ru
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Открыть в Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Больше
4 374
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
ሰባቱ መብራቶች.m4a1.06 MB

ሰላም ለኪ እንዘንሰግድ.m4a9.29 KB

ስምሽን_ጠርቼ_@EOTC2921.3gp2.59 MB

#የአምላክ_እናት_ውበት_በቅዱስ_ቴዎዶጦስና_በቅዱስ_ፕሮክልዩስ ☞✞ሰላምታ የተገባሽ ምልእተ ጸጋ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና፤ አንቺ የተባረክሽ ነሽ (ሉቃ ፩፥፳፰)፤ ከሴቶች ኹሉ በእጅጉ የተዋብሽና በጣሙኑ የተቀደስሽ ነሽ፤ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ ከኹሉም በላይ ቅድስት የኾንሽ ሆይ የተከበርሽና መልካም ነሽ፤ ጌታ ከአንቺ ጋር የኾነ ውዳሴ የተገባሽ ሆይ ተወዳዳሪ የለሽም፣ ከሞገስ በላይ የኾንሽ ሆይ ኹሉ የተትረፈረፈልሽ እግዚአብሔር ያከበረሽ ነሽና ምስጋና ኹሉ ይገባሻል (ሉቃ ፩፥፵፱)፨ ☞✞የእግዚአብሔር ማደሪያው፤ መለኮት የጠበቀሽ የተከባከበሽ ሀብት ነሽ፤ በአንቺም ውስጥ በኀጢአት ውስጥ መፅነስን ወይም በኀጢአት ውስጥ መውለድን በጭራሽ አላውጅም፤ በዚኽ ፈንታ የሔዋንን ሐዘን እንዲበቃ ያደረገው ደስታን አምጥቼያለኊ እንጂ፤ በአንቺ የመከራ ፅንስን ወይም ሕማመ ወሊድን ፈጽሞ አላውጅም፨ ☞✞ንጽሕት፣ ድንግል፣ ነውር የሌለባት፣ ያለነቀፋ የኾነች፣ ምንም ያልነካት፣ ሕጸጽ የማይገኝባት በሥጋም በነፍስም ቅድስት፣ በእሾኽ መኻከል እንደበቀለች የሱፍ አበባ ናት (መሓ ፪፥፩)፤ የሔዋንን ክፋት የማታውቅ፣ የሴትነት የፈቲው ጠባይ ያልታየባት፣ ከመፅነሷ በፊት ለፈጣሪ የተለየች፣ የቤተ መቅደስ እንግዳ፣የሕግ ደቀ መዝሙር የኾነች፣ በመንፈስ ቅዱስ የተቀባች፣ የመለኮትን ጸጋ እንደ ልብስ የተጎናጸፈች ናት” [ቅዱስ ቴዎዶጦስ (†፫፻፫ (303) ዓ.ም] “ያለ ስሕተት ከርሷ ተገኘ፤ ርሷንም ያለነውር እንድትኾን አደረጋት፤ እንዲኹም ማርያም የዐዲስ ፍጥረት ሰማያዊ ምልክት ምሕዋርን ኾነች፤ በዚኽም ምሕዋር የጽድቅ ፀሓይ ለዘላለም ያበራል፤ ርሷንም የኀጢአት ጨለማ ፈጽሞ አላያትም፨ ከእግዚአብሔር እናት የምትበልጥ ታገኝ እንደኾን ሰው ሆይ ፍጥረቱን ኹሉ በሐሳብኽ ዞረኽ እይ፤ ዓለምንና ውቅያኖሶችን ኹሉ ዙር፤ አየሩን ኹሉ መርምር፤ ሰማያትን ጠይቅ፤ የማይታዩትን ኀይላት ኹሉ ዐስብ፤ በድንቅ የሚመስላት ካገኘኽ መርምር ርሷ ብቻ ከቃላት በላይ የኾነች መንገድ ናት፤ መርዓዊ ሰማያዊ ባለበት በሠርግ አዳራሽ በማሕፀኗ ውስጥ ፍጥረት ኹሉ በፊቱ በመፍራትና በመንቀጥቀጥ የሚንበረከኩለትን ያሳደረች ናት”(ፕሮክልዩስ ዘቁስጥንጥንያ (†፬፻፵፮ (446)። ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ •✞ የአምላክ እናት ሆይ እንወድሻለን ዘመናችንን ሁሉ ባርኪልን አሜን ✞•

#ዝሙት_የስጋና_የነፍስ_በሽታ_ነው!!! በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ☞አሁን ባለንበት ዘመን በወንዶችና በሴቶች አደገኛ ፈተና የሆነው ዝሙት ነው። የሰው ልጅ ማለት ሴቷ ወንድ ልጅ የምትፈልግበት ወንዱም ሴት ልጅ የሚፈልግበት የተፈጥሮ ስጦታ አለው ። ቅዱስ ጳውሎስ" ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን" ( 1ኛ ቆሮ 14፥40) እንዳለው ማንኛው ሰው ተፈጥራዊ ስሜት ይንሮው እንጂ እንደ እንስሳ ሳይሆን በስርዓት መሄድ ይኖርበታል ። አንድ ሰው በሂወቱ ሃላፊነት ካልወሰደ በስተቀር ማንም ሃላፊነት ሊወስድለት አይችልም። ወንዱ ይሁን ሴቷ የእግዚአብሔር ሕግ ከማስቀደም ይልቅ ፋሽን እየተባለ ወንዱ በየቀኑ ሴቶችን እንደ ልብስ እየቀያየረ ፣ ሴቷም በየቀኑ ወንዶች እንደ ልብስ እየቀያየረች ወደ ሞት ይነዳሉ። ይህ የዝሙት መንፈስ የተጠናወተበት ሰው በስጋው ይሁን በነፍሱ የረከሰና የድያብሎስ መኖርያ ይሆናል። አላስተዋልም እንጂ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ በዋጋ የገዛን በመሆናችን በራሳችን ላይ ከእግዚአብሔር ሕግ ውጭ የማድረግ ስልጣን የለንም። ሰለዚህ እኛ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፡፡(1ቆሮ 3፥16) ☞ታድያ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ናችሁ ከተባልን የእግዚአብሔር መንፈስ መኖርያ እንሆን ዘንድ ከዝሙት መራቅ አለብን። አለበለዚያ ንስሐ ሳንገባ በዝሙት ተጠምደን የምንኖር ከሆንን ግን ነፍሳችን ከእግዚአብሔር ፀጋ ተራቁታ ወደ ሲኦል ትገባለች። ዝሙት የነፍስና የስጋ በሽታ መሆኑን የአምላክ ቃል እንዲህ ብሎ ያስተምረናል፦ ☞ " ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ፡፡ ( 1ኛ ቆሮ 3:17) #መፅሐፍ_ቅዱስ_ስለ_ዝሙት_እንዲ_ይለናል፦ ☞ " እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል "( ማቴ 5፥32)። ☞ " ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና" ( ማቴ 15፥19)። ☞ " ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ "( ሐዋ.ሥራ 15፥28-29)። ☞ " በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን ( ሮሜ 13፥13)። ☞ " በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና (1ኛ ቆሮ 5፥1)። ☞ " መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው " ( 1ኛ ቆሮ 6:13)። ☞ " ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል" ( 1ኛ ቆሮ 6:18)። #ታድያ_ምን_እናድርግ???? " እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ " (ራእ.ዮሐ 2፥10)። ይህ የህይወት አክሊል የሚገኘው በፆም ፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ ንስሐ ገብተን በቅዱስ ቁርባን መኖር፣ አስራት በኩራት በማውጣት ስንኖር ነው። ቅዱስ አምላካችን በማቴ 6፥33 ላይ " ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል" እንዳለው በምግባር በሃይማኖት ፀንተን ስንኖር የፈለግነው እንደሚሰጠን በተስፋው ቃል እንኖራለን። ☞እህቴ ሆይ ከላይ በማቴ 6:33 የተጻፈውን ስትፈፅሚ አምላካችን ሌላው ይጨመርላችኋል እንዳለን ከዝሙት ለመራቅ፣ ለመተጋገዝና ለመረዳዳት፣ ዘር ለመተካት በአጠቃላይ ለትዳር የሚሆንሽ ወንድ ልጅ ላንቺ ይሰጥሻል። ☞ወንድሜ ሆይ ከላይ በማቴ 6፥33 ላይ የተጻፈውን ስተፈፅም አምላካችን ሌላው ይጨመርላችኋል እንዳለን ከዝሙት እንድትርቅ፣ የምትረዳህና ዘር ለመተካት በአጠቃላይ ለትዳር የምትሆንህ ሴት ልጅ ላንተ ይሰጠሃል። 🙏ንስሐ ገብተን የአምላካችን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙን እንቀበል ዘንድ አምላካችን ይፍቀድልን🙏(ዮሐ 6፥53-56)!!! •✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ለዘላለሙ አሜን ✞•

