ru
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Открыть в Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Больше
603
Подписчики
Нет данных24 часа
-87 дней
-1630 дней
Архив постов
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ስብሰባ እየተካፈሉ ይገኛሉ፤ ++++++++++++++++++++++++++++++++++++ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸ
+1
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ስብሰባ እየተካፈሉ ይገኛሉ፤ ++++++++++++++++++++++++++++++++++++ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ስብሰባን ለመካፈል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ወክለው የተጓዙ ሲሆን ስብሰባው በጄናቫ ቦሴ የቴዎሎጅ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ በየጊዜው በሚያደርጋቸው ከፍተኛ ጉባኤዎች ላይ ቤተ ክርስቲያን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በሚመራ ልዑክ የምትሳተፍ ሲሆን በዚሁ መሠረት ከኅዳር 17-20 ቀን 2016 ዓ/ም በሚደረገው ጉባኤ ለመገኘት ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነትና ከልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የተወከሉ ልዑካንን በመምራት በጉባኤው እየተሳተፉ መሆኑን የውጪ ግንኙነት። መምሪያ ለኢኦተቤ ቴቪ በላከው መግለጫ አስታውቋል ፡፡ ብፁዕነታቸው በቅርቡ በቅዱስ ሲኖዶስ የታወጀውም የጸሎትና ምኅላ መርሐ ግብር ላይ በመጀመሪያዎቹ ሦስት ቀናት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ሲሳተፉ የቆዩ ሲሆን ከጉዳዩ አስፈላጊነት አንፃር ወደ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ቢጓዙም በዚያው ባሉበት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያወጀችውን ጾምና ጸሎተ ምኅላ የተረዱ የጉባኤው ተሳታፊዎች እነሱም ከኢትዮጵያውያን ጋር ያላቸውን አጋርነት በመግለጽ አብረው መሆናቸውን በጉባኤው ላይ ገልጸዋል፡፡ ብፁዕነታቸውም የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ለመፈጸም ባሉበት ከልኡካናቸውና ጋር ሥርዓቱን እያካሄዱ መሆኑን ታውቋል ፡፡ EOTC Tv

✝ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፲፰ (18) ቀን። ✝ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት አንዱ ለሆነው #ለሐዋርያው_ቅዱስ_ፊልጶስ_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕ
✝ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝             ✝ #ኅዳር ፲፰ (18) ቀን። ✝ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት አንዱ ለሆነው #ለሐዋርያው_ቅዱስ_ፊልጶስ_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ #ከሮሜ_አገር በንጉሥ እንድርያኖስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉ #ለቅዱስ_ኤላውትሮስና_ለእናቱ_ቅድስት_እንትያ ለዕረፍትና #ለቅዱሳን_ደናግል_አጥራስስና_ዮና ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከየዋህ  #ከቅዱስ_አትናቴዎስ ከዕረፍቱ መታሰቢያ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

አዲስ አበባ ሀገረ  ስብከት ሰንበት ት/ ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡ ኅዳር 16/2016 ዓ.ም ለ20ኛ ጊዜ  "አንድነታችን ለቤተ  ክርስቲያናችን "በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀናት በሃገረ ስብከቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ  በብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ፣ የሀገራቀፍ እና የአዲስ አበባ የሰ/ት/ቤቶች የአንድነ አመራሮች፣ የአድባራትና የገዳማት ሰንበት ት/ቤት  አመራራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት  ሲካሔድ የነበረው የአዲስ አበባ ሀገረ  ስብከት ሰንበት ት/ ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቀቀ  ። በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ የ3ዓመት የሥራ ትግበራ ሪፖርቶች እና የ6ወር የዕቅድ አፈጻጸም  ትኩረት ተደርጎ ሲሰራባቸው የነበሩ አምስት አብይት ጉዳዮች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ቀጣይ ሊሰራባቸው የሚገቡ የትኩረት አቅጣጫዎች ባማከለ የአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት  ሰብሳቢ ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል። በማስከተል በአቶ ልቅናው ደምሴ የ2016 ዓ.ም የዓመት ዕቅድ ቀርባል በዚህም ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል ። ሰ/ት/ቤቶች በቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ድርሻና አሁናዊ ተሳትፎ በሚል መነሻ ሃሳብ በላዕከ ሔራን መንክር ግርማ ጽሑፍ የቀረበ ሲሆን በዚህም ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከጉባዔው የመፍትሔ ሐሳቦች በመነሳት ውይይት ተደርጓል :: በመጨረሻም በብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ  የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ  ጉባኤው ተጠናቋል።

