ru
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Открыть в Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Больше
4 374
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
አቤት የዚያን ጊዜ.mp32.82 MB

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 👉💟እምነት ብታጣ ይሉኝታ አትጣ፤ ወደ እግዚአብሔር ሽሽ እንጂ ከእግዚአብሔር አትሽሽሸ💟👈 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ✍ልጄ ጸጉርህ ወጣት ሳለህ ጥቁር፣ ጐልማሳ ስትሆን ገብስማ፣ ስትሸመግል ነጭ ይሆንልሃል። በወጣትነት ማስተዋል ያጥርሀልና ፀጉርሕ ጥቁር፣ በጎልማሳነትህ ጉልበትና ጥበብ ተዋህደውሃልና ገብስማ በሽምግልናህ እውቀትህ በዝቷልና ነጭ ይሆንልሃል። 👉ጉልበት ያለው ወጣት ማስተዋል ያጥረዋል። ማስተዋል ያለው ሽማግሌ ጉልበቱ ይከዳዋል። ጉልበትና ጥበብ የተዋሃዱት ጎልማሳ ስትሆን ግን ብዙ መስራት ይጠበቅብሃል። 👉ሀኪም ታማሚ ታካሚውን አስቀምጦ ወይም አስተኝቶ እንጂ በቁሙ እንደማያክመው ሁሉ እግዚአብሔርም አሳምሞ ወይም ጥሎ ያስተምርሃል። ደግሞም ያክምሃል። ሲያስተኛሕና ሲጥልህ "ጌታ ሆይ የምታስተምረኝ ምንድን ነው?" በለው እንጂ አትዘን አትማረር። ለሰው በቁሙ መማርና መለወጥ ብዙ ጊዜ ጭንቅ ነውና እግዚአብሔር ጥሎ ያስተምርሃል። ያነሣሃል። 👉ልጄ ሽምግልናን እንድታያት ወጣትነትህ ሽምግልናን ታክብራት። የናቅኸውን ነገር እግዚአብሔር አይሰጥህምና ሽማግሌ እንድትሆን ሽምግልናን አክብራት። 👉ልጄ አምስት አይነት ዘውዶች አሉ። አምስተኛው ግን ከሁሉም ይበልጣል። ✟ የመጀመሪያው የንግስና ዘውድ፣ ✟ ሁለተኛው የትምህርት ዘውድ፣ ✟ ሦስተኛው የተክሊል ዘውድ፣ ✟ አራተኛው የክህነት ዘውድ ሲሆኑ ✟ አምስተኛው ግን የሽበት ዘውድ ናቸው። አራቱም ዘውዶች ሲመሽ ይወልቃሉ። የማይወልቀው የተፈጥሮ ዘውድ ሽበት ግን ከሁሉም ይበልጣል መብለጡም በኑሮ ማስተዋልን መውለዱ ነው። 👉ልጄ የክብር ኑሮ አድካሚ ነውና አትመኘው ሀብትም ርካታ የለሽ ያደርጋልና ፍቅርን ምረጥ። አፈር ሥጋዬን ካላከበሩልኝ ብለህ ጠብ አታብዛ የምትረግጣት መሬት አንድ ቀን ትረግጥሃለችና አረማመድህ በዝግታ ይሁን። ገንዘብ ካለኝ ወዳጅ ይኖረኛል ብለሕ አታስብ። ገንዘብ ከድህነት እንጂ ከሞት አያስጥልም። ፍቅር በፍቅር እንጂ በገንዘብ አይገዛምና በገንዘብሕ ሀሰተኛ ወዳጅና እውነተኛ ጠላት እንደምታተርፍ እወቅ። ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ የተባለው ለአውሮፕላን እንጂ ለፅድቅ አይደለምና ገንዘብሕን ተማምነህ የድንግልን አማላጅነት የክርስቶስን ቤዛነት አትርሳ። 👉ልጄ እኔ ብቻ በችግር እኖራለሁ ብለህ ሌላው ባለመቸገሩ አትቅና። ሁሉም ለማኝ ሲሆን ደግ (ጥሩ) አይደለምና። ዛሬ ዓለም የተጨነቀው ሁሉም ሀገር በመቸገሩ ነው። ሁሉም ሲቸገር ደግ አይደለምና ይሕን አትመኝ። 👉ሲነጋ ወደ ዓለም ሲመሽ ወደ እግዚአብሔር አትገስግስ። መከራህን ለጌታ ደስታህን ለዓለም አታድርግ። እምነት ብታጣ ይሉኝታ አትጣ።ወደ እግዚአብሔር ሽሽ እንጂ ከእግዚአብሔር አትሽሽ። ሕፃን ልጅ ሲቆሽሽም የሚሸሸው ወደ እናቱ ነውና አንተም (ኃጢያትህ ሲበዛ) ወደ እናት ቤተክርስቲያንህ ሽሽና ንስሀ ግባ። ንስሃ ደግሞ ያጣኸውን ለማግኘት የብልጠት መንገድ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ስጦታ በትዕቢት ስለመያዝህ የምትፀፀትበት ሊሆን ይገባዋል። 👉ልጄ የወጣህበት ሰረገላ በመሬት ላይ ቆሟል! መሬት ደግሞ በእግዚአብሔር እጅ ላይ ተቀምጣለች። የተሸከመንን የተሸከመ እርሱ እግዚአብሔር ነው። የኮራንባቸው ነገሮች ሁሉ የእርሱ ናቸው። ከእርሱ በቀር የሚችለን ማንም የለም። ብዙ ዘመን ግን ያለ እግዚአብሔር በራሳችን ለመኖር እቅድ አውጥተናል፤ ያለ እግዚአብሔር መኖር ግን አይቻልም። ያለ እርሱ መኖር ፍፃሜው ሞት ነውና። 👉ልጄ ሆይ ከእግዚአብሔር ተለይተሕ መኖር አይቻልም። እርሱ በነፍስም በሥጋም ገዢሕ ነውና ከእርሱ ጋር ተጣበቅ። መንግስት ችግር ሳይመጣ ወታደሩን በችግር ያሰለጥናል፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን መቆም እንድንችል በትግል ውስጥ ያሰለጥንሃልና አትመረር። 👉ልጄ አንተ የሠማይ ኮኮብ ነህ። የተደበቅህ ቢመስልህም ሁሉ ያይሃል። የክዋክብት ሕልውናቸው ብርሃናቸው ነው። የአንተም ክርስትና ሕልውናው የተለወጠ ሕይወት መሆኑን አስተውል። አዎ የሰማይ ኮኮብ ነህ አገርህም በሰማይ እንደሆነ እወቅ። ስምህ ክርስቲያን አገርህ በሰማይ ዘርህ ክርስትና እናትህ ድንግል ማርያም ንጉስህ ክርስቶስ ነው። 👉ልጄ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል። ብዙዎች ስለጠሉህም ይጠላሃል። አንተ ግን የብዙሃን እውነት ነው ሳይሆን እግዚአብሔር እውነት ነው በሚል መመሪያ ተመራ። ለመልካምነትህ ክፉ ምላሽ ለወሮታህ ከሳሽ ቢነሳብህ የመልካም ነገር ደሞዝ ሰጪ እግዚአብሔር መሆኑን አምነህ ሥራህን ሥራ። 👉ልጄ መልካም ነገርህ ነገ ሊረሳ ይችል ይሆናል መልካም መሆንህንም ሰዎች ላይረዱልህ ይችላሉ እውነተኛ መልካምነት ግን ምስጋናን ሳያደምጡ የሚፈፀም መሆኑን እወቅ። 👉ልጄ ታማኝ ስትሆን ያለፈብሕ ትመስል ይሆናል፤ ግልፅ ስትሆን በቀላሉ ልትጠቃ ትችላለህ፤ ታማኝና ግልፅ መሆንህን ግን እግዚአብሔር ስለሚወደው ብቻ አጥብቀህ ያዘው። 👉ልጄ ልጅነት የለሰለሰ መሬት፣ ወጣትነት ያዝመራ ዘመን፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል። በሽምግልናሕም የምታጭደው የወጣትነትሕን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ። "ምክር ከእማሆይ ፅጌ አሌልቱ ደብረ ሰዋሰው አደሬ ኪዳነ ምሕረት የሴቶች ገዳም 🌻💐🌹 #Join us...🌹💐🌻 #Share #Share #Share #Share 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 👇 @EOTC2921 👇 👇 @EOTC2921 👇 👇 @EOTC2921 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

