የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Открыть в Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Больше4 374
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
4 374
🌾✞ #መዝሙረ_ዳዊት_ዘኀሙስ ✞🌾
☑️✞ የመጀመሪያው ንጉስ {፹፩-፺}
☑️✞ #እግዚአብሔር_ቆመ
📖መምህር ሥነፀሐይ ቦጋለ ምሥራቀ ፀሐይ አዲሱ ቅዱስ ሚካኤል #ባሕርዳር
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
t.me/Geez_Abinet
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾 #ሰባ_የኢየሱስ_ክርስቶስ_ስሞች 🌾
1) የዳዊት ልጅ (ማቴ ፩፥፩)
2) የአብርሃም ልጅ (ማቴ ፩፥፩)
3) ክርስቶስ (ማቴ ፩፥፲፮)
4) ኢየሱስ (ማቴ ፩፥፳፩)
5) ዐማኑኤል (ማቴ ፩፥፳፫፤ ኢሳ ፯፥፲፬)
6) ተወዳጅ ልጅ (ማቴ ፫፥፲፯)
7) የእግዚአብሔር ልጅ (ማቴ ፳፮፥፷፫)
8) የሰው ልጅ (ማቴ ፳፮፥፷፬)
9) የአይሁድ ንጉሥ (ማቴ ፳፯፥፴፯)
10) የናዝሬቱ ኢየሱስ (ማቴ ፳፮፥፸፩)
11) ደንጊያና የመአዝን ራስ (ማር ፲፪፥፲)
12) የእስራኤል ንጉሥ (ማር ፲፭፥፴፪)
13) የልዑል ልጅ (ሉቃ ፩፥፴፪)
14) የመዳን ቀንድ (ሉቃ ፩፥፷፱)
15) ከላይ የመጣ ብርሃን (ሉቃ ፩፥፸፰)
16) ወልደ ማርያም (ሉቃ ፪:፱)
17) አቤቱ (ሉቃ ፰፥፳፬)
18) የተመረጠ ልጅ (ሉቃ ፱፥፴፭)
19) ሕያው (ሉቃ ፳፬፥፭)
20) ቃል (ዮሐ ፩፥፩)
21) አንድ ልጁ (ዮሐ ፩፥፲፰)
22) ረቢ (መምህር) (ዮሐ ፩፥፴፱)
23) መሲሕ (ዮሐ ፩፥፵፩)
24) ልጁ (ዮሐ ፰፥፴፮)
25) የእግዚአብሔር በግ (ዮሐ ፩፥፴፮)
26) እግዚአብሔር (ዮሐ ፩፥፩)
27) ሙሽራ (ዮሐ ፫፥፳፱)
28) የዓለም መድኀኒት (ዮሐ ፬፥፵፪)
29) የእግዚአብሔር እንጀራ (ዮሐ ፮፥፴፫)
30) የሰማይ እንጀራ (ዮሐ ፮፥፴፪)
31) የሕይወት እንጀራ (ዮሐ ፮፥፴፭)
32) የዓለም ብርሃን (ዮሐ ፰፥፲፪)
33) እኔ (ዮሐ ፰፥፶፰፤ ዘፀ ፫፥፲፬)
34) መልካም እረኛ (ዮሐ ፲፥፲፩)
35) ትንሣኤና ሕይወት (ዮሐ ፲፩፥፳፭)
36) መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት፣ በር (ዮሐ ፲፬፥፮)
37) እውነተኛ የወይን ግንድ (ዮሐ ፲፭፥፩)
[በሐዋርያት ሥራና በመልእክታት]
38) ቅዱስና ጻድቅ (የሐዋ ፫፥፲፬)
39) የሕያዋንና የሙታን ፈራጅ (የሐዋ ፲፥፵፪)
40) ጌታ (ሮሜ ፲፥፱-፲፫)
41) መድኀኒት (ሮሜ ፲፩፥፳፮)
42) የእግዚአብሔር ኀይልና የእግዚአብሔር ጥበብ (፩ኛ
ቆሮ ፩፥፳፬)
43) በግዐ ፋሲካ (፩ኛ ቆሮ ፭፥፯)
44) ኋለኛው (ዳግማይ) አዳም (፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፵፭)
45) የቤተ ክርስቲያን ራስ (ቆላ ፩፥፲፰)
46) ሕያው አምላክ (፩ኛ ጢሞ ፬፥፲)
47) በኲር (ዕብ ፩፥፮)
48) ሐዋርያ (ዕብ ፫፥፩)
49) ታላቅ ሊቀ ካህናት (ዕብ ፬፥፲፬)
50) የእምነታችን ራስና ፈጻሚ (ዕብ ፲፪፥፪)
