cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

🌸🌸ከሰለፍዮች ጎራ🌸🌸

•°~•°ለሚሞት ጒደኛህ መቃብር ስትቆፍር በጣም አታርቀው አታሳጣው አፈር ምናልባት ማን ያውቃል ይህንን አትርሳ ለርሱ ያልከው ጉድጒድ ላንተ ቢሆንሳ•°~•° ለማንኛውም አስተያየት ወቀሳ እንዲሁም ጥቆማ( @kukuya ) ይጠቀሙ @Alemenor1 @Alemenor1 እኔ

Больше
Рекламные посты
189
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

#ሀያዕ_ምንድ_ነው?? 👑 ««የዒማናችን ጌጥ ««የዒማናችን ውበት « «የዒማናችን ሽልማት ✍አንድ ሴት or ወንድ ሀያዕ አለው /አላት ለማለት ምንምን ማሟላት አለበት??/ «በመጥፎ ገፀ ባህሪ ወይም ሰነምግባረ ልትገለጭ/ልትገለጥ አይገባም!! ««በመጥፎ ንግግረ ልትገለጭ /ልትገለፅ አይገባም!! «««ተግባረሽ አኽላቅሽ የተስተካከለ ጥሩ ሊሆን ይገባል!! @ታላቁ ሸኹል ኢስላም ኢብኑ ቲይሚያ እንድህ ብለዋል ዒማን እረቃኑን ነው እራቁቱን ነው የዒማን ልብስ (ተቅዋ /ሀያዕ ነው) ሀያዕ የመልካም ነገሮች ቁልፉ ነው!! አንዳንድ ሰዎች አሏህ ይዘንልንና ማሀዳነ አሏህ ሀያዕ ለሴት ልጅ ብቻ አድርገን የምኒዝ አለን ወላኪን አልሀያዕ ለሴትም ለወንድም አስፈላጊ ነገረ ነው‼️ 🔹ሀያዕ የሌለው ሪጃል ፈሳድ እንጂ ምንም ጥቅም የለውም ቁጥብነት ጨዋነት ለሁሉም ይጠቅማል!! ይበልጥ ደግሞ ለሴት ልጅ ሂጃብ ኒቃብ ለሰውነታችን አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ ሀያዕ ለነፉስያችን ያስፈልጋታል!! So ሀያዕ ለሴት ልጅ ብቻ ነው እያልን ነፉስያችንን አትሸውዳት። #ሀያዕ በ3 ይከፉላል \<<________> «««አሏህን ሀያዕ ማድረግ ««« መላዒካዎችን «««ሰዎችን ሀያዕ ማድረግ አሏህን መፉራት ማለት―፣ በምንሰራቸው ስራ ሁሉ የቂን ማድረግ እሱ ያዬናል ብለን መፉራት ሲሆን መላዒካዎችን መፈራት ማለት―። እነሱም የምንሰራቸውን ስራዎች በቀኝም በግራ ተመልካቾች ናቸው እነሱንም ሀያዕ ልናደረግ ግድ ይለናል!! ሰዎችንም_ሀያዕ እንድህ አለኝ ይሉኛል የሚል እና ከዚህ ተግባረ መቆጠብ! አሏህ በሱራ አለቅ 14 አሏህ አይና ተመልካች መሆኑን አያውቁምን? ይላል ስለዚህ ሀያዕ የሁሉም ፍሬ ነገረ ቁልፉ ናትና ሀያዕ ሊኖረን ግድ ይለናል። ሀያዕ የሌለዉ ሰዉ መገለጫው ራቁቱን እንዳለ ሰዉ አይነት ነዉና‼️ አሏህ የሀያዕን ካባ ያልብሰን አሚን! 🎀እህቴ ሂጃብሽ ሱትራሽ ነው ሱትራሽ ደግሞ አትርሺ በዱንያ ብቻ አይደለም የሚጠቅምሽ ለአሄራሽም ነው🎀 እህቴ ተሰተሪ በሂጃብሽም ዳግም ንግስት ሁኚ👑 join us👇👇👇👇 https://t.me/kukusal https://t.me/kukusal
Показать все...
