cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ፍቅርሽን በትዝታ❤️

የይቅርታ ልብ ሁሌም ታላቅ ነው። ❤ 👉 በቻናላችን የሚያገኟቸው ነገሮች፦ 📒 የመፅሐፍ ጥቆማ 📗 ልብ አንጠልጣይ ትረካዎች 📘 እንዲሁም አዝናኝ እና ቁም ነገሮችን ስለ ፍቅር ስለ ናፍቆት ስለ ትዝታ ከሁሉም በላይ ስለ መልካምነት እናወራለን:: @fikrishinbetzta 👉 @Dinkish3

Больше
Эфиопия8 114Амхарский6 730Факты6 815
Рекламные посты
472
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-1630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
#አንድሰው_ላመስግን... ሰሞኑን ሴት እህቶቻችን የተራቆቱና የሰውነት ክፍሎቻቸውን በደንብ የሚያሳዩ ልብሶችን እየለበሱና መዝሙር አየዘመሩ ቪዲዮ እየለቀቁ በተለይም በቲክቶክ መንደር በስፋት መነጋገሪያ ሆነዋል። ብዙዎችም ሀዘንና ቁጣቸውን ገልፀዋል። አሁን አሁን የተራቆቱ አለባበሶችን በቤተክርስቲያን፣ በተለያዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ማየት እጅግ እየተለመደ መጥቷል። እህቶቻችንም ደምቀው መታየታቸውን እንጅ ለሰው መሰናከያ መሆናቸውን አያስቡም። እዚህ ጋር አንድ አገልጋይ ላመስግን የጳውሎስ ቤተክርስቲያን መሪ አገልጋይ ጥበቡ ወርቅዬ። በዚህች ቤተክርስቲያን የተራቆተ መልበስ አይደለም አጠር ያለ ቀሚስ ማድረግም አይቻልም። እንደ ግዴታ ሳይሆን ሴቶች ረዥም ቀሚስ፣ ፈፅሞ ቸርች ውስጥ የሌላውን ትኩረት የማይሰርቅ አለባበስ ለብሰው እንዲመጡ በየፕሮግራሙ ይነገራል። በዚህም ምክንያት የቸርቹ እህቶች ነገሩን ለምደውት ረዥም ቀሚስ፣ የማይረብሽና ትኩረት የማይሰርቅ አለባበስ ለብሰው ይመጣሉ። ቤተክርስቲያናት ከዚህ ወንድም መማር አለባቸው።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
መሄድ ይሻላል መሄድ ይሻላል ብላ ያቺ ምስኪን እራሷን ካጠፋች በኋላ ብዙ ወጣቶች መሄድ ይሻላል እያሉ በማህበራዊ ሚዲያ ባጋሩን ቁጥር ተሳቀን አለቅን። ወጣቶች ወንድሞቼና እህቶቼ እራስን ማጥፋት በጣም ለሀገር ለጓደኛ ለቤተሰብ የምንሰጠዉ ሀዘን ቀላል እንዳይመስላቹ። በተለይ ያልወለዳቹ አታቁትም ሰዉ ለልጁ ምን አይነት ስሜት እንዳለዉ። በተለይ የኛ የሀበሾች አባትና እናት በሌለ አቅማቸዉ ተሰቃይተዉ ተንከራተዉ አሳድገዉ ለነሱ አለማሰብ በጣም ሰነፍነት ነዉ። ሰሞኑን አንዲት እህት ደዉላ እራሴን ላጠፋ ነዉ መዝሙርህን ሰምቼ ምን አልባት አንተ የምትለኝ ነገር ሊኖር ይችላል ስትለኝ ስልኳን ተቀብዬ ደዉዬ ተመካከርን ከዛ ደህና ሆነች። የአንዳንድ ሰዉ የከበደበት ነገር የአንድ ስልክ ጥሪ ሊፈታዉ ሊያክመዉ ይችላል። እንደሚታወቀዉ ባደጉት ሀገራት ይሄ ነገር በጣም የተለመደ ነዉ። የዉጪዉ ባህል ሰዉ ከሰዉ ጋር አያወራም ጎረቤት አይተዋወቅም። ሰዉ አይተያይም። ሀገራቸዉ ከስራና ከመኖር ዉጪ ብዙ ንግግር የለም። እኔም በአገልግሎቴ ምክንያት ስዘዋወር የሀገሬዉን ሰዉ ትንሽ ወሬ ሳወራቸዉ በጣም ረጅም ብዙ ያወሩኛል። ከዛም በማህበራዊ ኑሮአቸዉ የዉጪ ሀገር ሰዉ ከእኛ ሀገር ጋር ሲስተያይ ደካማ እንደሆነ ተረዳዉ። ይሄ ባህል ወደ ሀገራችን እየመጣ ነዉ። ሰዉ በጣም ግለኛ እየሆነ የሰለጠነ እየመሰለዉ ነዉ። በእኛ ሀገር ሁኔታ ሰዉ ዝም ካለ ሰዉ አልፈልግም ካለ በጣም አደገኛ ነዉ። ሰዎች ይሄ ሁሉ ህዝብ እያለ የብቸኝነት ስሜት ሊሰማቸዉ አይገባም። እባካቹ በዙሪያችን ብዙ ምስኪኖች አሉ እንያቸዉ እንቀፋቸዉ እናሶራቸዉ እንስማቸዉ። አመሰግናለዉ ዘማሪ በረከት ተስፋዬ
Показать все...
