ru
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Открыть в Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Больше
602
Подписчики
Нет данных24 часа
-87 дней
-1630 дней
Архив постов
ቡልቡላ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አመታዊ በዓል ተከብሮ ዋለ።
+2
ቡልቡላ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አመታዊ በዓል ተከብሮ ዋለ።

የካ ኮተቤ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን እንዲህ ሲያምር ዋለ።
+3
የካ ኮተቤ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን እንዲህ ሲያምር ዋለ።

የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡
+9
የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን  በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡                     

ተዝካረ ስቅለቱ ለእግዚእነ ዓመታዊ ክብረ በዓል በአዳማ ናዝሬት ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ገዳም በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡
+4
ተዝካረ ስቅለቱ ለእግዚእነ ዓመታዊ ክብረ በዓል በአዳማ ናዝሬት ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ገዳም  በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡                     

የመድኃኔዓለምን ጥንተ ስቅለቱን በበደሌ ደብረ ሳህል መድኃኔዓለም ከቴድራል በድምቀት ተከበረ።
+3
የመድኃኔዓለምን ጥንተ ስቅለቱን በበደሌ ደብረ ሳህል መድኃኔዓለም ከቴድራል  በድምቀት ተከበረ።                     

የመድኃኔዓለምን የስቅለት በዓል እና የአባ መባአ ጽዮን ዓመትዊ በዓል በወልዲያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል በድምቀት ተከበረ፡፡
+6
የመድኃኔዓለምን የስቅለት በዓል እና የአባ መባአ ጽዮን ዓመትዊ በዓል  በወልዲያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል  በድምቀት ተከበረ፡፡                     

የ መድኃኔዓለም ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል(ጥንተ ስቅለቱ) #በአዶላ_ወዩ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከበረ።
+4
የ መድኃኔዓለም ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል(ጥንተ ስቅለቱ)  #በአዶላ_ወዩ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከበረ።                     

የአባታችን የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለቱ በወላይታ #ሌጋማ_ደብረ_መድኃኒት_መድኃኔዓለም_ወቅዱስ_ዑራኤል_ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
+4
የአባታችን የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለቱ በወላይታ #ሌጋማ_ደብረ_መድኃኒት_መድኃኔዓለም_ወቅዱስ_ዑራኤል_ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ውሏል።                     

የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለቱ እና የጻድቁ መባዓ ጽዮን መታሰቢያ ዓመታዊ ክብረ በዓል በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በድምቀት ተከበረ።
+3
የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለቱ እና የጻድቁ መባዓ ጽዮን መታሰቢያ ዓመታዊ ክብረ በዓል በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በድምቀት ተከበረ።                     

ጥቅምት 27 "በዓለ ስቅለት" ጥቅምት 27 በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው። መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ? ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው። ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር። በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት። በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ። አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ። በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡ ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን (#በዲያቆን_መላኩ_ይፍሩ)

ኦሮሚያ ጅማ ....ጌታዋን እና መድኃኒቷን የመድኃኔዓለምን በዓለ ንግስ ለማክበር እራሷን እንዲህ አሰማምራ ዋዜማ ላይ ደምቃለች **** እግዚአብሔር ይመስገን ድንግል ሆይ አይሁድ ልብሱን በነጠቁት ጊዜ
+2
ኦሮሚያ ጅማ ....ጌታዋን እና መድኃኒቷን የመድኃኔዓለምን በዓለ ንግስ ለማክበር እራሷን እንዲህ አሰማምራ ዋዜማ ላይ ደምቃለች **** እግዚአብሔር ይመስገን ድንግል ሆይ አይሁድ ልብሱን በነጠቁት ጊዜ ልጅሽ መራቆቱን ያንቺም አንጀት በሐዘን እሳት መንገብገቡን አሳስቢ። ጅማ መንበረ ጵጵስና ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን

ምስካየ ኀዙናን በዋዜማው
ምስካየ ኀዙናን በዋዜማው

ናዝሬት(አዳማ) መድሃኔዓለም በዋዜማው
+3
ናዝሬት(አዳማ) መድሃኔዓለም በዋዜማው

በዋዜማው ቀን እንዲህ አሸብርቋል ደብረ ኢያሪኮ ላፍቶ መድኃኔዓለም 26 02 2016 ዋዜማ
+2
በዋዜማው ቀን እንዲህ አሸብርቋል ደብረ ኢያሪኮ ላፍቶ መድኃኔዓለም 26 02 2016 ዋዜማ