ባሰማት ጊዜ @EOTC2921.m4a5.64 KB

•✞ #ድንግል_ማርያምና_የዕንቁ_ወፍ_በሊቃውንት ✞• ✞ዕንቆ ባሕርይ የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደችውን ቅድስት ድንግል ማርያምን ቀደምት ሊቃውንት ዕንቁ በምታስገኘው በብርጋና (በከርከቤዴል) ወፍ መስለዋት አስተምረዋል፤ ከሊቃውንቱ ውስጥ የአራቱን ትምህርት ከምሳሌው ጋር "በመጽሐፈ ፊስአልጎስ በግእዝና በዐማርኛ" በሚል ተርጉሜ ካሳተምኩት ጥቂቱን እነሆ ብያለሁ፨ ❖ የአምላክ ከ፲፫፻፶፯- ፲፬፻፲፯ (1357-1417) ዓ.ም. የነበረው ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በሰባቱ ጊዜያት የጸሎት መጽሐፉ (መልክአ ሕማማት) ላይ በመጽሐፈ ፊሳአልጎስ ክፍል ፶፫ ላይ ዕንቊን የምትወልደው የእመቤታችን ምሳሌ የኾነችው የብርጋና ወፍን በምሳሌነት ሲጠቅስ፡- “ማርያም ባሕርይ ጽድልተ ንጻሬ ወዜና እምጸዳል ዕንቈ በማሕፀና ዘትወልድ ዖፈ ብርጋና” (ከብርሃን ዕንቊን በማሕፀኗ የምትወልድ የብርጋና ዎፍ በመባል የታወቅሽ ታሪኳና ፊቷ የሚያበራ (ስመ ጥርና ብርኅተ ገጽ) የተባልሽ ባሕርይ (ዕንቊ) ማርያም ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል) ይላታል፡፡ ❖ ይኽቺ በመጽሐፈ ፊስአልጎስና በአክሲማሮስ የተጠቀሰችው ብርጋና የተባለችው ዎፍ የምትፀንሰው በመዠመሪያው ወር፣ በሦስተኛው ወር፣ በስድስተኛው ወር ነው፤ ይኽቺም ዎፍ ከወንዱ በዘር አትፀንስም፤ ከባሕር ወጥታ ሦስት መዓርግ ከፍ ብላ ወደ ሰማይ ወጥታ ወደ ፀሓይ ተጠግታ መላ አካሏን ከተመታች በኋላ ገላዋ ሲተኩስ ረባ ወርዳ ወደ ጥልቅ ባሕር ትገባለች፤ ያን ጊዜ ረባ ወርዳ ወደ ጥልቅ ባሕር ስትጠልቅ ከጸዳለ ፀሓይ ከውሃ ጠል ተከፍሎ በማሕፀኗ ይፀነሳል ይላሉ፡፡ ❖ ይኽቺም “ንጽሕት እምአዕዋፍ” (ከአዕዋፍ የነጻች) ስትባል ስትፀንስም በግራ ማሕፀኗ አዕዋፍን በቀኝ ማሕፀኗ የተለያዩ አዕናቁ ካስገኘች በኋላ በመጨረሻው ክቡር ዕንቊን ታስገኛለች፤ ይኽነንም ዕንቊ ዓሣ ተቀብሎ ይውጠዋል፤ በዋጠውም ጊዜ የዚኽ ዕንቊ ብርሃን የዓሣውን አካልና የባሕሩን ጥልቀት ሠንጥቆ ከባሕር ዳርቻ ላሉት ሰዎች ይታያቸዋል። ❖ ከዚኽ በኋላ ጠቢባኑ ብርሃን የማይከለክል ውሃ የማያስገባ ልብስ ተጐናጽፈው ገብተው ዓሣውን በቀስት ነድፈው በመግደል ዕንቁዉን አውጥተው ለነጋዴ ይሸጡታል፤ አንድም ዓሣው ምግቡን ለመፈለግ ወደ ዳር ይወጣል፤ ሰዎችም በግራና በቀኝ ጎጆ ሠርተው ይጠብቁታል፤ ዓሣውም ምግቡን ሲፈልግ በቀስት ገድለው ዕንቁዉን አውጥተው ለነጋዴ ይሸጡታል፨ ❖ ይኽም ነጋዴ ለነጋዴ ሲወዳጅ ወደ ቤተ መንግሥት ይደርሳል ይላሉ፡፡ ❖ ዖፈ ብርጋና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፤ ምሳሌነቷም እንደምንድነው? ቢሉ ይኽቺ ብርጋና “ንጽሕት እምአዕዋፍ” (ከአዕዋፍ የነጻች) እንደኾነች እመቤታችንም “ንጽሕት እምልማደ አንስት” (ከሴቶች ልማደ ተፈጥሮ ኹሉ የነጻች) ናትና (መሓ ፬፥፯፤ ሉቃ ፩፥፳፰)፨ ❖ ዖፈ ብርጋና ያለ ዘር እንደፀነሰች እመቤታችንም ያለ ዘርዐ ብእሲ አምላክን ፀንሳለች (ማቴ ፩፥፲፰)። ❖ ዳግመኛም ዖፈ ብርጋና ሦስት መዓርጋት ከፍ ብላ ወጥታ ከፀሓይ ተመትታ ዕንቊን እንዳስገኘች እመቤታችንም ሦስት መዓርጋተ ትውልድ ዐልፋ በአራተኛው ክፍለ ዘመን በዘመነ ካህናት በአራተኛው መዓርገ ትውልድ ከነገደ ይሁዳ ተወልዳ ዕንቈ ባሕርይ አምላክን በድንግልና ወልዳ አስገኝታልናለችና (ራእ ፭፥፭) ይላል፡፡ ❖ በርካቶች