የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Открыть в Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Больше4 374
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
4 374
#ታኅሣሥ_19
ዮሐንስ ኤጲስ ቆጶስ ወገብርኤል ሊቀ መላእክት፡፡
#ዘቅዳሴ
#2ኛ_ተሰሎ_1:6-ፍጻሜ፡ወርቱዕሰ ይትፈደዩ በኀበ እግዚአብሔር"መከራ የሚያጸኑባችሁ እነዚያ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍዳቸውን ይቀበሉ ዘንድ ይገባል፡፡.................
.........................................................የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ላይ ይከብር ዘንድ እናንተም በእርሱ ትከብሩ ዘንድ እንጸልያለን፡፡"
#ይሁዳ_1:20-ፍጻሜ፡ወአንትሙሰ አኃዊነ ሕንጹ"ወንድሞቻችን ሆይ እናንተ ግን በተቀደሰች ሃይማኖት ራሳችሁን እነጹ በመንፈስ ቅዱስም ጸልዩ፡፡....................................................................................................አሁንም እስከ ዘለዓለም ድረስ በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኀይልም ሥልጣንም ይሁን፡፡አሜን፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_7:30-35፡ወተፈጺሞ 40 ዓመት"አርባ ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ በበረሃ በደብረ ሲና የእግዚአብሔር መልአክ በቁጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው፡፡............................
........................................................በግብጽ ያሉትን የወገኖቼን መከራ ማየትን አይቻለሁ ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ ላድናቸውም ወርጃለሁ አሁንም ና ወደ ግብጽ ሀገር ልላክህ፡፡"
#ምስባክ
በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ
ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ
ወእገኒ ለስምከ፡፡
#ትርጉም
በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ
ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ በስምህ ሁሉ፡፡
#መዝ_137:1-2
#ወንጌል
#ሉቃስ_1:11-21፡ወአስተርአዮ መልአከ እግዚአብሔር"የእግዚአብሔር መልአክም በዕጣን መሠውያው በስተቀኝ ቆሞ ታየው፡፡...................
........................................................አሁንም በጊዜው የሚሆነውንና የሚፈጽመውን ነገሬን አላመንኸኝምና ይህ እስኪሆን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም ይሳንሃል፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘእግዝእትነ፡፡(ጎሥዓ)
4 374
#በእንተ_ልደቱ_ለእግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ
🌾🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾🌾
፩. #በኮከብ_መጽኡ
በኮከብ መጽኡ(፪) ሰብአ ሰገል
ለአማኑኤል(፬) ይስግዱ ለአማኑኤል
፪. #ቤዛ_ኩሉ
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ(፪)
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ(፬)
የዓለም ሁሉ መድኀኒት ዛሬ ተወለደ(፪)
የዓለም ሁሉ መድኀኒት ዛሬ ተወለደ(፬)
፫. #አንፈርዐጹ
አንፈርዐጹ ሰብአ ሰገል(፪)
አምኃሆሙ አምጽኡ መድምመ(፪)
፬. #አንፈርዐጹ
አንፈርዐጹ ሰብአ ሰገል ረኪቦሙ ህፃነ ህፃነ(፪)
ዘተወልደ ለነ(፬) ህፃነ ዘተወልደ ለነ
፭. #በቤተልሔም_ተወልደ
በቤተልሔም ተወልደ(፪) አማኑኤል
እምዘርአ ዳዊት (፬) ተወልደ አማኑኤል
፮. #ተወልደ_ኢየሱስ
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም(፪) ዘይሁዳ በቤተልሔም
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ(፪) በቤተልሔም
፯. #ወወለደት
ወወለደት ወልደ ዘበኩራ(፪)
መንጦላዕተ ደመና ሠወራ(፬)
፰. #ለዘተወልደ
ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ምንተንብሎ ናስተማስሎለመድኀኒነ
አርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ(2) ከራድዮን
፱. #ስብሐት_ለእግዚአብሔር
ስብሐት ለእግዚአሔር በሰማያት(፪)
ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብዕ ሃሌሉያ(፫)ሃሌ(፪)ሉያ
፲. #አማን_በአማን
አማን በአማን(፪) መንክር(፪)
መንክር ስብሐተ ልደቱ(፬)
እውነት በእውነት(፪) ድንቅ ነው (፪)
ድንቅ ነው የጌታ ልደቱ(፬)
፲፩. #ይትፌስሃ
ይትፌስሃ አድባረ ጽዮን ወይትሀስያ አዋልደ ኢትዮጵያ
እስመ ተወልደ ብኁተ ልደት መድኀኔዓለምበኢየሩሳሌም መድኀኔዓለም
፲፪. #ዮም_ሰማያዊ
ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል
ርዕይዎ ኖሎት (፪)አእኮትዎ መላእክት(፪)
፲፫. #ወእንዘ_ትፈትል
ወእንዘ ትፈትል(፪)ወርቀ ወሜላተ አስተርአያ ገብርኤል ግብተ
ወይቤላ(፪) እስመ ረከብኪ ሞገሰ በሀበ እግዚአብሔር
፲፬. #ወእንዘ_ትፈትል
ወእንዘ ትፈትል/፪/ ወርቀ ወሜላት
አስተርአያ ገብርኤል አስተርአያ ለማርያም
፲፭. #ለድንግል
ለድንግልገብርኤል አብሰራ
ሚካኤል/፪/በክነፍ ጾራ/፪/መንጦላዕተ ደመና ሠወራ
፲፮. #ሊቀ_መላእክት
ሊቀ መላእክት ገብርኤል ዘአብሠራ ለድንግል
ኃያል ኃያል/፬/ ሰዳዴ ሳጥናኤል ኃያል ገባሬ ኃይል
፲፯. #መጽአ_ከመ_ይቤዙ
መጽአ ከመ ይቤዙ ዓለም
የሀበነ ሰላመ ጋዳ ያበውዑ ቁርባነ
፲፰. #በጎለ_እንስሳ
በጎለ እንሰሳ
በጎለ እንሰሳ ተወልደ አማኑኤል
፲፱. #ብርሃን_ዘመፅአ
ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም(፪)
ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም(፬)
፳. #ኢየሱስ_ክርስቶስ
ኢየሱስ ክርስቶስ መፅአ ውስተ ዓለም
በብርሃኑ ንዑ ናንሶሱ
፳፩. #መድኀኒነ
መድኀኒነ ተወልደ ነዋ መድኀኒነ ተጠምቀ ነዋ(፪)
ይዕዜኒ ለሰላም ንትልዋ(፬)
፳፪. #ኢየሩሳሌም_በሆን
እንደ ዮሴፍ ወይ እንደ ሰሎሜ በሆን
ኢየሩሳሌም(3) በሆን አምላክ ሲወለድ ባየን
እንደ እረኞች ወይ ሰብአ ሰገልን በሆን
ኢየሩሳሌም(3) በሆን አምላክ ሲወለድ ባየን
፳፫. #በጎል_ሰከበ
በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ከሉ ዓለም(፪)ዮም ተወልደ
በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ
የዓለም መድኀኒት(፪) ዛሬ ተወለደ
፳፬. #እም_ሰማያት
እም ሰማያት ወረደ ወእማርያም ተወልደ(፪)
ከመይኩን ቤዛ(፪) ለኩሉ ዓለም ለብሰ ሥጋ ማርያም
ከሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያም ተወለደ
እንዲሆነን ቤዛ(፪)ለዓለሙ ሁሉ ተዋሐደየማርያምን ሥጋ
፳፭. #የምስራች
የምስራች ደስ ይበለን(፪)
የዓለም መድኃኒት ተወለደልን
ምስራች ደስ ይበለን
የምሥራች ደስ ይበለን(፪)
ጌታችን ተወልዶ አይተነው መጣን(፪)
ንጉሥ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ
ፈልጋችሁ አምጡት በቀን በጨለማ(፪)
ሰብአ ሰገል እንደታዘዙት
በኮከብተመርተው ህፃኑን አገኙት(2)
ሰገዱለት ከመሬት ወድቀው
ወርቅዕጣን ከርቤውንም ሰጥተው(2)
፳፮. #ይኸው_ተወለደ
ይኸው ተወለደ የዓለም መድኃኒት(3)
እሰይ ተወለደ የዓለም መድኃኒት(3)
ትንቢት ተናገሩ ነቢያት በሙሉ(3)
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ(3)
ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ(3)
የእስራኤል ንጉሥ ተወልዷል እያሉ(3)
ሰብአ ሰገል እጅ መንሻ ይዘው(3)
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው(3)
ህፃናት እንሂድ ከልደቱ ቤት(3)
ውኃው ሆኗልና ማርና ወተት(3)
