cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ካሊድ አቅሉ

"ከባባድ ጥያቄዎች በቀላል መልሶች ይረታሉ" ሀሳብ ለማስፈንጠር.... @kalu30 Facebook - https://www.facebook.com/profile.php?id=100007449047737

Больше
Эфиопия1 817Амхарский1 435Книги2 177
Рекламные посты
12 247
Подписчики
-224 часа
-187 дней
-17030 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

አንቺን ሳስብ ነው ። (ካሊድ አቅሉ) እሁድ ዕለት ወደ አመሻሽ መስኮት ግርጌ ተቀምጬ ወጪ ወራጁን እያየሁኝ በትዝታ ተመስጬ ምሽት ሳትቀድመኝ በሚል ፉክክር ብዕር ይዤ ሳሰላስል ተራማጁን ተከትዬ ስፍጨረጨር ትንፋሽ ልስል ። እራቀኝ ሆሄ የሚገጣጣም አጣሁኝ መምቻ ስሜት አካሌ ድንበር አበጁ ብቻ ለብቻ ! ብሃላ ሲገባኝ የመግቢያ በሩን ቁልፉን ዘንግቼ ስታገል ነበር ከልቤ በላይ እጄን ሰምቼ ፤ ምግብ በአምላክ ቃል ባርኮ እንደመብላት አንቺን ሳስብ ነው ውብ ግጥም ምፅፍ ማወጣው ቃላት !
Показать все...
32👍 11👏 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሳምንት እሁድ ምን ቀጠሮ ይዛችዋል? አረፋ በዓል መጣው መጣው እያለን ነው ዝያራ ደግሞ ጥሩ አጅርን ማጎልበቻ መንገድ ኑሪያ የሱፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት ዝያራ ማድረግ አስበናል ልበ ብርሃኖች ጋር ግዜ ማሳለፍ ያለውን እርካታ ያየ ነው ሚያውቀው እነሱስ ማን አላቸው አብሽር እንበላቸው የመሄድ ሀሳብ በውስጡ የሰነቀ ባስቀመጥነው ቁጥር ይደውል ወይንም በውስጥ መስመር ያውራኝ 👉 @Kalu30 ማስታወሻ : ከግቢው ስለማይወጡ ሰው ይናፍቃሉ ሚያጫውታቸው ይወዳሉ ( ይፈልጋሉ) በጣም ልጆች ስለሆኑ ተረት መስማት እንኳን ይማርካቸዋል ። እና መሄድ የማይችሉ ካሉ አማና እናደርሳለንም ባስቀመጥነው አድረሻ ።
Показать все...
20👍 11
Repost from ካሊድ አቅሉ
Фото недоступноПоказать в Telegram
(እሳት ያልገባው ልብ ) ገጣሚ ፦ ነብይ መኮነን ሚሚዬን ጠየቅኳት ሁል ግዜ አረንጓዴ . ለምለም ፍቅር አለ ። ትወጃለሽ የሚል ወይስ ያዝ ለቀቅ ጭልጥ አንዴ መቶ አፍ ጠራርጎ መሄድ ያገኙትን በልቶ ሚሚዬም እንዲ አለች . . . ሳስቃ መለሰች የምን እኚኚ ነው እድሜ ልክ ከአንድ ሰው ቆሚ ፍቅር ይቅር ለብለብ እናርገው ክትፎዋም ለብለብ ፍቅርዋም ለብለብ እውቀትዋም ለብለብ ኑሮዋም ለብለብ ነገር አለምዋ ግልብ እንዴት ይበስል ይሆን እሳት ያልገባው ልብ . ~ ~ ~ ~ ~ ~ ± ± ± ~ ~ ~ ~ ~~ ~ ይሄ ግጥም ነብይ መኮነን በፈረንሳይኛ ቋንቋ ከተተረጎሙለት የግጥም ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው ። @KALIDakelu
Показать все...
👍 25
ምን ደረሰ እያልሽ የኔን ማብቂያ አጠብቂ ፈጣሪ ማረው እንድባል ጣር ይዞኛል አንዴ ሳቂ ፤ ከቻልሽማ ! ደባብሺኝ ባለንጋ ጣትሽ እንድቆም በሁለት እግሬ የመክረምን ችቦ ልለኩስ የፍቅርን ፍም እሳት ጭሬ ( ካሊድ አቅሉ)
Показать все...