51) የነፍስ እረኛና ጠባቂ (፩ኛ ጴጥ ፪፥፳፭)
52) የእረኞች አለቃ (፩ኛ ጴጥ ፭፥፬)
53) የሕይወት ቃል (፩ኛ ዮሐ ፩፥፩)
54) የአብ ልጅ (፪ኛ ዮሐ ፩፥፫)
55) የእግዚአብሔር አንድ ልጅ (፩ኛ ዮሐ ፬፥፱)
በዮሐንስ ራእይ
56) በኲረ ሙታን (ራእ ፩፥፭)
57) የምድር ነገሥታት ገዢ (ራእ ፩፥፭)
58) የታመነው ምስክር (ራእ ፩፥፭)
59) አሜን (ራእ ፫፥፲፬)
60) የይሁዳ አንበሳ (ራእ ፭፥፭)
61) የታረደው በግ (ራእ ፭፥፲፪)
62) የታመነና እውነተኛ (ራእ ፲፱፥፲፩)
63) የእግዚአብሔር ቃል (ራእ ፲፱፥፲፫)
64) ፊተኛውና ኋለኛው (ራእ ፳፪፥፲፫)
65) የነገሥታት ንጉሥ (ራእ ፲፱:፲፮)
66) የጌቶች ጌታ (ራእ ፲፱፥፲፮)
67) አልፋና ኦሜጋ (ራእ ፳፪፥፲፫)
68) መዠመሪያውና መጨረሻው (ራእ ፳፪፥፲፫)
69) የዳዊት ሥርና ዘር (ራእ ፳፪፥፲፮)
70) የሚያበራ የንጋት ኮከብ (ራእ ፳፪፥፲፮)
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
✔ "በዚያም ቀን ፀሐይ በቀትር እንድትገባ አደርጋለኊ ይላል ጌታ እግዚአብሔር በብርሃንም ቀን ምድሩን አጨልማለኊ” (አሞ ፰፥፱) ተብሎ
🌾✞ በዕለተ ዐርብ በጌታችን ስቅለት ዕለት ስለተደረገው ስለዚኽ ታላቅ ተአምር ሊቃውንት እንዲኽ ይገልጹታል፡-
☞ “ጐየ ፀሓይ ወጸልመ ወርኅ ወከዋክብትኒ ተኀብኡ ከመ ኢያብርሁ ለምእመናን በጊዜ ስቅለቱ ቅዱስ እንዘ ፍጹም በገሃሁ ወርኅ ኢያብርሀ…” (ፀሓይ ብርሃኑን ነሣ ጨረቃም ጨለመ፤ ከዋክብትም በከበረ ስቅለቱ ጊዜ ለምእመናን እንዳያበሩ ብርሃናቸውን ነሡ፤ ጨረቃም በምልአቱ ሳለ አላበራም፤ ፀሓይ ብርሃኑን በነሣ ጊዜ ፍጡራን ኹሉ በጨለማ ተያዙ፤ የፈጠራቸው ፈጣሪያቸው እንደ ሌባ እንደ ወንበዴ በዕንጨት ላይ ተሰቅሎ እንዳያዩ ቀኑ ጨለመ፤ ባለሟሉ መልአክም ከሓድያንን ያጠፋቸው ዘንድ ሰይፉን በእጁ መዝዞ ይዞ ከመላእክት መኻከል ወጣ፤ የክርስቶስም ቸርነት በከለከለችው ጊዜ ያ መልአክ የቤተ መቅደሱን መጋረጃ በሰይፉ መታው ቀደደውም፤ ከላይ እስከ ታችም ወደ ኹለት አደረገው (ማቴ ፳፯፥፶፩፤ ማር ፲፭፥፴፰፤ ሉቃ ፳፫፥፵፭)፤ መላእክትም ኹሉ በሰማይ ኹነው ርሱን አይተው በአንድነት ሲቈጡ የአብ ምሕረቱ፣ የወልድ ትዕግሥቱ፣ የመንፈስ ቅዱስ ቸርነቱ ከለከለቻቸው፤ ፀሓይ ብርሃኑን ነሣ፤ በጨለማ ተይዞ ሲድበሰበስ ዓለምንም ተወው፤ ይኽ ኹሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው ከመለየቱ አስቀድሞ ተደረገ) (ቅዱስ አትናቴዎስ)
♥☞ “እስመ ሶበ ተሰቅለ ክርስቶስ ጸልመ ሰማይ አሜሃ ወፀሓይኒ ሰወረ ብርሃኖ ወወርኅኒ ደመ ኮነ…” (ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ያን ጊዜ ሰማይ ጨለማ ኾነ፤ ፀሓይም ብርሃኑን ነሣ፤ ጨረቃም ደም ኾነ፤ ምድርም ተነዋወጠች ደንጊያውም ተከፈለ፤ መቃብራትም ተከፈቱ፤ ስለዚኽም ለፍጡራን ከፈጣሪያቸው ጋር ሊታመሙ ተገባቸው (ማቴ ፳፯፥፵፭-፶፩) (ቅዱስ ሱኑትዩ)
