ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Открыть в Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Больше603
Подписчики
-324 часа
-87 дней
-1730 дней
Архив постов
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢
በሰንበት ትምህርት ቤታችን የተዘጋጀው የጉዞ መርሐግብር ለ ግንቦት 18 የተዘዋወረ በመሆኑ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ያልተመዘገባችሁ አባላት እንድትመዘገቡ እንዲሁም ለወንድም ለእህቶቻችሁ እንድታሳውቁ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!!!🙏🙏🙏
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ሚያዝያ ፱ (9) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ለዘጠኝ ዓመት በዓባይ ባሕር ውስጥ በራሳቸው ተዘቅዝቀው በመቆም ስለ ኢትዮጵያውያ ሕዝብ ለጸለዩ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_እስትፋሰ_ክርስቶስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ፦ የልደታቸው (የተወለዱበት) ቦታ ዳውንት ፀወን ዓባይ ይባላል። በአካባቢውም በገዳሙ አንፃር በሰሜን በኩል የእናታቸው አገር ደብረ ድባ የቄርሎስ ቦታ ይባላል የአባታቸውም አገር የእግዚአብሔር አብ ደብር አጠገብ ዳውንት ወይም ደብረ አስጋጅ ይባላል።
❤ አባታቸው ስም ቅዱስ መልአከ ምክሩ ሲሆን የእናታቸው ስም ቅድስት ወለተ ማርያም ይባላሉ።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለዐቢይ_ጾም_ስድስተኛ_ሳምንት_ለገብር_ኄር እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የገብር_ኄር_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "መኑ ውእቱ ገብር ኄር ወምዕመን ዘይረክቦ እግዚኡ በምግባረ ሠናይ ወይሠይሞ ዲበ ኵሉ ንዋዩ ካዕበ ይቤሎ እግዚአብሔር ገብር ኄር ወምዕመን ዘበውኁድ ምዕመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ ባዕ ውስተ ፍሥሓሁ ለእግዚእከ"። ትርጉም፦ በመልካም ሥራ ጌታው ያገኘው በጎ ታማኝ አገልጋይ ማነው? በንብረቱ ላይ ሁሉ የሚሾመው ታማኝ በጎ አገልጋይ ማነው? ዳግመኛም እግዚአብሔር አንተ በጎ ታማኝ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ።
✝ ✝ ✝
❤ #ገብር_ኄር፦ ማለት ቸር አገልጋይ ማለት ነው። ገብር ኄር ተብሎ በወንጌል የሚነገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ሲያስተምር ካስተማረቸው ትምህርት አንዱ ነው። እንዲህ ሲል ይጀምራል፦ ወደ ሌላ ሀገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ገንዘብ እንደሰጣቸው እንዲሁ ይሆናል ።
❤ ለእያንዳዱም እንደያቅማቸው ለአንዱ አምስት መክሊት፤ ለአንዱም ሁለት መክሊት፤ ለአንዱም አንድ መክሊት አድርጎ ሰጣቸውእና ወደ ሌላ ሀገር ወዲያው ሄደ። አምስት የተቀበለውም ነግዶ ሠርቶ አምስት ሌላ መክሊት አተረፈ፤ ሁለት የተቀበለውም እንደዛው ሁለት መክሊት አተረፈ፤ አንድ የተቀበለው ግን ምድር ቆፍሮ የጌታውን ገንዘብ ቀበረ ።
❤ ከብዙ ዘመን በኀላ የእኒዚያ ባሮቾ ጌታ መጥቶ ተቆጣጣረቸው የሰጠዋችሁስ ገንዘብ አላቸው ።
ባለአምስቱም፤ "ጌታ ሆይ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር ይኸው ሌላ አምስት መክሊት አትሪፊያለው" ብሎ መክሊቱን አስረከበ ጌታውም "አንተ መልካም ተማኝ ባሪያ በጥቂቱ የታመንክ በብዙ እሾምሃለው ወደ ጌታህ ደስታ ግባ" አለው። ሁለተኛውም "ጌታ ሆይ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር ሌላ ሁለት አተረፍኩ" ብሎ መክሊቱን አስረከበ ጌታውም "አንተ መልካም ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ የታመንክ በብዙ እሾምሃለው ወደ ጌታህ ደስታ ግባ" አለው። ባለአንዱም መክሊት ወደ ጌታው ቀረበ እንዲህም አለ "አንተ ካልዘራኅበት የምታጭድ ካልበተንክበት የምትሰበሰብ ጨካኝ ሰው መሆንክን አውቃለሁ ፈርቼም የሰጠኸኝን መክሊት ቀበርኩት እነሆ መክልቲህን" ብሎ ምንም ሳያተርፍ ሰጠው።
