ቅዱሳት መጻሕፍት
Открыть в Telegram
በዚህ ቻናል 👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ:: 👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ:: 👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ @Holy_scriptures
Больше7 907
Подписчики
Нет данных24 часа
-57 дней
+6630 дней
Архив постов
7 905
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ስለ እናንተ እንደ ተሰጠኝ እንደ እግዚአብሔር መጋቢነት፥ የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽሜ እንድሰብክ እኔ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ሆንሁ፤”
ቆላስይስ 1፥25
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ
ክፍል-3
በተጨማሪም፤ በጥንታዌቷ ቤተክርስቲያን በሥራ ላይ ይውል የነበረ “አስተምህሮ/ዲዳኼ” የተሰኘው መጽሐፍ ላይ፤ ማቴዎስን በቀጥታ እየጠቀሰ እንዲህ ብሎ ያስጠነቅቃል፦
❝not everyone who speaks in the spirit is a prophet, but only if he exhibits the Lord’s ways. By his conduct, therefore, will the false prophet and the prophet be recognized….If the one who comes is merely passing through, assist him as much as you can. But he must not stay with you for more than two or, if necessary, three days…But if he is not a craftsman, decide according to your own judgment how he shall live among you as a Christian, yet without being idle. But if he does not wish to cooperate in this way, then he is trading on Christ. Beware of such people.❞
ከላይ የጳውሎስን ማስጠንቀቂያ እንዲሁም ከቤተክርስቲያን ታሪክ ወስደን “የጌታ ተጠንቀቁ ጥሪ በመጀመሪያቱ ቤተክርስቲያን ላይ ይስተጋባ እንደነበር አይተናል። የጌታ ጥሪ ግልጽ ነው። በሐሰት ነብያት ጉዳይ አማኞች (በተለይ መሪዎች) ለአፍታ መተኛት አይችሉም። ብልሃታቸውንና መልካቸውን ቢለዋውጡም፤ እንደ ጉበኛ አይኖቻቸው ነቅተው ሊጠብቁ ይገባል። መቼም ቢሆን። ኢየሱስ እስኪመጣ።
ሐሰተኞች
ሁለተኛ፤ ማስጠንቀቂያው ያነጣጠረው፤ “በሐሰተኞች ነቢያት” ላይ ነው። አማርኛው ትርጉም ላይ “ሐሰተኞች” የሚለው ቃል ለአንዳንዶቻችን ምን አልባት “ድርጊት ገላጭ” ሊመስለን ይችል ይሆናል። ይህም እነዚህን ሰዎች “ሐሰተኞች” ያስባላቸው “ሐሰተኛ ትንቢት” መናገራቸው ነው የሚል ይመስል። ነገር ግን ቃሉ ድርብ-ቃል ነው “ሐሰተኞችነብያት/ψευδοπροφητῶν።” ምናልባት “የሐሰት-ነብያት” ወይም “የውሸት-ነብያት” ብንል ሐሳቡ ፍንትው የሚል ይመስለኛል። “ኛ” የሚለው ተቀጽላ ድርጊትንም ስለሚገልጽ፦ ለምሳሌ አንድ ሰው “የውሸት-መኪና” ቢል፤ መልክቱ ግልጽ የሚሆን ይመስለኛል (‘ኛ’ የሚለው ወጥቶ ማለቴ ነው)። ይህ ማለት፤ ገና ከጥንሥሡ ወይም ከነአካቴው “ይህ እቃ” መኪና እንዳልነበር ይነግረናል። ስለዚህ “ሐሰተኞች ነብያት” አስመሳይ-ነብያት እንጂ፤ ነብያት ሆነው ሐሰት ነገር የተናገሩ አይደሉም። ነብያት ሆነውም አያቁም። ይህ ወደ ሚቀጥለው ሐሳብ ያመራናል።