♥ ☞ “ፀሓይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ወከዋክብት ወድቁ ፍጡነ ከመ ኢይርአዩ ዕርቃኖ ለዘአልበሶሙ ብርሃነ” (ፀሓይ ጨለመ፤ ጨረቃም ደም ኾነ፤ ከዋክብትም ፈጥነው ወደቁ፤ ብርሃንን ያጐናጸፋቸውን የጌታን ዕርቃን እንዳያሳዩ) (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)
🌾✞ ሊቁ አባ ጊዮርጊስም ምስጢሩን በመጠቅለል በሕማማት ሰላምታው ላይም፡-
“ፀሓይ ብሩህ አሜሃ ጊዜ ቀትር ጸልመ
ወወርኅኒ ጽዱል ተመሰለ ደመ
ትንቢት ከመ ቀደመ፤ ስብሐት ለከ”
(ብሩህ የኾነ ፀሓይ ያን ጊዜ በቀትር (በስድስት ሰዓት) ጨለመ፤ ጽዱል የኾነ ጨረቃም ደምን መሰለ፤ አስቀድሞ ትንቢት እንደተነገረ፤ ጌታ ሆይ ምስጋና ይገባኻል) በማለት ከትንቢተ ነቢያት በመነሣት በዚኽ በስድስት ሰዓት ምስጋናው ላይ በሰዓቱ ከተከናወነው ምስጢር በመነሣት አስተምሯል፡፡
🌾✞ በመስቀል የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና በሰማይ ከላይ የተጠቀሱት ተአምራት ሲደረጉ ምድርንም የፈጠረ ነውና በምድር ደግሞ አራት ተአምራት ማለት የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለኹለት ተቀደደ፤ ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤ መቃብራት ተከፍተዋል፤ ከ፭፻ በላይ ሙታን ተነሥተዋል (ማቴ ፳፯፥፵፭፤ ፳፯፥፶፩፤ ፳፯፥፶፪-፶፫)፡፡
🌾✞ ከዚኽ በኋላ የተነገረው ትንቢት ኹሉ እንደተፈጸመ አይቶ የሕይወት ውሃ ምንጭ ጌታ ከእኛ ጽምዐ ነፍሳችንን ለማራቅ በፈቃዱ “ተጠማኊ” ባለ ጊዜ ነቢዩ ዳዊት አስቀድሞ በመዝ ፷፰፥፳፩ ላይ “ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ ወአስተዩኒ ብሒአ ለጽምእየ” (በምግቤ ሐሞት ጨመሩበት፤ ለጥማቴም ኾምጣጤ አጠጡኝ) በማለት የተናገረው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም አይሁድ በዚያም ኾምጣጤ የመላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበርና እነርሱም ኾምጣጤውን በሰፍነግ መልተው በሁስጱም አድርገው በአፉ ውስጥ ጨምቀውለታል፡፡
✔ በመጠማቱም ከእኛ ጽምዐ ነፍስን አርቆልናልና፤ ✔ መራራ ሐሞትን በመቅመሱ ከሰው ልጆች ላይ መራራው ሞት ጠፍቷል፡፡
♥ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በሰባቱ ጊዜያት የጸሎት መጽሐፉ ላይ፤ ጌታችን ሐሞትንና ከርቤን መጠጣቱ ስለምን እንደኾነ፡-
“ከመ ታስትየነ ለነ ደመ ገቦከ ነባቤ
እንተ አስተዩከ ሐሞተ ወከርቤ
ጸማእኩ በጊዜ ትቤ፤ ስብሐት ለከ”
(ነባቢ የሚኾን የጐንኽን ደም ታጠጣን ዘንድ ተጠማኊ ባልኽ ጊዜ ሐሞትን ከርቤን ያጠጡኽ ጌታ ምስጋና ለአንተ ይገባል) በማለት ገልጦታል፡፡
🌾✞ ቅዱሳን ደናግልም መራራ ሐሞትን ጌታችን በመቅመሱ ለ፭ሺሕ ፭፻ ዘመን የሠለጠነ መራራ ሞት ከሰዎች ስለመወገዱ፡-
