ru
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Открыть в Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Больше
607
Подписчики
-124 часа
-47 дней
-1230 дней
Архив постов
                           ✝️ ✝️ ✝️ 🌼 #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ብፁዓን እለ ተኀድገሎሙ ኃጢአቶሙ። ወእለ ኢሐሰበ ሎሙ ኵሎ ጌጋዮሙ። ብፁዕ ብእሲ ዘኢኈለቈ ሎቱ እግዚአብሔር ኃጢአቶ"። መዝ 31፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 1ቆሮ 7፥12-18፣ ያዕ 5፥14-17 እና የሐዋ ሥራ 19፥17-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 11፥5-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

🌼 "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼           🌼 መስከረም ፲፫ (13) ቀን። 🌼 እንኳን #ለታላቁና_ቅዱስ የሆነ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ባስልዮስ አንድ ጎልማሳ አገርልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት እርሷንም ከመውደዱ የተነሣ እርሷን ለማግባት ብሎ ወደ አንድ ከሀዲ ሥራየኛ ሔዶ እግዚአብሔር ክዶ በሰይጣን አምኖ በእጁ ፈርሞ ለሰይጣን ሰጠው ይህንን የጽሕፈት ደብዳቤ በእግዚአብሔር ኃይልና በጸሎቱ #ቅዱስ_ባስልዮስ በመደምሰስ ድንቅ ተአምር ላደረገበት ለመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከከበረ ከባሕታዊ #ከአባ_ይስሐቅ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                         ✝️ ✝️ ✝️ 🌼 #የቂሣርያ_ሊቀ_ጳጳሳት_ቅዱስ_ባስልዮስ ያደረገው ተአምር፦ ይህም እንዲህ ነው አንድ ጐልማሳ አገልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት ልቡ እርሷን ወዶ እንደ እሳት እስከ ነደደ ድረስ እርሷንም ከመውደዱ ብዛት የተነሣ ወደ አንድ ከሀዲ ሥራየኛ ሔደ። ሥራየኛውም የክህደት ደብዳቤ ጽፎ ሰጠው። ወደ አረሚ መቃብርም ሒዶ በመንፈቀ ሌሊት ደብዳቤዋን ይዞ ወደላይ እጁን አንሥቶ በዚያ እንዲቆም አዘዘው። 🌼 ይህም አገልጋይ ይህን ነገር ተቀብሎ ያ መሠርይ እንዳዘዘው አደረገ። በዚያንም ጊዜ ከሰይጣናት አንዱ መጥቶ ወደ አለቃቸው ወስዶ አደረሰው ያቺንም የክህደት ደብዳቤ ከእጁ ወሰደ። እንዲህም ብሎ ጠየቀው "ንጉሥህ ክርስቶስን ትክደዋለህን? ፈቃድህን ከፈጸምኩልህ በኋላ ወደእርሱ አትመለስምን?" ይህም ጐስቋላ ባሪያ "አዎን ጌታዬ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለው። መስሐቲ ዲያብሎስም "ይህን ልታደርግ በእጅህ ደብዳቤ ጻፍልኝ" አለው። እርሱም በከበረ ደሙ የዋጀውን የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክዶ በደብዳቤ ውስጥ የክህደቱን ቃል ጻፈለት። 🌼 በዚያንም ጊዜ ሰይጣን በጌታው ልጅ ልብ ውስጥ የፍትወት እሳትን አነደደ ይህንንም ባሪያ እጅግ ወደደችው ከእርሱም መታገሥ አልተቻላትም። ወደ አባቷ በመጮህ በግልጥ "ከዕገሌ ባሪያህ ጋር ካላጋባኸኝ አለዚያ ራሴን እገድላለሁ" ትለዋለች እንጂ መታገሥ አልተቻላትም። አባትና እናቷም ፈጽሞ አዘኑ በምንም በምን ሊያስታግሥዋት አልቻሉም። የዚያም አገልጋይ ፍቅሩ በየዕለቱ በልቧ ይጨመር ነበር እንጂ። ስለዚህም ራሷን እንዳትገድል አባቷ ፈራ ለዚያ ባሪያ ሰጠው። እርሱም የጌታውን ልጅ ተቀብሎ ወደቤቱ አስገባት። ከርሷ ጋር ያለውን ፍላጎቱንም ፈጸመ። ከእርሱም ጋር ረጅም ጊዜ ከኖረች በኋላ አባትና እናቷም ይቅር ብሎ ኀዘናቸውን ከላያቸው ያርቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ኀዘንንና ልቅሶን አብዝተው ነበር። 🌼 ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ጩኸታቸውን ሰማ ልመናቸውንም ተቀብሎ ይህ የወደደችው አገልጋይ ጐልማሳ ክርስቲያን እንዳልሆነ አስገነዘባት ከእርሷ ጋር በነበረበት በዚህ በረጅም ዘመን አንዲት ቀን እንኳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሔድ ሥጋውንና ደሙንም ሲቀበል ወይም አዳኝ በሆነ በመስቀል ምልክት ራሱን ሲአማትብ እርሷ አላየችውም። 🌼 ስለእምነቱም ጠየቀችው ግን አልገለጠላትም እርሷም እንዲህ አለችው "አንተ ክርስቲያን ከሆንክ ና በአንድነት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሒድና በፊቴ ቅዱስ ቊርባንን ተቀበል"። እንዲህም በአስገደደችው ጊዜ ስለርሷ ያደረገውን ሁሉ ወደ ሥራየኛ እንደሔደም በሰይጣንም አምኖ እምነቱንም በክርታስ ጽፎ ያንን ክርታስ ለሰይጣን እንደ ሰጠው ነገራት። 🌼 ይህንንም ነገር ከእርሱ በሰማች ጊዜ ደነገጠች መሪር ልቅሶንም አለቀሰች ራሷንም በማወዛወዝ እጅግ ተጸጽታ አዘነች። ያን ጊዜም ፈጥና ተነሣች የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ ወደሆነው ወደ ሀገርዋ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሔደች ከእግሩ በታችም ወድቃ ሰገደችለት በላይዋ የደረሰውን ሁሉ አስረዳችው ለሰው ልጆች ጠላት ከሆነ ከሠይጣን እጅ ፈጽሞ ያድናት ዘንድ ብዙ በማልቀስ ለመነችው። ቅዱስ ባስልዮስም ባሏ የሆነውን ባርያ ወደርሱ ልኮ አስመጣውና ጠየቀው እርሱም የሠራውን ሁሉ አስረዳው ቅዱስ ባስልዮስም "ተመልሰህ ክርስቲያን ልትሆን ከሰይጣንም እጅ ልትድን ትወዳለህን?" አለው ያም ባርያ "ጌታዬ ይሆንልኛልን?" አለ ይህ ቅዱስ አባትም "የፈጣሪህን ስም እየጠራህ ልብህን አጽና" አለው። 🌼 ከዚህም በኋላ ከእርሱ ዘንድ በአንድ ቦታ ዘጋበት በመስቀል ምልከትም አማተበበት እንዲጸልይም አዘዘው ራሱ ቅዱስ ባስልዮስም ስለርሱ ጸለየ። ከሦስት ቀኖች በኋላም ጎበኘው እንዲህም አለው "በእሊህ በሦስት ቀኖች የደረሰብህ ምንድን ነው" እርሱም በላዩ በመጮህ ሠይጣናት ሲያስፈራሩት ያንንም ደብዳቤ ሲአሳዩትና በእርሱ ላይ ሲቆጡ በመከራ ውስጥ እንደኖረ ነገረው ቅዱስ ባስልዮስም "ከእሳቸው ቁጣ የተነሣ አትፍራ እግዚአብሔር ይረዳሃልና አጽንቶም ይጠብቅሃል" አለው። 🌼 ከዚህም በኋላ ጥቂት እንጀራና ውኃ ሰጥቶ ወደ ቦታው መለሰው ቅዱስ ባስልዮስም ስለዚያ አገልጋይ ሒዶ ይጸልይ ጀመረ። ዳግመኛም ከሦስት ቀኖች በኋላ ጐበኘውና በእርሱ ላይ ምን እንደ ደረሰበት ጠየቀው ያ አገልጋይም "ጩኸታቸውን እሰማለሁ ግን አላያቸውም" ብሎ መለሰለት። እንጀራና ውኃም ሰጠውና መከረው ወደ ቦታውም መለሰውና ስለርሱ ሊጸልይ ቅዱስ ባስልዮስ ሔደ። እስከ አርባ ቀኖች ፍጻሜ ድረስ እንዲህ አደረገ። በአርባውም ቀን ፍጻሜ ከእርሱ ስለ ሆነው ጠየቀው ያ አገልጋይም እንዲህ አለው "ቅዱስ አባቴ ሆይ ስለ እኔ ሰይጣንን ስትጣላውና ድል አድርገህ ጥለህ ስትረግጠው በዛሬዋ ሌሊት አየሁ" አለው። 🌼 ቅዱስ ባስልዮስም ይህን ነገር ከእርሱ በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው የገዳማቱን መነኰሳትና ካህናቱንም ጠርቶ ስለዚያ ሰው ያቺን ሌሊት መላዋን እንዲጸልዩባት አዘዛቸ። በነጋ ጊዜም ያንን አገልጋይ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲአመጡት የዚያችንም አገር ሕዝብ ሁሉንም ሰብስቦ እጆቻቸውን ወደ ሰማይ አንሥተው "አቤቱ ክርስቶስ ማረን ይቅር በለን" እያሉ ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ እንዲማልዱ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም አደረጉ። 🌼 እንዲህም እያሉ ሲማልዱ ያ ሰው ጽፎ ለሰይጣን የሰጠው የክህደት ደብዳቤ ከሰይጣን እጅ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ወደቀ ሁሉም ደስ ብሏቸው ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት የከበረ አባት ባስልዮስም ባረካቸው ሥጋውንና ደሙንም አቀብሎ ወደ ቤቶቻቸው በሰላም በፍቅር አሰናበታቸው። እነርሱም ስለ ኃጢአታቸው ስርየትና ስለ ድኅነታቸው ፈጽሞ ደስ እያላቸው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይህንን ቅዱስ አባት ባስልዮስን እያከበሩ ወደ ቤታቸው ገቡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ባስልዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 13 ስንክሳር።                            ✝️ ✝️ ✝️ 🌼 "#በዛቲ_ዕለት_እግዚአብሔር_ገብረ። በእደ #ባስልዮስ_መንክረ። በአፍቅሮ ወለት አሐቲ ኀበ መሠርይ ዘሖረ። እንዘ ይከሥት በቅድመ መጽሐፈ ክህደቱ ስውረ። እምእደ ሰይጣን አንገፈ ወፄወወ ገብረ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_13።

🌼 "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼 🌼 እንኳን #ለዚህ_ዓመት_ሁለተኛ_ሳምንት #ዘመነ_ፍሬ_ለሚታሰቡበት_ዕለተ_እሑድ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                           ✝ ✝ ✝ 🌼 #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ "#እኩት_አንተ_ወስቡሕ_ስምከ ወዐቢይ ኃይልከ ዘተአርፍ በአርያም ወትሴባሕ በትሑታን ዘአንተ #ሠራእከ_ሰንበተ_ለዕረፍት ወወሀብከ ሲሳየ ዘበጽድቅ ለኵሉ እግዚኦ #ባርክ_ፍሬሃ_ለምድር መሓሪ ወጻድቅ መኑ ከማከ ዘታርኁ ክረምተ በጸጋከ ለነፍስ ድኅንት ወነፍስ ርኅብት እንተ ጸግበት ተአኵተከ። ትርጉም፦ #አንተ_ምስጉን_ነህ፤ #ስምህም_የተመሰገነ_ነው፤ ኃይልህም ታላቅ ነው፤ በአርያም የምትኖር በትሑታን የምትመሰገን አንተ ነህ፤ #ሰንበትን_ለዕረፍት_የሠራህ ለሁሉም በእውነት ምግብን የምትሰጠው አቤቱ #የምድርን_ፍሬ_ባርክ፤ ጻድቅና መሓሪ አምላክ ሆይ እንደ አንተ ያለ ማነው! #ክረምትን_በጸጋህ_ታፈራርቃለህ፤ የዳነች ነፍስ የተራበች በልታም የጠገበች ነፍስ ታመሰግንሃለች። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።                         ✝ ✝ ✝                        🌼 #ዘመነ_ፍሬ 🌼 #ከመስከረም 9 (ዘጠኝ) ጀምሮ እስከ #መስከረም_15 ድረስ "ዘመነ ፍሬ" በመባል ይታወቃል፤ይህም ሰምና ወርቅ ምሥጢር ያለው ሥያሜ ነው። 