sticker.webp0.33 KB

✞✞✞ #የአምላክ_አቃቤ_ሕግ ✞✞✞ https://telegram.me/EOTC2921 ገባሬ መንክራት በግብሩ ያወቅነው፣ የእግሮቹ ትቢያ የአራዊት ስንቅ ነው፣ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአምላክ አቃቤ ህግ፣ የኢትዮጵያ ዋስ ነው ፈጥኖ የሚታደግ፡፡ #አዝ•••••••✞✞✞••••••• ፀሐይ /2/ የምድራችን ፀሐይ፣ በገድሉ ያበራል እስከ ጥልቁ ቀላይ፣ የመላዕክት ወዳጅ /2/ ገብረ ህይወት ሰማይ፡፡ #አዝ•••••••✞✞✞••••••• መብረቅ/2/ ሰረገላው መብረቅ፣ የቃል ኪዳኑ ወንዝ ቢጠጣ የማይደርቅ፣ የፍጥረቱ ደስታ/2/ ገብረ ህይወት ጻድቅ። #አዝ•••••••✞✞✞••••••• ኮከብ/2/ ክብረ ገዳም ኮከብ፣ አለምን የሚያስንቅ መዓዛው የሚስብ፣ አልክ ስሉስ ቅዱስ/2/ ገብረ ህይወት ኪሩ። #አዝ•••••••✞✞✞••••••• ስሒን/2/ ፄና ልብሱ ስሒን፣ የነፍስን አዳራሽ በገድል የሚሸፍን፣ የሚነበብ መጽሐፍ/2/ ገብረ ህይወት ድርሳን። #አዝ•••••••✞✞✞••••••• መቅረዝ/2/ የማህቶት መቅረዝ፣ ምድረ ከብድ ዝቋላን ያለመለመ ወንዝ፣ የዝግቲው ፈዋሽ/2/ ገብረ ህይወት ምርኩዝ፡፡{➋} #አዝ•••••••✞✞✞••••••• https://telegram.me/EOTC2921