“ወሰሪቦ እግዚእ ኢየሱስ ብኂዐ ይቤ ተፈጸመ ኲሉ…” (ጌታችን ኢየሱስ መጣጣውን ቀምሶ በመጽሐፍ የተጻፈው ኹሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ፤ በጒረሮው መጠማትና በአንደበቱ መድረቅ ከሥጋና ከነፍስ መጠማት አዳነን፤ በቀትርም ጊዜ የዝኆን ሐሞትና ከርቤ የተቀላቀለበት መጻጻንና የበግ ሐሞትን በመጠጣቱ የጣፈጠ የበለስ ፍሬን ስለ በሉ ስለ አዳምና ስለ ሔዋን ከፈለ፤ ለእኛም መሪር የኾነ ሞትንና ርግማንን አጠፋልን) በማለት ተንትነው ጽፈዋል፡፡
ነገረ ክርስቶስ ክፍል አንድ ከሚለው 622 ገጽ ካለው መጽሐፌ በጥቂቱ የተወሰደ
በመስቀል ተሰቅለኽ ፈያታዊ ዘየማንን ያሰብከው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በቸርነትኽ ዐስበን፡፡
✍በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾⛪️ #የአምላካችን_የክርስቶስ_ጥንተ_ስቅለት 🌾⛪️
መጋቢት ፳፯
🌾✞ የነገሥታት ንጉሥ የሕይወት ራስ ኢየሱስ ክርስቶስን የአይሁድ ጭፍሮች በዕለተ ዐርብ የእሾኽ አክሊል ጐንጒነው በራሱ ላይ ደፍተውለታል፤ የእሾኽ አክሊል በመቀዳጀቱ በዘፍ ፫፥፲፰ ላይ አዳምን አስቀድሞ “ምድር እሾኽንና አሜከላን ታበቅልብኻለች” ብሎት ነበርና ያነን መርገም ደምስሶለት ለአዳም ክሷል፡፡
🌾✞ ዳግመኛም አዳምና ሔዋን ምክረ ከይሲን ሰምተው የድል ነሺዎች አክሊል ተለይቷቸው ነበርና ያነን ሰማያዊ አክሊል እንደመለሰልን ለማጠየቅ፡፡ ይኽ ለካሳ አምላካችን ስለፈጸመው የድኅነት ምስጢር ቅዱሳት ደናግል በጥልቀት እንዲኽ አብራርተዋል፡-
🌾✞ “አስተቀጸልዎ ከመዝ ለርእሰ ሕይወት አክሊለ ሦክ …” (የሕይወት መገኛ ርሱን የእሾኽ አክሊልን አቀዳጁት፤ መላእክትን የብርሃን ራስ ቁር የሚያቀዳጃቸው የነገሥታት ገዢ የሚኾን ርሱን የሾኽ አክሊል አቀዳጁት፤ በሾኽ አክሊልም ከራሱ ክፍል ያቆሰሉት ሺሕ ናቸው፤ ከራሱም ቊስሎች ደም እንደ ውሃ በዝቶ ፈሰሰ፤ ፊቱም ደምን ለበሰ ሰውነቱም በደም ተጠመቀ፤ የጽዮን ልጆች እናቱ ያቀዳጀችውን አክሊል ተቀዳጅቶ አዩት፤ ተድላ ደስታ የሚያደርግበትና የሙሽርነቱ ቀን ነውና (መሓ ፫፥፲፩) … ነገር ግን የሾኽ አክሊልን በመቀዳጀቱ በምድራችን ላይ የበቀሉትን አሜከላና እሾኽ ርግማንን አጠፋልን (ዘፍ ፫፥፲፰)፤ ራሱንም በዘንግ በመመታቱ የታላቁን እባብ ሰባቱን ራሶቹን ዐሥሩን ቀንዶቹን አጠፋልን (ራእ ፲፫፥፩)) ብለዋል፡፡
🌾✞ ሊቁ ቅዱስ ኤራቅሊስም ስለፈጸመው ካሳ እንዲኽ አስተምሯል፡-
♥☞ “እንዘ ይትቄጸል አክሊለ ሦክ አብጠለ ኲነኔሁ ለቀኖተ ሞት ወእንዘ ቅንው ዲበ ዕፀ መስቀል ኢተዐርቀ እምነ መንበሩ…” (የእሾኽ አክሊል ደፍቶ የሞትን ሥልጣን ፍርድ አጠፋ፤ በመስቀል ላይ ተቸንክሮ ሳለ ከዙፋኑ አልተለየም፤ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፤ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ አልተለየም፤ በምድር አይሁድ እንደ በደለኛ ሲዘብቱበት፤ መላእክት በሰማይ የከበረ ጌትነቱን ይናገሩ ነበር) (ቅዱስ ኤራቅሊስ)
