cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ንቁ ትውልድ

ወጣት ስትሆን ሁሉ ነገር ያምርሀል ስሜትህን ተቆጣጥረህ ለአላህዬ እንደመታዘዝ ግን የሚያረካህ ነገር አታገኝም ديلا

Больше
Рекламные посты
629
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-1130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
ለፍቅር ተብሎ ብዙ መስዋዕትነት ይከፈላል። ህይወትንም አሳልፎ ይሰጣል። እኔም ራሴን አሳልፌ ሰጥቼ ነበር......💔 የሚሰጠው ሰው በዛ  ልክ መስዋትነት የሚከፈልለት ነው ወይ የሚለውን አስብበት🤔🤔🤔 ወንድሞቼ ሁሉም ነገር ከራስ ቡሀላ ነው ተማምነህበት መደገፍ ያለብህ እራስህን ብቻ ነው የሚለውን  አስታውስ በዚህ ሁላ ስቃይና ማስዋትነት መሀል የተፈቃሪ ምላሹ ክፉ ከሆነ ግን ወሏሂ በህይወቱ ላይ የግፉ መልስ በከባድ እንደሚመጣበት ይወቅ። በብዙ ሰዎች ህይወት ላይ የተጀረበ ነው። በመንገዱ ላይ የተሰበረን ልብ የተወ ፍቅር መውደቁ አይቀርም join    join     join 👇👇👇👇👇👇👇👇   @wexat_ena_islam
Показать все...
😢 3🤔 2👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለፍቅር ተብሎ ብዙ መስዋዕትነት ይከፈላል። ህይወትንም አሳልፎ ይሰጣል። እኔም ራሴን አሳልፌ ሰጥቼ ነበር......💔 የሚሰጠው ሰው በዛ  ልክ መስዋትነት የሚከፈልለት ነው ወይ የሚለውን አስብበት🤔🤔🤔 ወንድሞቼ ሁሉም ነገር ከራስ ቡሀላ ነው ተማምነህበት መደገፍ ያለብህ እራስህን ብቻ ነው የሚለውን  አስታውስ በዚህ ሁላ ስቃይና ማስዋትነት መሀል የተፈቃሪ ምላሹ ክፉ ከሆነ ግን ወሏሂ በህይወቱ ላይ የግፉ መልስ በከባድ እንደሚመጣበት ይወቅ። በብዙ ሰዎች ህይወት ላይ የተጀረበ ነው። በመንገዱ ላይ የተሰበረን ልብ የተወ ፍቅር መውደቁ አይቀርም join    join     join 👇👇👇👇👇👇👇👇   @wexat_ena_islam
Показать все...
የነብዩላህ ሙሳ እና ተከታዬቻቸው ጉዳይ እጅግ በጣም ያሳሰበው ፈሪው ፈርዖን ነብዩላህ ሙሳ'ን "ድግምተኛ እና ውሸታም ነው" ብሎ የውሸት ስም መስጠቱ እና ፕሮፖጋንዳ መፍጠሩ ብቻ በቂ እንዳልሆነ ስለገባው ሰራዊቶቹን ሰብስቦ ሙሳ እና ተከታዬቹ ላይ ጦርነት ከፈተ! የመጀመሪያው Strateጂውም ሴቶችን አስቀርቶ ወንድ ልጆቻቸውን መ*ግደል ነበር! ልጆቻቸውን በገ*ደለ ቁጥር አላህ ላይ ያላቸው እምነት የሚቀንስ መሰለው። "አነ ረቡኩሙል አዕላ" ያለው አንባገነኑ ፈርዖን "አዎ! ሀያሉ አንተ ነህ!" ብለው እጅ የሚሰጡ መስሎት ያለርህራሄ ወንድ ልጆችን ጨፈ*ጨፈ። ግን የልጆቹ መ*ሞት ሙሳ እና ተከታዬቹ ላይ እምነትን እንጂ ሌላን አልጨመረም! በአላህ ብቻ መወከልን እንጂ ፍርሃትን አልፈጠረም! ፈርዖን እና ሰራዊቶቹ ግራ ገባቸው! ገዳዬቹ እነሱ፤ የተሸናፊነት ስሜት የሚሰማቸው'ም እነሱ ሆኑ። ስለዚህ ቀጣይ እቅዱ መሪያቸው ነብዩላህ ሙሳን መ*ግደል ሆነ። ጌታው ያድነው እንደሆነ እናያለን ብሎም ፎከረ! ነብዩላህ ሙሳ'ም «እኔ በምርመራው ቀን ከማያምን ትዕቢተኛ ሁሉ በጌታዬና በጌታችሁ ተጠበቅሁ» ብሎ መለሰ! ... ህፃን እያለ እናቱ ወንዝ ውስጥ በወረወረችው ሰአት ያዳነው ጌታ አሁን ላይም ከፈርዖን አረመኔያዊ ስራ እና ተንኮል እንደሚጠብቀው አረጋገጠ! መከራው እምነትን እንጂ ፍራቻን አልጨመረበትምና! አላህም ቁርኣኑ ላይ "إنه لا يفلح الظالمون : እነሆ! በደለኞች አይድኑም።" በሚለው ቃልኪዳኑ መሰረት ፈርዖንን እስከ የውመል አኺር ድረስ የሚቆይ ማስተማሪያ አደረገልን! 🙌🏽 ሁሉም ዘመን እንደ ፈርዖን ፈሪ የሆኑ ልጆችን እንኳን ያለ ርህራሄ የሚጨ*ፈጭፉ አምባገነን አውሬዎች አሉት! ሁሉም ዘመንም እንደ ነብዩላህ ሙሳ እና ህዝቦቹ መከራ እና እንግልቱ የበለጠ ኢማናቸውን የሚጨምርላቸው ህዝቦች አሉት! ታሪክ ታሪክን እንጂ አይደግምም! የአምባገነኖች ባህሪም አይለወጥም። አላህ ቁርኣኑ ላይ "ወየውመ ተቁሙ ሳኣቱ ዩብሊሱል ሙጅሪሙን: ሰአቲቱም በምትቆምበት ቀን አመጸኞች ጭጭ ይላሉ።" እንዳለው! ጭጭ የሚሉበት ቀን ተቀጥሮላቸዋል። የአላህ እርዳታም እውን መሆኑ አይቀርም! ከተቀጠረለት ቀን አይዘገይም። وَعْدَ اللَّهِ ۖ لَا يُخْلِفُ اللَّهُ وَعْدَهُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ "አላህ እርዳታን ቀጠረ፡፡ አላህ ቀጠሮውን አያፈርስም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡" ነውና የጌታዬ ቃል! ♥️ የአላህ እቅድ፤ ቀጠሮው እና እርዳታው እርግጥ ነው! ግን በዚህ መሃል ሚናችንን መለየት የሁላችንም የቤት ስራ ነው! አላህ ይታረቀን! የጋዛ ወንድም እና እህቶቻችንን በዱዓችን ውስጥ አንዘንጋቸው! #ጁመዓ_ሙባረክ ♥️ https://t.me/wexat_ena_islam
Показать все...
ንቁ ትውልድ

ወጣት ስትሆን ሁሉ ነገር ያምርሀል ስሜትህን ተቆጣጥረህ ለአላህዬ እንደመታዘዝ ግን የሚያረካህ ነገር አታገኝም ديلا

👍 2🔥 1👏 1
00:16
Видео недоступноПоказать в Telegram
ነገሮችህን ወደ አላህ ስታስጠጋ ትእግስትህ ከፍ ይላል። በጌታህ ፍርድ ታገስ ! https://t.me/wexat_ena_islam
Показать все...
