ru
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Открыть в Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Больше
602
Подписчики
Нет данных24 часа
-87 дней
-1630 дней
Архив постов
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ለሢመቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕ
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ለሢመቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕት የተባለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹ሊቀ ዲያቆናት› ሆኖ ተሾሟል ይህም ጥቅምት ፲፯ ቀን ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተጠቀሰው ይህ ቅዱስ በመጀመሪያ ገማልያል በተባለ መምህር ትውፊትን ኦሪትንና ነቢያቱን ተምሯል፡፡ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ስብከት ወቅትም እርሱ በዋለበት እየዋለ ባደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ ደቀ መዝሙሩም ሆነ ጌታችንም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ አደረገው፤ አጋንንትም ተገዙለት፡፡ (የሐዋ.፭፥፴፬፣፮፥፭-፲) በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሰባ ሁለቱ አርድእት መካከልየመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት ነበር ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነትም ወንጌልን ሰብኳል፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ፈተና ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሰባት ዲያቆናት ሲመርጡ አንዱ እርሱ ነበር፡፡ የስድስቱ ዲያቆናት አለቃና የስምንት ሺህ ማኅበር መሪ ሆኗል።(የሐዋ.፮፥፬)ስለ ወንጌል በመጋደል ኋላም በሰማዕትነት አርፏል። የሰማዕቱ በረከት ይደርብን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ጥቅምት ፲፯ (17) ቀን። ✝ እንኳን #ለዲያቆናት_አለቃ ለሰማዕታት መጀመሪያ ለሆነ #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ_ለተሾመበት_በዓል በሰላ
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝              ✝ #ጥቅምት ፲፯ (17) ቀን። ✝ እንኳን #ለዲያቆናት_አለቃ ለሰማዕታት መጀመሪያ ለሆነ #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ_ለተሾመበት_በዓል በሰላም አደረሰን።                            ✝ ✝ ✝ ✝ #የዕለቱ_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "ጳጳሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት ሊቃነ ካህናት ሥዩማነ ቤተ ክርስቲያን እለ ሎሙ ሕግ ወሎሙ ሥርዓት ብፁዕ እስጢፋኖስ ምስለ ኵሎሙ ቅዱሳን ለከ የዓርጉ ስብሐት እግዚኣ ለሰንበት አሠርጎካ ለምድር በስነ ጽጌያት ወሠራዕከ ሰንበት ለሰብእ ዕረፍተ ወብውህ ለከ ትኅድግ ኃጢአተ ረቢ ንብለከ ረቢ ሊቅ ነአምን ብከ። ትርጉም፦ ሕግና ሥርዓት ያላቸው የካህናት አለቆች የቤተ ክርስቲያን ሹማምንት፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስትና ጳጳሳት እስጢፋኖስ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ምስጋናን ያሳርጉልሃል፣ የሰንበት ጌታ ምድርን በአበቦች ውበት አስጌጥካት፣ ለሰው ዕረፍትን ሰንበትን ሠራኽ ኃጢአትን ትተውለት ዘንድ መምህር እንልሃለን፣ ሊቅ መምህር ሆይ እናምንብሃለን።  √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ መንፈሳዊ ትረካ 🧾🧾🧾🧾🧾 ክፍል ሁለት ፪ ✍️✍️✍️አዘጋጅ ቀሲስ ሄኖክ ወልደማርያም 📣📢📣📢📣አቅራቢ ሳሙኤል ገዛኸኝ

እንኳን #ለእስክድርያ_አርባ_ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ያቃቱ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_መቊሮፍዮን_ከእብሎ፣ #ከባሕታዊ
እንኳን #ለእስክድርያ_አርባ_ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ያቃቱ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_መቊሮፍዮን_ከእብሎ፣ #ከባሕታዊ_ኢሳይያስ_ረድእ_ከጴጥሮስ፣ #ከፋሩ_ከድርቄ_አገር_ከሆኑ_ከአርባ_አምስት ጻድቃን፣ #ከቃርቡ_ከአናልዩ_ከአባ_ጳውሊ ከመስተጋድል #ማርቆስ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። "#ሰላም_ለክሙ_መቊሮፍዮን ወእብሎ ብፁዓዊ። #ወጴጥሮስ_ረድኡ_ለኢሳይያስ_ባሕታዊ። ደናግል ዕደው እምነ ፍትወት ምድራዊ። ሀቡኒ እምቅብዕክሙ ፈትለ ማኅቶትየ አርዊ። አመ በውውዓ ሌሊተ ይመጽእ መርዓዊ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጥቅምት_16። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