🌾✞ እጆቹና እግሮቹ ስለመቸንከሩ አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት ዐድሮ በመዝ ፳፩፥፲፮ ላይ “ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዙኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፤ ዐጥንቶቼ ኹሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም” በማለት ውሻ ከአፉ ያወጣውን መልሶ ለምግብነት እንዲፈልገው፤ አይሁድም ኦሪትን እለፊ ካላት በኋላ ሲሠሯት በመገኘታቸው በውሻ መስሎ ትንቢት ያናገረባቸው ሲኾን፤ ይኽም ሊፈጸም ንጹሓት እጆቹና እግሮቹ በምስማር ከዕፀ መስቀሉ ጋር አያይዘው ቸንክረውታል፡፡
🌾✞ የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ሔዋን በእግሮቿ ወደ ዕፀ በለስን በማምራቷ በድላ ነበርና ለርሷ ካሳ ሊኾን ንጹሓን እግሮቹ ሲቸነከሩ፤ በእጆቿም በለስን በመቊረጧ ንጹሐ ባሕርይ አምላክ እጆቹ በችንካር ተቸንክረዋል፡፡ በመቸንከሩም ለ፭ሺሕ ፭፻ ዘመን በሰው ልጆች ላይ የሠለጠነ የሞት ችንካር ጠፍቶልናል፡፡
🌾✞ ምስጋና ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስ በመቸንከሩ ስለፈጸመው ካሳ ደናግል ሲተነትኑ፡-
♥☞ “ወበቅንዋቲሁ ሠበረ ለነ ቀኖተ ሞት …” (በመቸንከሩም የሞት ችንካርን አጠፋልን፤ ሔዋን በእግሮቿ ወደ ዕፀ በለስ ስለ ተመላለሰች እጆቹንና እግሮቹን በመቸንከር ከፍሏልና፤ በእጆቿም የበለስን ፍሬ ስለቈረጠች ፈንታ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል በሥጋው ከመስቀል ዕንጨት ጋራ ተቸነከረ) በማለት አስተምረዋል፡፡
🌾✞ መተርጒማን ሊቃውንት እንዳመሰጠሩት ጌታ በዕንጨት መስቀል ላይ መሰቀሉ ስለምን ነው ቢሉ?፤ እሾኽ በሾኽ ይነቀሳል ነገር በነገር ይወቀሳል እንዲሉ በዕፀ በለስ ምክንያት የገባውን ኀጢአት በዕፅ ለማውጣት በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሏል፡፡
🌾✞ ጌታችን ከምድር ከፍ ከፍ ብሎ ስለምን ተሰቀለ? ቢሉ፦ “እምከመ ተለዐልኩ እምድር እስሕብ ኲሎ ኀቤየ” (ከምድር ከፍ ከፍ ባልኊ ጊዜ ኹሉን እስባለኊ) ብሎ ነበርና ይኽነን ሊፈጽም ነው (ዮሐ ፲፪፥፴፪)፡፡
ዳግመኛም ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ መሰቀሉ “ኅሩይ ማእከለ እግዚአብሔር ወሰብእ” እንዲል አምላክ ወሰብእ ኾኖ እንዳስታረቀን ለማጠየቅ፡፡
በመጨረሻም ምድርን በኪደተ እግሩ እየተመላለሰ እንደ ቀደሳት፤ ዐየራትን ደግሞ ሥብ እያጤሱ አስተራኲሰውት ነበርና አየራትን ለመቀደስ ነው፡፡
🌾✞ ንጹሐ ባሕርይ ጌታችንን አይሁድ መስቀሉን አሸክመው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ከወሰዱት በኋላ ኹለት ወንበዴዎችን በቀኝና በግራ አድርገው ጌታችንን በመኻከል ሰቅለውታል (ማቴ ፳፯፥፴፰፤ ማር ፲፭፥፳፯፤ ሉቃ ፳፪፥፴፫፤ ዮሐ ፲፱፥፲፰)፡፡