ሐሰተኞች ነቢያት
ሦስተኛ፤ እነዚህን ሰዎች ጌታ በሁለት መልክ (አረፍተ-ነገሮች) ይገልጣቸዋል። ምንም እንኳ ከአማርኛው የቋንቋ ሥርዓት የተነሳ እነዚህ ሁለቱ አረፍተ-ነገሮች “ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ” ከሚለው ዓረፍተ-ነገር ቀደም ብለው ቢመጡም፤ በዋናው ቋንቋ ላይ ግን እንደሚከተለው ቀርቧል፦
—> ጠንቀቁ
—> ከሐሰተኞች ነቢያት (7:15 ሀ)
—> (7:15 ለ) የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ
—>(7:15 ሐ) በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።
ከላይ “15ለ” እና “15ሐ” ብለን የሰየምናቸው አረፍተ-ነገሮች፤ የሐሰት-ነቢያት “ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው?” ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጡናል። ጌታ በሁለት መልክ ይገልጻቸዋል፡-
«በውጪ ምን እንደሚመስሉ እና በውስጥ ማን እንደሆኑ»። በውጪ አንድ፤ በውስጥ ግን ሌላ ማንነት አላቸው። ማቴዎስ ሲጽፍ “በውሥጣቸው/ἔσωθεν” የሚለውን ቃል ወደ ፊት ያስቀደመው «ደመቅና ሠመር» አድርጎ ለመናገር ነው። የእነዚህ ሰዎች ትልቁ ችግር “በውስጣቸው” ያለው ነገር ነው። ይህ “የውስጥ-ውጪ” ጉዳይ በነገረ-ማቴዎስ ውስጥ (Matthean Theology) ያደገ ቁልፍ ሐሳብ ነው። ለምሳሌ “ጽድቃችሁ ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ…” ሲል የፈሪሳውያን ጽድቅ ከውስጥ-ወደ ውጪ የወጣ ሳይሆን፤ ውጪያዊ ብቻ በመሆኑ ነው (“በውስጣቸው ግን ቅሚያና ስስት ሞልቶባቸዋል”/ የተለሠነ መቃብር ናቸውና (ማቴ 23ን ይመልከቱ)። እንዲሁም ማቴ. 5:48 ላይ የሰማይ አባታችሁ ሙሉ (ፍጹም) እንደሆነ እናንተም ሙሉ (ፍጹም) ሁኑ (be telios as your heavenly Father is telios)። ይህ የፍጹምነት ጉዳይ ሐጥያት-አልባነትን አያመለክትም (sinless perfection)። ፍጹምነት ማለት ‘ያልተገመሠ’፤ ‘ያልተከፋፈለ’ የሚለውን ሀሳብ ያንጸባርቃል።ለምሳሌ ያህል በም 19:21 ላይ “ኢየሱስም፣ “ፍጹም (telios) ለመሆን ከፈለግህ፣ ሄደህ ንብረትህን ሁሉ ሸጠህ…ተከተለኝ!” ጎልማሳው ውስጡን ያጣበበ የብልጽግና ሐሳብ ስለነበር ጥሪውን መቀበል አልቻለም። ይህ ሰው “ፍጹም” አይደለም። በእብራይስጡም “ታሚም” የሚለው የዚህ ቃል አቻ ነው። እነ አብርሃም እና እነ ዳዊት “ታሚም” ነበሩ «ልባቸው ፍጹም ነበር»። ስለዚህ የክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች በውስጥም፤ በውጪም አንድ አይነቶች ናቸው። አምልኮታቸውና የልባቸው መሰጠት “ነጠላ" ሰዎች ናቸው። መንትያ የላቸውም። ሙሉ ናቸው። ውጪያዊ አይደሉም። ሐሰተኛ ነብያት ግን “ውስጣቸው” እና “ውጪያቸው” አይመሳሰልም። ይህ መጀመሪያ ራሳችንን እንድንጠይቅ ካላደረገን የማቴዎስ መልክት አልገባንም ባይ ነኝ። እኔ ነኝ? በፍጹም ልቤ ለአምላኬ ተሰጥቼአለሁ? በርግጥ?
[7፡15ለ] የሐሰት-ነቢያት “ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው?
የመጀመሪያው ዘይቤያዊ አነጋገር፤ “የበግ ለምድ ለብሰው” የሚለው፤ የሚያሳየን የሐሰት-ነቢያት በውጪ በሚገልጹት ማንነታቸው ከበግ እንደማይለዩ ነው። በርግጥ በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ሐሰተኛ ነቢይ/ አስተማሪ/ወንድም የሚለዩት በሚያምኑት (በሚያሳዩት) ነገር ሳይሆን በሚክዱት (በማያሳዩት) ነገር ነው። “ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ የሚክዱ” (1ዮሐ 4፡1-3) ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እኮ ያምናሉ። በተለይ ብዙዎች በጎችን ቅንነታቸውን በመጠቀም የሚያታልሉበት መሳሪያቸው ይህ ነው። መምሰላቸው። እንዲያውም ጠበቃ እንቁምላቸው ያስብላሉ። ስለሚመስሉ። በማቴዎስ ላይ “በግ” የሚለው ዘይቤ የክርስቶስን ደቀመዛሙርት ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል (ማቴ 10:16, 26:31)። ስለዚህ ከክርስቶስ እውነተኛ “በጎች” ጋር ቀልቀል ያሉ በመሆናቸው፤ በዓይን ለመለየት አዳጋቾች ናቸው።
ይቀጥላል...
ምንጭ:- www.samsontblog.com
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኃጢአተኞችን እንዳይሰማ እናውቃለን።”
ዮሐንስ 9፥31
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ
ክፍል-2
የተራራው ስብከት ዋና መልክት (5:17–7:12)
በአጭሩ የክርስቶስ ተከታዮች መታወቂያቸው፤ የጽድቅ-ኑሯቸው ነው፤ “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ” (ማቴ 5:16)። የተራራው ስብከት የታይታ የሆነ ውጪያዊ ጽድቅን ይኮንናል (ማቴ. 6:1-15)፤ አትኩሮቱ በውስጣዊ ጽድቅ ላይ ነው። የውስጥ ጽድቅ ማለት፤ ከተለወጠ ልብ የመነጨ፤ እያደገና እየሰፋ የሚመጣ፤ ትኩረቱን “የሰማይ አባት እንደሚያይና ዋጋ እንደሚከፍል” የተገነዘበ ነው። “ጽድቃችሁ ከፈሪሳውያንና ከኦሪት ሕግ መምህራን ጽድቅ ልቆ ካልተገኘ መንግሥተ ሰማይ መግባት አትችሉም።” ስለዚህ የአማኝ ጽድቅ በአንድ እጅ “ወግ-አጥባቂነት ወይም አትንካ/አትቅመስ አለመሆኑን (Nomisim) በሌላ እጅ ደግሞ በጸጋ-ብቻ እንጂ ሥራ-ምን ፋይዳ አለው ብሎ መረን እንደማይወጣ (Anti-Nomisim) ያስገነዝበናል። የአማኞች ጽድቅ “የላቀ-ጽድቅ” ነው። በመጨረሻ ማጤን ያለብን፤ በተራራው ስብከት ላይ “ጽድቅ” የደቀመዝሙሩ የሕይወት-ፍሬ እንጂ በሐዋርያው ጳውሎስ ነገረ-መለኮታዊ አስተምህሮ ጎልቶ የምናገኘውን “የተቆጠረልን-ጽድቅ/ reckoned or imputed righteousness” አለመሆኑን ደግሞ ከዚያም ጋር አለመጋጨቱን ነው። የማቴዎስ አጠቃቀም ጳውሎስ “የመንፈስ ፍሬ” ብሎ ከሚናገረው ጋር ሥምረት አለው (ለምሳሌ ማቴ. 5:20ን ከኤፌ 5፡5-13 ጋር ያወዳድሩ/ ገላ 5:5)። (ይህን ጹሑፍ አጠር ለማድረግ የጽሑፉን መዋቅር እዚህ ጋር እናበቃለን)።
