የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Открыть в Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Больше4 374
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
4 374
✝ " የሰው ልጅ በኅጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሶስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናተ እንደተናገረ አስቡ :: "
የሉቃስ ወንጌል 24:6- 7
🤲 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳቹ !
➠ ለመቤታችን ድንግል ማርያም
➠ ለቅዱሳን
➠ ለተዋሕዶ
➠ ለፀሎት
➠ ወዘተ.. የተገጠሙ ግጥሞች እና የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን OPEN የሚለውን ተጭነው የ TELEGRAM ቻናሉ ላይ ማግኘት ይችላሉ ! 👇
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇👇 👇
. 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
SHARE SHARE SHARE ⏩
4 374
♥ ከንፈሮችሽም የደስታ ምንጮች ናቸው፤ አንደበትሽም የምስጋና መፍለቂያ ነው፤ እጅግ በጣም አማርሽ፤ ቁመትሽም እንደ ዘንባባ ዛፍ ነው፤ የልብሶችሽ መዐዛም አፈው በመባል እንደሚታወቀው ሽቱ፤ የአፍንጫሽ መዐዛም እንደ ወይን አበባ ሽታ የሚኾንልሽ ድንግል ሆይ ደስታሽን እወደዋለኊ (ማሕ ፯፥፰) የአፍሽም አከፋፈት እንደ ቀናንሞስ አበባ የጣፈጠ ነው፤ ከሊባኖስ ዕንጨቶች ኹሉ ጋር (ማሕ ፬፥፲፬)) በማለት እንደ ሰሎሞን ርሱም የፈጣሪውን እናት አመስግኗል፡፡
♥ የፈጣሪያችን እናት ቅድስት ድንግል የተወለደችበትን ግንቦት አንድን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን “ልደታ ለማርያም” በማለት ከጥንት ዠምሮ በታላቅ መንፈሳዊ ሐሤት በቅዳሴ፣ በማሕሌት የምታከብርላት ሲኾን፤ በተለያዩ ክፍላተ ዓለማት ያሉ ክርስቲያኖችም ይኽነን በዓል “The Nativity of the blessed Virgin Mary” (የተባረከችው የድንግል ማርያም ልደት (መወለድ)) በማለት ያስባሉ።
♥ በጥንት ምሥራቃውያን (እንደ ቤዛንታይን ባሉ) ዘንድ ዐዲሱ ዓመት ልክ እንደኛ መስከረም ወር “September” ላይ ይውል ስለነበር ከዚኽ አያይዘው መስከረም ፰ (September 8) ያከብሩት የነበረ እንደነበር ታሪክ ሲያስረዳ ይኽነን ይዘው በዚኽ ዕለትም የሚያከብሩት ብዙዎች የዓለማት ሀገራት አሉ፡፡
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
[ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፤ ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል አንድ ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ]
#የአምላክ_እናት_በረከቷ_በእኛ_በአደራ_ልጆቿ_ላይ_በዝቶ_ይደር፡፡
4 374
ፈጣሪያችን ክርስቶስን በድንቅ ተአምር ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ የወለደችልን ምክንያተ ድኂን ርግበ ሰሎሞን የተባለች የቅድስት ድንግልን የመፀነሷን ነገር በአድናቆት ገልጸዋል፡፡
♥ “ወእምድኅረ ስድስቱ አውራኅ ተዐውቀ ፅንሳ ለሐና” ይላል፤ ከስድስት ወርም በኋላ የሐና ፅንሷ እየታወቀ ሲመጣ ጎረቤቶቿ መፅነሷን ይረዱ ዘንድ በአድናቆት ማሕፀኗን ይዳስሱ ነበር፤ በተለይም ዐይኗ የታወረ የሐና ዘመዷ የአርሳባን ልጅ የምትኾን አንዲት ሴት የሐናን ማሕፀን ዳስሳ ዐይኗን ብትነካው በርቶላት በታላቅ ደስታ ኾና “ብፅዓን ለኪ ኦ ሐና እስመ እም ፍጥረተ ዓለም አልቦ ዘከማኪ ዘይፌውስ በከርሡ አዕይንተ ዕውራን” (ሐና ሆይ ብፅዓን ይገባሻል ዓለም ከተፈጠረ ዠምሮ እንዳንቺ በማሕፀኑ የዕውራንን ዐይን የሚያበራ የለምና) በማለት አመስግናታለች፤ ከዚኽ በኋላ ዝናዋ በሀገሩ ኹሉ ተሰምቶ ሕሙማን ኹሉ ማሕፀኗን እየዳሰሱ ይፈወሱ ነበር፡፡
♥ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ይኽነን ሲገልጹ፦
✍ “ጸግይየ ሣዕረ ዘኪሩቤል ልሳነ