🌾✞ ክፉዎች አይሁድ ይኽነን ያደረጉበት ምክንያት በክፋት ነው፤ ይኸውም በቀኝ የሚመጡ ሰዎች በቀኝ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው “ይኽ ምንድነው?” ብለው ሲጠይቁ “ወንበዴ ነው” ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን “ይኽስ ምንድነው?” ብለው ሲጠይቁ “ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ” ብለው ሰዎችን ለማሳሳት፤ በግራ የሚመጡ ሰዎች በግራ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው “ይኽ ምንድነው?” ብለው ሲጠይቁ “ወንበዴ ነው” ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን “ይኽስ ምንድነው?” ብለው ሲጠይቁ “ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ” ብለው ሰዎችን ለማሳሳት ያደረጉት ነው፡፡
✔ዳግመኛም አነገሥንኽ ብለውታልና ቀኛዝማች ግራዝማች ሾምንልኽ ለማለት ለመዘበት፡-
በተጨማሪም ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕ ፶፫፥፲፪ ላይ “ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና” የሚለው ትንቢቱን ሊፈጽም ሲኾን ምስጢሩ ግን እኛን ከጻድቃን ጋራ አንድ ያደርገን ዘንድ ርሱ ከበደለኞች ጋር ተቈጥሯል፤ ሌላውም በዕለተ ምጽአት እኛን ኃጥኣንን በግራ ጻድቃንን በቀኝ ታቆማለኽ ሲያሰኛቸው ነበር (ማቴ ፳፭፥፴፫፤ ራእ ፩፥፯)፡፡
🌾✞ በኹለት ወንበዴዎች መኻከል ከሰቀሉት በኋላ ጲላጦስም “የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚል ጽሕፈት በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ (ዮሐ ፲፱፥፲፰-፳፪)፤ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን “ርሱ የአይሁድ ንጉሥ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለኽ አትጻፍ” ሲሉት፤ ጲላጦስም “የጻፍኹትን ጽፌአለኊ” ብሎ መልሶላቸዋል፤ ይኽነንም በሕማማት ድርሳኑ ላይ ሲተረጒሙት፡- “ወዝ መጽሐፈ ጌጋይ ዘጸሐፎ ጲላጦስ ወአንበሮ መልዕልተ ርእሱ ይደምስስ ለነ በኲሉ ጊዜ መጽሐፈ ዕዳነ ዘጸሐፉ አጋንንት” (ጲላጦስ ጽፎ ከራሱ በላይ ያኖረው በደሉን የሚናገር ይኽ መጽሐፍ ኹልጊዜ አጋንንት የጻፉትን የዕዳችንን መጽሐፍ ያጠፋልን ዘንድ ነው) በማለት አራቅቀው ገልጠዋል፡፡
🌾✞ ጌታችን በሚሰቀልበት ጊዜ ብርሃን ያለበሳቸውን አምላክ ዕርቃኑን ለመሰወር ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ፀሓይና ጨረቃ ብርሃናቸውን ነሥተዋል (ማቴ ፳፯፥፵፭፤ ማር ፲፭፥፴፫፤ ሉቃ ፳፫፥፵፬-፵፭)፡፡
❖ ይኽ በጌታ ስቅለት ዕለት እንደሚደረግ አስቀድሞ በነቢዩ አሞጽ ኹለት ጊዜ በትንቢት ተነግሯል፡- ይኸውም
✔“የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይኾን ጨለማ አይደለምን? ጸዳል የሌለውም ድቅድቅ ጨለማ አይደለምን?” (አሞ ፭፥፳)
4 374
•✞ #አልፋና_ኦሜጋ ✞•
https://t.me/EOTC2921
•••✞•••✞•••✞•••
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ (2)
በከሃዲዎች እጅ ተይዘክ ቀረብክ (2)
•••✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ
#አዝ•••
ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስርው
እንደ በግ ተጎትተህ ልትመራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑት ለመመጻደቅ
#አዝ•••
በአውደ ምኩና ከጲላጦስ ዘንድ
አሳልፈው ሰጡ አጋልጠው ለፍርድ
ከሃና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ
ከነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡ በአዋጅ
#አዝ•••
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ
#አዝ•••
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
ግፈኞች አይሁዶች ባንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ
#አዝ•••
4 374
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✞✞✞
#እንኳን_ለጌታችን_ለአምላካችንና_ለፈጣሪያችን_መድኃኔዓለም_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ዓመታዊ_የስቅለት_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሰን_አደረሳችሁ ✞•••
መጋቢት ፳፯
✞✞✞ #መድኃኔ_ዓለም ✞✞✞
☞✞ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ በዚሕ ዕለት ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት። ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና፡ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት፡ አስረው ሲደበድቡት አድረዋል።
☞✞ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት። ምራቃቸውን ተፉበት፤ ዘበቱበት። ራሱንም በዘንግ መቱት። እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ።
☞✞ በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት። በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ጊዜ በአለንጋ/በጅራፍ ገረፉት። ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት።
☞✞ ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት። የአምስቱ ቅንዋተ መስቀል ስማቸውም፦
➊ሳዶር፣ ➋አላዶር፣ ➌ዳናት፣ ➍አዴራና ➎ሮዳስ ነበር፡፡
☞✞ ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ። ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ። እነርሱም፦
➊አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
➋ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?አምላኬ አምላኬ ስለምን ተውኸኝ