ል ሁነኝ ብዙ ገንዘብ አለኝና" አለቻት። አባ አውጋንዮስ የተባለችው ቅድስቷም "እናቴ ሆይ ከእኔ ዘንድ ሒጂ ሰይጣን በከንቱ አድክሞሻል" አለቻት በአሳፈረቻትም ጊዜ ወደ እስክንድርያ ገዥ ሒዳ እንዲህ አለችው "እኔ ወደ ዕገሌ ቦታ በሔድኩ ጊዜ ሊደፍረኝ ሽቶ ወጣት መነኵሴ በሌሊት ወደእኔ መጣ ወደ አገልጋዮቼም ስጮህ ከእኔ ዘንድ ወጥቶ ሸሸ"። መኰንኑም በሰማ ጊዜ ይኸውም የቅድስት አውጋንያ አባቷ የሆነ መነኰሳቱን ሁሉ አሥረው ያመጧቸው ዘንድ አዘዘ በአደረሷቸውም ጊዜ እንዲአሠቃያቸው ለሌላ መኰንን አሳልፎ ሰጣቸው ከሥቃይም ጽናት የተነሣ ከእርሳቸው የሞቱ አሉ። + የመነኰሳቱንም መጐሳቈል በአየች ጊዜ መኰንን አባቷን እንዲህ አለችው "ጌታዬ ሆይ ምሥጢሬን ዕውነቱን እነግርህ ዘንድ የምፈልገውንም እንዳትከለክለኝ ማልልኝ" አለችው። በማለላትም ጊዜ ወደ ሥውር ቦታ ወስዳ ምስጢርዋን ሁሉ ገለጠችለትና ልጁ አውጋንያ እርሷ እንደሆነች አስረዳችው። መኰንኑም አይቶ "በእውነት አንቺ ልጄ አውጋንያ ነሽ እኔም በአምላክሽ አመንኩ" አላት። በዚያንም ጊዜ መነኰሳቱን ይፈቷቸው ዘንድ በመሠቃየት የሞቱትንም ይቀብሩአቸው ዘንድ አዘዘ ወዲውኑ ከቤተሰቦቹ ሁሉ ጋር ተጠምቆ ሁሉም ክርስቲያን ሆኑ። + የእስክንድርያ ሰዎችም የሃይማኖቱን ጽናት በአዩ ጊዜ በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት ክብር ይግባውና የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ሃይማኖት እያስተማረ ብዙ ዓመታትን ኖረ። ከዚህም በኋላ በእርሱ ላይ ሌላ ከሀዲ መኰንን ተነሥቶ ይህን ሊቀ ጳጳሳት ፊልጶስን በሥውር ይገድሉት ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ በቤተ ክርስቲያንም ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ገደሉት የሰማዕትነት አክሊል አገኘ። + የሮሜ ሊቀ ጳጳሳትም የቅድስት አውጋንያን ዜና በሰማ ጊዜ ወደርሱ ወስዶ እርሱ በሠራው ገዳም ላይ እመ ምኔት አድርጎ ሾማት የመነኰሳይያቱም ብዛት ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ነው እነዚያንም ከእርሷ ጋር የኖሩ ሁለት ጃንደረቦች በሁለት አገሮች ላይ ኤጲስቆጶስትነት ሾማቸው። ከዚህም በኋላ ሌላ ከሀዲ መኰንን በተሾመ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሷን ለሞት አሳልፋ እስከ ሰጠች ድረስ ቅድስት አውጋንያን ይዞ በጽኑ ሥቃይ አሠቃያት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት አውጋንያ በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። +++ + "ሰላም ለፊቅጦር ፍቁረ አምላኩ"። ትርጉም፦ የአምላኩ ወዳጅ ለኾነ ለፊቅጦር ሰላምታ ይገባል። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።                        +++ + ቅዱስ ፊቅጦር፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም መርመር የእናቱ ስም ማርታ ይባላል እነርሱም ያለ ፍርሀት እግዚአብሔርን የሚያመልኩት እውነተኞች ጻድቃን ናቸው ነገር ግን ልጅ አልነበራቸውምና ክብር ይግባውና ጌታችንን እየለመኑ ኖሩ ለድኆችም ምጽዋትን ይሰጡ ነበር። እግዚአብሔርም ልመናቸውን ተቀብለ ይቺ የተባረከች ማርታም ይህን ሊቅ ፊቅጦርን ፀንሳ ግንቦት ዘጠኝ ቀን ወለደችው እግዚአብሔርን በመፍራትም ሠርተው ቀጥተው አሳደጉት። + ሃያ ዓመትም ሲሆነው አባቱ ወደ ንጉሥ አቀረበውና ንጉሡም በአባቱ ፈንታ ምስፍና ሾመው አባቱ በዕድሜው ሸምግሎ ነበርና። ከጥቂት ወራትም በኋላ ጣዖታትን የማያመልኩ ክርስቲያኖችን ሁሉ ይገድል ዘንድ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ምልክትን ወደ እንጽና አገር መኰንን ደረሰ። መኰንኑም ክርስቲያኖችን እየፈለገ ወደ ሻው ከተማ ደረሰ ያን ጊዜ ክብር ይግባውና ክርስቶስን እንደሚአመልከው ክፉዎች ሰዎች ይህን ቅዱስ ፊቅጦርን ወነጀሉት ያን ጊዜም እንዲአመጡት አዘዘና በአመጡት ጊዜ ለጣዖታት እንዲሠዋ አስገደደው እምቢ በአለውም ጊዜ በወህኒ ቤት እንደመአሥሩት አዘዘ። + በዚያም እያለ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደ ሰማይ አወጣው የወህኒ ቤት ጠባቂዎችም በአጡት ጊዜ ተሸበሩ። ከሰባት ቀኖችም በኋላ አግኝተውት ወደ መኰንኑ ወሰዱት መኰንኑ ግን ራራለትና ወደ ንጉሡ ሰደደው ንጉሡም እግዚአብሔርን ከማምለክ ይመልሰው ዘንድ በማባበል ብዙ ሽነገለው። መመለስም በተሳነው ጊዜ አውጣኪያኖስ ወደሚባል መኰንን ሰደደው። እንዲህም ብሎ አዘዘው "እንሆ ፊቅጦርን ወደአንተ ልኬዋለሁ ያንተን ምክር ከሰማ ለአማልክት ይሠዋ ካልሰማህ ግን ግደለው እንጂ አትራራለት"። አለው። + ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ሊወስዱት እጆቹንና እግሮቹን አሠሩ በአፉም የብረት ልጓም አግብተው በመርከብ አሳፈሩት የእግዚአብሔርም መልአክ ወርዶ ከማሠሪያው ፈትቶ ወደ መኰንኑ አደረሰው ቅዱስ ፊቅጦርም መኰንኑንና ከሀዲውን ንጉሥ ሊረግም ጀመረ መኰንኑም ተቆጣ ጽኑዕ ሥቃይንም አሠቃይቶ በወህኒ ቤት አሠረው። በዚያም ሳለ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን በብርሃን ሠረገላ ላይ ሁኖ ተገለጠለትና ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚያችም ቀን ጀምሮ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙ በሽተኞችን የሚፈውስ ሆነ። + መኰንኑም ይህን ሰምቶ ተቆጣ ወደርሱ አስመጣውና ይመለሰው ዘንድ ደግሞ ሸነገለው ቅዱስ ፊቅጦር ግን የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ በዚያንም ጊዜ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው የአንድ ቀን መንገድ ያህል እንዲጐትቱት ከዚያም ከውሽባ ቤት እሳት ማንደጃ ውስጥ እንዲጨመሰሩት አዘዘ እንዲህም መልካም ተጋድሎውን ፈጸመ። ሥጋውን ግን ከዚያ ውሽባ ቤት አላወጡትም በመሰላል ወርደው በአማሩ ልብሶች ገንዘው በሽቱዎች አጣፈጡት እንጂ በላዩ ቤተ ክርስቲያንን ሠሩ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ፊቅጦር በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ5 ስንክሳር።                         +++ + "ሰላም ለአውጋንያ ዘተመሰለት ሕጽወ። በእንተ ክርስቶስ ታዝኅን መነኰሳተ አኃወ። ወጽድቀ አቡሃ ፊልጶስ እዜኑ መትልወ። እመንግሥተ ምድር ኃላፊ ለመንግሥተ ሰማይ አድለወ። እስከ በትሪያርከ ኮነ ዘይጌሥጽ አበወ"። ትርጉም፦ ወንድሞች መነኰሳትን ታረጋጋ ዘንድ ስለ ክርስቶስ በጀንደረባ የተመሰለች ለኾነች ለአውጋንያ ሰላምታ ይገባል፤ የአባቷ የፊልጶስን ጽድቅ አስከትዬ እናገራለኍ፤ ከኃላፊው የምድር መንግሥት ይልቅ ለመንግሥተ ሰማያት አደልቷልና፤ አባቶችን የሚገሥጽ በትርያርክ እስኪኾን ድረስ። +++ + "ሰላም ለከ መርዓዊ ሥርግው። በደመ ስምዕ ቀይሕ ወልብሰ አሚን ጽዕድው። ፊቅጦር ሰማዕት ዘደወለ ሻው። አጥዕሞ ለማኅሌትየ ውስተ ዕዝን ኵሉ ዕደው። ከመ ምረተ ማይ ነቢይ ቀሰመ በፄው። ትርጉም፦ በቀይ የምስክርነት ደምና በነጭ የእምነት ልብስ ያጌጥኸ ሙሽራ ሆይ ሰላምታ ላንተ ይገባል፤ በሻው አውራጃ ምስክር የኾንኽ ፊቅጦር የውሃውን ምረት ነቢይ ኤልሳዕ በጨው እንጣፈጠው በወንዶች ዦሮ ኹሉ ምስጋናዬን አጣፍጠው። አርከ ሥሉስ (አርኬ) የታኅሣሥ5።                         +++ + የዕለቱ ምስባክ፦ "ወለነዳያኒሃኒ አጸግቦሙ እክለ። ወለካህናቲሃኒ አለብሶሙ ሕይወተ። ወጻድቃኒሃኒ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑ"። መዝ131፥15-16። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ12፥32-41። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ አትናቴዎስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