ተአምረኪ በነጊር እመ ኢፈጸምኩ አነ
ባሕቱ አአኲት ማርያም ዘጾረተኪ ማሕፀነ
እንዘ ሀለወት ፀኒሳ ኪያኪ ርጢነ
ለለገሰስዋ ላቲ ትፌውስ ዱያነ”
♥ (ሳርን የኾንኊ እኔ የኪሩቤል አንደበትን ገንዘብ አድርጌ ታምርሽን በመንገር በማስተማር ባልፈጽምም ነገር ግን ማርያም የተሸከመቺሽን ማሕፀን አመሰግናለኊ፤ መድኀኒት አንቺን ፀንሳ ሳለች ርሷን የዳሰሷትን ድዉያንን ኹሉ ትፈውስ ነበር) በማለት እመ መድኅነ ዓለም ገና ሳትወለድ የተሠራውን ድንቅ ተአምር አመስግነዋል፡፡
♥ ይኽ የቅድስት ድንግል ማርያም የፅንሰት በዓል በመላው ዓለም የሚታወቅ ሲኾን ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት የኾነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን የአምላክ እናት የተፀነሰችበት ይኽነን በዓል ነሐሴ ፯ ቀን በታላቅ ድምቀት በማሕሌት፣ በቅዳሴ የምታስበው ሲኾን በዓሉም “ፅንሰታ ለማርያም” በመባል ይታወቃል።
♥ በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ደግሞ በዓሉን “The conception of the Theotokos” (የአምላክ እናት መፀነስ) በማለት ሲያከብሩት ወሩን ግን የልደት በዓልን ለማክበር በሚዘጋጁበት በታኅሣሥ አድርገው በ፱ኛው ቀን “December 9” ላይ ያስቡታል ፡፡
♥ በእጅጉ የሚደንቀው ደግሞ “ሳሚናስ ወልደ ጦሊቅ ዘይነብር ውስተ ቤተ ዶይቅ” ይላል ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጐቱ ቤት ኼዶ ሞተ፤ ሐናም በሀገራቸው ልማድ የአልጋውን ሸንኮር ይዛ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ፈጥኖ ተነሥቶ “ሰላም ለኪ ኦ ሐና እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ” (ሰማይና ምድርን ለፈጠረው አምላክ አያቱን የተባልሽ ሐና ሰላም ላንቺ ይኹን) አላት።
♥ ከዚያ የነበሩ አይሁድም በመደናገጥ “ሳሚናስ ምን አየኽ? ምን ትላለኽ?” አሉት፤ ርሱም “ከዚች ከሐና ማሕፀን የምትወለደው ሕፃን ሰማይ ምድርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ኹሉ ሲያመሰግኗት ሰማኋቸው፤ እኔንም ያነሣችኝ ርሷ ናት” አላቸው፤ እነርሱም ይኽነን በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔርን ከማመስገን ይልቅ በቅናትና በክፋት ተመልተው ሐና በማሕፀን ባለ ፅንሷ ካዳነች በኛ ላይ ልትሠለጥን አይደለምን? “ንዑ ንገሮሙ ለሐና ወለኢያቄም” ሳትወልድ አስቀድመን ሐናና ኢያቄምን በድንጋይ ወግረን እንግደላቸው ብለው ተነሣሡባቸው።
♥ ያን ጊዜ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ሐናን ሊባኖስ ወደሚባል ተራራ እንዲወስዳት ነገረው፤ ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ እመቤታችን በሊባኖስ ተራራ እንደምትወለድ ተገልጾለት፡-
✍“ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ንዒ ወተወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን አምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት” (ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነዪ ከሊባኖስ ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ) በማለት የተናገረው ትንቢት ሊፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም በ፭ ሺሕ ፬፻፹፭ (5485) ዓመተ ዓለም በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች (ማሕ ፬፥፲)፡፡
♥ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ የነገረ ማርያም መጽሐፋቸው ላይም፦
“ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ
በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ
ማእከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ እንዘ እነቡ
እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዐጽ እሌቡ
ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ”
♥ (ትንቢት ከተነገረለት ከአንበሳ ጉድጓድ፤ ድንግል ሙሽራ በተገኘሽ ጊዜ የንጉሦች ንጉሥ የሰሎሞን ልቡ እንደተደሰተ፤ ደስ ባላቸው በመላእክት አንድነት ፊት ታምርሽን እየተናገርኊ የሐና አበባ ማርያም እዘምርሻለኊ፤ ወተትን ጠብቶ እንደሚዘልል እንቦሳም ዝለል ዝለል ይለኛል) በማለት ሰሎሞን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን አግኝቶ ታላቅ ደስታን ለኹላችን እንደሰጠን አብራርተው ገልጠዋል፡፡
♥ ይኽ የእመቤታችን ልደት ለሰማያውያን መላእክትና ለደቂቀ አዳም ደስታ ሲኾን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከርሷ ተወልዶ ዲያብሎስ ፭ሺሕ፭፻ ዘመን በሲኦል ያኖራቸውን ነፍሳት ወደ ገነት የሚያስገባቸው ነውና፤ ሰይጣን በተቃራኒው ልደቷ እንዳላስደሰተው ሲገልጹ፦
✍ “ተፈሥሐት ምድር ወሰማይ አንፈርዐጸ
በዕለተ ጸገዩኪ አብላስ ወአውጽኡ ሠርጸ
ተአምረ ሕይወት ማርያም ዘአልብኪ ቢጸ
እስከ ፈርሀ መልአከ ሞት ወሰይጣን ደንገጸ
ዜና ልደትኪ ነጐድጓድ እስከ (ውስተ) ሲኦል ደምፀ”
(በለሶች (ኢያቄምና ሐና) ቡቃያ አንቺን ባስገኙሽ ጊዜ ምድር ደስ አላት ሰማይም ደስ አለው፤ ጓደኛ (ምሳሌ) የሌለሽ የድኅነት ምልክት ማርያም፤ መልአከ ሞት እስከ ፈራና ሰይጣንም እስከ ደነገጠ ድረስ የመወለድሽ ዜና እስከ ሲኦል ድረስ (በሲኦል) ተሰማ) በማለት አስተምረዋል፡፡
♥ ጠቢቡ ሰሎሞን አስቀድሞ በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ በማሕልዩ ላይ “መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ትሔውጽ ከመ ጎሕ ሠናይት ከመ ወርኅ ወብርህት ከመ ፀሓይ” (ይኽቺ እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ እንደ ጨረቃ የተዋበች፤ እንደ ፀሓይም የጠራች ዐላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሰራዊት የምታስፈራ ማን ናት?) በማለት እንደ ፀሓይ የሞቀ እንደ ጨረቃ የደመቀ ንጽሕናዋና ቅድስናዋ የመልኳ ደም ግባት በነቢያት ትንቢት አስቀድሞ የተጐበኘላት የእውነት ፀሓይ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብርና ደም ግባቷን እንደተናገረ በሊባኖስ ተራራ በግንቦት ፩ በተወለደች ጊዜ ፊቷ በእጅጉ ያበራ ነበር፤ መዐዛዋም ከሽቱ ኹሉ ይበልጥ ነበር፡፡
♥ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም የመዐዛዋን አስደናቂነት በሰሎሞንን ቃል በመነሣት የመዐዛዋን ነገር ሲያደንቅ፡-
✍ “ወእወዲ ውስተ አፉየ እምፍሬ ከርሥኪ…” (ከማሕፀንሽም ፍሬ ወደ አፌ እጨምራለኊ፤ የፍሬሽ ደምም ለጉሮሮዬ የጣፈጠ ነው፤ የሽቱሽ መዐዛም ለአፍንጫዬ ያማረ ነው፤ የድንግልናሽ ክብርም ልቡናዬን እንደ ከረመ ንጹሕ ወይን ደስ ያሰኘዋል፤ ስለ አንቺ ያለኝ ደስታ ምን ያኽል ነው፤ አነጋገርሽ ያማረ ነው፤ ቃልሽም የጣፈጠ ነው።
4 374
#የአምላክ_እናት_ልደት____ልደታ_ለማርያም
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
♥ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት መተርጒማን እንዳስተማሩንና እንደጻፉልን በእናቷ በሐና በኩል ያሉ የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ጴጥሪቃ ቴክታ ሲባሉ “ወኮኑ ክልኤሆሙ ጻድቃን ወፈራህያነ እግዚአብሔር ወይትአመንዎ ለአምላኮሙ በጥቡዕ ልብ እንበለ ኑፋቄ” ይላል (ኹለቱም ሰዎች ደጋጐችና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ያለምንም መጠራጠር በፍጹም ልቡናቸው በአምላካቸው የሚተማመኑ ነበሩ)፤ እነርሱም በጊዜው ይኽ ቀራችኊ የማይባሉ ባለጠጎች ነበሩ፤ ከሀብታቸው ብዛት የተነሣ ወርቁን ብሩን እንደ ዋንጫ እያሠሩ በላሙ በበሬው ቀንድ ላይ ይሰኩት ነበር፤ ይኽን ያኽል አቅርንተ ወርቅ፣ አቅርንተ ብሩር እየተባለ ይቈጠር ነበር፤ የዕንቊ ጽዋ እንኳ ፸፣ ፹ ያኽል ነበራቸው ይላል፡፡