የዝቅተኛነት ስሜት ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ ሰዎች በራሳቸው ላይ ያላቸው ግምት እጅግ የወረደ ከመሆኑ የተነሳ በአቅማቸው ልክ ከመኖር ይገታሉ፡፡ አንድ ሰው በራሱ ላይ ያለው ምልከታ እጅግ አናሳ ሲሆንና የዝቅተኝነት ስሜት ሲጫጫነው ያንን ስሜት ለመሸፈን ሲል የተለያዩ ባህሪዎችን ሊያንጻበርቅ ይችላል፡፡ 1. ሰዎችን ለማስደሰት መታገል የራስ-በራስ ምልከታው የወረደበት ሰው ሌሎች ሰዎች ሲቀበሉት ጊዜያዊ የሆነን ጥሩ ስሜት ስለሚሰጠው ያንን ላለማጣት ሲልና ያለበትን የዝቅተኝነት ስሜት ስለሚሸፍንለት ካለማቋረጥ ሰዎች ለማስደሰት ሲታገል ራሱን ያገኘዋል፡፡ በሌላ አገላለጽ የማንነቱን ዋጋ ከፍና ዝቅ የሚያደርገው በሰዎች መደሰትና አለመደሰት ነው፡፡ 2. ነገሮችን ማስተላለፍ የዝቅተኛት ስሜት ያለበት ሰው በራስ የመተማመኑ መጠን የወረደ ስለሆነና አንድን ነገር ጀምሮ ላይሳካለት እንደሚችል ስለሚያስብ ጉዳዩን ለሌላ ቀን በማስላለፍ ያልፈዋል፡፡ 3. ራስን ከሌሎች ጋር ማነጻጸር ራሱን ዝቅ አድርጎ የሚመለከት ሰው ካለማቋረጥ ራሱን ከሌሎች ሰዎች ሁኔታ ጋር በማነጻጸር የሚያይበት ምክንያት ስሜቱ በማን እንደተበለጠና ማንን እንደበለጠ እንዲመለከት ስለሚያስገድደው ነው፡፡ በተለይም ሰዎች ካልተሳካላቸው የእሱን ደረጃ ከፍ ያደረገለት ስለሚመስለው ከዚህ አዙሪት መውጣት ያስቸግረዋል፡፡ 4. ማሕበራዊ ግንኙትን መሸሽ የወረደ የማንነት እይታ ያለው ሰው በማሕበራዊ ግንኙቶቹ ውስጥ ስለሁኔታው ሰዎች ሊጠይቁት እንደሚችሉ ስለሚፈራና እንዲሁም ሰዎች ከእሱ የተሻለ ሁኔታን ይዘው እንደሚመጡ ስለሚያስብ ስጋት ያድርበታል፡፡ ስለዚህም፣ ምንም እንኳን የሰዎችን አብሮነት ውስጡ ቢፈልገውም ማሕበራዊ ግንኙነቶች ምቾት ስለማይሰጡት እንደሸሸ ይኖራል፡፡ 5. የስሜት ስስነት ራሱን ዝቅ አድርጎ የሚያይ ሰው ሰዎች የሚናገሩትን፣ የሚያደርጉትንና ሁኔታቸውን ሳይቀር ከራሱ ጋር በማገናኘት የመጎዳት ዝንባሌ አለው፡፡ ደውሎ ስልክ ካልተነሳለት፣ ሰዎች በደንብ ሰላም ያላት ከመሰለው፣ እሱ በሌለበት ጓደኞቹ ከተገናኙ . . . ይሰማዋል፡፡ 6. የግል ቀይ መስመር (Personal boundary) አለመኖር በዝቅተኝነት ስሜት የተመታ ሰው ሰዎች እንዳይርቁት ስለሚፈራ ለሚያቀርቡት ማንኛውም ጥያቄ፣ ምንም ባይስማማው እንኳን “እምቢ” የማለት አቅም የለውም፡፡ ያለበት የዝቅተኛነት ስሜት በሰዎች መገፋትን የመቋቋም አቅሙን ስላደከመበት ሰዎች እንዳየገፉት ሲል መስመር-አልባ ሕይወት ነው የሚኖረው፡፡ 7. ከልክ ያለፈ መስጠት ራሱን ዝቅ አድርጎ የሚመለከት ሰው ካለማቋረጥ ለሰዎች በመስጠት የዝቅተኛነት ስሜት ያጎደለበትን ባዶነት ለመሙላት ይጣጣራል፡፡ ጊዜውን ይሰጣል፣ ገንዘብ ያወጣል፣ ቁሳቁስ ይሰጣል . . .፡፡ ይህንን በማድረጉ ሰዎች ደስ እንዲላቸው፣ እንዲቀበሉትና በእሱ ላይ ያላቸው አመለካከት ከፍ እንዲል ይታገላል፡፡ ምንም አይነት ማሕበራ መስክ ውስጥ ዘልቃችሁ ከመሄዳች በፊት ከዝቅተኛነት ስሜት ነጻ የምትሆኑበትን መንገድ መፈለጋችሁ እርግጠኞች ሁኑ፡፡ የመፍትሄ ጉዞ ለመጀመር በነገው “ፓስቴ” በራሳችን ላይ ካለን የወረደ አመለካከት ለመውጣት ትልቅ መዋጮ ከሚያደርጉት ልምምዶች መካከል አንዱን አጋራችኋለሁ፡፡ @Dinkish3
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
በሕይወት ሩጫ ውስጥ የሚያሸንፈው ቀድሞ የደረሰ ብቻ አይደለም ውድድሩን የጨረሰ ነው ።የግድ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ቀድመን ወይም እኩል መድረስ አለብኝ ብለን ራሳችንን ማስጨነቅ የለብንም ።ራሳችንን ካወዳደርን አይቀር ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከትናንቱ ማንነታችን ጋር መሆን አለበት ።ስከት የሚለካው በራስ መነፅር እንጂ ከለሎች ጋር ባለን ንፅፅር አይደለም ።
Показать все...
አይ ጡዘት 😥 ይሄ አሁን ምን ይባላል 🤔እግዚኦ ማረን🙏 ሴት ልጅ ራቁታን ማሳየት ምን የምሉት ዝቅጠት ነው🤔 ጡትና ዳለ ማሳየት እርድና ምመስላቸው የዘቀጠ ትውልድ🙄
Показать все...