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ጥቅምት ፳፯ (27) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ጌታችን በዕለተ አርብ የጠጣው መራራ ሐሞት እያሰብ ሁል ጊዜ #አ
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝       ✝ #ጥቅምት ፳፯ (27) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ጌታችን በዕለተ አርብ የጠጣው መራራ ሐሞት እያሰብ ሁል ጊዜ #አርብ_አርብ_ኮሶ_ይጠጡና_የመድኃኔዓለም_ዝክር ይዘክሩ ለነበሩት ለታላቁ #አባት_ለአቡነ_መብዓ_ጽዮን፣ #ማኅሌተ_ጽጌን  ከአባ ገብረ ማርያም ጋር በመሆን ለደረሱት ለታላቁ #አባት_ለአቡነ_ጽጌ_ድንግልና በዋሻ ውስጥ #አርባ_ዓመት_ለኖሩ መና ሲመገቡ ለነበሩት ለታላቁ #አባት_ለአቡነ_ጊዮርጊስዘጣና_ለዕረፍታቸው_በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።           ✝ እንኳን #ለመድኃኔዓለም_ለስቅለቱ_ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና #ለሀገረ_ቃው_ኤጲስ_ቆጶስ #ለአባ_መቃርስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በዋሻ ከሚኖር #ከጳውሎስና_ከዮልያኖስ ከእነርሱም ጋር ላሉ ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።   √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በታንዛንያ የኢፌዴሪ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ ጋር በኢትዮጵያ ኤምባሲ በቤተክርስቲያናችን ሁለንተናዊ አገልግሎትና ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሰደድ የታንዛንያን ድንበር በሕገ ወጥ መንገድ
+2
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በታንዛንያ የኢፌዴሪ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ ጋር በኢትዮጵያ ኤምባሲ በቤተክርስቲያናችን ሁለንተናዊ አገልግሎትና ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሰደድ የታንዛንያን ድንበር በሕገ ወጥ መንገድ ሲያቋርጡ ተይዘው በእሥር ላይ በሚገኙ  ቁጥራቸው ከ5000 በላይ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ጉዳይ ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡ በታንዛንያ እስር ቤት ያለውን አሰቃቂ ሁኔታን መረዳታቸውን የገለጹት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ዜጎች ወደ ሀገራቸው በሰላም እንዲመለሱ ቤተክርስቲያን የሚጠበቅባትን ድርሻ እንደምትወጣ ገልጸዋል፡፡ ብፁዕነታቸው በታንዛንያ የሚኖራቸውን አገልግሎት በማጠናቀቅ ወደ ሌላው የሀገረ ስብከታቸው  ዩጋንዳ ካምፓላ በመሄድ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬን ጨምሮ ለአንድ ሳምንት መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን የሚቀጥሉ ይሆናል። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በታንዛንያ ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረጉ፡፡ ብፁዕነታቸው በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ የታንዛኒያን ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘው በእስር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸ
+3
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ  በታንዛንያ ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረጉ፡፡ ብፁዕነታቸው በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ የታንዛኒያን ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘው በእስር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ሁኔታ በታንዛንያ ከኢፌዴሪ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ ጋር በኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወያይተዋል። +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የብዙኃን መገናኛ ሥርጭት አገልግሎት  ድርጅት የበላይ ኃላፊና  የምሥራቅና ሰሜን  አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  በቅዱስ ሲኖዶስ በተመደቡባቸው ሀገራት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማድረግ ምእመናንን በማጽናናት ቀድሰው በማቁረብ ሐዋርያዊ አገልግሎት በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ ብፁዕነታቸው በሰሜን አፍሪካ ግብጽ በምሥራቅ አፍሪካ በኬንያና ጅቡቲ ያከናወኑትን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመቀጠል በታንዛንያ ዳሬሰላም በመገኘት  በስደት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በማጽናናት ከግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተገኘ የአምልኮ ሥፍራ ምእመናንን ቀድሰው አቁርበዋል ፣ ትምሕርተ ወንጌል መስጠታቸውን ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት መጋቤ ሃይማኖት ቆሞስ አባ አብርሃም ገረመው ለ EOTC TV (ኢኦተቤ ቴቪ) ገልጸዋል።