በሶርያ ታየ ፈጣሪ እንደእነግዳ(3)
ብስራተ ልደቱን ለሁሉ ሊያስረዳ(3)
፳፯. #ሳርቅጠሉ_ሰርዶው
ሳር ቅጠሉ ሰርዶ ሰንበሌጥ ቄጤማው
በዚያች ቀን በዚያች ወር ለምለም የነበረው
በእልልታ ዘመሩ በደስታ ተውጠው
ጌታ መወለዱን የምስራች ሰምተው
እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ
የታደሉ እረኞች ያደሩ በትጋት
ብርሃን ሆነላቸው በእኩለሌሊት
ጥሪ ተደርጎለት ከሰማይ ሰራዊት
ለመመልከት በቃ የጌታውን ልደት
እረኝነት ትንሽ የወራዳ ግብር
ብሎ ሰው በልማድ ደንግጎ ነበር
አምላክ የመረጠው መሆኑን እረኛ
ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ
የተነበዩለት ነቢያት በሙሉ
ጌታ ተወለደ የምስራች በሉ
ሰውን በመውደዱ ሰማያዊው ንጉስ
ይኸው ተወለደ እኛን ለመቀደስ
የሩቅ ምስራቅ ሰዎችሰብአ ሰገል ሰምተው
ሊሰግዱለት መጡ በኮከብ ተመርተው
ዕጣንና ከርቤ ወርቁንም አመጡ
እንደየስርአቱ እጅ መንሻ ሰጡ
ስለተወለደ መድኅን የእኛ ተስፋ
በደል ተወገደ ኃጢያትም ጠፋ
፳፰. #አንቺ_ቤተልሔም
አንቺ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ መሬት
በአንቺ ተወለደ የዓለም መድኃኒት
ለአዳም ክብር ሲሻ ቤተልሔም
ለሁሉም ሰላም ”
ዛሬ ተወለደ ”
ከድንግል ማርያም ”
እጅ መንሻ አቀረቡ ቤተልሔም
የምሥራቅ ነገሥታት ”
በከብቶች በረት ”
ተኝቶ ላገኙት ”
እሥራኤል ሕዝቤን ቤተልሔም
የሚጠብቃቸው ”
ከአንቺ ይወጣል ብሎ ”
እንደ ነገራቸው ”
፳፱. #እሰይ_እሰይ_ተወለደ
እሰይ እሰይ ተወለደ (፪)
ከሰማየ ሰማያት ወረደ (፪)
ከድንግል ማርያም ተወለደ
እሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ
ቸሩ አባታችን ”
መች ትገኝ ነበረ ”
ገነት ምድራችን ”
ብርሃን ወጣላቸውእሰይእሰይ
ለመላ ሕዝቦቹ ”
በጨለማ ጉዞ ”
እንዲያ ሲሰላቹ ”
እንደ ጠል ወረደ እሰይ እሰይ
ከሰማይ ወደ እኛ ”
ወገኖቹን ሊያድን ”
ከኃጢአት ቁራኛ ”
እግዚአብሔር አብ ላከ እሰይ እሰይ
አንድያ ልጁን ”
እርሱ ወዷልና ”
እንዲሁ ዓለሙን ”
፴. #አዳምን_ያልተወው
አዳምን ያልተወው እንደተሰደደ
እሰይ የምሥራች ዛሬ ተወለደ (፪)
አምላካችን መድኃኒታችን
ተወለደ ለነፃነታችን(፪)
አዳምን ያልተወው እንደ ተጨነቀ
እሰይ የምሥራች ዛሬ ተጠመቀ (፪)
አዳምን ሊጠራ የመጣው ሙሽራ
በገሊላ መንደር ለሠርግ ተጠራ(፪)
ሠርግ ቤት እንዳለ በክብር ተቀምጦ
የወይን ጠጅ ሆነ ውሃው ተለውጦ (፪)
እጅግ ያስደንቃል የጌታችን ሥራ
በገሊላ መንደር ይህን ተአምር ሠራ (፪)
ጌታችን አንድ ቀን ያደረገው ተአምር
ሲያስደንቅ ይኖራል ይህን ሁሉ ፍጡር (፪)
4 374
#ማርያም_ማለት፦ ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ማለት ነው።አካላዊ ቃል በእመቤታችን አድሮ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፈስዋ ነፍስ ነስቶ መለኮትን ከትስብእት (ከሥጋ) ትስብእትን ከመለኮት አዋሕዶ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው ሆኖ ስለተገለጠባት ለአምላክ ሰው የመሆኑ ምክንያት ለሰው የመዳኑ ምክንያት ናትና “ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብዕ” ትባላለች።የሰውን ልመና ወደ እግዚአብሔር የእግዚአብሔርን ይቅርታ ወደ ሰው በማድረስ ወደ ሰው በማድረስ ድህነተ ሥጋ ድህነተ ነፈስ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እያማለደች ታሰጠናለችና።ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብዕ ተብላለች።
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥሞች እንዳሉ ሆነው ሌላ ምስጢራዊ ወይም ዘይቤያዊ ስሞችም አሏት እነርሱም፦
ሀ. #እመ_ብርሃን፦ የብርሃን እናት ማለት ነው።ጌታችን እና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው (በማስተማር ዘመኑ) እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ።ብሏል (ዮሐ 8፥12) ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ሴት ብርሃን ተጎናጽፋ ጨረቃ ተጫምታ 12 ከዋክብት የተቀረፀበት ዘውድ ደፍታ ተገለፀችልኝ ብሏል።(ራዕ 12፥1)።
ብርሃን የተባለ የባሕርይ አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ የእርሱ እናት ደግሞ ድንግል ማርያም ስለሆነች ይህ እመ ብርሐን የተሰኘው ስም ይገባታል።
ለ. #ወላዲተ_አምላክ፦ የአምላክ እናት ይህ ስም ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የሚገባት ነው።ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ የሆነ በተዋሕዶ የከበረ የወልደ እግዚአብሔር የኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እናት ለመሆን ከሴቶች መካከል የተመረጠች እርሷ በመሆኗ ነቢዩ ኢሳይያስም በትንቢቱ እንደተናገረው ከእርሷ የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ ነው።(ኢሳ 9፥6)። በሌላም ሥፍራ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የምትወልደው አምላክ ስሙ አማኑኤል ተብሎ እንደሚጠራ ተናግሯል።(ኢሳ 7፥14)። “አማኑኤል” ማለትም የእግዚአብሔር መልአክ እንደተረጐመው እግዚአብሔር ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ ሰው ሆነ ማለት ነው።(ማቴ 1፥23)።
#በብሉይ_ኪዳን_ነቢያት “ይቤ እግዚአብሔር” እያሉ የተናገሩት ትንቢቱ በኢየሱስ ክርስቶስ መፈፀሙ የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት የባህርይ አምላክ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። (ኢዮ 2፥32፣የሐዋ ሥራ 2፥21-38፣ሮሜ 10፥9-13፣ኢሳ 40፥3፣ማር 1፥1-3)።እነዚህን ብቻ ማመሳከሩ በቂ ነው።ይህንን ሁሉ ይዘን ድንግል ማርያም ለአምላክ እናትነት ብቻ የተፈጠረች የእግዚአብሔር እናት ናት እንላለን።ከዚህ የወጣ ትምህርት የለም ቢኖርም የመናፍቃን ትምህርት ነውና ተቀባይነት የለውም።
በተጨማሪም የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት አባታችን ቅዱስ ቄርሎስ “አማኑኤልየባሕርይ አምላክ እንደሆነ ንጽሕት ድንግልም አምላክን የወለደች እንደሆነች ሰው የሆነ የእግዚአብሔርንም ቃል እንደወለደች የማያምን ሰው ቢኖር የተወገዘ ይሁን” በማለት ከአወገዘ በኋላ “ዳግመኛ በኋላ ዘመን ቅድስት ድንግል እርሱን በሥጋ በወለደችው ስለእኛ ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ወለደችው።”ስለዚህም ቅድስት ድንግልን ወላዲተ አምላክ እንላታለን።ሰው ሳይሆን ሰውም ከሆነ በኋላ አንድ ወልድ አንድ ክርስቶስ ነው።ከእግዚአብሔር አብ የተገኘ ቃል ሌላ አይደለም ከቅድስት ድንግል የተወለደውም ሌላ አይደለም የምናምንበት ከዓለም አስቀድሞ የነበረ ከድንግል በሥጋ የተወለደ ይህ አንድ ወልድ ነው እንጂ (ሃ.አ.ገጽ 277-305) በማለት ቅድስት ድንግል ማርያም እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ መሆኗን መስክሯል።
ሐ. #ኪዳነ_ምሕረት፦ ኪዳን ውል ስምምነት መሓላ የሚል ትርጉም ሲኖረው ምሕረት፣ቸርነት፣ ነፃ ስጦታ፣ፍቅርን የሚያመለክት ሀይለ ቃል ሲሆን ይህ ስም #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ከጌታችን_ከአምላካችን_ከመድኃኒታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ ስምሽን የጠራ እምርልሻለሁ የሚል ስለ ሓጥአን የተሰጣትን የምሕረት ቃል ኪዳን ማሳሰቢያ ነው።(መዝ 88፥3) “ከመረጥኳቸው ጋር የምሕረት ቃል ኪዳንን አደረግሁ።”እንዲል።
Page 5
👉 @EOTC2921 👈
4 374
#ስመ_ድንግል_ማርያም
✍በእስራኤላውያን ዘንድ “ስም” ጠባይን፣ግብርንና ሁኔታን እንደሚገልጥ ሁኖ ይሰየማል። ከዚህ የተነሳ #የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል_ማርያም እናት እና አባት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም “ማርያም” ብለው አወጡላት ይህ ስም የእመቤታችንን ማንነት የሚገልጥ ነው።ለመሆኑ “ማርያም” ማለት ምን ማለት ነው?