በአማራ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት በባህርዳር ሀገረ ስብከት ብቻ 24 የአብነት ተማሪዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተገለጸ። ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም (አዲስ አበባ ) በአማራ ክልል እየተካሄደ
በአማራ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት በባህርዳር ሀገረ ስብከት ብቻ 24 የአብነት ተማሪዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተገለጸ።   ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም (አዲስ አበባ ) በአማራ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት በባህርዳር ሀገረ ስብከት ብቻ 24 የአብነት ተማሪዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ እና በርካታ ጉባኤ ቤቶችም በጦርነቱ ምክንያት እንደተበተኑ ተገለጸ። ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ በአማራ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት ምክንያት  በርካቶች ሕይወታቸውን እና አካላቸውን እያጡ ሲሆን ከነዚህም መካከል በገዳማት እና አድባራት የሚገኙ የአብነት ተማሪዎች ይገኙበታል። በባህርዳር እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በ5 አጥቢያዎች የሚገኙ የአብነት ተማሪዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ 24 ተማሪዎች  ሕይወታቸውን እንዳጡ፤ የሟች ደቀመዛሙርት ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ነው የተገለጸው። ደቀመዛሙርቱ የአዴት ቅድስት ኪዳነምህረት ፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም ፣ የበዓለ እግዚአብሔር ፣ የአቡነ ሐራ ድንግል እና የቅድስት በዓታ ለማርያም አብያተክርስቲያናት የአብነት ተማሪዎች መሆናቸውን ተጠቁሟል ሲል የዘገበው ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት ነው። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በ3ኛ ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ውሎን በተመለከተ መግለጫ ሰጡ፡፡ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም (/አዲስ አበባ ) በመግለጫቸውም ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተክርስቲያን ኅልውና በሀገር ሰላም እና በአእምሯዊ ንብረት ጉዳዮች መወያየቱን ገልጸዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በ3ኛ ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ውሎን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ በዕለቱ በአብዛኛው ከጥበብና ከትምህርታዊ ጉዳየች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ምክክር ሲያደርግ መዋሉን ገልጸዋል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳው የቤተክርስቲያንን ኅልውና ለማስቀጠል ምን መደረግ አለበት? በሚልና በሀገር ሰላም ጉዳይ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ኅልውና ለማሰቀጠል ወደ ፊት ምን መደረግ አለበት? በሚል የቀረበው የዳሰሳ ጥናትና በወቀታዊ የሀገራዊ ሰላም ላይ የቀረበው ጥናት ለጉባኤው በንባብ የተሰማ ሲሆን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሰነዱን በሚገባ አንብበው ውይይት ለማድረግ አጀንዳው ለቀጣዩ ቀን ማደሩን ገልጸዋል፡፡ በ2016 ዓ .ም ሁለት ኮሌጆችና አንድ ማሰልጠኛ እንዲሁም አንድ የአብነት ትምህርት ቤት ወደ ሥራ እንዲገቡ ውሳኔ መተላለፉን የገለጹት ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በውሳኔው መሠረት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በ2016 ሁለት መንፈሳዊ ኮሌጆች በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት እና በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት እንዲሁም በጎንደር የአንድ የአራቱ ጉባዔያት የአብነት ትምህርት ቤት ወደ ሥራ እንዲገቡ እንዲያደርግ መወሰኑንና አንድ የካህናት ማሰልጠኛ በሆሳዕና ከተማ እንደሚከፈት ገልጸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ እስከ 2020 ድረስ ዓ.