cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

እኔ ነኝ 🤍🤍

ደረቅ...ጨካኝ ... ልብ የሌለህ ነህ ... ግን ደሞ አፈቅርሀለው በርግጥ ይሄ ያልኩት ላንተ አይገባህም ግን ?

Больше
Рекламные посты
189
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ምስኪኗ እናት 😔 🎤Hሀበሻman
Показать все...
2.88 MB
ከለሊቱ 7፡52 ነው የስልኬ ሰአት መቁጠሩን አላቆመም በህይወቴ ይህች ሰአት የመጨረሻ እስትንፋሴ መሰለችኝ ከአይኔ ይሚወጣውን እንባ ማቆም አቃተኝ የእኔ እና አንተ መለያየት ህልም መሰለኝ ደም ህልም ነው እያልኩ ለራሴ እየነገርኩት ነው እንቅ አድርግ የያዘኝ ነገር አለ ምን እንደሆነ እንጃ ተነስቼ በእንባ የራሰውን ፊቴን ታጠብኩ ግን ያው ነው እንባዬ አልቆም አለ ስልኬን አንስቼ አስቂኝ ምስሎችን ማየት ጀመርኩ ግን ጭራሽ አስለቃሽ ሆኑብኝ ምን ላድርግ ምሆነው ጠፋኝ የሞትክ እስኪመስለኝ ልቤን እያፈነው እንባዬ ይወጣል እንደመተኛት ስል ከኔ እቅፍ ወጥተህ ሌላኛዋ እቅፍ ስትገባ አየሁና ነቃሁ አባት ምን የታደለችው ናት ያንተ ምትሆነው እንጃ ብቻ ፍርሃት ተጨምሮ መተንፈስ ራቀኝ እይ የኔ ነገር ደሞ ምን ልሆን ነው የመጨረሻዬን ላቅፍህ ላይህ ቅጠረኝ ያልኩህ እ አይኔን ስጨፍን አቅፋህ የማያትን ሴት እነቂያት ጎትተሽ ጣያት የሚል መንፈስ ይይዘኛል አንድ ነገር ልንገርህ ሁሌም ያጋጠመኝን የሰራሁትን እፅፍልሀለው ቃሌ ነው እንደምታነበውም አውቃለሁ በአንተ ትላንቴን ረስቼ ሰላም ሁኜ ነበር አንተ ማስረሻዬ ነበርክ አባት ለአንተ ከእኔ የተሻለች እናት ታስፈልግሀለች ግን 😔😔😔😔😔 ብቻ አባት እወድሃለሁ ማንም ሴት እንደ እኔ አትወድህም አትችልምም አቢ እናት ትወድሀለች😔😔😔ለሊት 8፡40 ህዳር13ለ14 አጥቢያ ምስኪኗ#እናት 😔😔😔💔🖤
Показать все...
ናፍቆቴ እንደ ቀልድ ለስሜቴ ሳይጠነቀቁ ምንም ሳይመስላቸዉ ዳግም እንደማላኝህ ከኔ በጣም እንደራቅክ ነገሩኝ ልትመጣ ነዉ ብዬ እየጠበኩህ ባለሁበት ሰአት ይህንን አሉኝ ታዉቆኝ ነበር ታዉቃለህ እየጠበቁህ የነበሩት አይኖቼ በቃን ብለዉ አለቀሱ መቅረትህን የሰሙት ጆሮዎቼ አለመስማትን ፈለጉ በፊት ትመጣ የነበረበት ቦታ ሳይሰለች ይሄድ የነበረ እግሬ መሸሽ ፈለገ ብቻ ጨካኝ ነህ 😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔 #እናት
Показать все...
ለመናገር የምፈራቸው ስሜቶቼ ባይታፈኑ ፣ ከዛሬው የተሻለ ደስታ እንዲኖረኝ ያደርጉ ነበረ ወይስ ከዚህ የባሳ ሁኔታ ላይ ይጥሉኝ ነበረ?
Показать все...
