ሁለተኛ ደረጃ መሪነት ምንድ ነው ብለን ብንመለከት ጥሩ ነው። ✔.1 መሪነት አለቃ መሆን አይደለም ካለን አገልጋይነት ነው። ✔.2 መሪነት አምባገነን መሆን አይደለም ካለን ታጋሽነት ነው። ✔.3 መሪነት ከሁሉም የበላይ መሆን አይደለም ካለን ከሁሉም ዝቅ ብሎ መገኘት ነው። ✔.4 መሪነት ሀይለኛ ወይም ከሌሎች ሰዎች ትልቅ መሆን አይደለም ካለን ትዕግሥተኛ እና ለሌሎች ሰዎች ምሳሌ መሆን ነው። ✔.5 መሪነት ስልጣን ላይ መቀመጥ ሳይሆን በጥበብ እና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ አገልጋይ ነው። ✔.6 መሪነት ትልቅ ቦታ ላይ መቀመጥ ሳይሆን እራሱን የሚገዛ ልባም አገልጋይ ነው። ✔.7 መሪነት ለጥቂት ግለሰቦች የተሰጠ ሳይሆን ለሁሉም ለሰው ልጅ የተሰጠ ነው። ይህ ማለት ምን ማለት ነው ካለን ማንኛውም የሰው ልጅ አዕምሮ ጤናማ እስከሆነ ድረስ ህይወቱ በአግባብ የሚመራ ሰው መሪ መባል ይችላል። በአጠቃላይ መሪነት ማለት በራሱ ህይወት ላይ የሚገዛ ሰው እና በሌሎች ሰዎች ዘንድ ልብ የሚገዛ ሀሳብ መፈጠር የሚችል ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰው ነው። በመሪ እና በአለቃ መካከል ልዩነት አለ። አለቃ ማለት በሰዎች ላይ ትዕዛዝ የመስጠት የሚያተኩር ሲሆን መሪ ደግሞ በሰዎች ላይ ጭና መፈጠር ሳይሆን በራስ መተማመን ላይ የሚያተኩር በሰዎች ላይ ልብን የሚገዛ ተጽእኖ መፍጠር የሚችል ነው።
Показать все...
ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ መልዕክትመልዕክት ለምን አልነገርሽኝም? ከሲኦል የተጻፈ የፍቅር ደብዳቤ! በዶክተር ወዳጄነህ መሐረነ የተዘጋጀ ፅሁፍ ቤተልሔም ሰፈረዋ ስትደርስ ከምሽቱ 3 ሰአት ሆኖ ነበር። እጅግ ከምትወዳት ጓደኛዋ ከማኪ ጋር ነበር ያመሹት። ለሁለት የበሉት ትልቅ ፒዛ በጣም አጥግባት ስለነበር ቤትዋ የቀረበላት እራት ይቅርብኝ ብላ ለምሽት የምትመርጠው የካሞሜል ሻይ ጠጥታ በቀጥታ ወደ መኝታ ቤቷ ገባች። እንደ ልማዷ አጭር ጸሎት አድርሳ፣ ፒጃማዋን ለብሳ ለእንቅልፍ ራስዋን አመቻቸች። የቤቲ እንቅልፍ ሁልጊዜ ጣፋጭ ነው። ፀጉሯ ትራስ ከነካ እርሷ የለችም....ወደ ሌላ አለም ትሔዳለች! ደግሞም ህልሞች ታልማለች... ለዛውም የ7D ህልሞች! በህልም የምትቀበላቸው መልዕክቶች መሬት ላይ ጠብ አይሉም። ሁሉም ሲፈፀም አይታለች። "ዛሬ ህልም አይቼ..." ብላ ከጀመረች ሁሉም ሰው በጉጉት ነው የሚሰማት። በዚህ ሌሊት ያያችሁ ህልም ግን እጅግ የተለየ ነው። አንድ ሰው ደብዳቤ ይዞላት ይመጣል...