🎀እህቴ ሆይ በሂጃብሽ ዳግም 💎ንግስት ሁኚ

🎀እህቴ ሂጃብሽ ሱትራሽ ነው ሱትራሽ ደግሞ አትርሺ በዱንያ ብቻ አይደለም ሚጠብቅሽ ለአሄራሽም ነው🎀 አደራሽን እህቴ ተሳተሪ በሂጃብ ዳግም ንግስት ሁኚ💎 የኡሙ ሀኒፍ ና የ @fkrma ግጥሞችና ፅሁፎች ሚገኙበት ቻናል . . ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ @Alemenor1

00:31
Видео недоступноПоказать в Telegram
እውቀት የማንነት ልኬት መሆኑ ሊጠፋሽ አይገባም ኡህታዬ 🌺አደራሽን ሀያእሽንም አንቺ ማለት የአለማቱ ጌታ በእዝነቱ አንቀፅን ያሰፈረልሽ ስለክብርሽም ሀቢቡና የተታገሉልሽ ነሽና እህቴ ሆይ ሂጃብሽንም አደራ🌹ይህ ሂጃብሽ ለቀብርሽ ከፈን 🌹ለአሄራሽ ደግሞ ምስክር ሊሆንሽ ይችላል።🌹 🌹ኡሙ ሀኒፍ🌹 join and share👇👇👇 https://t.me/kukusal https://t.me/kukusal https://t.me/kukusal
Показать все...
1.16 MB
.      ➺.. #አስደሳች_ዜና! ➺. አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላህ ያጀመዓ ✋ ➺. ቁርአን ተፍሲር እና ሪያዱሷሊሂን ኪታብ መቅራት መከታተል ኢልምን መቅሰም ለምትፈልጉ ብቻ! ➺. ኢንሻአላህ ከሰኞ ማለትም ጥቅምት 14/02/2015 ጀምሮ ሁሌ ከሰኞ እስከ አርብ #ሪያዱሷሊሂን / #የደጋጎች_ጨፌ! በሼይህ #ሙሃመድ_ዘይን በውብ አገላለጽ እና ማብራሪያ እንድሁም ቅዳሜና እሁድ በተመሳሳይ ሰአት #የቁርአን_ተፍሲር! ያቀርቡልናል ይሄን ጣፋጭ ዝግጂት የኛ ቻናል #ሙስሊም_ነኝ_እኔ! በቀጥታ ስርጪት በቴሌግራም live ለተከታዮቻችን ለማቅረብ ዝግጂታችንን ጨርሰናል እናንተም ተዘጋጁ ኑኑ ዲናችንን በቤታችን ሆነን እንወቅ ሁላችሁም #ሼር_አድርጉ ወደ መልካም ነገር እንጣራ! ➺. በአካል መከታተል ለምትፈልጉ አድራሻችን :- በአየር ጤና አለፈሰ ብሎ #ካራ_ቆሬ #ሙአዝ_ኢብኑ_ጀበል መስጂድ ሁሌ #ከመግሪብ_እስከ_ኢንሻ ባለው ሰዓት ። ➺. ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ :- @Mah_Ye ላይ አድርሱልኝ!  🌹. https://t.me/Muslim_negn 🌹. https://t.me/Muslim_negn
Показать все...
አንዳንድ ጊዜ ሁሉ ነገር ይሰለቸኛል …… አለ አይደል ጠዋት ከተኛሁበት ለመነሳት ብዙ ሰዐታትን አባክናለሁ ……… ቀን ሙሉ የምሰራውን ብቻ ቁጭ ብዬ በማሰብ ምንም ሳልሰራ የቀኑን ሰዐት እጨርሰዋለሁ ። የምለብሰውን ልብስ መገልበጥ ሁላ ይታክተኛል …… አንዳንዴ የክላስ ፈተና ያለ ቀን ደብተር ገልፆ ማንበቡ ዳገት ይሆንብኛል…… የምቀራውን ኪታብ ሙራጃዕ ማድረግ ትልቅ ስራ ይሆንብኛል…… ከዚህ ሁሉ መታከት እና መሰልቸት ጀርባ ሁሉ ነገር አላህ ያለው ነው የሚሆነው የኔ ልፋት ምን ሊፈይድ የሚል ሹክሹክታ ነው ያለው …… ግን ግን ይህን ንግግር እና ይህን ስንፍና ወደኋላ ጥዬ እንድነሳ እና ብርታት እንዳገኝ ተወኩል ብቻ ሳይሆን ሰበቡንም እንዳደርስ ሰበብን ከተወኩል ጋር እንድይዝ የሚያደርገኝ አንቀፅ አለ …… وَهُزِّي إِلَيْكِ بِجِذْعِ النَّخْلَةِ تُسَاقِطْ عَلَيْكِ رُطَبًا جَنِيًّا «የዘምባባይቱንም ግንድ ወዳንቺ ወዝውዣት ባንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና፡፡ ሱረቱ መርየም ፥ 25 ከምወዳቸው ሱራዎች ውስጥ መርየም አንዱ ምዕራፍ ነው …… በሴት ስም የተሰየመ እና ባማሩ አንቀፆች የተሞላ ምዕራፍ…… እዚህ ምዕራፍ ላይ ጌታዬ ለመርየም ምጥ በያዛት ጊዜ በተራበች እና በተጠማችበት ወቅት ከበታቿ ወንዝን እንዳደረገላት እና የተምር እሸትን ትበላ ዘንድ የዘንባባይቱን ግንድ እንድታወዛውዘው ያዛታል …… ምጥ ላይ ያለች እንስት በምን አቅሟ ግንድን ማወዛወዝ ይቻላታል ? ጌታዬ እንዲው ሊያረግፍላት ይችል ነበር ግን ሰበቡን እንድታደርስ አዘዛት ከዛም ብይም ፡ ጠጪም፡ ተደሰችም ሲል አበሸራት ፥ መጀመሪያ ሰበቡን እንድታደርስ በምጥ አቅሟ አዘዛት ከዛም ደግሞ በረዘቃት ነገርም ትደሰት ዘንድ አባሸራት …… ልክ ወፊቷ በጠዋት ወጥታ ሆዷን ሞልታ እንደምትመለሰው…… ልክ እንደዛው ተማሪ ከሆንን ፈተናውን ለማለፍ በማንበብ ሰበቡን ማድረስ አለብን ከዛ ውጤቱን በአላህ ተወኩል አድርገን መጠበቅ…… ሰራተኛ አልያም ነጋዴ ከሆንም ጠንክረን መስራት አለብን ሪዝቃችንን እናገኝ ዘንዳ …… ነብሴ በሰለቸች ጊዜ እና አካሌ በደከመ ወቅት ይችን የመርየም አያ ለራሴ ሹክ እላታለሁ ብርታት ይሆነኝ ዘንድ ። 🗯R I H K
Показать все...
يَسْأَلُونَكَ عَنِ السَّاعَةِ أَيَّانَ مُرْسَاهَا ۖ قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ رَبِّي ۖ لَا يُجَلِّيهَا لِوَقْتِهَا إِلَّا هُوَ ۚ ثَقُلَتْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ لَا تَأْتِيكُمْ إِلَّا بَغْتَةً ۗ يَسْأَلُونَكَ كَأَنَّكَ حَفِيٌّ عَنْهَا ۖ قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ اللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ ከሰዓቲቱ መቼ እንደምትረጋ (እንደምትመጣ) ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ነው፡፡ በጊዜዋ እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጣትም፡፡ በሰማያትና በምድርም ከበደች፡፡ በድንገት ቢኾን እንጂ አትመጣችሁም» በላቸው፡፡ ከእርሷ አጥብቀህ እንደ ተረዳህ አድርገው ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀቷ አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም» በላቸው፡፡ join us 👇👇👇 https://t.me/kukusal https://t.me/kukusal
Показать все...
Repost from N/a
Фото недоступноПоказать в Telegram