🌼 #ሰም:— ገበሬው በግንቦትና በሰኔ የዘራውን እህል ፍሬ የሚያይበት እግዚአብሔርን የሚያመሰግንበት፤ ምድርም በጠጣችው ዝናም ለተዘራባት ዘር በፍሬዋ መልስ የምትሰጥበት ወቅት ነው። "ምድርኒ ትሁብ ፍሬሃ" እንዲል ምድርም ፍሬዋን ትሰጣለች፤ መዝ 66÷7። 🌼 #ወርቅ:— ከሰኔ 26 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ድረስ ያለውን ወቅት መዋዕለ ዘርእ ብለን እየተማርን ነበር፣ በወቅቱም ጌታ በዘርእ ያስተማረውን ትምህርት "ዘርእሰ ዘውእቱ ቃለ እግዚአብሔር" (ዘሩም የእግዚአብሔር ቃል ነው፣ ማቴ 13÷19) በማለት የተረጎመውን ስንማር ቆይተናል። 🌼 በዚህ ወቅት ደግሞ ያኔ የተማርነው የእግዚአብሔር ቃል በእኛ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ምን ያህል ፍሬ ሰጠ? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የምንገመገምበት ነው። 🌼 ምድሪቱ በሥርዓተ ተፈጥሮ መሠረት ገበሬውን አላሳፈረችውም የተዘራባትን አብዝታ አስረክባለች ፣ ምድር የተባለ የእኛ ልቡና የተዘራበትን የሕይወት ቃል የት አደረሰው? በመንገድ፣ በጭንጫ ፣ በእሾኻማና በመልካም መሬት እየተመሰለ ተምረን ነበር፤ የእኛ ልቡና የትኛውን መሬት ይወክላል? እነዚህን ጥያቄዎች እንመልስ ዘንድ አባቶቻችን ሊቃውንት ይህን ሥያሜ አስቀምጠውልናል። 🌼 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ምድር ለእመ ሰትየት ዝናመ ዘይወርድ ላዕሌሃ ትወልድ ሣዕረ" (ምድር የሚወርድላትን ዝናም ስትጠጣ ሣርን ትወልዳለች) (ዕብ 6 ÷7 )በማለት እንደነገረን መሬት በዚህ ወቅት በልምላሜ፤ በአበባና በፍሬ አጊጣ ተውባ የምትታይበት ወቅት ነው፣ ♠የተዘራባትን ባታበቅል ግን "ዘቅርብት ለመርገም ወደኃሪታ ለአንድዶ" (ለመረገም የቀረበች ናት፤ መጨረሻዋም መንደድ መቃጠል ነው።) በማለት ጠንከር አድርጎ አስተምሮናል። 🌼 ሰውም የተዘራበትን ቃለ ሕይወት ካልሠራበትና ካልተጠቀመበት እንዲሁ ይሆናል፣ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ "ግበሩኬ ፍሬ ዘይደልወክሙ ለንስሐ" ካለ በኋላ "ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ይቆረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል" ማቴ 3÷8-10 በማለት በዛፍ አንፃር የእኛን ሕይወት አስተምሮናል፤ ጌታም ይህንኑ ቃል በቃል የተናገረው ሲሆን አምኖ ተጠምቆ ፤ተምሮ ክርስቲያናዊ ሥራ የማይሠራ ፣ በሠራው ክፋትና ተንኰል የማይፀፀት ሁሉ ከግንዱ የተለየ ቅርንጫፍ እንደሚሆን አስረግጦ ነግሮናል ዮሐ 15÷6። 🌼 በዚህም መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ "ወኲሉ ዘተጽሕፈ ለተግሣጸ ዚአነ ተጽሕፈ ከመ በትዕግሥትነ ወበተወክሎ መጻሕፍት ንርከብ ተስፋነ "( መጻሕፍትን በማመን ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን እናገኝ ዘንድ የተጻፈው ሁሉ እኛ እንድንገሠጽበት ተጻፈ።") ሮሜ 15÷4 በማለት እንዳስተማረን የተማርነውን፤ የሰማነውን ያየነውን፤ያነበብነውንና የተረዳነውን የሕይወት ቃል ተግባራዊ እንድናደርግ የምንነሳሳበት ወቅት መሆኑን ልብ ይሏል!!! 🌼 ይህንን ቃል ስናስብና ስንረዳ ከእንስሳዊ ጠባይ ወጥተን ሰው ወደ መሆን እንሸጋገራለን፤ የፍቅርንና የአብሮነትን ትርጒም ወደ መረዳት እንመጣለን። እግዚአብሔርም የሰውነትን ፍሬ ሊለቅም ሲመጣ ከመረገም እንድናለን ማቴ 21÷18። አምላካችን እግዚአብሔር ሁላችንም ለልምላሜ ንስሐ  ለፍሬ ቊርባን እንድንበቃ ይርዳን!!! አሜን። ምንጭ፦ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው ዘመካኒሳ ሚካኤል።                             ✝ ✝ ✝ 🌼 #የዚህ_ሳምንት_የዕለቱ_ምስባክ፦ "ምድርኒ ወሀበት (ትሁብ) ፍሬሃ። ወይባርከነ እግዚአብሔር አምላክነ። ወይባርከነ እግዚአብሔር። መዝ 66፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ ፱፥1-ፍ.ም፣ ያዕ ፭፥1-10፣ የሐዋ ሥራ 19፥21። የሚነበበው ወንጌል ማር 4፥24-39። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ወይም የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ሚካኤል ወራዊ በዓልና የኤፌሶን ጉባኤ የተሰበሰቡ የ200 ኤጲስቆጶሳት በዓልና ዕለተ ሰንበት ለሁላችንም ይሁንልን።

🌼 ከዚህም በኋላ መጽሩስ መኰንን ከአማካሪዎቹ ጋር ተማከረ እንዲህም አላቸው "ስሙ ፋሲለደስ ስለሚባል ስለዚህ ሰው ምን ላድርግ እርሱን ያላሠቃየሁበት የሥቃይ መሣሪያ ምንም የቀረ የለም ከሐሳቡም አልተመለሰም" እነርሱም እንዲህ ብለው መከሩት "ራሱን በሰይፍ ቆርጠህ ከእርሱ ተገላገል እነሆ የዚች አገር ሰዎች በእርሱ ምክንያት አልቀዋልና"። 🌼 በዚያንም ጊዜ የቅዱስ ፋሲለደስን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘና ቆረጡት የድል አክሊልን ተቀበለ ንቆ ሰለ ተዋት ምድራዊት መንግሥት ፈንታም ሰማያዊት መንግሥት አገኘ። ከሥጋውም ድንቆች የሆኑ ታላላቅ ተአምራት ተገለጡ ከእርሱም ጋር ሰማዕት ሁነው የሞቱ ሁሉም ቊጥራቸው ሃያ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ሦስት ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ ፋሲለደስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                              ✝ ✝ ✝ 🌼 #ቅዱስ_ቆርኔሌዎስ፦ ይህም ቅዱስ የጭፍራ አለቃ የሆነ ትሩፋቱና ገድሉም ያማረ ጻድቅ፤ በቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ዘመን እግዚብሔርን ያገለገለ ነው። 🌼 የእግዚአብሔር መልአክም ተገልጦለት ሐዋርያ ጴጥሮስን ይጠሩት ዘንድ ሰዎችን እንዲልክ ጴጥሮስም ወደርሱ እንዲመጣ ሊሠራው የሚገባውን ከእርሱ ከጴጥሮስ እንዲሰማ አዘዘው። 🌼 ጴጥሮስም ወደርሱ በደረሰ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል አስተማረው ለርሱና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ ከሁሉ ቤተሰቡ ጋር አምኖ ተጠመቀ። ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ ለእስክንድርያ አገር ቅስና ሾመው ወደርሷ በደረሰ ጊዜ የጣዖታትን አምልኮ ተመልታ አገኛትና አስተማራቸው ብዙዎችንም ወደቀናች ሃይማኖት መልሶ አጠመቃቸው መኰንኑ ድሜጥሮስም አምኖ ከወገኖቹ ጋር በእርሱ እጅ ተጠመቀ። 🌼 የኑሮውን ዘመንና ሐዋርያዊ ተጋድሎውን አድርሶ በሰላም አረፈ እርሱም ከአሕዛብ አስቀድሞ ያመነ የመጀመሪያ አማኒ ነው።                              ✝ ✝ ✝ 🌼 #ቅድስት_ታዖድራ፦ ይችንም ቅድስት ሌላ ሰው አስገድዶ ከባሏ ወስዶ ከባሏ ጋር ያላትን አንድነት አበላሸ ያን ጊዜም ታላቅ ኀዘን በማዘን ተጸጸተች መሪር ልቅሶንም አለቀሰች የወንዶችንም ልብስ ለብሳ ወንድ መሰላ ከእስክንድርያ በሥውር ወጣች ስሟንም ቴዎድሮስ ብላ ሰየመችና ወደ ወንዶች ገዳም ገባች የምንኲስና ልብስንና የመላእክትን አስኬማ ለበሰች። የሚያዩዋት ሁሉ እርሷ እንደ ጃንደረባ የሆነች ወንድ ትመስላቸው ነበር እርሷ ግን በረኃብ፣ በጽምዕ ሌሊት በመትጋት ቀን በመቆም ጸንታ በመጋደል ላይ ታገሠች እንዲህም በመጋደል ተጠምዳ ብዙ ዘመን ኖረች። 🌼 በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ አንድ ሰው ከአንዲት ብላቴና ጋር አመነዘረ እርሷም ፀንሳ ወንድ ልጅን ወለደች ወላጆቿም "ድንግልናሽን ያጠፋው ማነው" ብለው ጠየቋት እርሷም "በገዳም ውስጥ የሚኖር አባ ቴዎድሮስ እርሱ ደፍሮኝ ከእርሱ ፀነስኩ" ብላ በዚች ቅድስት ታኦድራ ላይ በሐሰት ተናገረች። 🌼 ወላጆቿም በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ ሕፃኑንም ወደዚያ ገዳም አበ ምኔት ወሰዱት እንዲህም አሉት "ይህ ሕፃን የልጅህ የመነኵሴው የቴዎድሮስ ልጅ ነው"። ያን ጊዜም አበ ምኔቱ ይቺን ቅድስት ታኦድራን ጠራትና እንዲህ አላት "ይህን ክፉ ሥራ ለምን ሠራህ በመነኰሳቱም ሁሉ ላይ ኀፍረትንና ጒስቁልናን አመጣህ" እርሷ ሴት መሆኗን አላወቀምና እርሷም አባቴ ሆይ "በድያለሁና ይቅር በለኝ" አለችው። 🌼 አበ ምኔቱም ተቆጥቶ ከገዳሙ አስወጥቶ አባረራት በበረሀ ውስጥ ሰባት ዓመት ኖረች ያም ሕፃን ከእርሷ ጋር ሁኖ ከሰይጣናት በሚመጡባት በብዙ መከራዎች ብዙ መከራዎች ላይ ታገሠች ብዙ ሥቃያትንም ፈጽሞ አሠቃዩዋት። 🌼 ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ተቀብለው ወደ ገዳም አስገቡአት ጥቂት ቀንም ኖረች መልካም ተጋድሎዋንም ፈጽማ በሰላም አረፈች ነፍሷንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጥታ የዘላለም ሕይወትን አገኘች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ታኦድራ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ 🌼 #ሰማዕቷ_ቅድስት_በነፍዝዝ፦ የስሟ ትርጓሜ ጣፋጭ የሆነ ማለት ነው።  ይቺም ቅድስት በእድሜዋ ፈጽማ የሸመገለች ነበረች በፋርስ ንጉሥ በሳቦር ዘመንም መከራ ተቀበለች ከዘጠኝ መቶ ክርስቲያን ጋር ማርከው ወስደው አሠሩዋት የሠራዊቱም አለቃ ታላቅ ሥቃይን አሠቃይቶ ከዚያ በኋላ ራሷን በሰይፍ ቆረጠ። 🌼 ራሷንም ከአስቆረጣት በኋላ ከአንገቷ የፈሰሰው ደም እስከ ራቀ ድረስ ወደ ላይ ወጣ ከዚያ የተቀመጡ ጠላቶችም ኃይላቸው ደከመ። የፀሐይ ብርሃንም ጨለመ በዚያም ቦታ ደግሞ ጣፋጭ የሆነ መዐዛ ተመላ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት በነፍዝዝ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                               ✝ ✝ ✝ 🌼#የእስና_አገር_ሰዎች_ሦስቱ_ቅዱሳን_ሰማዕታት #ገበሬዎች_ሱርስ_አጤኬዎስ_መስተሐድራ፦ አርያኖስም ከሀገሪቱ በስተደቡብ ምንም ሳያስቀር ወታደሮቹ እስከ ደከሙ ድረስ ሰይፋቸውንም ወደ አፎቱ መልሰው ነበር የአገር ሰዎችን ጨርሶ ገድሎ ሲመለስ እሊህ ሦስቱ ገበሬዎች ከዱር ሲመለሱ በከተማ መካከል በተገናኙት ጊዜ "እኛ ክርስቲያኖች ነን" ብለው በግልጥ ጮኹ አርያኖስም ሰምቶ ወታደሮቹን "እሊህን ገበሬዎች ትገድሏቸው ዘንድ ይገባል" አላቸው። 🌼 ወታደሮቹም "እኛ ደክመናል ሰይፎቻችንንም ወደ አፎታቸው አስገብተናል" አሉት እሊህ ቅዱሳንም ሰምተው "እነሆ መቆፈሪያዎች ከእኛ ጋራ አሉ" በእነርሱ ግደሉን አሉ ከዚያም አንገታቸውን በደንጊያ ላይ አድርገውላቸው ቆረጡአቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 11 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ 🌼 "#ሰላም_ለፋሲለደስ_እምነ ክሣዱ ዘአንጠብጠበ። ደመ ቀይሐ ወጸዓድዒደ ሐሊበ። ምስለ አዝማዲሁ ወሰብኡ እስመ ለሞት ተውህበ። በከመ ኮኖሙ ዲበ ምድር አበ። ዘበሰማያት ተሠይመ አቡሆሙ ካዕበ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 11።                              ✝ ✝ ✝ 🌼 #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ተንሥኡ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ። ወዘኢየአመር ነበቡ ላዕሌየ። ፈደዩኒ እኪት ህየንተ ሠናይት"። መዝ 34፥3-4። የሚነበበው ወንጌል 16፥24-ፍ.ም።                             ✝ ✝ ✝ 🌼 #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ፡ለአግብርቲከ፡ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥1-12፣ ያዕ 3፥1-13፣ የሐዋ ሥራ 10፥1-9። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥12-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ፋሲለደስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