14👍 6😁 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
የደመቁ ገፆች . . . . . . አንዳንድ ታሪኮች ርእስ የላቸውም ተነግረው እንዳልተነገሩ ይረሳሉ ። አንዳንድ ሰዎች ስም የላቸውም _ ኖረው እንዳልኖሩ ይቆጠራሉ ። አንዳንድ ገድሎች አልተዘከሩም _ የባከኑ መሥዋትነቶች ይባላሉ። አንዳንድ ቅሌቶች ሰው ፊት አልታዩም እንዳልተፈፀሙ ሁሉ በጨለማ ውስጥ ይቀራሉ ። አንዳንድ አወዳደቆች ከትዝብት ተጋርደዋል _ ዙሪያውን ገላምጠን ልብሳችንን አራግፈን አንቀጥላለን። አንዳንድ ሕዝቦች በውል ተረስተዋል _ ለመታሰቢያነት የቀረላቸው ምንም የለም። አንዳንድ ኮቴዎች በመረሳት ተጠቅተዋል አንዳንድ ወኔዎች ለሞት ዳርገዋል። ከሁሉም በላይ ግን አንዳንድ ልቦች በሦስት መሃላ ተክደዋል። ፨፨፨ " ሀገር ያጣ ሞት " ( ሄኖክ በቀለ ለማ)
Показать все...
👍 18🥰 4 1
ጨረቃ ያለበት ( ካሊድ አቅሉ) በየወንዙ በየአውራጃው ፋኖስ ሆነሽ ትዞርያለሽ ልጠይቅሽ አንድ ሚስጥር ሻማ ማብራት ትችያለሽ? ወይንስ የጋን መብራት ነሽ ብቻሽን በርተሽ ከዛ ምትከስሚ ጨረቃ ያለበት እያሸረገድሽ ድቅድቆች መንደር አውቀሽ ምጠሚ !
Показать все...
👍 20 12🥰 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
ማንነታችንን ለማወቅ ትንሽ መሞት ያስፈልገናል ። የሚገርመው ነገር ፍልስፍናችንም ሆነ ፍርሃታችን ደስታና ሀዘናችን ከሆድ እርቆ አይሄድም ። በዓሉ ግርማ ( ከአድማስ ባሻገር)
Показать все...
👏 31 12👍 6
Repost from ካሊድ አቅሉ
( ፍቅር የመሰለሽ ) ✍ ካሊድ አቅሉ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ሰውን ለማስታወስ ምስል ምን ያረጋል በድኑ ገፅታ ነፍሱን ነው መከተብ በልብ ህያው ቦታ። ብዬ ብናገርሽ በጫወታ መሀል . . . ከስልክሽ እስክሪን ፈጥነሽ አጠፋሽኝ በቃሌ ተከፍተሽ አንቺ ከጅምሩ መሸነጋገል ነው ፍቅር የመሰለሽ ) ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ @kalidakelu
Показать все...
👍 32 15😁 8👏 4🤔 2
ጥቅም የማይሰጥ የምሽት ጥላ ( ካሊድ አቅሉ) ቃል ብሰድር አቃንቼ ፤ መልክ አስይዤ ባሻግረው ሌጣ አረገው ማንነቴን ፤ በሌሎች ዓይን አስወገረው ይሁን ብዬ ብንገላታ ፥ ቀን ላጠራ ብንደረደር የዕለት ቅፅበት ማሰብ እንጂ ለነገ አያውቅ አሉኝ ሀገር ። " ጥቅም የማይሰጥ የምሽት ጥላ " ብለው ይዙታል አብረው ሲሰግዱ ያመፀን ገላ፥ ከንፈር ለመምጠጥ ይሰናዳሉ ከዳር ለማውጣት ጥልቁን ማውጠንጠን የአቃፊ ክንዱ ይሰባብራል እንዳንራመድ ከረጋገጠን ! እስኪነጋ ተነቃቅተው ፣ በድቅድቁ ቦታ ስተው ሲዟዟሩ የነበሩ ድንገት ፀሃይ ብትከሰት ለመተኛት ተማከሩ የዶሮ ጩህት ፣ አይንን ለመክደን ከጠቀማቸው ለማንቀላፋት ደውሉን ቆሜ ማቃጭለውን እንዴት አይዩኝ እኔን በእንቅፋት ?