ም ምን ያህል ኮሌጆች እና ማሰልጠኛዎች ይከፈታሉ በሚለው ጉዳይ ዝርዝር ጥናት ለቅዱስ ሲኖዶስ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት የ3ኛ ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሎ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ዝውውርና ምደባ ማድረጉን የገለጹ ሲሆን ዝርዝሩ ወደፊት ይገለጻል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም አእምሮአዊ ንብረትን በተመለከተም ቅዱስ ሲኖዶስ መምከሩን ገልጸው በ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት 5 ሚሊዮን ብር በሚደርስ በጀት 60 የሚደርሱ ቅዱሳት መጻሕፍት በአእምሯዊ ንብረት ለማስመዝገብ የተሠራው ሥራ የሚያኮራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አጠቃላይ የቤተክርስቲያናችንን አእምሯዊ ንብረት ለማስመዝገብ ፕሮጀክቱ እስከ 27 ሚሊዮን ብር እንደሚፈጅ የተናገሩት ብፁዕነታቸው የተጀመረውን ሥራ ሒደቱ ጥሩ መሆኑን በመግለጽ የተሻለ ሥራ መሰራት እንደሚገባውም በውይይቱ ላይ መቅረቡን ገልጸዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በእሥር ላይ የሚገኙት መሪጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ የዋስትና መብት ተጠብቆላቸው ከእሥር ተፈተው ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠየቀ። የቅዱስ ሲኖዶ
+1
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በእሥር ላይ የሚገኙት መሪጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ የዋስትና መብት ተጠብቆላቸው ከእሥር ተፈተው  ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠየቀ። የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሠራተኛ የሆኑት መሪጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ የታሰሩበትን ምክንያት ለማጣራት ቢሞክርም ከሚመለከታቸው አካላት መረጃ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጿል። ጽ/ቤቱ ግለሰቡ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸውም ጠይቋል። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ጥቅምት ፲፭ (15) ቀን። እንኳን #ለዐሥራ_ሁለቱ_ቅዱሳን_ሐዋርያት ዓለም በእጣ ለተካፈሉበት ለመታሰቢያ ቀን፣ ለቅዱስ ጳውሎስ ረድ
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝               ጥቅምት ፲፭ (15) ቀን። እንኳን #ለዐሥራ_ሁለቱ_ቅዱሳን_ሐዋርያት ዓለም በእጣ ለተካፈሉበት ለመታሰቢያ ቀን፣ ለቅዱስ ጳውሎስ ረድ #ለቅዱስ_ሲላስና_ለኒቆድምያ አገር ለሆነ ለሰማዕቱ ለቅዱስ ቢላሞን ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቢላሞን_ማኅበር_ከሆኑ_ከመቶ_ሃምሣ_ስምንት ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ #ከሰላትዮን_ከአጥራኪስ #ከአርሞቅስ_ከአድማንያ_ከአርሚስ_ከቅድስት ጾመታ፣ #ከአባት_ኢሳይያስና_ከሐዋርያትም ከዕፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። "#ሰላም_እብል_ለርክበተ ዐፅምክሙ ወርቅ። #አዝቂር_ወኪርያቅ። #ወሰላም_ለሲላስ ረድአ ማዕነቅ። ዘጸለለ በጌጋይ እምነጽሮታ ለጽድቅ። ዐይነ ሐሊናየ ፈውሱ በምራቅ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጥቅምት_15።               √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 ውድ የፍኖተ ብርሃን ቤተሰቦች ይህ ቻናል የተለያዩ በዓላትን በፎቶ እና በቪዲዮ በአንድ ሰድረን የምናስቀምጥበት ነው እናንተም ይህንን ቻናል በመቀላቀል ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን ማግኘት ትችላላችሁ። 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣 https://t.me/+TYIEG82pLpEzZmNk 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣    ✨✨✨ Join ✨✨✨   ✨✨✨ Join ✨✨✨ ✨✨✨ Join ✨✨✨