❤️...ሲመሽ አንገትህ ከአንገቴ ሾር ተሸጉጦ.. እጆችህ በክንዴ ላይ ወድቀው.. ልባችን እኩል እየመታ.. ትንፋሻችን እየፈጠነ.. ሁሉም ሰላም የሚሆንበት የኛን ዓለም ናፍቂያለሁ!..             ...❤️
Показать все...
እስካገኝህ ........ ጥንቁቅ ነበርኩ ከፍላጎቴ ዝንፍ የማልል በደስታዬ የማላወላውል መከበርን አብዝቼ የምሻ እራሴን ካማከሉ እቅዶች የማልዘምም ምን አልባትም ባህሪዬ ከጥንቁቅነት ይልቅ ወደ ግትርነት የሚያደላብኝ በራሴ ዛብያ ብቻ የምሽከረከር አንድ እኔ ነበርኩ ። ከኔነቴ አጥር ውጪ ሌላ አለም ተመለከትኩ ለካ ከኔው አለም የተለየ ውብ ነበር ከዳመናው ፊቴ ይልቅ ሳቅ የዘራህበት ይበልጡኑ ለሰው አቅርቦኛል በትግል ያመጣሁትን ክብር ፍቅር ሰጥተህ አስጥለሀኛል ። ለካስ ሂወት ከሰው ጋር ሲጋሯት ትጣፍጣለች እስከ ጥግ ወደድኩህ ያኔ ይበልጡኑ ውብ ሆንኩኝ እጄን ይለዘህ ፍቅርን አስተማርከኝ ፣ አንተ የሂወቴ የኔታ እንኳንም በፍቅርህ ወደኩኝ እንኳንም ተሸለምኩህ ❤️❤️ ፊትህን ባየው ቁጥር የሂወቴን ፍቅር እመለከታለው አንዳንዴ መፃፍ ፈልጌ አልፅፍም ስላንተ ቃላቶች እራሱ ደክመው ይታዩኛል ለመቸክቸክ የሚፈጥነው እጄ ይዝለፈለፈል የፈረደበት ልቤ ከጭንቅላቴ ጋር መግባባት አይችልም ፍቅርህ ተስጥቶኝ ነው ።
Показать все...
ሲነጋ ናፍቆት🥺 ልቤ በጣም ያማረ ነው......እንደ ነብሴ ስለመረጠህ ❤️
Показать все...
ሰሞኑን ለአይኔ በዝታ የነበችው ጨረቃ መልሳ ጠፋች ፈለኳት ጠበኳት ግን ተመልሳ መምጫዋ ራቀብኝ እሷን ሳያት አንተን ያየውህ ያክል ውስጤ በሀሴት ትሞላለች ሰዎች ስለወጣችው ጨረቃ ሲያወሩ ስላንተ እያወሩ እየመሰለኝ እንደ ህፃን አፋቸው ስር እውላለሁ አዎ አንተን ትመስላለች ይኸው እንዳንተ ለአፍም ለአይንም እንዳትሆን ሆና ጠፋች ናፍቆቴ ማርያምን ናፍቀኸኛል ከብዙ አመታት በኋላ ላይህ ነው መሰለኝ ውስጤ ሰላም አጣ ናፍቀኸኝ በማታውቀው ልክ ናፈከኝ ብትመጣ ባይህም እኮ አላቅፍህም አንተም ናፍቀኸኝ እንደነበር አታውቅም ዝም ብዬ ግን አይንህን ብቻ ባየው ብዬ ተመኘሁ ሚገርምህ ናፍቆቴ አመታት ቢሆኑም ጠረንህ ግን እኔ ጋ አሁንም አለ አልጠፋም አረሳሁትም ግን ናፍቆቴ ፊቴ ጠፍቶብህ መልኬ ተረስቶህ ይሆን ብቻ አደራ ፈጣሪ ብሎ ዳግም ባገኝህ ማነሽ እንዳትለኝ እባክሽ ጨረቃ ከአንቺ ጋ የጠፋውን ናፍቆቴን ደግመሽ ስትመጪ መልሽልኝ ናፍቆኛል 😔😔😔😔😔 #እናት 😔
Показать все...