ሊቃውንት ይኽቺን ዎፍ ለምሳሌነት ሲጠቀሙባት የመልክአ ኢየሱስ ደራሲ አባ ዐምደ ሐዋርያት በዚኽች ወፍ አንጻር በመመሰል ሲያስተምር፦ “ኢየሱስ ክርስቶስ በላዕለ ቅዱሳን ዕሩፍ ይፀነስ ውስተ ከርሥየ ዘርዐ ቃልከ መጽሐፍ ጸዳለ እምጸዳል ከመ ትፀንስ ዖፍ” (በቅዱሳን ላይ ዐድረኽ የምትኖር ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የቃልኽ ዘር መጽሐፍ በማሕፀነ አእምሮዬ ይፀነስ፤ ዎፍ ጸዳልን ከጸዳል እንድትፀንስ) በማለት የወንጌል ትምህርት በአእምሮው እንዲቀረጽበት ተማፅኗል፡፡ ❖ ዳግመኛም የማሕሌተ ጽጌ ደራስያን አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በመጽሐፋቸው ላይ ከዚኽ ምስጢር በመነሣት የብርጋና ወፍ የወለደችውን ዕንቊ ስለሚውጠው ዓሣ ሲያስተምሩ ፦ ❖ “ዓሣ ባሕርኒ እንዘ ይጸውር ወርቀ ይጸብት ቀላያተ ወየዐርግ ሐይቀ” (የባሕር ዓሣም ወርቅን ተሸክሞ በባሕር ላይ ዋኝቶ ከጥልቁ ይወጣል) በማለት አስቀምጠውታል፡፡ ❖ የረቀቀ የሥነ ፍጥረት ዕውቀት የነበረው ሊቁም በመጽሐፈ ፊስአልጎስ ክፍል ፶፫ ላይ ስለ ብርጋና ዎፍ ምሳሌነት ይኽን ይላል፦ “በእንተ አክሊጦስ ወመርጋሊጦስ ዘውእቱ ብርጋና ሶበ ይፈቅድ ኖትያዊ ኬንያ ከመ ይርከብ ባሕርየ፤ የኀሥሥ መሥገርተ ወያወርድ ውስተ ባሕር እንዘ የአስር መቃጥነ በጽኑዕ ሀብል..." (ይኽ ክፍል ስለ አክሊጦስና መርጋሊጦስ የሚናገር ነው፤ ያም ብርጋና ነው፤ ጠቢብ ዋናተኛ ዕንቊን ሊያገኝ በወደደ ጊዜ ወጥመድን ፈልጎ በጠንካራ ገመድ መንጠቆን በማሰር ወደ ባሕር ውስጥ ያወርዳል፤ ያን ጊዜ መንጠቆውን ከቦታው ያንቀሳቅሰውና ያነቃንቀው እንደኾነ ለማየት ወደ ባሕሩ ዳርቻ ቀርቦ ይቆማል፤ ባንቀሳቀሰው ጊዜ ዕንቁዉን እስኪያገኙት ድረስ መንጠቆውን ወደ ኼደበት ይከተሉታል። ተናጋሪ እንዲኽ አለ ዕንቊ ከምን ይገኛል፤ ምላሽ ያውም ብርጋና ነው፤ ስሙ ኮንኮስ ከሚባል ዎፍ፤ ርሱ ግን የፀሓይ ሙቀትን ከመቀበል ጋራ የውሃ ቅዝቃዜንና የሰማያትን ጠልን በመሳብ አፉን ከፍቶ ሳለ ወደ ምሥራቅ ዳርቻ ይወጣል፤ የከዋክብትንና የጨረቃን ድምቀት ከማየት የተነሣ ዕንቊ ከብርጋና ማሕፀን ይወለዳል፤ ዕንቊ ከርሷ የሚገኝ ብርጋና ኹለት ክንፎች አሏት። ዕንቊም የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌው ነው፤ ዮሐንስ ስለ ርሱ “እነሆ የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በጉ ነው” አለ (ዮሐ ፩፥፳፱)፤ ብርጋናም ያለ ሩካቤ የወለደችው በኾነች በማርያም ትመሰላለች፤ ኹለቱ ክንፎችም በድንግልናዋ ይነገራሉ (በድንግልናዋ ይተረጐማሉ)፤ ጨረቃና ከዋክብት በመንፈስ ቅዱስ፤ ፀሓይም የፍጥረት ኹሉ መብራት በኾነ በአብ አምሳል ነው፤ ሰው ሆይ አንተም ሀብትኽን ኹሉ ሽጠኽ ለነዳያን ስጥ፤ የሰማያት ድልብን ሰብስብ፤ ያውም ዋጋው እጅግ የበዛ የኾነ የሕይወት ዕንቊ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ዳግመኛም ብዙውን እንድታገኝ በትንሹ ተወጃጅ (ማቴ ፲፱፥፳፩))፡፡ በማለት ድንቁን ምስጢር ያስቀምጠዋል፨ [የአምላክ እናት ሆይ ዕንቆ ባሕርይ ከሚባል ልጅሽ ከአእምሯችን ድንቁርናን አርቆ ከርሱ በሚገኘው ዕውቀት ብሩህ ያደርገው ዘንድ ዘወትር ለምኚልን፤ እንወድሻለን ] [መጽሐፈ ፊስአልጎስ በግእዝና በዐማርኛ ከሚለው በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ከግእዝ ተተርጉሞ ከታተመ መጽሐፍ የተወሰደ]