ጌታውም "አንተ ክፉ እና ኀኬተኛ ባሪያ እኔ ካልዘራውበት የማጭድ ካልበተንኩት የምሰበስብ መሆኔን ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበረ እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር መጥቼ እወስድ ነበር ፣ ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አስር ላለውም ጨምሩለት ላለው ይሰጠዋል ( ይጨመርልታል ) ለሌለው ያለውም ያለው ይወሰድበታል የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል" አለው።
❤ መክሊት የተባለ ጸጋ ስጦታ ሲሆን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታ ሰጥቶናል፡፡ በተሰጠንም ስጦታ ልናገለግልበት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪ መክሊት ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ የሰማናትን ቃለ እግዚአብሔር ለሌላው ማሰማት ይገባናል ፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ማሰማቱ ብቻ ነው፡፡ በልቦናው አድሮ ሥራ የሚሠራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡
❤ ወዳጆቼ ስንቶቻችን የተሰጠንን መክሊት ቀብረን ይሆን? ይህ ሰው በመፍራት እና ጌታውን ባለማመን የተሰጠውን መክሊት ቀበረ ዛሬም እኮ እኛ ከክርስቶስ የተሰጠንን ፍቅር እና አንድነት ቀብረነዋል ዛሬም እኮ ሃይማኖታችንን በፍርሃት ባለመመስከር ቀብረነዋል ዛሬም እኮ እኛ ከፈጣሪ ያገኘነውን በጎነት ደግነት ቀብረነዋል በዘመናችን ከፈጣሪ የተቀበል ናቸው ፤መክሊት ተቀብረው እኮ ነው ሰላም የጠፋው ሰው እንደ በግ የሚታረደው!።
❤ ወዳጆቼ ማነው መክሊቱን ያልቀበረ አምስት ተሰጥቶት አምስት ያተረፈ ሁለት ተሰጥቶት ሁለት ያተረፈ ይኖር ይሆን ጌታው ሲመጣ "መልካም ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ የታመንክ በብዙ እሾምሀለው ወደ ጌታህ ደስታ ግባ የሚባል ማን ይሆን? ሁላችንም የቀበርነውን መክሊት አለ አውጥተን እናትርፍበት ካህኑ እንደ ክህነቱ መምህሩ እንደ መምህርነቱ ዘማሪው እንደ ዘማሪነቱ ምዕመኑ እንደ አማኝነቱ ሁሉም መክሊቱን ከቀበረበት አወጥቶ በተሰጠው መክሊት ልክ ያትርፍበት አለበለዚያ የመክሊቱ ባለቤት ሲመጣ መልሳችን ምን ሊሆን? ፈርቼህ በምድር ቀበረሁት የሰጠኸኝ መክሊት ይኸው ውሰድ ይኽንን ከማለት ፈጣሪ ይሰውረን! አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ። ወሕግከኒ በማእከለ ከርሥየ። ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበረ ዓቢይ"። መዝ 39፥8-9። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 2፥1-16፣ 1ኛ ጴጥ 5፥1-12 እና የሐዋ ሥራ 1፥6-9። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥14-31። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአባታችን ቅዱስ አዳም፣ እናቻችን ቅድስት ሔዋንና የግብጻዊቷ የማርያም የዕረፍት መታሰቢያ በዓል፣ ዕለተ ሰንበት (ገብረ ኄር)ና የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣
📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌
ውድ የፍኖተ ብርሀን ሰ/ት/ቤት አባላት ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
እንደሚታወቀው በደብራችን ህንፃ ቤተክርስትያን ተጀምሯለ። እናም በቀን 5/8/2016 በእለተ ቅዳሜ የአርማታ ሙሌት ስለሚደረግ ከቅዳሴ በኃላ ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ አካፋ ...ወዘተ ይዘን በመምጣት የበረከቱ ተካፋይ እንሁን።
ማሳሰቢያ :- በእለቱ የሚመቻችሁ አባላት መገኘት ግዴታ ነው!!!
🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ #ሚያዝያ ፪ (2) ቀን።
❤ እንኳን #ለቅዱስ_ቃይናን_ልጅ_ለቅዱስ_መላልኤል ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ፊት እንደ ውሻ የሚመስል የሆነ በጸሎቱ ታላላቅ ተዓራትን አድርጎ አስተምሮ ሊይዞት የመጡትን ወታደሮችና ሊያስቱት የመጡ ሁለት አመንዝራ ሴቶችን #በእግዚአብሔር_አምነው ሰማዕትነት እንዲቀበሉ ላደረገ #ለቅዱስ_ክርስትፎሮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና ከሐሊባ አገር ሰው ለሆነ #ለከበረ_አባት_ለቅዱስ_ስምዖን ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡት፦ #በቅዱስ_ክርስትፎሮስ በትምህርቱና በሚታደርገው ተዓምራት አምነው ሰማዕትነት ከተቀበሉ #ከሁለት_ሴቶች_ከሁለት_መቶ_ወታደሮችና ከሌሎች ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_መላልኤል፦ መቶ ስልሳ አምስት ዓመት ኖረ ቅዱስ ያሬድን ወለደው። ቅዱስ መላልኤልም ያሬድ ከወለደው በኋላ ሰባት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
❤ የቅዱስ መላልኤል መላ ዘመኑ ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ነው። ይኸውም ሚያዝያ ሁለት ቀን በእሑድ ዕለት ሞተ በማከማቻም ውስጥ ቀበሩት። የፈጣሪው በረከት በላያችን ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ክርስትፎሮስ፦ ይህም ቅዱስ ሰውን ይበሉ ከነበሩ ሰዎች አገር ነው በጦርነትም ማረኩት አባቱም በሐዋርያ ቅዱስ ማትያስ እጅ ያመነ ነው።
❤ በማረኩትም ጊዜ ቋንቋቸውን አያውቅም ነበር የክብር ባለቤት ወደሆነ እግዚአብሔርም ማለደ ቋንቋቸውንም ገልጦለት እንደርሳቸው ተናገረ የክርስቲያን ወገኖችን የሚያሠቃዩአቸውንም ገሠጻቸው የጦር ሠራዊቱንም የሚመራ መኰንን ጽኑዕ ግርፋትን ገረፈው። ቅዱስ ክርትፎሮስም
መኰንኑን "የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዙ ኃይሉን ባትይዘኝና ባታስታግሠኝ አንተና ሠራዊትህ ከእኔ እጅ ባልዳናችሁ ነበር" አለው። መኰንኑም ስለ ርሱ ወደ ንጉሥ ላከ ከእርሱ የሆነውንም ነገረው።
❤ ንጉሡም ወደ ርሱ እንዲያመጡት ሁለኀት መቶ ወታደሮች ላከለት እርሱም ያለ መፍራት ያለ ማፈግፈግ አብሮቸው ሔደ። በእጁ በትር ነበረች በላይዋ በጸለየ ጊዜ በቀለችና አበበች። እነዚያ ወታደሮች ተርበው የሚበሉት እንጀራ በአጡ ጊዜ ቅዱስ ክርስትፎሮስ ጸለየ በእነርሱ ዘንድ እንጀራ በዝቶ ተትረፈረፈ እጅግም አድንቀው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ወደ አንጾኪያም ደርሰው በሊቀ ጳጳሳት አባ ጳውሎስ እጅ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቁ።
❤ ወደ ንጉሡም ፊት በደረሱ ጊዜ ንጉሥ ዳኬዎስ ሊያስፈራውና ሊሸነግለው ጀመረ ደግሞ እጅግ መልከ መልካም የሆኑ ሁለት አመንዝራ ሴቶችን ወደርሱ ሰደደ እነርሳቸው እንደሚያስቱትና በኃጢአት እንደሚጥሉት አስቧልና። እርሱ ግን ገሠጻቸው አስተማራቸውም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በደማቸው ምስክር ሆኑ። እንዲሁም እነዚያ ሁለት መቶ ወታደሮች በንጉሡ ፊት በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ራሶቻቸውንም በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥት ሰማያት ተቀበሉ።
❤ ቅዱስ ክርስትፎሮስም ንጉሡን "አንተ የሰይጣንን ሥራ የምትቀበል ማደሪያው የሆንክ" ብሎ ዘለፈው ንጉሡም ተቆጥቶ በትልቅ ብረት ምጣድ ውስጥ እንዲጨምሩትና ከበታቹ እሳትን እንዲያነዱ አዘዘ። እንዲሁም አደረጉበት ነገር ግን ከጉዳት እንዳሰቡት ምንም የደረሰበት የለም። ጤነኛ ሁኖ ሰዎችን አስተማራቸው እንጂ። እጅግም አድንቀው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ቅዱሱንም ከእርሷ ሊአወጡት ወደዚያች ብረት ምጣድ ቀረቡ ንጉሡም አንገታቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧቸው አዘዘ የሕይወት አክሊልንም ተቀበሉ።
