cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Mule Habeshaw

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
198
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

😇😇😇😇😇😇😇😇😇 ሲነፍስ ዕልፍ ደግሶ ድሮሽ በሆታ እልፍኝ ሲጠራ የማታ ማታ ፈቅዶ ተዘርፎ ኦና ዳስ ታቅፎ ኡኡ አለ ባላገር ማን ይሰማዋል ኡኡ አለ አባወራው ናላው ተነክቷል በላተኛውም የበላው ድግስ ጠኖት ተኝቷል ደጋሽ ደግሶ አክብሮ ጠርቶህ አጥሩን አትሰርስር አትገኝም አንሰህ ✍✍✍✍✍✍✍✍✍
Показать все...
👩‍🦱👩‍🦱👩‍🦱👩‍🦱👩‍🦱👩‍🦱👩‍🦱👩‍🦱👩‍🦱 ድብልቅ ጨረቃዎች ፈርሰው ከዋክብት 'ረግፈው ውበት ተዳፈነ አረማሞ ዘራን ጨለማ ገዘፈ ከጥላ'ት ጠለሸን ምድር ተቀብላ ሁሉን አበቀለች በሔዋን ልብ አድራ ዓለም ተሸከመች ልጁ እንግዳ ልጁ አንድ ላይ አደጉ በስሉስ ጀምረው በጂኒ አሳረጉ ✍✍✍✍✍✍✍✍✍
Показать все...
😭😭😭😭😭😭😭😭😭 አላለፈም ፊትነትን አይቶ ኋላ መቅረት አግኝቶ ማጣትን የሚያህል መከራ የለም ። እዩ'ት ይቺን ጉብል በደም ተለውሳ ውበቷ ተዳፍኖ ፍም እሳት ስትገሳ መዓዛዋን መጠው ከበው ያወደሷት ሙሽራዬ ብለው ሞሽረው ያገቧት አግብተው የፈቷት ፈትተውም የገፏት ገፍትረው የጣሏት ጥለው የረገጧት ዘመን ሲሄድ ሲያልፉ አዲሶቹ ጉብል ሊገቡ ከቤቷ አሰፍስፈው ቆመው ድብቅ ነው ውበቷ ብለው ያወደሷት ቀን ደርሶ ሲገፏት በተስፋ የወዛው ፊቷ ሲገረጣ የገፋትን ገፍታ በፍቅር ስትቀጣ እዩ'ት እዩ'ት ይቺን ጉብል በዘመን ጋጋታ በእንባዋ ማዕበል የገረጣው ፊቷ ሲታጠብ ይውላል... ✍✍✍✍✍✍✍✍✍
Показать все...
🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲 ተመለሽ መስለሽ መሆን ባታውቂ የቃልሽን ሰይፍ ብትሰብቂ መናገር ሆነና ግብርሽ ልባዌን ነስቶ ቢሰድሽ መኳንንት ሹማምት ቆመው እስክስታ ዳንኪራ ረግጠው ፊትሽ ብርሀን ለብሶ እንደ ማ'በል ፈሰሽ ኦሆይ ሆይ ብለሽ ጨፍረሽ በቡጊ የዳንኪራ ስልት ዓለምን ሁሉን ስትረሺ እኔ ግን በዕንባ የውሀ እንክብሎች በቅዠት ጩኸት ስደክም የደላሽ ያገዝኩሽ መስሎሽ እሪታው ፍፁም ቢለይም ለቡጊ ስልት ያጣ ጩኸት ጠራሽኝ ቆሜ እንድታደም ሲቃዬ ሲበዛ ብጮኽ እንዳንቺው ስልት ያጣ ጩኸት ዳንኪራ 'ረገጠ ብለሽ ሲቃዬን አትቀልጂበት የ'ንባዬ ከረጢት ደርቆ ማላዘን ማንባት ቢያቅተኝ ደረቅ ጩኸቴን ወስደሽ ደላው ብለሽ አትበይኝ አንቺ ቤት ሁሌም ድግስ ነው እኔ ቤት ሁል ጊዜ ለቅሶ እንዳይቆርጥ ብዬ እፈራለሁ ነገሩ ከዚህም ብሶ ✍✍✍✍✍✍✍✍✍
Показать все...
🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈 'ፀናለሁ ትመጣለች ብለዉ ተስፋ እያሰነቁኝ ስንት ጊዜ ነጋ ስንት ጊዜ መሸ ሳቅ እንደናፈቅሁኝ አንቺ ግን በናፍቆትሽ ገመድ ታስሮ 'ሚጠብቅሽ በእንባ 'ሚታጠበው ያው ቡቡው አድናቂሽ እንዲሉሽ ፈልገሽ ልክ እንደመስቀል ወፍ ታይተሽ ትጠፊያለሽ አበቦች ሲፈኩ ደምቀሽ ትመጪና ሲከስሙ ስትከስሚ ስጠብቅሽ ውዬ ተስፋዬ ተሟጦ ጠርቼ ገጣሚ "በል እንግዲህ ሆዴ ካለው ተላመድ ቢያስሩበት አያጠብቅ በስባሳ ገመድ" የሚለውን ስንኝ ከነፍሴ እንዲያዋህድ እንድረሳሽ ብሎ ቅኔ እየዘረፈ ስንኝ ቢያሰናኝም እንኳንስ ሊያስረሳኝ ትዝ አልሽኝ ሲገጥም እናም እርሳኝ ካልሽኝ መርሳቱን አልችልም ቀሰሩብኝ ብዬ ዓለሜን አልሰጥም አስበኝ ካልሽኝ ግን አስታውሰኝ ካልሽኝ ግን እጠብቅሻለሁ ጊዜው ለ'ኔ እስኪቆም ዓለሜን አፅድቆ የወል ሀቅ እስኪያረግ ውጣ ቢሉኝ ገደል ውረድ ቢሉኝ 'ረግረግ እከተልሻለሁ ዮናስ ነኝ አልፈራም እውድቅት ቢሆን እንጂ ከቶ አልሰበርም ... ✍✍✍✍✍✍✍✍✍
Показать все...
🤏🤏🤏🤏🤏🤏🤏🤏🤏 ተስፋ አለኝ ይኽ ሀጢያት ከሆነ ተመኝቼሻለሁ ፈቃዴ ፈቃድሽ ሲሆን አይቻለሁ እንደ መንፈቅ ህፃን ድሆ ሲከተልሽ ለቀረበሽ ሁሉ ባይቀር መፋጀትሽ ልቤ እንደሁ ድንድን ነዉ መመኘቱ አይቀርም ጥላ'ቸው ነው እንጂ በፍቅር ነበልባል ቢቃጠሉ አይፈጅም ✍✍✍✍✍✍✍✍✍
Показать все...
🤏🤏🤏🤏🤏🤏🤏🤏🤏 ሰውነት ተነፈግን ዳዊት ጠጠር ወርውር ሙሴም በትርህን ጣል ጎልያድ ሊውጠን ፈርዖን ሊያጠፋን ከፊታችን ቆሟል እኛም ቅንጣት ተስፋ ባህሩን ቢከፍለው ጎልያድን ጥሎ መቅደሱን ቢያከብረው ዝምታው ተሰብሮ ለዝማሬ እንቁም ነን ለማለት በቅተን ነበርን ይፈጸም ጥበብ ቤቷን ትስራ መሰረቱን ይወቅ ሀጢያት እንዳይባል ጥያቄ መጠየቅ ✍✍✍✍✍✍✍✍✍
Показать все...
🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈 🧜🏾‍♀ልትጠፋ ያለች ሀገር ከተማ ፣ ህዝብ እና መንግስት ነጋሪት ቢጎሰምም አትሰማሞ ። !!! "ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል ።/ የተማረ ይግደለን !" እያልን ያሳደግነው ልጅ ሲሾም ካልበላን ካልገደለን እንዳይቆጨው በእሳት ጠብሶ ቢበላን ለምን ይቆጨናል ። "አንተው ባስተማርከኝ ባንተው አስጨከንከኝ" ሆኖ ሳለወደላይ ማንጋጠጡ ጠቀሜታ የለውም ። ይልቁንም ትላንት ተጭነው የጫኑህን የድንቁርና ካባ አውልቀው እና ለትውልድህ ሀገር ማለት ሰው እንደሆነ ንገረው በይቅርታ ምሰሶህን አፅና ። ✍✍✍✍✍✍✍✍✍
Показать все...
🦵🏽🦵🏽🦵🏽🦵🏽🦵🏽🦵🏽🦵🏽🦵🏽🦵🏽 🐰ምክኒያት ነሽ መውደድ መሸነፍ ነው ለስሜት መገዛት ውሸትን የማያውቅ ልጓም ነው የእውነት እናም በደልሽ ቢበዛም ልሸከመው ቢከብድ ሰውነት ስናፍቅ ቢያስቀረኝ ከመንገድ ይወድሻል እና ይናደዳል እንጂ ልቤ አይቀየምሽ ቀን በቀን ብሞትም በየሞቴ መሀል ሁሌም ትኖሪያለሽ ✍✍✍✍✍✍✍✍✍
Показать все...
Join belew
Показать все...