🌼 "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼            🌼 #መስከረም ፲፩ (11) ቀን። 🌼 እንኳን #ለአንጾኪያ_ነገሥታት_አባታቸው፤ መካሪያቸው ለሆነ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ለነበረው፤ ጌታችን ከሞት እያስነሣው በጽኑ ሥቃይና ተጋድሎ ሲጋደል ለኖረው ለታላቁ ሰማዕት #ለቅዱስ_ፋሲለደስ፣ #በቅዱሳን_አባቶቻችን_ሐዋርያት ዘመን እግዚአብሔርን ያገለገለ #የጭፍራ_አለቃ (፻አለቃ) ለሆነ ትሩፋቱና ገድሉም ላማረ ለጻድቁ ሰው #ለቅዱስ_ቆርኔሌዎስ ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለእስክድርያ አገር በንጉሥ ዘይኑን ዘመን ለነበረች #ለቅድስት ታዖድራ ለዕረፍቷ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ሰላም አደረሰን፡፡ በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ የስሟ ትርጓሜ ጣፋጭ ከሆነ ከከበረች #ከሰማዕቷ_ከቅድስት_በነፍዝዝ ከዕረፍት በዓል፣ #ስማቸው_ሱርስ_አጤኬዎስና_መስተሐድራ ከሚባሉ ሦስት ገበሬዎች ከእስና አገር ሰዎች በሰማዕትነት ከዐረፉ፣ #ከቅዱሳን_ከባስልዮስ ሰማዕትና #ከኢየሩሳሌም_ኤጲስቆጶስ_ከቴዎድሮስ ከሰማዕት አለቃ #ከቀውስጦስም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                       ✝ ✝ ✝ 🌼 #ለአንጾኪያ_ነገሥታት_አባታቸውና_መካሪያቸው የሆነው #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ፋሲለደስ፦ እርሱም ለሮም ንጉሥ የሠራዊት አለቃ ነው መንግሥቱም ሁለመናዋ በእርሱ ምክር የጸናች ናት። ብዙዎችም ወንዶችና ሴቶች የቤት ውልዶች አገልጋዮች አሉት። 🌼 ዝምድናውም እንዲህ ነው ስሙ ኑማርያኖስ የተባለ የሮም ንጉሥ ለቴዎድሮስ በናድሌዎስ እናቱ የሆነች የቅዱስ ፋሲለደስን እኅት አግብቶ ዮስጦስን፣ ገላውዴዎስን፣ አባዲርን ወለደችለት እሊህም ለቅዱስ ፋሲለደስ የእኅቱ ልጆች ናቸው። የቅዱስ ፋሲለደስም ሚስት ለቅዱስ ፊቅጦር እናት እኅት ናት ከእርሷም ስማቸው አውሳብዮስና መቃርስ የተባሉ ሁለት ልጆችን ወለደ። 🌼 በዚያም ወራት የቊዝና የፋርስ ሰዎች የሮምን ሰዎች ሊወጓቸው በላያቸው ተነሡ ያን ጊዜ የንጉሥ ልጅ ዮስጦስን የፋሲለደስ ልጅ አውሳብዮስን ከጦር ሠራዊቶቻቸው ጋር ለውጊያ ላኳቸው። ንጉሡ ኑማርዮስም ሌሎች ጠላቶች በተነሡበት በኩል ለጦርነት ሒዶ በውጊያው ውስጥ ሞተ የሮም መንግሥትም የሚጠብቃትና የሚመራት የሌላት ሆነች። 🌼 እንዲህም ሆነ በዚያ ወራት ስለ ጦርነት ለመደራጀት የሮም ሰዎች ከሀገሩ ሁሉ አርበኞች የሆኑ ሰዎችን ሰበሰቡ ከውስጣቸውም ከላይኛው ግብጽ ስሙ አግሪጳዳ የሚባል የፍየሎች እረኛ የሆነ አንድ ሰው አለ። እርሱንም መኳንንቱ ወስደው በመንግሥት ፈረሶች ላይ ባልደራስ አድርገው ሾሙት እርሱም በጠባዩና በሥራው ሁሉ ኃይለኛና ብርቱ ነበር። 🌼 ከንጉሥ ኑማርያኖስ ሴቶች ልጆች አንዲቱ ወደርሱ በመስኮት ተመለከተች ወደደችውም መልምላም ወስዳ አገባችው ስሙንም ዲዮቅልጥያኖስ ብላ ሰይማ አነገሠችው። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ሰማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔርን ትቶ ጣዖታትን አመለከ ቅዱስ ፋሲለደስም ሰምቶ እጅግ አዘነ የመንግሥትንም አገልግሎት ተወ። 🌼 ከዚህም በኋላ የንጉሥ ኑማርያኖስ ልጅ ዮስጦስና የፋሲለደስ ልጅ አውሳብዮስ ጠላቶቻቸውን ድል አድርገው የጠላቶቻቸውንም አገሮች አጥፍተው ደስ ብሏቸው ተመለሱ። ነገር ግን የነገሠው ዲዮቅልጥያኖስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክዶ አምልኮ ጣዖትን አቁሞ አገኙት እጅግም አዘኑ ተቆጥተውም ተነሡ ሰይፎቻቸውን መዝዘው ዲዮቅልጥያኖስን ገድለው የንጉሥ ኑማርያኖስን ልጅ ዮስጦስን ሊያነግሡ ወደዱ ፋሲለደስም ከዚህ ሥራ ከለከላቸው። 🌼 ከዚህም በኋላ ቅዱስ ፋሲለደስ ዘመዶቹን፣ ሠራዊቱን፣ አገልጋዮቹንም ሁሉ ሰበሰባቸውና በክብር ባለቤት በክርስቶስ ስም ደሙን ሊያፈስ እንደፈለገ አስረዳቸው ሁሉም እንዲህ ብለው መለሱለት "አንተ በምትሞትበት ሞት እኛ ከአንተ ጋር እንሞታለን" በዚህም ምክር በአንድነት ተሰማሙ። 🌼 ከዚህም በኋላ በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ፊት ቁመው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ከእርሳቸውም ግርማ የተነሣ ታላቅ ፍርሃትን ፈራ እነርሱ የመንግሥት ልጆች ናቸውና። 🌼 የቅዱስ ፊቅጦር አባት ኅርማኖስም ወደ ግብጽ አገር ይልካቸው ዘንድ በዚያም እንዲያሠቃዩዋቸው መከረው ሁሉንም እየአንዳንዳቸውን ለብቻቸው አድርጎ ላካቸው አባዲርንና እኀቱ ኢራኒን ወደ አንዲት አገር፣ አውሳብዮስንና ወንድሙ መቃርስን ወደሌላ ቦታ፣ ገላውዴዎስንም እንዲሁ አደረጉ። በናድሌዎስ ቴዎድሮስም እሼ በሚባል ዕንጨት ላይ በመቶ ሃምሳ ሦስት ችንካር ተቸንክሮ ገድሉን ፈጸመ። 🌼 ቅዱስ ፋሲለደስን ግን አምስት ከተማዎች ወዳሉበት ወደ አፍሪካ ምድር ወደ መኰንኑ ወደ መጽሩስ ላከው መጽሩስም በአየው ጊዜ መንግሥቱን ክብሩን ስለ ተወ እጅግ አደነቀ። ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስም መልአኩን ልኮ በመንፈስ ወደ ሰማይ አውጥቶ በብርሃን ያጌጠ መንፈሳዊ ማደሪያን አሳየው ነፍሱም እጅግ ደስ አላት ከዚህም በኋላ ወደነበረበት መለሰው። ባሮቹን ግን ነፃ ያወጣቸው አሉ የቀሩትም ከእርሱ ጋር የሰማዕትነት አክሊልን የተቀበሉ ሰባት ሺህ ሠላሳ ሦስት የሚሆኑ አሉ። 🌼 ቅዱስ ፋሲለደስንም ታላቅ ስቃይን አሰቃዩት በመንኰራኲርና በተሣሉ የብረት ዘንጎች ሥጋውን ሰነጣጥቀውት ሞተ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለ ጥፋት ከሞት አድኖ አስነሣው አሕዛብም ሁሉ ይህን ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አመኑ መኰንኑንም ረገሙት ጣዖቶቹንም ሰደቡ በእነርሱ ላይም ተቆጥቶ ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ ወታደሮቹን አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ ቊጥራቸውም ዐሥራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ወንዶች ሠላሳ ሰባት ሴቶች ናቸው። 🌼 ከዚህም በኋላ ቅዱስ ፋሲለደስን ሥጋው ሁሉ ቀልጦ እንደ ውኃ እስከሚሆን በብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት መኰንኑም በተራራ ላይ ጥልቅ ጒድጓድ ቆፍረው በዚያ እንዲቀብሩት አዘዘ እንዲሁም አደረጉ። ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ፋሲለደስን ከሞት ደግሞ አስነሣው ወደ መኰንኑም መጥቶ እንዲህ ብሎ ጮኸ "መኰንን መጽሩስ ሆይ እፈር ከሀዲ ንጉሥህም የረከሱ ጣዖቶችህም ይፈሩ እነሆ ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጉዳት ከሞት ጤነኛ አድርጎ አስነሥቶኛልና"። ሕዝቡም ይህን ተአምር በአዩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ ቁጥራቸውም ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሆነ። 🌼 ከዚህም በኋላ ቅዱስ ፋሲለደስን በውስጧ መጋዝ ካላት መንኰራኲር ላይ አውጥቶ ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው ዳግመኛም በብረት ዐልጋ ላይ በሆዱ አስተኝተው ከበታቹ እሳትን አነደዱ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት ከዚያ ስቃይም ውስጥ አንስቶ ያለ ጉዳት ጤነኛ አደረገው እንዲህም ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው "ፋሲለደስ ሆይ ዕውቅ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ ወይም ለድኆች በስምህ ምጽዋትን ለሚሰጥ ወይም ለተራቈተ ልብስን ወይም በመታሰቢያህ ቀን ለቤተ ክርስቲያን መባ ለሚሰጥ በብዙም ቢሆን በጥቂት መታሰቢያህን ለሚያደርጉ ሁሉ እኔ በደላቸውን ሁሉ እተውላቸዋለሁ መኖሪያቸውንም በመንግሥተ ሰማያት ከአንተ ጋራ አደርጋለሁ"። ጌታችንም ይህን ካለው በኋላ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ ቅዱስ ፋሲለደስም በፍጹም ደስታ ደስ ተሰኘ።

                            ✝ ✝ ✝ 🌼 #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወዘሕጎ ያነብብ መዓልተ ወሌሊተ። ወይከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙኃዘ ማይ። እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ"። መዝ1፥2-3። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 12፥33-38።                             ✝ ✝ ✝ 🌼 #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአፅምዒ እዝነኪ"። መዝ 44፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 3፥1-ፍ.ም፣ ያዕ 3፥13-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥46-57 ወይም ማቴ 25፥1-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች ማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የፄዴንያ ማርያም በዓልና የመስቀሉ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

