cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ነገረ ሃይማኖት

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን መሰረት የደረጉ ✔የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ✔የቅዱሳን አባቶቻችን ገድል ✔የኢትዮጵያ ገዳማት ታሪክ ✔መጽሐፍት ዳሰሳ ✔የነገረ ሃይማኖት ትምህርቶች...ይቀርባሉ

Больше
Рекламные посты
389
Подписчики
Нет данных24 часа
-27 дней
-130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

✝ ስለ ምጽዋት "የምትነድ እሳትን ውኃ ያጠፋታል፡፡ ምጽዋትም ኀጢአትን ታስተሰርያለች፡፡ ምጽዋትን ለሚሰጥ ሰው በመጨረሻ ይታሰብለታል፡በሚሰነካከልበትም ጊዜ መጠጊያን ያገኛል፡፡"               መጽሐፈ ሲራክ  3:28-29
Показать все...
2
✝ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ትወዳለህን? "ወንድሜ ሆይ ወደ አግዚአብሔር መቅረብ ትወዳለህን? ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ ጋርስ እንዲህ ማለትን ትሻለህን? "..ልሄድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ።ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና።" ፊል 1:23 ይህን ለማለት ከፈለግህ ያ በሰዎች ፊት ከፍ ከፍ የምታደርገው የምታመጻድቀውና ከእግዚአብሔር ይልቅ ታመልከው ዘንድ ከጀመርከው አንተነትህ ተላቀቅ!" ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ (የነፍስ አርነት)  @bahiretibebat21
Показать все...
4
✝ "ክርስቲያን ማለት በሚችለው አቅም ሁሉ ክርስቶስን በሃሳብ፣ በቃልና በተግባር የሚመስል ነው።"   ቅዱስ ዮሐንስ ዘቅሊማቆስ(ዘሰዋስው) @bahiretibebat21
Показать все...
4👍 1
✝ " ጸሎትን ቅዱሳን አባቶቻችን 'ጣዕመ መንግስተ ሰማያት' እንደሚሏት አንተም መጸለይን በእግዚአብሔር ሕብረት ደስ እንደምትሰኝበት ልዩ ነገር ቁጠረው። በእርግጥም ከእግዚአብሔር ጋር መሆን ደስታ ነው። በአባቱ እቅፍ እንዳለና መታቀፉን ብቻ ከምንም በላይ እንደሚመርጥ፣ ሌላ ምንም ነገር እንደማይጠይቅ ሕፃን፤ ምንም የመጠይቅ ቃል ከአንደበትህ ባይወጣም፣ በሕሊናህ ምንም ሐሳብ ባይኖርም #ስትጸልይ በእግዚአብሔር ቸርነት እቅፍ ውስጥ ነህና እንዲሁ ደስ ይበልህ!"               ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ @bahiretibebat21
Показать все...
3
✝ " ጸሎትን ቅዱሳን አባቶቻችን 'ጣዕመ መንግስተ ሰማያት' እንደሚሏት አንተም መጸለይን በእግዚአብሔር ሕብረት ደስ እንደምትሰኝበት ልዩ ነገር ቁጠረው። በእርግጥም ከእግዚአብሔር ጋር መሆን ደስታ ነው። በአባቱ እቅፍ እንዳለና መታቀፉን ብቻ ከምንም በላይ እንደሚመርጥ፣ ሌላ ምንም ነገር እንደማይጠይቅ ሕፃን፤ ምንም የመጠይቅ ቃል ከአንደበትህ ባይወጣም፣ በሕሊናህ ምንም ሐሳብ ባይኖርም #ስትጸልይ በእግዚአብሔር ቸርነት እቅፍ ውስጥ ነህና እንዲሁ ደስ ይበልህ! ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ @bahiretibebat21
Показать все...
....መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ግን አስቀድሞ በነበረው ትምህርቱ "ከእኔ በኋላ የሚመጣውን የእግሩን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ ነው" እያለ እንዳስተማረ ጌታችን ወደ እሱ ቀርቦ አጥምቀኝ ቢለውም "አነ እፈቅድ እምኀቤከ እጠመቅ" በማለት ደቀ መዝሙር በመምህሩ ይጠመቃል እንጂ እንዴት መምህር በደቀመዝሙሩ ይጠመቃል ሲል ራሱን ዝቅ በማድረግ ከለከለው። ጌታችን ግን መልሶ፦ "አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው።" ያን ጊዜም ቅዱስ ዮሐንስ ሊያጠምቀው ፈቀደለት (ማቴ3፥15)። ጌታችንም በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ጥር ፲፩ ከሌሊቱ አሥር ሰዓት በሠላሳ ዓመቱ ተጠመቀ። ቀዳማዊ አባቱ አብ በደመና ሆኖ "ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር- የምወደው ልጄ ይህ ነው" አለ። መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወረደ። አንድነት ሦስትነትም ተገለጠ። በዮርዳኖስ መጠመቁ እንደ እንግድዓ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ የሆነ አይደለም። በብሉይ ኪዳን አባታችን አብርሃም በኮሎዶጎሞር ድል ቀንቶት ሲመለስ በዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ካህኑ መልከጼዴቅን አግኝቶት ነበር። ካህኑ መልከጼዴቅም ኅብስተ አኮቴት ጽዋዕ በረከት ይዞ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ በማለት ተቀብሎታል። በኋላ ዘመን እስራኤልም ወደ ተስፋይቱ ምድር የገቡት ይህን የዮርዳኖስ ወንዝ ተሻግረው ነበር። ነቢዩ ኤልያስም ወደ ተዘጋጀችለት ብሔረ ሕያዋን ያረገው ዮርዳኖስን ወንዝ በመጎናጸፊያው ከፍሎ ተሻግሮ ነው ። እነዚህና ሌሎች በብሉይ ኪዳን የተደረጉ ነገሮች በሐዲስ ኪዳን ስለሚሆነው የጥምቀቱ ነገር ከሩቅ ማሳያዎች ነበሩ። አብርሃም የምእመናን፣ ኅብሰተ አኮቴት ጽዋዕ በረከት ይዞ የጠበቀው ካህኑ መልከጼዴቅ ክቡር ሥጋውን ቅዱስ ደሙን እንካችሁ ብሎ የሰጠን የክርስቶስ፣ ዮርዳኖስ ደግሞ የጥምቀት ምሳሌዎች ናቸው። እስራኤልም ከባርነት ተላቀው ሲወጡ የተስፋይቱን ምድር ከነዓንን ያገኟት ዮርዳኖስን ተሻግረው መሆኑ የሐዲስ ኪዳን ምእመናን በጥምቀት በኩል የክርስቶስ አካል ሆነው ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን የሚያዩ የመሆናቸው ምሥጢር ነበር። ከዚህም ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት "ባሕርኒ ርእየት ወጎየት ወዮርዳኖስኒ ገባ ድኅሬሁ" በማለት ዮርዳኖስ አምላክን ለማጥመቅ የተመረጠ ወንዝ ስለመሆኑ ትንቢት ተናግሮለታል። ጌታችን የተጠመቀበት ቦታም ዮር እና ዳኖስ የሚባሉ ወንዞች በሚገናኛቸው ላይ ነው። ሕዝብና አሕዛብ ተጠምቀው አንድ ሆነው በአንድ መጠሪያ ክርስቲያኖች ተብለው የሚጠሩ ናቸውና።በዚህም መለያየት ጠፍቷል። ውድ ልጆቻችን፦ የጌታችን ወደዚህ ምድር መምጣትና መጠመቅ ብዙ ትምህርትና ተአምራት የታየበት ነው። ዋና ዓላማው አዳምን በተንኮል አሳስቶ ከልጅነት ጸጋ ያጎደለውን ጠላት ዲያብሎስን ድል ነሥቶ ወደ ቀደመው የልጅነት ጸጋው መመለስና አዳምና ልጆቹ ድል የሚነሡበትን መንገድ ማሳየት ነው። ሰይጣን ድል ከተነሣባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ የጌታችን ጥምቀት ነው። የአዳም የዕዳ ደብዳቤ የተደመሰሰው በጥምቀቱ ነውና። በሌላም በኩል ጌታችን ወደ ዮሐንስ ሔዶ ትሕትናን አስተምሮናል። ወደ ዮሐንስ ሔዶ መጠመቁም ነገሥታትም ቢሆኑ ምእመናንም ቢሆኑ ወደ ካህን