10.11 KB
👍 4 2
'የመልዓክት ዓለም ሰዉ! إنسان من عالم الملائكة.' ሙሉ ክፍሉን ለፈለገ ይኸዉ። ከአማረኛዉ በተጨማሪ የዓረበኛ ሊንኩንም ከስር በኮመንት መስጫዉ ስር ተቀምጧል። ::::::::::::::::::::::::::::::::: 1- ሰይድ ቁጥብን እወደዋለሁ። ቁጥብይ(የእርሱ ተከታይ) ግን አይደለሁም!። ስላመነበት አንገቱን ሰጥቷል። ስለእምነቱ ተሰዉቷል። ከጥቂት ለዉጥ ሰሪዎች አንዱ ነዉ። ከሀያ በላይ መጽሀፍትን ደርሷል። ያዉም በእያንዳንዱ ፊደል ዉስጥ ሕይወት ያለዉ። በእያንዳንዱ መጽሃፍት ዉስጥ የሕይወት መመሪያ ቀኖና አለ!። 2- ሰይድ ቁጥብን እወደዋለሁ። ቁጥብይ ግን አይደለሁም። በቋንቋ፣ በስነ-ጽሁፍና በግጥም መስክ የተዋጣለት መሪ ነበር። 'التصوير الفني فى القرآن ክሱት ጥበባዊ ምስሎች በቁርአን' የተሰኘዉ መጽሀፉ እጹብ ድንቅ ነዉ። የቁርአንን ዉበት በእርሱ በኩል አይቻለሁ!። በእርሱ በኩል የቁርአን ዲስኩር ዉስጥን ሰርስሮ መግባት ሲችል በራሴ ስሜት አረጋግጫለሁ። የቁርአን ዉበትና ለዛ በእርሱ በኩል አማሎኛል!። ቀጥሎ ያነበብኩት: 'مشاهد القيامة فى القرآن የትንሳኤ ክስተቶች በቁርአን' የሚለዉን ነዉ። እንደለመደበት ማራኪ ነበር። ለዚህ ነዉ እርሱ ከጥቂት ክስተቶች አንዱ ነዉ የምለዉ። 3- ሰይድ ቁጥብን እወደዋለሁ። ቁጥብይ ግን አይደለሁም!። ስለእዉነት የቆመ ጀግና ነበር። ማስመሰል አያዉቅም!። ለእርሱ ሁለት ፊት መሆን ፈጽሞ አይታሰብም። ወላዋይነት አያዉቀዉም። ከገሀዳዊ ማንነቱ ዉጪ በገጸ-ባሕሪ መተወን አይችልበትም!። ቀድሞ ሸሪዓዊ ሀገረ-መንግስትን የማይቀበል ሴኩላር ሙስሊም ነበር። ታዲያ ያኔ የምር አቋም ነበረዉ። ከዚያ ሁሉን አቀፍ የደዕዋ መስመር ያለዉ ቁርአናዊ መመሪያን የሚከተል ሙስሊም ሆነ። ይህኔም እንደመጀመሪያዉ የምር ሰዉ ነበር። 'العدالة الإجتماعية في الإسلام ማሕበራዊ ፍትህ በኢስላም' የተሰኘዉን መጽሀፍ ደረሰ። 'ማራኪ የሀሳብ ጠብታዎች' በሚል ርዕስ መጽሄት ላይ ታትሞ ነበር። ወደ በኋላም ተከታታይ ጽሁፎቹ ተሰብስበዉ 'እስልምና እና ዓለም-አቀፋዊ ሰላም' በሚል ርዕስ በመጽሀፍ መልኩ ተሰንደዋል። በዚህ ላይ ብቻም አልተወሰነ። የ'ኢማም'ነት ማዕረግን እስኪያገኝ በደዕዋ መንገዱ በጽናት ዘልቋል። 4- ሰይድ ቁጥብን እወደዋለሁ። ቁጥብይ ግን አይደለሁም!። ሰይድ ወደ መጨረሻ የዕድሜ ዘመኑ ኢጅቲሃዱን(የግል አስተዉሎቱን) በሌሎች የመጽሐፍ ድርሳኖቹ ላይ አስፍሯል። የእዉቀት አባ መስጠት ነበር!። ብዙ ልክነት ቀንቶታል። አልፎም አፎም ስቷል!። 