🌼 "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼           🌼 #መስከረም ፲ (10) ቀን። 🌼 እንኳን #ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም #በፄዴንያ_አገር_በማርታ_ቤት ሥጋ የለበሠች ከምትመስል #ከእመቤታች_ሥዕል ከሠሌዳዋ #ቅባት_እየተንጠፈጠፈ ተአምር ለሠራችበት ቀን መታሰብያ በዓል፣ #አምላክን_ለወለደች_ለእመቤታችን #ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_ለተወለደችበት_ለልደቷ በዓል መታሰቢያ (ይህም የአስቄጥስ ገዳም የከበረ አባ መቃርስ በጻፈው መጽሐፈ ግጻዌ ተጽፎል እንዲሁም ደግሞ በላዕላይ ግብጽ በሚገኝ መጽሐፈ ግጻዌ የከበረች ድንግል እመቤታችን የከበረች ሐና በታኅሣሥ ወር በዐሥራ ሰባት እንደፀነሰቻትና መስከም በዐሥር ቀን እንደወለደቻት ተጽፍአል)፣ ለከበረች  ሰማዕትነት ለተቀበለችበት #ለቅድስት_መጥሮንያ_ሰማዕትነት ለተቀበለችበት በዓል ዕረፍት፣ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #የጌታችን_የአምላካችን_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስ #ቅዱስ_መስቀል_ወደ_አገራችን_ኢትዮጵያ ድንበር ከደረሰበት (ተቀጽል ጽጌ) አፄ መስቀል) ቀን ለመታሰቢያ በዓልና ከከሀዲው #ሆሎፎርኒስ እጅ በጥበቧ እስራኤልን ካዳነቻቸው ከጥበበኛ ከከበረች #ከቅድስት_ዮዲት በዓለ ዕረፍትና #ከቅድስት_አትናስያና_ሦስት_ልጆቿ_ከመታሰቢያቸው በረከትና ረድኤትን ያሳትፈን።                                                       ✝ ✝ ✝ 🌼 #በዚህች_ቀን_ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ #አምላክን_የወለደች_የእመቤታችን_የድንግል_ማርያም_ተአምር ተገለጠ። ይቺንም ሥዕል የሣላት ወንጌላዊ ሉቃስ ነው ይባላል። ወደ ጼዴንያ አገርም የመጣችበት ምክንያት አንዲት ስሟ ማርታ የሚባል መበለት ሴት ነበረችና ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች ናት። አምላክን የወለደች እምቤታችን ድንግል ማርያምንም እጅግ ትወዳት ነበር። በሚቻላትም ሁሉ ታገለግላታለች። 🌼 በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኵሴ ከእርሷ ዘንድ እንግድነት አደረ በመልካም አቀባበልም ተቀበለችው በማግሥቱም ስተሸኘው "አባት ሆይ የምትሔደው ወዴት ነው" አለችው። እርሱም "በከበሩ ቦታዎች ውስጥ ልሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም እሔዳለሁ" አላት እርሷም "ከእኔ ገንዘብ ወስደህ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል ግዛልኝና በመመለሻህ ጊዜ አምጣልኝ" አለችው። እርሱም በራሴ ገንዘብ ገዝቼ አመጣልሻለሁ አላት። 🌼 ከዚህም በኋላ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከቅዱሳት መካናት ተባረከና ሥዕሏን ሳይገዛ ወደ ጎዳናው ተመለሰ። ያን ጊዜም "ሥዕል መግዛትን ለምን ረሳህ" የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰማ ወደ ገቢያም ተመልሶ ላሕይዋና መልኳ ያማረና የተወደደ የሆነ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል አግኝቶ ገዛት በሐርና በንጹሕ ልብስም ጠቀለላት። በጎዳናውም እየተጓዘ ሳለ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወንበዴዎች ተነሡበት ሊሸሽም ወደደ ከዚያቺም ሥዕል "መንገድህን ሒድ የሚል ቃል ወጣ" የተከተለውም ሳይኖር መንገዱን ተጓዘ። ሁለተኛም ነጥቆ ሊበላው አንበሳ ተነሣበት ያን ጊዜም ከዚያች ሥዕል የሚያሥፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረው። 🌼 አባ ቴዎድሮስም ይህን ሁሉ ድንቅ ተአምር ባየ ጊዜ ያቺን ሥዕል ወደ አገሩ ሊወስዳት ወደደ ግዛልኝ ላለችው መበለት ይሰጣት ዘንድ አልፈለገም። ✝ ከዚህም በኋላ በመርከብ ተሳፍሮ በሌላ አቅጣጫ ሲጓዝ ታላቅ ነፋስ ተነሣበት ወደ ማርታ አገር ወደ ጼዴንያም ወሰደው ከመርከቡም ወርዶ ከብዙ እንግዶች ጋር ወደዚያች መበለት ቤት ሔደ ማንነቱንም አልገለጠላትም እርሷም አላወቀችውም። በማግሥቱም ተሠውሮ ወጥቶ ወደ አገሩ ሊሔድ በፈለገ ጊዜ የቅጽሩን ደጃፍ አጥቶ ሲያጥመሰምስ ዋለ በመሸ ጊዜም ወደ ማደሪያው ተመለሰ። ያቺም መበለት በአየችው ጊዜ ታደንቃለች እንዲህም ሁኖ እስከ ሦስት ቀን ኖረ በመሸ ጊዜ በሩን ያየዋል ነግቶ መሔድን ሲሻ የበሩ መንገድ ይሠወረዋል። ያቺም መበለት ያዝ አድርጋ "አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን ስትቅበዘበዝ አይሀለሁና ምን ሆነህ ነው" አለችው። 🌼 ከዚህም በኋላ ከዚያች ሥዕል የሆነውን ሁሉ ነገራት ራሱንም ገለጠላት። ያቺንም ሥዕል ሰጣት ተቀብላም የተጠቀለለችበትን ልብስ ፈታች ወዝ ከሥዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች። ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የዚያን መነኩሴ እጆቹንና እግሮቹን ሳመች። 🌼 ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር የምትቀመጥበትን አዘጋጅታ አኖረቻት ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን ሠራችላት በቀንና በሌሊትም የሚበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቀለች ከመቅረዞችም ውጭ የሐር መጋረጃን ጋረደች። ከሥዕሊቱ በታችም ከሥዕሊቱ እየተንጠፈጠፈ የሚወርደው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች ያም መነኰስ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ የእመቤታችንን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገለ ኖረ። 🌼 የሀገሩም ሊቀ ጳጳሳት የዚያችን ሥዕል ዜና በሰማ ጊዜ ከኤጲስቆጶሳትና ከካህናት ከሕዝቡም ሁሉ ጋር መጣ በሠሌዳውም ውስጥ በአዩዋት ጊዜ ሥጋ የለበሰች ሁና አገኙዋት ከዚህ ከአምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ ከዚህም ቅባት ቀድተው ለበረከት በተካፈሉ ጊዜ ወዲያውኑ በወጭቱ ውስጥ ይመላል። ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜ ንውጽውጽታ ሆኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ በዚያች አገር ትኖራለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእናቱ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ 🌼 #ሰማዕቷ_ቅድስት_መጥሮንያ፦ ይቺም የከበረች መጥሮንያ ለአንዲት አይሁዳዊት ሴት አገልጋይዋ ናት። ይችም አይሁዳዊት እመቤቷ ከክርስትናዋ አፍልሳ ትክክል ወደ አልሆነ ሃይማኖቷ ልታስገባት ትሻ ነበር ስለዚህም ታጉሳቁላታለች በላይዋም የአገልግሎት ሥራን ታከብድባታለች ። 🌼 ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን አይሁዳዊት እመቤቷን ተከትላ ወደ አይሁድ ምኵራብ ሔደች ተመልሳም ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ገብታ ጸለየች። ወደ ቤት በገቡም ጊዜ "ወዴት ሒደሽ ነበር ወደእኛ ምኩራብ ለምን አልገባሽም" ብላ ጠየቀቻት ቅድስት መጥሮንያም "ከእናንተ ምኵራብ እግዚአብሔር ርቋል እኮን እንዴት ወደርሱ እገባለሁ። በውስጧ ልገባባት የሚገባኝ ቦታዬ ግን ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ በከበረ ደሙ የዋጃት ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት" ብላ መለሰችላት። እመቤቷም ይህ ነገር በሰማች ጊዜ ተቆጣቻት እጅግም ደብደባ በጨለማ ቤት ውስጥ አሠረቻት ያለ መብልና መጠጥም አራት ቀን ኖረች። 🌼 ከዚህም በኃላ ከእሥር ቤት አውጥታ በጅራፍ ታላቅ ግርፋትን ገርፋ ሁለተኛ ወደ እሥር ቤት መልሳ አሠረቻት በዚያም ዐረፈች። እመቤቷም በድኗን አንሥታ ከቤቷ ደርብ ላይ አውጥታ በውጭ ወደታች ጣለቻት። ወድቃ የሚያዩዋት ሰዎች በገዛ ፈቃድዋ እንደወደቀች አድርገው እንዲናገሩ ብላ ነው ስለ መገደሏ ዳኞች እንዳይመራመርዋት ፈርታለች። 🌼 በዚያንም ጊዜ በዚያች አይሁዳዊት ሴት ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ወረደ ከደርቧ ላይ ስትወርድም በድንገት ወድቃ ሞተች ወደ ዘላለማዊም እሳት ሔደች ይህች የከበረች መጥሮንያ ግን የሰማዕታትን አክሊል ተቀብላ ወደ ዘላለም ሕይወት ሔደች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በቅድስት መጥሮንያ በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 10 ስንክሳር።

