ru
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Открыть в Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Больше
4 374
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
#እግዚኦ_መሐረነ_ክርስቶስ {ለምን እንላለን}? ✞✞✞ —“#ሚስጢሩ ”— በቤተክርስቲያናችን ስርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔር ከታሰራችሁበት ኃጥያት ማሰሪያ ይፍታቹ ሲሉ 12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና 12 ጊዜ ደግሞ በእንተ እግዝትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ያስብላሉ ። ካህናትና ምእመናን በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህኑን 12 ጊዜ እንላለን ። እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት አቤቱ ክርስቶስ ማረን ሲሆን በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ደግሞ ስለ እመቤታችን ማርያም ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን ማለት ነው ። አስራ ሁሉት ጊዜ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12 ሰዓት በእንተ እግዝእትነ ማርያም ደግሞ ለሊቱን 12 ሰዓት ሲሆን በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሰራነው ኃጥያት በሃያ አራቱ 24ቱ ሰዓት ምሕረት እናገኝ ዘንድ ነው። ሌላው አስራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት፦ #1ኛው በስመ ሥላሴ ነው በእያንዳንዱ ፊደል #አ_ብ_ወ_ል_ድ_መ_ን_ፈ_ስ_ቅ_ዱ_ስ ፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪ #2ኛው የድህነታችን ምክንያት በሆነች በእመቤታችን ስም ፊደል ነው ። #ቅ_ድ_ስ_ት_ድ_ን_ግ_ል_ማ_ር_ያ_ም ፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪ ———✞ “እግዚኦ” ✞——— አቆጣጠረም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራ ጣት እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ፣ ቀጥሎ በመሐል ጣት ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደ ታች ተደርጎ በማርያም ጣት /በትንሿ/ ጣት ወደ ላይ ነው ። ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ~ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር መመላለሱን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን ። መሐል ጣት ወደ ላይ ~ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን በቀለበት ጣት ወደ ታች ስንቆጥር ወደዚች አለም ለፍርድ መምጣቱን፤ በትንሿ ጣት ወደ ላይ ስንወጣ ደግሞ በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደ ሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው። ———✞ “ብእንተ” ✞——— በእንተ እግዝትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ ከትንሿ ጣት ወደ ታች ይጀመርና በጠቋሚ ጣት ወደ ላይ ይፈጸማል ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና ከፍ ማለቷን የሚያሳይ ምሥጢር ነው ። ብእንት ሲባል በትንሿ ጣት ወደ ታች የሚጀመር ራሷን ዝቅ አድርጋ የትህትናዋ ምሳሌ ስለሆነ ነው ከላይ ወደ ታች ሚጀመረው። “ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል” - የማቴ፡ 23፥12 ደግሞ የበእንት ፍጻሜ ወደላይ የሚያልቀ ሚስጢሩ እመቤታችን በመቃብር አልቆየችም ወደላይ አረገች ማለት ነው። “ አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት” መዝ፡ 132፥8 ስንዱዋ እመቤት ቅድስት ቤተክርስቲያን ማንኛውም ነገር ያለ ትርጉም አታደርግም።