ጻድቁ አባታችን አምላክን በወለደች በእመቤታችን በድንግል ማርያምና ጌታችን ዐሥራት አድርጎ በሰጣት በኢትዮጵያ ፍቅር ልባቸው በመነደፉ ከሁለት ደቀ መዛሙርቶቻቸው ጋር ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ከእርሳቸው ጋር ዘጠኝ ለሆኑት ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ምክንያት የሆኑ አባት ናቸው፡፡ በጥቅምት ፲፬ ዕለትም እንደነ ሄኖክ ፣ ኤልያስና ዕዝራ ሞትን ሳያዩ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተሰወሩበትን በዓል የምናከብራላቸው ክርስቶስን በእውነት የተከተሉ አባት ናቸው፡፡ የቅዱስ ገብረ ክርስቶስም ሕይወት እንደ ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ ክርስቶስን የመከተል ሕይወት ነው፡፡ የቊስጥንጥንያ ንጉሥ የሆነው አባቱ ቴዎዶስዮስ እና እናቱ መርኬዛ ከሮም ንጉሥ ልጅ ጋር ቢያጋቡትም ክርስቶስን ለመከተል ከሙሽራ ቤት የወጣ ታላቅ የትሕትና እና የትዕግሥት መምህር ነው፡፡ በጥቅምት ፲፬ ቀን የሚነበበው የስንክሳር መጽሐፋችን ስለ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ የሰርግ ምሽት እንዲህ ይላል ፡- “ከሌሊቱ እኩሌታም በሆነ ጊዜ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ተነሥቶ ወደ ሙሽራዪቱ ገባ፤ እጅዋንም ይዞ ከእርስዋ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፡፡ ከዚያም የሃይማኖት ጸሎት “በአንድ አምላክ እናምናለን” የሚለውን እስከ መጨረሻ ጸለየ፤ የተሞሸረበትንም ልብስ ከላዩ አውልቆ የግምጃ ልብስን ለበሰ፤ ወደ ሙሽሪቱም ሒዶ ራስዋን ሳማት፤ እንዲህም እያለ ተሰናበታት፤ “እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይኑር፤ ከሰይጣን ሥራ ሁሉ ያድንሽ፡፡ እርሷም አልቅሳ “ጌታዬ ወዴት ትሔዳለህ? ለማንስ ትተወኛህ?” አለችው፤ እርሱም “በእግዚአብሔር ዘንድ እተውሻለሁ፤ እኔም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሔዳለሁ፤ የአባቴ መንግሥት አላፊ ነውና አንቺም መሐላሽን አስቢ” አላት፤ ያን ጊዜ መሐላዋን አስባ ዝም አለች፡፡  ቅዱስ ያሬድ ይህን የቅዱስ ገብረ ክርስቶስን የልዕልና ተግባር “ቦ ዘፈለሰ ኀዲጎ ብእሲቶ ኃዲጎ ብእሲቶ ቦ ዘፈለሰ ወቦ ገዳመ ዘተግሕሠ መኒኖ መንግሥቶ መንግሥቶ ገብረ ክርስቶስ፤  ሚስቱን ትቶ ተሰደደ ገብረ ክርስቶስ ንግሥናውን ንቆ ገዳም ገብቶ ተቀመጠ” በማለት ጠቅሶታል፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በአርማንያ አገር በተሠራች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ደጅ የሚኖር ሆነ ፡፡ በዚህም ‹‹አብደርኩ እትገደፍ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር፤እምንበር ውስተ ቤተ ኃጥአን፤ በኃጥአን ድንካኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ” የሚኖረውን የቅዱስ ዳዊትን ቃል ፈጸመ፡፡ (መዝ.፹፫፥፲) ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሔዳለሁ››  በማለት እውነተኛውን ፍቅር በመከተል ለክብር በቅቷል፡፡ እኛስ ምን እንከተል? ምንስ እንተው?  ፍቅርን ትተን ጥላቻን በመከተላችን በእያንዳንዳችንም ሆነ በሀገር ደረጃ ትልቅ መከራ እያሳለፍን ነው፡፡ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተክርስቲያን ደጅ መጣልን መርጧል፤ እኛስ ከየትኛው ደጅ ተጥለን እንገኝ? ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለት ዕለት ከምትሰብከው በኅብረት የመኖር ደጅ ወይስ በዘር የመለያየት ደጅ? አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም፣ በአባቶቻችን በአቡነ አረጋዊ እና በቅዱስ ገብረ ክርስቶስ አማላጅነት ጥላቻን ትተን፣ ንቀንና ፍቅርን ተከትለን በቤተ ክርስቲያን ኅብረት በአንድነት እንድንኖር ይርዳን፡፡ ምንጭ ፡- ስንክሳር ዘወርኀ ጥቅምት፣ ገድለ አቡነ አረጋዊ √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨

“ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሄዳለሁ” (መጽሐፈ ስንክሳር) ለመንግሥቱ ፍጻሜ ለባሕርዩ ኅልፈት ውላጤ የሌለበት ወይም የማይኖርበት እግዚአብሔር አብ፣ አዳምን ለማዳን ከእመቤታችን ከቅድስት ድን
+1
“ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሄዳለሁ” (መጽሐፈ ስንክሳር) ለመንግሥቱ ፍጻሜ ለባሕርዩ ኅልፈት ውላጤ የሌለበት ወይም የማይኖርበት እግዚአብሔር አብ፣ አዳምን ለማዳን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍስዋ ነፍስ ነሥቶ ሥጋዋን ተዋሕዶ ሰው የሆነ እግዚአብሔር ወልድ፣ በባሕርዩ መጉደል ወይም መጨመር ሳይኖርበት በመንግሥቱ ከአብ ከወልድ ጋር አንድ የሚሆን በኀምሳኛው ቀን በደብረ ጽዮን የወረደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይድረሳቸውና ለእኛ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ውስጥ ለምንኖር ምእመናን ብንቆጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ የሚበዙ ድንቅ ምስክሮችን ጻድቃንን በአማላጅነታቸው እንድንጠቀም አድለውናል፡፡ ከእነዚህ መካከል ጥቅምት ፲፬ ቀን በዓላቸውን የምናከብረው ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ እና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ይገኙበታል፡፡ አባታችን አቡነ አረጋዊ አስቀድሞ ራሱ ባለቤቱ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ የመሠረተውን ሥርዓተ ገዳምን ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያመጡ ታላቅ መናኝና ጻድቅ አባት ናቸው፡፡ አባታችን ከእንጦንስና ከመቃርስ፣ ከጳኵሚስም የምንኵስና ሐረግ ዐራተኛ ትውልድ ናቸው፡፡ ከሮም ነገሥታት መካከል ከሆኑት ከአባታቸው ከይስሐቅ ከእናታቸው ከእድና የተወለዱት አባታችን ወላጆቻቸው የታላላቅ ነገሥታት ወገን የምትሆን ሚስት ቢያጩላቸው እምቢ በማለት ከሮም ወደ ፅርዕ (ግሪክ) አገር በመሔድ ታላቁን የመንፈሳዊ ማኅበር ከመሠረተውና የመነኮሳት አባት ከሆነው ከቅዱስ ጳኵሚስ ዘንድ የምንኵስናን ልብስ የተቀበሉና ክርስቶስን ለመከተል ገና በልጅነታቸው የመረጡ አባት ናቸው፡፡ በሥጋዊ መጠነ ቁመታቸው ወይም በዕድሜ ታናሽ የሆኑት አባታችን በጥበብ ፣ በምክርና በዕውቀት ግን የልጅ ዐዋቂ በመሆናቸው ዘሚካኤል ከተባሉበት ስማቸው አረጋዊ ለመባል በቅተዋል፡፡

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ጥቅምት ፲፬ (14) ቀን። እንኳን #ከዘጠኙ_ቅዱሳን_አንዱ ለሆኑት #ለአባ_ዘሚካኤል በሚሰሩት ስራቸው አረጋዊ ለተባሉት ለታላቁ አባት
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝            ጥቅምት ፲፬ (14) ቀን። እንኳን #ከዘጠኙ_ቅዱሳን_አንዱ ለሆኑት #ለአባ_ዘሚካኤል በሚሰሩት ስራቸው አረጋዊ ለተባሉት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_አረጋዊ ከዚህ ዓለም ከሞት ለተሰወሩበት ቀን ለመታሰቢያ በዓል፣ ለቊስጥንጥንያ ንጉሥ ለቴዎዶስዮስ ልጅ ለሙሽራወ #ለቅዱስ_ለገብረ_ክርስቶስና ከሮሜ ሀገር ለሆነ ለእግዚአብሔር ሰው #ለቅዱስ_ሙሴ_ለዕረፍታቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከመራክዋና ከእርሱ ጋር ካሉ ሰማዕታት፣ #ከድማቴዎስና_ከምራይስ #ከአራት_መቶ_ሠላሳ_አንድ_ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት አንዱ ለሆነው፤ ሐዋርያት ኮሾሟቸው #ከሰባቱ_ዲያቆናት ውስጥ የተቆጠረ ለሆነ፤ #ኢትዮጵያዊውን_ጃንደረባ_ባኮስን (አቤላክን) ላጠመቀው #ለቅዱስ_ፊሊጶስ_ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።               √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን "ከእግዚአብ
+9
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን "ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ።" መዝ 117 ÷26  🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓 🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓 በግራር ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን በፍኖተ ብርሃን ሰንበት በቀዳማይ ካልዓይ እና ሳልሳይ ክፍል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ ተማሪዎች የእውቀትና ሰርተፍኬት እና የ12 ክፍል ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። 📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸ከሚዲያና ዕቅበተ እምነት ክፍል የምስል ማህደር በጥቂቱ ይህን ይመስላል 📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽 🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥

√ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanz
√ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አጀንዳ አርቃቂ ብፁዓን አባቶችን ሰየመ። **** ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም """""""""""""""""""""""""" አዲስአበባ -ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
+6