🌼 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼           🌼 #መስከረም ፱ (9) ቀን። 🌼 እንኳን #በሮሜ_አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ #በመላእክት_አለቃ_በቅዱስ_ሚካኤል በስሙ በተሠራ ቤተ ክርስቲያን #ላደረገው_ተአምር መታሰቢያ በዓል፣ ከኃላፊው #ከዚኽ_ዓለም_መንግሥቱ_መንኖ ተጋድሎውን በዛፍ ላይ ኹኖ ለፈጸመ፤ የደረቀውን ግንድ ላለመለ፣ ለጽጌ፣ ለፍሬ ለአደረሰ ላሳየ እግዚአብሔርን ደስ ላሰኘ #ለንጉሥ_ለቅዱስ_ለአባ_ያሳይ ለዕረፍት በዓልና ለመጺል ለምትባል አገር ኤጲስቆጶስ ለሆነ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_ቢሶራ_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ፋሲለደስ_ጋር_ዐሥራ_አራት_ሺህ_ሰባት መቶ #ሠላሳ_ወንዶችና_ሰባት_ሴቶችም በሰማዕትነት ከዐረፉ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                               ✝ ✝ ✝ 🌼 በዚህች ቀን #በሮም_አገር_ፍሩምያ በምትባል ከተማ ለሆነው ተአምር መታሰቢያ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው የሰማይ ሠራዊት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ #በቅዱስ_ሚካኤል_ቤተ_ክርስቲያን ውስጥ በሚታዩ ድንቆችና ተአምራቶች ምክንያት ዮናናውያን ሰዎች ሰይጣናዊ ቅናትን እንደ ቀኑ ከመቅናታቸውም ብዛት የተነሣ በዚያ አካባቢ የሚወርደውን የወንዝ ውኃ በዚያች ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊመልሱትና ከሚጠብቃት መጋቢዋ ጋር በውኃ ስጥመት ሊአጠፉአት ፈልገው መለሱት። 🌼 የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለቤተ ክርስቲያኑ መጋቢ ለናርጢኖስ ተገለጠለት ወደርሱም ቀርቦ "ጽና አትፍራ" አለው ይህንን ብሎ በእጁ ውስጥ ባለ በትር አለቱን መታው አለቱም ተሰንጥቆ እንደ በር ሆነ የዚያ ወንዝ ውኃም በውስጡ አልፎ ሔደ። 🌼 ይህንንም ያዩ ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልንም አከበሩት። ከዚያች ቀን እስከ ዛሬ የወንዙን ውኃ በዚያች በተሠነጠቀች አለት ውስጥ አልፎ ሲሔድ ያዩታል ወደ መላእክት አለቃ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቶ አይቀርብም። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማለጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።                                                    ✝ ✝ ✝ 🌼 #ንጉሥ_ቅዱስ_አባ_ያሳይ፦ ይህም ቅዱስ ከኃላፊው ከዚኽ ዓለም መንግሥቱ መንኖ ተጋድሎውን በዛፍ ላይ ኹኖ የፈጸመ ነው፤ የደረቀውን ግንድ ከልምላሜ፣ ከጽጌ፣ ከፍሬ አድርሶ ያሳየ፤ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘ በቅዱስ ነው። ከንጉሥ ከቅዱስ (አባ) ያሳይ ያሳይ በጸሎቱ የምትገኝ በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝ 🌼 #የመጺል_አገር_ኤጲስቆጶስ_አባ_ቢሶራ፦ ይህም ቅዱስ በግብጽ አገር እግዚአብሔርን በምትወድ መጺል በምትባል ከተማ ኤጲስቆጶስ ሆነ። ዲዮቅልጥያኖስም ነግሦ ክርስቲያኖችን በሚያሠቃያቸው ጊዜ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ደሙን ያፈስ ዘንድ ይህ አባት ወደደ። 🌼 ሕዝቡንም ሀሉ ሰብስቦ በቤተ መቅደሱ ፊት በዐውደ ምሕረቱ አቆማቸው ሊጠብቁት የሚገባውን ለጽድቅ የሚያበቃቸውን ትእዛዝ ሁሉ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ደሙን ማፍሰስ እንደሚሻ ነገራቸው ይህንንም በሰሙ ጊዜ ታላቆችም ታናሾችም በላዩ አለቀሱ። "የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ የምትተወን ምን ያደርግልሃል እኛስ እንድትሔድ አንለቅህም" አሉት ሊይዙትም ቃጡ ግን አልተቻላቸውም ተውትም እርሱም ወደ ክብር ባለቤት ክርስቶስ አደራ አስጠበቃቸውና ሰላምታ ሰጥቷቸው ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ተጓዘ። እነርሱም መሪር ልቅሶን እያለቀሱ ሸኙት። 🌼 ስማቸው ቢስኮስ ፊናቢክስ ቴዎድሮስ የሚባሉ ኤጲስቆጶሳት አብረውት ሔድ መኰንኑ ወደ አለበት አገርም ደርሰው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ። እርሱም መኰንኑ አሠቃያቸው ኤጲስቆጶሳትም እንደሆኑ አውቆ ሥቃያቸውን አበዛ እሊህ አባቶች ግን በታላቅ ትዕግሥት የጸኑ ናቸው። ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ያጸናቸዋልና። 🌼 ከዚህም በኋላ መኰንኑ ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ የሕይወት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። የቅዱስ ቢሶራ ሥጋው ግን ንሲል በሚባል አገር እስከ ዛሬ ይኖራል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                                ✝ ✝ ✝ 🌼 "#ሰላም_እብል_ለዓቢይ_መንክሩ። ዘተክሥተ ዮም በውስተ ዳቤሩ። ፈለገ ማይ ይሚጡ እንዘ ይመክሩ። ተሠጥቀ ኰኵሕ እንተ ዐላውያን አንበሩ። #ሶበ_ሚካኤል_ዘበጦ_በበትሩ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_9።                             ✝ ✝ ✝ 🌼 #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ደምፁ ወተሐምገ ማያቲሆሙ። ወአድለቅለቁ አድባር እምኃይሉ። ፈለገ ዘይውኅዝ ያስተፌሥሕ ሀገረ እግዚአብሔር"። መዝ 45፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 8፥35-ፍ.ም፣ ያዕ 1፥2-13 እና የሐዋ ሥራ 20፥16-22። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 7፥24-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ሚካኤል የተአምራት በዓል፣ የንጉሥ ቅዱስ ያሳይ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

🌼 "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼            🌼 #መስከረም ፰ (8) ቀን። 🌼 እንኳን #ለመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ አባት ለበራክዩ ልጅ ለካህንና ለነቢዩ ለሆነ ለከበረ #ለቅዱስ_ዘካርያስ_በንጉሥ_ሄሮድስ_እጅ_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ለእግዚአብሔ_ሰው ለሆነ፣ ለየዋሁ፣ ለቅኑ፣ ለጻድቁ፣ ለነቢያት አለቃ #ለቅዱስ_ሙሴ_ለዕረፍት_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከከበረ_ቅዱስ_ዲማድዮስ ከግብጽ ደቡብ ደንጡ ከሚባ አውራጃ በሰማዕትነት ከዐረፈ፣ ምግቡ የአጋዝን ወተት ከሆነ በዕረፍቱም ጊዜ ብዙ ተአምራትን ከአደረገ ከከበረ #ከገዳማዊ_ከቅዱስ_ቂርቆስ ዕረፍት፣ #ከሰማዕቱ_ቅዱስ_ሉክዮስ ከመታሰቢያው፣ #ከቅዱስ_ኤርምያስና_ከቅዱስ_ዮሐንስ፣ #ከቅዱስ_አንዲዎና_ከቅዱስ_ኤልያኖስና ከመነኰስ #አሞንም_ከመታሰቢያቸወ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                                      ✝ ✝ ✝ 🌼 #በዚች_ቀን_የዓመቱ_ወሮች_መቊጠራያ የሚሆን የመጀመሪያ ኮከብ ይወጣ ይኸውም መናዝል የሚለው ነው የዐሥራ ሁለቱ ወር ኮከቦች ከእልሐመል እስከ ሑት ያሉ መገብተ አውኅራ አሉ ምግብናቸውን ፈጽመው በዚች ቀን እንደገና አንድ ብለው የሚጀምሩበት ነው።                                                               ✝ ✝ ✝ 🌼 #ካህን_ወነቢይ_የበራክዩ_ልጅ #ቅዱስ_ዘካርያስ፦ ይህም ካህን ስለ ልጁ ዮሐንስ መወለድ የመላእክት አለቃ ገብርኤል በነገረው ጊዜ ነገሩን አምኖ አልተቀበለም። ስለዚህም ሕፃኑ እስቲወለድ ዲዳ ትሆናለህ አለው። በተወለደም ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው የልጁንም ስም ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። እርሱና ሚስቱ በእግዚአብሔር ሕግ ያለ ነቀፋ የጸኑ ደጎች እንደሆኑ የከበረ ወንጌል ስለዚህ ምስክር ሆኗል። 🌼 ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስም በተወለደ ጊዜ ሊሰግዱለት የጥበብ ሰዎች መጡ። ሄሮድስም ስለ መንግሥቱ ፈራ ደነገጠም። ስለዚህም ጭፍሮቹን ልኮ በይሁዳ አገር የቤተ ልሔምንና የገሊላን ሁሉንም ሕፃናት ዕድሜያቸው ሁለት ዓመት የሚሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ገደላቸው ሰነፍ የሆነ ሄሮድስ ክርስቶስን ከሕፃናት ጋር እንደ ሚገድለው አስቦ ነበርና። 🌼 ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጾለት ስለአዘዘው ጌታችን ሕፃኑንና እናቱን እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብጽ አገር መጡ። ኤልሳቤጥ ግን ሕፃኗን ዮሐንስን ይዛ ወደ ዱር ወጣች ወደ ሲና በረሃም ሸሸች በዚያም ሕፃኗን እያሳደገች ሰባት ዓመት ኖረች ከዚህም እርሷ አረፈች ሕፃኑም በመምህርነት ለእሥራኤል እስከሚገለጥበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ኖረ። 🌼 ሕፃናትንም ከገደላቸው በኋላ ዮሐንስ ክርስቶስ እንደሆነ ሄሮድስ አሰበ ተጠራጠረ ከአባቱ ከዘካርያስ ዘንድ ሕፃኑን ይሹ ዘንድ ወታደሮቹን ላከ ዘካርያስም "ሕፃኑ ያለበትን ወይም እናቱ ያለችበትን እኔ አላውቅም" አለ። ሄሮድስም ልጅህን "ካላመጣህልኝ እኔ እገድልሃለሁ" አለው። ዘካርያስም ከእርሱ ዛቻ የተነሣ አልፈራም ወታደሮቹንም አዝዞ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካከል ገደሉት ክብር ይግባውና እግዚአብሔርም ሥጋውን ሠወረ ደሙ ግን እንደ ደንጊያ ሆነች። 🌼 ካህናቱና ሕዝቡ እንደ ልማዳቸው ለጸሎት በመጡ ጊዜ ከካህናት አንዱ ወደ ቤተ መቅደስ ውስጥ ገባ። የረጋ ደምን አገኘ ከመጠዊያውም እንዲህ የሚል ቃልን ሰማ "እነሆ የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ተገደለ የሚበቀልም እስሚመጣ ደሙ ስትጮኽ ትኖራለች"። 🌼 እንዲህ የሚልም አለ ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት የሆነ የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ይህ አይደለም ያ አልተገደለም በዕድሜው ኡረት በሚባል አገር ሞተ እንጂ ሥጋውም በዚያ ያለ ጥፋት ተገኝቶ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለታል። የዚህ ዘካርያስ ግን ሥጋው አልተገኘም ስለ መገደሉ የደሙ ድምፅ ምስክር ሆነ እንጁ። 🌼 ደግሞ እንዲህ ተባለ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ከአይሁድ አንድ ሰው መጥቶ "የእግዚአብሔር መልአክ ትወልዳለህ" ብሎ ነግሮት ለዘካርያስ ልጅ ተወልዶለታል "ምናልባት እርሱ ክርስቶስን ይሆን" አለው። ስለዚህ ሄሮድስ ሕፃኑን ዮሐንስን ይገድሉት ዘንድ ወታደሮችን ላከ። 🌼 ዘካርያስም ወታደሮችን እንዲህ አላቸው "ሕፃኑን እኔ ወደሌላ ቦታ ወስጄዋለሁ ከእኔ ጋራ መጥታችሁ ራሳችሁ ከዚያ ቦታ ውሰዱት" ወደ ቤተ መቅደስም እስከ አስገባቸው ድረስ ወታደሮቹ አብረውት መጡ። እርሱም ሕፃኑን ልጁን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኑሮ ጸለየበት ይህም የልጁን መወለድ የእግዚአብሔር መልአክ ለእርሱ የነገረበት ነው። 🌼 ያን ጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ሕፃኑን ዚፈታ ወደሚባል በረሀ ነጥቆ ወሰደው ሕፃኑንም ባላገኙት ጊዜ አባቱን ዘካርያስን ገደሉት። ስለዚህም ጌታችን አይሁድን "በቤተ መቅደሰ መካከል የገደላችሁት የዘካርያስ ደም በላያችሁ ይደርሳል" አላቸው ለመገደሉ ምክንያት አይሁድ ናቸውና እንዲህ አለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በካህኑ ቅዱስ ዘካርያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም  ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                          