❤ ከዚያም በኋላ ታላቅ ደንጊያ በአንገቱ አንጠልጥለው ከጥልቅ ጒድጓድ እንዲጨምሩት ንጉሡ አዘዘ በጨመሩትም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በጤንነት አወጣው። ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ አንገቱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ ንጉሡ አዘዘ። ቅዱሱም በእግዚአብሔር መንግሥት የድል አክሊል ተቀዳጀ። ጸሎቱ በረከቱ ከእኛ ጋር ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ2 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለክርስትፎሮስ_ዘተፄወወ_በጸብእ። በውስተ ሀገሩ ዘእምነ በትምእምርተ ማትያስ ረድእ። በህየ ተቀትለ በእንተ ክርስቶስ እግዚእ። ወሰላም ለእለ ሞቱ ምስሌሁ በስንዕ። ክልኤቱ አንስት ወአምዓት ሰብእ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ(አርኬ) #የሚያዝያ_2።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወዓመቲከኒ ዘኢየኀልቅ። ደቂቀ አግብርቲከ ይነብርዋ። ወዘርዖሙኒ ለዓለም ይጸንዕ"። መዝ 101፥27-28። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 11፥13-25፣ ያዕ 3፥1-13 እና የሐዋ ሥራ 14፥11-19። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 15፥21-29። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው።መልካም የጾም ጊዜና በዓል። በሁላችንም ይሁንልን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለስልዋኖስ_ቢጸ_መላእክት_ዘኮነ። ፍትወተ ዓለም እምልቡ እስመ ተመነነ። እምአመ ርዕየ ጽልመተ ኃጥአን ደይነ። በቆብዐ ርእሱ ገጾ ከደነ። ህየንተ በዘምድር ይርአይ በሰማይ ብርሃን"።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ "#የተባረከ_የሚያዝያ_ወር_ቀኑ_ዐሥራ_ሦስት ሰዓት ሲሆን ከዚያም ይጨምራል" ።
❤ #ሚያዝያ ፩ (1) ቀን።
❤ እንኳን #ለካህኑ_ለቅዱስ_አሮን (ለሊቀ ነቢያት #ለቅዱስ_ሙሴ_ወንድሙ) ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ለከበረ አባት የሲዖል ሥቃይ አይቶ "ወደዘላለም ጨለማ ሊወስዱኝ ዛሬ የዚህን የኃላፊውን ዓለም ብርሃን ማየት አልሻም" እያለ ፊቱን በቆብ ሽፍኖ ዕድሜው ሙሉ ሲያለቅስ ለነበረ #ለአባ_ስልዋኖስ ለዕረፍት በዓልና #ለቅድስት_መጥሮንያ_ለዕረፍቱ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_አበከረዙንም ጋር በሰማዕትነት ከዐረፉ #ከቅዱስ_ዮስጦስና_ከሚስቱ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን በእስክንድርያ ከተማ በሚገኝ በግብጻውያን መጽሐፍ እንደ ተጻፈ በላዕላይ ግብጽ ያለ ግብጻዊውም እንደተጻፈ ለእንበረም ልጅ #ለቅዱስ_ሙሴ_ወንድሙ_ለሆነ_የካህኑ_ቅዱስ_አሮን የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ ይላሉ።
❤ በኦሪቱ መጽሐፍ የተጻፈው ግን እስራኤል ከግብጽ ከወጡ በሁለተኛው ወር በሦስተኛው ቀን ዐረፈ ይላል። ይኸውም ግንቦት ስምንት ነበር የእስራኤል ወሮች በጨረቃ እየተቈጠሩ ዓመቱን ስለሚዞሩ በዚያች ዓመት ሚያዝያ አንድ ቀን ሁኖ ስለተገኘ።
❤ በእኛ(በኢ.ኦ.ተ) ዘንድ ግን የኦሪት ዘኊልቊ መጽሐፍ በአምስተኛው ወር መባቻ ስለሚል መታሰቢያውን ነሐሴ አንድ ቀን እናደርጋለን።
+ + +
❤ ካህኑ ቅዱስ አሮን፦ ይህም ሰው የነቢያት አለቃ ለኦሪት ሕግ መምህር ለሆነ ለሙሴ ለነቢዪት ማርያምም ወንድም ነው እርሱም ከሌዊ ነገድ ነው።
❤ እግዚአብሔርም በግብጽ ምድር ብዙ አስደናቂ ተአምራትን በእጆቹ አደረገ። እግዚአብሔርም እርሱንና ልጆቹን መርጦ ካህናቶቹ አድርጎ ከእስራኤል ልጆች ከገንዘባቸውና ከመሥዋዕታቸውም ዓሥራትን ሰጣቸው። የቆሬም ልጆች በጠላትነት በተነሡበት ጊዜ እግዚአብሔር ፈርዶ አጠፋቸው ምድርንም አዘዛት አፍዋንም ከፍታ ዋጠቻቸው።