Показать все...
👍 9👏 5
የኔዋ ዮዲት ጉዲት ! (ካሊድ አቅሉ) ፨ ዕለቱ ሰኞ ነው ክላሱ ጢም ብሎ ብሎ ሞልትዋል ዶክተር አብርሃም በጣም ተፈሪ የግቢያችን መምህር ነው። ከዚ ቀደም የተለያዩ ኮርሶችን ሰቶናል " በሚቀር ተማሪ አልደራደርም !" ይላል ከሶስት ቀን በላይ ቀሪ አለን ማለት F እንደሚሰጠን አንጠራጠርም ለዛ ቀደም ብለን መገኘት ልምዳችን ነው ። በዚህ ሴሚስተር የሚሰጠን ኮርስ ማትስ ነው ፣ እንደተለመደው ክላሱን መፈናፈኛ አሳጥተን ሞልተናል ስምንት ሰዓት ላይ ነበር ክፍሉ የጀመረው በሚወብቅ ሙቀት እንቅልፍ እንቅልፍ በሚል ድባብ የማትስ ውስብስብ ቁጥሮች እሹሩሩ እያሉ አንድ በአንድ እያስተኙት ነው። እኔ ማልተኛበት ትልቅ ምክንያት አለኝ እሷም ዮዲት ናት! "ዮዲት ጉዲት" እላታለው እኔ በምግባር ከዮዲት ጉዲት ጋር ብትፃረርም ልቤን ጉድ ያረገች የፍቅርዋ ምርኮኛ ነኝ፣ውብ ናት ውብ መልክ ታድላ ሰው እሱን ትቶ ስለ ውብ ፀባይዋ ሚያወራላት እፁብ ድንቅ ወዳታለው እሱን ማውቀው ደግሞ ማትስን በፍቅር ስማር ነው የሰው ልጅ የማይወደውን ነገር በሚወደው ነገር በኩል ሲያሻግሩለት በደስታ እንደሚቀበለው ያወኩት ዬዲትን እያየው ማትስ ማትስ ሳይለኝ መጨረሴን ሳይ ነው ። ግን ሙቀቱ በብርታቱ አልቀጠለም በሀይል ለመጣው ንፍስና መብረቅ ቦታውን ቀስ እያለ ለቀቀ በምትኩ ፍጡር ሚቋቋመው ማይመስል ዝናብ በመብረቅ ታጅቦ እንደ ጉድ ወረደ መምህራችንም አብርሃም "ኦኦ ከበድ ያለ ነው!" ብሎ ዝናቡ ሲበረታ በሩ ጋር ወዳለችው መቀመጫው አቀና ደግነቱ ትንሽ ነበር የቀረን 9:40 አካባቢ ነው ዝናቡ የበረታው መውጫችን ደግሞ አስር ሰዓት ሁሉም ተማሪ ግልግል ባለ ፊት መንጠራራት እና ፊቱን ከተኛበት መቀስቀስ ጀመረ ። "ዣንጥላ መያዜ በጀኝ እንጂማ ጉዴ ነበር" አለች ውጪ ውጪውን በነዛ ውብ አይኖች አሻግራ እያየች " እርግጠኛ ነኝ ቅድም ከቤት ስትወጪ ለፀሐይ ብለሽ ነው ይዘሽ የወጣችዋ ? " አልኳት መልኮችዋን እያየው "አዎ አይገርምም አሁን ደግሞ ለዝናብ ሆነ" "ህይወት እንደዚህ ናት! ለፀሐይ የታሰበ መከላከያ ከዝናብም ያወጣል እውነተኛ ወዳጅም እንደዚሁ ነው ወቅት ሳይመርጥ የሚሆን ጥላ " ብዬ ንግግሬን እንዳበቃው የሆነ ነገር እንደገባት ለማሳየት አንገትዋን ነቀነቀች እኔም ዣንጥላዋ መሆንን እንደዛ ቀን ናፍቄ አላውቅም ከሁሉም ነገር ልከልላት እሷ ላይ የመጣ ዶፍና ሀሩር እኔን አጊንቶ እንዲመለስ . . . . .
Показать все...
👍 4