የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Открыть в Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Больше4 374
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
4 374
✍✞ኢትዮጵያዊው ፃዲቅ አቡነ ሀብተ ማርያም ታሪክ ባጭሩ,,,✞
አምስቱን መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን የተሰጠው ፃዲቁ አቡነ
ሀብተማርያም የነበረበት ዘመን 1486 ዓ.ም ንጉስ እስክንድር በነገሰበት ጊዜ
ነው። አባቱ ፍሬ ቡሩክ እናቱ ዮስቴና ይባላሉ። ፍሬ ቡሩክና ዮስቴና በህገ
እግዚአብሔር በሃይማኖት በትሩፋት በምግባር ፀንተው የሚኖሩ ደጋግ
ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ አቡነ ሀብተማርያም ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ
አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነሱም፡-
1/ መብረቅ፣
2/ ቸነፈር፣
3/ ረሃብ፣
4/ ወረርሽኝ፣
5/ የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡
ከብዙ ተጋድሎ በኃላ ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም በፀሎት ላይ ሳለ በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ የቆምክባትን ቦታ ምስራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣
ደቡቡን ባርክ አለው፡፡ ሲባርክም ሶስት አጋንንት በፀሎቱ ስልጣን ታስረው በፊቱ
ታዩት።
እነዚህም አጋንንት ከኖህ ጀምሮ ሰውን በማሳት ከኖርን በኋላ ከአንተ ጋር ምን
ፀብ አለን አሉ አባታችንም አቡነ ሀብተማርያም በትዕምርተ መስቀል ሲያማትብ
ሁለቱን አጋንንት ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው አንዱ ጊዜዬ ስላልደረሰ አታጥፋኝ
አለው፡፡ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይህንን ተወው
ጊዜው አልደረሰም አለው።
የጌታ ቃል እንዲህ ብሎ በተናገረ ጊዜ ሰይጣን ከአባታችን ተለይቶ ጠፋ፡፡ ማር 9፡
23 ከዚህም በኋላ ዕለተ ሞቱ በደረሰ ጊዜ ለሞቱ ምክንያት የሚሆን ቸነፈር
ያዘው፡፡ ጌታችንም በምስጋና ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ዛሬ
ወደአንተ የመጣሁት ከድካም ወደ እረፍት እወስድህ ዘንድ ነው ሰባት የጽድቅ
አክሊሎችን አዘጋጅልሃለሁ አለው።
1/ ስለ ንፁህ ድንግልናህ፣
2/ አለምንና በውስጡ ያለውን ንቀህ በመኖርህ፣
3/ ስለ ፍፁም ምንኩስናህ፣
4/ ዘወትር አራቱን ወንጌላትን በማንበብህና በመፀለይህ፣
5/ ስለ እኔ ብለህ ስለተራብከው፣
6/ በጾም ስለተጋደልክ፣
7/ ቂምና ጥላቻን፣ ትዕቢትን፣ ትምክህትን፣ በልብህ ውስጥ ባለማስቀመጥህ
ስለ ንፁህ ተልዕኮ ክህነትህ፣ ስለ ንፁህ መስዋዕትህ ነው ብሎ ቃል ኪዳን
ሰጠው፡፡
በተጨማሪም እኔ የሰጠሁህን ቃል ኪዳን ተስፋ አድርጎ መጽሐፈ ገድልህን
ለሚጽፈው ስሙን በመንግስተ ሰማያት በእውነት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፣
ለቤተክርስቲያንህ ዘይትን፣ ወይንን፣ ዕጣንን፣ ህብስትን እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ
በአንተ ስም መብዓ የሰጠውን የወደደውን ሁሉ አደርግለታለሁ፡፡ በመንግስተ
ሰማያትም ከወዳጆቼ ከቅዱሳን ጋር በደስታ አኖረዋለሁ፡፡
የአቡነ ሀብተማርያም ፈጣሪ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ብሎ ያንተን ስም ጠርቶ
ቢለምነኝ ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገባለት ይህንንም ካለው
በኋላ ጌታችን አፉን ሶስት ጊዜ ሳመው፡፡ ያን ጊዜም ከመድኃኒዓለም ጣዕም ፍቅር
የተነሳ ነፍሱ ከስጋው ተለየች። # መዝ [115*6] በሰማያዊ መልአክት
በምድራውያን ስውራን ቅዱሳን ዘንድ ታላቅ ደስታ ሆነ # ህዳር 26 ቀን አረፈ፡፡
ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማህሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ
ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በፃዲቁ መቃብር ቀበሩት፡፡
አሜን የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከተ ረድኤት ምልጃቸው ከሁላችን
ጋር ይሁን።
✍ @EOTC2921 ✍
✍ @EOTC2921 ✍
✍ @EOTC2921 ✍
4 374
ሰላም የተዋህዶ ልጆች እንዴት ናችሁ? ዛሬ በቀዳሚተ ሰንበት የሚከበረው የፃዲቁ አባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም ክብረ በዓል ነው፡፡ የፃዲቁ በረከት ረድኤት ይደርብን፡፡ በሰላም ያሳደረ አምላክ በሰላም ያውለን፡፡ ሰላማችሁ ይብዛ!!!