#እግዚኦ_መሐረነ_ክርስቶስ {ለምን እንላለን}? ✞✞✞ —“#ሚስጢሩ ”— በቤተክርስቲያናችን ስርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔር ከታሰራችሁበት ኃጥያት ማሰሪያ ይፍታቹ ሲሉ 12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና 12 ጊዜ ደግሞ በእንተ እግዝትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ያስብላሉ ። ካህናትና ምእመናን በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህኑን 12 ጊዜ እንላለን ። እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት አቤቱ ክርስቶስ ማረን ሲሆን በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ደግሞ ስለ እመቤታችን ማርያም ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን ማለት ነው ። አስራ ሁሉት ጊዜ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12 ሰዓት በእንተ እግዝእትነ ማርያም ደግሞ ለሊቱን 12 ሰዓት ሲሆን በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሰራነው ኃጥያት በሃያ አራቱ 24ቱ ሰዓት ምሕረት እናገኝ ዘንድ ነው። ሌላው አስራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት፦ #1ኛው በስመ ሥላሴ ነው በእያንዳንዱ ፊደል #አ_ብ_ወ_ል_ድ_መ_ን_ፈ_ስ_ቅ_ዱ_ስ ፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪ #2ኛው የድህነታችን ምክንያት በሆነች በእመቤታችን ስም ፊደል ነው ። #ቅ_ድ_ስ_ት_ድ_ን_ግ_ል_ማ_ር_ያ_ም ፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪ ———✞ “እግዚኦ” ✞——— አቆጣጠረም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራ ጣት እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ፣ ቀጥሎ በመሐል ጣት ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደ ታች ተደርጎ በማርያም ጣት /በትንሿ/ ጣት ወደ ላይ ነው ። ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ~ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር መመላለሱን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን ። መሐል ጣት ወደ ላይ ~ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን በቀለበት ጣት ወደ ታች ስንቆጥር ወደዚች አለም ለፍርድ መምጣቱን፤ በትንሿ ጣት ወደ ላይ ስንወጣ ደግሞ በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደ ሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው። ———✞ “ብእንተ” ✞——— በእንተ እግዝትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ ከትንሿ ጣት ወደ ታች ይጀመርና በጠቋሚ ጣት ወደ ላይ ይፈጸማል ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና ከፍ ማለቷን የሚያሳይ ምሥጢር ነው ። ብእንት ሲባል በትንሿ ጣት ወደ ታች የሚጀመር ራሷን ዝቅ አድርጋ የትህትናዋ ምሳሌ ስለሆነ ነው ከላይ ወደ ታች ሚጀመረው። “ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል” - የማቴ፡ 23፥12 ደግሞ የበእንት ፍጻሜ ወደላይ የሚያልቀ ሚስጢሩ እመቤታችን በመቃብር አልቆየችም ወደላይ አረገች ማለት ነው። “ አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት” መዝ፡ 132፥8 ስንዱዋ እመቤት ቅድስት ቤተክርስቲያን ማንኛውም ነገር ያለ ትርጉም አታደርግም።

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን መጋቢት 3 እና 4 #አባ_ቆዝሞስ_ዕረፍታቸው + ከፍንዮስ አገር የተገኙት አባ በርፎንዮስ ዕፍታቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡ አባ ቆዝሞስ፡- እኚኽም ቅዱስ 58ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ሲሆኑ በጽድቅ ሥራቸው የቀና ሰይጣን በዘመናቸው አሳዛኝ ነገር አመጣባቸው፣ በኢትዮጵያ በተሾሙት አባ ጴጥሮስ ፈንታ ሰይጣን ሁለት የሶርያ መነኩሴዎችን አስነሥቶ እሳቸው እንደሾሙ አድርጎ የሐሰት ደብዳቤ አጽፎ ላካቸው፡፡ የንጉሡንም ወንድም አንተ መንገሥ ይገባሃል ብለው ወንድሙን ንጉሥ እንዲገድል አደርገው፡፡ አባ ጴጥሮስንም አሳስረው እነርሱ ተሾሙ፡፡ አባ ጴጥሮስም በታሰሩበት ዐረፉ፡፡ በዚህም ምክንያት ለ84 ዓመታት (ከ911-995 ዓ.ም ድረስ) ጳጳስ ሳይላክልን ቀረ፡፡ የአባ ቆዝሞስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን! + + + + + + + + + + + + + + + መጋቢት 4- #ከጵንፍልያ_አውራጃ_የተገኘው_መኮንኑ_ቅዱስ_ሐኑልዮስ_በሰማዕትነት_ዐረፈ፡፡ + በሥርዓታቸው ከአይሁድ ጋር ተሳታፊዎች ስለሆኑ ሰዎች በአሞር ደሴት የአንድነት ስብሰባ ሆነ፡፡ + የከበረች ቅድስት ሐይመተ ሥላሴ ዕረፍቷ ነው፡፡ ቅድስት ሐይመተ ሥላሴ፡- ቅድስት ሐይመተ ሥላሴ የትውልድ ሀገሯ ጎጃም ደብረ ጽላሎ ነው፡፡ ብዙ እናቶች በጣና ደሴት ውስጥ እየገቡ እንደጸለዩ ሁሉ እሷም ወደ ዝዋይ ሄዳ በዝዋይ ደብረ ጽዮን ሐይቅ ውስጥ ገብታ 5 ዓመት ከባሕሩ ላይ የጸለየች ቅድስት እናት ናት፡፡ በታዘዘ መልአክ መሪነት ከሐይቁ ውስጥ ከወጣች በኋላ በገዳሙ ውስጥ 