#ማርያም_ማለት፦ በእብራይስጥ ማሪሃም ማለት ሲሆን እመ ብዙኃን የብዙዎች እናት ማለት ነው።አብርሃም ማለት አበ ባዙኅን (የብዙዎች አባት) ማለት እንደሆነ ዘፍ 17፥5
#ማርያም_ማለት፦ መርሕ ለመንግስተ ሰማያት ወደ መንግስተ ሰማያት መርታ የምታስገባ ማለት ነው።ምክንያቱም ከሕገ እግዚአብሔር የወጣው ከፀጋ እግዚአብሔር የተራቆተው አዳም ወደ ቀደመ ክብሩ እንዲመለስ ምክንያተ ድህነት የሆነችው ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ናትና ወደ መንግስተ ሰማይ መርታ የምታስገባ ትባላለች።
የእመቤታችን አማጅነት ተስፋ ሳያደርግ ወደ መንግስተ ሰማይ መግባት የሚቻለው የለምና።
#ማርያም_ማለት፦ ፀጋ ወሃብት ማለት ነው ለጊዜው እናትናአባቷ በሰው ዘንድ ባለ ልጅ መውለዳቸው ተንቀው ተዋርደው ይኖሩ ነበር እርሷን በመውለዳቸው ተከብረውባታል ስለዚህ ለእናትና ለአባቷ ፀጋ እና ሃብት ሁና ተሰጥታለች።
ለፍፃሜው አማላጅነቷን አውቀው ቃል ኪዳኗን አምነው ለሚመጡ ምዕመናን ሁሉ በዮሐንስ ወንጌላዊ አማካኝነት ለምዕመናን ሁሉ እናት አማላጅ ሁና ተሰጥታለች።ስለዚህ ማርያም ተብላለች። (ዮሐ 19፥26፣ሉቃ 1፥28-30)።
ማርያም ማለት፦ ፍፅምተ ሥጋ ወነፍስ ማለት ነው።ፍፅምት ማለት ምንም አይነት እንከንና ጉድለት የሌለባት ንፅሕተ ንፁሐን ቅድስተ ቅዱሳን አዳማዊ በደል (ጥንተ አብሶ) ያልነካት ማህደረ እግዚአብሔር ትሆን ዘንድ የተገባት ማለት ነው። እንኳን እመቤታችን በፀጋ ያከበራቸው ቅዱሳንም ከፍፁምነት መድረሳቸውን መፃህፍት ምስክር ሆነዋል።(ዘፍ 6፥1፣ኢዮብ 1፥1)።
#ማርያም_ማለት፦መልዕልተ ፍጡራን ከፍጡራን በላይ ስንል ከ 22 ሥነ ፍጥረት ማለታችን ነው።ከእነዚህም ፍጡራን መካከል እግዚአብሔር አክብሮና አልቆ የፈጠራቸው ሰውንና መላእክትን ነው ሰውና መላእክት በተለየ ክብር መፈጠራቸው ዛሬ ሕጉን አክብረው ስሙን ቀድሰው በኋላ ክብሩን ስለሚወርሱ ነው።እመቤታችን ከፍጡራን በላይ ናት ስንልም ከሰው ልጆችም ሆነ ከመላእክት የምትከበር ማለታችን ነው።ምክንያቱም በቅዱሳን መላእክትም ሆነ በቅዱሳን አባቶቻችን እግዚአብሔር በረድኤት አድሮባቸው ይኖራል።እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነሥቶ በፍፁም ተዋህዶ ዓለምን ለማዳን ምሕረቱን የገለጠባት እመ መሐሪ በመሆኗ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ከእርሷ በቀር ማንም የለም።
ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ “የዐቢ ክብራ ለማርያም እምኩሎሙ ቅዱሳን” የማርያም ክብር ከቅዱሳን ክብር ይበልጣል።ይህች ከኪሩቤል ትበልጣለች……..ከሱራፌልም ትበልጣለች ከሦስቱ አካል ለአንዱ #ለእግዚአብሔር_ወልድ ማደሪያ ሆናለችና ብሏል።
Page 4
👉 @EOTC2921 👈
4 374
#በኦርቶዶክሳዊት_ተዋህዶ_ቤተ_ክርስቲያናችን_እንደሚተረከው_የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል_ማርያም_ዕረፍት_በሆነበት_ዕለት_ሐዋርያት_የእመቤታችንን_ሥጋ (አስክሬን) ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ መካነ ዕረፍት (የመቃብር ቦታ) ይዘው ሲሄዱ አይሁድ በቅንአት መንፈስ ተነሳስተው ቀድሞ ልጇን በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሣ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ እንደገናም ተመልሶ ይህን ዓለም ለማሳለፍ ይመጣል።እያሉ በማስተማር ሕዝቡን ፈፅመው ወስደውታል።አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷንም እንደ ልጇ ተነሣች ዐረገች እያሉ በማስተማር ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለምን? ኑ!ተሰብሰቡና በእሳት እናቃጥላት ብለው ተማክረው መጥተው ከመካከላቸው ታውፋንያ የተባለ ጎበዝ አይሁዳዊ ተመርጦ ሄደ የእመቤታችንን ሥጋ (አስክሬን)የተሸከመበትን አልጋ ሸንኮር ያዘ የአልጋውን ሸንኮር በያዘ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁለት እጆቹን ስለቆረጣቸው ከአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ።
ነገር ግን ታውፋኒያ በፈፀመው ድርጊት ተፀጽቶ ወደ እመቤታችን ለተማፀነ በኅቡዕ ተአምር የተቆረጡ እጆቹን እንደ ቀድሞው አድርጋ ፈውሳቸዋለች።
በዚያን ጊዜም መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ (አስክሬን) ከሐዋርያው ከዮሐንስ ጋር ነጥቆ ወስዶ በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው ቅዱስ ዮሐንስም ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ሐዋርያት ሲመጣ የእመቤታችን ሥጋ (አስክሬን) በገነት መኖሩን ነገራቸው ሐዋርያትም #የእመቤታችንን_ሥጋ (አስክሬን) አግኝተው ለመቅበር በነበራቸው ምኞትና ጉጉት የተነሣ ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ጀምረው ሲጾሙና ሲፀልዩ ከሰነበቱ በኋላ በ14ኛው ቀን (በሁለተኛው ሱባኤ መጨረሻ)ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ አስክሬን አምጥቶ ስለሰጣቸው በታላቅ ዝማሬ በውዳሴና በጽኑ ምሕላ ወስደው ቀድሞ በተዘጋጀ መካነ ዕረፍት በጌቴ ሴማኒ ቀበሯት።
የእመቤታችን የቀብር ሥነ ሥርዓት በተፈጸመ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው #ቅዱስ_ቶማስ አልነበረምና ከሀገረ ስብከቱ ከህንድ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጇ ትንሣኤ ተነስታ ስታርግ ያገኛታል። በዚያ ጊዜም #ትንሣኤዋን ሌሎቹ ሐዋርያት አይተው ለእርሱ የቀረበት መስሎት ተበሳጭቶ ፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይለዋል ማለትም በፊት የልጅሽን ትንሣኤ አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ ከማዘኑ የተነሣ ከደመናው ተወርውሮ ሊወድቅ ቃጣው በዚህ ጊዜ እመቤታችን ከእርሱ በቀር ሌሎች ሐዋርያት ትንሣኤዋን እንዳላዩ ነግራው ቅዱስ ቶማስን አፅናናችው ሄዶም ለወንድሞቹ ለሐዋያት የሆነውን ሁሉ እንዲነግራቸው አዘዘችው ለምልክት ምስክር ይሆነው ዘንድ የተገነዘችበትን ሰበኗን ሰጥታው በመላእክት ታጅባ እየተመሰገነች ወደ ሰማይ #ዐርጋለች።
ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስም ሐዋርያት ወደ አሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን እኮ ቀበርናት ብለው ነገሩት እርሱም ዐውቆ ምስጢሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንደምን ይሆናል አላቸው።አንተ እንጅ ቀድሞ የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠርክ አሁንም አታምንምን ብለው #በቅዱስ_ጴጥሮስ መሪነት ወደ እመቤታችን መካነ መቃብር ይዘውት ሄደው ሊያሳዩት መቃብር ቢከፍቱ የእመቤታችንን ሥጋ አስክሬን አጡት ደነገጡም በዚህ ጊዜም ቅዱስ ቶማስ አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ተነሥታ ዐርጋለች ብሎ የሆነውን ሁሉ ከተረከላቸው በኋላ ለማረጋገጫ ምልክት እንዲሆን የሰጠችውን ሰበኗን አሳየችው እነርሱም ሰበኗን ቆራርጠው ከተከፋፈሉት በኋላ ወደ አህጉረ ስብከታቸው ሄደዋል።
በዓመቱ #ትንሣኤሽን ቶማስ አይቶ እኛ እንዴት ይቅርብን ብለው ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ በሱባኤው መጨረሻም በነሐሴ በአሥራ ስድስተኛው ቀን (ነሐሴ 16) ቀን ጌታችን የለመኑትን ልመና ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር፣ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቅ (ረዳት) ቄስ፣ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ ዋና ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም ከአቆረባቸው በኋላ የእመቤታችንን ዕርገቷን ለማየት አብቅቷቸዋል። #የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል_ማርያም_ትንሳኤ_እና_ዕርገት በትንቢተ ነቢያት የተነገረ ነበር።(መዝ 131፥8፣መኃ 2፥10-15)።