+++ በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። +++          + ታኅሣሥ5 ቀን + እንኳን ዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ለሆነው ለኬልቅዩ ልጅ ለታላቁ ነቢይ ለቅዱስ ናሆም ለዕረፍት በዓል፣ ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለእግዚአብሔር ሕግ ለሚቀና ገድለኛ ለሆነ ለንጹሕ ድንግል ለቅዱስ አባት ለአባ ገብረ ናዝራዊ ለዕረፍት በዓል፣ ከሮም አገር ለሆነች ለቅድስት አውጋንያ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓልና አስዩጥ አውራጃ ሻው ከሚባል ከተማ ለሆነ ለቅዱስ ፊጦር ሰማዕትነት ለተቀበ ለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት፣ ቅዱሳን ከፊንጦስ፣ ከሐናንያ፣ ከባርክዮስ፣ ከዮሐንስ፣ ከተጋዳይዋ ከቅድስት አውጋንያ አባት ከፊልጶስና ከሰማዕት ቅዱስ ኤላውትሮስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                         +++ + ነቢዩ ቅዱስ ናሆም፦ ከስምዖን ነገድ የሆነ ይህ ጻድቅ ነቢይ ከነቢዩ ሙሴ በትንቢት ዐሥራ ሰባተኛ ነው። በካህኑ ዮዳሄ በነገሥታቱ በኢዮአስ፣ በአስሜስያስ፣ በልጁ በኦዝያን ዘመን ትንቢት ተናገረ ስለ ክህደታቸውና ጣዖታትን ስለ ማምለካቸውም የእስራኤልን ልጆች ገሠጻቸው። እግዚአብሔርም ምንም መሐሪና ይቅር ባይ ምሕረቱም የበዛ ቢሆን ካልተመለሱ ጠላቶቹን ይበቀላቸው ዘንድ እንደ አለው ለሚቃወሙትም የፍርድ ቀን እንደሚጠብቃቸው በትንቢት ገለጠ። + ዳግመኛም ስለ ከበረ የወንጌል ትምህርትና ስለ ሐዋርያት እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "የምሥራች የሚናገሩ ሰዎች እግራቸው እንሆ በተራራ ላይ ቁሟል ሰላምንም ይናገራሉ"። ስለነነዌም ውኃና እሳት ያጠፋአት ዘንድ እንዳላቸው ትንቢት ተናገረ እንደ ቃሉ ሆነ ከዕውነት መንገድ ተመልሰው በበደሉ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር በውስጡ ታላቅ ንውጽውጽታ አድርጎ እሳትም አውርዶ እኩሌታዋን አቃጥሏልና። በንስሐ ጸንተው ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን ግን ከክፉ ነገር ከቶ ምንም ምን አልደረሰባቸውም። የትንቢቱንም ወራት ሲፈጸም እግዚአብሔርም አገልግሎ በዚች ቀን ታኅሣሥ5  በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ነቢይ በቅዱስ ናሆም ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።    +++ + አባ ገብረ ናዝራዊ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ በወገን የከበሩ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው አባቱም የቤተ ክርስቲያንን ሕጓንና ሥርዓቷን የሚጠብቅ ካህን ነው እናቱም ፈጣሪዋን የምትወድ ደግ ሴት ናት። ይህም ቅዱስ በተወለደ ጊዜ በዕውቀት እግዚአብሔርን በመፍራት በመማር አደገ ከዚህም በኋላ ዲቁናን በተሾመ ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን የሚያነብ ሆነ በኦሪትም ውስጥ "የሰንበትን ቀን የሻረና ሥራ የሠራባት በሞት ይቀጣ" የሚል አገኘ። ከወንጌልም ውስጥ እንዲህ የሚል አገኘ "ከእነዚህ ትእዛዛት ታንሳለች ብሎ የሚያስተምር አንዲቱን የሻረ ለሰውም እንዲህ ብሎ የሚያስተምር በመንግሥተ ሰማይ የተለየ ይሆናል የሚያደርግና የሚያስተም ግን እርሱ በመንግሥተ ሰማይ ታላቅ ይሆናል" ዳግመኛም መድኃኒታችን "አባትና እናቱን ያልተው ሰውነቱንም ለመከራ አሳልፎ ያልጣላት ሊአገለግለኝ ደቀ መዝሙሬም ሊሆነኝ አይችልም" ያለውን አስተዋለ። + ከዚህም በኋላ ወደ አቡነ ጎርጎርዮስ ሔደ እርሱም ጽጋጃ በሚባል ገዳም የአቡነ አኖሬዎስ ልጅ ነው በዚያም መንኵሶ በጾም፣ በጸሎትና በስግደት እየተጋ ኖረ። ከዚህም በኋላ ቅስና ተሾመ ከዚያም ወደ ትግራይ አገር ሔዶ ከአባ ያዕቆብ ጋር ተገናኝቶ በቅዱሳት መጻሕፍት ቃሎች