♥ ከዕለታት ባንዳቸው ጴጥሪቃ ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ የሀብቱን ብዛት አይቶ ሚስቱ ቴክታን “ለመኑ ዘዘገብነ መዛግብቲነ አልብነ ውሉድ ዘይወርሰነ አንቲኒ ወአነሂ መካን ንሕነ” (የሰበሰብነው ገንዘብ ስንኳን ለኛ ለልጅ ልጅ ይተርፍ ነበር አንቺም እኔም መካኖች ነንና የሚወርሰን ልጅ የለንም) በማለት ተናገራት፤ ርሷም እንዲኽ ማለቱ ወላድ የፈለገ መስሏት በሐዘን ኾና “አምላከ እስራኤል ከኔ ልጅ ባይሰጥኽ ከሌላ ይሰጥኽ ይኾናልና ሌላ አግብተኽ ውለድ” አለችው፤ ርሱም “አነሂ ኢይፈቅድ የአምር አምላከ እስራኤል ከመ ኢየሐስቦ ለልብየ” (ይኽንስ እንዳላደርገው በልቤም እንዳላስበው የእስራኤል አምላክ ያውቃል) በማለት ተናገረ፡፡
♥ ርሷም ዐዝና ሳለ ራእይ ታያለች፤ ነጭ እንቦሳ ከማሕፀኗ ስትወጣ እንቦሳዪቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ሰባት ስትደርስ ሰባተኛዋ ጨረቃን ስትወልድ፤ ጨረቃ ፀሓይን ስትወልድ አይታ በአድናቆት ለባሏ፦ ❖ “ግሩም ግብሩ ለእግዚአብሔር ትማልም ርኢኩ በሕልምየ ጸዐዳ ጣዕዋ ወጽአት እምከርሥየ ይእቲኒ ወለደት ጸዐዳ ጣዕዋ እስከ ሰብዐቲሆን ወሳብዕታኒ ወለደት ወርኀ ወወርኅኒ ወለደት ፀሓየ”
♥ (የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው፤ ትናንትና ማታ በሕልሜ ነጭ ጥጃ ከማሕፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ደግሞ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንደዚኽ እየኾነ እስከ ሰባት ትውልድ ሲደርሱ ሰባተኛዪቷም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየኊ) በማለት አስረዳችው።
♥ ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ሕልም ወደሚፈታ ሰው ዘንድ በመኼድ የሚስቱን ራእይ ነገረው፤ ያም ሕልም ተርጓሚ ምስጢር ተገልጾለት ሰባት አንስት ጥጆች መውለዳችኊ ሰባት ሴቶች ልጆች ይወለዳሉ፤ ነጭ መኾናቸው ደጋጎች ልጆች መኾናቸው ሲኾን “ወሳብእታኒ ትከብር እመላእክት ወትትሌዐል እምኲሉ ሰብእ ወበእንተ ፀሓይኒ ኢያእመርኩ” (ሰባተኛዪቱ ጨረቃን መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ናት፤ የፀሓይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም) በማለት ተረጐመለት፤ ርሱም ለሚስቱ ነገራት፤ ርሷም “የእስራኤል አምላክ የሚያደርገውን ርሱ ያውቃል” በማለት ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡
♥ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች ስሟንም ሔሜን አሏት፤ ሔሜን → ዴርዴን ወለደች፤ ዴርዴም → ቶናን፤ ቶናም →ሲካርን ወለደች፤ ሲካርም→ ሴትናን፤ ሴትናም →ሔርሜላን ወለደች፤ ሔርሜላም የተከበረችና የተመረጠች ዓለሙን ኹሉ ለፈጠረ ጌታ አያት ለመኾን የበቃች ሐናን ወልዳለች።
♥ ሐናና ኢያቄምንም “ወክልኤሆሙ ኄራን ወሥሙራን እሙንቱ ወየሐውሩ በሕገ እግዚአብሔር እስመ እግዚአብሔር ኀረዮሙ ወአፍቀሮሙ ትካት” ይላቸዋል እግዚአብሔርን የሚወድዱ በሕጉ የሚኖሩ ደጋጎችና አምላክም የመረጣቸው ሲኾኑ ሐና መካን በመኾኗ ምክንያት ኹለቱም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ዕለት ዕለት በመኼድ ለዐይናቸው ማረፊያ ለልባቸው ተስፋ የሚኾን ልጅ እንዲሰጣቸው ይለምኑ እንደነበር፤ “Protoevangelium of James” (ፕሮቶቫንጊሊዩም ኦፍ ጀምስ) የሚለው ያዕቆብ የጻፈው ጥንታዊዉ መጽሐፍ በስፋት ይገልጻል፡፡
♥ ከዕለታት ባንደኛው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ሲመለሱ “ወርእዩ አርጋበ እንዘ ይትፌሥሑ ምስለ ውሉዶሙ” ይላል ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ደስ ብሏቸው ሲጫወቱ አይተው ሐና “አቤቱ ጌታዬ ግዕዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠኽ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሣኸኝ” ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፤ ወዲያው ሱባዔ ይገባሉ፤ ኢያቄም ወደ በረሓ ኼዶ ሲጸልይ ሐና ደግሞ በቤቷ ዙሪያ ባለው የተክል ቦታ ሱባዔ ያዘች።
