cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ

የቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ ቻናል ተከታታዮች ይህ ቻናል ለተለያዩ ትምርቶች የተዘጋጀ ሲሆን 1. ስለ ዕምነታችን 2. የቤተ ክርስቲያን ስነ-ምግባሮችን የምናውቅበት 3. ስለ ህይወታችን በምን መንገድ ማሳለፍ እንዳለብን በቅዱሳን አባቶቻችን ትምህርት በምክር መልክ እንማማራለን 4. የተለያዩ መዝሙራት እንዲሁም መዝሙረ ዳዊት በየቀኑ ከዚህ ቻናል ማግኘት ይችላሉ። ጓደኞትን በማስገባት ይተባበሩን አመሰግናለው

Больше
Рекламные посты
690
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ፤ ***   1. በክልል ትግራይ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት አህጉረ ስብከት ጋር ተቋርጦ የነበረውን መዋቅራዊ ግንኙነት ችግር በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና ልዑካኑን በአካል ልኮ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ተብለው በሚጠሩበት በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 15 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከናወነ ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፈጸሙን በመገናኛ ብዙኃን ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም በዚህ የዶግማና የቀኖና ጥሰት ተግባር የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በእጅጉ አዝኗል፡፡  2. በመሆኑም የተከሰተው የዶግማ፣ የቀኖና እና አስተዳደራዊ ጥሰት አስመልክቶ ተወያይቶ ተገቢውን ለመወሰን ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ ተላልፏል፡፡ 3. የስብሰባው ቀን ሊራዘም የቻለው በውጭው ክፍለ ዓለማት ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት መገኘት ስላለባቸው የጉዞ ቀኑ እንዳያጥር እና በሀገር ውስጥ የሚገኙትም ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት ለአገልግሎት ወደ አህጉረ ስብከታቸው የሄዱ በመሆኑ ለመመለሻ የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡ 4. በየደረጃ ያሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ኃላፊዎች እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምዕመናን ከአሁን ቀደም በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በደረሰው ፈተና በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን በመቆም ላሳያችሁት ጽናት እያመሰገንን አሁንም በደረሰው ፈተና እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን ጸንታችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ 5. በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በትግዕስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡ 6. ምንም እንኳን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ ጥሪው በደብዳቤ የተላለፈ ቢሆንም የመልእክቱ በፍጥነት መድረስ ካለው ስጋት አንጻር የችግሩን ተደጋጋሚነትና አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ተጠቃላችሁ ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ 7. ሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን ሚዲያዎችና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን ይህን መልዕክት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን መልእክቱን በማስተላለፍ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እንጠይቃለን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም.
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ደስታ የት ነው ያለችው? ደስተኛ ሕይወት መኖር የብዙ ሰው ፍላጎት ነው ሰው ከሁሉም ነገር በላይ ለደስታ ሲል እውቀቱን ጉልበቱን ገንዘቡን ያወጣል በዚሕ መልኩ ደስታውን ሲፈልግ ብዙ ሰው አያገኘውም የደስታ መገኛ ወዴት ነው?  ደስታን ሰው በተለያየ ቦታ እየዞረ ይፈልጋታል አንዳንዱ መንፈሳዊ ቦታዎች በመሔድ ይፈልጋታል አንዳንዱ በእውቀት መገኛ ቦታ በትምሕርት ቤት ይፈልጋታል አንዳንዱ በሥራ ቦታ በሥራ ውስጥ ይፈልጋታል አንዳንዱ ደግሞ በመዝናኛ ቦታዎች ዘና እያለ ይፈልጋታል አንዳንዱ ደግሞ በመጠጥ ቤት እየጠጣ መጠጥ ውስጥ ይፈልጋታል አንዳንዱ በስፖርት ቤት በስፖርት ውስጥ አንዳንዱ በማሕበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ አንዳንዱ በእንቅልፍ አንዳንዱ በሀብትና ንብረት ውስጥ ይፈልጋታል ግን በሁሉም ውስጥ ደስታ አትገኝም ደስታ ለአንተ ታስፈልግሀለች እንጂ አንተ ለእርሷ አታስፈልጋትም ደስተኛ መሆን የሁሉም ፍላጎት ነው ሰው ለረጅም ዘመን ያካበተውን ሀብት ለደስታ ለማውጣት አይግደረደርም ምክንያቱም ሁሉም ለደስታ ነውና ታዲያ እቺ በሰው የምትወደድ የምትፈለግ ደስታ መገኛዎ ወዴት ነው?  መገኛዎማ ራስሕ ውስጥ ነው አንተ በውጪ ትፈልጋታለሕ እንጂ ደስታ ያለቺው ውስጥሕ ነው ዎጋዎም ርካሽ ነው ደሀውም ሀብታሙም እኩል ገንዘብ ሊያደርጓት ይችላሉ ። ደስታ ውስጥሕም ብትሆን የአንተ አያያዝና አጠቃቀምሕ ነው ሕይወት የሚዘራባት ካለበለዚያ በውስጥሕም ብትኖር ትገድላታለሕ ደስታን የምትፈልጋት ከሆኔ እኔ ልጠቁምሕ በሕሊናሕ ውስጥ ወዳለው እውነት ግባ በዛም ውስጥ ደስታሕን ታገኘዎለሕ እውነትን ተቀበል በእውነት ኑር እውነተኛ እርዳታ አድርግ በእውነት የኑሮ ደረጃሕን አምነሕ ተቀበል ገንዘብ ስትሰበስብ ሳይሆን ገንዘብን ስትሰጥ ነው ደስታ ምታገኘው  በእውነት ፍረድ በእውነት ምከር በእውነት ሥራ በእውነት አግባ በእውነት ጸልይ በእውነት አግኝ በእውነት ተማር ለእውነት ተጠቀምበት በእውነት አስተዳድር በእውነት ተመራ በእውነት ውደድ በእውነት ተወደድ በእውነት ዝቅ ዝቅ በል በእውነት ድከም በእውነት አግኝ ለእውነት ኑር ለእውነት ሙት እዛ ውስጥ ነው ደስታ የምትገኘው ።         መልካም ምሽት ይሁንላችሁ
Показать все...
#የአባ_እንጦንስ_ምክሮች ✞ ከዕለታት በአንድ ቀን አባ ፓምቦ አባ እንጦስን "ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድን ነው?" ብሎ ይጠይቃል።አባ እንጦስም እንዲህ ሲል መለሰለት "በራስህ ጽድቅ አትታመን፤ላለፈው አትጨነቅ፤ይልቁኑ አንደበትህንና ሆድህን ግዛ።" ✞ አባ እንጦስ በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፦ "በዚች ምድር ላይ ስንኖር ህይወታችንንም ሆነ ሞታችን ከባልጀራችን ጋር ነው። ወንድማችንን ገንዘብ ካደረግነው እግዚአብሔርን ገንዘብ እናደርጋለን፤ ወንድማችንን ካስቀየምነው ግን በክርስቶስ ላይ ኃጢአትን እናመጣለን።" ✞ በአንድ ወቅት አንድ ወንድም አባ እንጦስን "ጸልይልኝ" በማለት ይጠይቃል። እንጦስም "አንተ ራስህ ጥረት የማታደርግና ወደ እግዚአብሔር የማትጸልይ ከሆነ እኔም ሆንሁ እግዚአብሔር ምህረት ልናደርግልህ አንችም" አለው። ✞ እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ። ✞ ኃጢአታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል፤ ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል። ✞ ብዙ ጊዜ ሰዎች ብልህ ነን እያሉ ይሳሳታሉ። ነገር ግን ብልህ የሚባሉት ብዙ የተማሩና ብዙ ያነበቡ ብዙ የሚናገሩ ብቻ አይደሉም። ይልቁንም ጠቢባን የሚባሉት ጥብብት መጥበቢት ብልህ ነፍስ ያላቸው፤ የእግዚአብሔርንና የሰይጣንን ለይተው ለእግዚአብሔር ሆነው የሚኖሩ ናቸው። ፍጹም ምልዓተ ኃጢአትንና ከጦር ይልቅ የሚወጉ የኃጢአት እሾሀቸውን የነቀሉ ናቸው ጠቢባን። ✞ ጠቢባንስ እግዚአብሔርን ያለጥርጥር በሙሉ ልብ የሚያምኑት፤ አምነውም እንደ ፈቃዱ የተከተሉት፤ በክንፈ ጸጋ ተመስጠው ከልብ በሚወጣ ውዳሴ ከእርሱ ጋር ተዋሕደው የሚኖሩ ናቸው። የነፍሳቸውን ረብሕ ጥቅም አውቀው ዕለት ዕለት ያንን የሚለማመዱ በእውነት ጠቢባን እነዚህ ናቸው። ✞ የጋለ ብረትን ለመቀጥቀጥ የሚነሣ ሰው አስቀድሞ በብረቱ ምን ለመሥራት እንዳሰበ መወሰን አለበት፤ መጥረቢያ፥ ሰይፍ፥ ወይስ ማጭድ? እኛም በምን ዓይነት የሕይወት መስመር ፍሬ ለማፍራት እንዳሰብን አስቀድመን ልቡናችንን ማዘጋጀት አለብን፡፡ ✞ ዘወትር በዐይንህ ፊት ፈሪሃ እግዚአብሔር ይኑር፤ ሕይወትና ሞት የሚሰጠውን አዘክረው፡፡ ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ጥላው፤ ከሥጋ የሚመጣውን ደስታና ሰላም አትሻ፤ ለዚህኛው ኑሮ ሙትና ለእግዚአብሔር ሕያው ሁን፤ ለእግዚአብሔር ቃል የገባኸውን አትርሳ፤ ያም በፍርድ ቀን ካንተ ይፈለግብሃል፡፡ ረኀብን በጸጋ ተቀበለው፤ ተጠማ፥ ተራቆት፥ ንቁና በሐዘን የምትኖር ሁን፡፡ በልቡናህ አልቅስና ጩኽ፤ ለእግዚአብሔር የምትመች መሆን አለመሆንህን ፈትን፤ ሥጋህን ቀጥተህ ነፍስህን ታድናት ዘንድ፡፡ ✞ የቱንም ያህል በመከራ ቢወድቅብህ የቱንም ያህል በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ብታልፍ ይህንን ለጌታዬ ለመድኃኒቴ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስል እቀበላለሁ በል። ቀላል ይሆንልሀል። የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ኃይል ነውና። በእርሱ ማእበሉ ፀጥ ይላል ሰይጣንም ይሸሻል። ✞ ለተወሰን ጊዜ ለሀይማኖት መከራከር፤ ጠበቃ መሆን፤ መዋጋት ብሎም መሞት አይከፋም ሁልጊዜ ለሀይማኖት መኖር ግን ከሁሉ የበለጠ መስዋእትና ክብር ያለው ህይወት ነው፡፡ (#ከተለያዩ_ጽሑፎች_የተሰበሰቡ)
Показать все...
ዘፈን ጥበብ ነውን???? (ከቃለ እግዚአብሔር) ዘፈን ጥበብ ነው የሚሉ አሉ። አዎን ጥበብ ነው ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከሰይጣን የተገኘ ጥበብ ነው፤ ቅዱስ ሳይሆን ርኩስ ጥበብ ነው፤ መዳኛ ሳይሆን መጥፊያ ጥበብ ነው፤ የህይወት ሳይሆን የሞት ጥበብ ነው፡፡ ይህን ሳስብ ቅዱስ ጳውሎስ የዚች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነት ነው ያለውን እናስታውስ። እግዚአብሔር ድምፅ የሰጠን እሱን እንድናመሰግንበት እሱን እንድናወድሰው፣ እሱ የፈቀደላቸውን እሱ ያከበራቸውን ቅዱሳኑን እንድናመሰግንበት ነው እንጂ ለሰው እንድንዘፍን አይደለም። ወይ የእግዚአብሔር ወይም የዓለም ልንሆን ግድ ይለናል፤ ሁለት ጌታ የለም።  