"ይህችን ዓመት ተወኝ!" ከዓመትእስከ ዓመት - ፍሬን ሳላፈራ - ደረቅ እንደሆንኩኝ በራድ ወይም ትኩስ - ሁለቱንም ሳልሆን - እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ አለሁኝ በቤትህ - ለሙን መሬትህን - እያጎሳቆልኩኝ አውቃለሁ አምላኬ - ፍሬዬን ለመልቀም - እንዳመላለስኩህ ዛሬም ሳላፈራ - እሾህን አብቅዬ - ደርቄ ጠበቅሁህ ያልተደረገልኝ - ያላፈሰሰክብኝ - ያልሰጠኸኝ የለም ነገር ግን ይህ ሁሉ - አላርምህ አለኝ - አልለየኝም ከዓለም የማትሰለቸኝ ሆይ - ተነሥቼ እስክቆም - እባክህ ታገሠኝ የእኔን ክፋት ተወው - መልአክህን ሰምተህ - ይህችን ዓመት ተወኝ! አውቃለሁታውቃለህ - ቀጠሮን ሰጥቼ - እንደማላከብር ብዙ ጊዜ አቅጄ - ብዙ ጊዜ ዝቼ - በወሬ እንደምቀር ‹ዘንድሮስ…!›እንዳልኩኝ - አምና ይሄን ጊዜ - ሰምተኸኝ ነበረ ምንም ሳልለወጥ - ‹ዘንድሮዬ› አልፎ - በአዲስ ተቀየረ ፍሬ የማይወጣኝ - እኔን በመኮትኮት - እጆችህ ደከሙ እኔ ግን አለሁኝ - ዛሬም አልበቃኝም - በኃጢአት መታመሙ የቃልህን ውኃ - በድንጋይ ልጅህ ላይ - ሳትታክት ስታፈስስ - ዘመን ተቆጠረ ወደ ልቤ ሳይሰርግ - ሕይወቴን ሳይለውጥ - እንዲያው ፈስሶ ቀረ ቃልህን ጠግቤ - እያገሳሁት ነው - ሌሎች እስኪሰሙ በቃልህ መኖር ግን - አልያዝህ አለኝ - ከበደኝ ቀለሙ ብዙ ጥቅስ አገኘሁ - ከቅዱስ መጽሐፍህ - ገልጬ አይቼ ከራሴ ላይ ብቻ - አንድ ጥቅስ አጣሁኝ - በበደል ተኝቼ ውጤቴ ደካማ - ትምህርት የማይሠርጸኝ - ተማሪ ብሆንም ይህችን ዓመት ተወኝ - ደግሞ ትንሽ ልማር - ታገሠኝ አሁንም! እባክህአልቆረጥ - በቅዱስ መሬትህ - ልቆይ ፍቀድልኝ ያፈሩት ቅዱሳን - የፍሬያቸው ሽታ - መዓዛ እንዲደርሰኝ የተሸከምከኝ ሆይ - ዛሬም ተሸከመኝ - አትሰልቸኝ አደራ ማን ይታገሠኛል - ጠላት እየሆንኩት - አይሠሩ ስሠራ! አታውጣኝከቤትህ - ብዙ ቦታ አልይዝም - ፍሬ ስለሌለኝ ስፍራ የማያሻኝ - ቤት የማላጣብብ - ፍሬ አልባ በለስ ነኝ! ቦታስየሚይዙት - ባለ ምግባሮቹ - ቅዱሳንህ ናቸው ልክ እንደ ዘንባባ - የተንዠረገገ - ተጋድሎ ጽድቃቸው! ከሊባኖስዝግባ - እጅጉን የበዛ - ገድል ትሩፋታቸው! እኔአይደለሁም - ቦታስ የምትይዘው - የአንተው እናት ናት ሥሮቿ በምድር - ጫፎቿ በሰማይ - ሲደርሱ ያየናት ይሀችን ዓመት ተወኝ - ከሥርዋ እሆናለሁ - ባፈራ ምናልባት!.. ይህችን ዓመት ተወኝ - እባክህ አምላኬ - አንድ ዓመት ምንህ ናት ሺህ ዓመት አንድ ቀን - አይደለም ወይ ለአንተ - ዓመት ኢምንት ናት! ይሄዓመት አልፎ - ዳግም ‹ዓመት ሥጠኝ› - እስከምልህ ድረስ እባክህን ጌታ - ይህችን ዓመት ተወኝ - የወጉን እንዳደርስ!

♥ ከንፈሮችሽም የደስታ ምንጮች ናቸው፤ አንደበትሽም የምስጋና መፍለቂያ ነው፤ እጅግ በጣም አማርሽ፤ ቁመትሽም እንደ ዘንባባ ዛፍ ነው፤ የልብሶችሽ መዐዛም አፈው በመባል እንደሚታወቀው ሽቱ፤ የአፍንጫሽ መዐዛም እንደ ወይን አበባ ሽታ የሚኾንልሽ ድንግል ሆይ ደስታሽን እወደዋለኊ (ማሕ ፯፥፰) የአፍሽም አከፋፈት እንደ ቀናንሞስ አበባ የጣፈጠ ነው፤ ከሊባኖስ ዕንጨቶች ኹሉ ጋር (ማሕ ፬፥፲፬)) በማለት እንደ ሰሎሞን ርሱም የፈጣሪውን እናት አመስግኗል፡፡ ♥ የፈጣሪያችን እናት ቅድስት ድንግል የተወለደችበትን ግንቦት አንድን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን “ልደታ ለማርያም” በማለት ከጥንት ዠምሮ በታላቅ መንፈሳዊ ሐሤት በቅዳሴ፣ በማሕሌት የምታከብርላት ሲኾን፤ በተለያዩ ክፍላተ ዓለማት ያሉ ክርስቲያኖችም ይኽነን በዓል “The Nativity of the blessed Virgin Mary” (የተባረከችው የድንግል ማርያም ልደት (መወለድ)) በማለት ያስባሉ። ♥ በጥንት ምሥራቃውያን (እንደ ቤዛንታይን ባሉ) ዘንድ ዐዲሱ ዓመት ልክ እንደኛ መስከረም ወር “September” ላይ ይውል ስለነበር ከዚኽ አያይዘው መስከረም ፰ (September 8) ያከብሩት የነበረ እንደነበር ታሪክ ሲያስረዳ ይኽነን ይዘው በዚኽ ዕለትም የሚያከብሩት ብዙዎች የዓለማት ሀገራት አሉ፡፡ ✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ [ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፤ ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል አንድ ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ] #የአምላክ_እናት_በረከቷ_በእኛ_በአደራ_ልጆቿ_ላይ_በዝቶ_ይደር፡፡