'في ظلال القرءآن በቁርአን ጥላ ስር' የተሰኘዉን የቁርአን ማብራሪያ መጽሀፉን ጽፎ በስድስት ጥራዝ ታትሟል። በምጡቅ የስነ-ቋንቋ ህግጋት ላይ የቆሙ ዉለኛ ሀሳቦቹን ገልጾ እስረኛ ሀሳቦችን አርነት አዉጥቷል። መሐይምነት፣ አገዛዝና ሌሎች አደገኛና ጥልቅ ምርምር የሚጠይቁ ርዕሰ-ጉዳዮችን እያነሳ ተችቷል። ይህም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በምጡቅ የስነ-ጽሁፍ ቋንቋ ከፍ ብሎ የታየበት ነዉ። እዚህም ላይ በእንብዛም ስህተት ብዙ ልክ ሆኗል። በሰፊዉ የታሪክ በር በኩል ወደ ዉስጥ ዘልቆ ገብቷል። የሚጽፈዉ ይኸን ሁሉ ነበርና። ይህን ሁሉ ሀሳብ የሚያብላላዉ እስር ቤት ዉስጥ መሆኑ ሌላኛዉ ተዓምር ነዉ!። ስንቱ የሴት ጭን እየሞቀ፣ አልጋ ላይ እየተገላበጠ በምቾት ሲኖር ስለኡማዉ ጉዳይ አንዲት ገጽ መጻፍ ተስኖት እርሱ በፍርግርግ ዉስጥ ሆኖ ህዝብን ነጻ ስለማዉጣት ያስባል!። 5. ሰይድ ቁጥብን እወደዋለሁ። ቁጥብይ ግን አይደለሁም!። ሰይድ ለትልቅ ህልም ኑሯል። ስለ-ህልሙም ሙቷል። አንባገነኖችን በቀለሙ ተፋልሟል። በሀሳቡ ተገዳድሯል። እየሞተ ግፈኛ ስርዓተ-መንግስትን ንዷል። ስለሕይወት ጎዳናዉ ሊሰዋ፣ ስላመነበት ራሱን ሊሰጥ፣ ገመድ በአንቱ ባጠለቀበት ወቅት አንድ የስርዓተ-መንግስቱ ደጋፊ ወደርሱ መጣ። ሆድ አደር ዙፋን አስጠባቂ የሐይማኖት ምሁር ነበር!። ፕሮፌሽናል ምሁሩ የመጨረሻ ቃል የሆነዉን 'ላ ኢላሃ ኢለላህ! ሙሐመዱን ረሱሉላህ'ን ሊያናዝዘዉ መጣ። "ሰይድ ሆይ! ከመሞትህ በፊት ከአላህ በስተቀረ በእዉነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩንና ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸዉን እመሰክራለሁ" በል አለዉ። ሰይድም: "አንተም ጨዋታዉን ልትቋጭ!? እኛ ስለላኢላሃ ኢለላህ እንሞትላታለን። አንተ በላኢላሃ ኢለላህ ትኖርባታለህ!" አለዉ። በመጨረሻም: ሰይድ ቁጥብ ሰዉ ነዉ። ነገር ግን ከሰዉም ሰዉ አንድያዎች አሉ!። መጪዉን የሚመለከቱ እሩቅ ተላሚዎች። የአካልነት መሻት ተጽዕኖን ድባቅ መትተዉ በመብረቅ ፍጥነት ወደ ዓላማቸዉ መዳረሻ የተስፈነጠሩ። እነርሱ ዘንድ በነጻ የተበረከተ ጸጋ የለም። ስለ ጸጋዉ ሁሉ ዋጋ እንዲከፈልበት የታለመለት ቢሆን እንጂ። እርሱ ከሌላ መዓድን የተሰራ ነዉኮ የሚመስለዉ። በመጪዉ ዓለም ሩሕ የሚቀዝፍ በቅርቢቱ ዓለም ነዋሪ!። በሰማያት ነዋሪ ብርታት ምድር ላይ የሚንቀሳቀስ። ሰይድ በአንድ መጽሀፉ ላይ ይህን ብሎ ነበር። "የምድ ነዋሪዎችን ከላይ ሆኜ ስመለከታቸዉ እነርሱን የሚያሳስባቸዉ ነገር እንደ ልጆች ሀሳብ ይመስለኛል።" ይህቺ በከፍታ ላይ ያለች ከፍ ያለች ሩሕ ናት። ከላይ ተንጠልጥላ ሰዎችን ወደታች የምትመለከት ነፍስ። "وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَنتُمُ الْأَعْلَوْنَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ ባለፈባችሁ ሁሉ ምክንያት የበታችነት አይሰማችሁ። አትዘኑም። የእዉነት ምእመናን እንደኾናችሁ እናንተ የበላዮች ናችሁ። የድል ፍጻሜዉ የእናንተዉ ነዉ።" የሚለዉ የአላህ ቃል ያቆመችዉ ሰዉ ነዉ። በእዉነቱ አንቀጿ የጠፋብህን የሕይወት ሚዛን ትመልስልሀለች። ከልቦናህ ጋር ታስታርቅሀለች። ይህ እንዴት ያለ አስደናቂ ብዕር እና ታላቅ አእምሮ ነው። ህዝቤ ግን ይዋልላል። ሰይድ ቁጥብ ባራመዳቸዉ የተወሰኑ አስተሳሰቦች ጉምቱ የኢስላም ምሁራኖችን ጭምር ተቃርኗል!። ሙሐመድ ዓማራ(ዶ/ር) ሰይድ ቁጥብን አስመልክቶ በጻፈዉ ለተቃርኖዉ ትችት አዘል ምላሽ ሰጥቷል። ያም ሆኖ ግን "እርሱ(ሰይድ ቁጥብ) ታላቅ ሙጅተሂድና ትልቅ ታጋይ ነዉ!" ሲል በአንድ ቃል አሞካሽቶታል። አል-ኢማም ዩሱፍ አልቀረዷዊ(ዶ/ር)ም ሰይድ ቁጥብን አስመልክተዉ ጽፈዋል። ስቷል ብለዉ ያመኑባቸዉ ብዙ ነጥቦች ላይ ስህተቱን ገልጠዉ ምላሽ ሰጥተዋል። ሆኖም "እርሱ ትልቅ ሰዉ! ትልቅ ታጋይ! ትልቅ አሰላሳይ! ነዉ። ጀግናን ጀግና እንጂ አያዉቀዉም!። የስለላ ማዕከላት ምልምል ጥሩንባዎች ወንድ አያዉቁም። እኔ በግሌ አስተሳሰቡን አስመልክቶ የራሴ ምልከታ አለኝ። ለዚህም በሊቀ-አዕላፍ ሸይኽ ዩሱፍ አል-ቀረዷዊ የትችት ሀሳቦች አልስማማም። ምክንያቱም አቡል-አዕላ አል-መዉዱዲም ከሰይድ ቁጥብ ሀሳብ ጋር ተመሳሳይ አመለካከቶችን አራምዷል። ሸይኹ ግን ሰይድ ቁጥብን በብርቱ ሲተቹ መዉዱዲን አልተቹም!። ስለዚህም ሁለቱም ጉልሀን ጽፈዋል፤ አስተዉሏዊ ጥረት አድርገዋል። ግን ደግሞ የማይሰራ ሰዉ አይሳሳትም። በአንጻሩ የሚሰራ ሰዉ ለልክነትም ለስህተትም የተጋለጠ ነዉ። እዚህ ጋር የብራታኒያዎችን አባባል ልጥቀስ: "የብሪታኒያ ንግስት ከስህተት የጸዳች ነች!። ምክንያቱም እርሷ ፖለቲካዊ ስራዎችን አትሰራም።"
Показать все...