Page 3
👉 @EOTC2921 👈
4 374
ሰባት አቀንስታት ጥጆች መወለዳቸው ወይም ሲወለዱ ማየታቸው ሰባት ሴት ልጆች ትወልዳላችሁ ሰባተኛይቱ ጨረቃን መውለዷከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለፀልኝም ጊዜ ይፍታው አላቸው፡፡በዚያም ወራት ቴክታ ፀነሰች ሴት ልጅ ወለደች ስሟንም ሄሜን ብለው አወጡላት በመቀጠልም የሚከተሉት በተከታታይ ተወለዱ።
ሄሜን ዴርዴን ወለደች ዴርዴም ቶናን ወለደች ቶናም ሲካርን ወለደች ሲካርም ሴትናን ወለደች ሴትናም ሄርሜላን ወለደች ሄርሜላም ማጣትን አግብታ ከአንስት ዓለም ተመርጣ የአምላክ አያት ለመሆን የበቃችውን ቅድስት ሐናን መስከረም 7 ቀን ወለደች ሐናም በሥርዓት አደገች ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግሥት የተወለደውን ክቡር ፃድቅ የሆነ ኢያቄም የሚባለውን ሰው አጋቧት።
#በዚህ_በተቀደሱ_አባቶችና_እናቶች_የዘር_ሐረግ_ውስጥ_አልፈው_የመጡት_ቅዱስ_ኢያቄም_እና_ቅድስት_ሃናም_እግዚአብሔር_ለድህነተ_ዓለም_የመረጣት_ቅድስት_ድንግል_ማርያምን_ወለዱ።በነገረ ማርያም እንደተፃፈ ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ሃና የፃድቃን መሰረቶች ቢሆኑም ከዚህ ዓለም ብዕል ግን ድሆች ነበሩ ምንም ድሆች ቢሆኑም ፍቅራቸው ወደር የሌለው አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ ተባብለው የሚኖሩ ደጋግ ባልና ሚስት ነበሩ መካንነታቸውን ሰበብ አድርገው ሕገ ጋብቻቸውን ያላሰደፉ ንፁሐን ነበሩ።
አምላካችን እግዚአብሔርም ንፅሕናቸውን ቅድስናቸውን ተመልክቶ ከብዙ ደጅ ፅናት (ፆምና ፀሎት) በኋላ ልጅ እንድትሆናቸው እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሰጣቸው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ነሐሴ 7 ቀን ተፀንሳለች በተፀነሰችም ጊዜ ብዙ ተአምራት ተደርጓል።የቅድስት ሃናን ማሕፀን እየዳሰሱ ዕውራን በርተዋል ጐባጦች ቀንተዋል ብዙ በሽተኞች ተፈውሰዋል ሞቶ የነበረ ሳሚናስ የሚባል የቅድስት ሃና የአጐት ልጅ የቅድስት ሃና ጥላዋ ቢያርፍበት ከሞት ተነስቶ የፀሐይ እናቱ የምትሆን ድንግል ማርያም በሃና ማህፀን መላእክት ክብሯን ሲናገሩ መስማቱን መሰከረ በዚህ ጊዜ አይሁድ ቀንተው ኢያቄምን እና ሃናን ሊገድሏቸው በጠላትነት ሲነሱ ቅዱስ ገብርኤል ሊባኖስ ወደ ሚባል ተራራ ወስዷቸው በዚያ እመቤታችን ድንግል ማርያም ግንቦት 1 ቀን ተወልዳለች።
ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ሃና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በንፅህና በቅድስና በቤታቸው 3ዓመት ካሳደጓት በኋላ ስዕለት ተስለው ስለነበር የወለዷት “የሰጠ ቢነሳ የለበት ወቀሳ”ብለው ለቤተ እግዚአብሔር የሚያስፈልገውን እጅ መንሻ ይዘው እመቤታችንን ለቤተ እግዚአብሔር እንድታገለግል ሊሰጧት ወደ ቤተ መቅደስ አመጧት ካህኑ ዘካርያስም መጥቅዕ (ደወል) መትቶ ህዝቡን ሰበሰባቸው ሕዝቡም ሲሰበሰቡ ቀድሞ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት ስዕለት ይመጣ የነበረው ወርቅ፣ብር፣በሬ፣በግ፣ ነበር አሁን ግን ሰው ነው።ይህቺን ብላቴና ተቀብለን ምን እናበላታለን ምን እናጠጣታለን የት እናኖራታለን ብሎ ህዝቡን ቢጠየቃቸው ።በዚህ ነገር ሲጨነቁ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤልን ኅብስት ሰማያዊ ፅዋዕ ሰማያዊ አስይዞ ወደ እነርሱ ላከው ከሊቀ ካህኑ ጀምሮ ሌሎችም እንደየ ማዕረጋቸው ይህንን እንቀበላለን ብለው ሲቀርቡ ለእነርሱ ስላልመጣ ከእነርሱ እራቀ በኋላ እመቤታችንን ከሰው ለይተው ለብቻዋ ባቆሟት ጊዜ ከሰማይ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ እመቤቴ ደጅ ባስጠናሁሽ ይቅር በይኝ ብሎ መግቧት አርጓል።የምግቧ ነገር ከተያዘ ከሰው ጋር ምን ያጋፋታል ቤተ መቅደስ ትኑር ብለው በታህሣስ 3 ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብተዋታል።በዚያም ህብስት ሰማያዊ ፅዋዕ ሰማያዊ እየተመገበች መላእክት እያረጓጓት ሐር እና ወርቅ እያስማማች እየፈተለች ቤተ መቅደሱን እያገለገለች 12 ዓመት ተቀምጣለች።አባ ሕርያቆስም ይህንን ሲያጎላ በቅዳሴ ማርያሙ እንዲህ ብሏል “ድንግል ሆይ ምድራዊ ህብስትን የተመገብሽ አይደለሽም ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ህብስትን እንጂ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን እንጅ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች እድፍ ጉድፍ የምታውቂ አይደለሽም በንፅህና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ።”እንዲል።
ከ12 ዓመት በኋላ አይሁድ በእመቤታችን ላይ በምቀኝነት ተነስተው በእናት በአባቷ ቤት 3 ዓመት በቤተ መቅደስ 12 ዓመት በድምሩ 15 ዓመት ሆናት ልማደ አንስት ታደርሳለች ቤተ መቅደሳችንን ታሳድፋለች ትውጣ አሉ ካህኑ ዘካርያስ ወደ እመቤታችን ገብቶ ነገራት እርስዋም ወደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ እንጂ እኔ ምን አውቃለሁ አለችው እርሱም ወደ እግዚአብሔር ሲያመለክት ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን የእስራኤል ሽማግሌዎች በትራቸውን ሰብስበህ ስትፀልይበት እደር እኔ ምልክት አሳይሃለሁ አለው እርሱም እንደ ታዘዘው ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን ሽማግሌዎች በትራቸውን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ ሲፀልይ አድሮ ሲነጋ ቢያወጣው የዮሴፍ ወልደ ዳዊት በትር ሰው ሳይተክላት ውሃ ሳያጠጣት ለምልማ አብባ አፍርታ ዮሴፍ ሆይ ድንግል ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ የሚል ቃል ተፅፎበት ተገኘ ዕጣም ቢጣጣሉ ለዮሴፍ ደርሳዋለች።ርግብም በእራሱ ላይ አርፋለች በእነዚህ ሦስት ምልክቶች ዮሴፍ አረጋዊ እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዲጠብቃት (እንዲያገለግላት) በመመረጡ እመቤታችን ለዮሴፍ ተሰጥታዋለች አባ ሕርያቆስም በቅዳውድንግል ሆይ ለዮሴፍ የታጨሽ ለመገናኘት አይደለም ንፁህ ሆኖ ሊጠብቅሽ ነው እንጂ እንዲል።ድንግል ማርያም ለዘመዷ ለዮሴፍ ንፁህ ሆኖ ይጠብቃት ዘንድ በአደራ ተሰጠሽ።ከርህራሄዋ ብዛት የተነሣም በቤተ ዮሴፍ ሳለች ዮሴፍን ትረዳው (ታገለግለው) ነበርና ውሃ ስትቀዳ የተጠማ ውሻ አግኝታ በወርቅ ጫማዋ ውሃ አጠጥታዋለች።
ከዚህ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መጋቢት 29 ቀን በዕለተ እሁድ በ3 ሰዓት በቤተ መቅደስ ሳለች በቅዱስ ገብርኤል አብሳሪነት አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንደምትወልደው በነገራት ጊዜ እርሷም በእምነት ይሁንልኝ ባለች ጊዜ የአምላክ እናት ለመሆን ተመርጣለች((ሉቃ 1፥26-38 ጌታን በ9 ወር ከ5 ቀን በኋላ ታህሣስ 29 ቀን ምጥ ሳይሰማት የደም መፍሰስ አራስነት ሳያገኛት በቤተልሔም ግርግም በድንግልና ወልዳዋለች ከወለደችውም በኋላ በዘለዓለማዊ ድንግልና ፀንታ ኖራለች። (ኢሳ 7፥14፣ሉቃ 2፥1-20)።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጌታ ጋር 33 ዓመት ከ3-ወር አብራ አልተለየችም ጌታችን በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ሳለ ከእግረ መስቀሉ ሥር አብራ ነበረች።ጌታም ለሚወደው ደቀ መዝሙር ለቅዱስ ዮሐንስ አደራ ሰጣት ቅዱስ ዮሐንስም ወደ ቤቱ ወስዶ አገለገላት።(ዮሐ 19፥26)። እመቤታችንም በዮሐንስ ቤት ለ15 ዓመት ተቀምጣለች በድምሩ 64 ዓመት ሲሆናት ጥር 21 ቀን በ49 ዓ.ም ገደማ ከዚህ ዓለም ድካም አርፋለች።
Page 2
👉 @EOTC2921 👈
4 374
⛪️ምዕራፍ 1⛪️
#ነገረ_ማርያም_ማለት_ምን_ማለት_ነው?