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፲፯ (17) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊቷ_ሰማዕት_ወጻድቅ ለሆነችው በጣና ባሕር ላይ ቆማ ስትጸልይ ልብሷ ለገዳሙ ያበራ
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝            ✝ #ኅዳር ፲፯ (17) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊቷ_ሰማዕት_ወጻድቅ ለሆነችው በጣና ባሕር ላይ ቆማ ስትጸልይ ልብሷ ለገዳሙ ያበራ ለነበረችው ለታላቋ እናት #ለቅድስት_ወለተ_ጴጥሮስ_ለዕረፍት_በዓልና ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ዐፅማቸውን የተሸከች በቅሎም ለወለደችና ለመካኖች ልዩ ቃል ኪዳን ለተሰጣቸው ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሲኖዳ_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ✝ #ሰማዕት_ወጻድቅ_ቅድስት_ወለተ_ጴጥሮስ፦ የትውልድ ሀገሯ ጎንደር ደዋሮና ፈጠጋር ነው፡፡ አባቷ ቅዱስ ባሕር ሰገድ እናቷ ቅድስት ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ፡፡ በሕግ በሥርዓት በሊቀ ጳጳሱ ትእዛዝ የንጉሥ ሱስንዮስን የአማካሪዎች አለቃ የሆነውን መልክአ ክርስቶስን አግብታ ሦስት ልጆችን ወልዳለች፡፡ ባሏም ታላቅና እጅግ ባለጸጋ ነበርና ከልጆቿ ጋር በተድላ በደስታ መኖር እንደ ጀመረች "አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ እነዚህ ሦስት ልጆቼ አንተን የማያስደስቱ ከሆነ በሞት ውሰዳቸው" ብላ ከጸለየች በኋላ እንደፍላጎቷ ሦስቱም ልጆቿ በሞት ተወስደውላታል፡፡ √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨

የአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ " አንድነታችን ለቤተክርስቲያናችን " በሚል ርዕስ ተከናወነ። ዘጋቢ ሰላም አምባዬ (#EOTCTV ኅዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም) +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚከናወነው የአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ   ዘንድሮም ከኅዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ኅዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም " አንድነታችን ለቤተክርስቲያናችን" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ ዓመታዊ ጉባኤውን አከናውኗል። በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የቅድስት ሥላሴ  ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና የደቡብ ኦሞ ጅንካ ፣ የአሪ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  የተገኙ ሲሆን "መልካም አገልጋይ በንጉሡ ላይ ይወደዳል" በማለት ሰንበት ትምህርት ቤት ትውልድን ለመቅረጽ የሚሰጠው ጠቀሜታው ታላቅ ስለሆነ ከነበረው አገልግሎት በተሻለ መልኩ በንጉሡ በእግዚአብሔር የሚያስወድድ ሥራ ሊሰራ ይገባል በማለት አባታዊ መልእክታቸውን  አስተላልፈዋል ። በመርሐ ግብሩ የሰንበት ትምህርት አባላትና ምእመናን  በቃለዓዋዲ በተሰጠው የመወሰን ድርሻና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አወቃቀር ተጠሪነትና ኃላፊነት  የሚዳስስ  ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ። በመቀጠልም በሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ  የተዘጋጀውን የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ  ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም ቤተክርስያን አሁን ካለችበት ፈተና (ከወቅታዊ ) አንጻር  ቤተክርስቲያናችንን ልንጠብቅ ቀና የሆነ ተሳትፎ ሊኖረን ይገባል ሲሉ መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወልደ ትንሳኤ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ምክትል ኃላፊ  መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በመጨረሻ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ  ለሦስት ዓመት የሚያገለግሉ አዳዲስ አባላት ኮሚቴ ምርጫ በማከናወን በብፁዕነታቸው  ጸሎትና ቡራኬ የሥራ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል ።