ሔደው እንዲጠመቁ ሥርዓት ሲሠራ ነው። ባዕለጸጋ እና ድሃ እኩል በሚያገኙት በውኃ መጠመቁም ጥምቀት የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ ናትና መንግሥተ ሰማያት በገንዘብ ብዛት የማትገዛ ለሁሉም የተሰጠች መሆኗን ሲያሳይ ነው። በጥምቀቱ ትሕትናን ገንዘብ ብታደርጉ ታላቅነትን ታገኛላችሁ ሲል አስተምሮናልና ትሑት ልቡናን ገንዘብ ማድረግ ይገባል። ይህንም የትሕትና መምህር አምላካችን በትሕትና ወደ ዮሐንስ ተጉዞ አሳይቶናል። በጥምቀቱ መለያየት የጠፋበት ነው። ሕዝብና አሕዛብ መባባል አሁን የለምና። "አንተም እንዲሁ አድርግ..." እያለ በወንጌል የሚያስተምረን አምላክ እኛም ከመካከላችን መለያየትን አርቀን ፍቅርን አንድነትን አጽንተን መኖር ይገባል። መልከ ጼዴቅ ለአብርሃም ኅብስተ አኮቴት ጽዋዕ በረከት ይዞ መታየቱም ከጥምቀት ባሻገር ምእመናን እንዲቆርቡ ማስተማሩ ነውና ከሁሉም በላይ ይህን በዓል ስታከብሩ በዓላቶቻችን መጽደቂያ እንጂ መመጻደቂያ እንዳይሆን በምግብና መጠጥ ብቻ ሳንይሆን ክቡር ሥጋውና ደሙን በመቀበል፤ ከዘፈንና ከዳንኪራ ርቃችሁ በመዝሙርና በምስጋና እንድታከብሩ እናሳስባችኋለን። በመጨረሻም የተወደዳችሁ ውድ ልጆቻችን ኾይ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ እያልን አሁን ዓለማችንም አገራችንም ሰላም ያጣችበት ዘመን ላይ ነንና የአዳምን በደል ይቅር ብሎ የዕዳ ደብዳቤውን አጥፍቶ እውነተኛ ሰላሙን የመለሰለት የሰላም አምላክ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ሰላምን ለአገራችን ይሰጥልን ዘንድ ወደ አምላካችን እንድትጸልዩ አሳስባችኋለሁ። መልካም በዓል!!        አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
✝ "በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።”  (ማር 1፥9 ) አምላካችን እግዚአብሔር ሰው ሆኖ የመወለዱና በዚህ ምድር ሠላሳ ሦስት ዓመት የመኖሩ ዋና ዓላማ ሰውን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ለማዳን ነው። በመወለዱም አምላክነቱን ሳይለቅ የሰውን ባሕርይ ባሕርይው አድርጓልና ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም እንደሰውነቱ እየታዘዘ እንደ አምላክነቱ ታምራት እየሠራ በየጥቂቱ አደገ። "ልኅቀ ከመ ሕፃን እንዘ ይትኤዘዝ ለአዝማድኢሁ ወለይእቲ እሙ ድንግል"  ዕድሜው ሠላሳ ሲሞላ የተነገረው ትንቢት፣ የተቆጠረው ሱባዔ ይፈጸም ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ አካባቢ "ነስሑ ወእመኑ እስመ ቀርበት መንግሥተ ሰማያት" እያለ የሚሰብከውን ዮሐንስን በዮርዳኖስ ወንዝ እንዲያጠምቀው ጠየቀው።
Показать все...
✝ "..እመኑኝ እግዚአብሔር የተጋለጥንባቸውን እና በእርሱ የተጠበቅንባቸውን አደጋዎች ሁሉ ቢገልጥልን ሕይወታችን ሁሉ እርሱን ለማመስገን አይበቃም ነበር።"     ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ
Показать все...
3
✝ "ነፍስህ ቃለ እግዚአብሔር ማንበብ ስትሰለች ቃለ እግዚአብሔርን ማንበብና መስማት ደስ የማይላት ሲሆንና መንፈሳዊ ተግሳፅን ስታቃልል ካየሃት በክፉ ደዌ ላይ እንደወደክ ተገንዘብ።ሰዎች የሞትን ፍሬ የሚቀጥፉበት የመጀመሪያው ይህ ነውና።"     ቅዱስ እንጦንስ
Показать все...
6
✝ "ኃጢአትን በሠራት ጊዜ ሕሊናህን በመክሰስ በራስህ ተስፋ እንድትቆርጥና ሕይወትህም ትርጉም እንደሌለው አድርገህ እንድታስብ የሚያደርገው ሰይጣን ነው። በምህረቱና በአባታዊ ፍቅሩ ወደ ንስሐ እንድታመራ በማሳሰብ የሚወቅስህ ግን መንፈስ ቅዱስ ነው።"
Показать все...
👍 7