ያን ሰዉ(ሰይድ ቁጥብን) አላህ ይዘንለት። በሰዉ መሀል ባይተዋር ሆኖ ኖረ። እንግዳ በመሰለ ቀንም ወደ ትልቅ ቀዉስ ዉስጥ ገባ። ይኼዉ እስካሁን(ተሰዉቶ አልፎ እንኳን) ስሙ ባይተዋር ነዉ!። ይህ የሆነዉ: ሰዎች የእርሱን መጽሀፍ ከሌላ የአስተሳሰብ አንጃ ተጽዕኖ ነጻ ሆነዉ ወይም ራሳቸዉን ብቻ ሆነዉ ስለማያነቡ ነዉ። ትልቅ ሰዉ እንዲህ ትልቅ ሆኖ ይቀራል! ባይተዋር ሰዉ አስተሳሰቡም ባይተዋር ሆኖ ይኖራል። ኢብን-ተይሚያም እንዲህ ነዉ የኖረዉ። ይሄዉ አሁንም ያዉ ሕያዉ አስተሳሰቡ ባይተዋር ነዉ። ጁወይኒም ይኸዉ እጣ ደርሶታል። ኢብን ሩሽድም አልቀረለት!። የሁሉም ባይተዋርነት ምክንያት የነጻነትና መዳኛ መንገዶችን ፕሮግራም ቀርጸዉ ማመላከታቸዉ ነዉ። ስለ ሐይድና ወሊድ የሚናገሩ አጫጭርና ብጣሽ ኪታብ የላቸዉማ!። ያን ሰዉ አላህ ይዘንለት። በፕሮግራሙ ሁሉ የሰዉ ልጆችን ያናገረ። በተለይም በዘመኑ የመሐይምነት ጨለማ ዉስጥ ያንቀላፉትን ለማንቃት ቅድሚያ መስጠትን የሻተ ሰዉ!። ሰማያዊ መልዕክቷን ረስታ እየዋለለች ያለችን ትዉልድ ከማይምነት ጨለማዎች ወደ ኢስላም ብርሃን ማዉጣት ተቀዳሚ ስራዉ ያደረገ። ግና የእርሱ መልዕክት እንዴ ይታያት!። ከመሐይምነት ጋር ተሳብዛለቻ!። መቀበል እንጂ መስጠትን የማትወድ ትዉልድ ሁና በቁሳዊ መሻት ታዉራለች። እንዲያዉም ደርዝ በራቀዉ የታሪክ ጠርዝ ላይ ለዘመናት መኖርን መርጣለች!። ደግሞ በዚህ መከረኛ ሁኔታ ላይ ሁና "ኸይር ኡማ ነኝ!" እያለች ትሸልላለች!። ምን የሚሉት ብልህነት ነዉ!? በእርሱ ላይ የምትቀጥፍ አንደበት ሁሉ ጥፋት ይዉረሳት!። ፀኃፊ: sh. Abdirahman Bashir ትርጉም: Hamudi Hamudi https://t.me/wexat_ena_islam
Показать все...
ንቁ ትውልድ

ወጣት ስትሆን ሁሉ ነገር ያምርሀል ስሜትህን ተቆጣጥረህ ለአላህዬ እንደመታዘዝ ግን የሚያረካህ ነገር አታገኝም ديلا

1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጫጉላ ላይ የነበረች ልጇ በፅዮናዊቷ ወታደሮች ህይወቷ ተቀጥፎ ተንሰቅስቃ ስታነባ ተንቀሳቃሽ ምስሉን አልጀዚራ ሲያስተላልፍ አየሁ። ይህ አሳማሚ ክስተት ዘመናትን ተሻግሬ እዚያው ፍልስጤም ምድር የተከሰተን ሌላ ታሪክ እንዳስታውስ ምናቤ እየደለቀ ወደ ሩቅ ዘመን አነጎደኝ።   ሀገሩ ፍልስጤም ነው። እርሷም በኢማን ተጠብቃ በተርቢያ ተኮትኩታ ያደገች አመለ ሸጋ ናት። የወደዳት የዕድሜ አቻዋ ሽማግሌ ልኮ ጋብቻውን አባት ከተቀበሉ ወዲህ የሰርጉ ቀን ሲቆረጥ ከኢድ ጋር ተገጣጠመ።   