cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የመካነ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስና አቡነ አረጋዊ ቤ/ክ ልጆች

ሰላም ለሀገሩ ወሰላም ለደብሩ ወሰላም ለመቃብሩ ገ/መንፈስ ቅዱስ አቡዬ ለእግዚአብሔር ፍቁሩ ደመናት አንኰርኲሩ አእዋፈ ሰማይ ዘመሩ በጊዜ ሞትከ መላእክት አንከሩ ሰአል ለነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቅድመ መንበሩ ለክርስቶስ።

Больше
Рекламные посты
196
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

​​እንኳን #አቡነ_ገብረመንፈስ_ቅዱስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን! አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው። አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ። ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል። አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ " የሚል ድምጽ ሰማች። በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ። አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል። አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል። በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል። በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው። በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ። ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው። ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ። ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ። ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር። በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው። መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት። 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው። ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል። ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር። 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው። እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል። ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል። ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል። ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው። 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል። ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ስላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው። በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው። አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው። ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል። ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ። #ምንጭ - ገድለ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ተአምር 14  ለወዳጅዎ ያጋሩ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Показать все...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን #ጾመ_ፍልስታ ​ይህን ፆም ለመጀመሪያ ጊዜ የፆሙት ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ የፍስለታ ፆም ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 16 ድረስ ያለው ነው፡፡ ይህም ፆም የእመቤታችን ትንሳኤና ዕርገት መታሰቢያ ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን አሰተምሮ መስረት እመቤታችን በጥር ወር 21 ቀን በ49 ዓ.ም በ64 አመቷ አርፋለች፡ https://t.me/yeabuyelejoch ሐዋርያትም በድኗን ሊቀብሩ ወደ ጌቴ ሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ በቅንዓት መንፈስ ተነሳስተው በእሳት ሊያቃጥሏት ሲሉ መላዕክት አስክሬኗን ወስደው በገነት አኑረዋታል፡፡ በስምንተኛው ወር በነሐሴ አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምሕላ ተቀብሯል፡፡      https://t.me/yeabuyelejoch   በዚህ የቀብር ስነ ሥርዓት ላይ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሐዋርያው ቶማስ አልነበረም እመቤታችንም በተቀበረች በሶስተኛው ቀን እንደልጅዋ ተነስታ ስታርግ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ህንድ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ ያገኛታል፡፡ https://t.me/yeabuyelejoch      በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው ለእርሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንችን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቻለሁ ብሎ ከደመናው ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አፅናናችው ከእርሱ በቀር ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያት እንዳላዩ ነገረችው፡፡ ለምስክር እንዲሆነውም ሰበኗን ሰጥታው አረገች፡፡ ​ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችንን እኮ ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ሚስጥሩን ደብቆ አይደረግም ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር ››አላቸው እነርሱም ለማሳየት መቃብሩን ሲከፍቱ አጧት ለምስክር ይሁንህ ብላ የሠጠችውን ሰበኗንም አሳያቸው እነርሱም ሰበኗን ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደየ ሐገረ ስብከታቸው ሄደዋል፡፡        በዓመቱ ትንሳኤሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ሳናይ ይቅርብን ብለው ከነሐሴ ጀምረው ሱባኤ ገቡ ከነሐሴ 14 ቀን ትኩስ በድን አድርጎ ጌታችን ሰጥቷቸው ከቀበሯት በኋላ በነሐሴ 16 ተነስታለች በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም መንበር አድርጎ አቁርቧቸዋል እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች፡፡         ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሐዋርያት ቤተክርስቲያን የእመቤታችን በረከት ለማግኘት ትፅማለች በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ይህ ፆም በተለይ ሕፃናት ያከብሩታል በዚህም 15 ቀን ፆም የማይፆም የማይቆርብ ሕፃን የለም፡፡ የእመቤታችን ፍቅር የበዛላቸው ብዙ ምዕመናን ቤታቸውን እየዘጉ በየቤተ ክርስቲያኑ ሱባኤ ገብተው በፆም በፀሎት ይሰነብታሉ፡፡ ፆሙም የሚፈታው በትንሳኤዋ መታሰቢያ ዕለት በነሐሴ 16 ነው፡፡ https://t.me/yeabuyelejoch ✝ፈጣሪያችን ጾሙን የበረከት የረድኤት የንሰሐ የምህረት ያደርግልን አሜን!!! 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹✝✝✝🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 https://t.me/yeabuyelejoch #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ #ይቀላቀሉ
Показать все...
የመካነ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስና አቡነ አረጋዊ ቤ/ክ ልጆች