የምንባቡ ሐቲት (ፍታቴ) – 7:15 – 21
(በዚህ ክፍል የምንመለክተው ማቴ. 7:15 ብቻ ይሆናል)
❝የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ❞
ተጠንቀቁ
በመጀመሪያ ደረጃ ምንባባችን የሚጀምረው “ተጠንቀቁ” በሚል የማስጠንቀቂያ ትዕዛዝ ነው። ጌታ ምክር-ቢጤ ወይም “ብታደርጉት ትጠቀማላችሁ” የሚል አስተያየት ማከሉ አይደለም። ይህ ማስጠንቀቂያ የሞትና የሕይወት ጉዳይ ነው። ለምን? ይህንን ከሁለት አንጻር መመልከት ይኖርብናል። አንደኛ፤ ምንባባችን የሚገኘው በማቴ. 7:13-8:1 ባለው ክፍል እንደመሆኑ፤ ይህ ክፍል ደግሞ የተራራው ስብከት ተብለው ለሚታወቁት ሦስት ምዕራፎች (ማቴ. 5 – 7) መደምደሚያና የመልክቱ ማጠቃለያ ስለሆነ ነው። ስለዚህ ማስጠንቀቂያው ከ5:17 ጀምሮ እስከ 7:12 ድረስ ለዘለቀው ደቀ-መዝሙራዊ አስተምህሮ መቋጫ ነው። በተጨማሪ፤ ይህ መዝጊያ ክፍል (7:13-8:1) ሦስት ክፍሎች አሉት። ሁሉም ተምሳሌታዊ አነጋገሮች ሲሆኑ የተራራውን ስብከት መልዕክት ጠቅለል አድርገው የሚያቀርቡ እና ጥበብ-ነክ ቅርጽ/ይዘት ያላቸው ናቸው፡-
➳ ማቴ. 7:13-14 (ሁለት ዓይነት መንገዶችና ደጆች)፤
➳ ማቴ. 7:15-23 (ሁለት ዓይነት ዛፎችና ፍሬዎች እንዲሁም የሐሰት-ነቢያት የመጨረሻ ዕጣ-ፈንታቸው።
➳ ማቴ. 7:24-27 (ሁለት ዓይነት ሰሚዎችና ቤት-ሠራተኞች)
ስለዚህ ከላይ እንዳየነው “ከሐሰተኞች ነብያቶች ተጠንቀቁ” የሚለው ትዕዛዝ የሞትና የሕይወት ጉዳይ የሆነበት የመጀመሪያው ነጥብ 7:13-27 ያለው የተራራው ስብከቱ መቋጫ ከመሆኑ የተነሳ ነው። የስብከቱን ሙሉ ክብደት የተሸከሙት እነዚህ መደምደሚያ ክፍሎች በመሆናቸው። ሁለተኛውን ምንክያት ከቃሉ ሰዋሰው ማግኘት እንችላለን። የቃሉ ንብረት “ትዕዛዛዊ” ነው/Imperative Mood” ወዮታን ያዘለ ትዕዛዝ ነው። በማቴዎስ ወንጌል ላይ “ተጠንቀቁ/Προσέχετε” ስድስት ጊዜ ተደጋግሟል (6:1፤ 7:15፤ 10:17፤ 16:6፤ 16:11፤16:12) (ምንም እንኳ የ6ኛው ንብረት ትዕዛዛዊ ባይሆንም አውዳዊ አጠቃቀሙ ግን “ተጠንቀቁ” የሚለውን ስሜት ያንጸባርቃል)። ለምሳሌ፤ 6:1 ላይ ከታይታ-ጽድቅ “ተጠበቁ”…”ከ[ክፉ] ሰዎች ተጠበቁ”…”ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠብቁ።” ሁሉም አበክረው የሚናገሩት ማስጠንቀቂያውን አለማድመጥ ከባድ የሆነ መዘዝ እንዳለው ነው። ተጠበቁ የሚለውን ቃል BDAG የተሰኘው የግሪክ-መዝገበ ቃላት ሲተነትነው “በንቅሀት ውስጥ መሆን፤ የጉዳዩን አሳሳቢና አንገብጋቢነት ማየት ፤ ጠንቃቃ ሆኖ መገኘት፣ እንክብካቤን ማሳየት ነው ይለዋል…(to be in a state of alert, be concerned about, care for, take care)።