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አጀንዳ አርቃቂ ብፁዓን አባቶችን ሰየመ። **** ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም """""""""""""""""""""""""" አዲስአበባ -ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የጥቅምት ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ምልአተ ጉባኤውን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የመክፈቻ መልዕክት ዛሬ ጠዋት መጀመሩ ይታወቃል ። ከቅዱስነታቸው የመክፈቻ መልእክት በኋላም የመወያያ አጀንዳ ቀርጸው የሚያቀርቡ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን ሰይሟል። በዚህም መሰረት፦ ፩ኛ ብፁዕ አቡነ ሔኖክ ፪ኛ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፫ኛ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ፬ኛ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ፭ኛ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ፮ኛ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ፯ኛ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል  በመሆን አጀንዳ የማርቀቅ ተግባራቸውን በማከናወን ላይ ይገኛሉ።የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ የሚያቀርቡትን ረቂቅ አጀንዳ ከመረመረና ማስተካከያ ካደረገበት በኋላ የጸደቀውን አጀንዳ መሰረት በማድረግ በቅደም ተከተል እየተወያየ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨

ስለሆነም ሐዋርያው እንዳለው በውስጣችን ያለው ኃይል አቀጣጥለን ሙሉ በሙሉ መጠቀም እንችል ዘንድ ራሳችንን ክደን ለእግዚአብሔር ክብርና ለቤተክርስቲያኑ ተልእኮ በአንድነት መቆም የግድ ይላል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያለ መከራ አልኖረችም ለወደፊትም ከዚያ የተለየ ዕድል አትጠብቅም፡፡ ለምን ቢባል ጥበበኛው ሰሎሞን እንደነገረን “በእሾኽ መካከል ያበበች የሃይማኖት አበባ” ናትና ነው፡፡ ጌታችንም ስለ ስሜ በሁሉም ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ያሳድዱአችኋል፣ይገርፉአችኋል፣ ይገድሉአችሁማል ብሎ ዕቅጩን ነግሮናል፡፡ ዓለም እንደ ካሁኑ በፊት አሁንም በእሾኽነትዋ ቤተ ክርስቲያንን እየወጋች ነው ታዲያ ከመጽናት በቀር ከኛ ሌላ ምን ይጠበቃል? ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወኤጲስ ቆጶሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!! እኛ ያለንበት የመልክዐ ምድር አቀማመጥ እጅግ ፈታኝ ነው፡፡ ዓለም እኛን ለመጥቀም ሳይሆን ለራሱ ሲል የሚቀራመተው አካባቢ ነው፡፡ ለዚያ ሲባል የደረሰብንም ጫና ምን ያህል እንደሆነ የምንስተው አይደለም እኛም አንድነታችንንና ወንድማማችነታችንን አጽንተን መቆም ባለመቻላችን ለአደጋው ይበልጥ ተጋላጭ ሆነናል፡፡ ሕዝብ ተጐዳ ማለት ቤተክርስቲያን ተጐዳች ማለት እንደሆነ አንርሳው ቤተክርስቲያን ማለት በዋናነት ሕዝበ ክርስቲያን ነውና፡፡ ያለንበት አካባቢ ለልዩ ልዩ ጥቃት የተጋለጠ ሆኖ ሳለ ቤተክርስቲያናችን ለሁለት ሺሕ ዓመታት ያህል ብቻ ለብቻ ሆና በሃይማኖተ ክርስትና መዝለቋ እጅግ የሚያስደንቅ መሆኑን እናስታውስ፡፡ ይህ የሚያሳየው የቀደምት አባቶቻችን ጽንዐ ሃይማኖትና ጥንካሬ ስለሆነ ሳናመሰግናቸው ብናልፍ ትልቅ ኃጢአት ይሆንብናል እነሱን ማመስገንም በቃላት ብቻ አይሆንም፡፡ እነሱ የሰሩትን በመጠበቅና በመድገምም እንጂ ለዚህ ተልእኮ ይህ ጉባኤ ኃላፊነት አለበትና ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ይኖርበታል፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወኤጲስ ቆጶሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!! ከሁኔታዎች በትክክል መገንዘብ እንደሚቻለው ቤተክርስቲያናችን ከሚተቻት ይልቅ የሚወዳት ይበልጣል። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ፈላጊዎቿ ብዙ ናቸው፡፡ ለዚህ ተጠቃሽ የሚሆኑን በሀገር ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ እንደዚሁም በአፍሪካና በላቲን አሜሪካ የሚገኙ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ለነዚህ ሕዝቦች ፈጣንና ዘላቂነት ያለው ግብረ መልስ ከዚህ ጉባኤ ይጠበቃል ይህ በቀጣዮቹ ዓመታት በመሪ ዕቅዱ መሠረት በስፋት የምንሰራው ስራ ይሆናል፡፡ ቤተክርስቲያን በዓሥር ሚሊዮኖች የሚቈጠሩ ተከታዮች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያሏት በመሆኗ የሀብት ዕጥረት ያጋጥማታል ተብሎ አይጠረጠርም፡፡ ምክንያቱም ትልቁ ሀብት ሰው ስለሆነ ሰውን በቃለ ቅዱስ ወንጌል በሚገባ ከገነባች፣ አስተዳደርዋና የሀብት አያያዟ በትክክልና በሓቅ ጠብቃ ለሚገባው የሃይማኖት ተልእኮ ለማዋል የሚያስችል አሰራር ከዘረጋች። ይህንንም በምእመናን አእምሮና ዓይን ከተረጋገጠ እንኳን ለገንዘቡ ለሕይወቱ የማይሳሳ ምእመን እንዳላት ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ታድያ ሀብት ማለት ይህ አይደለምን? አሁን መስራት ያለብንስ ይህ ሀብት በትክክል መጠበቁ ላይ አይደለምን? ይህም በቀጣዩ ዓመት በስፋት የሚሰራበት ይሆናል። የዕቅበተ ንዋይ፣ የዕቅበተ ሃይማኖት፣ የሥልጠናና ትምህርት፣ የገዳማትና ቱሪዝም፣ የምርትና የደን ሀብት፣ የፋይናንሱ ሴክተርና የስብከተ ወንጌሉ ተልእኮ ዘመኑ በሚጠይቀው የአመራርና የአሰራር ጥበብና ስልት እየታገዝን፣ ሕዝባችንንም ከጎናችን እያሰለፍን የምንሰራበት ጊዜው አሁን ነው፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወኤጲስ ቆጶሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!! ለጀመርናቸውና ለወደፊት ለምንጀምራቸው የመልካም አስተዳደርና የልማት ስራዎች ዋስትና እንደሚያስፈልጋቸው እሙን ነው፡፡ የስራዎቻችን ዋስትናም በሀገርና በቤተክርስቲያን ፍጹም የሆነ ሰላምና አንድነት መኖር ነው፡፡ በመሆኑም የጠማንን ሰላምና አንድነት መልሶ ለማምጣት የቤተክርስቲያን ኃይል የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ሆኖም የቤተክርስቲያን የሰላም ጉዞ ከማንኛውም ወገንተኝነት በጸዳ፣ ማእከሉና ዓላማው የሀገርና የቤተክርስቲያንን አንድነት ብቻ መሠረት ያደረገ መሆን ይገባዋል። ከዚህ አንጻር በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በቤተክርስቲያናችንም እንከን የለሽ አንድነት እንዲረጋገጥ በብርቱ መስራት ይኖርብናል፡፡ አኲርፈው የተለዩትን በጠባይ ወደ እኛ እናምጣቸው እኛም ኲርፊያን ከሚያስከትል ድርጊት እንራቅ በአንድነት፣ በእኩልነትና በጋራ ሆነን ታላቋን ቤተክርስቲያን እንሰብስብ፣ እናገልግል፣ እንምራ፣ እንጠብቅ፡፡ ለዚህም ሙሉ ዝግጅት እናድርግ የዕለት ተዕለት ስራችን የቤተ ክርስቲያንን ጭንቀት የሚያቃልል ይሁን ይህ ከሆነ ቤተ ክርስቲያንን ያለምንም ጥርጥር በዕድገት ጐዳና ወደፊት እናሻግራለን፡፡ በመጨረሻም የታላቋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን መርምሮ ገምግሞና አጥንቶ ችግር ፈቺ ውሳኔን የመስጠት ኃላፊነት ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተከፈተ መሆኑን በቤተክርቲያን ስም እናበስራለን፡፡ እግዚአብሔር የተባረከና የተቀደሰ ጉባኤ ያድርግልን! እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!አሜን፡፡ አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ምንጭ: የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርከ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! •ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ •ብፁ
+2
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርከ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! •ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት    ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ    ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ •ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና    ጸሐፊ እና በሰሜን አሜሪካ የኒዮርክ እና    አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ •ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ     አባላት፤ ሁሉንም ጠብቆ የሚያስጠብቅ እግዚአብሔር አምላካችን ከተሠማራንበት የጥበቃ ስፍራችን አሰባስቦ በደሙ ስለዋጃት ቅድስት ቤተክርስቲያን እንድንመክር ስለፈቀደልን ምስጋና ለእሱ እናቀርባለን፣ እናንተም እንኳን ደኅና መጣችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡ “ወዘእንበለዝ ብዙኅ ባዕድ ዘረከበኒ ኲሎ አሚረ እንዘ እኄሊ ቤተ ክርስቲያናት፡- የቀረውንም ነገር ሳልቈጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሐሳብ ነው” (2ኛ ቆሮ 11፦28) ከዚህ ጥቅስ እንደምናስተውለው ከስራ ሁሉ የሚያስጨንቅ ተግባር የቤተ ክርስቲያን ነገር እንደሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሚገባ አስቀምጦአል፡፡ እርግጥ ነው ሌሎች የሚያስጨንቁ ችግሮች በዓለም አሉ@ ግን ሌሎቹ ለጊዜውም ቢሆን ባላቸው ማቴሪያላዊ ኃይል ማስታገሥ ይችላሉ፡፡ ቤተክርስቲያን ግን ከመንፈስ ቅዱስ ከተሰጠ ረቂቅ ኃይለ መዊዕ በቀር ሌላ ማቴሪያላዊ ኃይል የላትም አይፈቀድላትምም፡፡ ይሁን እንጂ ከኃይል ሁሉ የበለጠ ኃይል እንዳለን ጌታችን ነግሮናል  እኛም እናውቀዋለን፡፡ ነገር ግን የኛ ድክመት ኃይሉ እንደሚፈለገው እንዳይሰራ ያደርገዋል  ይህም እውነት ነው የተሰጠን ኃይል በእኛ ድክመት የተቀዛቀዘ ቢመስልም የማይሸነፍ ነውና ኃይላችንን አውቀን ካልተጠቀምንበት እኛንም ጭምር ቀጥቶ የበላይ አሸናፊነቱን ያረጋግጣል  ይህም የታየ እውነት ነው፡፡