🌾🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾🌾
✍ነገረ ማርያም ከሁለት ቃላት የተገኘ /የተሰናሰለ/ ሲሆን እንደ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ስለ እመቤታችን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ንፅህና፣ቅድስና፣ዘለዓለማዊ ድንግልና ወ.ዘ.ተ የምንማርበት እንዲሁም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሰው ልጆች መዳን ውስጥ( በነገረ ድህነት) ያላትን ሱታፌ (አስተዋጽኦ) የምንረዳበት የትምህርት ክፍል ነው።
#ነገረ_ማርያምን_መማር_ለምን_አስፈለገ?
#ሀ. #ክርስትናን_በአግባቡ_ለመረዳት፦ ክርስትና አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር በሥጋ ማርያም ተገልጦ የመሰረታት ናት ቅድመ ዓለም ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ሆኖ ዓለምን የፈጠረ እና የሚገዛ እግዚአብሔር ቃል (ወልድ) ድህረ ዓለም የጠፋውን አዳምን ፍለጋ በትሕትና እራሱን ዝቅ አድርጎ በሰው ባህርይ መገለጡን ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው መሆኑን የምናምንበት የምንረዳበት ትምህርት ነው።በዚህ በነገረ ድህነት የክርስትና ትምህርት ሰፊውን ድርሻ ይዛ የምትገኘው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓለም ሁሉ ለዳነበት ምስጢር መፈ ጸሚያ መቅደስ ለመለኮት ማደሪያ እነድትሆን ተመርጣለች።በሰዎች ላይ ሰልጥኖ የነበረው የጨለማው ገዢ ዲያብሎስ ድል የተነሳበት አዳም ከጨለማ ግዞት ነፃ የወጣበት አማናዊ ብርሃን ፀሐየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘባት ምስራቅ የድህነታችን መሰረት የመዳናችን ምክንያት በመሆኗ ነገረ ማርያምን ትምህርት መማር አስፈልጓል።
#ለ. #ስለ_እመቤታችን_ፀጋ_እና_ክብር_ለማወቅ፦እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአምላካችን ከልዑል እግዚአብሔር በተሰጣት ፀጋ ከነገደ መላእክት ከደቂቀ አዳም በክብር የሚመስላት በፀጋ የሚተካከላት የለም ይኸውም ከፍጡራን መካከል ተለይታ የአምላክ እናት ለመሆን የተመረጠች አምላክን በህቱም ድንግልና ፀንሳ በህቱም ድንግልና የወለደች ሁሉን የሚመግበውን አምላክ ጡቶቿን አጥብታ ያሳደገች በጀርባዋ ያዘለች ስለ ልጇ የተሰደደች በማለት ማስተማር ዘመኑ ከጌታችን ጋር የነበረች እስከ እግረ መስቀል ያልተለየች በመሆኗ ስለ እርሷ ስለተሰጣትም ፀጋ እና ክብር ለማወቅ አውቆም ለማክበር ነገረ ማርያም ትምህርት መማር ያስፈልጋል።
#ሐ.#በሕይወታችን_ለመጠቀም፦እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጣት የከበረ ቃል ኪዳን አለ ቃልኪዳኑም “ስምሽን የጠራ ዝክርሽን የዘከረ በቃል ኪዳንሽ የታመነውን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ አድነዋለሁ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እሰጠዋለሁ” የሚል ነው።ይህ ቃል ኪዳን በህይወታችን እንዲሰራ በነፍስም በሥጋም ከኃጢአት በስተቀር የምንፈልገውና የሚገባን (የሚጠቅመን) ነገር እንዲፈፀምልን ይህንን የምናውቅበትን እና የመንረዳበትን ትምህርት ነገረ ማርያምን መማር ያስፈልጋል።
#የነገረ_ማርያም_ትምህርት_ምንጮች
የነገረ ማርያም ትምህርት ምንጭ አለው የነገረ ማርያም ትምህርት ልብ ወለድ ፈጠራ ሳይሆን ምንጭ አለው ምንጩም የመንፈሳውያን መፃህፍትና ትምህርት መሰረታቸው የሆነ መፅሐፍ ቅዱስ ነው። ይኸውም በሁለት የተከፈለ ነው “ብሉይ ኪዳን እና ሐዲስ ኪዳን” በዚሁ በብሉይ ኪዳን እና በሐዲስ ኪዳን የእመቤታችን ነገር በዘመነ ብሉይ በአበው ቀደምት ምሳሌ በነቢያት ትንቢት የተገለጠ በዘመነ ሐዲስ በሐዋርያት ስብከት ፍፃሜውን አግኝቶ የተሰበከ በመሆኑ ቅዱስ መፅሐፍ የነገረ ማርያም ምንጭ ነው።
ከመፅሐፍ ቅዱስ ቀጥሎ የነቢያትን የሐዋርያትን አሰረ ፍኖት ተከትለው ሊቃውንት በድርሰታቸው የእመቤታችንን ነገር ገልጠው ፅፈዋል በተለይ በጊዜው ከተነሱ መናፍቃን ለክህደት ትምህርታቸው መልስ ለመስጠት ባዘጋጁት በሃይማኖተ አበው የነገረ ማርያም ትምሀርት የተገለጠ በመሆኑ ለነገረ ማያርም ትምህርት ምንጭ ሆኗል።
ከዚህ በተጨማሪ ለነገረ ማርያም ትምህርት ምንጭ የሚሆኑ ተአምረ ማርያም፣የቅዱስ ያሬድ የድጓ ድርሰት፣የአባ ጊዮርጊስ ድርሰቶች ማለትም፦እነ አርጋኖን ዘእግዝእትነ ማርያም፣እነ ሆሕተ ብርሃን፣እነ እንዘራ ስብሐት፣መዓዛ ቅዳሴ የአባ ሕርያቆስ ቅዳ የቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴ ወ.ዘ.ተ።ያሉ ድርሰቶች ናቸው።እነዚህን ድርሰቶች ያስደረሳቸው እና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ነገር የገለፀላቸው ያደረባቸው እና የመረጣቸው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው።መንፈስ ቅዱስ ያላደረበት የእመቤታችን ክብር ገልፆ መናገር አይችልምና።(ሉቃ 1፥39)።በኤልሳቤጥ መንፈስ ቅዱስ መላባት ድምጿን ከፍ አድርጋ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው………።አለች” እንዲል።
“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር”። (ኢሳ 1፥9)።ይህ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ የተናገረው ቃል ምስጢር አዘል ሲሆን የተነገረውም ለወላዲተ አምላክ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ነው።ነቢዩ በመንፈስ ቅዱስ ተቀኝቶ እንደተናገረ ስለ አዳም ልጆች መዳን ያስቀራት ንፅሕት ዘር ማለትም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።በሌላም ሥፍራ ቅዱስ ዳዊት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷ ነገር ሲገልፅ እንዲህ አለ ።(መዝ 86፥1)።“መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱስን (መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው)።”ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት መሰረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው ብሎ ከአዳም ጀምሮ እነ አብርሃምን እነ ዳዊትን እነ ሰሎሞንን ወ.ዘ.ተ እስከ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሃና ያሉትን በምስጢር ማንሳቱ ነው።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷን ታሪክ ከዚህ እንደሚከተለው እንመለከታለን።በኢየሩሳሌም አካባቢ በቅዱስ ጋብቻ ተወስነው እግዚአብሔርን እያመለኩና እያመሰገኑ የሚኖሩ ጰጥርቃና ቴክታ የሚባሉ ደጋግ ሰዎች ነበሩ።ይሁን እንጂ ልጅ የሌላቸው መካኖች በመሆናቸው ያፈሩትን ሀብት የሚወርስ ልጅ ባለመውለዳቸው ያዝኑ ይተክዙ ነበር።
ከዕለታት በአንዱ ቀን ስለ ሀብታቸው ብዛት በሰፊው ከተወያዩ በኋላ ጰጥርቃ ተስፋ በመቁረጥ ስሚ “እህቴ ሆይ ይህ ሁሉ የሰበሰብነው ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን የሚወርሰን ልጅ የለንም ምክንያቱም አንቺ መካን ነሽ እኔ ደግሞ ከአንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም።አላት ቴክታም “ጌታዬ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደ እኔው ትቀራለህን ከሌላ ውለድ እንጅ?” ብላ ብታሰናብተው እርሱም “እንዲህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቡናዬ እንደማላስበው አምላከ እስራኤል ያውቃል”አላት።
ከዚህ ሁሉ ውይይት በኋላ ቴክታ ለጰጥርቃ እንዲህ አለችው እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በሕልሜ ነጭ ጥጃ ከማህፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድና እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ ሲዋለዱ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃ ፀሐይን ስትወልድ አየሁ አለችው በዚህ ተደንቀውና እግዚአብሔርን አመስግነው ወደ ሕልም ፈች ዘንድ ሂደው የሆነውን ሁሉ ነገሩት ያም ሕልም ፈች እግዚአብሔር በምሕረቱ አይቷችኋል በሣህሉ መግቧችኋል ብሎ ሕልማቸውን እንዲህ ሲል ፈታላቸው።
Page 1
4 374
#ዕረፍቱ_ለአባ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ
🌾🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾🌾
👉አባ ሳሙኤል አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው አመተ-ማርያም ይባላሉ፡፡ በ12 ዓመታቸው ሹም በተባለው ባሕር
ገብተው ሲጸልዩ ባሕሩ በብርሃን ተከቦ ይታይ ነበር ፡፡ ከባሕሩም ወጥተው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው እያለቀሱና
እያዘኑ ሲጸልዩ ካህናቱ "ይህ ህፃን የእኛ ኃጢአት እየታየው ? ወይስ ምን ኃጢአት ኖሮበት ነው እንዲህ የሚያዝነው እና
የሚያለቅሰው ?እያሉ ያደንቁና ይገረሙ ነበር፡፡
👉አባ ሳሙኤል እናታቸው ቤተሰቧንና ቤት ንብረቷን ትታ ከመነኮሰች በኃላ እርሳቸውም ካልመነኮስኩ በማለት አባታቸውን ቢለምኑ እምቢ ስላለቸው በራሳቸው ፈቃድ ከአንድ ሽማግሌ ጋር
ወደ አባ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ደብረ በንኮል ገብተው መነኮሱ፡፡
በዚያም ነፍሳቸውን "ነፍሴ ሆይ ! እነሆ ለክርስቶስ ታጨሽ፣ የቅዱሳንን ቀንበር እነሆ ተሸከምሽ የመላእክትን ንፅህና ትጠብቂ ዘንድ ዛሬ በእግዚአብሔርና በቅዱሳኑ ሁሉ ፊት ቃልኪዳን ገባሽ
፣ ቃልኪዳንሽን ብትጠብቂ መላእክት ይደሰቱብሻል ፣ ባትጠብቂ ግን አጋንንትን ይዘባበቱብሻል . . . .እያሉ ብዙ መከራን
በራሳቸው ላይ በማብዛት 7 ዓመት በዚያች ገዳም ኖሩ፡፡
እህልም አይቀምሱም ነበር ይልቁንም የሚሰጧቸውን እንጀራ ለሕፃናት እና ለውሾች እየሰጡ አሠር ይመገቡ ነበር፡፡
ዳግመኛም በሌላ ጊዜ ቅጠልን እየቀቀሉ እስከ 5 ቀን ከድነው ያስቀምጡታል እስከሚተላም ድረስ ይጠብቁትና ያን ይመገባሉ፡፡ አባታቸውም ልጁን አባ ሳሙኤልን ተከትለው ወደ እርሱ
መጥተው በአባ አድኃኒ እጅ መነኮሱ፡፡
👉✞አባታችን አባ ሳሙኤል በሕይወተ ስጋ ሳሉ እጅግ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተዓምራትን አድርገዋል ፡፡
👉እንደ ሙሴ ባሕርን የከፈሉበት ጊዜ አለ፣ በልዑል ዙፋን ፊት እየቀረቡ
ከቅዱሳን መላእክት ጋር የሚያመሰግኑበት ጊዜ አለ፣ ከ24ቱ
ካህናተ ሰማይ ጋር ሆነው የሚያጥኑበት ጊዜ አለ ፣ በሰማያዊት ኢየሩሳሌምም ሆነው ከነ ቅዱስ ጴጥሮስ እና ከሁሉ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ጋር በአንድ ላይ ማዕድ የሚቀርቡበት ጊዜ አለ
፣ በእጃቸው የያዟቸው መፃህፍቶች ምንም ሳይርሱ ትልቅ ወንዝን
በውስጡ እያቋረጠ የሚሻገርበት ጊዜ አለ ፣ እመቤታችንንም ሲያመሰግናት ከምድር ወደ ላይ 1 ክንድ ያህል ከፍ የሚሉበት ጊዜ አለ ፣ በቤትም ውስጥ ሆኖ ምስጋናዋን ሲጀምሩ የቤቱ
መሰረት እየተናወጠ ዝናብ እንደያዘ ደመና ቤቱ ከምድር ከፍ ብሎ የሚቆምበት ጊዜ አለ ፣ መንፈስ ቅዱስም በብርሃን ክንፍ
እንደወሰዳቸው ወደ ተለያዩ ገዳማት ያደርሳቸውና ስጋ ወደሙን እንዲቀበሉ ያደርጋቸው ነበር፡፡ መልአኩ ቅዱስ
ሚካኤልም የሁልጊዜ ጠባቂያቸው ነውና በሁሉም ነገር ይራዳቸውና እንደ ጓደኛም ያማክራቸው ነበር፡፡
👉✞ አባ ሳሙኤልን የዱር አራዊትም ሁሉ ይገዛላቸው ነበር፡፡ ታላቅ የሆነ ዘንዶ ፣ ነብር ፣ ጅብ ፣ ቶራህ ፣ ዝሆን ፣ አንበሳና
ሌሎችም የዱር አራዊት ሁሉ እየመጡ እግራቸውን እየላሷቸው ወደ ቦታቸው ይመለሱ ነበር፡፡ ከገዳም ወጥተው መሄድ በፈለጉ ጊዜ አንበሶችን እንደ ፈረስና በቅሎ ይጋልቧቸዋል
መፃህፍቶችንም ይጭኑባቸዋል፡፡
👉✞ ዋልድባ የተመሰረተው በቀደምት ጥንታውያን አበው ቢሆንም
አባ ሳሙኤል ሲገቡበት ምድረ በዳ ሆኖ ጠፍቶ ቋያ በቅሎበት የወባ ትንኞች መፈልፈያ ሆኖ ነበር፡፡ አባታችን ግን የተበታተኑትን መነኮሳት ሰብስበው ዋልድባን እንደገና አደራጅተውና አድሰው
አቀኑት፡፡ የተባህትዎ ኑሮንም አጠናከሩበትና ገዳሙን የመናንያን
አበው መሰብሰቢያ አደረጉት፡፡
👉✞ አባታችን ዋልድባን እንደ መሶብ አንስተው አስባርከዋታል፡፡
👉✞ አባ ሳሙኤል ጊዜያቸው ደርሶ ከማረፋቸው በፊት ቅዱስ ሚካኤል ነሐሴ 16 ቀን ወደ ገነት ነጥቆ ወስዶ ከዕረፍታቸው በኃላ ከልጆቻቸው ጋር የሚኖሩበትን ስፍራ አሳይቷቸዋል፡፡በገነት
ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ ካሳያቸው በኃላ በእግዚአብሔርም ዙፋን ፊት
ቀርበው ምስጋና ቃልኪዳንን ተቀብለው ወደ በዓታቸው ተመልሰው ታህሳስ 12 ቀን በታላቅ ክብር አርፈው ነፍሳቸውን
ጌታችን በእጆቹ ተቀብሏታል፡፡
👉✞ የአቡነ ሳሙኤል በዓለ ዕረፍት በሚከተሉት ቦታዎች በዋነኛነት ይከበራል፡፡
#1. በሁሉም የዋልድባ ገዳም ክፍልች (በውስጡ ባሉት 3ቱ ገዳማት፣ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት፣ ጸሎት/ስዕል/ ቤቶችን፣ የአትክልት ቦታዎችንና ሞፈር ቤቶች)፤ እነዚህም፡-
#1.1. ዋልድባ አብረንታንት ገዳም (የአብረንታንት መድኀኔዓለም ገዳም)
#1.2. ዋልድባ ዳልሽህ ገዳም
#1.3. ዋልድባ ሰቋር ገዳም (የኪዳነምሕረት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስና የመድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን ያካተተ)
#1.4. አቴና (መቃብረ ሳሙኤል)፤ ሌሊቱንና ቀኑን ሙሉ ገድላቸው እየተነበበ
#1.5. አባ ናፃ የአቡነ ተሥፋ ሐዋርያት ገዳም
#1.6. ደንደሮቃ ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ
#1.7. ማይገባ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም
#1.8. ማይ ሃርገጽ ቅ/ጊርጊስ ቤ.ክ
#1.9. ዕጣኖ ማርያም ቤተክርስቲያን
#1.10. ማይ ለበጣና ሌሎችም የስዕል ቤቶች፣ የአትክልት ቦታዎች
#2. በተወለዱበት በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አኵሱም ጽዮን ማርያም፤
#3. ምንኵስናን በተቀበሉበት በደብረ በንኰል አቡነ መድኀኒነ አግዚእ ገዳም
#4. በቆብ ወንድማቸው በአባ ያሳይ መንዳባ ገዳም
#5. በቆብ አያታቸው በአቡነ ተክለሃይማኖት ደብረ ሊባኖስ ገዳም
በውዳሴና በቅዳሴ (ከጥንት ጀምሮ)
#6. አቡነ ሳሙኤል በመሠረቷቸው ገዳማት
#6.1 በደብረ ዐባይቡነ ሳሙኤል ገዳም /ሽሬ አጠገብ/ ፣ እጅግ
ደማቅ በኾነ ኹኔታ
#6.2 በአብጠራ (አብጠራህ) አቡነ ሳሙኤል ገዳም /ደባርቅ/፣
#6.3 ደብረ ገነት አቡነ ሳሙኤል ገዳም /አዲስ አበባ አቃቂ አጠገብ/) በታላቅ ድምቀት
#6.4 ጎንደር አዘዞ አባ ሳሙኤል
በተጨማሪም በስማቸው በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ይከበራል፤
ለአብነትም፤
#7. በአዲስ አበባ ወረገኑ ቅዱስ ሚካኤል እና ጻድቁ አቡነ
ሳሙኤል
#8. በአዲስ አበባ ሲምሲ ሚካኤል (በድርብነት)
#9. በአዲስ አበባ ሳሙኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም (ጋራ
መድኀኔዓለም ሳይደርሱ)
#10. አዲስ አበባ አቡነ ሳሙኤል፤ ሳሪስ አቦ አጠገብ
ባርከኒ አባ እንሣእ በረከተከ በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተክርስቲያን አባ ሳሙኤል/፫/ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ፡፡
🙏የጻድቁ አባ ሳሙኤል ረድኤት በረከት ምልጃና ጸሎት ከሁላችን ሕዝበ ክርስቲያን ከሀገራችን ከኢትዮጵያ ጋር ይሁን አሜን!!!🙏
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር
4 374
#ንስሐ_ምን_ማለት_ነው?