❤ በበጎ ተጋድሎውና የኦሪትንም ሕግ በመጠበቅ እግዚአብሔርን ከአገለገለ በኋላ የክብር ባለቤት ወደሆነ እግዚአብሔር ሔደ። የካህኑ የቅዱስ አሮን ጸሎቱ በረከቱ ከእኛ ጋር ለዘላለም ትኑር አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ስልዋኖስ፦ ይህም አባት በአስቄጥስ ገዳም ከከበረ አባ መቃርስ ዘንድ በታናሽነቱ መነኰሰ በጠባብ መንገድ ሁሉ ተጋደለ በብዙ ጾምና ጸሎት በመትጋት በትሕትና በፍቅር ተወስኖ ኖረ ታላቅ አባትም ሆነ።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችንም አምላካዊ ራእይን ይገልጽልት ነበር ድንቅ የሆኑ ነገሮችንም ይነግረዋል። ይህም እንዲህ ነው በአንዲት ዕለት ልቡ ተመስጦ በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቶ ብዙ ጊዜ ቆየ በዚያም በኋላ ነቅቶ ራሱን ቀና አደረገ። ከእርሱ ዘንድ ያሉ ወንድሞች መነኰሳትም በእርሱ ላይ የደረሰበትን ይነግራቸው ዘንድ ለመኑት ዝም ብሎ መሪር ልቅሶ ያለቅሳል እንጂ ሊነግራቸው አልወደደም። ከእርሱ የሆነውን ያስረዳቸው ዘንድ ግድ ባሉት ጊዜ እንዲህ አላቸው "ተድላ ወዳለበት ገነት አውጥተውኝ በዚያ የጻድቃንን መኖሪያ አየሁ ደግሞ የሥቃይ ቦታዎችንም። ሁለተኛም ብዙዎች መነኰሳትን ወደ ገሀነም ብዙዎች ምዕመናን ወደ መንግሥተ ሰማያት ሲወስዷቸው አየሁ እንግዲህ እኔ ለነፍሴ የማላለቅስ ለምድንድነው" አላቸው። ከዚያች ቀንም ጀምሮ "በኋላ ወደዘላለም ጨለማ ሊወስዱኝ ዛሬ የዚህን የኃላፊውን ዓለም ብርሃን ማየት አልሻም" እያለ ፊቱን በቆብ ሽፍኖ የሚያለቅስ ሆነ።
❤ ይህም አባት በመንፈሳዊ ሥራ የተጠመደ ሆነ ደቀ መዛሙርቱንም ለምግባቸው የሚሆን ሥራን ከመሥራት እንዳያቋርጡ ከዕለት ምግባቸው የሚተርፈውንም እንዲመጸውቱ ያዛቸዋል።
❤ በአንዲት ቀንም አንድ ታካች የሆነ መነኰስ ወደርሱ መጣ ሽማግሌውን አባትና ደቀ መዛሙርቱን ሲሠሩ አይቷቸው "ለኃላፊ ምግብ ትሠራላችሁ ትደክማላችሁ የዘላለም ሕይወት ለሚሆን ምግብ ሥሩ ድከሙ እንጂ ይህ በከበረ ወንጌል የተጻፈ አይደለምን "ማርያምም የማይቀሟትን በጎ ዕድል ትምህርትን አንደመረጠች" ብሎ ጠቀሰ። ሽማግሎው አባ ስልዋኖስም እንዲህ ሲናገር በሰማው ጊዜ ደቀ መዝሙሩን እንዲህ ሲል አዘዘው "ይህን መነኰስ ከእንግዳ ማሳረፊያ ቤት አስገብተህ የሚያነበው መጽሐፍ ስጠው በሩንም በላዩ ዝጋ በእርሱ ዘንድም ለመብል የሚሆን ምንም ምን አትተው "። ረድኡም ሽማግሌው መምህሩ እንዳዘዘው አደረገ። ዘጠኝ ሰዓትም ሲሆን መነኰሳቱ ተሰበሰቡ ከሽማግሌው አባትም ጋር ጸሎት አድርገው ምግባቸውን ተመገቡ። ያን እንግዳ መነኰስ ግን አልጠሩትም እርሱም ቢጠሩኝ ብሎ ወደ ደጃፍ እየተመለከተ ይጠብቅ ነበር። በረኃብም በተቃጠለ ጊዜ ከበዓቱ ወጥቶ ወደ አባ ስልዋኖስ ሒዶ "አባቴ ሆይ መነኰሳቱ ራታቸውን በሉን" አለው ሽግሌውም "አዎን በሉ" ብሎ መለሰለት። ሁለተኛ ደግሞ "እኔ እንግዳ ስሆን ለምን አልጠራችሁኝም" አለ የከበረ አባት ስልዋኖስም "አንተማ ሥጋዊ መብል የማትሻ መንፈሳዊ ሰው ነህ በጎ ዕድልን ስለመረጥክ እኛ ግን ሥጋዊያን ሰዎች ለሥጋዊ መብል የምንሠራ የምንደክም ነን ስለዚህም ለምግባች የሚሆነውን በእጃችን እንሠራለን" ብሎ መለሰለት። ያ መነኰስም በንግግሩ እንደበደለ አወቀ። አባ ስልዋኖስንም "አባቴ ሆይ እኔ በድያለሁና ይቅር በለኝ" ብሎ ሰገደለት።
❤ አባ ስልዋኖስም " ማርታ በመሥራት እንደ ደከመች እንድከም እንሥራ ከማርያም ይልቅ ማርታ የተዘጋጀች ሁናለችና" ብሎ መለሰለት። ያ ታካች የነበረ መነኰስም በዚህ አባት ትምህርት ተመክሮና ተገሥጾ ሁልጊዜ የሚሠራና ከእርሱ የሚተርፈውንም ለድኆች የሚመጸውት ሆነ።
❤ ይህም አባት ስለ መንፈሳዊ ተጋድሎ ጥቅም ያላቸው ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ።
❤ ዕድሜውም በመልካም ሽምግልና በተፈጸመ ጊዜ የሚያርፍባትን ሰዓት እግዚአብሔር ነገሮት በእርሱ አቅራቢያ ያሉ መነኰሳትን ጠርቶ ከእርሳቸው በረከትን ተቀበለ። በጸሎታቸውም እንዲያስቡት ለመናቸው እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲያስባቸው ለመኑት እርስበርሳቸውም ተሰነባበተው በፍቅር በሰላም ሚያዝያ1 ዐረፈ። የአባ ስልዋኖስ ጸሎቱ በረከቱ ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን ደግሞ በላይኛው ግብጽ ያሉ ዐረቦች ተሰብሰበው በአስቄጥስ ያሉ አድባራትናንና ገዳማትን የአባ መቃርስንም ቤተ ክርስቲያን ከበቡ በአድባራቱና በገዳማቱ ያለውንም ዕቃ ሁሉ ማረኩ። መነኰሳትም ተሰበሰቡ በከበረ አባቶችም ስም ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ማለዱ።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚያን ዓረቦች አስደግጦ አሳደዳቸው ያንጊዜም ማንም የተከተላቸው ሳይኖር ድል ሁነው ሸሹ። ከክብር ባለቤት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በቀር ማንም የተከተላቸው ሳይኖር ነው። ይቅር ብሏቸዋልና ጌታችንን አመሰገኑት ለእርሱም ክብር ምስጋና ገንዘቡ ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ1 ስንክሳር።