♥ በሱባዔያቸው ፍጻሜ ኹለቱም ራእይ አይተው ተነጋግረዋል፡፡ “ይቤላ ኢያቄም ለሐና ብእሲቱ እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ” ይላል ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዎፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ብሎ የተገለጸለትን ለሐና ነግሯታል።
♥ ይኸውም የራእዩ ምስጢር፡- ወፍ የተባለው አካላዊ ቃል ክርስቶስ ሲኾን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፤ ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ ሲያጠይቅ ሲኾን፤ ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ምልአቱ፣ ስፍሐቱ፣ ርቀቱ፣ ልዕልናው፣ ዕበዩ ናቸው፡፡
♥ ሐናም ተገልጾላት “ትቤሎ ሐና ለኢያቄም ብእሲሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ” ይላል ለባሏ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ብላዋለች።
♥ ይኽ የራእይ ምስጢር፡- ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትኾን፤ ነጭነቷ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፤ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ ወደ ዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በዦሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መኾኗን ሲያጠይቅ ነው፡፡
♥ ኢያቄምና ሐናም ይኽነን ራእይ ሐምሌ ፴ ቀን ካዩ በኋላ “ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ይኾናል፤ ሴትም ብንወልድ ለቤተ እግዚአብሔር መጋረጃ ፈትላ ትኑር” ብለው ስእለት ከተሳሉ በኋላ ራእይ አየን ብለው ዕለቱን አልተገናኙም፤ አዳምንና ሔዋንን “ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት” ብሎ የተናገረው አምላክ ለእኛም ይግለጽልን ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ሰባት ቀን ድረስ እየብቻቸው ሰነበቱ።
♥ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን “ከሰው የበለጠች ከመላእክት ኹሉ የከበረች ልጅ ትወልዳላችኊ" ብሎ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለሐና ነግሯት በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን ነሐሴ ሰባት እሑድ ተፀንሳለች፤ በእናቷ ማሕፀን ሳለችም “መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እምከርሠ እማ” እንዲል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥንተ አብሶ ባመጣው መርገም እንዳትያዝ ጠብቋታል፡፡
♥ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም መፀነስ ከሊቃውንት መኻከል አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ፦
✍ “ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ
ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ
ወፈረየኪ ለሕይወት ኢያቄም መዋቲ
እሴብሕ ተአምረኪ ርግብየ አሐቲ
ወድኀኒተ ኲሉ ዓለም እስመ ኮንኪ አንቲ”
♥ (ሐና አንቺን የፀነሰችባት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ አንዲቱ ርግቤ ማርያም አንቺ የዓለሙ ኹሉ መድኀኒት ኾነሻልና ታምርሽን አመሰግናለኊ) በማለት ዓለምን ኹሉ በደሙ ፈሳሽነት ያዳነ ንጉሣችን፣
4 374
•✞✞✞ #ግን_መቼ_ነው ? ? ? ✞✞✞•
☞መቼ ነው ፣ እውነተኛ ክርስቲያን የምሆነው? ?