🌾🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾🌾
👉ንስሐ ማለት አንድ ሰው በሠራው ጥፋት፣ ባደረገው ስህተት፣ በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑና መቆርቆሩ፣ መፀፀቱ፣ ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው። በአጭሩ ንስሐ ማለት ትርጉሙ ይህ ሲሆን፤ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስገነዝበን ቀጥሎ የተጠቀሱትን ፍችዎች ያጠቃለለ ሆኖ እናገኘዋለን።
👉ንስሐ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው። ሚልኪ፡3፥7
👉ንስሐ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ነው። 2ኛ ቆሮ፡6፥19
👉ንስሐ ከኃጢአት እንቅልፍ መንቃት ነው። ሮሜ፡13፥11
👉ንስሐ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ነው። ኤፌ፡5፥14
👉ንስሐ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ እግዚአብሔርን የሚያስወድድ ከንጹህ ልብ የሚመነጭ ጸጋ ነው። ሕዝቅ፡36፥25-27
👉ንስሐ ከኃጢአትና ከዲያቢሎስ ባርነት ነጻ መውጣት ነው። ዮሐ፡8፥34-36
👉ንስሐ ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ስለ ቅድስና ብሎ ኃጢአትን መተው ነው።
ምሳ፡28፥13
👉ንስሐ ስለ አለፈው ስህተት አብዝቶ ማልቀስ፤ ያለፈውን የኃጢአት ኑሮ
ማውገዝና መኮነን ነው። ኢዩኤል፡2፥12
👉ንስሐ ፍጹም የሆነ የሕይወት ለውጥ እንጂ ጊዜያዊ ስሜት አይደለም፤ ሮሜ፡12፥2
👉ንስሐ ኃጢአትን ሲሠሩ ከመኖር ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር መኖርን መሻት ነው።መዝ፡73፥28
👉ንስሐ የአዕምሮ መታደስ ነው። ሮሜ፡12፥2
👉ንስሐ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የሚያስችል ወደ መንግሥተ
እግዚአብሔር የሚያስገባ ቁልፍ ነው። ማቴ፡25፥1-13
👉ንስሐ በቀራንዮ መስቀል ላይ እኛን ለማዳንና ከኃጢአት ባርነት ነጻ ለማውጣት የፈሰሰልንን የክርስቶስን ደም እንድናስብ የሚያደርግ መንፈሳዊ ሃብት ነው።
👉ንስሐ ከኃጢአት የሚያነጻ ሱራፌል ከመንበረ ሥላሴ የወሰዱት የእሳት ፍም
ነው። ኢሳ፡6፥4
👉ንስሐ ከሚመጣው የመጨረሻ መከራና ሃዘን መዳኛ ወይም ማምለጫ መንገድ ነው። ዮና፡3፥10
👉ንስሐ እግዚአብሔር የሰውን ኃጢአት ይቅር የሚልበትና ከኃጢአት ውጤት
የሚያድንበት መሳርያ ነው።
👉ንስሐ ከሰዎች ጋር ለመታረቅ የተዘረጋ የእግዚአብሔር እጅ ነው። መዝ፡50/51
👉ንስሐ እግዚአብሔር ወደ ሰው የሚጣራውን ጥሪ ሰምቶ ወደ እርሱ መመለስ ነው። ዮሐ፡7፥51 ኤፌ፡4፥30
👉ንስሐ ስለ አለፈው ኃጢአት ከመፀፀት የተነሳ የተሰበረ ልብ ነው። መዝ፡50/51፥17
👉ንስሐ ሰዎች ስለ ኃጢአታቸው ተፀፅተው ከእግዚአብሔር ጋር እንዳይታረቁ በብርቱ በሚጥረው ሰይጣን ላይ የተገኘ ድል ነው። መዝ፡123/124፥6-7
🙏አምላከ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ሁላችንንም ለንስሐ ሞት ያብቃን አሜን🙏
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
#ተአምር_አድራጊዋ_ቃል_ኪዳኗ_ከድንገተኛ_ሞት_የሚጠብቀው_ቅድስት_በርባራ_ድንቅ_ታሪኳና_ቃልኪዳኗ_በቀደምት_ኢትዮጵያውያን_የቀረበላት_ውዳሴ
🌾🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾🌾
ታህሳሥ ፰ ይከበራል
❖ ቃል ኪዳኗም ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው ቅድስት በርባራ
በከሓዲው መክስምያኖስ ዘመነ መንግሥት መስፍን የነበረው የዲዮስቆሮስ ልጅ
ናት፤ ለርሷም ማረፊያ ታላቅ ሕንፃ አሠርቶ በመታጠቢያ ክፍሏ ላይ ደግሞ ኹለት
መስኮቶች እንዲሠሩላት ዐናጺዎችን አዘዘ፤ ርሷ ግን የክርስቶስን የባሕርይ
አምላክነት በማመኗና በመጠመቋ ሦስተኛ መስኮትን እንዲጨምሩ ዳግመኛም
አዳኝ የኾውን የመስቀሉን ምልክት በውሃ መታጠቢያው ላይ እንዲሠሩ
ሐናጺዎችን አዘዘቻቸው፡፡
❖ አባቷም ወደዚኽ ሕንጻ በገባ ጊዜ ልጁ ያሠራችውን አይቶ ዐናጺዎችን
ሲጠይቃቸው፤ ይኽነን እንዲሠሩ ያዘዘቻቸው ልጁ መኾኗን ነገሩትን ርሱም
“ለምን እንደዚኽ አደረግሽ” ብሎ ጠየቃት፡፡ “ወትቤሎ አእምር ወለቡ ኦ አቡየ
እስመ በሥሉስ ቅዱስ ይትፌጸም ኲሉ ግብር በእንተዝ አግበርኩ ሣልሲተ
መስኮተ፤ ወዘንተኒ መስቀለ በአምሳለ ስቅለቱ ለመድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ”
ይላል ርሷም “አባቴ ሆይ አስተውል፤ ልዩ ሦስት በኾነ በሥላሴ ስም ሥራ ኹሉ
ይፈጸማልና ስለዚኽ ሦስተኛ መስኮት አሠራኊ፤ ይኽም መስቀል ዓለሙ ኹሉ
በርሱ በዳነበት በመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል አምሳል ነው አንተም
አባቴ ሆይ ከስሕተትኽ ተመልሰኽ የፈጠረኽን አምላክ አምልከው” በማለት
ተናገረችው፡፡
❖ አባቷም ከርሷ ይኽነን በሰማ ጊዜ በንዴት ሰይፉን መዝዞ በኋላዋ
ሮጠ፤ ያን ጊዜ ሸሽታ በዐለት ውስጥ ገብታ ለጊዜው ብትሸሸግም በኋላ ግን ወደ
አባቷ ተመለሰች፤ ርሱም እንድትሠቃይ ለሌላ መኰንን አሳልፎ ሰጣት፤ ርሱም
እየገረፈ በጊዜው አሉ በተባሉ በታላላቅ ሥቃይን ቢያሠቃያትም የባሕርይ አምላክ
ክርስቶስን ግን አልካደችም፤ ከዚያም ብቻዋን ወደ ወህኒ ተጣለች፤ በዚያም ኾና
“ጌታዬ አምላኬ ሆይ አትተወኝ” ብላ ጸለየች፤ በእኩለ ሌሊትም የእስር ቤቱን
ደማቅ ብርሃን መላው፤ “ከአንቺ ጋር ነኝና አትፍሪ” የሚለውን የአምላክን ድምፅ
ሰማች፤ ከዚያም ጌታችን ቊስሎቿን ኹሉ ፈወሰላት፡፡
❖ በነጋታው ቅድስት በርባራን በማርቲያኑስ ፊት አቆሟት፤ ኹሉም ሰዎች
ሙሉ በሙሉ እንደዳነችና ፊቷም እንደ ፀሓይ ጨረር ሲያንጸባርቅ ተመለከቱ፤
መኰንኑም “አማልክቶቻችን ስለፈወሱሽ የምስጋና መሥዋዕትን ሠዊ” አላት፤
ቅድስት በርባራም ለአገረ ገዢው “በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው የዳንኩት”
አለችው፡፡ ማርቲያኑስም በቊጣ ኾኖ በአስከፊ ኹኔታ ቅድስት በርባራ
እንድትሠቃይ አዘዘ፤ በዙሩያዋ ቆመው ይመለከቱ የነበሩ ሕዝቦች ርሷን
ለመከላከል ምንም ቃል አልወጣቸውም፡፡
❖ በዚያም ዮልያና የምትባል ሴት ነበረችና ቅድስት በርባራን አይታ
የምታጽናናትና የምታረጋጋት ኾነች፤ ክብር ይግባውና ጌታችን ለቅድስት በርባራ
ተገልጾ አረጋጋት ቃል ኪዳንም ሰጣት፡፡ በመጨረሻም ጨካኙ መኰንን ምንም
ዐይነት ሥቃይ ቢደርስባቸው እነዚኽ ቅዱሳት አንስት በክርስቶስ ላይ ያላቸውን
እምነት እንደማይለውጡ ባየ ጊዜ አንገታቸው እንዲቈረጥ አዘዘ።
❖ ከወታደሮቹ መኻከል አንዱ አንገታቸው ለመቊረጥ ሰይፉን መዘዘ፤