ደብረ ዘይት፡- ዳግም ምጽአት
ዘመነ ሥጋዌ የጌታችን መገለጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመለከትንበት፣ ይህም ከሰማያት ወርዶ እኛን ለማዳን ከንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው በመሆን ዓለምን ያዳነበት ነው፡፡ እርሱ እንደ ሰው ተወልዶ፣ እንደ ሕፃናት በጨርቅ ተጠቅልሎ፣ ጡት ጠብቶ፣ በየጥቂቱ አድጎ፣ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ፣ በእግር ተመላልሶ፣ እንደ ሰው ተርቦና ተጠምቶ፣ ኀዘን መከራን ተቀብሎ በፍጹም ፍቅሩ አድኖናል፡፡
ፈውሰ ነፍስ በሆኑት ትምህርቶቹ ዓለምን አጣፍቶ፣ አዳኝ በሆኑት እጆቹ ልምሾዎችን፣ ድዊዎችንና አንካሶችን አድኖ፣ ጎባጣን አቅንቶ፣ የዕውራንን ዓይን አብርቷል፡፡ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ መሆኑንም በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቀ መለኮት እጅ ተጠምቆ አስመስክራል፡፡ ብርሃነ መለኮቱ በታየበት በደብረ ታቦር ተራራም አምላክነቱን ገልጧል፡፡ (ማቴ.፫፥፲፫-፲፯፣፲፯፥፩-፰)
ይህን ሁሉ ያደረገው ሰዎች አምላክነቱን አውቀን፣ ከሰማየ ሰማያት የወረደውና መከራን ተቀብሎ በመስቀል ላይ የሞተው ለእኛ ድኅነት መሆኑን እንዲሁም ድንቅ ሥራውን የፈጸመበት ይህን ጥበቡን ተረድቶና፣ የእጁን ሥራ፣ የቃሉን ተእምራት ያመነውን ሁሉም እንደሚድነን ሲያበስረን ነው፡፡ በተጓዳኝም በመዋዕለ ስብከቱ ስለ ዳግም ምጽአቱና ምልክቶቹ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በዝርዝር በደቀ መዛምርቱ በኩል አሳውቆናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ (ማር.፲፫፥፫-፴፯)
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፳፯ (27) ቀን።
❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላካችንና_ለመድኀኒታችን፤ #ለፈጣሪያችንና_ለአዳኛችን_መድኃኔዓለም ለጥንተ ስቅለት መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል፣ ከአዳም ቀድሞ ገነት ለገባው #ለቅዱስ_ጥጦስ (ፈያታይ ዘየማን) ገነት ለገባበት፣ ጌታችን ለገነዙት ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ለመታሰቢያ በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
❤ በዚችም ቀን የክቡር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ።
❤ ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳይለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር። እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋራ አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደሲኦል ወረደች።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፳፮ (26) ቀን።
❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካችን #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ደቀ የመዛሙርቱን እግር ላጠበበትና፣ #የሐዲስ_ኪዳንን_የቊርባን_ሥርዓት_ለመሰረተበት (ለጥንት ጸሎተ ሐሙስ) ና ለከበረችና ለተመሰገነች ለድንግሊቱ ከዘጠኛ ዓመቷ ጀምሮ ስትጋደል ለኖረች፤ ዐቢይ ጾም ምን ሳትባለ ትጾም ለነበረች #ለቅድስት_ኢዮጰራቅስያ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከቅድስት_ኢዮጰራቅስያ_ጓደኛ (ከመጋቢዋ)ና #ከእመ_ምኔቷ ከዕረፍታቸው መታሰቢያና #ከቅዱስ_ፍርፍርዮስ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ዕለት #የክብር_ባለቤት_ጌታችን_የደቀ_መዛሙርቱን_እግር_አጠበ እንዲህም አላቸው "እናንተም ለባልንጀሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉ"።