❤ ቅዱስ ዮሐንስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፡፡ በሕይወቱና በኑሮው ሁሉ ጌታችንን ለመምሰል ይጥር ነበርና ጌታችንም እጅግ ይወደው ስለነበር "ፍቁረ እግዚእ" ተባለ፡፡ የታላቁ ያዕቆብ ታናሽ ወንድም ስለሆነና አባቱም ዘብድዮስ ስለሚባል "ዮሐንስ ወልደ ዘብድዮስ" ተባለ፡፡ ለጌታችን ባለው ቅናትና ከወንድሙ ጋር ሆነው ባሳዩት የኃይል ሥራ እንዲሁም የጌታችንን አምላክነት በመግለጡ "ወልደ ነጎድጓድ" ተብሏል፡፡ ነገረ መለኮትን ከሌሎቹ በበለጠ ሁኔታ አስፍቶና አምልቶ በማስተማሩ "ነባቤ መለኮት ወይም ታኦሎጎስ" ተብሏል፡፡ ኃላፊውንና መጻዒውን ጊዜ በራእዩ ስለገለጠ "አቡቀለምሲስ" ተባለ፣ ይህም በግሪክኛ ባለራእይ ማለት ነው፡፡ የጌታችንን መከራ መስቀሉን እያስታወሰ 70 ዘመን ሙሉ እያለቀሰ ስለኖረና ፊቱም በሀዘን ስለተቋጠረ "ቁጽረ ገጽ" ተብሏል፡፡ ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያስትፈን። በጸሎቱ ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።                                                                               ✝ ✝ ✝ ❤ #የእስክንድርያ_ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_መቃርስ፦ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ከቍጥራቸው ውስጥ ነው። ይህም አባት ከታናሽነቱ ጀምሮ በገድል የተጠመደ ሆነ የምንኲስናንም ልብስ ሊለብስ ወዶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወጣ። በዚያም በመጀመሪያው አባት በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መነኰሰ በምንኲስና ያለውንም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ❤ ይህምእርሱም ሁልጊዜ መጻሕፍትን የሚያነብና ትርጓሜያቸውንም የሚያስረዳ ሁኗልና በትሩፋት ስራ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ቅስና ተሾመ። ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤልም በዐረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶሳቱ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔዱ። ከእርሳቸውም ጋር ሃይማኖታቸው የቀና ብዙዎች አዋቂዎች ካህናት ነበሩ በአስቄጥስ ገዳም ከሚኖሩ ከታላላቅ መነኰሳትም ጋራ ስብሰባ አድርገው ለዚች ለከበረች ሹመት ስለሚገባው ሰው እየመረመሩ ብዙ ቀኖች ተቀመጡ። ❤ ከዚህም በኋላ የተሻለና ለዚች ለከበረች ሹመት የሚገባ ይህን አባ መቃርስን አግኝተው ሊቀ ጵጵስና ሊሾሙት ሁሉም በአንድ ምክር ተስማው። ስለ ትሩፋቱና ስለ ተጋድሎው በአስቄጥስ ገዳም የሚኖሩ ብዙ መነኰሳት ምስክሮች ሁነዋልና ይዘውትም ሊሔዱ ያለ ፍቃዱ ይዘው አሰሩት እርሱ ግን እንዲህ እያለ ይጮህ ነበር። "እኔ ለዚች ለከበረች ሹመት የማልገባ ነኝ እናቴ ሁለት ባሎችን አግብታ ስለነበር" ይህንንም ያለው እንዲተዉት እንጂ እናቱ ግን በአንድ ባል ብቻ የኖረች ሌላ የማታውቅ ንጽሕት እንደሆነች ስለርሷ ብዙዎች ምስክሮች ሁነዋልና። ስለዚህ እርሱ  የተናገረውን ምክንያት አልተቀበሉትም። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት ከዚያም ወደ ምስር አውጥተው በመዓልቃ በሚገኘው አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሹመቱ ደብዳቤ በዮናኒ በቅብጥ በአረብ ቋንቋ ተነበበች። ❤ ከዚህም በኋላ በሹመቱ ወራት በጎ ስራ ትሩፋትን ተጋድሎውን አብዝቶ የሚሰራ ሆነ ። ሁል ጊዜም ለህዝቡ እግዚአብሔርን እንዲፈሩ ያስተምራቸዋል ስለ ነፍሳቸውም ድኀነት ይገሥጻቸው ነበር። ❤ በሹመቱ ወራትም ከራሱ ከሚገባው ከግብሩ ለቤተ ክርስቲያን ይሰጣል ለድኆችና ለችግረኞችም ይመጸውታል እንጂ ከቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም። በሹመቱም ሃያ ሰባት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ደስ አሰኝቶ በሰላም በፍቅር ሳለ ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ መቃርስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 4 ስንክሳር።                           ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለመቃርስ_በእስክንድርያ_ዘተአምነ። መርዔተ ክርስቶስ ይርዓይ መሲሐውያነ። ለእለ ኀረይዎ ሕዝብ ዘይሰመዩ ኄራነ። ጸሊዖ ሢመተ እንዘ ውእቱ ኢኮነ። ወልደ ዳግሚት ብእሲት ይቤሎሙ አነ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_4።                           ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ። ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት። ወይድኀኑ ፍቁራኒከ"። መዝ 59፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 1 ጢሞ 3፥1-8፣ 1 ጴጥ 5፥9-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥44-51። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 6፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ የልደት በዓል እና የብፁዕ አባ ሙሴ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንል።

❤ "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #መስከረም ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን #ለሐዋርያው_ለወንጌላዊው ለወልደ ነጎድጓድ #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ለልደት_በዓል፣ #ለነዌ_ልጅ_ለቅዱስ_ኢያሱ ለመታሰቢያ በዓሉና ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_መቃርስ_ዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #በአንጾኪያ_በሰማዕትነት_ከዐረፉ_ከ_2መቶ_ሰዎች ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊ፡- ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልን ለመስበክ ዕጣ የደረሰው እስያ ስለነበር ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን አስከትሎ ሄደ፡፡ ይኽችውም ኤፌሶን በጥንቱ በታናሽ እስያ በዛሬው የቱርክ ግዛት ውስጥ ከተማ ናት፡፡ ዛሬ ኢያዞሎክ ተብላ የጥንት ታሪኳ ጠፍቷል፡፡ አስቀድሞ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ሰብኮባታል፡፡ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ጢሞቴዎስንም በከተማዋ ላይ ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾሞት ነበር፡፡ እርሱም በግፍ እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ ቅዱስ ዮሐንስን እየረዳው በከተማዋ ብዙ አገልግሏል፡፡ በኋላ ግን በግፍ ገድለውታል፡፡ ❤ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ኤፌሶን ለመሄድ በመርከብ ሲሳፈር መርከቡ በማዕበል ተሰበረ፡፡ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን ማዕበሉ ወደ አንዲት ደሴት አደረሰው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በመርከቡ ስባሪ ተንጠልጥሎ በባሕሩ ማዕበል መካከል 40 ቀንና 40 ሌሊት ከኖረ በኋላ ማዕበሉ ተፍቶ አብሮኮሮስ ካለበት ደሴት አደረሰውና ተያይዘው ኤፌሶን ከተማ ገቡ። የከተማይቱም ሰዎች እጅግ ክፉዎች ስለነበሩ መጀመሪያ ላይ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አልቻሉም ነበር፡፡ እነርሱም እጅግ ክፉዎች መሆናቸውን ስላወቀ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ዕጣው ሲደርሰው በሀዘን አልቅሶ ነበር፡፡ አሁንም ከተማው በገቡ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ምክንያት በመፍጠር ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤቷ እሳት አንዳጅ ሆኖ አብሮኮሮስም ዕቃ አጣቢ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ የቀጠረቻቸው ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ጀመር፡፡ ባሮቿ እንደሆኑ ተስማምተው ስለጻፉላት ትደበድባቸውም ነበር፡፡ እነርሱም በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እየኖሩ እያለ በአንዲት ዕለት የአገረ ገዥው ልጅ ለመታጠብ ወደ ውሽባው ቤት ገባ፡፡ በውሽባ ቤቱም የሰይጣን ኃይል ስለነበረበት የመኰንኑን ልጅ አንቆ ገደለው፡፡ የአገሪቱም ሰዎች ሁሉ ለሞተው የመኰንን ልጅ ሊያለቅሱ ሲሰበሰቡ ቅዱስ ዮሐንስም አብሮ ቆሞ ሲመለከት ሮምና መጥታ "በጌታዬ ልጅ ሞት ልትደሰት መጣህን" እያለች ረገመችው፡፡ እርሱም "አይዞሽ አትዘኚ" አላትና ወደ ሞተው ልጅ ቀርቦ በመስቀል ምልክት ካማተበበት በኋላ በፊቱ እፍ አለበት፡፡ የሞተውም ልጅ ድኖ ተነሣ፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች እጅግ ደነገጡ፡፡ ሮምናም ደንግጣ "እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን" ብላ ጠየቀችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም "በፍጹም እኔ አምላክ አይደለሁም፣ እኔ የእርሱ አገልጋዩና ሐዋርያው ነኝ እንጂ" አላት፡፡ ሮምናም ስለበደለቻቸው በደል ሁሉ መሪር ዕንባን እያለቀሰች ይቅር እንዲሏት ለመነቻቸው፡፡ እነርሱም አረጋጉዋት፡፡ ከሕዝቡም ውስጥ ብዙዎቹ በጌታችን አመኑ፡፡ ❤ ቅዱስ ዮሐንስም ሌሎች ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ ወንጌልን እየሰበከ ከጣዖት አገልጋዮች በቀር ሁሉንም አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡ አገልጋዮችን ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ከሾመላቸው በኋላ ወደ ሌሎች አቅራቢያ አገሮች ሄደ፡፡ በመጨረሻም በከሃዲውና በጨካኙ በድምጥያኖስ ዘመን በጣዖት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ፡፡ በፈላ ውኃ ካሠቃዩት በኋለ በፍጥሞ ደሴት አጋዙት፡፡ በዚያም ሳለ ራእዩን ተመልክቶ ጻፈው፡፡ ድምጥያኖስም ከተገደለ በኋላ ከግዞቱ ተመልሶ ሦስቱን መልእክታቱንና ቅዱስ ወንጌሉን ጽፏል፡፡ ❤ ጌታችንም አስቀድሞ ሞትን እንደማይቀምስ ለዮሐንስ ቃል ገብቶለት ነበርና (ዮሐ 21፡22) ጥር 4 ቀን እንደ ኤልያስና ሄኖክ ሞትን እንዳያይ ወደ ብሔረ ሕያዋን ወስዶታል፡፡ ጌታችን ለዮሐንስ ያልነገረው እርሱም ያላስተማረው ምሥጢር የለም፡፡ ወንጌሉን መጻፍ ሲጀምር "በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ..." ብሎ የጌታችን ነገር ተመራምሮ ለመድረስ ሲል በመሀል መልአኩን በዮርዳኖስ ባሕር ላይ ሲሄድ አገኘው፡፡ መልአኩም የዮርዳኖስን ባሕር በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፈ ወደ ውጭ ሲያፈስ ተመለከተው፡፡ ዮሐንስም ተገርሞ "ምን ማድረግህ ነው" አለው፡፡ መልአኩም "የዮርዳኖስን ባሕር ቀድቼ እየደፋሁ ልጨርሰው ነው" ሲለው ዮሐንስም መልሶ "ታዲያ በእንቁላል ስባሪ ነውን?" አለው፡፡ መልአኩም "አዎን" አለው፡፡ ዮሐንስም "በከንቱ ደከምክ" አለው፡፡ ይህን ጊዜ መልአኩም መልሶ "አንተስ እንጂ ደግሞ የአምላክን መገኘት፣ አኗኗሩንም ተመራምረህ በጥበብ ለማግኘት ብለህ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ.." ብለህ ጀምረህ የለምን? አንተ ጌታን ተመራምረህ ካገኘህና ከደረስክበት እኔም የዮርዳኖስን ወንዝ በዚህ እንቁላል ቅርፊት ቀድቼ እጨርሰዋለሁ" አለው፡፡ ዮሐንስም ይህን ጊዜ ደንግጦ ዝቅ ብሎ "ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ…" ብሎ ሀሳቡን ለወጠና ሌላ ታሪክ ቀጠለ፡፡ ❤ ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ክርስቲያኖችን ሁሉ ወክሎ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ እርሱም ለእመቤታችን በአደራ የተሰጠ ሲሆን እመቤታችንን ከወሰዳት በኋላ ለ15 ዓመት እየተንከባከበ ጠብቋታል፡፡ እናቱም በሕፃንነቱ ስለሞተች እመቤታችን ናት እየተንከባከበች ያሳደገችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በመልኩም ከጌታችን ጋር ይመሳሰል ነበር፡፡ ❤ ቅዱስ ዮሐንስ ሥዕል የመሳል ተሰጥኦም ነበረው፡፡ ጌታችን በተሰቀለበት ዘመን የነበረው ጢባርዮስ ቄሳር ልጁ በሽተኛ ነበር፡፡ የጌታችንን የማዳን ሥራ እየሰማ እነ ጲላጦስም ስለጌታችን የሚጽፉለትን ይሰማ ስለነበር ልጁን ከጌታችን መቃብር ላይ እንዲያኖሩለት ላከው፡፡ ልጁም ፈጥኖ ተፈወሰለት፡፡ ጢባርዮስ ቄሳርም በልጁ መዳን ምክንያት የጌታችንን ውለታ ማስቀመጥ ፈልጎ የጌታችንን ሥዕሉን የሚሥልለትን ሲያጠያይቅ ቅዱስ ዮሐንስን አገናኙት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ጌታችንን ልክ በዕለተ ዓርብ እንደተሰቀለ አድርጎ በመሣል ለጢባርዮስ ቄሳር ሰጠው፡፡ ሲሥለውም በመጀመሪያ ጌታችንን ልክ እንደተሰቀለ አድርጎ ራቁቱን ነበር የሳለው፡፡ ዮሐንስ የሳለው የጌታችን ሥዕልም አፍ አውጥቶ "በመጀመሪያ አይሁድ በኢየሩሳሌም ራቁቴን ሰቀሉኝ፣ አሁን ደግሞ አንተ ድጋሚ በሮም ራቁቴን ትሰቅለኝን?" ብሎ ተናገረው፡፡ ዮሐንስም እጅግ ደንግጦ "እንዴት አድርጌ ልሳልህ?" ብሎ የሳለውን ሥዕል ቢጠይቀው ሥዕሉም "ከለሜዳ አልብሰህ ሳለኝ" አለው፡፡ ዮሐንስም እንዳለው ከለሜዳ አልብሶ ከሳለው በኋላ ሥዕሉን ትኩር ብሎ ተመልክቶ ቢስመው ከንፈሩ አንድ ቀን ተኩል ያህል ተጣብቆ ቆይቷል፡፡ ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀምባቸውን የጌታችንን ስነ ስቅለት የሚያሳዩ ሥዕሎች መገኛቸው ይህ ወንጌላዊው ዮሐንስ የሳለው ሥዕል ነው፡፡

❤ "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #መስከረም ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ታላቁ የሥውራ ቅዱሳን መኖርያ የሆነው ገዳም #ደብረ_ሐዘሎው ለመሰረቱ፤ አንበሳ እንደ ፈረስ ያገለግላቸው ለነበሩ #ለታላቁ_አባት_ለአቡነ_አንበስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።                             + + + ❤ አባ አንበስ፦ እኚህ አባት ከቅድስናቸው የተነሣ ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱት በአንበሳ ላይ ተጭኖ ነው፡፡ ተአምራትን በማድረግና ወንጌልን በማስተማር በጾም ጸሎት አብዝቶ የደከመ ሲሆን ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሌት ተቀን በጸሎት ይተጉ የነበረ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ አቡነ አንበስ ትውልዳቸው ትግራይ አድዋ በእንጭጮ ወረዳ ነው፡፡ በስማቸው ትግራይ አድዋ "እንጭጮ አቡነ አንበስ ገዳም" እና በትግራይ ሽሬ ሁለት ትላልቅ ገዳማት አሏቸው፡፡ ቅዱስ ያሬድ በድርሰቱ ደጋግሞ የጠቀሳቸው ሲሆን የያሬድንም የድርሰቱን የአቋቋም ሥርዓት ያመጡት አቡነ አንበስ ናቸው፡፡ ❤ አቡነ አንበስ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና በአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ጊዜ የነበሩ ሲሆን እሳቸውንም አንበሶች ያገለግሏቸው ነበር፡፡ ጻድቁ አቡነ አንበስ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጋር የተገናኘ ትልቅ ታሪክ አላቸው፡፡ የላዕላይ ግብጹ አባ ብንያም፣ በአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እና የሐዘሎው አቡነ አንበስ እነዚህ 3ቱ ቅዱሳን ከየአሉበት በአንበሳቸው ተጭነው ምድረ ከብድ አቡዬ ዘንድ እንደደረሱ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንበሶች የ3ቱንም ቅዱሳን አንበሶች ዋጡዋቸው፣ አቡዬም በዚህ አዝነው ከበዓታቸው ወጥተው አንበሶቻቸውን "ትፉ" ብለው የበሉአቸውን አንበሶቻቸውን አስተፍተዋቸው ለ3ቱም ቅዱሳን የተበሉባቸውን አንበሶቻቸውን መልሰውላቸዋል፡፡ ❤ ይኸውም የሆነው እኝዲህ ነው፡- አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዝቋላ 7ቱ ሊቃነ መላእክት እየረዷቸው 70 ሺህ እልፍ አጋንንትን በእሳት ሰይፍ ፈጅተው ካጠፏቸው በኋላ ወደ ምድረ ከብድ ተመለሱ፡፡ ከዚህም በኋላ መንፈስ ቅዱስ የጠራቸው ሦስቱ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ አቡነ አንበስ ዘሐዘሎ እና የላዕላይ ግብጹ አቡነ ብንያም በአንበሶቻቸው ሆነው ወደ ጻድቁ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ምድረ ከብድ ገዳም መጡ፡፡ አባታችን ግን ስለተሰወራቸው እስከ 7 ቀን ድረስ በምህላ ሰነበቱ፡፡ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንበሶችም መጥተው የ3ቱን ቅዱሳን አንበሶች በልተውባቸው ተሰወሩ፡፡ 3ቱም ቅዱሳን ፈጽመው ደነገጡ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም የቅዱሳኑን ሀዘንና ድንጋጤ ተመልክተው በታላቅና በሚያስፈራ ግርማ ሆነው ስልሳ ነብሮችንና ስልሳ አንበሶችን አስከትለው ተገለጡላቸው፡፡ ቅዱሳኑም ከአቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ግርማ የተነሣ ስለደነገጡ እንዳይፈሩም አረጋጉአቸው፡፡ ❤ ከዚህም በኃላ አባታችን "በምን ምክንያት ወደዚህ ገዳም ወደ እኔ መጣችሁ?" አሏቸው፡፡ ሦስቱ ቅዱሳን እንዲህ አሉ፡- "ጸሎትህ ቅድስት እንደሆነች ባወቅን ጊዜ ወደ አንተ መጣን፤ አንተ በሁሉ ርእሰ ባሕታውያን ነህና የእግዚአብሔርን ሥራ ትነግረን ዘንድ መጣን፤ ባላገኘንህም ጊዜ እስከ 7ቀን አለቀስን" አሉት፡፡ ❤ ዳግመኛም "አንበሶችህ መጥተው አንበሶቻችንን ደማቸውን ጠጡ ቆዳቸውንም በጥፍራቸው በጣጠሱ" ብለው ነገሯቸው፡፡ አባታችንም ይህንን ሲሰሙ አንበሶቻቸውን "እስከ ዕለቴ ሞቴ ድረስ በእግሬ ከረገጥኩት ትቢያ በቀር ምንም እንዳትበሉ ታዛችሁ የለምን? እግዚአብሔር ያላዘዛችሁትን ለምን በላችሁ? በሉ አሁንም የበላችሁትን ትፉ" አላቸው፡፡ እነዚያም አንበሶች አፋቸውን ከፍተው አንዳች ሳያስቀሩ አጥንታቸውን ሥጋቸውን በሙሉ ተፉአቸው፡፡ ጻዲቁ አባታችንም ወደ ምሥራቅ ተመልሰው እግዚአብሔርን ከለመኑ በኋላ በአንበሶቹ ሥጋ ላይ ባረኩና "በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ተነሡ" አሏቸው፡፡ አንበሶቹም እንደ ዐይን ፈጥነው ተነሥተው እንደ ቀድሞው ሆኑ፡፡ ከአባታችን ከአቡነ አንበስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለአባ_አንበስ በፍኖተ ፃሞ ወሥራሕ። ዘይጼዓን ዘልፈ ዲበ አንበሳ መፍርህ። ለዘይጻድቅ ብእሲ እስከ ይገብእ ፍትሕ። ኢያጠፍኦ ማይ ወርደተ ዝናም ብዙኅ። ለዓሠረ ደሙ ቀይሕ ዘሀሎ በኰኵሕ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_3።