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ጥቅምት ፳፮ (26) ቀን። ✝ እንኳን #ጌታችን_ከመረጣቸውናና በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ አጋንንትንም ያወጡ ዘንድ ሥልጣን ከ
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝           ✝ #ጥቅምት ፳፮ (26) ቀን። ✝ እንኳን #ጌታችን_ከመረጣቸውናና በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ አጋንንትንም ያወጡ ዘንድ ሥልጣን ከሰጣቸው #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእትና_ከሰባቱ_ዲያቆናት አንዱ ለሆነው #ለቅዱስ_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ጢሞና ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ለጌታችን_ወንድም ለተባለው #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ያዕቆብ ለመታሰቢያ በዓሉ በሰላም አደረሰን፡፡ በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከፊልጶስና ከሰማዕት አግናጥዮስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። "#ሰላም_ለጢሞና_እምኍልቈ_ሰብዓ_ወክልኤቱ አርድእት። #ወእምሰብዓቱ_ዲያቆናት። ዘፈጸመ ስምዐ በዋዕየ እሳት። ወካዕበ ዓዲ በዛቲ ዕለት። ሰላም እብል ለኄራስ ሰማዕት"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጥቅምት_26። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ጥቅምት ፳፭ (25) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያ_ጻድቅ_ለአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ለአጎት_ልጅ ለታላቁ አባት ከበሬ ጋር ተጠምደው
✝  "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝           ✝ #ጥቅምት ፳፭ (25) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያ_ጻድቅ_ለአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ለአጎት_ልጅ ለታላቁ አባት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነትን ለተቀበሉት #ለአቡነ_ሕፃን_ሞዐ_ቃል_ኪዳን_ለተቀበሉባት ለመታሰቢያ በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። እንኳን #ለታላቁ_አባት_ሰው_ቢረሳ_ቢረሳ_ምግቡን_አይረሳምና #ስብሐት_ብሎ_በእንተ (ስለ) አባ አቢብ  ብሎ በሚመገብ ጊዜ  ያሰበውን እምርልሃለሁ ብለው ታላቅ ቃል ኪዳንን መድኃኔዓለም ለሰጣቸው፤ የጌታችንን መከራ መስቀሉን በማሰብ #ራሳቸውን_ሰባት_ጊዜ_ለገደሉ ለታላቁና ክቡሩ ለሆኑ #አባ_አቢብ_ለተባሉት_ለመስተጋድል_አባ_ቡላ፣ #አክሚም_ከሚባል_አገር_የመላእክት_አምሳል_ለሆነ#ለአባ_እብሎኝ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_አቢብ ማኅበር ከሆኑ #ዐሥር_ሺህ_አርባ_ሦስት_ወንዶችና_ሦስት_መቶ_ሰባት_ሴቶች_ሰማዕታትና ከሰማዕቱ #ከቅዱስ_ዮልዮስ_ከሥጋው_ፍልሰትና_ቤተ_ክርስቲያኑ ከከበረችበት ዕለት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ከስልጤ ቅበት ከተማ የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳውያንን መልሶ ለማቋቋም ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ። ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) ከስልጤ ቅበት ከተማ የተፈናቀሉ ኦርቶ
+2
ከስልጤ ቅበት ከተማ የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳውያንን መልሶ ለማቋቋም ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ። ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) ከስልጤ ቅበት ከተማ የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳውያንን መልሶ ለማቋቋም ከ5 ሚሊየን ብር በላይ በደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ አኅጉረ ስብከት በሚገኙ ምዕመናን ድጋፍ ተደርጓል። በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ አስተዳደር የሙስሊም ተማሪዎች ላይ ድግምት ተደርጓል  በሚል ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ቤቶች እና የንግድ ሱቆቻቸው ላይ ቃጠሎና ዝርፊያ መፈጸሙ ፤ ከ 1,520 በላይ የሚሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ነፍሳቸውን ለማትረፍ ተሰደው በቡታጅራ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አጸድ መጠለላቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ተፈናቃዮቹ መልሰው ይቋቋሙ እና ወደ ቀድሞ ኑሯቸው ይመለሱ ዘንድ የተደረገላቸውን ድጋፍ ለብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የሀዲያ ስልጤ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና ለብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የዜና ማርቆስ መንፈሳዊ  ኮሌጅ የበላይ  ጠባቂ አስረክበዋል። በደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ አኅጉረ ስብከት ከሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን የተሰበሰበው የገንዘብ መጠን አምስት ሚልዮን አንድ መቶ አንድ ሺ አስራ አራት (5,101,014) ብር ሲሆን በርክክቡ ወቅት ሊቃነ ጳጳሳቱን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ እንዲሁም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ካህናት እና መዘምራን ተገኝተዋል።