✍❀ @EOTC2921 ❀✍
4 374
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክEOTC2921:
⛪ ✞ይትባረክ አምላክ አበዊነ✞ ⛪
አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮ ላስፈፀመን ለአባቶቻችን አምላክ ለኛ አባት ለድንግል ማርያም ልጅ ክብርና ምስጋና አምልኮና ውዳሴ ከአጽናፋ አለም እስከ አጽናፋ አለም በፈጠረው ፍጥረት ሁሉ የተከበረና የተመሰገነ ይሁን፡፡
ለሊቱን የያቆብ ሌሊት ያድርግልን
እነሆ በሰላም ያዋለን አምላክ በሰላም
ያሳድረን ዘንድ የርሱ ቅዱስ ፍቃድ
ይሁንልን አሜን አሜን አሜን✞✞✞
🍃🍃🍃🍂🍂🍃🍃
ወስብአት ለእግዚአብሔር
ወለወልዱቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
አሜን አሜን አሜን
🍃🍃🍃🍃🍃🍃
ለአገራችን ኢትዮጵያ ሰላም
🇪🇹🇪🇹ይስጥልን🇪🇹🇪🇹
አሜን
📚📚📚📚📚📚
✍ @EOTC2921 ✍
✍ @EOTC2921 ✍
✍ @EOTC2921 ✍
⛪🔐🌴🔐🌴🔐⛪
🍃🍃🍃🍃🍃🍃
4 374
ዳም ልጅ እንደሆነ ሲያስረዳ ዝቅ
ብሎ መለየቱም እስራኤል በኦሪት አሕዛብ በጣዖት
ተለያይተዋል፡፡ ዝቅ ብሎ መገናኘቱ ሁሉም በአንድ
ወንጌል የማመናቸው ምሳሌ ነው፡፡ ጌታችንም ሁለቱ
ከተገናኙበት ቦታ ተጠመቀ ሁላችሁንም አንድ
ላደርጋችሁ መጥቻለሁ ሲል ነው፡፡ ሌላው ምስጢር ግን
አዳምና ሔዋን ሕግ ተላልፈው ከገነት ተባረው ጸጋቸው
ተገፎ ራቁታቸውን ሆነው ከገነት ሲወጡ ዲያብሎስ
የጨለማ ግርዶሽ ጋርዶ ፍዳ አጽንቶባቸው አዳም ገብሩ
ለዲያብሎስ ፤ አዳም የዲያብሎስ ወንድ አገልጋይ ነው
፤ሔዋን አመቱ ለዲያብሎስ ፤ ሔዋን ደግሞ የዲያብሎስ
ሴት አገልጋይ ናት፡፡ ብላችሁ ስመ ግብርናችሁን ጽፋችሁ
ስጡኝ አላቸው፡፡ እነርሱም ፍዳ የሚያቀልላቸው
መስሏቸው እንዳላቸው አድርገው አዘጋጅተው ሰጡት
ዲያብሎስም ያንን የዕዳ ደብዳቤ አንዱን በሲዖል አንዱን
በዮርዳኖስ ወንዝ አኖረው፡፡ ዲያብሎስ በዮርዳኖስ ወንዝ
ያስቀመጠውን የዕዳ ደብዳቤ ጌታ በጥምቀቱ ጊዜ
ተረግጦት ስለነበር በተጠመቀ ጊዜ በጥምቀቱ
አጥፍቶታል፡፡
ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም በሰኞ ውዳሴ ማርያም ድርሰቱ