19 ዓመት ቆማ ጸልያለች፡፡ በመልአኩ መሪነት ወደ ቡልጋ ሄዳ በዚያም 15 ዓመት በታላቅ ተጋድሎ ኖራለች፡፡ ሰውነቷም እጅግ ከስቶ ሥጋዋ አልቆ ይታይ ነበር፡፡ በመጨረሻም መልአኩ ተገልጦ ጊዜ ዕረፍቷን ከነገራት በኋላ ወዲያው መጋቢት 4 ቀን በሰላም ስታርፍ ሦስት አክሊላት ወርደውላታል፡፡ ቅድስት ሐይመተ ሥላሴን ስንክሳሩም ‹‹የጽድቅ ኮከብ›› እያለ ይጠቅሳታል፡፡ ቅዱስ ገድሏ በደብረ በግዕ ይገኛል፡፡ + + + በአሞር ደሴት የተደረገው የአንድነት ስብሰባ፡- በአሞር ደሴት የሚኖሩ ክርስቲያኖች በዓላቸውን ከማያምኑ ከአይሁድ ጋር ያከብሩ ነበር፡፡ የከበረውን የፋሲካን በዓል ዕረቡም ይሁን ዐርብ ከአይሁድ በዓል ጋር አብረው ያከብሩ ነበር፡፡ የደሴቷ ኤጲስቆጶስም ይህንን ተግባራቸውን እንዲተው ቢያወግዛቸውም እነርሱ ግን ማቆም አልቻሉም ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የደሴቷ ኤጲስቆጶስ ወደ ኢየሩሳሌም፣ አንጾኪያ፣ እስክንድርያና ወደ ሮሙ ኤጲስቆጶሳት መልእክትን በመላክ ነገራቸው፡፡ እነዚህም አራቱ ኤጲስቆጶሳት የትንሣኤን በዓል በእሑድ ቀን ብቻ እንዲያከብሩ አዘዙ፡፡ ከዚህም የወጣውን እንዲያወግዝ ለደሴቷ ኤጲስቆጶስ መልእክት ላኩለት፡፡ የደሴቷም ኤጲስቆጶስ ጉባኤ ሠራና 15 ኤጲስቆጶሳት ተሰበሰቡ፡፡ እነዚያንም ከአይሁድ ጋር በዓልን ያከብሩ የነበሩትን ሰብስቦ የአራቱን ሊቃውንት ኤጲስቆጶሳት መልእክት አነበበላቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ከክፋታቸው የተመለሱ አሉ፣ ደግሞም በአመጸኝነታቸው ጸንተው አልታዘዘ ያሉ ነበሩ፡፡ እነዚህንም ክፉዎች አልመለስ ብለው ስላመጹ 15ቱም ኤጲስቆጶሳት ረግመው ከምእመናን አንድነት ለዩአቸው፡፡ ሃይማኖትን አጽንተው የጠበቁ የቅዱሳን አባቶቻችን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸ ይማረን! + + + #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ሐኑልዮስ፡- ይኽም ቅዱስ ጌታችንን በማመን በሃይማኖቱ የጸና ነው፡፡ የከሃዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ መኮንን የሆነው ብርይንኮስ ተልኮ ወደ ጵንፍልያ አውራጃ በመጣ ጊዜ ቅዱስ ሐኑልዮስን አገኘው፡፡ ቅዱስ ሐኑልዮስም በመኮንኑ ፊት ቆሞ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መሰከረ፡፡ የረከሱ የንጉሡንም ጣዖታት ረገማቸው፡፡ መኮንኑም ጣዖታቱን ሲረግምበት በሰማ ጊዜ ቅዱስ ሐኑልዮስን ይዞ ማሠቃየት ጀመረ፡፡ ብዙ ካሠቃየውም በኋላ በመጨረሻ በዕንጨት መስቀል ላይ ሰቀለው፡፡ ቅዱስ ሐኑልዮስም ስለ ስሙ መስክሮ የእርሱን ሞት በሚመስል ሞት እንዲሞት ስለፈቀደለትና ለሰማዕትነት ክብር ስላበቃው ጌታችንን አመሰገነው፡፡ ከዚህም በኋላ በዚያው በዕንጨት መስቀል ላይ እንደተሰቀለ ነፍሱን ለጌታችን አደራ ሰጥቶ ሰማዕትነቱን በክብር ፈጸመ፡፡ የክብርንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ 🙏በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!🙏

☞✞ ✝ማቴ፡6፥16✝ ስትጦሙም፥እንደ፡ግብዞች፡አትጠውልጉ፤ለሰዎች፡እንደ፡ጦመኛ፡ሊታዩ፡ፊታቸውን፡ያጠፋሉና፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ዋጋቸውን፡ተቀብለዋል። አንተ፡ግን፡ስትጦም፥በስውር፡ላለው፡አባትኽ፡እንጂ፡እንደ፡ጦመኛ፡ለሰዎች፡እንዳትታይ፡ራስኽን፡ተቀባ፡ፊትኽንም፡ታጠብ፤በስውር፡የሚያይ፡አባትኽም፡በግልጥ፡ይከፍልኻል። #ራስኽን_ተቀባ፦ የተባለውም ፍቅርን፣ ትህትናን፣ ሰላምን፣ ጥሩ ምግባርን ተላበሱ ማለት ነው፡፡ #ፊትህንም_ታጠብ፦ ማለት ራስኽን ከሀሜት፣ ከክፋት፣ ከዝሙት፣ በአጠቃላይ ከመጥፎ ስራዎች ሁሉ ንፃ/አፅዳ ማለት ነው፡፡ ---✞መልካም ዕለተ ቅድስት ሰንበት✞---

#ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ለምን_በመስቀል_ላይ_ተሰቀለ? ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ቅዱስ ሥጋውን ቆርሶልናል፥ ክቡር ደሙን አፍስሶልናል፥ ክብርት ነፍሱንም በፈቃዱ አሳልፎ ሰጥቶልናል። ይህንንም ያደረገው በቤዛነቱ እኛን ከእርግማን ሊዋጀን ነው። ምክንያቱም የሰው ልጆች በጠቅላላ በመርገመ ሥጋ በመርገመ ነፍስ ተይዘን ነበርና። በመሆኑም በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም፥ በሞተ ሥጋ ላይም ሞተ ነፍስ ተፈርዶብን ከእርግማን በታች ወድቀን ነበር። ይሁን እንጂ ፈጣሪያችን “እንደ ወጡ ሳይመለሱ፥ እንደወደቁ ሳይነሱ ይቅሩ፤” ሳይል እኛን ለመፈለግ ከሰማየ ሰማያት ወረደ። /ማቴ. 18፥12-14/። በመንፈስ ቅዱስ ግብር በማኅፀነ ድንግል ማርያም ተፀነሰ። /ሉቃ. 1፥35/። ✞ ከእመቤታችንም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ በቤተልሔም በከብቶች በረት ተወለደ። /ሉቃ. 2፥7/። በተዋሕዶ ሰው አምላክ፥ አምላክ ሰው ሆነ። /ማቴ. 16፥13፣ 1ኛ ዮሐ. 1፥1-2፪፤ 5፥20/። ቀስ በቀስም አደገ። /ሉቃ. 