በህልሟ። ደብዳቤው የተጻፈው ከታች ከሲኦል ሲሆን የፃፈችላት ደግሞ አብራት ያመሸችው ባልንጀራዋ ማኪ ናት። ደብዳቤው እንዲህ ይነበባል። "ውድ ጓደኛዬ ቤቲዬ! በድንገት ሳላስበው ዛሬ ሌሊት ወደማላውቀው ስፍራ መጣሁ። ሲኦል ነው ብለው ነግረውኛል። የምፅፍልሽ ከዛ ነው። በጣም የሚያስፈራ፣ የሚያስጨንቅ ቦታ ነው። በቅጽበት ከመንገድ ወደዚህ ሲያመጡኝ ለምን ብዬ ጠይቄያለሁ። የሰጡኝ መልስ "ከጠላት አላመለጥሽም... የጉብኝትሽን ወራት አላወቅሽም... የተከፈለለልሽን አልተረዳሽም!" የሚል ነው። አንቺ ግን ታውቂ ነበር አይደል? ተረድተሽም ነበር አይደል? ግን ለምን አልነገርሽኝም? ቤቲዬ! እንዳንቺ የሚቀርብኝ ጓደኛ ኖሮኝ አያውቁም። ሚስጥረኛዬ አንቺ ነበርሽ! አንድ ቀን እንኳን ሳላገኝሽ ከዋልኩ ቅር ይለኝ....ትናፍቂኝ ነበር። አሁንም በፍቅር ልውቀስሽ ብዬ እንጂ ተጣልቼሽ አይደለም። ቤቲዬ! ብዙ ቀን ሳውና አብረን ገብተናል...ጃዙኪ ውስጥ ተዝናንተናል። ስለ ብዙ ነገር አውርተናል .... መካሪዬ ነበርሽ! ግን ቤቲዬ ልጠይቅሽ...ለምን ስለ ክርስቶስ አልነገርሽኝም? ፀጉራችንን፣ ጥፍራቸው ስንሰራ ሁሌም አጠገብ ላጠገብ ሆነን ነበር፤ ለብዙ ሰአታት እናወራ ነበር። አንቺ ግን ታወቂ ነበር አይደል...? መዳን ከቅድስት ማርያም በተወለደው በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ? እስቲ አሁን እያነባሁ በፍቅር ልጠይቅሽ...ቤቲዬ የኔ ቆንጆ...ለምን አልነገርሽኝም? ምሳ አብረን ስንበላኮ ከ3 እስከ 4 ሰአታት ይፈጀብን ነበር። ስለሔድባቸው ከተሞች...ስለ ፓሪስ፣ ስለ ለንደን፣ ስለ ኒውዮርክ፣ ስለ ባንኮክ ስታወሪልኝ አፌን ከፍቼ ነበር የምሰማሽ። ግን ቤቲዬ የኔ ጓደኛ...የኔ ማር...በመስቀል ላይ ስለተሰራው ስራ ለምን አልነገርሽኝም? አያስፈልጋትም ብለሽ ነው? በየጊዜው ከውጪ ስትመጪ ስጦታ ታመጪልኝ ነበር። ዛሬ እንኳን ይዤው የነበረው ቦርሳ አንቺ የሰጠሸኝ ነው...አንገቴ ላይ የነበረውም ሀብል እንዲሁ። ለእኔ ስጦታ መስጠት ደስታሽ ነበር። ግን ቤቲዬ! እህቴ! መጽሐፍ ቅዱስ ለምን አልሰጠሸኝም? አልዋሽም? መንፈሳዊ ወሬዎች ከሌሎች ጋር ሆነን ስታወሩ ሰምቻለሁ። ስለ ታዋቂ ሰባኪዎች... ስለ ቄሶች፣ ስለ ፓስተሮች... ስለመጣላቸው ትንቢቶች... ስላገኛችኋቸው በረከቶች ስታወሩ ሰምቼ አውቃለሁ... ግን ለምን ከሞት ስለ መድሀኔያለም አልነገራችሁኝም? ለምን ከሞት እንደሚያድን፣ ከሲኦል እንደሚታደግ አልተረካችሁልኝም? ቤቲዬ! እሺ እል እኮ ነበር! ዛሬ እንደሆነው ሰይጣን ያለ እድሜዬ አይቀጥፈኝም ነበር! በደሙ እሸፈን ነበራ! መላዕክቱ ይጠብቀኝ ነበራ! አሁንማ አበቃ! ጊዜው አልፏል አሉኝ... ወደዚህ ስፍራ አመጡኝ። በጣም ያስፈራል ቤቲዬ ....