➌አባት ሆይ ነፍሴን በእጅ አደራ እሰጣለሁ
➍እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከኔ ጋር በገነት ትኖራለህ
➎ተጠማሁ
➏እንሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ እና
➐ተፈፀመ የሚሉት ሲሆኑ
☞✞የአሥራ ሦስቱ ኅማማተ መስቀል ስሞችም፦
➊የኋሊት መታሰር
➋ራሱን በዘንግ መመታት
➌መስቀሉን መሸከም
➍መስቀሉን ተሸክሞ በምድር መውደቅ
➎በእግር መረገጥ
➏በምድር መጎተት
➐ጀርባውን 6666 ጊዜ መገረፍ
➑ፌቱን በጥፌ መመታት
➒መጋፌያው እስኪ ላጥ ድረስ በሀብል ታስሮ መገረፍ
➓በመስቀል ላይ መሰቀል
➊➊በራሱ ላይ የሾህ አክሊል መቀዳጀት(መልበስ)
➊➋መራራ ሀሞት መጠጣት
➊➌በ5ቱ ቅንዋተ መስቀላት መቸንከር እነርሱም ሳዶር ፣አላዶር፡ዳናት ፡አዴራ እና ሮዳስ ናቸው።
•••✞✞✞••• ደግሞም ጌታችን በተሰቀለበት ጊዜ በሰማይ እና በምድር ላይ የተፈፀሙ ተአምራት፦
#በሰማይ ፀሀይ ከ6 ሰዓት እስከ 9 ሰዓት ብርሃኗን ከለከለች፣ ጨረቃ ደም መሰለች፣ ከዋክብት ረገፉ።
#በምድር ምድርም ተናወጠች፣ አለቶች ተሰነጣጠቁ፣ መቃብሮችም ተከፈቱ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፡፡ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ። አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት።
☞✞"የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና። እርሱም ኃጢአት አላደረገም። ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም። ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም። መከራንም ሲቀበል አልዛተም... እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ።"
፩ኛ ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭
☞✞በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ። ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ። ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ። {ማቴ.፳፯፥፩, ማር.፲፭፥፩, ሉቃ.፳፫፥፩, ዮሐ.፲፱፥፩}
🙏✞ጌታችን አምላካችን ፈጣሪያችን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ቅዱስ መስቀሉ: ስለ ድንግል እናቱ ለቅሶና ስለ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ብሎ ይማረን ይቅር ይበለን አሜን ✞🙏
•✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞✞✞•
4 374
በኩረ ሰባኪያን መ/ር ምህረተአብ አሰፋ
በማንቂያ ደወል ባህርዳር ላይ ከሚታየው በላይ እግዚአብሔር በፈቀደ በሚያምር ጉባኤ በዚህ መልኩ በሰላም ተጠናቋል፤ ለሁሉም ምዕመናን እና ምዕመናት በሙሉ ቃለ ህይወት ያሰማልን፤ ዝማሬ መላእክት ያሰማልን🙏🙏🙏
፳፮/፯/፳፻፲፫ ዓ/ም