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ጥቅምት ፲፪ (12) ቀን። እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት ለአንዱ ለሆነው #ለወንጌላዊ_ለቅዱስ_ማቴዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕ
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝               ጥቅምት ፲፪ (12) ቀን። እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት ለአንዱ ለሆነው #ለወንጌላዊ_ለቅዱስ_ማቴዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።  እንኳን #ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል #ቅዱስ_ዳዊትን በሳኦል ፈንታ እንዲሾመው ለሳሙኤል ለነገረበትና #ዳዊት_ጎልያድን_በሚገድልበትን ልዩ  ኃይል እዲሰጠው ለረዳበት ለወራዊ መታሰቢያ በዓል፣ #ለእስክንድርያ_ዐሥራ_ሁለተኛ ለሆነ ሊቀ ጳጳሳት ለንጹሕ ለድንግል ከሚስቱ በአንድነት ሲኖር ለ48 ዓመታት የጠባይን ፍላጎት ድል ለነሳ፤ ባሕረ ሀሳብ ለቀመረ (ላዘጋጀ) ለታላቁ አባት #ለአባ_ድሜጥሮስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከጻድቃን_ከጴጥሮስና ከተወራራሽ #ጳውሎስ_ከዲዮናስዮስ_ከያዕቆብ_ከአቡጥፋ፣ #ከቴዎድሮስና_ከሚናስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። #በዚች_ዕለት_የመላእክት_አለቃ የከበረ መልአክ #የቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም እየተካሄደ ነው የጥቅምት 2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ
+2
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም እየተካሄደ ነው የጥቅምት 2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመካሄድ ላይ ይገኛል። ©EOTCTV #EOTC_ETHIOPIA √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨

ለሁሉም አህጉረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጥ ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ መመሪያ ስለማስተላለፍ በሚል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የተጻፈ ደብዳቤ ለሁሉም አ
ለሁሉም አህጉረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጥ ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ መመሪያ ስለማስተላለፍ በሚል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የተጻፈ ደብዳቤ ለሁሉም አህጉረ ስብከቶች የተጻፈ ሲሆን ሁሉም በሥራቸው ለሚገኙ ገዳማትና አድባራት መመሪያውን እንዲያሰራጩና በእቅድ ውስጥ አድርገው እንዲከታተሉ በማሳሰብ የሚከተሉትን ዋና ዋና ሐሳቦች ተግባራዊ እንዲያደርጉ መመሪያው ተላልፏል። ይኸውም፦ ፩_ በሁሉም ገዳማት እና አድባራት ለሰ/ት/ቤቶች  የመምህራን ስልጠና እንዲሰጥና የመምህራን ቅጥርና ምደባ እንዲመደብ ፤ ፪_ ለሰ/ት/ቤቶች ከመማሪያ ቦታ ማመቻቸትና በቂ ቦታ በማዘጋጀት የመማሪያ ክፍሎች እንዲገነቡ እንዲደረግ ፤ ፫_ ለሥርዓተ ትምህርቱ ትግበራ በጀት በመመደብ መጻሕፍት ግዢ መፈጸም ፤ ፬_ ለትግበራው አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት እና ምዕመናን ልጆቻቸውን ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲልኩ በየዐውደ ምህረቱ በመቀስቀስና ሥርዓተ ትምህርቱን የማስታወቅ ሥራ በመሥራት ለተግባራዊነቱ የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤያቱ ዕቅድ ውስጥ በማስገባት እንዲሠሩ መመሪያው ተላልፏል። ሁሉም ሰንበት ት/ቤት በቀጣይ በሀገረ ስብከቶች ወደአጥቢያ የሚወርደውን መመርያ ደብዳቤውን ተከትሎ አፈጻጸሙን ከአንድነት መዋቅሩ ጋር በመናበብ ተፈጻሚነቱን በየአጥቢያው እንዲተገበር ክትትል እና ሪፖርት እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ያሳስባል።