ru
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Открыть в Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Больше
4 374
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
t.me/EOTC2921 ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ #ክፍል_፪

t.me/EOTC2921 ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ #ክፍል_፩

🌾✞ #ያከብርዋ_ለሰንበት ✞🌾 ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት ||፪ ወኩሉ ፍጥረት ዓሣት ወአናብርት እለ ውስተ ደይን ያዕረፋ ባቲ እስመባቲ አዕረፈ እምኩሉ ገብሩ |||፪ 🌾✞¤¤¤~~~✞~~~¤¤¤✞🌾 ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት ጻድቃንም በገነት ||፪ ፍጥረታት በሙሉ ዓሣዎችና አንበሪዎች በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ በእርሷ እንዳረፈ ከሥራው ሁሉ |||፪ ➤➤➤➤➤➤✞➤➤➤➤➤➤ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Orthodox2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

#በደላችንን_ይቅር_በለን https://telegram.me/EOTC2921 1. እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን እንደሚወድ አምላካችን ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ባይወድ ኖሮ ይቅርታን እንድንጠይቅ አይነግረንም ነበር፡፡ አዎ እኛ ከተመለስን ምንም ያህል በደለኛ ብንሆን ይቅር ሊለን፤ ምንም ያህል ብንቆሽሸ ሊያድነን ዝግጁ ነው፡፡ እንዲህ እያለ ይጠራናል፤ «እናንተ ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ»፡፡ ስለዚህ በዚሀ ጸሎትም ላይ «በደላችንን ይቅር በለን» ብለን እንድንጠይቀው አስተማረን፤ ይቅር ይለን ዘንድ፡፡ 2. ይቅር ለመባል ምን ማድረግ እንዳለብን፤ ይቅር ሊለን ስለወደደም ይቅርታን ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን በዚሁ ቃል ነግሮናል፤ ማድረግ ያለብን ምንድን ነው? - ኀጢአታችንን ማወቅ፣ ማመን፣ ማስታወስ - የበደሉንን ይቅር ማለት - ይቅርታን መለመን #ኅጢአታችንን_ማወቅ /ማመን/ ጌታ «በደላችንን ይቅር በለን» ብለን እንድንጸልይ ሲነግረን በመጀመሪያ ደረጃ በደለኛ እንደሆንን እያስታወስን /እንድናስታውስ እያደረገን/ ነው፡፡ ሁልጊዜም በማሰብ፣ በመናገርና በማድረግ የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ የሆነውን ልባችንን /ኅሊናችንን/ እና ሰውነታችንን እናቆሽሻለን፤ መድኃኔዓለም ክርስቶሰ የሞተለትን ማንነታችንን እናጎድፋለን፡፡ ይህም የሰው ልጆች በቅድስና እርሱን መስለን እንድንኖር በኋላም የተዘጋጀልንን የዘለዓለም መንግሥት እንድወርስ ብቻ ፈቃዱ የሆነውን እግዚአብሔርን ያሳዝናል፤ በአርአያውና በአምሳሉ ለክብር የፈጠረው ሰውነታችን መጉደፍ ያስቆጣዋል፤ ንጹሐ ባሕርይ የሆነ እርሱ ኀጢአት አይስማማውምና፡፡ እንግዲህ ይቅር ለመባል በመጀመሪያ እንዲህ ኀጢአት እየሰራን መሆኑን ማወቅና ማመን ያስፈልገናል፡፡ ወደዚህ ዕውቀት ለመድረስም የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል መማር የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ስህተት የሚታወቀው ያለውን ሁኔታ /ድርጊታችንን ንግግራችንን፣ ሀሳባችንን.. / መሆን ከነበረበት /ከትክክለኛው/ ጋር በማነጻጸር በሚዛን ላይ በማስቀመጥ ነው፡፡ የማነጻጻሪያ ሚዛኖቻችን ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈ ሕግጋትና ትዕዛዛት ናቸው፡፡ እነዚህን ስናውቅ ጉድለቶቻችን፣ ድካሞቻችን ፍንተው ብሎ ይታዩናል፡፡ አሊያ ግን እየበደለን ያልበደልን ሊመስለን ይችላል፡፡ https://telegram.me/EOTC2921 #የበደሉንን_ይቅር_ማለት ጌታ በዚህ ጸሎት ይቅርታ እንድንጠይቀው በማስተማር ይቅር ሊለን እንደሚወድ ዝግጁም እንደሆነ ቢነግረንም ይቅር ለመባል ግን እኛ የበደሉንን ይቅር ማለታችን የግድ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦልናል፤ «በደላችንን ይቅር በለን» ከማለታችን በፊት «እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል» እንድንል ያዘዘን እኛ ይቅርታ የምናገኘው ሌሎችን