ru
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Открыть в Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Больше
4 374
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
🌾✞ #ፅንሰታ_ለማርያም ✞🌾 #የአምላክ_እናት_የተፀነሰችበት ❖ ነሐሴ ፯ የአምላክ እናት የፅንሰቷ በዓል በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል። በነገረ ማርያም ላይ እንደተጻፈ በእናቷ በሐና በኩል ያሉ የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ጴጥሪቃ ቴክታ ሲባሉ “ወኮኑ ክልኤሆሙ ጻድቃን ወፈራህያነ እግዚአብሔር ወይትአመንዎ ለአምላኮሙ በጥቡዕ ልብ እንበለ ኑፋቄ” ይላል (ኹለቱም ሰዎች ደጋጐችና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ያለምንም መጠራጠር በፍጹም ልቡናቸው በአምላካቸው የሚተማመኑ ነበሩ)። ❖ እነርሱም በጊዜው ይኽ ቀራችኊ የማይባሉ ባለጠጎች ነበሩ፤ ከሀብታቸው ብዛት የተነሣ ወርቁን ብሩን እንደ ዋንጫ እያሠሩ በላሙ በበሬው ቀንድ ላይ ይሰኩት ነበር፤ ይኽን ያኽል አቅርንተ ወርቅ፣ አቅርንተ ብሩር እየተባለ ይቈጠር ነበር፤ የዕንቊ ጽዋ እንኳ ፸፣ ፹ ያኽል ነበራቸው ይላል ፡፡ ❖ ከዕለታት ባንዳቸው ጴጥሪቃ ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ የሀብቱን ብዛት አይቶ ሚስቱ ቴክታን “ለመኑ ዘዘገብነ መዛግብቲነ አልብነ ውሉድ ዘይወርሰነ አንቲኒ ወአነሂ መካን ንሕነ” (የሰበሰብነው ገንዘብ ስንኳን ለኛ ለልጅ ልጅ ይተርፍ ነበር አንቺም እኔም መካኖች ነንና የሚወርሰን ልጅ የለንም) በማለት ተናገራት፤ ርሷም እንዲኽ ማለቱ ወላድ የፈለገ መስሏት በሐዘን ኾና “አምላከ እስራኤል ከኔ ልጅ ባይሰጥኽ ከሌላ ይሰጥኽ ይኾናልና ሌላ አግብተኽ ውለድ” አለችው። ❖ ርሱም “አነሂ ኢይፈቅድ የአምር አምላከ እስራኤል ከመ ኢየሐስቦ ለልብየ” (ይኽንስ እንዳላደርገው በልቤም እንዳላስበው የእስራኤል አምላክ ያውቃል) በማለት ተናገረ፡፡ ርሷም ዐዝና ሳለ ራእይ ታያለች፤ ነጭ እንቦሳ ከማሕፀኗ ስትወጣ እንቦሳዪቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ሰባት ስትደርስ ሰባተኛዋ ጨረቃን ስትወልድ፤ ጨረቃ ፀሓይን ስትወልድ አይታ በአድናቆት ለባሏ “ግሩም ግብሩ ለእግዚአብሔር ትማልም ርኢኩ በሕልምየ ጸዐዳ ጣዕዋ ወጽአት እምከርሥየ ይእቲኒ ወለደት ጸዐዳ ጣዕዋ እስከ ሰብዐቲሆን ወሳብዕታኒ ወለደት ወርኀ ወወርኅኒ ወለደት ፀሓየ” (የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው፤ ትናንትና ማታ በሕልሜ ነጭ ጥጃ ከማሕፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ደግሞ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንደዚኽ እየኾነ እስከ ሰባት ትውልድ ሲደርሱ ሰባተኛዪቷም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየኊ) በማለት አስረዳችው። ❖ ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ሕልም ወደሚፈታ ሰው ዘንድ በመኼድ የሚስቱን ራእይ ነገረው፤ ያም ሕልም ተርጓሚ ምስጢር ተገልጾለት ሰባት አንስት ጥጆች መውለዳችኊ ሰባት ሴቶች ልጆች ይወለዳሉ፤ ነጭ መኾናቸው ደጋጎች ልጆች መኾናቸው ሲኾን “ወሳብእታኒ ትከብር እመላእክት ወትትሌዐል እምኲሉ ሰብእ ወበእንተ ፀሓይኒ ኢያእመርኩ” (ሰባተኛዪቱ ጨረቃን መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ናት፤ የፀሓይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም) በማለት ተረጐመለት፤ ርሱም ለሚስቱ ነገራት፤ ርሷም “የእስራኤል አምላክ የሚያደርገውን ርሱ ያውቃል” በማለት ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ ❖ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች ስሟንም ሔሜን አሏት፤ ሔሜን →ዴርዴን ወለደች፤ ዴርዴም →ቶናን፤ ቶናም →ሲካርን ወለደች፤ ሲካርም→ ሴትናን፤ ሴትናም →ሔርሜላን ወለደች፤ ሔርሜላም የተከበረችና የተመረጠች ዓለሙን ኹሉ ለፈጠረ ጌታ አያት ለመኾን የበቃች ሐናን ወልዳለች፤ የዝማሬና የትንቢት ጸጋ ከእግዚአብሔር የተሰጡት ክቡር ዳዊት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በተለይም ስለ ሥርወ ልደቷ አስቀድሞ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት በመዝ ፹፮፥፩‐፯ ላይ “መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን” (መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ላይ ናቸው) በማለት የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥት ከቤተ ክህነት ከኾኑት ከተቀደሱት ከቅዱሱ ኢያቄምና ከቅድስቲቱ ሐና የመኾኑን ነገር በምሳሌ የገለጸው። ❖ ሐና በመልካም አስተዳደግ አድጋ አካለ መጠን ስታደርስ ከነገደ ይሁዳ ከመንግሥት ወገን የተወለደ የቅስራ ልጅ የአልዓዛር የልጅ ልጅ ከሚኾን ከኢያቄም ጋራ አስተጫጭተው አጋቧት፡፡ ሐናና ኢያቄምንም “ወክልኤሆሙ ኄራን ወሥሙራን እሙንቱ ወየሐውሩ በሕገ እግዚአብሔር እስመ እግዚአብሔር ኀረዮሙ ወአፍቀሮሙ ትካት” ይላቸዋል እግዚአብሔርን የሚወድዱ በሕጉ የሚኖሩ ደጋጎችና አምላክም የመረጣቸው ሲኾኑ ሐና መካን በመኾኗ ምክንያት ኹለቱም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ዕለት ዕለት በመኼድ ለዐይናቸው ማረፊያ ለልባቸው ተስፋ የሚኾን ልጅ እንዲሰጣቸው ይለምኑ እንደነበር፤ “Protoevangelium of James” (ፕሮቶቫንጊሊዩም ኦፍ ጀምስ) የሚለው ያዕቆብ የጻፈው ጥንታዊዉ መጽሐፍ በስፋት ይገልጻል፡፡ ❖ ከዕለታት ባንደኛው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ሲመለሱ “ወርእዩ አርጋበ እንዘ ይትፌሥሑ ምስለ ውሉዶሙ” ይላል ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ደስ ብሏቸው ሲጫወቱ አይተው ሐና “አቤቱ ጌታዬ ግዕዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠኽ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሣኸኝ” ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፤ ወዲያው ሱባዔ ይገባሉ፤ ኢያቄም ወደ በረሓ ኼዶ ሲጸልይ ሐና ደግሞ በቤቷ ዙሪያ ባለው የተክል ቦታ ሱባዔ ያዘች፤ በሱባዔያቸው ፍጻሜ ኹለቱም ራእይ አይተው ተነጋግረዋል፡፡ ❖ “ይቤላ ኢያቄም ለሐና ብእሲቱ እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ” ይላል ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዎፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ብሎ የተገለጸለትን ለሐና ነግሯታል፤ ይኸውም የራእዩ ምስጢር፡- ዎፍ የተባለው አካላዊ ቃል ክርስቶስ ሲኾን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፤ ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ ሲያጠይቅ ሲኾን፤ ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ምልአቱ፣ ስፍሐቱ፣ ርቀቱ፣ ልዕልናው፣ ዕበዩ ናቸው፡፡ ❖ ሐናም ተገልጾላት “ትቤሎ ሐና ለኢያቄም ብእሲሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ” ይላል ለባሏ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ብላዋለች፤ ይኽ የራእይ ምስጢር፦ ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትኾን፤ ነጭነቷ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፤ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ ወደ ዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በዦሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መኾኗን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ❖ ኢያቄምና ሐናም ይኽነን ራእይ ሐምሌ ፴ ቀን ካዩ በኋላ “ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ይኾናል፤ ሴትም ብንወልድ ለቤተ እግዚአብሔር መጋረጃ ፈትላ ትኑር” ብለው ስእለት ከተሳሉ በኋላ ራእይ አየን ብለው ዕለቱን አልተገናኙም፤ አዳምንና ሔዋንን “ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት” ብሎ የተናገረው አምላክ ለእኛም ይግለጽልን ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ሰባት ቀን ድረስ እየብቻቸው ሰነበቱ። ❖ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን “ከሰው የበለጠች ከመላእክት ኹሉ የከበረች ልጅ ትወልዳላችኊ" ብሎ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለሐና ነግሯት በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን ነሐሴ ሰባት እሑድ ተፀንሳለች፤ በእናቷ ማሕፀን ሳለችም “መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እምከርሠ እማ” እንዲል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥንተ አብሶ ባመጣው መርገም እንዳትያዝ ጠብቋታል፡፡ ~~~✞ #ይቀጥላል ✞~~~

#ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰው ✍️የኢትዮጵያ ሊቃውንት እንደ ተረጎሙት

ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ @EOTC2921.pdf15.57 MB

#ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰው ✍️የኢትዮጵያ ሊቃውንት እንደ ተረጎሙት

#ውዳሴ_ማርያም ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰው ✍️የኢትዮጵያ ሊቃውንት እንደ ተረጎሙት

​​🌾✞ #መልክአ_ፍልሰታ ✞🌾 https://t.me/EOTC2921 ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን ✞ ፩ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ሕያዊት ከምትሆን ነፍስሽ ጋር በፍጹም ተዋህዶ ለተከናወነው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ አንቺ ወለተ ማቲ የተባልሽ በነፍስ በስጋ በውስጥ በአፍአ አማናዊት ድንግል ነሽ እኮን ብልሆችና አዋቂዎች የአፌዝን ወርቅ አሳፍረው የሚጓዙብሽ ሰሎሜናዊት የተርሴስ መርከብ አንቺ ነሽ፡፡ ፪ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ኅዘንን ወደሚረሱበት ትካዜን ወደማያስቡበት የተረጋጋ ፍጹም ደስታ ወዳለበት ለተጓዘው ፍልሰተ ስጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ቅድመ አለም በአምላክ ልቡና ታስበሽ ያለሽ ነሽ እኮን፡፡ እንግዲህ በፍልሰትሽ በፍጹም ደስታ ዛሬ ደስ ተሰኝቻለሁ ነገር ግን ፊትሽን የማየው መቼ ይሆን፡፡ ፫ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ በሰው ልብ የማይታሰበውን ግርማ ሞገስን የተላበሰ ጸጋ ክብርን ለተጎናጸፈ ፍልሰተ ስጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ሥጋሽ ዕንቈ ባሕርይ ነው፡፡ ስለዚህም በደመና ሲያርግ በተመለከተ ጊዜ ሞት በፍጹም ኃፍረት አፈረ፡፡ ፬ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ከባረካ ልጅ ከኄኖክ ፍልሰት ከፍ ከፍ አድርጎ እግዚአብሔር አክብሮ ለባረካት ፍልሰተ ስጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ከብርሃናት ሁሉ የምትበልጭ ብርህትና አስደሳች ነሽ እኮን ስለዚህም የብዙ ብዙ የሚሆኑ የሰማይ መላእክት በአንቺ ምክንያት በሰማያዊት አዳራሽ ታላቅ ደስታን ያደርጋሉ፡፡ ፭ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ክብሩ ባለሟልነቱ ለማይገሰስ የምስጋናው ባሕር (ባሕርይ) ለማይጎድል ፍልሰተ ስጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ የእግዚአብሔር የልዩ ምስጋናው አዳራሽ ነሽ እኮን ስለዚህ በፍልሰትሽ ጊዜ አንቺን የተቀበሉ መላእክት ማርያምስ በሰማይም በምድርም የከበረች ነች ተባባሉ፡፡ ፮ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ከጌታ ወዳጅ ከያዕቆብ ፍልሰት ይልቅ ክብር ምስጋና ለተገባው ፍልሰተ ስጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ቀናንሞ የተባለ ሽቱ ነሽ። የልዩ ሽቱ አይነትም መገኛ ነሽ፡፡ ስለዚህም ብርሀን ለብሰው በብርሃን ነፀብራቅ ተጎናጽፈው የፍልሰትሽን በዓል መላእክት ያከብራሉ፡፡ ፯ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ከፀሐይና ከጨረቃ ሥነ ጸዳል ይልቅ ፈጽሞ ለሚያበራውና ፍጹም ምስጋና ለተገባው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ሁሉን ከሚያስደስትና የደስታ መገኛ ከሚሆን ልጅሽና ያለ አንቺ የሞትን ማሰሪያ በጣጥሶ የሲኦልን ደጃፍ ሰባብሮ ነፍሳትን ከዲያብሎስ የባርነት አገዛዝ ነጻ ያወጣ ማንም የለም፡፡ ፰ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ሱራፊ መልአክ እየጠበቃት በኪሩቤል ከተማ ትኖር ዘንድ ከዚህ ከአላፊውና ከጨለማው ዓለም ለተዛወረችው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ከጥቅምት ወር የጽጌ የአበባ ሽታ ይልቅ የመዓዛሽ ጣዕም እጅግ የጣፈጠ ነው፡፡እነሆ በስህተት ባሕር ልሰጥም ተቃርቤአለሁና በንጽሕናሽ በቅድስናሽ መርከብ አሳፍረሽ እኔን አገልጋይሽን አሻግሪኝ፡፡ ፱ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ በቅድስተ ቅዱሰን ቆሞ የነግሁን መስዋዕት ሲያሳርግ የካህናቱን አለቃ ለአስደነቀው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ አምላክ ያተመው የፍልሰትሽ ግርማ ሞገስ ያን የቂም በቀል መልአክና የክፉ መጨረሻ የሆነ መልዐከ ሞት ምንኛ አሰቃየው ምንኛ መከራውን አሳየው እሰይ እሰይ። ፲ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ የይቅርታው ክናድ ለዘላለሙ ጸንቶ ለሚኖረውና የኃይለኞች ኃይለኛ ለሚሆን ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል። #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ መታሰቢያሽ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለዘላለም ሲታሰብ ይኖራል። በምድር ላይ ለሚኖሩ ኃጥአን ሁሉ አማልደሽ ምህረት የምታስገኝ ነሽና እመቤቴ ሆይ የተባረክሽ የክርስቶስ አካሉን ነሽ፡፡ ፲፩ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ለተመረጡት ልጆች እናት ትሆኛቸው ዘንድ ምጡቅ በሆነ በብርሀን ሰረገላ ለመጠቀ ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል። #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ብዙዎች ወገኖች በሁለት ድሪም በአስፈላጊው ጊዜ በትጋትና በመፋጠን ወገንን እንደሚዋጁ እኔን አገልጋይሽን በይቅርታሽ ወርቅ ዋጅተሽ ገንዘብ አድርጊኝ፡፡ ፲፪ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ እግዚአብሔር ለተዋሐዳትና ስነ ስርአቷንም ለተካፈላት ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ በፍልሰትሽ ጊዜ በምድረ ይሁዳና በኢየሩሳሌም አደባባይ የተርሴስና የደስያት ነገስታት ለመታሰቢያሽ መዓዛቸው የጣፈጠ ሽቶና ልዩ ልዩ እጅ መንሻዎች ይዘው ቀረቡ፡፡ ፲፫ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ከሴሎ ነቢይ ከኤልያስ ፍልሰት ይልቅ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ላደረገው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ሁሉን እንዳውሬ የሚያድን ሞት ተከትሎኝ የኔ በተድላ ደስታ መኖር ምኔም ስለአይደለ በአውሎ ነፋስ ክንፍ ጠልፈሽ ጻድቅ ካለበት ቦታ ወስደሽ ከዚያ አድርሽኝ። ፲፬ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ተጠባቢዋና መጋቢዋ እግዚአብሔር የሆነ ወደ አማረችውና ወደ ተደላደለችው ሀገር ለፈለሰው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ መሪር ከሆነ የሞት አገዛዝ ነፃ አውጪኝ የሰማይና የምድር ንግሥት ሆይ አንቺ እኮ ከፈቀድሽ ኃጥኡን ባሪያ ነፃ ማውጣት አይሳንሽም ፡፡ ፲፭ #ለትንሣኤ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ሕያው ባሕርዩን በውስጧ ሰውሮ ለተነሳባት የክርስቶስ ትንሳኤ መንትያ ለሆነች ትንሣኤ ስጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ በዚያች በቁርጥ ቀን የፍርድ ምርመራ በተደረገ ጊዜ ምድርም አደራዋን በመለሰች ጊዜ አንቺ የኤፍራታ ርግብ ሆይ በክንፈ ረድኤትሽ ሠውሪኝ በጥላሽም ሥር ሸሽገሽ አድኚኝ፡፡ ፲፮ #ለዕርገተ_ሥጋ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ አንቺን ለሚያመሰግኑ ቅዱሳን ሰዎች ሁሉ የዕርገታቸው መመሪያ ለሆነ ዕርገተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ የሊቀ ካህናቱ የካህኑ የአሮን የሽልማቱ ጌጥ ነሽ እኮን በአንደበታችን የሚነገረው የምስጋናሽ ፍሬ ሁሉ በውስጥም በውጭም ላለው ልብስሽ ላይ በስዕል መልክ ተቀርጾ ይኑር፡፡ ፲፯ #ስብሐት_ለኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ በሥጋዊ በደማዊ አንደበት ሁሉ ለአንቺ ምስጋና ይገባል፡፡ በመላእክትም አንደበት ያለማቋረጥ ለአንቺ ምስጋና ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ የደብተራ ኦሪት ቃል ኪዳን የተጻፈብሽ የሕግ ታቦት ላንቺ ሰላምታ ይገባል፡፡እንደዚሁም ለኔ ለአገልጋይሽ ለ........ የክብር ጌጥ ወይም ሽልማት ሆኖኝ ይኖር ዘንድ የልዩ ችሮታሽን የነጭ ሐር ልብስ አጎናጽፊኝ፡፡ ይልቁንም በሥጋ በነፍስ ጥበቃሽ አይለየኝ፡፡ አሜን። ---✞ #አቡነ_ዘበሰማያት ✞--- ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