❤ ደግሞ #የሐዲስ_ኪዳንን_የቊርባን_ሥርዓት አሳያቸው። አሁንም በዚች ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችንን ለአይሁድ ይሁዳ አሳልፎ ሰጠው። ነቢያት ትንቢት እንደተናገሩ የሽያጩን ዋጋ ሠላሳ ብር ተቀበለ። ይቅርታው ቸርነቱ ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፳፭ (25) ቀን።
❤ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት ለአንዱ ጌታችንም በአገረ ናይን የመበለቲቱን ልጅ በአስነሣው ጊዜ አይቶ ከአይሁድነት #በኢየሱስ_ክርስቶስ_አምኖ ለተከተለው ለከበረና ለተመሰገነ #ለሐዋርያ_ለቅዱስ_አንሲፎሮስ ለዕረፍት በዓልና #ለዘመነ_ሐጋይ(በጋ) መውጫ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሐዋርያ_ቅዱስ_አንሲፎሮስ፦ ይህም ከእስራኤል ልጆች ከብንያም ነገድ ነው። ወላጆቹም የኦሪትን ሕግ የሚጠብቁ ናቸው። እርሱም ሥራዎቹን በአየ ጊዜ ትምህርቶቹንም በሰማ ጊዜ ጌታችንን ተከተለው።
❤ ድንቅ የሆኑ ተአምራቶችን እየተመለከተ ጥቂት ቀን ተቀመጠ ጌታችንም በአገረ ናይን የመበለቲቱን ልጅ በአስነሣው ጊዜ ከዚያ ነበር። ይህን አይቶ ወዲያውኑ አመነ ሌላ ምልክት አልሻም ብልጭ ብልጭ ሲል የነበረ የአይሁድ የሕግ ፋናን ትቶ ወደ እውነተኛ ፀሐይ ወደ ጌታ ኢየሱስ ቀርቦ ደመ መዝሙሩ ሆነው እንጂ።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፳፬ (24) ቀን።
❤ እንኳን እንኳን ለታላቁ አባት ለሐዲስ ሐዋርያ ለኢትዮጵያ ብርሃኗ ለሆኑት #ለአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ለፅንሰታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝
❤ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት (ፅንሰታቸው)፦ እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው "አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ" ማለትም "አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው" በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነውታል፡፡ ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍሥሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ይኸውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ የወላጆቻቸው የቀድሞ ስማቸው ዘርዐ ዮሐንስና ሣራ ይባል ነበር፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፳፫ (23) ቀን።
❤ እንኳን #ከአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት በኋላ ለደብረ ሊባኖስ ሦስተኛ መምህር (እጨጌ) ለሆኑት #ለአቡነ_ፊሊጶስ_ፍልሰተ_ዐፅማቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ፊሊጶስ_ዘደብረ_ሊባኖስ፦ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው በምናኔ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገቡ፡፡ ከብዙ ጊዜ አገልግሎትም በኋላ በአቡነ ተክለሃይማኖት እጅ መንኩሰው ከእርሳቸውም ዕረፍት በኋላ ሦስተኛ አበምኔት ሆነው አገልግለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከተወለዱት የመጀመሪያ ፓትርያርክ ሆነዋል፡፡ አባታቸው ቅዱስ ተክለሃይማኖትም በመንፈቀ ኢትዮጵያ ጳጳስ ሆነው ነበር፡፡ በመጀመሪያ የአቡነ ፊሊጶስን የጽድቅ ሕይወትና ሹመታቸውን በተመለከተ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድልና በራሳቸው በአቡነ ፊሊጶስ ገድል ላይ የተጻፈውን እንመልከት፡- "ክቡር አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ከዚህ ዓለም ተለይቶ የሚሄድበት ጊዜ ሲደርስ "ከአንተ በኋላ አንተን ተክቶ በዙፋንህ የሚቀመጥ ማነው?" አሉት፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለዐቢይ_ጾም_አራተኛ_ሳምንት_ለመጻጒዕ እግዚአብሔር አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የመጻጒዕ_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "አምላኩሰ ለአዳም #ለዕረፍት_ሰንበተ_ሠርዐ ወይቤልዎ አይሁድ በዓይ ሥልጣን ትገብር ዘንተ #ወይቤሎሙ_ኢየሱስ አነ እገብር አንትሙኒ እመኑ በግብርየ #አነ_ውእቱ_እግዚኣ_ለሰንበት_ወልድ_ዋሕድ ወይቤሎሙ ብውህ ሊተ ኅድግ በዲበ ምድር እስብክ ግዕዛነ ወእክሥት አዕይንተ ዕውራን አቡየ ፈነወኒ"። ትርጉም፦ #የአዳም_አምላክ_ሰንበትን_ለዕረፍት ሠራ፤ አይሁድ በምን ሥልጣን ይህን ታደርጋለህ አሉት፤ #ኢየሱስም_በራሴ_ሥልጣን_አደርጋለሁ፤ እናንተ ግን በሥራዬ እመኑ፤ #እኔ_የሰንበት_ጌታ_ነኝ፤ እኔ ወልድ ዋሕድ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር እል ዘንድ፤ ነጻነትን እሰብክ ዘንድ #የዕውራንን_ዐይን_አበራ_ዘንድ የባሕርይ አባቴ ላከኝ አላቸው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
✝ ✝ ✝
❤ #መጻጒዕ፦ አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት "መጻጒዕ" ይባላል። ስያሜው በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩። ላይ ከሚገኘው ኃይለ ቃል የተወሰደ ነው፡፡
❤ በዚህ የወንጌል ክፍል ጌታችን በቤተ ሳይዳ ሕሙማንን እንደ ፈወሰ ተነግሮአል፡፡ ብዙ ሕሙማን ፈውስ ሽተው አንዲት የመጠመቂያ ሥፍራን ከበው ይኖሩ ነበር፡፡ በዚያች ሥፍራ ቀድሞ የወረደ እና የተጠመቀ አንድ በሽተኛ ብቻ ይፈወስ ነበር፡፡ ጌታችን በዚህ ሥፍራ ተገኝቶ በሽተኞችን ጐብኝቷል፡፡
❤ በዚያም ልዩ ልዩ ደዌ ያለባቸው አምስት ዓይነት ሕሙማን እንደ ነበሩ ተገልጧል፤ እነዚህም፡- ሰውነታቸው የደረቀ፣ የሰለለና ያበጠ፤ እንደዚሁም ዕውራን እና ሐንካሳን ነበሩ፡፡
❤ ከዚህ አምስት የተለያየ ዓይነት በሽታ ከተያዙ ሰዎች መካከል ደዌው የጸናበት፣ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት በደዌ ዳኛ፣ ባልጋ ቍራኛ ተይዞ የኖረው፤ ከደዌው ጽናት የተነሣ "መጻጒዕ" ተብሎ የተጠራው በሽተኛ አንዱ ነበር፡፡ መጻጒዕ ስም አይደለም፡፡ ደዌ የጸናበት በሽተኛ ሕመምተኛ ማለት ነው እንጂ፡፡
❤ ሰውየው ከበሽታው ጽናት የተነሣ ስሙ ጠፍቶ በበሽታው ሲጠራ የነበረ ነው፡፡ አምላካችን ይህን ሰው "አልጋህን ተሸክመህ ሒድ" ብሎ ሠላሳ ስምንት ዘመን የተኛበትን አልጋ ተሸክሞ ወደ ቤቱ እንዲገባ ማድረጉ የሚነገርበት ወቅት በመኾኑ ሳምንቱ "መጻጒዕ" ተብሎ በተፈወሰው በሽተኛ ስም ተሰይሟል፡፡ (ሙሉ ታሪኩን በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩-፳፭ ይመልከቱ)፡፡
❤ ዛሬምዛሬም ቢኾን በሰዎች ላይ ልዩ ልዩ ደዌያት አሉ፤ የሥጋውን ደዌ ሐኪሞች ያውቁታል፡፡ ከዚህ የከፉ የነፍስ ደዌያት እጅግ ብዙዎች ናቸው፡፡ በኃጢአት ብዛት ልባቸው የደረቀና ያበጠ፤ ሰውነታቸው የሰለለ፤ ዓይነ ሕሊናቸው የታወረ፤ እግረ ልቡናቸው የተሰበረ ብዙዎች ሕሙማን አሁንም አሉ፡፡ ፈውስን ይሻሉ፤ ድኅነትን ይፈልጋሉ፡፡ እንደ መጻጕዕ ቦታቸውን ሳይለቁ እግዚአብሔርን በተስፋ ቢጠብቁት አንድ ቀን ይፈወሳሉ፡፡
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ። ወይመይጥ ሎቱ ኵሎ ምስካቢሁ እምደዌሁ። አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ"። መዝ 40፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 5፥1-ፍ.ም፣ ያዕ 5፥14-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 3፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 5፥1-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም ዕለተ ሰንበት (መጻጕዕ)ና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