2፥40/። ሠላሳ ዓመት በሞላውም ጊዜ በፈለገ ዮርዳኖስ በዕደ ዮሐንስ ከተጠመቀ በኋላ ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ሄዶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ጾመ። /ማቴ. 3፥13-17፣ ሉቃ. 3፥21-23፣ ማቴ. 4፥2/። ከዚያም አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ሰባ ሁለቱን አርድዕትና ሠላሳ ስድስቱን ቅዱሳት አንስት መረጠ። / ሉቃ. 10፥1፣ የሐዋ. 1፥15/። ✞ አዲስ ሕግ ወንጌልንም ሦስት ዓመት ከሦስት ወር አስተማረ። በመጨረሻም ሰለእኛ እርግማን /ኃጢአት/ ተላልፎ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞተ። /ማር. 15፥23-37/። የሞተውም በፈቃዱ ነው። /ዮሐ. 10፥11፤ 15፥13/። በዚህም የዕለት ፅንስ ሆኖ በእመቤታችን ማኅፀን ጀምሮት የነበረውን የማዳን ሥራ በመስቀል ላይ ፈጸመው። /ዮሐ. 19፥30/። ----✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞----

ፍስሶ፤ ጠላት ዲያብሎስን ሰራዊቱ አጋንንትን ድል ነሥቶ ምእመናን በኀጢአታቸው ከመጣባቸው ፍዳ አድኖ ነውና የስሙን ነገር ካነሣ ብሎ ለማነጻጸር ያመጣዋል፡፡ ❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም የኢያሱን ለኢየሱስ ምሳሌነት እንዲኽ አመሰጥሮታል፡- “በከመ ኢያሱ ዜናዌ ተሰምየ ኢየሱስሀ እምቅድመ ኢየሱስ ናዝራዊ ኢየሱስ ብሂል መድኅን ብሂል …” (የነዌ ልጅ ኢያሱ ከናዝሬቱ ኢየሱስ በፊት መድኅን እንደተባለ፤ ኢየሱስ ማለት መድኀኒት ነውና፤ ኢያሱ ወገኖቹን ከጠላት ጦር እንዳዳናቸው ጌታ ኢየሱስም ወገኖችን ከኀጢአታቸው አዳናቸው (ዘዳ ፴፬፥፱)፤ ኢያሱ ከሙሴ በረከትን እንደተቀበለ ጌታ ኢየሱስም ከአባቱ ዘንድ ክብሩ ተገለጠ (ማቴ ፫፥፲፯)፤ ኢያሱ ከወገኖቹ ጋር የብስ የኾነ የዮርዳኖስን ወንዝ እንደተሻገረ (ኢያ ፫፥፲፯) ጌታ ኢየሱስም የዮርዳኖስን ውሃ በጥምቀቱ ቀደሳት (ማር ፩፥፱-፲፩)፤ ኢያሱ የእስራኤልን የሰውነታቸውን ሸለፈት በስለታም ምላጭ እንደገዘረ (ኢያ ፭፥፯) ጌታ ኢየሱስም በወንጌል ምላጭ የአሕዛብን የበደላቸውን ሸለፈት ገዘረ፤ ኢያሱ በገባዖን ፀሓይን እንዳቆመ ኹለተኛውንም ቀን አንድ ቀን እንዳደረገ (ኢያ ፲፥፲፪-፲፫) ጌታ ኢየሱስም ፀሓይን በቀራንዮ አጨለመ አንዲቱንም ቀን ኹለት ዕለት አደረጋት (ማቴ ፳፯፥፵፭)፤ ኢያሱ ምድረ ርስትን ለወገኖቹ በየነገዳቸው እንዳደላቸው ጌታ ኢየሱስም የገነትን ምድር ለነቢያቱ በየወገናቸው አደላቸው (ኢያ ፲፩፥፳፫፤ ኤፌ ፩፥፲፩)) እንዲል፡፡ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (መልክአ ኢየሱስ ንባቡና ትርጓሜው የተወሰደ)

✞✞✞ #የመልክአ_ኢየሱስ_ለዝክረ_ስምከ_ለጌታ_ስም_የቀረበ_ትርጓሜ ✞✞✞ ☞✞“ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሐላ ዘኢይሔሱ ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሡ አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቄጸል በርእሱ አህጉረ ጸር ወረሰ ኢያሱ” (የማይከዳ የቃል ኪዳን ስም ለኾነ የስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል፤ እግዚአብሔር አስቀድሞ በዙፋኑ ያስቀመጠኽ የዳዊት የኾዱ ባሕርይ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ኢያሱ መድኀኒትነት ያለው የስምኽን አክሊል ተቀዳጅቶ የጠላቶችን ሀገሮች ወረሰ (ገንዘብ አደረገ)) ❖ (ትርጓሜ)፡- ሊቁ በዚኽ የመልክአ ኢየሱስ ድንቅ ድርሰቱ ላይ “ነገርን ከሥሩ ውሃን ከጥሩ” እንዲሉ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ከሚለው ከስም አጠራሩ በመነሣት ምስጋናውን ይዠምራል፤ “የማይከዳ የቃል ኪዳን ስም” ስለምን አለው? ቢሉ አዳምና ሔዋን ከገነት ከተባረሩ በኋላ እንኳ አዳም የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም፤ ቤተ ፈት በዚኽ ጊዜ እበላ እጠጣ፤ በዚኽ ጊዜ ተድላ ደስታ አድርግ ነበር ብሎ ያዝናል፤ አዳም ግን ፈጣሪዬ አትብላ ያለኝን ዕፀ በለስን በልቼ በደልኍ ብሎ በኀጢአቱ ፲፬ ሱባዔ ፺፰ ዓመት መሪር ልቅሶን አለቀሰ፡- “ወአልቦቱ ካልዕ ኅሊና ላዕለ ኀጢአቱ ዘእንበለ ብካይ ወላህ” (ኀጢአቱን እያሰበ ከማልቀስ ውጪ ሌላ ዐሳብ አልነበረውም) እንዳሉ አሞንዮስና አውሳብዮስ በመቅድመ ወንጌል ❖ ያን ጊዜ የምሕረት ባለቤት አዳምንና ሔዋንን እንደሚቤዣቸው እንደሚያድናቸው የማይታበል ጽኑ ቃል ኪዳንን ገብቶላቸዋል፡- ☞ “ወእምድኅረ ኀሙስ መዋዕል ወመንፈቀ መዓልት እምሕረከ ወእሣሃለከ በብዝኀ ሣህልየ ወምሕረትየ፤ ወእወርድ ውስተ ቤትከ ወአኀድር ውስተ ከርሥከ ወበእንቲኣከ ኦ አዳም እትወለድ ከመ ሕፃን ወበአንቲኣከ ኦ አዳም አሐውር ውስተ ምሥያጥ፤ ወበእንቲኣከ እጸውም ፵ መዓልተ ወ፵ ሌሊተ፤ ወበእንቲኣከ እትዌከፍ ወእትዔገሥ ሕማማተ ወበእንቲኣከ እሰቀል ዲበ ዕፀ መስቀል” (በፍጹም ይቅርታዬ ከዐምስት ቀን ተኩል በኋላ በፍጹም ምሕረቴ ይቅር እልኻለኍ፤ ወደ ቤትኽም ወርጄ በባሕርይኽ ዐድራለኍ፤ አዳም ሆይ ስለ አንተ እንደ ሕፃን እወለዳለኍ፤ ስለ አንተ ወደ ገበያ እኼዳለኍ፤ ስለ አንተም አርባ ቀን አርባ ሌሊት እጾማለኍ፤ ስለ አንተ መከራ መስቀልን በትዕግሥት አቀበላለኍ፤ ስለ አንተም በዕንጨት መስቀል ላይ እሰቀላለኍ) እንዲል (መጽሐፈ ቀሌምንጦስ፣ ፫ኛ መቃ ፬፥፳፫-፳፬፤ ዕዝ ሱቱ ፬፥፩፤ ሲራ ፳፬፥፮፤ ገላ ፬፥፬)፡፡ ❖ በመኾኑም “እትቤዘወከ” ብሎ እንደሚቤዠው እንደሚያድነው ለአዳም የነገረው ሊደርስ ሊፈጸም ዘመኑ ሲፈጸም ቅዱስ ገብርኤል ወደ እመቤታችን ተልኮ “ወናሁ ትፀንሲ ወትወልዲ ወልደ ወትሰምዪዮ ስሞ ኢየሱስ” (እነሆም ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ) በማለት የስሙን መድኀኒትነት ነግሯታልና ደራሲው “የማይከዳ የቃል ኪዳን ስም ለኾነ የስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል” ይለዋል (ሉቃ ፩፥፴፩)፡፡ ❖ መጋቤ ሐዲስ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊዉ ለዮሴፍም ኢየሱስ የሚለውን ንባቡንም ትርጓሜውን ሲገልጽለት፡- “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ ከርሷ የተፀነሰው በግብረ መንፈስ ቅዱስ ነውና ዕጮኛኽን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ ልጅም ትወልዳለች፤ ርሱ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለኽ” በማለት ወገኖቹን በኀጢአታቸው ከመጣባቸው ፍዳ የሚያድናቸውን መድኅነ ዓለም ኢየሱስን ቅድስት ድንግል ማርያም በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደፀነሰችው ነግሮታልና (ማቴ ፩፥፲፰-፳፫)፡፡ ❖ ከሊቃውንት አንዱ ሶርያዊዉ ቅዱስ ኤፍሬምም ስለዚኽ ነገር በጥልቀት በትርጓሜ ወንጌሉ ላይ ሲገልጸው፡- “The words in the ‘sixth month’ are reckoned in Elizabeth’s pregnancy…” (መልአኩ “በስድስተኛው ወር” የሚለው ኤልሳቤጥ ከፀነሰችበት ወራት ዠምሮ በመቊጠር ነው፤ መልአኩ ወደ አንዲት ድንግል ተላከ ወደ ርሷ ገብቶም “እነሆ ድንግልናሽ ሳይነዋወጥ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” አላት፤ ይኸውም በሥጋ ተገልጦ ሊመጣ ስላለው ስለ አካላዊ ቃል ሲናገር ነው፤ ሲነግራትም “ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” አላት እንጂ “ኢየሱስ የተባለው” አላላትም፤ ይኸውም ወልደ እግዚአብሔር በተዋሐደው ሥጋ የሰው ልጆች የሚድኑበት ስም መኾኑን የሚያመለክት ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ማለት በዕብራይስጥ “መድኅን” ማለት ነውና፤ መልአኩ “ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” ሲላት መድኅን ትዪዋለሽ ማለቱ ነው፤ ለምን? ቢሉ ሕዝቡን ኹሉ ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና) በማለት ተርጒሞታል፡፡ ❖ ክርስቶስ “Χριστός” የጽርዕ ቃል ነው፤ በዕብራይስጥ “መሲሕ” ሲባል፤ በግእዝ ቋንቋ “ቅቡዕ” ማለት ነው፤ ይኸውም ብቻ የትስብእት፤ ብቻ የመለኮት ስም አይደለም፤ ከኹለት አካል አንድ አካል፤ ከኹለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ቢኾን የወጣለት የተዋሕዶ ስም ነው፤ “ቅቡዕ” መባሉም ሥጋ ከአካላዊ ቃል ጋር ቢዋሐድ የባሕርይ አምላክ መኾኑን ያመለክታል፤ ይኸውም የአካል የባሕርይ ተዋሕዶ ነውና ትስብእት ከባሕርይ ልጅ ከባሕርይ አምላክ የባሕርይ ተዋሕዶ ቢዋሐድ ሥጋ የባሕርይ አምላክነትን የባሕርይ ልጅነትን አገኘ፤ በባሕርይ አምላክነት፣ በባሕርይ ልጅነት ከበረ፤ ውሱን ሲኾን ምሉዕ፤ ግዙፍ ሲኾን ረቂቅ፤ መዋቲ ሲኾን ሕያው ኾነ፤ ኀየሰ፣ ወረሰ፣ ነግሠ፣ ዐብየ፣ ከብረ፣ ተለዐለ ተባለ፡፡ ኹሉ የሚቻለው ከሌላ አካል ክብር ከማይሻ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ዕሩይ ከሚኾን ከቃል ጋራ የባሕርይ ተዋሕዶን ቢዋሐድ ሥጋ በተዋሕዶተ ቃል ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ የባሕርይ አምላክ ኾኗልና፡፡ ❖ አንድም “ስመ መሐላ” ብሎ የያዘውስ ለዳዊት የገባለትን ቃል ኪዳን ነው ብሎ፤ ለዳዊት አስቀድሞ ከባሕርዩ የተከፈለ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን በዙፋኑ እንደሚያስቀምጥለት፡- “መሐለ እግዚአብሔር ለዳዊት በጽድቅ ወኢይኔስሕ እስመ እምፍሬ ከርሥከ አነብር ዲበ መንበርከ” (እግዚአብሔር ለዳዊት እንዲኽ ሲል በእውነት ማለ አይጸጸትምም፤ ከኾድኽ ፍሬ በዙፋንኽ ላይ አስቀምጣለኹና) ብሎታልና፤ ደራሲውም ከዚኽ አያይዞ “እግዚአብሔር አስቀድሞ በዙፋኑ ያስቀመጠኽ የዳዊት የኾዱ ባሕርይ ኢየሱስ ክርስቶስ” በማለት ተናገረ (መዝ ፻፴፩፥፲፩)፡፡ ❖ ይኽማ የተነገረው ለሰሎሞን አይደለም ቢሉ? ለጊዜው ለሰሎሞን ቢኾን ፍጻሜው ለጌታ ነውና፤ ለጊዜው ለሰሎሞን ፍጻሜው ለጌታ መኾኑ እንደምን ነው? ቢሉ ሰሎሞን በጸጋ የገዛቸውን ኹሉ ጌታ በባሕርይ ገዝቷቸዋልና፡፡ አንድም ሰሎሞን በሥጋ የገዛቸውን ኹሉ ጌታ በነፍስ ገዝቷዋልና፡፡ አንድም ሰሎሞን በግድ የገዛቸውን ጌታ በፈቃድ ገዝቷቸዋልና፡፡ አንድም የጌታ መንግሥት መታወቁ ነቢዩ “መንበርከ እግዚኦ ለዓለመ ዓለም” ብሎ በተናገረለት ነውና (መዝ ፵፬፥፮)፡፡ አንድም “ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምኢ እዝነኪ” ብሎ የትንቢት ዙፋን አድርጎ በተናገረላት በምእመን ላይ ነውና (መዝ ፵፬፥፲)፡፡ አንድም “ዲበ መንበረ ዳዊት ትጸንዕ መንግሥቱ ለክርስቶስ” እንዲል ከዳዊት የነሣው ሥጋ እንደ አብ እንደ መንፈስ ቅዱስ የሚያድን የሚገድል ኾኗልና ፡፡ ❖ ደራሲው በመጨረሻ፡- “ኢያሱ መድኀኒትነት ያለው የስምኽን አክሊል ተቀዳጅቶ የጠላቶችን ሀገሮች ወረሰ (ገንዘብ አደረገ)” በማለት ኢያሱን አነሣ ስለምን ቢሉ? ኢያሱ ማለት የስሙ ፍቺ መድኀኒት ማለት ነውና ይኸውም ኢያሱ መድኀኒት መባሉ በዐጭር ቃጥቆ ዘገር ነጥቆ ጦር ነቅንቆ አማሌቃውያንን አጥፍቶ እስራኤልን ከሥጋዊ ጠላት አድኖ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን መድኀኒት መባሉ ሥጋውን ቈርሶ ደሙን አ

#ሀዲስ_ሀዋርያ_አቡነ_ተክለ_ሀይማኖት #የካቲት_24 ☞✞ጸሎታቸው በረከታቸው ቃልኪዳናቸው በእኛ በተዋሕዶ ልጆች ሁሉ ላይ አድሮብን ይኑርና የኢትዮጵያ ብርሃኗ ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡- ‹‹ጸሎታቸው›› ያልነው ‹‹የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለችና›› (ያዕ 5፡16) ቅድመ እግዚአብሔርን ትደርሳለችና ነው፡፡ መዝ 33፡15፡፡ ‹‹በረከታቸውም›› ያልነው የጻድቅ መታሰቢያ ለኃጥአን ሥርየትን ያሰጣል የነፍስ ይሆናልና ነው፡፡ (ምሳ 10፡7፣ ማቴ 10፡ 40-42፡፡) ☞✞‹‹ቃልኪዳናቸውም በእኛ ላይ ይደር›› ማለታችን እግዚአብሔር ለሙሴ ሕጉን ሲሰጠው እንዲህ ብሎ ነግሮት ነበርና ‹‹ትእዛዜን ለሚጠብቁ እስከሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝ›› ብሏልና (ዘጸ 20፡26) ስለዚህም በሃይማኖት ትውልድ ለሆኑ በቃልኪዳን ምሕረት እንደሚገኝ አምላካችን ተስፋ ስለሰጠን እንዲህ አልን፡፡ ☞✞‹‹ያደረጉት ተአምር›› ማለታችንም ጌታችን በአምላካዊ ቃሉ በቅዱስ ወንጌሉ ‹‹በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ተአምር ያደርጋል፤ ከእኔም የበለጠ ያደርጋል›› (ዮሐ 14፡12) እንዳለ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡- ወረብ በሚባል አገር የአባችንን የተክለ ሃይማኖትን መታሰቢያ በዓል የሚያደርግ አንድ ባለጸጋ ሰው ነበር፡፡ ቁጥራቸውም ብዙ የሆኑ ከብቶች አሉት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለአቡ ተክለ ሃይማኖት በዓል ለድኆች አርዶ ለማብላት 'ለዝክር የሚሆኑ ናቸው' ብሎ ለይቶ የሚጠብቋቸውን እረኞች አዘጋጀ፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓል በሆነ ጊዜ ከምእመናን ጋራ በቤተክርስቲያን ተገኝቶ የአባታችንን ገድል እየሰማ ሳለ ሰዎች ከመንደር መጥተው "አሽከሮችህ በቤት ውስጥ ያለህን ንብረት ከብቶችህንና የባለቤትህንም መቀነት ሳይቀር ወስደው ኮብልለዋል" ብለው ነገሩት፡፡ በዚህም ጊዜ ያ አማኝ ባለጸጋ "እኔ ምን ቸገረኝ! የምሰማው የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ገድል ነው፡፡ እርሳቸው ደግሞ ብዙ ተአምራትን እንደሚያደርጉ ይኸው በገድላቸው እረዳለሁ፡፡ ከብቶቹንስ ይጠብቁ የነበሩት የእርሳቸው አገልጋዮች አይደሉምን? ስለዚህ አባቴ ተክለ ሃይማኖት የተዘረፈውን ንብረት ባለበት ቦታ ተረከቡኝ" በማለት በእምነት አስረክቦ በረከት የሚገኝበትን ዝክራቸውን አዘክሮ መታሰቢያቸውን አድርጎ ወደቤቱ ገባ፡፡ ይኽም ባለጸጋ ወደመኝታው ሲሄድ "በአገልጋዮቼ አማካኝነት በጠፉት ንብረቶች ላይ እርስዎ የፈቀዱትን ያድርጉ፡፡ ድንቅ ተአምራትን ሁልጊዜ የሚሠሩ አባቴ እኔ ለዕረፍትዎ ቀን መታሰቢያ የሚሆነውን ዝክር የማዘክርበት ነገር እንደሌለኝ እርስዎ ያውቃሉ፡፡ አሁንም የወደዱትን ያድርጉ" ብሎ ደጋግሞ አመለከተ፡፡ ወዲያውም ይህን እንዳመለከተ አንቀላፋ፡፡ በዚያው ሌሊት አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሕልም ተገለጡለት፡፡ ይኸውም በአካለ ነፍስ ነው፡፡ ☞✞የክብር ባለቤት ጌታችን ሲያስተምር "እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሃቅ አምላክ የያዕቆብ አምላክ ነኝ፣ የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አምላክ አይደለሁም" (ማቴ 22:31) እንዳለ ጻድቃን በነፍስ ሕያዋን ናቸውና አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተገልጠውለት እንዲህ አሉት፡- "አንተ ሰው በማለዳ ፈጥነህ ተነሥ እነዚህ አገልጋዮችህን እንዲህ ካለች ዛፍ ሥር ተሰውረዋልና ከዚያ ታገኛቸዋለህ" ብለው ነገሩት፡፡ ሰውየውም በማለዳ በቅሎውን ጭኖ አባታችን ወዳመለከቱት ቦታ ሄደ፡፡ በዚያም አባታችን እንደነገሩት አገልጋዮቹን በዛፉ ሥር አገኛቸው፡፡ እነርሱም ንብረቱን እንዳያንቀሳቅሱ ምድር ጭልሞባቸው መሬት ለመሬት ወዲያና ወዲህ እየተመላለሱ ግራ ገብቷቸው ሲደነባበሩ ነበር፡፡ ሰውየውም ይዟቸው እየመራ ወደቤቱ ወሰዳቸው፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ የሶርያ ጮፍሮችን ዐይኖቻቸውን በተአምራት አሳውሮ ወደ ከተማ እንዳስገባቸው አባታችን ተክለ ሃይማኖትም በተሰጣቸው ታላቅ ጸጋ ይህንን አደረጉ፡፡ 2ኘ ነገ 6፡18፡፡ ከዚህም በመቀጠል ሰውየው አገልጋዮቹን ቆጠራቸው፡፡ ☞✞ከመካከላቸውም አንዱ የለም ነበር፡፡ አገልጋዮቹንም የት እንደሄደ ሲጠይቃቸው እነርሱም "እርሱማ የባለቤትህን መቀነት ሸጦ ጠላ ገዝቶልን ሊያመጣ ሄዷል፡፡ እርሱም 'ገዝቼ እስክመጣ ድረስ በዚህች ዛፍ ሥር አረፍ ብላችሁ ጠብቁኝ' ብሎን ነበር፡፡ ከሄደም በኃላ ዐይኖቻችን ድንገት ጠፉ" አሉት፡፡ እርሱም ሁሉንም ወደቤት አስገባቸው፡፡ ያጠፋ የተባለው አገልጋይም ደጅ ቆሞ "ቤቶች ጠላ ካላችሁ አንዲት መቀነት ልስጣችሁና ግዙኝ" እያለ ሲጮህ ሰሙት፡፡ ወጥተውም ያዙትና ጌታው ካለበት ቦታ አደረሱት፡፡ ከጌታውም ፊት በቆመ ጊዜ እጅግ ደነገጠ፡፡ ፊቱም ጠቆረ፡፡ ጉልበቱም እየተብረከረከ "እኔ ይህንን መቀነት ሌላ አገር የምሸጠው ነበር የመሰለኝ፡፡ ወደቤታችን እንደተመለስኩ ፈጽሞ አላወቅሁም" ብሎ ፈጽሞ አደነቀ፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር ያዩ ሰዎች ምስጋና የሚገባውን አምላክ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት "ለቅኖች ምስጋና ይገባል" (መዝ 32፡2) እንዳለ እነዚያ ሰዎች ድንቅ ተአምር ያደረጉትን አባታችን ተክለ ሃይማኖትን 'ዕፁብ ዕፁብ' ብለው አመሰገኑ፡፡ 🙏የቅዱስ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሎታቸው በረከታቸው የተዋሕዶ ልጆች በሆንን በሁላችን ላይ አድሮብን ይኑር፡፡🙏

#እንኳን_ለታላቁ__ዓብይ_ፆም__በሰላም_በፍቅርና_በጤና_አደረሰን_አደረሳችሁ!!! የዘንድሮው ዘመነ ሉቃስ ዓብይ ጾም በየካቲት 25 ማለትም ሰኞ ይገባል። ☞✞ በዓለ ደብረ ዘይት፦ በመጋቢት 22 በዕለተ እሁድ ይውላል። ☞✞ በዓለ ሆሣዕና፦ ሚያዝያ 13 በዕለተ እሁድ ይውላል። ☞✞ በዓለ ስቅለት፦ ሚያዝያ 18 በዕለተ ዓርብ ይውላል፡፡ ☞✞ በዓለ ትንሣኤ፦ ሚያዝያ 20 በዕለተ እሁድ ይውላል። ☞✞ @EOTC2921 ✞☜ ☞✞ @Ethio_Orthodox1 ✞☜ የኹላችንም ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ፥ ልክ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ዛሬም ባለፉት ወራት ለሠራነው ኃጢአት ሥርየት እናገኝበት ዘንድ ሽቶ መድኃኒት የሚኾን ቅዱስ ጾምን አዘጋጅቶልናል፡፡ ስለዚህ የነፍሳችን ጠባቂ እግዚአብሔር የሕመማችንን ፈውስ የምናገኝበትን መድኃኒት ስላዘጋጀልን እያመሰገን ወርሐ ጾሙን ደስ ብሎን ተቀብለን ደስ ብሎን እንድንጨርሰው የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡፡ አርምሞንና ጸጥታን፣ ፍቅርንና ደስታን፣ ሰላምንና ራስን መግዛትን፣ እንዲሁም ሌሎች እዚህ መዘርዘር የማንችላቸው ብዙ ምግባር ትሩፋቶችን ገንዘብ የምናደርግበት ፆም ይሁንልን። 🙏ፆሙን የሰላም የፍቅርና የበረከት ያድርግልን አሜን፫🙏 ላልሰሙ እናሰማ !?! ☞✞ @EOTC2921 ✞☜ ☞✞ @Ethio_Orthodox1 ✞☜

✞ #_ቅዱስ_ኡራኤል_መልአክ_ብርሃን✞ ☞✞ኡራኤል የሚለው ስም 'ዑር' እና 'ኤል' ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሰረተ ስም ነው ። ☞✞ኡራኤል ማለት ትርጉሙ "የብርሃን ጌታ" የአምላክ ብርሃን" ማለት ነው ። ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ አለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልዓክ ነው ። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። መፅ ሄኖክ {6፤2} ☞✞ሚስጢር ሰማይና እዉቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለፀለት የፀሀይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል ። መፅ ሄኖክ {28 ፤13} ☞✞ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብፅ ስትሰደድ መንገድ የመራ ፤ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ፅዋ ተቀብሎ ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ ፤ እዉቀት ለተሰወረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ፅዋ ጥበብን ያጠጣ መለአክ ነው ። 🙏በረከቱ በሁላችንም ላይ ባለንበት ቦታ ይደርብን፡፡🙏