ድንኳን ተተከለ ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ተሰባሰበ እልልታውና የሰርግ ነሺዳው ተጀመረ ዕለቱ ድርብ ደስታ ሆነ። ዱፍና የሴቶቹ ጭብጨባ ተደማምሮ ልዩ ስሜትን ፈጥሯል ። ሙሽራው መጣ ኒካህ ታሰረ። ድግሱ እየተበላ ሳለ ከሰማዩ በላይ የአይሁድ የጦር ጀቶች የቦንብ ናዳ አዘነቡ። የበርካቶች ህይወት ተቀጠፈ። ሙሽሪትና ሙሽራ ተያይዘው ሮጡ። ሙሽራው ሆዱን በመሳሪያ ስለተመታ ደሙ መፍሰሱን አላቆመም። ደከመ አቅም አነሰው መራመድ አቃተው። ሚስቱ ኢንቲሳር ተንሰፈሰፈች የሙሽርነት ልብሷን ቀዳ ቁስሉን አሰረችለት። ውሀ ውሀ ማለት ጀመረ ከየት ታምጣ በድሮን ድብደባ አካባቢው ወና ያሉበትም ቦታ በረሀ ነው የገዛ ደሙን አትግተው ጨነቃት ምናልባትም እንጥሉን ካረጠበው በሚል የእንባዋን ዘለላ በአፉ አንጠባጠበችለት። "በጀነቱ ሀገር እስኪያገናኘን ደህና ሁኚ ፍቅር" አለና ስብርብር ባለ ቃና አመልካች ጣቱን ቀስሮ ላኢላሀ ኢለላህ ሙሀመዱን ረሱሉላህ እያለ ነፍሱ ከሩሁ ተላቀቀች። ከኔ ተሞሽሮ ሄዷል ወደ ሌላ ብዬም አላወራ አላህ ያስተቃቅፍህ ከሁረል ዐይን ጋራ በእርግጥ ዛሬ ማታ እንደሰው ያሰብኩት ነፍሴ ተመኝታ ቀጠሮ  ነበረኝ  ካንተ  ጋር  ጨዋታ      አለችና ተናነቃት ሲቃ እንባዋ ባንገቱ መሀል ፈሰሰ ጀናዛውን ከጭኗ ላይ ወደመሬት አለችው። ግንባሩን ሳም አርጋ የሸማዋን ቅዳጅ ደም ያረጠበውን የጨርቅ ትራፊ አውልቃ አለበሰችው።        Mahi Mahisho https://t.me/wexat_ena_islam
Показать все...
ንቁ ትውልድ

ወጣት ስትሆን ሁሉ ነገር ያምርሀል ስሜትህን ተቆጣጥረህ ለአላህዬ እንደመታዘዝ ግን የሚያረካህ ነገር አታገኝም ديلا

3👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
የመከራው መበርታት፣ የሰቆቃው ልክ ማጣት፣ የበደለኛውና የወራሪው ኃይል በደል መግዘፍ የድል መቅረቢያው ምልክት ነው። የሙእሚን ኢማንም ዋነኛው የፈተና ወቅት ይህ ነው። በጌታው ላይ ያለው ጥርጣሬ ምን ይሆናል? ተስፋን ይቆርጣል ወይንስ ይበልጥ የድል መቅረብን አምኖ በፅኑ በደሙ እንጥፍጣፊም ቢሆን ይታገላል? "فما ظنكم برب العالمين" " ከአለማቱ ጌታ ላይ ያላችሁ ጥርጣሬ ምንድነው? (ምንስ ታስባላችሁ?" ቁርኣን የሷፋት ምዕራፍ ★በአላህ ድል አብሽሩ። ቃሉም አይታጠፍም። ውርሱም አይነጠቅም። ብርሃኑም አይጨልምም‼ " ولقد سبقت كلمتنا لعبادنا المرسلين... إنهم لهم المنصورون... وإن جندنا لهم الغالبون " " መልእክተኛ ለሆኑት ባሮቻችን (የእርዳታ) ቃላችን በእውነት ተላልፋለች፤  እነርሱ ናቸው ተረጂዎቹ (የአላህ እርዳታ ያላቸው)። አሸናፊዎችም ሰራዊቶቻችን ናቸው " ቁርኣን የሷፋት ምዕራፍ اللهم كن مع عبادك اللهم كن مع أهل غزة وأهل الأقصى يارب افرع عليهم الصبر وثبت اقدامهم وانصرهم على الظالمين الغاصبين المعتدين #الأقصى حياتنا والموت في سبيلها اسمى امانينا
Показать все...
👍 1
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.