በትግራይ የሚገኘው እና ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ተወግዞ የተለየው የፖለቲከኞች ጉዳይ አስፈጻሚ ቡድን መናፍ_ቁ  ሠረቀብርሃንን በሕገወጥ መንገድ ልብሰ ጵጵስና ማልበሱ ተገለጸ ! ኅዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም +++ ኢትዮጵያን ኤልዛቤል በማለት በድፍረት የተናገረው እና በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ላይ የመናፍ_ቃን ትምህርቶችን እና አበው ቀደምት ያወገዟቸውን አስተምህሮዎች የሚያቀነቅነው በቀድሞ ስሙ "አባ" ሠረቀ ብርሃን ወልደሳሙኤል በአሁኑ መጠሪያው አቶ ሠረቀብርሃን በዛሬው ዕለት በጥንታዊቷ እና በታሪካዊቷ በአሁኑ ወቅት በሕገወጡ የፖለቲከኞች ጉዳይ አስፈጻሚ ሽማግሌዎች ቁጥጥር ሥር በምትገኘው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ ርስት ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ላይ  ልብሰ ጵጵስና በማልበስ እና በመልበስ በትግራይ የሚገኙ የቀድሞ ጳጳሳት ድፍረት በተሞላበት መልኩ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ከቀኖና እና ከዶግማ ባፈነገጠ መልኩ ለ3ተኛ ጊዜ ሕገወጥ ሢመት በመፈጸም ታሪክ ይቅር የማይለውን በደል ፈጽመዋል። አቶ ሠረቀብርሃን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባለፈው ዓመት ተወግዘው ከቤተ ክርስቲያን ከተለዩ መናፍ'ቃን መካከል አንዱ ሲሆን ቀደም ሲል በልብሰ ጵጵስና የማልበስ ተግባር ውስጥ ለመሳተፍ የሰደባትና ያዋረዳት ኢትዮጵያን ለመጎብኘት በሚል የዳቦ ስም ወደ አዲስ አበባ በመጣ ጊዜ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ሆኖ ወደመጣበት መመለሱ ይታወሳል። በአሁኑ ወቅትም በየትኛው የማለፊያ መስፈርት ወደሀገር ቤት እንደገባ ባይገለጽም በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ገዳም ተገኝቶ የልብሰ ጵጵስና ሥነ ሥርዓቱ ላይ መሳተፉን በትግራይ የሚገኙ የመንግስት ሚዲያዎች እና የዚህ ሕገወጥ ተግባር ዋነኛ አቀንቃኞች ካሰራጩት መረጃ ለመረዳት ተችሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ ለሚገኙ ምዕመናን ጠባቂ የሚሆኑ ኤጲስ ቆጶሳትን እንዲሾም እና ከእነዚህ ሕገወጥ የፖለቲከኞች ጉዳይ አስፈጻሚ አካላት ቤተ ክርስቲያንን ነጻ እንዲያደርግ በርካቶች እየጠየቁ ባሉበት ሁኔታ የሀገሪቱ ሀገረ መንግስት አንድነት በተጠበቀበት እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ ሰውነት በሕግ ባልተሻረበት ሁኔታ በዚህ መልኩ ወረራ የሚፈጽሙ እና ምዕመናንን ለመከራ እየዳረጉ የሚገኙት አካላት ይህንን ሕገወጥ ተግባር መፈጸማቸው እጅግ አሳዛኝ መሆኑን ምዕመናን ይገልጻሉ። በጥር 14ቱ ሕገወጥ ሢመት ላይ ንቃት የተሞላበት የቤተ ክርስቲያንን ክብር የማስጠበቅ እና የሕግ ጥሰቱን የመከላከል ተግባር ሲፈጽሙ የቆዩት የቤተ ክርስቲያኒቱ የመዋቅር አካላት ይህንን ሕገወጥ ሢመት በአሁኑ ወቅት በምን አግባብ እየተመለከቱት እንደሚገኙ ለማወቅ አልተቻለም። ©ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

✨✨ ስደተኞች  ክፍል ሁለት ፪✨✨ ተዋንያን      ሳሙኤል ገዛኸኝ      አቤል ለታ     ረድኤት ብርሃኑ     አብርሃም ሙላቱ ምንጭ ከ ቪኒሲያ መፅሐፍ