#የአዳም_ኅቱም_የታተመ_ጐኑ_የአምላክ_እናት ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን ክፍል አንድ መጽሐፌ በጥቂት የተወሰደ) ❖ ልዑል እግዚአብሔር ስሙን እንዲቀድሰው ክብሩን እንዲወርሰው በአርአያውና በአምሳሉ ለፈጠረው ለአዳም አባታችን ረዳት እንድትኾነው፤ እናታችን ሔዋንን ከመኻል ጐኑ አንድ ዐጥንት በመንሣት፤ በእንቅልፍ ላይ ሕመም ሳይሰማው አካል ሳይጐድለው ድንቅ በኾነ አምላካዊ ሥራ ሔዋንን ፈጥሮለታል፤ ዐጥንት በወጣበት በአዳም ጐድንም ሥጋ መልቶበታል “ወነሥአ እግዚአብሔር አሐደ እምዐፅመ ገቦሁ ወመልአ ሥጋ መካና” (እግዚአብሔርም ከጐኑ ዐጥንት አንድ ዐጥንትን ነሣ ቦታውንም ሥጋ መላ) እንዳለ (ዘፍ ፩፥፳፩፤ ኩፋ ፬፥፭)፡፡ ❖ አዳምም ከተኛበት ቢነቃ ረዳት ልትኾነው እግዚአብሔር ከአካሉ ያስገኛትን ሔዋንን እርሱን መስላና አኽላ ከአጠገቡ ቢያገኛት፤ “ይኽቺ ዐጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት ርሷ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል…” (ዘፍ ፪፥፳፫)፤ በማለት ከአካሉ የተገኘች እንጂ ባዕድ አለመኾኗን መስክሯል፡፡ ❖ ይኽነን የሔዋን ከኅቱም የአዳም ጐን ያለ ዘር ያለ ሩካቤ መገኘትንና፤ ከአካሉ ዐጥንት ቢነሣለት እንኳ አካሉ ያለመጉደሉን፤ በተጨማሪም ምንም ሕመም ሳይሰማው ሔዋን ከሱ የመገኘቷን ድንቅ ምስጢር ከነገረ ሥጋዌ ልዩ ምስጢር ጋር በርካቶች የነገረ መለኮት ምሑራን በማነጻጸር ብዙ መጻሕፍትን ጽፈዋል፤ ከነዚኽም ሊቃውንት መኻከል ቅዱስ ቄርሎስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ይገኙበታል። ❖ ይኸውም አዳም በዕለተ አርብ በካልዕ ሱባዔ ማእከለ ነቂህ ወነዊም ኹኖ ሔዋንን ከጐኑ እንዳስገኘ፤ ከድንግል ማርያምም በዕለተ ዐርብ ምውት በሥጋ ሕያው በመለኮት ኾኖ፤ ከጐኑ ዳግሚት ሔዋን ጥምቀትን ያስገኘ ኢየሱስ ክርስቶስ ተገኝቷል (ዮሐ ፲፱፥፴፭)፡፡ ❖ ዳግመኛም ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ አዳም ከጐኑ አንድ ዐጥንት ስለተነሣ አካሉ ጒድለት እንዳላገኘው ኹሉ፤ ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን በሥጋ በወለደችው ጊዜ ማኅተመ ድንግልናዋ ያለመለወጡን ነገር በቅዳሴው በቊ ፺፮‐ ፺፯ ላይ “ወበከመ ኢሐጾ ለአዳም እምሕንፃ ሥጋሁ ዘቀዲሙ በእንተ ዘተነቅለ ዐፅመ ገቦሁ ከማሁ ኢሐጸ ማኅተመ ድንግልናሃ ለማርያም አመ ወለደቶ ለአበ አዳም በሥጋዌሁ” (አዳምም የጐኑ ዐጥንት ስለተነቀለ ከቀደመው የሥጋው ፍጥረት እንዳልጐደለበት፤ እንደዚኹ የአዳምን አባት በሥጋ በወለደችው ጊዜ የማርያም ማኅተመ ድንግልናዋ አልጐደለም) በማለት ቅድመ ፀኒስ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ፀኒስ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ፀኒስ ድኅረ ወሊድ ማኅተመ ድንግልናዋ ያልተለወጠ ዘላለማዊት ድንግል መኾኗን ከአዳም ጐን ምሳሌ ይዞ አስተምሯል፡፡ ❖ ይኸው ሊቅ በተጨማሪም አዳም ሔዋን ከኅቱም ጐኑ ስትገኝ ምንም ሕመም እንዳልተሰማው ኹሉ፤ ቅድስት ድንግል ማርያምም ጌታን በኅቱም ድንግልና ስትወልደው ምንም ዐይነት ሕማመ ወሊድ ያልተሰማት መኾኑን “ወበከመ ኢያሕመሞ ለአዳም ሶበ ተነቅለ ዐፅመ ገቦሁ ከማሁ ኢረከባ ሕማመ ወሊድ ለእመ አምላክ ገሊላዊት” (አዳምን የጐኑ ዐጥንት በተነቀለ ጊዜ እንዳላሳመመው፤ እንደዚኹ የገሊላ ወገን የምትኾን የአምላክን እናት ሕማመ ወሊድ አላገኛትም) ሲል አመስጥሮታል፡፡ ❖ የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም በተመሳሳይ መልኩ የአዳምን ጐንና የቅድስት ድንግል ማርያምን ማኅተመ ድንግልና እያነጻጸረ ሲያስተምር “ወበከመ አውፅአ አፅመ ገቦ እምገቦሁ ለአዳም ወኢሐጾ ለአዳም ከማሁ ዓዲ ነሥአ እምድንግል ሥጋ ዘቦቱ ነፍስ ነባቢት ወለባዊት ወኢተወለጠ ድንግልናሃ ኮነ አዳም ፍጹመ እምድኅረ ፀአተ ዐፅመ ገቦ እምኔሁ፤ ወድንግልሂ ዓዲ ነበረት እንበለ ሙስና እምድኅረ ፀአተ ሕፃን እምኔሃ” (ከአዳም ጐን የጐድን ዐጥንት እንደተነሣ አዳምንም አካል እንዳልጐደለው፤ እንዲኹ ከድንግል የምትናገር የምታውቅ ነፍስ ያለችውን ሥጋን ነሣ፤ ማኅተመ ድንግልናዋ አልተለወጠም፤ አዳም የጐድን ዐጥንት ከእርሱ ከተነሣ በኋላ አካል ሳይጐድለው ፍጹም ኾኖ ኖረ፤ ድንግልም ሕፃን ክርስቶስ ከርሷ ከተወለደ በኋላ እንዲኹ ያለመለወጥ በድንግልና ጸንታ ኖረች) በማለት የረቀቀውን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምስጢር አጒልቶ አስተምሯል፡፡ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የጸናውን የእምነታችንን መታጠቂያ ሊፈታብን የሚሞክረውን ረቂቁ ጠላታችን ሰይጣን ፈጽሞ ወደ እኛ ወደ ልጆችሽ እንዳይቀርብ በምልጃሽ ጠብቂን፨ ❖ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ❖