‍ 📩ይድረስ👇 ኢንተርኔት ለምትጠቀሙ እህቶች‼️ ♻️በኢንተርኔት ከንቱ ምኞት ትዳርዋን የተበላሸባት፤ ህይወቷን የጨለመባት እንስት አስተማሪ ታሪክ… ወጉ ወዲህ ነው👇 ሚስት አላህ ይጠብቀንና በኢንተርኔት ሱስ የተጠመደች ናት። ባለቤትዋ ከዚህ ተግባርዋ እንድትቆጠብ በተደጋጋሚ ቢመክራትም ልትቀበለው አልቻለችም። ብዙ ለመናት ብዙ አስመከራት "አሻፈረኝ" አለች። የምትጠቀምበትን ስልክ ሳይቀር ወስዶባታል። እሷም ሌላ ስልክ በመፈለግ ኢንተርኔት ላይ መዘውተሯን ቀጠለች። በዚህ ጊዜ ባል አንድ ዘዴ ይዘይዳል👇 ወደ facebook በመግባት እንደ ሚባለው "fake acount" (የውሸት አድራሻ) በመክፈት ስሙን ይቀይርና ፕሮፋይሉ ላይ ሀብታምና ቆንጆ የሚመስል የወንድ ምስል ያስቀምጣል። ከዝያ በኋላ የሚስቱን የ facebook አድራሻ በመፈለግ ያናግራት ጀመረ። 👆ጨዋታው የተጀመረው እዚህ ቦታ ነበር በሰላምታ የተጀመረው ንግግር ወደ ትውውቅ ይሸጋገርና ያለችበትን የኑሮ ሁኔታ ጨርሳ ትነግረዋለች። እሱ ግን እየዋሻት እሷን በምትፈልገው አይነት ራሱን እየገለፀ ያጫውታታል። ባለ ትዳር እንደሆነችና ነገር ግን በትዳሯ ላይ ደስተኛ እንዳልሆነች ስትነግረው "እንግዲያውስ ባልሽን ይፍታሽና ከእኔጋ እንደመር" ይላታል። ባቀረበላት ሀሳብ ደስተኛ ሆና ከባልዋ ጋ በምን ዓይነት መልኩ መፋታት እንዳለባት መላ ይፈልጋሉ። እሱም "በቃ ሳትጎዳዱና ሳትጨቃጨቁ እንድትለያዩ ችግር በማይፈጥር መልኩ ባህሪሽን ቀይሪበት" ይላታል። ባል ስራ ውሎ ማታ ሲገባ የሚስቱ ባህሪይ ከቀን ወደ ቀን እየተቀያየረ ይመጣል። ሚስት የማታውቀው ባል የፈጠረው ጨዋታ ነውና ቀን እያወራት ማታ ገብቶ ይታዘባታል። [አላህ ይጠብቀን] ጨዋታው ሲጧጧፍ ባል ማታ ይገባና "ሰሞኑ እያየሁብሽ ያለው ነገር እያስደሰተኝ አይደለም ምን ተፈጥሮ ነው?" ይላታል "ምንም" ትለዋለች "ንገሪኝ ችግርሽ ዝምታ መፍትሄ አይሆንም" ሲላት "ምንም አልሆንኩም" ትለዋለች "ሀሳብሽ በግልፅ ንገሪኝ ከእኔ መለየት ትፈልጊያለሽ ያልተመቸሽ ነገር አለ እንዴ?" ሲላት "ቢሆን አይከፋኝም" ብላ ፍላጎትዋን ገለፀችለት። ፍላጎቷን ግልፅ ካደረገች በኋላ ባልየው ቀጥታ ወደ ፈለገው ጨዋታ ይገባና ያናግራታል👇 "እንግዲህ መለያየታችን አይቀሬ ከሆነ አንቺም የሄድሽበት እንዲቀናሽ እኔም ቤቴና ንብረቴ ተበታትኖ ህይወቴ እንዳይበላሽ ከመሄድሽ በፊት ሁለተኛ ላግባና ልክ እንዳገባኋት ለእሷ አስረክበሽ ትሄጃለሽ" ይላታል። ሚስትም ያሳሰባት ሁለተኛ ማግባቱ አለ ማግባቱ ሳይሆን የእሷ መፈታት ነበርና "ምንም ችግር የለውም" ብላ ትስማማለች። ባልየው በማግስቱ ወደ ሚስቱ ቤተሰቦች በመሄድ የተነጋገሩበት ነገር ያጫውታቸውና ሁለተኛ ሊያገባ መሆኑ ይነግራቸዋል። ሁለተኛ ሚስት ፍለጋ ተ ጀ መ ረ ባል ሊያገባት ሚስት ደግሞ አስረክባት የምትወጣዋ ሁለተኛ ሚስት በሁለቱም ብርቱ ፍለጋ "ትሆናለች፣ ትመጥናለች" የተባለችዋን አፈላልገው አገኙ። ያዝ እንግዲህ…… የሁለተኛዋ ሚስት የኒካህ ቀጠሮ ይያዛል። ልብ በሉ ሁለተኛዋ እንደ መጣች የመጀመሪያዋ ተሸኝታ 👉ያ በኢንተርኔት መንፈስ ብቻ የምታውቀው ባልዋ ሊያገባት ነው። የማይደርስ የለምና የኒካሁ ቀን ደረሰ። ባል ልክ የሁለተኛ ሚስቱ ኒካህ እንዳሰረ ያ ሚስቱን ሌላ ሰው መስሎ ያወራበት የነበረው የ facebook አድራሻ ዘግቶት ከኢንተርኔት መንደር ይወጣል። لا إله إلا الله የመጀመሪያዋ ሚስት ባልዋ ሌላ እንዳገባና ከባልዋ ተለያይታ አዲስ የተዋወቀችው ሰወዬ ልታገባው እንደሆነ ልታበስረው ስትገባ ያ በውሸት ሲያወራት የነበረው ባለ facebook አድራሻው ዘግቶ ከመንደሩ ጠፍቷል። ዱንያ የት አትጥበባት? "ምድር ዋጭኝ" ብትላት መች ልትውጣት? ህይወት ጨልሞባት፣ መኖር አስጠልቷት ራሷን እየረገመች አዝና ተክዛ ቁጭ ብላለች። ባል አዲሷ ሙሽራው ጋ መቆየት ያለበትን ቆይቶ መጫወት ያለበትን ተጫውቶ ወደ ቀድሞ ሚስቱ ቤት ሲሄድ በሀዘን ተውጣ ተቀምጣለች። "ምንድን ነው ሰላም አይደል እንዴ?" ሲላት "ሰላም ነው" ትለዋለች "ምን ሆንሽ?" "ምንም" ትቷት ይሄዳል። አሁንም ተመልሶ ሲመጣ ሰውነቷ ከሳስቶ ፊቷ ተሸብሽቦ ያገኛታል "ምንድን ነው የሆንሽው?" "ምንም አልሆንኩም" "ያስቀየምኩሽ ነገር አለ" "ኧረ የለም" "ሀሳብ መቀየር አስበሽ ነው?" ፀጥ ረጭ አለች። የዛኔ ባል አጠገቧ ቁጭ ብሎ እያፅናናት "ምን ላርግ ታድያ? ከአንቺ መኖር እየፈለግሁ፣ ሳልጠላሽ፣ ሳላስከፋሽ በራስሽ ፍላጎት ያመጣሽው ሀሳብ ነው። እኔ ግን አሁንም ቢሆን የማከብርሽ የምወድሽ ባለቤቴ ነሽ። አንቺም ከእኔ የመለየት ፍላጎት ከሌለሽ ያመጣኋትም ሙስሊም እህትሽ ናት አብራችሁ ትኖራላችሁ። እሷም በቤቷ አንቺም በቤትሽ አብረን እንኑር።" አላት በዚህ ሰዓት ካላይዋ ላይ የተጫናት ተራራ የተነሳላት በሚመስል መልኩ በደስታ ፈንጥዛ ባልዋን እየሳመችና እያመሰገነች እያለቀሰች ደስተኝነቷን ገለፀችለት። በመጨረሻም ባልየው ባለ ሁለት ሲም ሆኖ ከሁለቱም ሚስቶቹ ጋ አብረው መኖር ጀመሩ። NB: ታሪኩ ላይ የተጠቀሱ በሸሪዓ ክልከላ ያለባቸው ነጥቦች አሉ [ፎቶ መጠቀምና ውሸትን] ይመስል ዘንግተናቸው ሳይሆን ከታሪኩ ብዙ ሰው ሊማር ይችላል ብለን ስላሰብን ነው። ማስተላለፍ የተፈለገውም ባሎች እንዲህ እንዲያደርጉ ሳይሆን ሴቶች ከምንም ነገር በፊት ክብራቸውን (ትዳራቸውን) ማክበርና መታዘዝ እንዳለባቸው ለማስገንዘብ ነው። ከአረብኛ ፅሁፍ የተገለበጠ join us👇👇👇 https://t.me/kukusal https://t.me/kukusal https://t.me/kukusal
Показать все...
🎀እህቴ ሆይ በሂጃብሽ ዳግም 💎ንግስት ሁኚ

🎀እህቴ ሂጃብሽ ሱትራሽ ነው ሱትራሽ ደግሞ አትርሺ በዱንያ ብቻ አይደለም ሚጠብቅሽ ለአሄራሽም ነው🎀 አደራሽን እህቴ ተሳተሪ በሂጃብ ዳግም ንግስት ሁኚ💎 የኡሙ ሀኒፍ ና የ @fkrma ግጥሞችና ፅሁፎች ሚገኙበት ቻናል . . ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ @Alemenor1

00:53
Видео недоступноПоказать в Telegram
ያአላህ አላህ ይጠብቅህ 🌺🌺🌺 እነዚህን የመሳሰሉ video ለማግኘት join join join👇👇👇👇 https://t.me/kukusal https://t.me/kukusal https://t.me/kukusal
Показать все...
2.05 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
አላህ እድሜሽን ያርዝምልኝ🌸 🌺ኡማዬ ሀያቲ🌺 join and share👇👇 https://t.me/kukusal https://t.me/kukusal https://t.me/kukusal
Показать все...