ከማቴዎስ ውጪ ይህ ቃል በሐዋ. 20፡28 ላይ (ከማቴዎስ ጋር እጅብ በተቀራረበ መልኩ) ተገልጾ እናገኘዋለን። ሐዋርያው ጳውሎስ የቤተክርስቲያን መሪዎችን አስጠርቶ የመጨረሻ የኑዛዜ ቃሉን ሲሰጣቸው እንዲህ ይላል፤
❝ለራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ኤጲስቆጶሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ…እኔ ከሄድሁ በኋላ፣ ነጣቂ ተኵላዎች (λύκοι βαρεῖς) መጥተው በመካከላችሁ ሰርገው እንደሚገቡና ለመንጋውም እንደማይራሩ” ዐውቃለሁም…❞
ይህ የጳውሎስ ንግግር የኢየሱስን ቃሎች እንዲያሳስቡ ተደርገው የተቀናበሩ ናቸው (Verbal Allusions)። ልክ እንደ ኢየሱስ ጳውሎስም “ለገዛ ራሳችሁ” እና “ለመንጋው ሁሉ ተጠንቀቁ” (προσέχετε ἑαυτοῖς καὶ παντὶ τῷ ποιμνίῳ) ሲል “መጠንቀቅ…መንጋ/በግ (ምዕመናንን የሚወክል ዘይቤያዊ አነጋገር)” እንዲሁም ቀጥሎ “ነጣቂ ተኵላዎች” ብሎ ሲል ጳውሎስ የጌታን ማስጠንቀቂያ እያሰበ መሆኑን ያሳየናል (ምንም እንኳ ማቴዎስ ገና ባለመጻፉ በ7:15 ላይ ላይ የተመሰረተ ነው ባንልም)። ይህም የጌታ ማስጠንቀቂያ (የሐሰተኞች ነቢያት ጉዳይ) ገና ቤተክርስቲያን ከመቆርቆሯ አንገብጋቢ ደረጃ መድረሱን ያመልክተናል። ይህ ማለት ጌታ እስኪመለስ ድረስ፤ ቤተክርስቲያን ባለችበት ቦታ ሁሉ፤ ይህ ጉዳይ የማያባራ ማስጠንቀቂያ ነው። ቤተ-ከርስቲያን አርፋ አታውቅም፤ ማረፍም የለባትም።
ይቀጥላል...
ምንጭ:- www.samsontblog.com
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የይሁዳ ንጉሥ የሆነው እና በትዕቢት ዕጣን ለማጠን ወደ ቤተ መቅደስ ከገባ በኋላ በለምጽ የተመታው ማነው?
7 905
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፤”
ፊልጵስዩስ 1፥29
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።”
1 ዜና 16፥10
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ
ክፍል-1
❝የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ❞ (ማቴ. 7:15–20)
❝Προσέχετε ἀπὸ τῶν ψευδοπροφητῶν, οἵτινες ἔρχονται πρὸς ὑμᾶς ἐν ἐνδύμασιν προβάτων, ἔσωθεν δέ εἰσιν λύκοι ἅρπαγες. ἀπὸ τῶν καρπῶν αὐτῶν ἐπιγνώσεσθε αὐτούς.❞
የምንባቡ መዋቅራዊ ዓውድ (Structural Context of the Passage)
የማቴዎስ ወንጌል “በትረካ-ንግግር” የተዋቀረ መጽሐፍ ነው። ለምሳሌ ያህል፦
(ትርካ) – ከማቴ. 1 – 4: የክርስቶስ ትውልድ፤ ልደትና አገልግሎት
(ንግግር) – ከማቴ. 5 – 7: የክርስቶስ ቃሎች/የተራራው ስብከት
(ትረካ) – ማቴ. 8 – 9: የክርስቶስ ሥራዎች/የፈውስ አገልግሎት
(ንግግር) – ማቴ. 10:1 – 11:1: የደ/መዛ. ተልዕኮ (ወዘተ..)