✝ በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ✝ ✝ #ኅዳር ፲፮ (16) ቀን። ✝ እንኳን #በሮሜ_አገር በከሀዲ መኰንን በእስክድሮስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለች #ለቅድስት_ጣጡስ_ለዕረፍ
✝  በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።  ✝            ✝ #ኅዳር ፲፮ (16) ቀን። ✝ እንኳን #በሮሜ_አገር በከሀዲ መኰንን በእስክድሮስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለች #ለቅድስት_ጣጡስ_ለዕረፍት በዓል፣ ለመነኰስ #አባ_ዳንኤልና #ለንጉሥ_አኖርዮስ_ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለእስክድርያ አገር አርባ ስምንተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ ለከበረና ለተመሰገነ #ለገዳማዊ_አባ_አቡናፍር ከምስር ከተማ ውጭ ለተሰራች ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበት፣ #ለቅዱስ ኪስጦስ በመኰንኑ በመክሲሞስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ በሐይቅ ዳር እንዳለ ጽጌ ረዳ መዐዛው ከሚጥም #ከቅዱስ_ፊቅጦር_ከመታሰቢያው፣ #ከንጉሥ_አኖሬዎስ_መምህር_ከአባ_አውሎጊስና #ከንጉሥ_አኖሬዎስ_ረድኡ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ተጀመረ። 15-03-2016 ዓ.ም (ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ  የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን የሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ ቀሲስ ጥላሁን ደሲሳ ፣ ምክትል ሰብሳቢ ዲ.ን ስንታየሁ ምስጋናው ፣ የአንድነቱ የሥራ አመራር ኮሚቴዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ ፣ መምህር አንተነህ አወቀ የአንድነቱ ጸሐፊና ሥራ አመራሮች እንዲሁም የአጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች ሰብሳቢዎች በተገኙበት የመጀመሪያ ቀን ጉባኤ ዛሬ ኅዳር 15 ቀን በአ.አ ሀገረ ስብከት አዳራሸ ተካሂዷል። በጠቅላላ ጉባኤውም የ 6ወር የዕቅድ አፈጻጸምና አጠቃላይ የ3ዓመት የሥራ ትግበራ ሪፖርቶች ቀርበዋል። በሪፖርቱም ትኩረት ተደርጎ ሲሰራባቸው የነበሩ አምስት አብይት ጉዳዮች ፤ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በፐርሰንት፤ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ቀጣይ ሊሰራባቸው የሚገቡ የትኩረት አቅጣጫዎች ተመላክተዋል። የ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በያዝነው ዓመት የአመራር ዘመኑ በሚያበቃው ሥራ አመራር በ 3ዓመታት ውስጥ ጽሕፈት ቤት 85 በመቶ ፣ ልማት ክፍል 71 በመቶ ያሳካ ሲሆን በሪፖርቱ መሠረት የመረጃና ግንኙነት ክፍል ዝቅተኛ አፈጻጸም እንደነበረው ተገልጿል። የበጀት እጥረት መኖር ፣ በአንድነቱ ስም የተከፈተ የባንክ አካውንት አለመኖር ፣ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች ለአንድነቱ ትኩረት አለመስጠት እንደ ተግዳሮት የተነሱ ሲሆን ሥርዓተ ትምህርቱን ከዓመት ወደ ዓመት በሁሉም ሰንበት ት/ቤቶች እንዲተገበር ማስቻል በዚህም ከ57 ሰንበት ት/ቤቶች ተነስቶ በዘንድሮው ዓመት 208 ሰንበት ት/ቤቶች መተግበራቸውን፣  ከ300 በላይ ተተኪ መምህራንን ማፍራት እንዲሁም ለ600 ሰንበት ተማሪዎች በኢኮኖሚና ራስን ማስቻል ሥልጠና በመስጠት 50 ሰዎች የብድር ፍቃድና 5 ሰዎች ደግሞ ብድር ወስደው የስራ ትግበራ ላይ መግባታቸውን  እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት ሲሳተፍ ነበር የሚሉት ጉዳዮች በስፋት ተገልጸዋል። የስድስት ወር ዕቅድ ትግበራ በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዕቅድና ክትትል ኃላፊ ተስፋዓለም ከተማ የ3 ዓመታት ሥራ አፈጻጸም ትግበራ ደግሞ በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሰብሳቢ ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ ቀርቧል። ጉባኤው በነገውም ዕለት ቀጥሎ የሚውል ሲሆን  የሰንበት ት/ቤቶች ድርሻ በቤተ ክርስቲያን የውስጥ አስተዳደር ጉዳይ ላይ ይመክራል የጋራ አቋምም ይይዛል ተብሎ ይጠበቃል። (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)