ፈጣሪያችን ክርስቶስን በድንቅ ተአምር ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ የወለደችልን ምክንያተ ድኂን ርግበ ሰሎሞን የተባለች የቅድስት ድንግልን የመፀነሷን ነገር በአድናቆት ገልጸዋል፡፡ ♥ “ወእምድኅረ ስድስቱ አውራኅ ተዐውቀ ፅንሳ ለሐና” ይላል፤ ከስድስት ወርም በኋላ የሐና ፅንሷ እየታወቀ ሲመጣ ጎረቤቶቿ መፅነሷን ይረዱ ዘንድ በአድናቆት ማሕፀኗን ይዳስሱ ነበር፤ በተለይም ዐይኗ የታወረ የሐና ዘመዷ የአርሳባን ልጅ የምትኾን አንዲት ሴት የሐናን ማሕፀን ዳስሳ ዐይኗን ብትነካው በርቶላት በታላቅ ደስታ ኾና “ብፅዓን ለኪ ኦ ሐና እስመ እም ፍጥረተ ዓለም አልቦ ዘከማኪ ዘይፌውስ በከርሡ አዕይንተ ዕውራን” (ሐና ሆይ ብፅዓን ይገባሻል ዓለም ከተፈጠረ ዠምሮ እንዳንቺ በማሕፀኑ የዕውራንን ዐይን የሚያበራ የለምና) በማለት አመስግናታለች፤ ከዚኽ በኋላ ዝናዋ በሀገሩ ኹሉ ተሰምቶ ሕሙማን ኹሉ ማሕፀኗን እየዳሰሱ ይፈወሱ ነበር፡፡ ♥ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ይኽነን ሲገልጹ፦ ✍ “ጸግይየ ሣዕረ ዘኪሩቤል ልሳነ ተአምረኪ በነጊር እመ ኢፈጸምኩ አነ ባሕቱ አአኲት ማርያም ዘጾረተኪ ማሕፀነ እንዘ ሀለወት ፀኒሳ ኪያኪ ርጢነ ለለገሰስዋ ላቲ ትፌውስ ዱያነ” ♥ (ሳርን የኾንኊ እኔ የኪሩቤል አንደበትን ገንዘብ አድርጌ ታምርሽን በመንገር በማስተማር ባልፈጽምም ነገር ግን ማርያም የተሸከመቺሽን ማሕፀን አመሰግናለኊ፤ መድኀኒት አንቺን ፀንሳ ሳለች ርሷን የዳሰሷትን ድዉያንን ኹሉ ትፈውስ ነበር) በማለት እመ መድኅነ ዓለም ገና ሳትወለድ የተሠራውን ድንቅ ተአምር አመስግነዋል፡፡ ♥ ይኽ የቅድስት ድንግል ማርያም የፅንሰት በዓል በመላው ዓለም የሚታወቅ ሲኾን ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት የኾነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን የአምላክ እናት የተፀነሰችበት ይኽነን በዓል ነሐሴ ፯ ቀን በታላቅ ድምቀት በማሕሌት፣ በቅዳሴ የምታስበው ሲኾን በዓሉም “ፅንሰታ ለማርያም” በመባል ይታወቃል። ♥ በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ደግሞ በዓሉን “The conception of the Theotokos” (የአምላክ እናት መፀነስ) በማለት ሲያከብሩት ወሩን ግን የልደት በዓልን ለማክበር በሚዘጋጁበት በታኅሣሥ አድርገው በ፱ኛው ቀን “December 9” ላይ ያስቡታል ፡፡ ♥ በእጅጉ የሚደንቀው ደግሞ “ሳሚናስ ወልደ ጦሊቅ ዘይነብር ውስተ ቤተ ዶይቅ” ይላል ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጐቱ ቤት ኼዶ ሞተ፤ ሐናም በሀገራቸው ልማድ የአልጋውን ሸንኮር ይዛ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ፈጥኖ ተነሥቶ “ሰላም ለኪ ኦ ሐና እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ” (ሰማይና ምድርን ለፈጠረው አምላክ አያቱን የተባልሽ ሐና ሰላም ላንቺ ይኹን) አላት። ♥ ከዚያ የነበሩ አይሁድም በመደናገጥ “ሳሚናስ ምን አየኽ? ምን ትላለኽ?” አሉት፤ ርሱም “ከዚች ከሐና ማሕፀን የምትወለደው ሕፃን ሰማይ ምድርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ኹሉ ሲያመሰግኗት ሰማኋቸው፤ እኔንም ያነሣችኝ ርሷ ናት” አላቸው፤ እነርሱም ይኽነን በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔርን ከማመስገን ይልቅ በቅናትና በክፋት ተመልተው ሐና በማሕፀን ባለ ፅንሷ ካዳነች በኛ ላይ ልትሠለጥን አይደለምን? “ንዑ ንገሮሙ ለሐና ወለኢያቄም” ሳትወልድ አስቀድመን ሐናና ኢያቄምን በድንጋይ ወግረን እንግደላቸው ብለው ተነሣሡባቸው። ♥ ያን ጊዜ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ሐናን ሊባኖስ ወደሚባል ተራራ እንዲወስዳት ነገረው፤ ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ እመቤታችን በሊባኖስ ተራራ እንደምትወለድ ተገልጾለት፡- ✍“ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ንዒ ወተወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን አምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት” (ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነዪ ከሊባኖስ ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ) በማለት የተናገረው ትንቢት ሊፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም በ፭ ሺሕ ፬፻፹፭ (5485) ዓመተ ዓለም በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች (ማሕ ፬፥፲)፡፡ ♥ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ የነገረ ማርያም መጽሐፋቸው ላይም፦ “ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ ማእከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ እንዘ እነቡ እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዐጽ እሌቡ ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ” ♥ (ትንቢት ከተነገረለት ከአንበሳ ጉድጓድ፤ ድንግል ሙሽራ በተገኘሽ ጊዜ የንጉሦች ንጉሥ የሰሎሞን ልቡ እንደተደሰተ፤ ደስ ባላቸው በመላእክት አንድነት ፊት ታምርሽን እየተናገርኊ የሐና አበባ ማርያም እዘምርሻለኊ፤ ወተትን ጠብቶ እንደሚዘልል እንቦሳም ዝለል ዝለል ይለኛል) በማለት ሰሎሞን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን አግኝቶ ታላቅ ደስታን ለኹላችን እንደሰጠን አብራርተው ገልጠዋል፡፡ ♥ ይኽ የእመቤታችን ልደት ለሰማያውያን መላእክትና ለደቂቀ አዳም ደስታ ሲኾን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከርሷ ተወልዶ ዲያብሎስ ፭ሺሕ፭፻ ዘመን በሲኦል ያኖራቸውን ነፍሳት ወደ ገነት የሚያስገባቸው ነውና፤ ሰይጣን በተቃራኒው ልደቷ እንዳላስደሰተው ሲገልጹ፦ ✍ “ተፈሥሐት ምድር ወሰማይ አንፈርዐጸ በዕለተ ጸገዩኪ አብላስ ወአውጽኡ ሠርጸ ተአምረ ሕይወት ማርያም ዘአልብኪ ቢጸ እስከ ፈርሀ መልአከ ሞት ወሰይጣን ደንገጸ ዜና ልደትኪ ነጐድጓድ እስከ (ውስተ) ሲኦል ደምፀ” (በለሶች (ኢያቄምና ሐና) ቡቃያ አንቺን ባስገኙሽ ጊዜ ምድር ደስ አላት ሰማይም ደስ አለው፤ ጓደኛ (ምሳሌ) የሌለሽ የድኅነት ምልክት ማርያም፤ መልአከ ሞት እስከ ፈራና ሰይጣንም እስከ ደነገጠ ድረስ የመወለድሽ ዜና እስከ ሲኦል ድረስ (በሲኦል) ተሰማ) በማለት አስተምረዋል፡፡ ♥ ጠቢቡ ሰሎሞን አስቀድሞ በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ በማሕልዩ ላይ “መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ትሔውጽ ከመ ጎሕ ሠናይት ከመ ወርኅ ወብርህት ከመ ፀሓይ” (ይኽቺ እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ እንደ ጨረቃ የተዋበች፤ እንደ ፀሓይም የጠራች ዐላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሰራዊት የምታስፈራ ማን ናት?) በማለት እንደ ፀሓይ የሞቀ እንደ ጨረቃ የደመቀ ንጽሕናዋና ቅድስናዋ የመልኳ ደም ግባት በነቢያት ትንቢት አስቀድሞ የተጐበኘላት የእውነት ፀሓይ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብርና ደም ግባቷን እንደተናገረ በሊባኖስ ተራራ በግንቦት ፩ በተወለደች ጊዜ ፊቷ በእጅጉ ያበራ ነበር፤ መዐዛዋም ከሽቱ ኹሉ ይበልጥ ነበር፡፡ ♥ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም የመዐዛዋን አስደናቂነት በሰሎሞንን ቃል በመነሣት የመዐዛዋን ነገር ሲያደንቅ፡- ✍ “ወእወዲ ውስተ አፉየ እምፍሬ ከርሥኪ…” (ከማሕፀንሽም ፍሬ ወደ አፌ እጨምራለኊ፤ የፍሬሽ ደምም ለጉሮሮዬ የጣፈጠ ነው፤ የሽቱሽ መዐዛም ለአፍንጫዬ ያማረ ነው፤ የድንግልናሽ ክብርም ልቡናዬን እንደ ከረመ ንጹሕ ወይን ደስ ያሰኘዋል፤ ስለ አንቺ ያለኝ ደስታ ምን ያኽል ነው፤ አነጋገርሽ ያማረ ነው፤ ቃልሽም የጣፈጠ ነው።

#የአምላክ_እናት_ልደት____ልደታ_ለማርያም በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ♥ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት መተርጒማን እንዳስተማሩንና እንደጻፉልን በእናቷ በሐና በኩል ያሉ የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ጴጥሪቃ ቴክታ ሲባሉ “ወኮኑ ክልኤሆሙ ጻድቃን ወፈራህያነ እግዚአብሔር ወይትአመንዎ ለአምላኮሙ በጥቡዕ ልብ እንበለ ኑፋቄ” ይላል (ኹለቱም ሰዎች ደጋጐችና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ያለምንም መጠራጠር በፍጹም ልቡናቸው በአምላካቸው የሚተማመኑ ነበሩ)፤ እነርሱም በጊዜው ይኽ ቀራችኊ የማይባሉ ባለጠጎች ነበሩ፤ ከሀብታቸው ብዛት የተነሣ ወርቁን ብሩን እንደ ዋንጫ እያሠሩ በላሙ በበሬው ቀንድ ላይ ይሰኩት ነበር፤ ይኽን ያኽል አቅርንተ ወርቅ፣ አቅርንተ ብሩር እየተባለ ይቈጠር ነበር፤ የዕንቊ ጽዋ እንኳ ፸፣ ፹ ያኽል ነበራቸው ይላል፡፡ ♥ ከዕለታት ባንዳቸው ጴጥሪቃ ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ የሀብቱን ብዛት አይቶ ሚስቱ ቴክታን “ለመኑ ዘዘገብነ መዛግብቲነ አልብነ ውሉድ ዘይወርሰነ አንቲኒ ወአነሂ መካን ንሕነ” (የሰበሰብነው ገንዘብ ስንኳን ለኛ ለልጅ ልጅ ይተርፍ ነበር አንቺም እኔም መካኖች ነንና የሚወርሰን ልጅ የለንም) በማለት ተናገራት፤ ርሷም እንዲኽ ማለቱ ወላድ የፈለገ መስሏት በሐዘን ኾና “አምላከ እስራኤል ከኔ ልጅ ባይሰጥኽ ከሌላ ይሰጥኽ ይኾናልና ሌላ አግብተኽ ውለድ” አለችው፤ ርሱም “አነሂ ኢይፈቅድ የአምር አምላከ እስራኤል ከመ ኢየሐስቦ ለልብየ” (ይኽንስ እንዳላደርገው በልቤም እንዳላስበው የእስራኤል አምላክ ያውቃል) በማለት ተናገረ፡፡ ♥ ርሷም ዐዝና ሳለ ራእይ ታያለች፤ ነጭ እንቦሳ ከማሕፀኗ ስትወጣ እንቦሳዪቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ሰባት ስትደርስ ሰባተኛዋ ጨረቃን ስትወልድ፤ ጨረቃ ፀሓይን ስትወልድ አይታ በአድናቆት ለባሏ፦ ❖ “ግሩም ግብሩ ለእግዚአብሔር ትማልም ርኢኩ በሕልምየ ጸዐዳ ጣዕዋ ወጽአት እምከርሥየ ይእቲኒ ወለደት ጸዐዳ ጣዕዋ እስከ ሰብዐቲሆን ወሳብዕታኒ ወለደት ወርኀ ወወርኅኒ ወለደት ፀሓየ” ♥ (የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው፤ ትናንትና ማታ በሕልሜ ነጭ ጥጃ ከማሕፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ደግሞ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንደዚኽ እየኾነ እስከ ሰባት ትውልድ ሲደርሱ ሰባተኛዪቷም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየኊ) በማለት አስረዳችው። ♥ ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ሕልም ወደሚፈታ ሰው ዘንድ በመኼድ የሚስቱን ራእይ ነገረው፤ ያም ሕልም ተርጓሚ ምስጢር ተገልጾለት ሰባት አንስት ጥጆች መውለዳችኊ ሰባት ሴቶች ልጆች ይወለዳሉ፤ ነጭ መኾናቸው ደጋጎች ልጆች መኾናቸው ሲኾን “ወሳብእታኒ ትከብር እመላእክት ወትትሌዐል እምኲሉ ሰብእ ወበእንተ ፀሓይኒ ኢያእመርኩ” (ሰባተኛዪቱ ጨረቃን መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ናት፤ የፀሓይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም) በማለት ተረጐመለት፤ ርሱም ለሚስቱ ነገራት፤ ርሷም “የእስራኤል አምላክ የሚያደርገውን ርሱ ያውቃል” በማለት ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ ♥ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች ስሟንም ሔሜን አሏት፤ ሔሜን → ዴርዴን ወለደች፤ ዴርዴም → ቶናን፤ ቶናም →ሲካርን ወለደች፤ ሲካርም→ ሴትናን፤ ሴትናም →ሔርሜላን ወለደች፤ ሔርሜላም የተከበረችና የተመረጠች ዓለሙን ኹሉ ለፈጠረ ጌታ አያት ለመኾን የበቃች ሐናን ወልዳለች። ♥ ሐናና ኢያቄምንም “ወክልኤሆሙ ኄራን ወሥሙራን እሙንቱ ወየሐውሩ በሕገ እግዚአብሔር እስመ እግዚአብሔር ኀረዮሙ ወአፍቀሮሙ ትካት” ይላቸዋል እግዚአብሔርን የሚወድዱ በሕጉ የሚኖሩ ደጋጎችና አምላክም የመረጣቸው ሲኾኑ ሐና መካን በመኾኗ ምክንያት ኹለቱም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ዕለት ዕለት በመኼድ ለዐይናቸው ማረፊያ ለልባቸው ተስፋ የሚኾን ልጅ እንዲሰጣቸው ይለምኑ እንደነበር፤ “Protoevangelium of James” (ፕሮቶቫንጊሊዩም ኦፍ ጀምስ) የሚለው ያዕቆብ የጻፈው ጥንታዊዉ መጽሐፍ በስፋት ይገልጻል፡፡ ♥ ከዕለታት ባንደኛው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ሲመለሱ “ወርእዩ አርጋበ እንዘ ይትፌሥሑ ምስለ ውሉዶሙ” ይላል ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ደስ ብሏቸው ሲጫወቱ አይተው ሐና “አቤቱ ጌታዬ ግዕዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠኽ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሣኸኝ” ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፤ ወዲያው ሱባዔ ይገባሉ፤ ኢያቄም ወደ በረሓ ኼዶ ሲጸልይ ሐና ደግሞ በቤቷ ዙሪያ ባለው የተክል ቦታ ሱባዔ ያዘች። ♥ በሱባዔያቸው ፍጻሜ ኹለቱም ራእይ አይተው ተነጋግረዋል፡፡ “ይቤላ ኢያቄም ለሐና ብእሲቱ እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ” ይላል ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዎፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ብሎ የተገለጸለትን ለሐና ነግሯታል። ♥ ይኸውም የራእዩ ምስጢር፡- ወፍ የተባለው አካላዊ ቃል ክርስቶስ ሲኾን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፤ ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ ሲያጠይቅ ሲኾን፤ ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ምልአቱ፣ ስፍሐቱ፣ ርቀቱ፣ ልዕልናው፣ ዕበዩ ናቸው፡፡ ♥ ሐናም ተገልጾላት “ትቤሎ ሐና ለኢያቄም ብእሲሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ” ይላል ለባሏ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ብላዋለች። ♥ ይኽ የራእይ ምስጢር፡- ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትኾን፤ ነጭነቷ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፤ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ ወደ ዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በዦሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መኾኗን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ♥ ኢያቄምና ሐናም ይኽነን ራእይ ሐምሌ ፴ ቀን ካዩ በኋላ “ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ይኾናል፤ ሴትም ብንወልድ ለቤተ እግዚአብሔር መጋረጃ ፈትላ ትኑር” ብለው ስእለት ከተሳሉ በኋላ ራእይ አየን ብለው ዕለቱን አልተገናኙም፤ አዳምንና ሔዋንን “ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት” ብሎ የተናገረው አምላክ ለእኛም ይግለጽልን ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ሰባት ቀን ድረስ እየብቻቸው ሰነበቱ። ♥ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን “ከሰው የበለጠች ከመላእክት ኹሉ የከበረች ልጅ ትወልዳላችኊ" ብሎ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለሐና ነግሯት በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን ነሐሴ ሰባት እሑድ ተፀንሳለች፤ በእናቷ ማሕፀን ሳለችም “መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እምከርሠ እማ” እንዲል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥንተ አብሶ ባመጣው መርገም እንዳትያዝ ጠብቋታል፡፡ ♥ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም መፀነስ ከሊቃውንት መኻከል አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ፦ ✍ “ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ ወፈረየኪ ለሕይወት ኢያቄም መዋቲ እሴብሕ ተአምረኪ ርግብየ አሐቲ ወድኀኒተ ኲሉ ዓለም እስመ ኮንኪ አንቲ” ♥ (ሐና አንቺን የፀነሰችባት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ አንዲቱ ርግቤ ማርያም አንቺ የዓለሙ ኹሉ መድኀኒት ኾነሻልና ታምርሽን አመሰግናለኊ) በማለት ዓለምን ኹሉ በደሙ ፈሳሽነት ያዳነ ንጉሣችን፣