በአባቷ ወደተዘጋጀው ወደመግደያው ስፍራ ይዟቸው ኼደ፤ ያን ጊዜ ቅድስት
በርባራ እንዲኽ ብላ ጸለየች “ዘላለማዊ እግዚአብሔር ሆይ ከእኔ ሞት በኋላ
እኔንና መከራዬን ለሚያስቡ ኹሉ ሥጦታኽን ስጣቸው፤ ድንገተኛ ሕመምና ብርቱ
(አስጨናቂ) ሞትን በእነርሱ ላይ ፈጽሞ አታምጣባቸው” አለች፡፡
❖ ከዚያም የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ መሻቷን ኹሉ
እንደሚፈጽምላት ቃል ኪዳን ሲገባላት በሰጣት ቃል ኪዳን የሚታመኑ ኹሉ
ድንገተኛ ሞት እንደማያገኛቸው ቃል ኪዳን ገባላት።
❖ በመጨረሻም አባቷ የርሷንና የባልንጀራዋ የዮልያና አንገታቸው
እንዲቈረጥ አዘዘና ታኅሣሥ 8 አንገታቸው ተቈርጦ የሰማዕትነት አክሊል
ሲቀዳጁ፤ ቅድስት ዮልያናንም በኹለት ጡቶቿ በኩላብ ሰቅለው ሰይፈዋታል፡፡
በዚያን ጊዜ ከሰማይ መብረቅ ወርዶ አባቷንና ጓደኛው የኾነ መኰንን
መርትያኖስን አቃጠላቸው፤ ከዚኽ የተነሣ በዓለም ባለው ሥዕሏ ላይ የመብረቅ
ብልጭታ ይሣላል፡፡
❖ ያም በመታጠቢያ ቤት ውስጥ በመስቀል ምልክት ያሠራቸው
መታጠቢያ ለታመመ ኹሉ ከርሱ በታጠበ ጊዜ የሚያድን ኾነ፤ ከዚኽም በኋላ
የሰማዕታቱን ሥጋቸውን ወስደው ከከተማ ውጪ ባለች ቤተ ክርስቲያን ስሟ
ገላልያ በሚባል ቦታ አኖሯቸው፤ ይኽ ሥጋቸውም በቅዱሳን ሰማዕታት በአቡቂርና
በዮሐንስ በምስር አገር ባለ ቤተ ክርስቲያን ተቀመጠ፡፡
❖ ይኽነን ተጋድሎዋን ለማዘከር በመላው ዓለም በሚሣለው ሥዕሏ
ላይ ሦስት መስኮት ያለው ሰገነት፣ ዘንባባ፣ ጽዋ፣ መብረቅ፣ የሰማዕትነት አክሊል
ይዛ ይታያል፡፡ በዓለም ላይ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ የታነጹላት ሲኾን
በሩሲያ ብዙዎች ቤተ ክርስቲያናት በስሟ ሲሠየሙላት አንደኛው በሞስኮ ከቅዱስ
ባስልዮስ ካቴድራል አጠገብ ይገኛል::
❖ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ቅድስት በርባራን አመስግነው በቃኝ
አይሉም ነበር፤ ለምሳሌ ያኽል ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እና ቅዱስ አርከ
ሥሉስ እንዴት እንዳመሰገኗት ብናይ፤ አባ ጊዮርጊስ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ
ላይ፡-
“ሰላም ለበርባራ ወዮልያና በፍኖተ ስምዕ እለ ቆማ፤
በድሮን እለ ፈጸማ
እለ ተጋደላ ከመ ሐራ
አርዑተ መስቀሉ ለክርስቶስ እለ ጾራ
መርዓዊሆን እስከ ረከባ
ድንግልናሆን እለ ዓቀባ”፡፡
(ሙሽራቸው ክርስቶስን እስኪያገኙ ድረስ ድንግልናቸውን የጠበቁ፤ የክርስቶስ
መከራ መስቀሉን የተሸከሙ፤ እንደ ጭፍሮች የተጋደሉ፤ ሩጫቸውንም የፈጸሙ፤
በምስክርነት ጐዳና የቆሙ ለኾኑ ለበርባራና ለዮልያና ሰላምታ ይገባል) በማለት
አወድሷቸዋል፡፡
ኢትዮጵያዊው ሊቅ አርከ ሥሉስም ይኽነን በዐርኬው ላይ፡-
“ሰላም ለበርባራ እንተ አግሀደት ሃይማኖታ
እንዘ ታርኢ ሥላሴ በመስኮተ ቤታ
ኢያፍርሃ መጥባሕት ወሞሠርተ ሐጺን ኢያሕመመታ
ወሰላም ካዕበ ለዮልያና ካልዕታ
እንተ ሰቀልዋ በክልኤ አጥባታ”
(በቤቷ መስኮት የሥላሴን ምሳሌ እያሳየች ሃይማኖቷን የገለጠች ለኾነች
ለበርባራ ሰላምታ ይገባል፤ ሰይፍም አላስፈራትም የብረት መጋዝም
አላሳመመቻትም፤ ዳግመኛም በኹለት ጡቶቿ የሰቀሏት የርሷ ኹለተኛ ለምትኾን
ለዮልያናም ሰላምታ ይገባል) በማለት የተቀበሉትን ጽኑ መከራ ጽፏል፡፡
❖ ቅድስት በርበራ እመቤታችንን ለምና የገድሏን መጽሐፍ በሰረቁት
ላይ ያደረገችውን የመስከረም 25 ተአምሯን ደግሞ፦
"ሰላም ለበርባራ ወለዮልያና አምሳላ
በዛቲ ዕለት ዘአስተርአየት ኀይላ
በክልኤ ዕደው ዘሰረቁ መጽሐፈ ገድላ
ፈደየቶ ለአሐዱ እንባዜ እምኀበ ማርያም ስኢላ
ወለዐይነ ቢጹ ካልዕ አጽለመት ጸዳላ" ይለዋል የመስከረም 25 ስንክሳር አርኬ
❖ በእጅጉ የሚገርመው ከጥንት ዠምሮ በየክፍላተ ዘመናቱ እስከ ዛሬ
ድረስ በበርካታ የዓለም ክፍሎች በቅድስት በርባራ ከሚፈነዱ የጦር
መሣሪያዎች፤ ከመብረቅ አደጋና ከድንገተኛ ሞት በቃል ኪዳኗ እንደምትጠብቅ
ሲታመን፤ በጣሊያን የባሕር ኀይላችን ጠባቂ (the patron of the Italian
Navy.) ይሏታል።
❖ በቃል ኪዷና በእጅጉ ከመታመን የተነሣ በጊዜያችን ያሉ በርካቶች
ኀያላን ሀገራት ብሪታኒያ (Royal Artillery, RAF Armoures, Royal
Engineers) በካናዳ (Explosiv Ordance Technicaians) በአውስራሊያ
(RNZAF Armourers) በኒውዝላንድ፤ በስፔን፣ በአሜሪካ፣ በግሪክ የቅድስት
በርባራን በዓል በዐየር ኀይላቸው፣ በጦር ካምፓቸው፣ በባሕር ኀይላቸው
እ
4 374
#መጽሐፍ_ቅዱስ_ስለ_ይቅርታ_ምን_ይላል
🌾🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾🌾
👉 ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን
ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። - [የማርቆስ
ወንጌል 11:25]
===========
👉 አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም
ትባላላችሁ። - [የሉቃስ ወንጌል 6:37]
==========
👉 እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ
ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ። - [ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:32]
============
👉 እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው
ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ። ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ
አድርጉ። - [ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:13]
=============
👉 ፤ አትበቀልም፥ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፥ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ
ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። - [ኦሪት ዘሌዋውያን 19:18]
=============
👉 ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር
ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን
ይቅር አይላችሁም። - [የማቴዎስ ወንጌል 6:14,15]
=============
👉 የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና። - [የማቴዎስ ወንጌል 5:7]
=============
አሜን አምላካችን ፍጹም ይቅርታን ያልብሰን
