cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

#መቅረዝ

🕎 መቅረዝ የብርሀናት ሁሉ መገኛ ዘወትር ብርሀን የማይጠፋ ዘይቱ የማይጎድልበት ለዘለዓለም የሚያበራ እውነተኛውን ብርሀን እየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው 🕎

Больше
Рекламные сообщения
246Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-1030 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የቤትህን ዉበት ወደድኩት በዓታ ማርያም አ.አ 3
Показать все...
የአስቆርቱ ይሁዳ ታሪክ፡- ታሪኬ ለብዙዎች ደስ አይልም፡፡ አባቴን ገድዬ እናቴን አግብቻለሁ፡፡ የስምኦን ልጅ የአስቆሮቱ ይሁዳ ነኝ፡፡ ነብዩ እንባቆም ለማስተማር ሲሄድ እንደገናም ሲመለስ አባቴ በመንገድ ላይ ከተቀመጠበት ድንጋይ ተነስቶ ኖር ባለማለቱ ነብዩ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተቀምጧል አለው፡፡ ከዚያም ከዚህ ሰው የሚወለደው ልጅ አባቱን ገድሎ ይሰልባል እናቱን ያገባል ጌታውንም ይሸጣል ብሎ ትንቢት ተናገረብኝ፡፡ ሁኔታው ያሳሰበው አባቴ ይህ ትንቢት እንዳይፈፀም ተጨነቀ፡፡ ወደ ቤቱም ሄዶ የሆነውን ለሚስቱ ነገራት፡፡ እናቴም አንተስ ብትሆን ትክክል አድርገሃልን የእግዚአብሔር ነብይ ሲመጣ ዝም ብለህ ማሳለፍ እንደማይገባህ አታውቅምን አለችው፡፡ ስለዚህም ትንቢቱን ለመከላከል አብረው መተኛት አቆሙ፡፡ ኖረው ኖረው ግን አንድ ቀን አባቴ እናቴን ስጋዊ ፍቃዴን ፈፅሚልኝ አላት ፤ እርሷም እንተወዋለን ተባብለን የለም ወይ አለችው፡፡ ወንድ ቢሆን እንገድለዋለን ፤ ሴትም ብትሆን እናሸንፋታለን አላት፡፡ በዚህ ተስማምተው እኔ ተፀነስኩ፡፡ ስወለድ ወንድ ሆኜ ቁጭ! ከተወለድኩ በኋላ በሳጥን አድርገው ወደ ባህር ጣሉኝ፡፡ የ1 ቀን ተኩል መንገድ ከተጓዝኩ በኋላ በአንድ ሰው እጅ ገባሁ፡፡ እሱም አሳደገኝ፡፡ በነገራችን ላይ የኔ የትውልድ አገርና ያደግኩበት አስቆሮቱ ጠበኞች ነበሩ፡፡ ይህ ጠብ አድጐ ጦርነት ሆነ፡፡ እኔም አሳዳጊ አባቴ ጐበዝ ጦረኛ አድርጐ አስተምሮኝ ነበርና ጭፍራዬን አስከትዬ ዘመትኩ፡፡ በዚያም አባቴን አግኝቼ ገድዬ ሰለብኩት፡፡ እናቴም ምርኮዬ ሆና አገኘኋትና አገባኋት፡፡ ወላጆቼ የፈሩት ሁለት ትንቢቶችም ተፈፀሙብኝ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን እኔ የማውቀው ታሪክ አልነበረም፡፡ አንድ ቀን ማርኬ ያገባኋት እናቴ ምነው ያገርህ ሰዎች ብዙ አይቀርቡህም አለችኝ፡፡ እኔም ባህር ላይ ወድቀህ የተገኘህ ነህ ይሉኛል አልኳት፡፡ እርሷም ማንነቴንና ጉደኛ ታሪኬን ነገረችኝ፡፡ ይህ ጊዜ ማለት ክርስቶስ ወንጌልን ያስተምር የነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ እናም ወደ እርሱ ጋር ሄደን የሆነውን ነገርነውና ከኃጥያታችን አነፃን፡፡ እኔም በጌታ ፊት ሞገስን አግኝቼ ከ12ቱ ሀዋሪያት አንዱ ለመሆን በቃሁ፡፡ እናቴም ከ36ቱ ቅዱሳን አንስቶች አንዷ ሆነች፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገልኝ ነገር እንዴት አይነት እፎይታን እንደሰጠኝ አታውቁም፡፡ ምን ዋጋ አለው ሲያልቅ አያምር ሆነ እንጂ፡፡ ጌታ ያንን ሲያደርግልኝ አባቴ ላይ ትንቢት የተናገረውን ነቢይ ቃል ያሸነፍኩት መስሎኝ ነበር፡፡ በፍቅሩ የማንንም ልብ የሚያንበረክከው ክርስቶስን እወደው ነበር፡፡ ወይም እወደው ይመስለኝ ነበር፡፡ አሁን አለም ላይ የማይታመን፣ የማይረባ ከሀዲ ሰውን መግለፅ ሲፈለግ የእኔ ስም መጠሪያው ሆኗል፡፡ ስሜን “ይሁዳ!” ሲሉ በስድብ ሀይለቃል የማይታመን ሰውን ይጠሩበታል፡፡ የሚገርማችሁ ስሜን ሳስበው ስላቅ ይመስለኛል፡፡ የስሜ ትርጉም ታማኝ ማለት ነው፡፡ በፀሎተ-ሐሙስ ምሽት ጌታ የፋሲካውን እራት ለደቀ መዛሙርቱ ባበላበት በዚህች ቀን ላይ ያንን የሰውን ልጅ አብዝቶ የወደደውን ጌታ አሳልፌ ሰጠሁት፡፡ ያውም ፍቅር፣ መውደድ፣ ማክበር በሚገለፅበት ሰላምታ፡፡ ስሜ ነከስኩት---- አቤት ገንዘብ! አቤት ንዋይ መውደድ! ግዴላችሁም ከእኔ ተማሩ---- ለገንዘብ ልክ ያጣ ፍቅር ሲኖር ይኸው ነው በቃ! እናም በ30 ዲናር ጌታዬን ሸጥኩት፡፡ በነገራችን ላይ አይሁድ በ30 ዲናር ጌታን እንድጠቁማቸው የጠየቁኝ የእየሱስ ክርስቶስ መልክ ከሐዋሪያው ዮሐንስ መልክ ጋር በእጅጉ ይመሳሰልባቸው ስለነበር ነው፡፡ እናንተ ኢትዮጵያውያን አንድ ተረት አላችሁ ደስ የምትለኝ ተረት መማሪያ አታድርገኝ መማሪያ ስጠኝ ትላላችሁ፡፡ እኔ ግን ለእናንተ የክህደት የአሳልፎ መስጠት የገንዘብ መውደድ ክፋት መማሪያ ሆንኳችሁ፡፡ በስራዬ ተፀፀትኩ ፤ እናም አንድ ነገር አሰብኩ፡፡ ጌታ ከተሰቀለ በኋላ በ3ኛው ቀን ከሙታን እንደሚነሳ ሲናገር በእለት አርብ ነፍሳትን እንደሚያወጣ የነገረንን አስታወስኩ፡፡ እናም እራሴን ባጠፋ አብሬ መውጣት እንደምችል አሰብኩና ወደዱር ሮጥኩ፡፡ የያዝኩትን ገመድ በዛፍ ላይ አስሬ ተንጠለጠልኩ፡፡ ይሁንና ነፍሴ ሳይወጣ 2 ቀናትን እዚያው ዛፍ ላይ ተንጠልጥዬ አሳለፍኩና ህይወቴ አለፈች፡፡ እናም የምርኮውን ነፍሳት ላጣው ዲያብሎስ የመጀመሪያ ምርኮ ሆኜ ሲኦል ገባሁ፡፡ መቼም ጌታዬን በ30 ዲናር በመሸጥ ካጠፋሁት ጥፋት ባልተናነሰ በእግዚአብሔር ላይ የብልጠት ሥራ ለመስራት መሞከሬ ሳያስገርማችሁ አይቀርም፡፡ አንዱን ጥፋት ለማረም ሌላ ጥፋት ማጥፋቴ ትልቅ በደል ነበር፡፡ https://youtu.be/XnwWTWfUf_M?list=TLPQMTAwNDIwMjNt2DhcdHNv2w https://youtu.be/XnwWTWfUf_M?list=TLPQMTAwNDIwMjNt2DhcdHNv2w
Показать все...
ሕማማት መዝሙሮች ስብስብ

ሕማማት መዝሙሮች ስብስብ part 2

Показать все...
ሕማማት መዝሙሮች ስብስብ part 1

ሕማማት መዝሙሮች ስብስብ part 1

Показать все...
ሕማማት መዝሙሮች ስብስብ

ሕማማት መዝሙሮች ስብስብ part 2

ሆሳዕና ሆሳዕና ሆሳዕና በአርያም እንኳን አደረሰን https://www.youtube.com/watch?v=zEIjwD2sRSs https://www.youtube.com/watch?v=WkQORXPqdqI
Показать все...
Показать все...
ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና

ሆሳዕና ሆሳዕና ሆሳዕና በአርያም ለወደደን ላፈቀረን መድሐኔአለም አሳድጎ በመቅደሱ ቀና አረገኝና አስተምሮ ልቤን መክሮ ከፈተልኝ አፌን በምስጋና