በመጽሐፉ ውስጥ አምስት ንግግሮች አሉ። አምስቱም ወደ “ትርካ” ከመመለሳቸው በፊት “ኢየሱስም ይህን ነገር በጨረሰ ጊዜ…” የሚል ሐረግ እና የማስጠንቀቂያ ቃል ይታከልባቸው። ስለዚህ ምንባባችን የሚገኘው በክርቶስ “በመጀምሪያው ንግግር/First Discourse Unit”፤ ይኸውም “የተራራው ስብከት (ማቴ. 5 – 7)” ተብሎ በሚጠራው ክፍል ውስጥ ነው። የተራራው ስብከት ያተኮረው በብጹዓን ላይ ሲሆን፤ እነዚህ ብጹዓን ደግሞ መለዮአቸው ከጻፎችና ከፈሪሳውያን “የሚልቅ-ጽድቅ” ስላላቸው ነው። የተራራውም ስብከት ማዕከላዊ መልክት “የሚልቀው-ጽድቅ” ምን እንደሚመስል ለማተት (5:21-5:48) እና ደቀመዛሙርት ይህንን ጽድቅ ጽድቃቸው ያደርጉ ዘንድ ለሚያስጠንቀቅ ነው (7:13-27)።
የተራራው ስብከት አወቃቀር (5:3-7:27)
በአጠቃላይ፤ የስብከቱ ይዘት በማቴ. 5:3 ላይ ይጀምርና በማቴ. 7:27 ላይ ያበቃል። ሆኖም ግን ማቴ. 4:23-5:2 እና 7:28-8:1 ያሉት የስብከቱ ክፈፎች ናቸው፡ መንደርደሪያ እና መቋጪያ። መንደርደሪያውም መቋጫውም አንድ ዓይነት የሐሳብ ቅኝት አሏቸው። ሁለቱም ክፍሎች ስለ ኢየሱስ፦
➳ (1) ብዙ ሕዝብ እንደተከተለው፤
➳ (2) ወደ ተራራ
➳ (3) እንደወጣ/እንደወረደ፤
➳ (4) ስለ ትምህርቱ (4:23-5:2) ይናገራሉ።
ምንም እንኳ የማቴ. 4:23 – 5:2 እና 7:28 – 8:1 ዓላማ ሰባኪውና ተሰባኪው ማን እንደሆነ ለመጦቆም እንደዚሁም ከስብከቱ በኋላ የሕዝቡ ምላሽ ምን እንደሚመስል ለማሳየት ቢሆንም፤ ከዚያ ያለፈ ትልቅ ግልጋሎት ግን አላቸው። ወንጌላዊው ማቴዎስ በ5:1-2 ላይ ስለ ኢየሱስ “ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ (ἀνέβη εἰς τὸ ὄρος)” ብሎ ሲጽፍ በማያወላውል መልኩ ዘጸ. 19:3ን ሊያስታውሰን ብሎ ነው (በተለይ ከሰብዓ-ሊቃናት ትርጉም)። በዚያ ሥፍራ ላይ “ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ዘንድ [ተራራ] ወጣ/ Μωσῆς ἀνέβη εἰς τὸ ὄρος” የሚል እናነባለን። ይህንን ሲል ማቴዎስ የኢየሱስን ስብከት/አገልግሎት ከሙሴ ጋር እንድናመሳስል እየጋበዘን መሆኑን ማስተዋል አለብን። ሙሴ ወደ ተራራው እንደወጣ፤ ኢየሱስም ወደ ተራራ ወጣ።
እንዲያ ከሆነ፤ እነዚህ ሦስቱ ምዕራፎች የሚያትቱት ከዳዊት የሚልቀው ንጉሥ እና ከሙሴ የሚልቀው ታላቁ ነቢይ ኢየሱስ (ዘዳ. 18:15,18) ለደቀመዛሙርቱ ስለ ሰጠው ደንብ ነው (but not a new law)። ሙሴ ሲወለድ ህጻናት እንዳለቁ ኢየሱስም ሲወለድ እንዲሁ (ማቴ. 2:20)፤ በሙሴ አማካኝነት ጸዓት ለእግዚአብሔር ሕዝብ እንደሆነ ኢየሱስም “ስሙን ኢየሱስ ትይዋለሽ እርሱም ህዝቡን ከሃጥያት ያድናቸዋል” ይላል። በሙሴ መሪነት ህዝቡም በደረቅ ምድር እንደተሻገረ፤ በምድረበዳ ለ40 ዓመታት እንደተፈተኑ፤ ደግሞም በኢያሱ መሪነት ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደገቡ፤ ኢየሱስም እንዲሁ በውሃ በዮርዳኖስ ማዶ ተጠመቀ፤ ከዚያም ወደ ምድረበዳ ተነድቶ ለ40 ቀንና ለሊት ተፈተነ፤ በመስቀል ሞቱም አዲስ-ጸዓት ተካሔደ..ወዘተ..