ይቅር ስንል ብቻ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ ጌታችን ይህንን ጉዳይ በሌሎች የተለያዩ ቦታዎችም በተደጋጋሚ አስተምሮናል፤ በዚሁ በተራራው ስብከት ይኸው ጉዳይ ሁለት ጊዜ በጌታችን ትምህርት ተሰጥቶበታል፡፡ «እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል፡፡ » /ማቴ.7-2/ በሌላ ቦታም እንዲህ ሲል ይህንኑ ጉዳይ በምሳሌ አስተምሯል፤ መንግስተ ሰማያት ባሮቹን ለመቆጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች መቆጣጠርም በጀመረ ጊዜ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፡፡ ባለ እዳው ሰው የሚከፍለው ስላጣ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ንጉሡ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ባርያው ወድቆ ሰገደለትና ጌታ ሆይ ታገሰኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው፡፡ የዚያም ባርያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፡፡ ይህ ባርያ ግን ወጥቶ ከባልጀሮቹ /እንደርሱ ባርያ ከሆኑት/ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው፡፡ ባልንጀራው ባርያም ወድቆ ታገሰኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፤ ብሎ ለመነው፡፡ እርሱ ግን ሊተወው አልወደደም፡፡ ዕዳውን እስኪከፍልም በወኀኒ አኖረው፡፡ ይህንን ያዩ ሰዎችም አዘኑ፤ ሄደውም የሆነውን ሁሉ ለንጉሡ ተናገሩ፡፡ «ከዚህ ወዲያ ንጉሡ ጠርቶ፣ አንተ ክፉ ባርያ ስለለመንከኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህን የሆነውን ባርያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን አለው፡፡ ጌታውም ተቆጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚያሰቃዩት አሳልፎ ሰጠው፡፡» ጌታ ይህንን ምሳሌ ከተናገረ በኋላ የምሳሌውን ትርጉም እንዲህ ሲል ገልጦታል፤ ብሏል፤ «ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርገባችኋል»/ማቴ.18. 23- 35/ በአጠቃላይ ይቅር ለመባል ይቅር ማለት የግድ ነው፡፡ በእኛ ላይ የሚፈረድብን ፍርድ በእኛው እጅ ላይ ነው፡፡ ጌታችን በእነዚህ ትምህርቶች እንዲህ እያለን ነው «እኔ እናንተ ላይ የምፈርደው እናንተ በራሳችሁ ላይ በፈረዳችሁበት መንገድ /መልኩ ነው/»፡፡ #ይቅርታ_መጠየቅ ኀጢአታችንን ካወቀንና ካመንን፣ የበደሉንንም ከልብ ይቅር ካልን በኋላ ይቅር እንድንባል መጠየቅ /መለመን/ አለብን ፡፡ «ይቅር በለን» ብላችሁ ጸልዩ ብሎ በማስተማሩ ይህንን እንረዳለን፡፡ ወደ ንስሐ አባት መሄድና ኀጢአትን ተናዞ ቀኖና መቀበለ የሚገባወሙ መጀመሪያ በዚህ መልኩ ስለ ኀጢአት ካለቀሱ በኋላ ነው፡፡ ከዚያም ቀኖና ተቀብለን ስንፈጽምም ሆነ ከዚያ በኋላ ይኸው ስለ ኀጢአት ይቅርታ መጠየቁ ይቀጥላል፡፡ በእርግጥም ይቅርታ የምንጠይቀው አዳዲስ ስለሰራናቸውና ንስሐ ገና ስላልገባንባቸው ኀጢአቶቻችን ብቻ ሳይሆን ንስሐ ስለገባንባቸው ስለ ቀደሙት በደሎቻችንም ጭምር ነው፡፡ እንደ ቅዱስ ዳዊት «የቀደመ በደላችንን አታስብብን ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን» /መዝ.78-8/ እያልን ሰለ ቀድሙ በደሎቻችንንም እያሰብን በሕይወታችን ዘመን ሁሉ መጠየቅ አለብን፡፡ ይቅርታ የምንጠይቀው ስለምናውቃቸው /ስለምናስተውላቸው/ ኀጢአቶቻችን ብቻ ሳይሆን ስለማናስተውላቸውም መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ «ይቅር በለን» ስንል እኛ ካስተዋልናቸው መንገዶች ውጪ በብዙ መልኩ እርሱን እንደምንበድል አስበን ተማጽኗችን ስለነዚህም መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ለጸሎት ከመቆማችንና የጌታን ጸሎት ከመጸለያችን በፊት የበደሉንን ይቅር እንዳልን እርግጠኛ መሆን አለብን እኛ የበደሉንን ይቅር እንዳልን ልንል ነውና፡፡ «እኛንም በደላችንን ይቅር በለን» ስንልም ከላይ ያየናቸውን ነገሮች ሁሉ እያሰብን፤ ይቅር ሊለን የወደደ አምላካችንንም እያመሰገንን መሆን አለበት፡፡ በእውነት ይህንን ጸሎት የምንጸልየው በዚህ መልኩ ነውን? ካልሆነ ልምምዱን ዛሬውኑ እንጀምረው ፡፡ ይህንን ማድረግ እንችል ዘንደ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ አሜን፡፡ https://telegram.me/EOTC2921 ወስብሐት ለእግዚአብሔር