‹‹ ወሰጠጠ መጽሐፈ ዕዳሆሙ ለአዳም ወለሔዋን ፤
የአዳምንና የሔዋንን የዕዳ ደብዳቤያቸውን ቀደደላቸው››
ይላል፡፡(ቆላ 2፡13)፡፡በአዳምና በሔዋን አንጻር የእኛንም
የዕዳድበዳቤያችን ቀደደልን ፡፡
ጌታችን ወደ ዮሐንስ ሄዶ የተጠመቀበት ምክንያት
1. ትሕትናን ሲያስተምር ነው፡፡ ምነው ጌታ ፈጣሪ፤
እግዚእ ሲሆን ወደ ትሑት ዮሐንስ ሄደ ቢሉ ሥጋ
መልበሱ ለትሕትና ነውና፡፡ ይህ ባይሆን ዛሬ
ነገሥታት ቀሳውስትን ከቤታችን መጥታችሁ
አጥምቁን አቁርቡን ይሉ ነበርና፡፡
2. ትንቢቱና ምሳሌውን ለመፈጸም (ት.ሕዝ 36፡20 ፤ መዝ113፡3-5)
ጌታን ለምን በ፴ ዘመኑ ተጠመቀ?
ሰው ሁሉ በ፴ ዘመኑ ሕገ ነፍስን ይሠራልና
ለአብነትአንደም ቅስና ምንኩስና በ፴ ዘመን
ይገባል ሲል ነው፡፡
ቀጥሎም አዳምን የ፴ ዘመን ጎልማሳ አድርጎ
ፈጥሮት የሰጠውን ልጅነት አስወስዶ ነበርና
የአዳምን ልጅነት ለመመለስ በ፴ ዘመኑ ተጠመቀ። ጌታን ተጠምቆ ከውኃ ሲወጣ የሚከተሉት ተአምራት
ተፈጽመዋል
1. ሰማያት ተከፈቱ፡- ጌታችን አምላካችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዩሐንስ
በፈለገ ዮርዳኖስ ተጠምቆ ከውኃው ሲወጣ
“ወናሁ ተርኀወ ሰማይ ወርእየ መንፈሰ
እግዚአብሔር እንዘ ይወርድ ከመ ርግብ
ወነበረ ላዕሌሁ ፤ሰማይ ተከፍቶ መንፈስ
ቅዱስ በአምሳለ ርግብ በራሱ ላይ
ሲቀመጥበት መጥምቁ ዩሐንስ አየ” አሁን
ሰማይ የሚዘጋና የሚከፈት ሁኖ ሳይሆን ታይቶ
የማይታወቅ ታላቅ ምሥጢር ተገለጠ፡፡
ማለትም የልዑል እግዚአብሔር የሦስትነቱ
ምሥጢር ጎልቶ ወጣ ለማለት ነው፡፡
2. መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ
ላይ ተቀመጠ
3. እግዚአብሔር አብ ከላይ ‹‹ መጽአ ቃል
እምደመና ዘይብል ዝንቱ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ
ዘአፈቅር ወሎቱ ስምእዎ፤ ለተዋሕዶ
የመረጥሁት በእርሱ ሕልውና በመሆን
ልመለክበት የወደደሁት ልጄ ይህ
ነው›› (ማቴ 3፡17) በማለት የባሕርይ
አምላክነቱን መስክሯል፡፡ወንጌላውያኑ በዚህ
ቃል ምሥጢረ ሥላሴን በግልጽ
አስተምረውናል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን በውኃ
ተጠመቀ?