•✞✞✞ #ግን_መቼ_ነው ? ? ? ✞✞✞• ☞መቼ ነው ፣ እውነተኛ ክርስቲያን የምሆነው? ? ☞መቼ ነው ፣ እግዚአብሔርን መፍራት የምጀምረው? ? ☞መቼ ነው ፣ እግዚአብሔርን ማመስገን የምጀምረው? ? እስከመቼስ ነው በዋዛ በፈዛዛ ጊዜየን የምጨርሰው? ? ☞በከንቱ ጊዜዬን እጨርሳለሁ እፍፍፍ መቼ ነው ፣ እግዚአብሔር በሰጠኝ ነገር ደስተኛ የምሆነው ? ? ሁልግዜ አማርረዋለሁ ግን ለምን? ☞ኦ አምላኬ እዳስተውል እርዳኝ መቼ ነው ፣ ሰውን እደራሴ አድርጌ የምወደው? ? ☞መቼ ነው ፣ ለጠሉኝ ሁሉ መልካም የማደርገው ? ? እኮ መቼ? ☞መቼ ነው? እግዚአብሔር ለምን እደፈጠረኝ የምረዳው? ? ☞እኔማ ሁሌም በአለም ከንቱነት ጠፋሁ አለም አታለለችኝ ☞መቼ ነው ፣ እግዚአብሔር እንደፈለገው መኖር የምጀምረው ? ? ☞እኮ መቼ? እድሜዬን አንድም ቀን መልካም ሳልሰራበት..? ☞መቼ ነው፣ ክፉ ንግግር ከመናገር ተንኮል ከመስራት የምቆጠበው ? ? ☞መቼ ነው ፣ለፆም ለፀሎትና ለስግደት በሙሉ ልቤ ሆኘ የማገለግለው እኮ መቼ? ? ☞መቼ ነው፣ ለመልካም ስራ ምሳሌ የምሆነው? ? ☞መቼ ነው ፣ ይህን ከንቱ አለም ከልቤ የማወጣው ? ? ? እኮ መቼ ? ☞መቼ ነው ፣ እኔ ማለት ትቼ እህት ወንድሞቼ ወገኖቼ ማለት የምጀምረው ? ሁሌም እራስ ወዳድ እፍፍፍፍ.... ☞መቼ ነው ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የማከብረው ? ?? ☞እኮ መቼ ነው እንደ ቃሉ የምኖረው ? ☞እስከመቼስ ነው የሚፈልገውን ነገር ትቼ የሚጠላውን ነገር የምከተለው እፍፍፍ.... ☞መቼ ነው ፣ ጥሩ እና ለጋሽ አዛኝ የምሆነው? ? ☞መቼ ነው ፣ በፍቅር መኖር የምጀምረው ? ? ? ሁልጊዜ ልቤ በጥላቻ ተሞልቷል... ☞መቼ ነው ሰውን ከመበደል ከማስቀየም የምቆጠበው? ?? ☞መቼ ነው ከራስ ወዳድነት የምላቀቀው ? ? ? ☞መቼ ነው ተመስገን አምላኬ የምለው? ? ? ☞ኦ አምላኬ አንተ እርዳኝ እኔስ ግራ ገባኝ ??? አምላኬ ሆይ ጥበብና ማስተዋሉን፤ ልብና ልቦናውን፤ ጥንካሬና ብርታቱን እምነትና የዋህነቱን፤ ትግስትና ፍቅሩን•••ለኛ ለባሮችህ ትሰጠን ዘንድ አማላጅ በምትሆን በቅድስተ ቅዱሳን በእመአምላክ በንፅህት ቅድስት ድንግል ማርያም፤ እንዲሁም አንተ ባከበርካቸው ቅዱሳን ፀሎትና ቃልኪዳን ማረን ይቅር በለን፡፡ አቤቱ ሆይ እኛ ሀጢያተኛ ባሮችህን ለንሰሀ ሞት አብቃን፡፡ •••✞ አሜን ✞ አሜን ✞ አሜን ✞•••