🌀✅ ባለትዳሮች ወደ መኝታቸው እያመሩ ነው፡፡ በድንገት ባልየው ከቤታቸው ጀርባ ያለውን አትክልት ቤት መብራት እንዳላጠፋው ትዝ አለውና ተነስቶ ወደዛ አመራ ነገር ግን አትክልት ቤቱ ውስጥ ሶስት ሌቦች ሰብረው ገብተው ተመለከተ፡፡ ወዲያው ፖሊስ ጣቢያ ደውሎ እርዳታ ጠየቀ፡፡ ኦፊሰሩም "አሁን ሁሉም ፖሊሶች ለስራ ወጥተዋል፤ ምንም ፖሊስ የለም፡፡ እንደተመለሱ እልክልሀለው" አለ፡፡ ሰውዬው በጣም ከመፍራቱ የተነሳ ከተወሰኑ ደቂቆች በኀላ መልሶ ደወለ፡፡ "አታስብ ኦፊሰር፤ ሶስቱንም ሌቦች ገደዬ ቆራርጬ ለውሻዬ ሰጥቻቸዋለው፤ ምንም ፖሊስ መላክ አይጠበቅብሕም" አለው፡፡ ብዙም ሳይቆይ በሶስት የፖሊስ መኪና የታጨቁ ከ10 የሚበልጡ ፖሊሶች የሰውዬውን መኖሪያ ቤት ከበቡት፡፡ ኦፊሰሩም አብሮ ነበረ፡፡ ነገር ግን ሌቦቹ እንደተባለው ተገለው ተቆራርጠው ለውሻ ተሰጥተው ሳይሆን ከእነ ነፍሳቸው ሲሰርቁ ተያዙ፡፡ #ኦፊሰር ፡- "ገድዬ ቆራርጬ ለውሻዬ ሰጥቻቸዋለው ያልክ መስሎኝ" #ሰውየው ፡- "አንተም አሁን ምንም ፖሊስ የለም፤ ሁሉም ስራ ወጥተዋል ያልክ መስሎኝ" አለው፡፡ #ጭብጥ :- ብዙ ግዜ አብዛኞቹ በህይወታችን ያሉ ሰዎች እኛ ስንፈልጋቸው አናገኛቸውም፤ ነገር ግን በእኛ የውድቀት እና የመከራ ወቅት ያዘኑ መስለው ለማፌዝና ወደ ጥልቁ ስንወርድ ከንፈር ለመምጠጥ በዙሪያችን ይሰበሰባሉ፡፡ ታሞ አንድ ብርጭቆ ውሃ ያልሰጠነውን ሰው ሲሞት አፈር ለመጫንና ንፍሮውን እየበላን "እንዲህ ነበር እሱ" እያልን የውሸት ድርሰታችን ለማንበብ አንጣደፍ፡፡ እውነት የምንላቸውን ሰዎች ከወደድናቸው፤ ስለ እነሱ የምናስብ ከሆነ ሰው በሚያስፈልጋቸው ወቅት ከጎናቸው እንሁን። @Dinkish3 የተመቸው ሼርርርር ያድርገው
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ህይወት በኦሾ እይታ ብላችሁ ለጠየቃችሁኝ!! *** ህይወትን አክብሩ። ከህይወት የበለጠ የተቀደሰ ፣ ከሕይወት የበለጠ መለኰታዊ የሆነ ነገር የለም። ***/** እንድታስታውሱ የምመክራቹሁ በህይወት እንድትኖሩ እና ህይወት ምን እንደሆነች ለማወቅ እንድትሞክሩ ነው። በሕይወት መኖራችሁ በጣም ውድ ነገር መሆኑ አስታውሱ። ህይወትን አክብሩ ። : ከህይወት የበለጠ የተቀደሰ ፣ ከሕይወት የበለጠ መለኰታዊ የሆነ ነገር የለም። #ህይወታችሁን አክብሩ። ህይወታችሁን በማክበርም የሌሎችን ህይወት ማክበር ትጀምራላችሁ። : #ዋናው ምክንያት ህይወትን ካከበራችሁ #አበባን እንኳን መቅጠፍ ይከብዳችኃል። አበባው ያስደስታችኃል ፣ ትወዱታላችሁ ፣ ትዳስሱታላችሁ ፣ ታሸቱታላችሁ ነገር ግን አበባውን መቅጠፍ ልክ እንደ እናንተ ህይወት ያለውን አካል ማጥፋት እና ማሰቃየት ነው።
Показать все...
-💔 አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን ውስጥ የማያልፍ የሚመስሉ ትልቅ ችግሮች ያጋጥሙናል ፤ ሲጨልምብን ሰው ፈልገን ልናጣ እንችል ይሆናል ... በጨለመብን ጊዜ እንኳን የሚረዳን ሰው በብርሃን አብሮን የነበረው የራሳችን ጥላ እንኳ አብሮን እንደማይኖር ማመን አለብን ፥ ካልሆነ ግን ስሜታችን የበለጠ ደካማ ያደርገናል ...... የከፋችሁ ሰዎች አውቃለሁ የበለጠ ብቻ መሆን ምን ያህል ልብ እንደሚሰብር ነገር ግን የቀረንን ጥንካሬ ሰብስበን በቂ ጉልበት እስክናገኝ ድረስ ለአእምሮችን ሽንፈትን አንንገረው ... በተቻለን አቅም አማራጮችን ደጋግመን እንሞክር ፥ ለጊዜው ቢጨልም እንኳ ጨለማ በብርሃን እንደሚተካ እንመን ፤ ተስፋችንን እናለምልም 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 @Dinkish3
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.