cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
179
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

በሰመአብ ወወልድ ወመንፈስ ክዱስ አሃዱ አምላክ አሜን ታላቅ መንፈሳዊ የአዳር ፕሮግራም በቃሊቲ ደብረ መድሃኒት መደኃኒአለም ቤተ-ክርስትያን ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት ቀን-ሰኔ 26, ምሽት 3 ሰዓት ጀምሮ ቦታ - የሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ ውስጥ በእዚሁ አለት የተዘጋጁ የተለያዩ አስተማሪ አና ምርጥ ፕሮግራሞች ሰለተዘጋጁ በጊዜው በተባለው ቦታ መጣችሁ የዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ አካል ሁኑ ብለን በእናቱ በእናታችን በ ድንግል ማርያም እና በእግዚአብሔር ስም በትህትና አንጠይቃለን..... የፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት ኪነ-ጥበብ ክፍል
Показать все...
✍ ምን ብዬ ልጸልይ? በግሪክ ሀገር ሁለት ሴት ልጆቹን ያሉት አንድ አባት ነበር። በአንድ ዓመት ብቻ የሚበላለጡትን እነዚህን ሕጻናት እንደ አባትም እንደ እናትም ሆኖ ተንከባክቦ ማሳደግ የዚህ ሰው ዋነኛ ሥራው ነበር። ስለዚህ ወጥቶ በገባ ቁጥር ልጆቹን የሚያስደስት ነገር እየገዛ ፣ የሚጠይቁትን እያሟላ በድሎት ያኖራቸው ነበር። የራሱን ሕይወት ወደ ጎን ትቶ ለልጆቹ መኖሩ ያለ ዋጋ አልቀረም። ሁለቱም ልጆቹ በጤንነት አድገው ዕድሜያቸው ለጋብቻ ደረሰ። አባት የለፋባቸው ልጆቹን ከመዳሩ በፊት ብዙ መሰብ ነበረበት። አስተዋይ ነበርና ብዙ ሽማግሌ ቢላክበትም ልጆቹን ለመሥጠት የወሰነው ግን በጥንቃቄ ነበር። ስለዚህ ልጆቹ ሁለቱም በአንድ ጊዜ እንዳይቸገሩ በማሰብ የተለያየና የማይነጥፍ መተዳደሪያ ላላቸው ወንዶች ባል እንዲሆኑ ለማድረግ ወሰነ። እንዲህ ሲልም ያወጣና ያወርድ ጀመር : "ሰዎች ሁልጊዜም ምግብ ያስፈልጋቸዋል ስለዚህ ገበሬ መቼም ቢሆን እህል ገዢ አያጣም። እንዲሁም ሰዎች ውኃ ለመቅዳት ምግብ ለመሥራት ሸክላ ስለሚፈልጉ ሸክላ ሠሪም ገበያ አያጣም። ስለዚህ ልጆቼን የምሠጠው ለሸክላ ሠሪና ለገበሬ ነው" አለ። እንዳለውም አንዲቷ ልጁ የገበሬ ሚስት ሌላኛዋ ደግሞ የሸክላ ሠሪ ሚስት እንዲሆኑ ሠጣቸው። ከብዙ ጊዜ በኋላ በአንድ ሰንበት ይህ ሽማግሌ ዛሬስ ልጆቼን ልጠይቅ ብሎ ተነሣ። በመጀመሪያ ወደ ገበሬው ሚስት ሔዶ ሲጫወት አረፈደ። ተሰናብቶ ሊወጣ ሲል ልጁ እንዲህ አለችው : "አባዬ እስካሁን ኑሮአችን ሰላም ነበር። አሁን ግን ችግር ላይ ነን። ላለፉት ሁለት ወራት ዝናም ጨርሶ አልዘነበም። በዚሁ ከቀጠለ የዘራነው አይበቅልም ፣ ተክሎቻችንም ይደርቃሉ። አባዬ አደራ! በሚመጣው ወር ከባድ ዝናም እንዲጥል ወደ ፈጣሪ ጸልይልን!" አባት አደራውን ተቀብሎ ተሰናብቶ ወደ ሁለተኛዋ ልጁ ቤት ለመሔድ ጉዞውን ጀመረ። ከሰዓት በኋላ ወደ ሁለተኛዋ ልጁ ቤት ሲደርስ ከሸክላ ሠሪው ባሏ ጋር በአክብሮት ተቀብለው አስተናገዱት። ከጠዋቱ የበለጠ ደስተኛ ሆኖም አሳለፈ። መሰናበቻው ላይ ግን ልጁ ተነሥታ እንዲህ አለችው: "አባዬ ለአንተ ለጸሎተኛው አባቴና ለጠንካራው ባለቤቴ ምስጋና ይሁንና ኑሮአችን እስካሁን ጥሩ ነው። እንደምታውቀው ላለፉት ሁለት ወራት ዝናም አልዘነመም። በዚህም ደስተኞች ነን። አሁን የምለምንህ አንድ ነገር ብቻ ነው። በሜዳ ላይ ተደርድሮ እንደምታየው እጅግ ብዙ ሸክላዎች እየሠራን ነው። በሚመጣው ወር ዝናም ካልዘነመና ደረቅ ከሆነ የሠራናቸው ዕቃዎች ሁሉ ደርቀው ለገበያ ይደርሱልናል። ስለዚህ በሚመጣው ወር ዝናም እንዳይጥል ወደ ፈጣሪህ ጸልይልን" አባት ተሰናብቶ ሲወጣ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ "ፈጣሪዬ ሆይ አንዲቱ እንዳይዘንም ጸልይ አለችኝ ፣ ሌላዋ እንዲዘንም ጸልይ አለችኝ ፣ ምን ብዬ ልጸልይ?" አለ። (500 BC Greek www.the-essayist.com) 👉 ይህ አረጋዊ የእኛን ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቢያስቀድስ ኖሮ ግን እንዲህ አይጨነቅም ነበር። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ላይ ዲያቆኑ የሚያነበው ምእመናን በግንባራቸው ተደፍተው የሚሰሙት "በእንተ ቅድሳት" የሚባል ጸሎት ላይ የዚህን ሽማግሌ ልብ የሚያረጋጋ ስለ ዝናም የሚጸለይ አንቀጽ አለ። እንዲህ ይላል: "በሚሻበት ቦታ እግዚአብሔር ዝናሙን ያዘንም ዘንድ ስለ ዝናም እንማልዳለን" 👉 "በሚሻበት" የሚለው ቃል ላይ "ሻ" ጠብቃ ትነበባለች። "በሚፈለግበት ቦታ እግዚአብሔር ዝናሙን ያዘንም ዘንድ" (ኀበ ዘይትፈቀድ መካን) ማለት ነው። ቀሳውስቱም ስለ ዝናማት በሚጸልዩት መስተብቁዕ ላይ "ወደ ሚሻበት ቦታ ዝናሙን ይልክ ዘንድ" (ከመ ዝናሞ ይፈኑ ውስተ ኀበ ይትፈቀድ መካን) "ወደሚሻበት ቦታ ዝናሞችህን ላክ"(ዝናማቲከ ፈኑ ውስተ ኀበ ይትፈቀድ መካን) ይላሉ። 👉 ዝናም እንደ ገበሬው ቤት የሚፈለግበት ቦታ እንዳለ ሁሉ እንደ ሸክላ ሠሪው ቤት ደግሞ የማይፈለግበት ቦታ አለና ቤተ ክርስቲያን ከፈጣሪዋ ዝናም ከመለመን አልፋ የሚያዘንምበትን ቦታም እየጠቆመች ትጸልያለች። ✍ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን ይቆየን
Показать все...
Показать все...
የጨሪ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፈለገዮርዳኖስ የጉዞ ዝማሪዎች