ናፍቆቴ😔💔🖤❤️ ልጠላህ እየፈለኩ ........ አፈቅርሀለው ማግኘት አለመቻሌ አሳጣኝና በሀሳቤ ደጋግመህ እንድትመጣ አደረገህ። ሰው የልቡን ሰው ትላንቱን በምክንያት ያስታውሳል ቢባል ለምን እንዳልል አድርገኸኛል! ከተነጣጠልን ተለያይተን መኖር ከጀመርን ብዙ ግዜ ተቆጥሯል። ታድያ በነዚህ ጊዚያት የማስታውሰውን የነበረንን እያሰብኩ ብብዙ ወደኋላ ስመለስ አንተ ግን እነዚያን ግዚያት ተጠቅመህ ለታሪክ እስኪቸግር ርቀኸኛል😔 ናፍቆቴ.... ከራሴ በላይ ነው አሁንም የማፈቅርህ ማንንም ብቻ ሳይሆን ዛሬዬን በህመም እንዲዳኙብኝ አልፈልግም ብዙ ምክንያቶች ሊኖራቸው፣ እውነት ከነሱ ቤት ታድር ይሆናል። ግን የኔን ባንተ ሚዛን እንዲሰፍሩት እንዲፈርዱልኝ አልሻም ! ናፍቆቴ..... ትላንት ነው ብዬ በተለያየንበት ቦታ ልተውህ አልተቻለኝም ሌላ ጓደኛ ይዘሃል እኔን ረስተኸኛል፣የራስህን ኑሮ እየኖርክ ነው አውቃለሁ የሄደም አይመለስም የሰውም የሰዉ ነው ፣የተበጠሰ አይቀጠልም ግን የወደደህ እኔነቴ ያነገሰህ፣ያፀደቀህ አንደበቴ በምን ምክንያት ይጥላህ?? ደከመኝ ናፍቆቴ.... መርሳትን አላውቅበትም መንገዱንም የሚያሳየኝ የለም።ልቤም ጠቆረ 🖤 ደከመኝ ተሰበርኩ💔 ጠልቼህ በለያየንበት ብተውህ እኔም በወደድኩ። ናፍቆቴ....ልጠላህ እየፈለኩ አፈቅርሀለው።።😔😔 ስለወደድኩት #እናት
Показать все...
የትኛው ነው ትክክል??😕 ውስጤ የሆነ ነገር አለ ግን መፃፍ ያልቻልኩት የመጣልኝን ልፅፈው ሳስብ ውስጤ ከሱ የባሰ አለ ይለኝና ሌላ ሀሳብ ይደርብብኛል ትላንት ስለነበርኩበት ልፃፍ ወይስ ዛሬ ስላለሁበት አይ አይ ቆይ ስለ ነገዬ ይሻላል ግን ነገን ስደርስበት ይሻላል አደል ትላንትም አልፏል ዛሬም ያው ዛሬ ነው ኤጭ ለምን ራሴን አጨናንቃለሁ ውስጤ የሚመላለሱ ብዙ ነገሮች መልሳቸው የት ነው? እኔጋ? አንተጋ? አንቺጋ? ቆይ ማን ጋር ነው ብዙዎች መጥፎ ሰው መሆኔን ይነግሩኛል ግን አይርቁም እየነገሩኝ አብረውኝ ናቸው ሌሎች አንዳንዶች ደግሞ ጥሩነቴን እየነገሩኝ ግን ይሸሹኛል የትኞቹ ናቸው ትክክል ?? ትላንት ያገኘሁት ወዳጄ ደሞ የባሰ ነበር መጥፎነቴን ሲነግረኝ ቆየና ቀናት ሳይቀያየር ሰአት ሳይደራረብ መልካም ሰው መሆኔን ይነግረኝ ጀመር ወቸ ጉድ እህ ብዬ ካዳመጥኩ ሰው በዙ ነገር ነሽ ይለኛል ስለዙህ የራሳቸው ጉዳይ ብዬ ሀሳቤን ዘጋሁ #እናት
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.