ዘፈን መዝፈን ኃጢያት ነው። አሁን ባለንበት ዘመን ዘፈን ኃጢያት እንደሆነ፤ የዲያቢሎስ ታላቅ መሳሪያ እንደሆነ፤ ዘፋኝነት ከክርስቶስ ማህበር እንደሚለይ በግልጽ እየተመለከትን ነው። ዘፈን ስራ ነው የሚሉ አሉ አዎን ለዘፋኝ መዝፈን ስራው ነው፤ ለሌባም መስረቅ ስራው ነው፤ ለዝሙት አዳሪዋም ዝሙት ስራዋ ነው፤ ለቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይም መግደል ስራው ነው ግን ደግሞ ኃጢያት ናቸው ስራዬ ነው ብሎ ኃጢያትነቱን ማስቀረት አይቻልም፡፡ እንግዲህ ምን እንላለን ኃጢያትን ስራ ነው ብለን ሙግት እንገጥማለንን?? እየመረጥን ብንዘፍንስ ለመልካም የተዘፈኑ ዘፈኖች አሉ የሚሉም ብዙ ናቸው። ዘፈን ሀጥያት ነው በቃ ምንም ጥያቄና መልስ የለውም ቴዲ ስለዘፈነው መዝሙር መሆን አይችልም ስለ ሀገር ሆነ ስለምን.. ስለ ሀገር ጸልዩ እንጁ ዝፈኑ አልተባለም፣ እናት ቢዘፈንላትስ ይላል ደሞ አንዱ፣ እድሜህ እንዲረዝም እናትና አባትህን አክብር ይላል እንጂ ዝፈንላቸው አይልም!! ብዙ ሰው ጥብቅና ለቆመለት ሰው ቃሉ ይህን ይላል << ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም!!።">> (ወደ ገላትያ ሰዎች 5:21) አንድ ሌባ ሰርቆ የተራበ ቢያበላ ጽድቅ ነውን??? የተቸገሩ ሰዎችን ከችግራቸው ያላቅቅ ዘንድ አጥብቆ የሚተጋ አንድ ሰው ሌሎችን ለመርዳት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማግኘት ዝሙትን መፈጸም ግድ ቢሆንበት እርሱም ሰውነቱን አርክሶ ዝሙትን ፈጽሞ ገንዘቡን ቢቀበል ችግረኞቹንም ከችግራቸው ቢያላቅቅ መልካም አደረገ እንለዋለንን??? ዘፈን ያስደስታል፣ ዘና ያደርጋል፣ ደስታ ይፈጥራል ... ወዘተ ምክንያቶች እየደረደርን ጥብቅና አንቁም! መልካምን ነገር ለማድረግ በኃጢያት ውስጥ ማለፍ አይጠበቅብንም፤  ኃጢያትን ያደረገ ኃጢያተኛ እንጂ ጻድቅ ሊባል አይችልም፡፡ ነገሩ ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ ነው እንዲያ ካልሆነማ፤ ከኃጢያት ከተመረጠማ ለዘፈን ብቻ ለምን??? የዘፈነው ለመልካም ነው፤ ፍቅርን ለመስበክ ነው፤ አንድነትን ለማምጣት ነው ካልን ሌባውም የሰረቀው የተቸገሩትን ሊያበላ ነው፤ ሰውየውም ዝሙት የፈጸመው ችግረኞችን ለመርዳት ነው፣ ነፈሰ ገዳዩም እንጀራ ሆኖበት ነው። ስለዚህ እነዚህም አብረው ይጽደቁ? እንዲህ ከሆነ ደግሞ ኃጢያተኛ ሁሉ ጻድቅ ሆነ ማለት ነው። ራሳችንን ከማታለል እንውጣ፤ ከአዚም እንላቀቅ አትግደል ከተባለ አትግደል ነው፤ አትስረቅም አትስረቅ ነው፤ አትዝፈን ሲልም አትዝፈን ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ተመራጭ አገዳደል፤ ተቀባይነት ያለው ስርቆት፤ የሚወደድ ዘፈንም የለም፡፡ ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!
Показать все...
ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ፤ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ኹሉ በእርሱ ላይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም፥ አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ስለዚህ በምታደርገው ነገር ኹሉ ሽማግሌህ እርሱ እግዚአብሔር እንዲኾን ዘወትር ጠይቀው፡፡ አስቀድመህ እንደዚህ ካደረግህም፥ ወደ ትዳር ከገባህ በኋላ ፍቺ አይገጥምህም፡፡ ሚስትህ ሌላ ሰውን አትመኝም፡፡ በሌላ ሴት እንድትቀናም አታደርግህም፡፡ በመካከላችሁ [ለክፉ የሚሰጥ] ጠብና ክርክር አይኖርም፡፡ ከዚህ ይልቅ ታላቅ የኾነ ሰላምና ፍቅር በመካከላችሁ ይሰፍናል፡፡ እነዚህ ካሉ ደግሞ ሌሎች በጎ ምግባራትን፣ ትሩፋትን ለመፈጸም አትቸገሩም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Показать все...