ሰላም ለሀገሩ ወሰላም ለደብሩ ወሰላም ለመቃብሩ ገ/መንፈስ ቅዱስ አቡዬ ለእግዚአብሔር ፍቁሩ ደመናት አንኰርኲሩ አእዋፈ ሰማይ ዘመሩ በጊዜ ሞትከ መላእክት አንከሩ ሰአል ለነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቅድመ መንበሩ ለክርስቶስ።

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ሥርዓተ ማህሌት ዘ ሐምሌ ቅዱስ ገብርኤል << ፲፱ >> 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 በመጀመሪያ ሥርዓተ ነግስ፦ ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን: አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን: ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን: ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን: ወሥርጋዌሁ እሳት ለቂርቆስ ሕጻን፡፡ ዚቅ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አንቃዕዲዎ ሰማየ: ጸለየ ወይቤ ቅዱስ ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ: ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር: እጼውዓከ እግዚእየ: ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ። ነግሥ ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡ ዚቅ ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል: ወብሥራት ለገብርኤል: ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል። ዘጣዕሙ፦ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣእሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ:ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ:እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡ ዚቅ ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ: ወአዘዘ ደመና በላዕሉ። መልክአ ቂርቆስ ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕጻን: ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን: ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን: ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን: ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡ ዚቅ ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ: ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ: መላእክት ይትዋነይዋ: ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ: ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን: እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር። ወረብ "ኢየሉጣ ወለደት"/፪/ ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት/፪/ ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ: እንተ ተመትረ እምጒንዱ: ሕፃን ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ: ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ: ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ። ዚቅ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት: ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት። ወረብ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ/፪/ ድምጻ "ለጽሕርት"/፪/ ከመ ነጎድጓደ ክረምት/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ: ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ: ሕጻን ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ: መኑ ከማከ ለእቶን አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ: ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ። ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ኢትፍርሂ እም ንፈጽም ገድለነ። ወረብ ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት/፪/ ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ: ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ: በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስዕለትከ መብረቅ: አቊረርከ ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ: ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ። ዚቅ በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት: ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር: ጽዋዓ ሕይወት ወሀቦሙ: መገቦሙ ወመርሆሙ: እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡ ወረብ በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት/፪/ ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ/፪/ መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ: እለ ሥዑላን በነድ: አስተምሕር ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ: ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ: ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡ ዚቅ በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም: ወኢብድብድ በሰብእ: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ: ወኢአባረ እክል: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ: ወልደ አንጌቤናይት፡፡ ወረብ በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ/፪/ ባርካ ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን/፪/ መልክዐ ኢየሉጣ ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ: ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ: ኢየሉጣ ቅድስት ለቂርቆስ ወላዲቱ: ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ: ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ። ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት: ሰላም ለኪ: ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ: ኢየሉጣ እምነ: ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ: ሰአሊ ለነ አስተምሕሪ ለነ: ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡ መልክዐ ገብርኤል ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ: ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ: ገብርኤል ዉኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ: አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ: ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ። ዚቅ ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት: ወበላሕኮሙ እምእሳት: አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ: እምዕለት እኪት። ወረብ ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት ሊቀ መላእክት/፪/ እግዚኦ አድኅነነ "ሃሌ ሉያ"/፪/ እም ዕለት እኪት/፪/ ምልጣን፦ ይቤላ ሕፃን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ አመላለስ: ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/ ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ/፪/ ወረብ ይቤላ ሕፃን ለእሙ "ኢትፍርሂ እም"/፪/ ነበልባለ እሳት/፪/ ዘአድኃኖሙ "ለአናንያ"/፪/ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/ እስመ ለዓለም ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ: አምላኮሙ ለቂርቆስ ወእሙ: በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም: ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ ዕቶን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አኃዘ ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሀባ ቅድመ መኮንን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ: እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አእኰትዎ ወሰብሕዎ: ወባረክዎ ለአብ፡፡ አመላለስ አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፪/ አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፬/ ወረብ ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ/፪/ እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ እምዝ ዳግመ/፪/ ✥✥✥✥✥✥✥ https://t.me/ermiasyeabolje https://t.me/ermiasyeabolje https://t.me/ermiasyeabolje
Показать все...
ማህሌት ዘያሬድ