☞መቼ ነው ፣ እግዚአብሔርን መፍራት የምጀምረው? ?
☞መቼ ነው ፣ እግዚአብሔርን ማመስገን የምጀምረው? ? እስከመቼስ ነው በዋዛ በፈዛዛ ጊዜየን የምጨርሰው? ?
☞በከንቱ ጊዜዬን እጨርሳለሁ እፍፍፍ
መቼ ነው ፣ እግዚአብሔር በሰጠኝ ነገር ደስተኛ የምሆነው ? ? ሁልግዜ
አማርረዋለሁ ግን ለምን?
☞ኦ አምላኬ እዳስተውል እርዳኝ
መቼ ነው ፣ ሰውን እደራሴ አድርጌ የምወደው? ?
☞መቼ ነው ፣ ለጠሉኝ ሁሉ መልካም የማደርገው ? ? እኮ መቼ?
☞መቼ ነው? እግዚአብሔር ለምን እደፈጠረኝ የምረዳው? ?
☞እኔማ ሁሌም በአለም ከንቱነት ጠፋሁ አለም አታለለችኝ
☞መቼ ነው ፣ እግዚአብሔር እንደፈለገው መኖር የምጀምረው ? ?
☞እኮ መቼ? እድሜዬን አንድም ቀን መልካም ሳልሰራበት..?
☞መቼ ነው፣ ክፉ ንግግር ከመናገር ተንኮል ከመስራት የምቆጠበው ? ?
☞መቼ ነው ፣ለፆም ለፀሎትና ለስግደት በሙሉ ልቤ ሆኘ የማገለግለው እኮ መቼ? ?
☞መቼ ነው፣ ለመልካም ስራ ምሳሌ የምሆነው? ?
☞መቼ ነው ፣ ይህን ከንቱ አለም ከልቤ የማወጣው ? ? ? እኮ መቼ ?
☞መቼ ነው ፣ እኔ ማለት ትቼ እህት ወንድሞቼ ወገኖቼ ማለት የምጀምረው ? ሁሌም እራስ ወዳድ እፍፍፍፍ....
☞መቼ ነው ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የማከብረው ? ??
☞እኮ መቼ ነው እንደ ቃሉ የምኖረው ?
☞እስከመቼስ ነው የሚፈልገውን ነገር ትቼ የሚጠላውን ነገር የምከተለው እፍፍፍ....
☞መቼ ነው ፣ ጥሩ እና ለጋሽ አዛኝ የምሆነው? ?
☞መቼ ነው ፣ በፍቅር መኖር የምጀምረው ? ? ? ሁልጊዜ ልቤ
በጥላቻ ተሞልቷል...
☞መቼ ነው ሰውን ከመበደል ከማስቀየም የምቆጠበው? ??
☞መቼ ነው ከራስ ወዳድነት የምላቀቀው ? ? ?
☞መቼ ነው ተመስገን አምላኬ የምለው? ? ?
☞ኦ አምላኬ አንተ እርዳኝ እኔስ ግራ ገባኝ ???
አምላኬ ሆይ ጥበብና ማስተዋሉን፤ ልብና ልቦናውን፤ ጥንካሬና ብርታቱን እምነትና የዋህነቱን፤ ትግስትና ፍቅሩን•••ለኛ ለባሮችህ ትሰጠን ዘንድ አማላጅ በምትሆን በቅድስተ ቅዱሳን በእመአምላክ በንፅህት ቅድስት ድንግል ማርያም፤ እንዲሁም አንተ ባከበርካቸው ቅዱሳን ፀሎትና ቃልኪዳን ማረን ይቅር በለን፡፡ አቤቱ ሆይ እኛ ሀጢያተኛ ባሮችህን ለንሰሀ ሞት አብቃን፡፡
•••✞ አሜን ✞ አሜን ✞ አሜን ✞•••
4 374
✝ " የሰው ልጅ በኅጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሶስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናተ እንደተናገረ አስቡ :: "
የሉቃስ ወንጌል 24:6- 7
🤲 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳቹ !
➠ ለመቤታችን ድንግል ማርያም
➠ ለቅዱሳን
➠ ለተዋሕዶ
➠ ለፀሎት
➠ ወዘተ.. የተገጠሙ ግጥሞች እና የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን OPEN የሚለውን ተጭነው የ TELEGRAM ቻናሉ ላይ ማግኘት ይችላሉ ! 👇
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇👇 👇
. 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
SHARE SHARE SHARE ⏩
4 374
✝ " የሰው ልጅ በኅጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሶስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናተ እንደተናገረ አስቡ :: "
የሉቃስ ወንጌል 24:6- 7
🤲 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳቹ !
➠ ለመቤታችን ድንግል ማርያም
➠ ለቅዱሳን
➠ ለተዋሕዶ
➠ ለፀሎት
➠ ወዘተ.. የተገጠሙ ግጥሞች እና የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን OPEN የሚለውን ተጭነው የ TELEGRAM ቻናሉ ላይ ማግኘት ይችላሉ ! 👇
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇👇 👇
. 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
SHARE SHARE SHARE ⏩
4 374
✝ " የሰው ልጅ በኅጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሶስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናተ እንደተናገረ አስቡ :: "
የሉቃስ ወንጌል 24:6- 7
🤲 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳቹ !
➠ ለመቤታችን ድንግል ማርያም
➠ ለቅዱሳን
➠ ለተዋሕዶ
➠ ለፀሎት
➠ ወዘተ.. የተገጠሙ ግጥሞች እና የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን OPEN የሚለውን ተጭነው የ TELEGRAM ቻናሉ ላይ ማግኘት ይችላሉ ! 👇
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇👇 👇
. 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
SHARE SHARE SHARE ⏩
4 374
✝ " የሰው ልጅ በኅጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሶስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናተ እንደተናገረ አስቡ :: "
የሉቃስ ወንጌል 24:6- 7
🤲 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳቹ !
➠ ለመቤታችን ድንግል ማርያም
➠ ለቅዱሳን
➠ ለተዋሕዶ
➠ ለፀሎት
➠ ወዘተ.. የተገጠሙ ግጥሞች እና የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን OPEN የሚለውን ተጭነው የ TELEGRAM ቻናሉ ላይ ማግኘት ይችላሉ ! 👇
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇👇 👇
. 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
SHARE SHARE SHARE ⏩
4 374
✝ " የሰው ልጅ በኅጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሶስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናተ እንደተናገረ አስቡ :: "
የሉቃስ ወንጌል 24:6- 7
🤲 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳቹ !
➠ ለመቤታችን ድንግል ማርያም
➠ ለቅዱሳን
➠ ለተዋሕዶ
➠ ለፀሎት
➠ ወዘተ.. የተገጠሙ ግጥሞች እና የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን OPEN የሚለውን ተጭነው የ TELEGRAM ቻናሉ ላይ ማግኘት ይችላሉ ! 👇
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇👇 👇
. 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
SHARE SHARE SHARE ⏩
4 374
#መድኃኔዓለም_አዳነን
መድኃኔዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ /2/
ደስ ይበለን /2/ እልል በሉ /2/
አዳነን በማይሻር ቃሉ /2/
4 374
✝ " የሰው ልጅ በኅጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሶስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናተ እንደተናገረ አስቡ :: "
የሉቃስ ወንጌል 24:6- 7
🤲 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳቹ !
➠ ለመቤታችን ድንግል ማርያም
➠ ለቅዱሳን
➠ ለተዋሕዶ
➠ ለፀሎት
➠ ወዘተ.. የተገጠሙ ግጥሞች እና የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን OPEN የሚለውን ተጭነው የ TELEGRAM ቻናሉ ላይ ማግኘት ይችላሉ ! 👇
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇👇 👇
. 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
SHARE SHARE SHARE ⏩