•✞✞✞ #ግን_መቼ_ነው ? ? ? ✞✞✞• ☞መቼ ነው ፣ እውነተኛ ክርስቲያን የምሆነው? ? ☞መቼ ነው ፣ እግዚአብሔርን መፍራት የምጀምረው? ? ☞መቼ ነው ፣ እግዚአብሔርን ማመስገን የምጀምረው? ? እስከመቼስ ነው በዋዛ በፈዛዛ ጊዜየን የምጨርሰው? ? ☞በከንቱ ጊዜዬን እጨርሳለሁ እፍፍፍ መቼ ነው ፣ እግዚአብሔር በሰጠኝ ነገር ደስተኛ የምሆነው ? ? ሁልግዜ አማርረዋለሁ ግን ለምን? ☞ኦ አምላኬ እዳስተውል እርዳኝ መቼ ነው ፣ ሰውን እደራሴ አድርጌ የምወደው? ? ☞መቼ ነው ፣ ለጠሉኝ ሁሉ መልካም የማደርገው ? ? እኮ መቼ? ☞መቼ ነው? እግዚአብሔር ለምን እደፈጠረኝ የምረዳው? ? ☞እኔማ ሁሌም በአለም ከንቱነት ጠፋሁ አለም አታለለችኝ ☞መቼ ነው ፣ እግዚአብሔር እንደፈለገው መኖር የምጀምረው ? ? ☞እኮ መቼ? እድሜዬን አንድም ቀን መልካም ሳልሰራበት..? ☞መቼ ነው፣ ክፉ ንግግር ከመናገር ተንኮል ከመስራት የምቆጠበው ? ? ☞መቼ ነው ፣ለፆም ለፀሎትና ለስግደት በሙሉ ልቤ ሆኘ የማገለግለው እኮ መቼ? ? ☞መቼ ነው፣ ለመልካም ስራ ምሳሌ የምሆነው? ? ☞መቼ ነው ፣ ይህን ከንቱ አለም ከልቤ የማወጣው ? ? ? እኮ መቼ ? ☞መቼ ነው ፣ እኔ ማለት ትቼ እህት ወንድሞቼ ወገኖቼ ማለት የምጀምረው ? ሁሌም እራስ ወዳድ እፍፍፍፍ.... ☞መቼ ነው ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የማከብረው ? ?? ☞እኮ መቼ ነው እንደ ቃሉ የምኖረው ? ☞እስከመቼስ ነው የሚፈልገውን ነገር ትቼ የሚጠላውን ነገር የምከተለው እፍፍፍ.... ☞መቼ ነው ፣ ጥሩ እና ለጋሽ አዛኝ የምሆነው? ? ☞መቼ ነው ፣ በፍቅር መኖር የምጀምረው ? ? ? ሁልጊዜ ልቤ በጥላቻ ተሞልቷል... ☞መቼ ነው ሰውን ከመበደል ከማስቀየም የምቆጠበው? ?? ☞መቼ ነው ከራስ ወዳድነት የምላቀቀው ? ? ? ☞መቼ ነው ተመስገን አምላኬ የምለው? ? ? ☞ኦ አምላኬ አንተ እርዳኝ እኔስ ግራ ገባኝ ??? አምላኬ ሆይ ጥበብና ማስተዋሉን፤ ልብና ልቦናውን፤ ጥንካሬና ብርታቱን እምነትና የዋህነቱን፤ ትግስትና ፍቅሩን•••ለኛ ለባሮችህ ትሰጠን ዘንድ አማላጅ በምትሆን በቅድስተ ቅዱሳን በእመአምላክ በንፅህት ቅድስት ድንግል ማርያም፤ እንዲሁም አንተ ባከበርካቸው ቅዱሳን ፀሎትና ቃልኪዳን ማረን ይቅር በለን፡፡ አቤቱ ሆይ እኛ ሀጢያተኛ ባሮችህን ለንሰሀ ሞት አብቃን፡፡ •••✞ አሜን ✞ አሜን ✞ አሜን ✞•••

photo content

🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 #የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ተጋድሎ_በኢትዮጵያ_ሊቃውንት 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ❖ የዚኽም ቅዱስ አባቱ በቀጶዶቅያ መስፍኑ አንስጣስዮስ ሲኾን እናቱ ቴዎብስታ ትባላለች፤ የተወለደውም በልዳ በሶርያ ፍልስጥኤም በ፪፻፹ ዓ.ም. ነው፤ ታናሽ ኾኖ ሳለ አባቱ ዐርፏል፤ ቅዱሳት መጻሕፍትን ፈረስ ግልቢያን ተምሮ ኻያ ዓመት በኾነው ጊዜ ቢሩት ሀገር በመኼድ በዚያ ሀገር ይመለክ የነበረውን መንፈሰ ሰይጣን ያደረበትን የመኰንኑን ልጅ እንዲበላት የተሰጠውን ዘንዶ በክርስቶስ ስም ከገደለው በኋላ እጅ መንሻ ይዞ ወደ ንጉሠ ፋርስ ኼደ፡፡ ❖ በዚያ ሀገር ግን ነገሥታቱ ጣዖታትን በማምለክ ክርስቲያኖችን ሲያሳድዷቸው አይቶ ዐዘነ፤ ልቡም በክርስቶስ ፍቅር ነድዶ ወደ ሀገሬ አልመለስም ስለ ክርስቶስ ስም እሞታለኊ አለና “ክርስቲያናዊ አነ ወአአምን በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ” (እኔ የክርስቲያን ወገን ነኝ እምነቴም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው) በማለት መሰከረ፡፡ ❖ ከዚያም ንጉሡ ልብሱን ገፍፈው በዕንጨት ላይ እንዲሰቅሉት፤ ዳግመኛ የዘንባባ እሾኽ የመሳሰሉ ፸ የብረት ችንካሮች ሠርተው በነዚያ እንዲቸነክሩትና ዐጥንቱን ኹሉ እንዲቀጠቅጡት አዘዘ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን በትዕግሥት በመኾን “እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል” (ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል እንደተሰቀለ እንዴት አላስብም) አለ፡፡ ❖ ዳግመኛም በውስጡ ረዣዥም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማን ባጫሙት ጊዜ “ሠጠቅዎ ወመተርዎ ዐሥራዊሁ እስከ ውኅዘ ደሙ ዲበ ምድር ከመ ማይ ወሶበ ስዕነ ሠጊረ ድቡተ ሖረ” ይላል ችንካሮቹ ደሙ እንደ ውሃ በምድር ላይ እስኪፈስስ ድረስ እግሩን ዘልቀው ሥሩን በጣጠሱት፤ መኼድም ባልቻለ ጊዜ አጐንብሶ ኼዷል፤ ከዚያም የፈላ የብረት ጋን ውስጥ ከትተው ሰውነቱ በደም እስኪጥለቀለቅ ድረስ ራሱን በመዶሻ ሲመቱት ወደ ጌታችን ጸለየ፤ ያን ጊዜ “ጊዮርጊስ ሆይ ከአንተ ጋር ነኝና ጽና” የሚል ቃል ከሰማይ መጣለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ተገልጾ ከሕመሙ ፈውሶታል፡፡ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች በጌታችን አመኑ፡፡ ❖ ንጉሡም ይኽነን ባየ ጊዜ እጅግ የሚያስጨንቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀን አሠርቶ ለቅዱስ ጊዮርጊስ “እመሰ ትሠውዕ ለአጵሎን ትነሥእ ጌራ መንግሥት ወእመሰ ኊልቊ አንተ ከመ ትትልዎ ለክርስቶስ ነጽር ዘንተ መንኰራኲረ ዘግበርኩ ለከ ከመ እግድፍ በውስቴታ ታማስን ሥጋከ” (ለአጵሎን ብትሠዋ የመንግሥትን ዘውድ ትቀዳጃለኽ፤ ግን ክርስቶስን ለማገልገል የቈረጥኽ ብትኾን ሥጋኽን ትፈጭ ዘንድ በውስጧ ልትጣልባት ያዘጋጀኋትን መንኰራኲር ተመልከት) አለው፤ ይኽ ሲኾን ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጣሪው ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ ❖ እነርሱም ወደ መንኰራኲሩ በመወርወር ፵ ሰዎች ያዞሩት ዠመር ከዚያም ሰውነቱ ለዐሥር ክፍል ተከፋፈለ፤ እነርሱም ሥጋውን በጒድጓድ ውስጥ ቀበሩት፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመምጣት እንደገና ከሞት አስነሣውና ባረከው፡፡ ❖ ርሱም ከሞት ተነሥቶ እንደገና ወደ ከተማ ገብቶ ስለ ክርስቶስ አምላክነት መሰከረ፤ እነርሱም እጅግ ለመስማት የሚከብዱ መከራዎችን አደረጉበትና ሰውነቱን ጨምቀው አንጀቱን ዘረገፉት፤ ከዚያም ሥጋውን አቃጥለው በዕንጨት ቀፎ በማድረግ ይድራስ ወደተባለ ተራራ ወስደው ዐመዱን በትነውት ተመለሱ፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመውረድ አራቱን ነፋሳተ ምድር የተበተኑትን የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥጋዎች እንዲሰበስቡ አዝዞ እንደገና ከሞት አስነሥቶታል፤ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች በክርስቶስ አምነው የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅተዋል፡፡ ❖ በመጨረሻም ብዙ ተጋድሎዎችን ለሰባት ዓመታት ከፈጸመ በኋላ ንጉሡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ራስ በሰይፍ እንዲቈረጥ አዝዞ ወደ መሰየፊያው ቦታ ሲኼድ እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን ነገሥታት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያኖች ጸጥ ይል ዘንድ ጸለየ፤ ወዲያውኑም እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን ነገሥታት አቃጥሏቸዋል፤ ከዚያም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብዙ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፤ ከዚያም ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ራሱን ዘንበል አድርጎ ሚያዝያ ፳፫ በሰይፍ ቈርጠውት የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅቷል፡፡ ❖ ከአገልጋዮቹ የቀሩት ሥጋውን ወስደው በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ወደ ሀገሩ ልዳ በመውሰድ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በውስጡ አኖሩት፤ ከርሱም ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራት ተገልጠዋል፡፡ ❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ጽጌ ብርሃን በማሕሌተ ጽጌ ድርሰታቸው ላይ፦ “ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየሐቱ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ” (የስሙና የሞቱ መታሰቢያ ባንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከኾነ ዕንቈ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለርሱ ኹሉን ታሰግጅለታለሽ (ታንበረክኪለታለሽ) ርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል) ይሉታል፨ ❖ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቁ አርከ ሥሉስም የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስን ተጋድሎ፡- “ሰላም ለከ ሰርዌ ሰማዕታት አእላፍ ዘሞገሰ ስምከ በጽሐ መንገለ ኲሉ አጽናፍ በቅድመ ፀሓይ ብሩህ ዘኢየዐርብ ለዘልፍ ሕማምየ ዝሩ ነሢአከ ወጸዊረከ እስትንፋሰ አፍ ጊዮርጊስ ቀሊለ ክንፍ ከራድዮን ዖፍ” (ዘወትር በማይጠልቅ በብሩህ ፀሓይ ፊት በምድር ዳርቻዎች ኹሉ የስምኽ ባለሟልነት የደረሰ የአእላፍ ሰማዕታት አለቃቸው ሰላምታ ለአንተ ይገባል፤ ክንፈ ፈጣን ከራድዮን ዖፍ የተባልኽ ጊዮርጊስ ሆይ የአፍ እስትንፋስን ተቀብለኽና ተሸክመኽ ሕማሜን በትን) እያለ ተማፅኖታል፡፡ ❖ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦ “ሰላም ለጊዮርጊስ ሰማዕት ዘፀሓየ ጽድቅ ዘተአምሪሁ ከመ ኆጻ ባሕር ዘኢይትኌለቊ ኮከበ ክብር ዘማእከለ ሰማይ ወምድር ዘአርአየ ኀይለ በዲበ ሰሌዳ መንበር ብእሲ አዛል ወመስተጋድል ኀያል ዝሕዙሐ ገድል”፡፡ (ገድሉ የበዛ የተትረፈረፈ ኀያል፤ ተጋዳይ ጐልማሳ (ብርቱ) ሰው፤ በተዘረጋ ዙፋን ላይ ኀይልን ያሳየ፤ በሰማይና በምድር መኻከል ያለ የማይቈጠር የክብር ኮከብ፤ ተአምሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ የኾነ፤ የፀሓየ ጽድቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት ለኾነ ለጊዮርጊስ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፨ ❖ የስብሐተ ፍቁር ዘጊዮርጊስ ደራሲ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ፦ "እምብሩር ወወርቅ ይትበደር ሞገሱ ለጊዮርጊስ ቅዱስ በዲበ ጸዐዳ ፈረሱ ለረዲኦትነ ይምጻእ ወያንሶሱ" (ከወርቅና ከብር ይልቅ ሞገሱ የሚበልጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረሱ እኛን ለመርዳት ይምጣ፤ ይመላለስም) ይለዋል፨ 👇👇👇👇👇👇👇 ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