ተነጋገሩ። ከዚህም በኋላ ሀሳብን ገለጠለት አባ ያዕቆብም "እንዴት ይቻላል" አለው አባ ገብረ ናዝራዊም "እግዚአብሔር ይረዳኛል" አለ። ከአባ ያዕቆብም ጒልት ተቀብሎ እርስበርሳቸው በእግዚአብሔር ፈቃድ ተለያዩ። + ከዚህም በኋላ ተስፋፍቶ ገዳምን ሠራ ብዙ ሰዎችም ወደርሱ ተሰብስበው መነኰሳትን ሆኑ ስለሰንበታትና በዓላትም አከባበር እንደሚገባ ሥርዓትን ሠራ። ለመነኰሳትም ከመድኃኒታችን ከልደቱና ከጥምቀቱ በዓል ከሰንበታትና ከበዓለ ሃምሳ በቀር በየሰሞኑ ሁሉ እስከ ማታ ያለ ማቋረጥ መጾም እንደሚገባቸው ሥርዓትን ሠራ። ዳግመኛም የሌላውን ገንዘብ እንዳይነኩ እንዳይረግሙ በሕያው እግዚአብሔርም ስም እንዳይምሉም ለልጆቹ ይህን ሁሉ ያስተምራቸው ነበር። ለእርሱ ግን ለሚጸልየው ጸሎት ልክ የለውም ነቢይ ዳዊት "እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ አመሰግነዋለሁ። ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ውስጥ አለ" ያለውን አስቦ ዳግመኛም "ትእዛዝህን በማሰብ እጫወታለሁ ሕግህን እሻለሁ ትእዛዞችህንም አስተምራለሁ ቃልህም አልረሳም" ያለውን አስቦ። + ዳግመኛም ከሰባውና ደም ካለው ጣዕም ካላቸውም መብሎች ሁሉ ይከለከላል የጌታውን መከራ ለነፍሱ ያሳስባታልና ዕንባው ያለ ማቋረጥ ይፈስ ነበር ያለ ማቋረጥም ይሰግዳል ያመሰግናልም እንግዳና መጻተኛውን ይቀበላል "በጽዮን ዘር በኢየሩሳሌም ቤቶች ያለሐት ብፁዕ ነው" ያለውን የነቢይ ቃል አስቦ ድኆችንና ችግረኞችን ይጎበኛቸዋል። ለዚህም አባት ትሩፋቱ ብዙ ነው ደጋግ ተአምራትንም በማድረግ በሰው ልቡናም ተሠውሮ ያለውን በማወቅ ብዙ የተለያዩ ሀብቶች ተሰጥተውታል ለልጆቹም የቀናች ሃይማኖትን አስተማራቸው በእርሷም እንዲጸኑ አዘዛቸው ከዚህም በኋላ በሸመገለ ጊዜ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በዚች ቀን ታኅሣሥ5 ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት በአባ ገብረ ናዝራዊ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። +++ + "ሰላም ለአውጋንያ ቅድስት፤ ፍኖተ ስምዕ ዘሮጸት ከመ ወራዙት"። ትርጉም፦ እንደ ጐልማሳ ወደ ምስክርነት ጐዳና የሮጠች ለኾነች ለቅድስት አውጋንያ ሰላምታ ይገባል። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።                                                    +++ + ቅድስት አውጋንያ፦ የዚችም ቅድስት የአባቷ ስም ፊልጶስ ነው እርሱም የእስክንድርያ አገር ገዥ ነበር ጣዖትንም ያመልካል ስሙ መምድያኖስ የሚባል የሮም ንጉሥም ለጣዖት የሚሰግድ ነው ይቺም ቅድስት አውጋንያ በእስክድርያ ከተማ ተወለደች እናቷም ክርስቲያን ስለሆነች በሥውር የክርስቲያን ሃይማኖትን አስተማረቻት። + በአደገችም ጊዜ ታላላቆች መኳንንት አጯት አባቷም ይህን በነገራት ጊዜ "አባቴ ሆይ መጀመሪያ ወደ እስክንድርያ ገዳም እንድገባና እንድጎበኝ ተራሮችን በማየት ዐይኖቼ አይተው ደስ ይለኝ ዘንድ ፍቀድልኝ" አለችው አባቷም ሰምቶ ሁለት ጃንደረቦችን ጨምሮ የወደደችውን ታደርግ ዘንድ ፈቀደላት። በወጣችም ጊዜ የመነኰሳትን ገዳማት ሁሉ ዞረች ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል ጻድቅ ደግ ኤጲስቆጶስ ወደሚኖርባትም ቤተ ክርስቲያን ደረሰች ቀረብ ብላም በልቧ ያለውን ሁሉ ነገረችው ካጃንደረቦቿም ጋር ተጠምቃ በዚያ መነኰሰች በወንድ አምሳልም ሁና ስሟን አባ አውጋንዮስ አሰኘች እርሷ ሴት እንደሆነች ማንም አላወቀም። ወደ አባቷም ባልተመለሰች ጊዜ በቦታው ሁሉ ፈለጋት ሲአጣትም በርሷ አምሳል ጣዖት ሠርቶ ማታና ጧት እየሰገደላት ኖረ። + አንድ ዓመትም ከኖረች በኋላ የዚያ ቦታ አበ ምኔት አረፈ መነኰሳቱም መረጧትና አበ ምኔት አድርገው ሾሟት እግዚአብሔርም አጋንንትን ታስወጣ ዘንድ የዕውራንን ዐይኖች ትገልጥ ዘንድ ደዌውን ሁሉ ታድን ዘንድ ሀብተ ፈውስን ሰጣት። + ከዚህም በኋላ ሰይጣን በአንዲት ሴት ልብ ክፉ አሳብ አሳደረባት ከአዳነቻት በኋላ ወንድ መስላታለችና "ገዳምህንና ምንኵስናህን ትተህ ለእኔ ባ