"ያሬድ ማኅሌታይ ለእግዚአብሔር ካህኑ፤ ስብሐተ ትንሣኤሁ ዘይዜኑ፤ ኦሪት ቶታኑ ወወንጌል አሣዕኑ፤ ትርድአነ ነዓ በህየ መካኑ፤ ከመ ፀበል ግሁሣን ፀርነ ይኩኑ።" ' ' የየበዓላቱን ሥርዓተ ማኅሌትንና የሰንበት መዝሙራትን እዚህ ያገኛሉ ። @Yeabuyeljenegi

እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ መልካም በአል ይሁንላችሁ ሀምሌ 05 2014 ዓ.ም 💚@yeabuyelejoch💚 💛@yeabuyelejoch💛 ❤️@yeabuyelejoch❤️
Показать все...
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል "ሰኔ ፲፪" የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ: ብኡላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ: እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ: ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ: ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ። ዚቅ ኢይጽሕቅ ዘይመክሮ ወኢየኀሥሥ ዘይመክሮ: አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት: ኢየኀልቅ መንግሥቱ ወአልቦ ዘይክል መዊዓ ኀይሉ: ወአልቦ ኁልቊ ለሠራዊተ መላእክት እለ ይትለአክዎ: አንተ ውእቱ አቡሃ ለጥበብ: ገባሬ ኲሉ ፍጥረት ወገባሪሃ ለሕግ። ነግሥ ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል: እንበለ ባህቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል። ዚቅ አመ ይነፍህ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት። መልክዐ ሚካኤል ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ: ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ፀሃፈ: ሶበ እጼውእ ስመከ ከሢትየ አፈ: ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ: ለረዲኦትየ ነዓ ሠፊሐከ ክንፈ። ዚቅ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዓቢተነ በመድኃኒትከ: ጸግወነ ንጸውዕ ስመከ: ኖላዊነ ኄር ትጉሕ ዘኢትነውም ሰላመከ ሀበነ። ወረብ ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ/፪/ ዘኢትነውም ትጉሕ "ኖላዊነ ኄር"/፪//፪/ መልክዐ ሚካኤል ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ: በእንተ ስጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ: ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ: ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ: በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ። ወረብ ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/ "በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምአኒ ቃለ/፪/ ዚቅ አመ ይነፍሕ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት። መልክዐ ሚካኤል ሰላም ዕብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ: ዘኢይረክቦን ጥረስ: ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ: እስመ ረሰይከ ካህነ ምሥዋኡ ክርስቶስ: መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ። ዚቅ ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ ምስሌሁ: ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ: ዮም ሰማያዊ በምድር አስተርአየ። ወረብ ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ/፪/ ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ ስዕንኩ/፪/ መልክዐ ሚካኤል ሰላም ለእስትንፋስከ ቁሱላነ ነፍስ ለአጥዕዮ: ዘይነፍሕ ፄና አንህዮ: ሚካኤል ነዓ ኲናተከ በተረስዮ: ለገቢር ከመ ቀዳሚ ለአርዌ አመፃ ደርብዮ: እስመ ኢኃደገ እንከ ዘትካት እከዮ። ዚቅ ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ: ወእከስተ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን: ወእፈውስ ሎሙ ለቁሱላነ ልብ: ወእሰምዮ ለባሕራን ኅሩየ: ዝኬ ዘተነግረ በመዋዕለ ትካት: ለ፳ኤል ኅብስተ መና ዘአውረደ በገዳም: ወርእየቱ ከመ ተቅጻ ወከመ አያያተ መዓር ጥዑም ፈድፋደ። ወረብ "ወከሢቶ ረከበ"/፪/ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ/፪/ ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ/፪/ መልክዐ ሚካኤል ሰላም ለአጻብኢከ መጽሐፈ እለ ለክዑ: ዕጒለ አባግዕ እምኖሎት በጊዜ ተመልዑ: ሚካኤል አንተ ለንጉሠ ነገሥት ካህነ ምሥዋኡ: አሣዕነ መድኃኒት ለእገርየ አጻብኢከ ይቅጽዑ: ከመ በፍናውየ የኀዝ ለሰላም ቅብዑ። ዚቅ ቅዱሳት አጻብኢከ ለጽሒፈ መጽሐፍ እለ ተቀንያ: ወብጹዓት አዕይንቲከ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ: ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ። ወረብ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ አዕይንቲከ/፪/ ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ "ሚካኤል መልአክ"/፪//፪/ መልክዐ ሚካኤል አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክዕከ ኲሉ: ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ: ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ: ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኃ ሰማያት ዘላዕሉ: ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ። ዚቅ መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል: ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ: አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ። ወረብ መልአከ ሰላምነ/፬/ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል በእንቲአነ/፪/ ምልጣን አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ: ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ: ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ: ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ። አመላለስ ወሪዶ እመስቀሉ/፪/ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ/፬/ ወረብ አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ/፪/ ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ/፪/ እስመ ለዓለም እምድኅረ ተንሥአ እሙታን ዓርገ ውስተ ሰማያት በስብሐት አምላከ ምሕረት: ወተቀብልዎ አዕላፋ አዕላፋት: ወሚካኤል ሊቀ መላእክት በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር: ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር። ዓዲ (ወይም) እስመ ለዓለም ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ: አዓርግ ሰማየ አቡየ ወአቡክሙ: ኀበ አምላኪየ ወአምላክክሙ: ዘንተ ይቤሎሙ ዓርገ ውስተ ሰማያት: ካዕበ ይመጽእ በዘዚአሁ ስብሐት: ሠርጎሙ ለሐዋርያት ብርሃኖሙ ለእለ ውስተ ጽልመት: መድኃኔ ነገሥት ክብሮሙ ለመላእክት ኖላዊሆሙ። አመላለስ በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር/፪/ ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር/፪/ ኦ አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ዕቀብ ሕይወተነ ወሥረይ ኀጢአተነ፤ አድኀነነ ወባልሐነ ከመ ኢይርከብ ኃይለ ላዕሌነ ዝንቱ ደዌ ዘኮነ በመዋዕሊነ፡፡ ክፍለነ እምበረከትከ ቅድስት፡ በጸሎተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለ አሥመሩከ እምፍጥረተ ዓለም፡፡ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 @yeabuyelejoch 💚 💛 @yeabuyelejoch 💛 ❤️ @yeabuyelejoch ❤ Join & Share መልካም በአል
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንኳን ለሐዋርያት ጾም በሰላም አደረሰን መልካም ጾም 💚@yeabuyelejoch💚 💛@yeabuyelejoch💛 ❤️@yeabuyelejoch❤️
Показать все...
5/10/14 ዓ.ም በዓለ ጰራቅሊጦስ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበ ወንጌልና ምስባክ፡፡ የዕለቱ_ምስባክ:- መዝ 117÷24 ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ። ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ። ኦ እግዚኦ አድኅንሶ። ትርጒም፦ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት። ሐሴትን እናድርግ በእርሷም ደስ ይበለን። አቤቱ እባክህ አሁን አድን። የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ፥20 ÷1- 19 ቅዳሴ፦ ዘዲዮስቆሮስ 💚 @yeabuyelejoch 💚 💛 @yeabuyelejoch 💛 ❤️ @yeabuyelejoch ❤️
Показать все...
393355556.mp31.14 MB
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.