#የቅዱሱ_ኪዳን_ቅርስ_ወይም_ቅዱሱ_ጽዋ https://telegram.me/EOTC2921 ✔✞ አባቶቻችን እንደተናገሩንና በድርሳነ ዑራኤልም እንደተፃፈው ጌታችንና መድኃኒታችን በዕለተ አርብ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ ከሰውነቱ የፈሰሰውን ደም በብርሃን ጽዋ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ተቀበለው፡፡ ደሙንም በመላው ዓለም ረጨው፡፡ የደሙ ንጣቢ ያረፈበት ቦታ ሁሉ የቤተክርስቲያን ሕንፃ ማረፊያ፣ የቅዱስ ቁርባን መፈፀሚያ እንዲሁም ታላቅ ቃል ኪዳን ለዓለም ተሰጠ፡፡ ✔✞ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ክቡር ደሙን በዐራቱም ማዕዘናት ከረጨ በኃላ ጽዋውን በመድኃኔዓለም ፈቃድ በቅድስ አገር ኢትዮጵያ መንዝ ውስጥ እመጓ ቆላ አምጥቶ ቀበረው፡፡ #መንዝ ማለት ነዝሃ ከሚለው ግእዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡ ይኸውም መርጨት ማለት ነው፡፡ የክርስቶስ ደሙ የተረጨበት ጽዋ ማረፊያ ስለሆነ ነው፡፡ #እመጓ ማለት እመ እጓል ከሚለው የግእዝ ሐረግ አጥሮ የተገኘ ቃል ነው፡፡ ይህም የልጅ እናት ማለት ነው፡፡ ✔✞ የቅዱሱ ኪዳን ቅርስ /የቅዱሱ ጽዋ/ ጠባቂዎች፦ ለዚህ ቃል ኪዳን የታመኑና የተገቡ በመሆናቸው የነፍሳቸውን ጽድቅ ብቻ ሳይሆን እስከ ዳግም ምጽአት ድረስ የከበረ ስጋቸው እንዳይበሰብስ ዐፅማቸው እንዳይፈርስ በመድኃኔዓለም ቃል የተገባላቸው ናቸው፡፡ ✔✞ የአርማትያሱ ዮሴፍ ይህን ክቡር ጽዋ ወደ ቤቱ ወሰደው ከዚያም ወደ አርማትያስ ኬብሮን ሸሸ፡፡ ከዚያም ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ባኮስ ወደ ኬብሮን ተጓዘ ከዛም ዮሴፍ ወደ ሶርያ ተሰዶ ስለነበር ከሶሪያ ከዮሴፍ ተቀብሎ ወደ አክሱም ፅዮን አመጣው፡፡ የዚህ ጃንደረባ ታሪክ በጌምድር እንዳቤት ከግሼና ተክለሃይማኖት ደብር ይገኛል፡፡ ✔✞ ቅዱሱን ጽዋ ለመመልከት የታደለ ሰው ታሞም ቢሆና ይድናል፡፡ በዛች ሳምንት አይሞትምና የቻለውን ያክል ዘመን ጽዋዋን ቢመለከታት የፊቱ ጸዳል ሳይቀር እንደልጅነቱ እንደለመለመ ይኖራል፡፡ ድንጋይ የተባለው ቅዱሱ ጽዋ የሰውን ልጅ አጥንትና ሥጋ ከመስበስ ታደጎ ለምለም ያደርገዋል፡፡ ምንጭ፦ ከእመጓ መጽሐፍ https://telegram.me/EOTC2921 🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🙏