#አለማመኔን_እርዳው በዘመነ ሐዲስ በሰው ፍቅር ተስቦ ወደዚህ ዓለም የመጣው ቸሩ አምላክ ለአገልግሎት ከመረጣቸው ሰዎች አንዳንዶቹ ምንም ዓይነት መሠረታዊ የሃይማኖት ዕውቀት አልነበራቸውም፡፡ እግዚአብሔር እነዚህን አላዋቂዎችን የመረጠው በዘመኑ በዕውቀታቸው የሚታበዩ ሰዎችን ዕውቀት ከንቱ ለማድረግ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጌታችን የዓለምን ጥበብ ከንቱ ለማድረግ አላዋቂዎችን እንደመረጠ ሲያስረዳ፤ «እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔር የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም መረጠ፡፡» ብሏል፡፡ 1ኛቆሮ.1፣26-29፡፡ #እግዚአብሔር ለእምነት አገልግሎት ሰዎችን ሲመርጥ ሞኞች ጠቢባን ይሆናሉ፤ አላዋቂዎች ሀብተ እውቀት ያገኛሉ፤ ደካማዎች ብርቱዎች ይሆናሉ፡፡ አላዋቂ የነበሩት ተከታዮቹ ጠቢባን፤ ደካማ የነበሩት ብርቱዎች እስከሚሆኑ ድረስ ለቀጣይ የእምነት ሕይ ወታቸው ብርታት እንዲሆናቸው የተለያዩ ጥያቄዎችን ለጌታችን ያቀርቡ ነበር፡፡ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይከተሉ ከነበሩ ሰዎች ለጌታችን ካቀረቡት ጥያቄ አንዱ «አለማመኔን እርዳው» የሚል ነው፡፡ ጌታችን የቃሉን ትምህርት ሰምተው የእጁን ተአምራት አይተው የተከተሉትን በሕይወት ሰጪ ትምህርቱ በነፍስ የተመሙትን ተስፋ የቆረጡትን፣ ባዶነት የሚሰማቸውን መንፈሳዊ ዝለት የገጠማቸውን ሲፈውስ፤ በተአምራቱ ደግሞ በሕማመ ሥጋ የታመሙትን ፈውሷል፡፡ #የጌታችንን ሕይወት ሰጪ ትምህርት ፈልገው የተከተሉ አብዛኛዎች በተከፈለ ልብ ነበር፡፡ መድኃኒታችን የተከፈለ ልብ ያላቸውን ማረጋጋት፣ ያዘኑትን ማጽናናት ግብሩ በመሆኑ ድክመታቸውን ሳይሸሸጉ የሚቀርቡትን ፈጣን ምላሽ ይሰጣል፡፡ #የጌታችን_ደቀ መዛሙርት ልጁን እንዲፈውሱለት የወሰደው ሰው፤ ከእርሱና ከደቀ መዛሙርቱ የእምነት ማነስ የተነሣ ፍቱን መፍትሔ ቢያጣም ከጌታችን ዘንድ መጥቶ የእምነቱ ጉድለት በጌታችን እንዲስተ ካክልለት የልጁን ሕማም ሁኔታ ከዘረዘረ በኋላ፤ «ቢቻልህ ግን እዘንልን እርዳን» ማር.9፣22 የሚል ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ «ቢቻልህ የሚለውን» የጥርጣሬ ቃል «#ቢቻልህ_ትላለህ_ለሚያምን_ሰው_ሁሉ_ይቻላል፡፡» በሚል ቃል ሲያርመው የተቸገረው ሰው አለማመኑ በእርሱ እንዲጠገንለት «#በታላቅ_ድምፅ_አምናለሁ_አለማመኔን_እርዳው» ብሎታል፡፡ ይህ ሰው አምናለሁ አለማመኔን እርዳው በማለት በእምነት ሕይወት ውስጥ ያለበትን ችግር ሳይሸሸግ መናገሩን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም እያመን የማናምን፣ ንስሐ እየገባን የማንፀፀት፣ እየቆረብን ለሥጋ ወደሙ ክብር የማንሰጥ፣ እየቀደስን ያልተቀደስን ብዙዎች ነን፡፡ እኛም እናምናለን ነገር ግን እምነታችን በአንተ ይታገዝ እርዳን ብለን መጠየቅ አለብን፡፡ ብዙ ሰዎች ክርስቶስ መወለዱን፣ መጠመቁን፣ ከሙታን መነሣቱን (ትንሣኤውን መግለጡን) ያምናሉ፡፡ በዚህ ሕይወት ውስጥ ያላቸውን ድርሻ እና ተስፋ ግን ይጠራጠራሉ፡፡ በሌላ አነጋገር እያመንን በእምነት ሕይወት ውስጥ አንኖርም ለዚህ ማለዘቢያ ግን እምነታችን፣ አለማወቃችንና ድካማችን በጌታችን እንዲደገፍ መማጸን ነው፡፡
Показать все...
📍📍   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ  አሐዱ አምላክ አሜን። 🛎በምስጋና መጠለፍ ና ከንቱ ውዳሴ    ✅ምስጋና የ ባህርይ ገንዘቡ የሆነዉ ለ እግዚአብሔር ነው ።1ኛ ዜና 16፥25, መዝ 18፥3  መዝ 96፥4 ,2ኛ ሳሙ 22፥4 እኛ ሰዎች ደሞ ከ አፈር የተበጀን ፈጣሪ የሰራን ፍጥረቱ ነን በ እኛ  ዘንድ የ ፈጣሪ ክብር እንዲገለጥ ይገባል። ለ ፈጣሪ  ምስጋና ለማቅረብም  አንደበት ተሰርቶልናል። መዝ 34፥1 "ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው።" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ። ❇️  ሆኖም ግን   ለ ፈጣሪ የሚገባውን ምስጋና ለ ራስ ማድረግ መጣጣር በዘመናችን አገልጋዮች በስፋት ይታያል። በዘመናችን  በብዙ አገልግሎቶች ስብከቱ፣ ዝማሬው ፣ ክህነቱ  የራሳቸው እስከሚመስል አገልጋዮች  ሲመፃደቁበት ማየት የተለመደ እየሆነ መጥትዋል ። በዚህ የተነሳ ለ ቤተክርስትያን እኛ እናውቅልሻለን የሚል አካል እየበዛ ፤ አገልጋዮች ከሚሰበከው  ወንጌል በላይ ስለ ድምፅ ጥራት ና ስለ መድረክ አያያዝ ጉዳይ ሲጨነቁ ማየትም የተለመደ ነው።       🛳⛴⛴አንድ መርከብ በ ውሃ የተሞላ ውቅያኖስ ላይ ሳይሰጥም መከሄድ ይችላል። መርከቡ  መስመጥ የምትጀምረው በ ራስዋ ቀዳዳ ተከስቶ፤   በ ውሃ ከተሞላ ውቅያኖስ  ውሃው ሰርስሮ የገባ ጊዜ ነው። አንድ አገልጋይም በሚያገልግልበት ጊዚያት የ ምስጋና ብዛት የ መቆለጳጰስ ጥግ ስለተነገረው ሳይሆን ፤ በ ልቡ ለ ምስጋናዎቹ ና አድናቆቶች ቦታ መስጠት ሲጀምር ነው በ ከንቱ ውዳሴ ተጠልፎ የሚወድቀው። 👨👱በርግጥ ምእመናን ናቸው አገልጋዮች በ ከንቱ ዉዳሴ እንዲወድቁ ፆር እየሆኑ ያሉት  ።  ታቦት ያላቸው ብዙ መካናት ትቶ አገልጋዮች ተከትሎ ሚዋትት ፤ እግዚአብሔር ሳይሆን አገልጋዮች የሚያመልክ ስለ ክርስቶስ ከመስበክ ይልቅ ላንቃዉ እስኪያመው ስለ መምህር እገሌ ዘማሪት እገሊት ሲኸራከር የሚውል ምእመን እንደ ፈሪሳውያኑ በ ነቀፋ የተሞላ ክርስትና የሚኖር ከሆነ ቆይትዋል። ምእመናን ለ እናታችን ሄዋን እንዳሳታት ዲያብሎስ ያለ የ ሽንገላ  ቃላትም ለ አገልጋዮች ከ መናገር መከልከል ይገባናል። ⏹⏹ከመነኮሳት ታሪክ አንድ ታሪክ ለማስታወስ ያክል።⏹⏹        ከዘመናት በ አንዱ አንዲ ወጣኒ መነኩሴ   በ መንፈሳዊ አገልግሎቱ የተነሳ  በብዙ ምእመናን ዘንድ አድናቆትመንፈሳዊ ና  ዉዳሴ ማግኘት ጀመረ በዚህም የተነሳ ደስ  ብሎት ወደ አበመኔቱ ሄደና ስለ መንፈሳዊ አገልግሎቱ በብዙ ምእመናን መወደዱን  አድናቆት ና  ዉዳሴ ማግኘቱን ነገራቸው። አበመኔቱ እንዲህ ብለው  ምክር ሰጡት "ልጄ ሂድና ሙታንን ተሳደብ አሉት  እንዳሉትም ወደ መቃብር ስፍራ ሄዶ ሙታንን ተሳደበ ። በ ሁለተኛው ም ቀን ሂደህ ሙታንን አመስግናቸው አሉት ፤እንዳሉትም ወደ መቃብር ስፍራ ሄዶ ሙታንን አመስግኖ ወደ አበመኔቱ ተመለሰ።አበመኔቱም ሙታን ስትሰድባቸው ሆነ ስታመሰግናቸው ምን አሉህ አሉት ። ወጣኒ መነኩሴዉም ምንም መልስ አልሰጡኝም አላቸው።አበመኔቱም ለ መነኩሴዉም ልጄ አንተም ልብህ ለ ሰዎች ምስጋና  ና ለ ሰዎች ስድብ ክፍት አድርገህ ኑር አሉት።"ስለዚህ ኣእምሮህን ገዝተህ ምስጋና ለ መቀበል እንደምንደረደረው ሁሉ ስድብ የ መቀበልን ፀጋ ቢኖረን  ከ ከንቱ ውዳሴ መራቅ እንችላለን። መፅሓፍ ቅዱስም እንዲህ ይለናል "ሰዎች ስለሰው ልጅ ሲጠሏችኹ ሲለይዋችኹም ሲነቅፏችኹም ስማችኹንም እንደ ክፉ ሲያወጡ ብፁዓን ናችኹ እንሆ ሰርቶም በ ሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችኹ ዝለሉም አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና።" ሉቃ 6፥ 22 -23 ስለዚህ ክርስትያን ቅን ሰርቶም ለሚመጣበት ዘለፋ ለመቀበል ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል።ከንቱ ዉዳሴ የተሞላን ከሆንን ግን እሄ ማድረግ ይከብደናል። 🔅🔅 ለ አንድ ነገር በ ሃላፊነት ስሜት ኣድርጌዋለው ብሎ መናገር ከንቱ ውዳሴ መፈለግ አይደለም። ይልቁ ግን ስለ ችሎታህ ና ስለ ዓቅምህ ከሌሎች የ ምስጋና ችሮታ መጠበቅ ከንቱ ውዳሴ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ በ ቂሳርያ መንፈስቅዱስ የገለጠለትን የ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ሲመሰክር በ ጌታ ዘንድ ሞጎስ አግኝትዋል ። በራሱ  ፍቃድ ሲደገፍ የ ወንድሞቹ የ እነ ዮሃንስ ትጋት ግምት ውስጥ ሳያስገባ "ሁሉ ቢተዉህ እኔ እስከ መጨረሻ እከተልሃለው " የሚል ከንቱ ዉዳሴ ፈልጎ የተናገረዉ ንግግር ግን ያመጣው ውጤት መልካም አልነበረም። እኛም ስናገለግል ጌታ በ እኛ እንዲናገር ፈቅደን የ ወንድማችንን  አገልግሎት አክብረን ሊሆን ይገባል። ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላቹ ወዮላችሁ"ሉቃ 6፥26 ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን በ ከንቱ ዉዳሴ ተጠልፈክ የሚደረግ እዩኝ እዩኝ ማለት የሚሰጠን በረከት ፤ የሚጨምርልን ፀጋ የለም።ስለዚህ ከ ውዳሴ ከንቱ የ ራቀ ቅን አገልግሎት እንድናገለግል ይገባል።
Показать все...
#ማርያም "የሚመጥናትን ምን ዓይነት ልዩ ምስጋና እናቅርብላት? የዚኽ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና፤ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር “ዓለም አልተገባቸውም” (ዕብ ፲፩፥፴፰) ካላቸው፤ ለአምላክ እናትማ ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሓይ ለኾነችው ለርሷ ምን ልንል እንችል ይኾን? (ራእ ፲፪፥፩) ምን ምስጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናንና አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነ አስተውል፤ ታዲያ የአምላክን እናት ታላቅነት ኹሉም ሰው እንደምን አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ላገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፤ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፤ ጴጥሮስ በጥላው ካደነ (የሐዋ ፭፥፲፭)፤ የጳውሎስ የልብሱ ጨርቅ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ (የሐዋ ፲፱፥፲፩)፤ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኃይል ተሰጥቷት ይኾን? ለቅዱሳኑ ይኽንን ያኽል ድንቅ እንዲያደርጉ ባለሟልነትን ከሰጣቸው ወልዳ ላሰደገችው እናቱማ ምን ያኽል ይሰጣት ይኾን? በምን ዓይነትስ ስጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ “ክርስቶስ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነኽ” ስላለው ብፁዕ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቊልፍ ከተሰጠው (ማቴ ፲፮፥፲፮-፲፱)፤ እርሷ ከኹሉም ይልቅ እንዴት የተባረከች (ብፅዕት) አትኾን? (ሉቃ ፩፥፵፭)፤ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ “ምርጥ ዕቃ” ከተባለ (የሐዋ ፱፥፲፭)፤ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች እርሷ ምን ዓይነት ልዩ ዕቃው ትኾን? ነገር ግን ስለእርሷ ብዙ እናገራለሁ ብዬ ስለክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለሁ ስለዚኽ ካኹን ወዲኽ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጫለሁ።" #ሊቁ_ቅዱስ_ባስልዮስ
Показать все...
   ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይሁን!!          #የማስተዋል_ስንቅ   #ከእለታት አንድ ቀን ሁለት የዜን ገዳም ወጣት መነኮሳት ለተግባር ከገዳማቸው ወጥተው ከከተማ በስቲያ ባለችው የተልዕኮ ቦታቸው ውለው ቆይተው ወደ ገዳማቸው ለመድረስ በሚፋጠኑበት አንድ ማምሻ ላይ በመንገዳቸው የሚገኝን ወንዝ እየተሻገሩ ሳለ አንዲት ሴትን የሚገማሸረው ወራጅ ውሃ ከወዲያ ወዲህ እያላጋት እርሷም በጎርፉ ላለመወሰድ ሳሩንና አለቱን እየቧጠጠች ስትታገል  የሞት ሞቷን ያገኘችሁን ሁሉ ይዛ ከሚያንገላታት ሊወስዳትም ከሚጣጣረው ወራጅ ውሃ  ለማምለጥ ስትታገል ያይዋታል።እናም ሴቲቱ እጃቸውን ብትዋስ ልትድን የምትችል ቢሆንም የሴትን ገላ መንካት በሚከለክለው በዜን ገዳም ሕግ የታጠሩት ሁለቱ መነኮሳት ግን አልፈዋት ሊሄዱ ሆነ እጅግ ከባድ ቅጽበት ሰብዓዊነት ጥያቄ ላይ ሊወድቅ ነው? በዚህ መሃል ግን  አንዱ መነኩሴ ከጉዞው ተናጠበና ወደ ወንዙ ዘልሎ ገባ በሞት አፋፍ ላይ ያለችውን ሴቲቱንም ተሸክሞ በማውጣት ከወንዙ ዳር አድርሶ አስፈላጊውን እርዳታ አደረገላት። በእዛች ሰዓት አምላክ ከምድራዊው ሕግ ያለፈ ሰብዓዊነትን በልቡ ብርሃን ላይ ጭሮበት በአንዱ መነኩሴ ላይ ሊያተርፋት የቻለውን መነኩሴንም ሴቲቱ በአጸፋው ምስጋና አቀረበች። የምስጋናው በይ ተመልካች የሆነው ባልንጀራው ዳር ቆሞ ሁኔታውን ይታዘባል። በልቡናው የዜን ገዳም ሕግን ያመላልሳል በምድራዊው ሕግ ራሱን አጥሮ ከሰማያዊው ፍቅር ተካፍሎትን ዘንግቶዋል ብቻ እርሱ ትኩር ብሎ የወዳጁን እርዳታ በሰይጣናዊው መንገድ ይዳኘዋል።    በዚህ ሰዓት ፀሐይ እየጠለቀች ነው። መነኩሴዎቹ ለሰርክ ምለላ ፈጥነው ከገዳማቸው መድረስ ይኖርባቸዋል  እናም ወደዚያው ተፋጠኑ ብዙ ተጉዘው ከገዳማቸው በር ሲደርሱ ዳር ሆኖ ሲመለከት የነበረው መነኩሴ ሴቲቱን ለረዳት ባልንጀራው እንዲህ አለው... "ቅድም ግን ሴቲቱን መንካትህ ልክ ነበር?... እንዴት መነኩሴ ሆነህ ይህን ታደርጋለህ?" በማለት በፈጣን ጉዞ ላይም ሳሉ ይህን ሁሉ ሲያስብ ነበርና  ሰብዓዊነትን ከአምላክ ቸርነት ጋራ ያጣመረው ይህ መነኩሴ  አስገራሚ ምላሽ ሰጠ   #"ልክ ነህ ሴቲቱን ከወንዙ አውጥቻታለሁ... ገላዋንም ነክቻለሁ በምችለው ሁሉ ከአካልዋ ያለውን ሁሉ በእጄ እየዳበስኩኝ እርዳታዬን ሰጥቻታለሁኝ. ሆኖም እዚያው ወንዙ ዳር ትቻት መጥቻለሁ። አንተ ግን በልብህ እዚህ ድረስ ተሸክመሃታል" አለው።       እናስተውል #እኛስ ወንዙ ዳር ጥለናቸው ልንመጣ የሚገባን ነገሮች ምን ያክል አሉን? #ከወንዙ ዳር ባልተውነው ቂም ምክንያት ስንቴ ከበደሉ የሚልቅ ህመም ዕድሜ ዘመናችንን በላው? ወንዙ ጋ እያለን ማራገፍ ያሉብንን ነገሮች ሁሉ እናራግፍ ዘንድ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን።
Показать все...