🌿🌾✞ #በዓታ_ለማርያም ✞🌾🌿 ✔እመቤታችን አባትና እናቷ ኢያቄምና ሐና በስዕለት (ለቤተ መቅደስ ሊሰጡ ብፅዓት ገብተው) ያገኟት ናት፡፡ በአባት በእናቷ ቤትም ፫ ዓመት ተቀመጠች፤ ከእንግዲህ ወዲያማ ስእለት መብለት ይሆንብን የለምን ወስደን እንስጥ ብለው ይዘዋት ወደ ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ ጉባኤ አድርጎ ቆያቸው። ✔ከዚያውም ደርሰው እነሆ ተቀበሉን አሏቸው እነርሱም እንቀበላለን ብለው ቢያዩዋት ከፀሐይ ፯ እጅ አብርታ፥ ከመብረቅ ፯ እጅ አስፈርታ፥ ዕንቈ ባሕርይ መስላ ታየቻቸው፤ እነርሱም እኛ ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምን እንጋርድላታለን? ብለው ሲጨነቁ በዚህም መካከል እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያም መንፈሳዊ ረኀብ ተነስቶባት ምርር ብላ አለቀሰች። ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል በመሶበ ወርቅ ኅብስት ሰማያዊ፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ታያቸው፡፡ ሕዝቡም ዘካርያስን አባታችን ይህ የወረደው ክብር ላንተ ነው የሚኾነውና ተነስተህ ታጥቀህ እጅ ነስተህ ሰግደህ ተቀበል አሉት፤ ዘካርያስም እሽ ብሎ እጅ ነስቶ ሰግዶ እቀበላለሁ ብሎ ሲጠጋ ወደ ሰማይ ራቀው፥ መጠቀው፡፡ ከሕዝቡም እያንዳንዱ እየተነሱ እንቀበላለን ብለው ቢያዩ ወደ ሰማይ ራቃቸው፥መጠቃቸው፡፡ ✔ከዚህም በኋላ ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ ለናንተ ለእንግዶች የወረደ ክብር እንደሆነ ሕፃኒቱን ይዘሽ ወደዚያ ፈቅ ብለሽ ተቀመጪ አላት፡፡ እርሷም ሕፃኒቱን ይዛ ወደዚያ ፈቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ መልአኩም ከራሳቸው ላይ ረቦ አልወርድም አለ፡፡ ✔ሁለተኛም ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ነገር የሚያውቅ የለም፤ ሕፃኒቱን ከዚያው ትተሽ አንቺ ወዲህ ነዪ አላት፤ እሽ ብላ ሕፃኒቱን እዚያው ትታ ወደነሱ ሄደች፡፡ ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወርዶ ፩ ክንፉን ጋርዶ ፩ ክንፉን አጎናፅፎ ኅብስቱን አብልቷት፥ ወይኑን አጠጥቷት፤ እመቤቴ ሆይ መንገድ ባስመታሁሽ ማሪኝ ብሎ የብርሃን መሶብ፥ የብርሃን ጽዋ ይዞ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ✔ሕዝቡም የምግቧማ ነገር ከተያዘ ከሰው ጋራ ምን ያጋፋታል፤ ቦታዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን እንጂ ብለው ዙፋኑን ዘርግተው፥ ምንጣፏን አንጥፈው፥ መጋረጃውን ግራና ቀኝ ጋርደው ከቤተ መቅደስ አኖሯት፡፡ ✔ይኸውም የተደረገው ታኅሣሥ ፫ ዕለት ነው፤ በኣታ የሚለው ስያሜም የተሰጠው በዚሁ ነው፡፡ ‹‹አመ ፫ ለታኅሣሥ በኣታ›› እንዳለ መቅድመ ተአምር፡፡ በዚህም፤ ✔ መቅደሲቱ ወደ መቅደስ ገባች፤ ✔ ቅድስቲቱ ወደ ቅድስት ገባች፤ ✔ ክብርቲቱ ወደ ክብርት ቤቷ ገባች፤ ✔ ልዩ የሆነችው ወደ ልዩ ሥፍራ ገባች፤ ✔ ቅድስተ ቅዱሳኗ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገባች፤ ✔ ንጽሕተ ንጹሐኗ ወደ ንጽሕ አዳራሽ ገባች፤ ✔ ቤተ መቅደሷ ወደ ቤተ መቅደስ ገባች፡፡ ሊቃውንትም ‹‹መቅደስ ዘኢትትነሠት /የማትፈርሺ መቅደስ ነሽ››/ እያሉ አመሠገኗት፡፡ ✔እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች፤ ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላእክት ጋራ እየተጫወተች 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀመጠች፡፡ ✔‹‹ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ፤ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ፲ተ ወ፪ተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ወስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ። ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ››። እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ✔ምግቧ ከየት የተገኘ ነው ቢሉ በገበሬ እጅ ያልተዘራ በቤተ ሰብእ እጅ ያልተሠራ በእግዚአብሔር እጅ የተፈጠረ ያማረ የተመረጠ ነው እንጂ ፡፡ ‹‹ኦ ድንግል አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይኪ፤ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እም ሰማየ ሰማያት ዘበሰለ፡፡ ኦ ድንግል አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይኪ አላ ስቴ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘተቀድ›› (ድንንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን እንጂ፡፡ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጥን ነው እንጂ፡፡) /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/። ✔✞ ስታድግም በንጽሕናና በቅድስና ነው፡፡ ‹‹ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም በንጽሕና በቅድስና ኖርሽ እንጂ።›› /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/ ✔✞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ሳለች አይሁድ ብዙ የክፋት ምክር ይመክሩ ነበር። ከዚህም ውስጥ አንዱ መጥቁል ወደሚባል ጠንቋይ ሄደው ‹‹ፍታሕ ማዕከሌነ ኢያቄም ወሐና›› ብለው እመቤታችንን እንዲያጠፋ እጅ መንሻን ሰጡት፤ መጥቁልም በመካከል አይሁድ በኋላ ሁነው ነጋሪት እየጎሰሙ፥ እምቢልታ እየነፉ እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያምን ለመግደል ለቤተ መቅደስ ፪ ምንዳፈ ሐፅ ሲቀራቸው፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ እዚያ ድረስ ያልተደረገና ያልተነገረ መብረቅ ነጎድጓድ ወርዶ አጋንንትንም፥ መጥቁልንም፥ አይሁድንም ቀጥቅጦ አጠፋቸው። እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በማግሥቱ ወጥታ አይታ መጥቁል ሆይ እኔን አጠፋ ብለህ መጥተህ አንተ እንዲህ ሆንህ ካንተ መከራ መዓት ያወጣኝ አምላክ ይክበር ይመስገን ብላ ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ ከዚህ በኋላ በድኑ ለዝክረ ነገር የ፫ ቀን መንገድ እየሄደ ይሸት ጀመር። ✔✞እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ‹‹ዮሰሜር፣ አድሜሽ፣ ድቸር፣ አዶናዊሮስ፣ ሰራሰቅሰሬል›› ብላ የአምላክ ኅቡዕ ስምን ብትደግም መሬት ተከፍቶ ዋጣቸው ከነሥጋቸውም ሲኦል ወረዱ፡፡ ከዚህ በኋላ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እጅግ ታፈረች የሚናገራት ጠፋ ‹‹ኦ ግርምት ድንግል›› /እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም/። 🙏የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጣዕጧ፡ ፍቅሯ፡ በረከቷና ረድኤቷ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኒታችን ከፈጣሪያችንና ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለዘላለሙ ይኑር፡፡ አሜን🙏 ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