❤ከ #መጥምቀ _መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ❤ ታሪክ ምን ያስተምረናል..... #አስቀድሞ መሐላ መማል ፈጽሞ ተገቢ እንደልሆነ፡- "የሄሮድያዳ ልጅ ንጉሥ ሄሮድስን በዘፈኗ በጣም አድርጋ ስላስደሰተችው እርሱም በተራው ሊያስደስታት ፈለገ፡፡ ‹እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ይሰጣት ዘንድ በሕዝቦቹና በመኳንንቱ ሁሉ ፊት እንዳይከዳት በፅኑ ቃልኪዳን ማለላት፡፡› እንዲህም እያለ ‹የፈለግሽውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ምን ላድርግልሽ?› እያለ በመሐላ ባላት ጊዜ በእናቷ ምክር የዮሐንስን አንገት ቆርጦ ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፡፡ ንጉሥ ሄሮድስም ይህን ልመና ከአፏ በሰማ ጊዜ ‹የፈለግሽውን እሰጥሻለሁ› ብሎ በሕዝቡ ፊት ስለማለ ለሰው ይምሰል አዘነ፣ ተከዘ፡፡ ኃዘኑም ስለ ዮሐንስ መሞት አይደለም፣ ዮሐንስን ሕዝቡ ይወደው ስለነበር እነርሱን ስለ መፍራቱና መሐላ ምሎ ከዳ እንዳይባል ነው እንጂ፡፡ ስለ ዮሐንስ አዝኖ ቢሆን ኖሮ ቀድሞውንም በግፍ እንዲታሰር ባላደረገው ነበር፡፡ #ወንድሞቼ እኅቶቼ ሆይ! ከመሐላ የተነሣ መፍራት ይገባችኋል፡፡ ‹የለመንሽውን ሁሉ እሰጥሻለሁ› ብሎ ስለማለ ሄሮድስ የዮሐንስን አንገት እንድትቆረጥ አደረገ፡፡ 📌ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በቅዱስ ወንጌል ‹ፈጽማችሁ አትማሉ› ብሏል፡፡ ከዚህ በኋላ ወታደሮች ሠይፍ ይዘው የዮሐንስን አንገት ይቆርጡ ዘንድ ወደ መኅኒ ቤት ሄዱ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሄሮድስ ጭፍሮች ሊገድሉት እንደመጡ በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስላወቀ ከጨለማው ቤት ውስጥ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ እንደሚመቻቸው አድርጎ ጠበቃቸው፡፡ የሄሮድስን ቃል እንዳያቃልሉ ጭፍሮቹም የ"መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን" አንገት ስለ መሐላው ቆረጡት፡፡ በመሐላ ምክንያት ባይሆን ኖሮ ሄሮድስ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ባላስገደለው ነበር፡፡ ስለዚህ ወንድሞቸ እኅቶች ሆይ! እናንተም ከመሐላ የተነሣ መፍራት ይገባችኋል፣ ፈጽማችሁም መማል የለባችሁም፡፡›› 📌ስካርና ዘፈን ከሚገኙበት ቦታ አጋንንትና ኃጢአት ከዚያ አሉ፡- ‹‹ወንድሞችና እኅቶች ሆይ! አለልክ መብላትና መጠጣት ካለበት ቦታ #እግዚአብሔርን መበደል፣ ማስቀየምና ማስቆጣት ይገኝበታል፡፡ ስካር ከሚገኝበት ቦታ አጋንንትና ኃጢአት ከዚያ አሉ፡፡ ስካርና ዘፈን ከሚገኝበት ቦታ የ #እግዚአብሔር መቅሰፍት የፈጣሪያችን ቁጣና በቀል ይፈጸምበታልና፡፡ እናንተ ሕዝበ ክርስቲያኖች ሆይ! ከስካር፣ ከዘፈንና ከዝሙት መራቅ ይገባችኋል፡፡ 📌መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ያስገደለው ዘፈን፣ ስካርና የዜማ ፍቅር መሆኑን ልብ በማለት መገንዘብ አለባችሁ፡፡››

መቅደስ ደመና 🌼እንኳን ከዘመነ ዩሀንስ ለዘመነ ማቴዎስ አደረሳችሁ አደረሰን🙏 አዲሱ ዘመን የሰላም የመተሳሰብ የፍቅር የአንድነት እንዲሁም ያሰብነው የሚሳካበት ያድርግልን 🙏               ✍ ኪነ-ጥበብ ክፍል

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #መስከረም ፪ (2) ቀን። ❤ እንኳን #ለታላቁ_ነቢይ_ሰማዕት_ሐዋርያ_ካህን #ለመጥምቀ_መለኮት_ለሰማዕቱ_ለቅዱስ_ዮሐንስ ሕግ አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ አንገቱን በመሰየፍ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በዚች ቀን በጨማሪ ከሚታሰቡ፦ በግብጽ ውስጥ ታዕዳ ከሚባል አገር በሰማዕትነት ከዐረፈ #ከቅዱስ_ዳስያ፣ #ከሰማዕት_ዲዲሞስና #ቅድስት_መሪና ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የታላቁ_ነብይ_ሰማዕት_ሐዋርያ_ካህን፣ #የመጥምቀ_መለኮት_የቅዱስ_ዮሐንስ_ሰማዕትነት፦ ይህም እንዲህ ነው ፊሊጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ነቢዩ ቅዱስ ዮሐንስ በገሠጸው ጊዜ ፊሊጶስ ወንድሙ ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስም የወንድህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ይለው ነበርና። ❤ ቅዱስ ዮሐንስም ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ። ስለዚህም ቅዱስ ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው። ❤ ሄሮድስም ቅዱስ ዮሐንስን ይፈራው ነበር ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ። ❤ የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና "የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ" አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት። ወጥታም እናቷን "ምን ልለምነው" አለቻት እናቷም "የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ" አለቻት። ❤ ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ "የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በውጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ" ብላ ለመነችው። ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም። ✝ ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የቅዱስ ዮሐንስን ራስ ቆረጡ ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጡአት እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች። ❤ በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ። "ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም" እያለች በመጮኸ ዘልፋዋለችና። ❤ ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ በአጥማቂው ቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝                           ❤ #ቅዱስ_ዳስያ፦ ይህም ቅዱስ በግብጽ ውስጥ ታዕዳ ከሚባል አገር ነው። ቅዱስንም የእንዴናው አገረ ገዥ አርያኖስ አሠቃየው ጽኑ ሥቃይንም ከአሠቃየው በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። የቅዱስ ዳስያ በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 2 ስንክሳር።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወእመኒ ነሣእኩ ክንፈ ከመ ንስር። ወሠረርኩ እስከ ማኅለቅተ ባሕር። ህየኒ እዴከ ትመርሀኒ ወታነብረኒ የማንከ"። መዝ 138፥9። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 14፥1-13።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 6፥1-11፣ 1ኛ ዮሐ 3፥10-16 እና የሐዋ ሥራ 13፥24-28። የሚነበበው ወንጌል ማር 6፥14-29። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #መስከረም ፩ (1) ቀን። ❤ እንኳን #ለርእሰ_ዐውደ_ዓመት_ለቅዱስ ዮሐንስ፤ #ከዘመነ_ቅዱስ_ዮሐንስ_ወደ_ዘመነ_ቅዱስ_ማቴዎስ አሸጋግሮ እግዚአብሔር አምላክን በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                                                         ✝ ✝ ✝ ❤ #የተባረከ_የመስከረም_ወር_የግብፅና #የኢትዮጵያ_ዓመታት_ወሮች_ርእስ_ነው። የቀኑ ሰዓትም ከሌሊት ሰዓት የተስተካከለ ዐሥራ ሁለት ነው። ከዚህ በኋላ እያነሰ ይሔዳል። አሁንም በፍጹም ንጽሕና ታላቅ በዓልን አድርገን ልናከብር ይገባናል። ❤ ይህች ዕለት ከሌሎች ዕለታት ተለይታ የተባረከች ናትና ከክፉ ሥራዎችም ሁሉ ተለይተን እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝባቸውን አዳዲስ የሆኑ በጎ ሥራዎችን እንሥራ። ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ "እነሆ የቀደሙት ሥራዎች አልፈው ሁሉ በክርስቶስ ሐዲስ ሆነ" እንዳለ። ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁ የጐላ የተረዳ ሆነ እርሱም በክርስቶስ ልጅነትን በመስጠት ይቅርታውንና ቸርነቱን አደለን። ❤ ኢሳይያስም እንዲህ አለ "በኔ ህልውና ያለ ያዋሐደኝ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ ስለርሱ ድኆችን በልብ ያዘኑ ሰዎችን ደስ አሰኛቸው ዘንድ ለተማረኩም ሰዎች ነፃ መውጣትን አስተምራቸው ዘንድ ዕውሮችም ያዩ ዘንድ እግዚአብሔር የወሰነውን ዘመን የተመረጠ እለው ዘንድ ፍዳ የሚደረግባትንም ቀን ደግ እላት ዘንድ ያዘኑትንም ሰዎች ደስ አሰኛቸው ዘንድ ላከኝ"። ❤ ነቢዩ ዳዊትም ዳግመኛ እንዲህ አለ "የምሕረትህንም ዓመት እህል ትባርካለህ። ምድረ በዳዎችም ከበረከትህ ጠሎችን ይጠግባሉ። ምንጭ፦ የመስከረም 1 ስንክሳር።                                                           ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወትባረክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ። ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም። ወይረውዩ አድባረ በድው"። መዝ 64፥11-12 ወይም 146፥6። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 4፥17-23።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "አድኅንኒ እምእለ ሮዱኒ እስመ ይኄይሉኒ። ወአውጽነ እሞሕቅ ለነፍስየ። ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ"። መዝ 141፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 6፥1-11፣ ያዕ 5፥8-13 እና የሐዋ ሥራ 5፥12-16። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 11፥1-20። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ወይም የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም አዲስ ዓመት፣ የመልአኩ የቅዱስ ራጉኤል የሲሞት በዓል፣ የሐዋርያው በርተሎሜዎስም የዕረፍት በዓልና የታላቁ አባት የአባ ሚልኪ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።