•✞✞✞ #እመቤቴ_ስልሽ ✞✞✞• እመቤቴ ስልሽ ነይልኝ ለልጅሽ፣ ቅረቢኝ በህይወቴ እናቴ ስጠራሽ፡፡/፪/ #አዝ••••••• ኑሮዬ ተዛብቶብኝ ደክሜኣለሁ እናቴ፣ እኔን ቅረቢኝና ልፅናና በህይወቴ፣ በደሳሳ ጎጆዬ በቤቴ ገብተሽልኝ፣ በኔ የነገሰውን ሀዘኔን ለውጪልኝ፡፡ #አዝ••••••• እሻለሁ ፍቅርሽን እናትነትሽን፣ ዘወትር ከጎንህ ነኝ ብለሽ አረጋጊኝ፣ ስምሽን ለዘላለም እጠራለሁኝ እኔ፣ ለመንገዴ መሪ ነሽ ለአይኔ ብርሃኔ፡፡ #አዝ••••••• በድቅድቁ ጨለማ እኔ እንዳልወድቅብሽ በቀኝ እና ከግራ ደግፊኝ እባክሽ፣ ኑሪ ከልጅሽ ጋራ እመአምላክ በዘመኔ፣ አደራ አትራቂኝ ጠበቃ ሁኝ ለኔ፡፡ #አዝ••••••• ከኔ ጋራ ስትሆኚ ድምፅሽም ያፅናናኛል፣ ከሀዘን ከትካዜ እናቴ ያስረሳኛል፣ በኖርሁበት ኑሪልኝ በምጓዝበት ሁሉ፣ የአንድዬ እናት ስጠራሽ ነይ ቤዛዊተ ኩሉ፡፡ #አዝ•••••••

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Ethio_Orthodox1 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Ethio_Orthodox1 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Ethio_Orthodox1 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

#ከትንሣኤ_እሁድ_በኋላ_ያሉ_ዕለታት_ስያሜ፦ ✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 ✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ ✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ ✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ ✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ ✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

#የልዳው_አንበሳ የቤሩቱ ኮከብ የልዳው አንበሳ ሦስት ጊዜ ሞቶ ጊዮርጊስ ተነሳ/2/ #አዝ........ በተጋድሎ ጸና........ቅዱስ ጊዮርጊስ በእውነት መሰከረ...ቅዱስ ጊዮርጊስ ኃያሉ ጊዮርጊስ......ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰይፍ ተመተረ.....ቅዱስ ጊዮርጊስ የልዳው አንበሳ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠላት አይገዛህ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰይጣንን ተዋጋው..ቅዱስ ጊዮርጊስ ጎልማሳው ሥጋህ...ቅዱስ ጊዮርጊስ #አዝ.......... ዲድያኖስ ተቆጣ....ቅዱስ ጊዮርጊስ ጽናትህን አይቶ.......ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀጣ ተነሳ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ በትዕቢት ተሞልቶ...ቅዱስ ጊዮርጊስ ባንተላይ ወገኑ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባ ነገሥታት........ቅዱስ ጊዮርጊስ ከምድረ ገፅ አንተን....ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍፁም ለማጥፋት.....ቅዱስ ጊዮርጊስ #አዝ......... በመበለቷ ቤት ..........ቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ተአምር ሰራ....ቅዱስ ጊዮርጊስ ምሶሶ አለምልሞ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ እውራን አበራ................ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባት አክሊላትን ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ተቀበለ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለ ጌታ ፍቅር ..............ቅዱስ ጊዮርጊስ ባደባባይ ዋለ................ቅዱስ ጊዮርጊስ #አዝ.......... ዝክርህን ዘክሮ......ቅዱስ ጊዮርጊስ ስምህን የጠራ......ቅዱስ ጊዮርጊስ በነፍስም በሥጋ....ቅዱስ ጊዮርጊስ የለበት መከራ.......ቅዱስ ጊዮርጊስ ደራጎንን አጥፋ.....ቅዱስ ጊዮርጊስ አርቅልን ከኛ........ቅዱስ ጊዮርጊስ በዝሙት በኃጢአት....ቅዱስ ጊዮርጊስ ደርሶብናልና..............ቅዱስ ጊዮርጊስ

የ_መዝሙር_ግጥሞች_ይህ_ነው_ጊዮርጊስ_24k.m4a2.63 KB

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏 - Статистика и аналитика Telegram-канала @eotc2921