•✞ #አልፋና_ኦሜጋ ✞• •••✞•••✞•••✞••• አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ (2) በከሃዲዎች እጅ ተይዘክ ቀረብክ (2) •••✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሱህ ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ #አዝ••• ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስርው እንደ በግ ተጎትተህ ልትመራቸው የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ ፊትህን ሸፈኑት ለመመጻደቅ #አዝ••• በአውደ ምኩና ከጲላጦስ ዘንድ አሳልፈው ሰጡ አጋልጠው ለፍርድ ከሃና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ ከነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡ በአዋጅ #አዝ••• ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ #አዝ••• የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ ግፈኞች አይሁዶች ባንተ ላይ ቀለዱ ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ #አዝ•••

አልፋ እና ኦሜጋ.mp32.71 MB

#ድንግል_ሆይ_ስላንቺ •••✞•••✞•••✞••• ድንግል ሆይ ስላንቺ ነውና መሀሪ አማልጅኝ ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ ፊቱንም እንዳላይ ስራዬ አስቸገረኝ #አዝ••••••• ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ ትዛዙን እንደሻርሁ ህጉን እንደጣስኩኝ #አዝ••••••• በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ እለምንሃለሁ ከአሁኑ ይቅርታ #አዝ••••••• አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሳሪ አማልደኝ ከጌታዬ ከፈጣሪ #አዝ••••••• ፃድቃን ሰማዕታት እናንተ ሁላችሁ አማልዱኝ ከአምላኬ ከአምላካችሁ #አዝ•••••••

ድንግል ሆይ ስላንቺ @EOTC2921 .mp31.67 MB

የሚጠብቀኝ አይተኛም.m4a8.93 KB

አድነኝ አምላኬ.m4a8.84 KB

#አበው_ስለ_እመቤታችን ✔"አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ✔"ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው " ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ✔"ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት" ቅዱስ አውግስጢኖስ ✔"ሔሮድስ የማይያዘውን ይይዝ ዘንድ ተነሣ ፣ ዓውሎ ነፋስንም በቤቱ አስገብቶ ሊዘጋ ታገለ" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ✔"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??" ቅዱስ ኤፍሬም ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✞✞✞ #ጾም_ስጦታ_ነው ✞✞✞ ✔የጾምን ጥቅሞች እያወቅን ስንመጣ ጾም የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን እንረዳለን፡፡ አዎን፤ጾም እንዲሁ ከአሥሩ ትእዛዛት እንደአንድ ትእዛዝ የሚቆጠር ብቻ ሳይሆን መለኮታዊ ስጦታ፣ጸጋ እና በረከት ነው፡፡ እኛን ሥጋና ነፍስ አድርጎ የፈጠረን ለመንፈሳዊ ሕይወታችን የሚጠቅመው ጾም እንደሚያስፈልገን የሚያውቀው ለመንፈሳዊ ዕድገታችንና ለዘላለማዊነታችን የሚያስብልን እግዚአብሔር ጾምን ተግባራዊ የምናደርግበትን እውቀት አድሎናል፡፡ እሱም እንደ ቸር አባትና እንደ ጠቢብ መምህር ጾምን ለእኛ አዞልናል፡፡ በራሱ ኃይልና እውቀት የሚተማመን ሰው በራሱ ይመካል፤ ድካሙን የተገነዘበ ሰው ግን ችግር ሲገጥመው ልመናውን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበው በጾም ውስጥ ሆኖ ነው፡፡እግዚአብሔረ ለችግሮቻችን ሁሉ የደርስ ዘንድ ጾም ትክክለኛው ጊዜያችን ነው፡፡ ይህ ጊዜ የተሰበረ ልብ ወደ እግዚአብሔር የሚጣራበት እግዚአብሔር ደግሞ የሚሰማበት ጊዜ ነው፡፡ በእውነተኛ ጾም ውሰጥ ሰው የእግዚአብሔርን ልብ ማራራት ይችላል፡፡ አንድ ቅዱስ መነኩሴ"ፀሐይ ምግብ ስበላ ከተመለከተችኝ እንሆ ሠላሳ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡" በማለት ተናግረዋል፡፡ እስክንድርያዊው ቅድስ መርቆርዮስ ምግብ ይበላ የነበረው በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ነበር፡፡ሰው በተራበ ጊዜ የሚያቀርበው ልመና(ጸሎት) ይበልጥ ተሰሚነት አለው፡፡ሆድህ በምግብ ተሞልቶ ከምትጸልየው ሰዓታት ከሚወስድ ፀሎት ይልቅ በረሀብ ውስጥ ሆነህ የምታቀርበው የሁለት ደቂቃ ጸሎት ጥልቀት፣ ተሰሚነትና ተቀባይነት አለው፡፡ #አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