ለማስረዳት እንኳን ያስቸግራል! ማንም ወደዚህ እንዲመጣ አይፈልግም። ጓደኛዬ ማሬ! ቤቲዬ ሚስጥረኛዬ! አንቺኮ ልብስሽን ሲነኩብሽ አትወጂም ነበር። እኔ ግን ሌዘር ጃኬትሽን ስለብስብሽ....ለዛውም ሳላስፈቅድሽ... ስካርፍሽንም ለብሼ ስወጣ....በነዚያ ትላልቅ አይኖችሽ አየት ታደርጊኝና ዝም ትይኝ ነበር። ሽቶሽ ሽቶዬ... ጥፍር ቀለምሽ ጥፍር ቀለሜ... ሊፕስቲክሽ ሊፕስቲኬ ነበር። አንቺኮ የልብ ጓደኛዬ...አስተማሪዬ ነበርሽ። ስለ ዳይት፣ ስለ ቫይታሚኖች፣ ስለ ጂም... ያስተማርሽኝ አንቺው ነሽ። ግን ቤቲዬ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን አልነገርሽኝም? በእርሱ በሀጢአትሽ እንደተሰረየልሽ.... የዘላለም ህይወት እንደወረስሽ ለምን አላወራሽልኝም? ብዙ ቀን ሲኒማ ስንሔድ አንድ ቀን እንኳን ቤተክርስቲያን እንሂድ ለምን አላልሽንም? ልቤ አዘነብሽ...ተቀየምኩሽ ጓደኛዬ...ቤቲዬ! ምንም እንኳን ባዝንብሽም ሁሌም ጨክኜ አንቺን ማኩረፍ አልችልም....ታወቂ የለም። መልካም ህይወት ይሁንልሽ! አምላክሽ ያሰብሽውን ሁሉ ያሳክልሽ! ሁልጊዜ እወድሻለሁ! አንዳንድ ቦታ አልነበብ ካለሽ ቀለሙን ያበላሸው የተንጠባጠበው እንባዬ ነው! ደህና ሁኚልኝ አክባሪ እህትሽ...ጓደኛሽ...ሚስጥረኛ ባልንጀራሽ ማኪ ነኝ....ከታች....ከሲኦል!" ቤቲ ከእንቅልፏ በታላቅ ድንጋጤ ነቃች። ህልም ነበር! በህልሟ ያነበበችው የማኪ ደብዳቤ ግን በጣም አስደንግጧታል። ፊቷ ላይ ላብ ችፍ ብሏል! እየተንቀጠቀጠች ስልኳን አንስታ ወደ ማኪ ደወለች። ስልኩ ተነሳ.... ያነሳችው ግን ማኪ አልነበረችም። እነ ማኪ ቤት ለቅሶ ይሰማል...."ጓደኛዬን ማኪን ፈልጌ ነው" አለቻቸው እየተበርተበተች። ስልኩን ያነሱት እናትም በሲቃ...."አዬ! ማኪንማ የመኪና አደጋ ነጠቀኝ! ጉልበተኛ ሰይጣን ነጠቀኝ! ለማን አቤት ይባላል?" አሏት። የቤቲ ሞባይል ከእጇ ወደቀ....ማኪን?...የመኪና አደጋ? በህልሟ ያነበበችው የማኪ ጥያቄ ይጮህባት ጀመር....ለምን? ጓደኛዬ...ቤቲዬ...እህቴ...ባልንጀራዬ...ማሬ ለምን አልነገርሽኝም?...ለምን? የሚል ጥያቄ በአዕምሮ ውስጥ ይመላለስ ነበር። __ይቀጥላል_________
Показать все...