Emegua_Part_17_እመጓ_ክፍል_፲፯ @EOTC2921.wma3.88 MB

Emegua_Part_16_እመጓ_ክፍል_፲፮ @EOTC2921.wma7.65 MB

Emegua_Part_15_እመጓ_ክፍል_፲፭ @EOTC2921.wma6.79 MB

Emegua_Part_14_እመጓ_ክፍል_፲፬ @EOTC2921.wma7.60 MB

Emegua_Part_13_እመጓ_ክፍል_፲፫ @EOTC2921.wma7.58 MB

Emegua_Part_12_እመጓ_ክፍል_፲፪ @EOTC2921.wma7.71 MB

Emegua_Part_11_እመጓ_ክፍል_፲፩ @EOTC2921.wma7.57 MB

Emegua_Part_10_እመጓ_ክፍል_፲ @EOTC2921.wma7.44 MB

Emegua_Part_9_እመጓ_ክፍል_፱ @EOTC2921.wma7.71 MB

Emegua_Part_8_እመጓ_ክፍል_፰ @EOTC2921.wma7.22 MB

Emegua_Part_7_እመጓ_ክፍል_፯ @EOTC2921.wma7.50 MB

Emegua_Part_6_እመጓ_ክፍል_፮ @EOTC2921.wma7.26 MB