✝ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፲፭ 15 ቀን። ✝ እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት የስሙ ትርጓሜ ቡሩክና የታመነ ለሆነ #ለቅዱስ_ሚናስ_ለዕረፍት_በዓል፣ #ለታላቁ_
✝ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝          ✝ #ኅዳር ፲፭ 15 ቀን። ✝ እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት የስሙ ትርጓሜ ቡሩክና የታመነ ለሆነ #ለቅዱስ_ሚናስ_ለዕረፍት_በዓል፣ #ለታላቁ_ሰማዕት_ለሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስ_ለልደት መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰ። በተጨማሪ በዚችን ቀን ከሚታሰበው፦ ከአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ አንደኛ ከእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ከቅዱስ አባት ከሁለተኛው #አባ_ሚናስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳፈን።                            ✝ ✝ ✝ ✝ #ታላቁ_ሰማዕት_ቅዱስ_ሚናስ፦ የዚህም ቅዱስ አባቱ አናቅዮስ ከሚባል አገር ነው ስሙም አውዶክስዮስ ነው እርሱም አገረ ገዥነት ተሹሞ ሳለ ወንድሙ ቀንቶበት በንጉሥ ዘንድ ነገር ሠራበት ንጉሡም ወደ አፍራቅያ አገር ሰደደውና በዚያም አገረ ገዢ አድርጎ ሾመው የአገር ሰዎችም ሁሉ ደስ አላቸው እርሱ ለሰው የሚራራ እግዚአብሔርም የሚፈራ ደግ ሰው ነውና። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

የመርሐ ግርብር ማስተካከያ!!! ኅዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ የጸሎትና የምሕላ አዋጅ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ በመግለጫው፡- ታቦታት ይወጣሉ ተብሎ የነበረ መሆኑ ይታሳል፡፡ ይህ
የመርሐ ግርብር ማስተካከያ!!! ኅዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ የጸሎትና የምሕላ አዋጅ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ በመግለጫው፡- ታቦታት ይወጣሉ ተብሎ የነበረ መሆኑ ይታሳል፡፡ ይህንንም በተመለከተ ኅዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ባስተላለፉት መልእክትም ከኅዳር 15 እስከ 21 ቀን ባለው የጸሎት መርሐ ግብር ታቦት ሳይወጣ ልብሰ ተክህኖ በመልበስ ብቻ ቅዳሜ እና እሁድ ከቅዳሴው በኋላ በአውደ ምሕረት ምህላ ተደርጎ ሰርሖተ ህዝብ ይሆናል ትምህርት አይሰጥም። በማታው መርሐ ግብር 11 ሰዓት ላይ ልብሰ ተክህኖ በመልበስ ጸሎትና ምሕላ ብቻ ተደርጎ ስንብት ይደረጋል፡፡ ትምህርት አይሰጥም፡፡ ከኅዳር 22 ጀምሮ እስከ ታኅሳስ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጸሎትና ምሕላው ከትምህርተ ወንጌል ጋር ይቀጥላል፡፡ እንደየሁኔታው ከቅዱስ ሲኖዶስና ከመንረ ፓትርያክ በየውቅቱ ማሳሰቢያ ይሰጣል ሲሉ ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ገልጸዋል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት

     🕊🕊🕊  ጾመ ነቢያት   🕊 🕊🕊    🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟 የጾመ ነብያት ምስጢር ምንድነው ? ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨      ጾመ ነቢያት [ የገና ጾም ] ከልደት አስቀድሞ የሚጾም ጾም ነው፡፡ ከህዳር ፲፭ [ 15 ] ጀምሮ ለ ፵፫ [43] ቀናት የሚጾም ሲሆን ፋሲካው [ ፍቺው ] በልደት በዓል ነው፡፡ ይህም ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳንና ምዕመናን ጾመውታል፡፡ ጾመ ነብያት ስያሜውን ያገኘው ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት ነው፡፡ በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምስጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ ፣ የረቀቀው ገዝፎ ጎልቶ እየተመለከቱ ትንቢት ተናገሩ ፤ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ጾሙ ጸለዩ፡፡ ነቢያት ከእመቤታችን ስለ መወለዱ ፥ ወደ ግብፅ ስለ መሰደዱ ፥ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ ፥ ብርሃን በሆነው ትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ ፥ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ ፥ ስለ ትንሣኤው ፥ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፡፡ ለአዳም የተሠጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ፡፡ በየዘመናቸው ፦ "አንሥእ ኃይልከ ፣ ፈኑ እዴከ" እያሉ ጮኹ፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም እግዚአብሔር ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት ፣ በሳምንታት ፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ኤርምያስ ስለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ በ፬፵፮ ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡ ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር ፦ "አያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር" ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩ እነ ነቢዩ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም፡፡ [ኢሳ.፶፰፥፩]፡፡ በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለተፈጸመበት ይህ ጾም "የነቢያት ጾም" ይባላል፡፡ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ስለሆነም "ጾመ ስብከት" ይባላል፡፡ ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፦ † ፩. [    ጾመ አዳም   ] ፦ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገነት ከተባረረ በኋላ በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ ፤ አለቀሰ [እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ] ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ "ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ፣ በደጅህ ድኼ ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡" የሚል ነው፡፡ [ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ] ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት "ጾመ አዳም" ይባላል፡፡ † ፪. [   ጾመ ነቢያት   ] ፦ ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው ፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች : ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም : ቅዱስ ሙሴ : ቅዱስ ኤልያስ ፣ ቅዱስ ዳንኤልና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: [ዘዳ.፱፥፲፱ ፣ ነገ.፲፱፥፰ ፣ ዳን.፱፥፫ መዝ.፷፰፥፲ ፻፰፥፳፬] ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል:: † ፫.  [   ጾመ ሐዋርያት  ] ፦ ሐዋርያት "ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን ፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?" ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡ † ፬.  [   ጾመ ማርያም   ] ፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና "ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?" ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና "ጾመ ማርያም" ይባላል፡፡ † ፭.  [   ጾመ ፊልጶስ   ] ፦ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት ፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡ † ፮.  [   ጾመ ስብከት  ] ፦ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት ፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡ † ፯.  [   ጾመ ልደት   ] ፦ የጾሙ መጨረሻ [ መፍቻ ] በዓለ ልደት ስለሆነ "ጾመ ልደት" ይባላል፡፡ በጾማችን በጸሎታችን - ስለ ቤተክርስቲያን ፥ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝብ በማሰብ በእንባ እራሳችንን ዝቅ በማድረግ እንጾም ዘንድ ይገባል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡ ወለወላዲቱ ድንግል ፡ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡   🌟🌟🌟🌟🌟 ፍኖተ ብርሃን 🌟🌟🌟🌟

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨የኃያሉ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በግራር ደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ።✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ኅዳር 12 ቀን 2016 ዓ
+9
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨የኃያሉ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በግራር ደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ።✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ኅዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም ✝በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ዘንድ ኅዳር ፲፪ ቀን መልአኩ እስራኤላውያንን እየተራዳ ከግብፅ እንዲወጡ ያደረገበትን ተራድኢነትን በማሰብ  በመልአኩ መታሠቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተከብሮ ይውላል። ✝በዚሁ መሠረት በዓሉ በዚሁ ዕለት በ2016 ዓ.ም በግራር ደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውተ ቤተ ክርስቲያን እና በርካታ ምእመናን በተገኙበት ተከብሯል። በበዓሉ ላይ የደብሩ ሊቃውንተ እና የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች  ያሬዳዊ ዜማ አቅርበዋል። ከፍኖተ ብርሃን ማሕደር በጥቂቱ                 🔹〰️🔹〰️🔹〰️ ✨✨✨ፍኖተ ብርሃን ✨✨✨

✝ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፲፬ (14) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ኤርትራ አገር ውስጥ በሚገኘው #ታላቁ_ገዳም_ደብረ_ቢዘን_ከአቡነ_ፊሊ
✝ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝            ✝ #ኅዳር ፲፬ (14) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ኤርትራ አገር ውስጥ በሚገኘው #ታላቁ_ገዳም_ደብረ_ቢዘን_ከአቡነ_ፊሊጶስ በኋላ አበምኔት ለነበሩት ልክ እንደ #ነቢዩ_ኤልያስ ዝናብ እንዳዘንብ #ሦስት_ዓመት_ሰማይን_ለለጎሙት ለታላቁ አባት ለሃይማኖት መምህር #ለአቡነ_ዮሐንስ_ለዕረፍት በዓል መታሰቢያና #ለአቡነ_ቀሌምንጦንስ_ዘሽሬ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                              ✝ ✝ ✝ ✝ #አቡነ_ዮሐንስ_ዘአስገዶ፦ እኚህ ጻድቅ ትውልድ አገራቸው ትግራይ አድዋ ነው። የመነኰሱት በአቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ቢዘን እጅ ነው። ደቀ መዝሙራቸውም ሆነው በጸሎት አብረው ኖረዋል። ወደ ደብርነት የተለወጠው ገዳማቸውም ከደብረ ቢዘን አጠገብ ይገኛል። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