@felegeguzozimare

Показать все...
የጨሪ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፈለገዮርዳኖስ የጉዞ ዝማሪዎች

@felegeguzozimare

ዓመታዊ ሰንበት ትምህርት ቤታችን በቋሚነት የምታዘጋጃቸው የንግስ ጉዞዎች ጥቅምት 05 ዝቋላ አቦ መጋቢት (የደብረዘይት ዕለት)- ሳማ ሰንበት እና ምሑር ኢየሱስ ገዳም ግንቦት 21 ፃድቃኔ ማርያም ሲሆኑ እንዲሁም በንግስ ዕለት ያልሆኑ መንፈሳዊ ጉዞዎችን ስናዘጋጅ እናሳውቃለን።
Показать все...
#ደብረ_ምጥማቅ ( #ግንቦት_21 ) ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው። የአርያም ንግሥት የሰማይና የምድር እመቤት የሰውነታችን መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች። ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር። ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር። ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ። እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታትን አስከትላት ትመጣ ነበር። በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም አሕዛብም ከየአገሩ ያሉ ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው ይከትማሉ፤ ድንግልም ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር፤ ህዝቡም የተለያየ ጥያቄ ይጠይቋታል አዳም አባታችንን አሳይን ይሏታል ገሚሱ ነብዩ ዳዊትን ገሚሱ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሳይን ይሏታል አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው ይጠይቃታል፤ እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው ነበር፤ አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር ዳዊትን ስትጠራው ከበገናው ጋር ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ ጋር ታሳያቸው ነበር። እመቤታችንን አይደለም በአካል መመልከት ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው። ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው። የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው። ፈልገው የሚያጡት ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም። ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል፣ መነኮሳት፣ መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና። እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸውም ነበር። እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል። 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል። እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከ ግንቦት 21-25 #በደብረ_ምጥማቅ መገለፅዋን አስመልክቶ ምዕመናንን በፃድቃኔ ማርያም የማጠን ስርአት ያደርጋሉ፡፡ ወደ እዚች ቅድስት ቦታ በቅድስቷ ዕለት መንፈሳዊ ጉዞ ስለተዘጋጀ እንዳትቀሩ።
Показать все...
ግንቦት 20 እና 21 የሚጎበኙ አጃና ሚካኤል ዋሻ መድኃኔዓለም ንግስ ግንቦት 21 እመቤታችን ደብረምጥማቅ ብላ የተገለጠችበት የአፄ ዘርዓያዕቆብ እመቤት የምትነግስበት ፃድቃኔ ማርያም
Показать все...
ሰላም ለፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት ተቋርጦ የነበረዉ የመዝሙር ቅጂ መልቀቅ ጀምረናል
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.