እነዚህ ሁሉ ንፅፅሮች የሚያሳዩን የአዲስ ኪዳን ታላቁ ነቢይ ኢየሱስ መሆኑን ነው! ሙሴ የኪዳኑን ሕግ ተቀብሎ ለእስራኤል ሰጠ። በኢየሱስም አዲስ ኪዳን ተመረቀ። እንደ ሙሴ ኢየሱስም ወደ “ተራራው” ወጣ (ውሱን ምስተአምሩን ልብ ይበሉ) “አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ (5:2)”። ስለዚህ ኢየሱስ ከሙሴ የሚልቅ ነብይ ነው፤ ደግሞም አስተማሪ ነው። ይህ የመጀመሪያው ወንጌል በኢየሱስ አስተማሪነት (በቃሎቹ) ላይ አጽንኦት አድርጓል (8:19; 9:11; 10:24-25; 2:38; 17:24; 19:16; 22:16, 24, 36; 23:8; 26:18)።
ከላይ ያየነው የስብከቱን መንደርደሪያ እና መዝጊያ (5:1-2/7:28-8:1) ሲሆን፤ ከዚህ ቀጥሎ የሚመጣው ደግሞ የስብከቱ ይዘት ነው (ማቴ. 5:3 – 7:27)። የተራራውን ስብከት ይዘት በትልቁ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይመደባል፦
➳ (1) የስብከቱ ራስ: ብፁዓንና የቀረበላቸው ጥሪ (5:3–16)
➳ (2) የስብከቱ ሰውነት: የደቀመዛሙርቱ የላቀ-ጽድቅ (5:17–7:12).
➳ (3) የስብከቱ መዝጊያ: ከዘመን-ፍጻሜ ፍርድ ለማስመለጥ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ (7:13–27)
ይቀጥላል...
ምንጭ:- www.samsontblog.com
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።”
ኢሳይያስ 48፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
#እራሳችንን_እንመርምር
“በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን?”
2ኛ ቆሮ 13፥5
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ካህናቱም። እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ ኦሪቶችም አላወቁኝም ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበኣል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባንም ነገር ተከተሉ።”
ኤርምያስ 2፥8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የአምላካችን የእግዚአብሔር ብርሃን በላያችን ይሁን። የእጆቻችንንም ሥራ በላያችን አቅና።”
መዝሙር 90፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከይሁዳ ነገሥታት መካከል በ8 ዓመቱ የነገሠው እና በኋላም ትልቅ ሃይማኖታዊ ተሐድሶ ያካሄደው ንጉሥ ማን ነው?
7 905
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ደስ ይለኛል በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።”
ኤርምያስ 32፥41
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
ርዕስ፦ የልጆች መጽሐፍ ቅዱስ
ጸሐፊ፦ ፓት አልክሳንደር እንደተረከው
አዘጋጅ፦ሣህለ ጥላሁን
መጠን፦ 19.4 MB
ገጽ፦ 250
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 905
ስለፕሮቴስታን ተሐድሶ አምስት መቶ ዓመት ከደፈነ ሰነበተ። ነገ ኦክቶበር 1 የተሐድሶ ወር የሚጀምርበት ነው። በዚህ ነገር ላይ እውቀት እንዲኖራችሁ የምትፈልጉና የመሟገት አሳብ ያላችሁ ከላይ የተጠቀሰውን ቻናል ይከታተሉ