#ጌታችን_ሆይ_ስማን!!! ✔ሞት ሞትን ስቦ እልቂትን እንዳያመጣብን አምላክ ሆይ ጠብቀን፡፡ ሥጋ ወዳዶች ለአንድ አጥንት እርሱም ሥጋ ላልተረፈው እርስ በእርሳቸው ተባልተው ይህን ምስኪን ሕዝብ እርስ በእርሱ እንዳያባሉ ከላይ ከአርዓያም ያለህ አምላክ ሆይ ተቤዠን፡፡ ደምን ለተጠሙ ሞት የልብ ልብ ሰጥቶአቸው ሰይፋቸውን በልባችን ውስጥ እንዳይስጉ ፣የዘለዓለም ቤተ መቅደስህ ላደረግኸው ለዚህ ሰውነትህ እና ለእናትህ ልጆች ጌታ ሆይ እራራልን፡፡ ✔ሕዝቡን ከእልቂት ጠብቅ፤ ከውጭ እኛን ሊውጡ ከሚያገሡ ከውስጥ አጥንቶቻችንን ሊቆረጣጥሙ ካሴሩ ጌታ ሆይ ታደገን፡፡ ✔ለያዕቆብ በሴኬማውያን ፊት ሞገስና ፍርሃት እንደሆንከው፡ ጌታ ሆይ ለእኛም እንዲሁ ሁነልን፡፡ እኛንና የዚህችን ሀገር ሕዝብ ከጥፋት አድን፡፡ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያስማማ መሪን ስጠን፡፡ ✔ጌታ ሆይ! ኃይላችን አንተ ነህና አንተን አርዓያ አድርገን እኛ በዚህች ምድር መጻተኞች የሆንና ሀገራችን በሰማይ ያደረግን እንደሆነ ተረድተው፣ ሞት ድል የሚነሣት የዚህች ዓለም ሰዎች በእኛ ላይ እንዳይከፉ ፈቃድህንና ፈቃዳችንን አስታውቃቸው፡፡ ✔በላይ በአርያም ያለህ ፈጣሪያችን ሆይ! አሁን ንቃ መንጎችህንም ጠብቅ! ጊዜው ሥጋ የተጣለበት ጊዜ ነውና ሥጋ ናፋቂዎች እርስ በእርሳቸው ተባልተው ሲያበቁ በመርዘኛ ጥርሳቸው ጤናማውን ሕዝብ ነክሰው እንዳያሳብዱትና እርስ በእርሱ እንዳያነካክሱት መጠጊያችን ሆይ! ስምህን ታዛችን አድርገናልና በአንተ እንመካ እንጂ አንፈር፡፡ ክብር ላንተ ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን!!! ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር✞

#ጌታችን_ሆይ_ስማን!!! ✔ሞት ሞትን ስቦ እልቂትን እንዳያመጣብን አምላክ ሆይ ጠብቀን፡፡ ሥጋ ወዳዶች ለአንድ አጥንት እርሱም ሥጋ ላልተረፈው እርስ በእርሳቸው ተባልተው ይህን ምስኪን ሕዝብ እርስ በእርሱ እንዳያባሉ ከላይ ከአርዓያም ያለህ አምላክ ሆይ ተቤዠን፡፡ ደምን ለተጠሙ ሞት የልብ ልብ ሰጥቶአቸው ሰይፋቸውን በልባችን ውስጥ እንዳይስጉ ፣የዘለዓለም ቤተ መቅደስህ ላደረግኸው ለዚህ ሰውነትህ እና ለእናትህ ልጆች ጌታ ሆይ እራራልን፡፡ ✔ሕዝቡን ከእልቂት ጠብቅ፤ ከውጭ እኛን ሊውጡ ከሚያገሡ ከውስጥ አጥንቶቻችንን ሊቆረጣጥሙ ካሴሩ ጌታ ሆይ ታደገን፡፡ ✔ለያዕቆብ በሴኬማውያን ፊት ሞገስና ፍርሃት እንደሆንከው፡ ጌታ ሆይ ለእኛም እንዲሁ ሁነልን፡፡ እኛንና የዚህችን ሀገር ሕዝብ ከጥፋት አድን፡፡ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያስማማ መሪን ስጠን፡፡ ✔ጌታ ሆይ! ኃይላችን አንተ ነህና አንተን አርዓያ አድርገን እኛ በዚህች ምድር መጻተኞች የሆንና ሀገራችን በሰማይ ያደረግን እንደሆነ ተረድተው፣ ሞት ድል የሚነሣት የዚህች ዓለም ሰዎች በእኛ ላይ እንዳይከፉ ፈቃድህንና ፈቃዳችንን አስታውቃቸው፡፡ ✔በላይ በአርያም ያለህ ፈጣሪያችን ሆይ! አሁን ንቃ መንጎችህንም ጠብቅ! ጊዜው ሥጋ የተጣለበት ጊዜ ነውና ሥጋ ናፋቂዎች እርስ በእርሳቸው ተባልተው ሲያበቁ በመርዘኛ ጥርሳቸው ጤናማውን ሕዝብ ነክሰው እንዳያሳብዱትና እርስ በእርሱ እንዳያነካክሱት መጠጊያችን ሆይ! ስምህን ታዛችን አድርገናልና በአንተ እንመካ እንጂ አንፈር፡፡ ክብር ላንተ ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን!!! ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር✞