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በውኃ
ተጠምቋል ጥምቀቱ በውኃ የሆነበት ምክንያት
‹‹ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ
ወጣ ›› ይላል (ማቴ 3፡16)፡፡ በቃሉም እንዲህ
አስተማረ ‹‹ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ
ካልተወለደ በቀር ወደ መንግስተ ሰማያ ይገባ
ዘንድ አይቻልም›› (ዮሐ 3፡5)፡፡ በቅዱሳን
ነቢያትም ሲነገር የነበረ ትንቢት ነበር‹‹ጥሩ
ውኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ
ከእርኩሳችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ
አጠራችኋለሁ፡፡( ት.ሕዝ 36፡25)የሚል
አስቀድሞ ትንቢት ተነግሮ ነበር፡፡
ውኃ የሰውነትን ቆሻሻ እንደሚያጠራ ጥምቀትም
የነፍስን ኃጢአት ያጠራልና፡፡ አንድም ውኃ ጽንፍ
እስከ ጽንፍ ይፈሳል ጥምቀትም ጽንፍ እስከ ጽንፍ
ይከናወናልና፡፡ አንድም ውኃ በዙፋኑ ካለ ንጉሥ
አንስቶ በዐደባባይ እስከ አለ ችግረኛ ሁሉ
የተሰጠ በሁሉ ቤት የሚገኝ ነው፡፡ ጥምቀትም
የተሰራው ለሰው ሁሉ ነው፡፡
ጎሳ፣ጎጥ፣ቀለም፣ደሀ፣ሀብታም አይለይበትም፡፡
አንድም በውኃ የታጠበ ልብስ ጥንካሬ
እንደሚያገኝ ምእመናንም በውኃ ተጠምቀው
ገድልና ትሩፋት እየሠሩ በጥምቀት ባገኙት ኃይል
ባላጋራቸውን ዲያብሎስን ድል ይነሱታል፡፡
አንድም የራሔል ለይስሐቅ መታጨት በውኃ
ምክንያ ሁኗል፡፡ (ዘፍ 24፡10-27) መንፈሳዊ
መታጨትም (ለእግዚአብሔር መንግስት) በውኃ
(በጥምቀት) ሁኗል፡፡
ጌታችን በማር በወተት ጥምቀቱን ማድረግ
ሲቻለው በውኃ ያደረገበት ምክንያት ማርና ወተት
በሁሉ አይገኝምና ሁሉም በሚያገኘው
አደረገው፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያትም ከአምላካቸው በቃልና በተግባር
የተማሩትን በሥራ ሲተገብሩ ሕዝቡን በውኃ
አጥምቀዋል፡፡ ለጥምቀት የውኃ አስፈላጊነት በፍትሕ
መንፈሳዊ አንቀጽ3 ላይ ተደንግጓል፡፡ቅድስት ቤተ
ክርስቲያናችን የጥምቀት በዓልን የምታከበረው የጌታችን
የማዳኑን ምስጢር ለማዘከርና ለመመስከርም ነው፡፡
አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ “የጠበሉን መረጨት አይተው
በቀድሞ ዘመን ወደ ሀገራችን መጥተው የነበሩ
ኢየሱሳውያን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ይህን
ምትፈጽመው ጌታችን ለእኛ ብሎ ያሳየውን ትሕትና
ለመመሥከር ለምእመናን የጌታችን በረከተ ጥምቀት
ለማሳተፍ እንጂ የተጠመቁትን ምእመናን እመለሰች
በየዓመቱ አታጠመቅም” ብለዋል፡፡( የኢትዮጵያ ቤተ
ክርስቲያን ታሪክ ገጽ123)
አምላካችን ከረከተ ጥምቀቱን ያደለ!!!
✍ @EOTC2921 ✍
✍ @EOTC2921 ✍
✍ @EOTC2921 ✍
4 374
ከዳነ የማይድነው ወይም የሚፈረድበት ደግሞ
ፈያላመነና ያለተጠመቀው ጭምር
መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
ዮሐ 10፡1 ፣ ዮሐ 13፡9 ስለዚህ ግድ ለመዳን ማመን
ብቻ አይጠቅምም መጠመቅም ያሻል፡፡
2. ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ እንወለዳለን- ጌታችን
ምስጢረ ጥምቀትን በትምህርት ለኒቆዲሞስ በሥጋ
ከወላጆቻችን እንደተወለድን ሁሉ ‹‹ከውሃና ከመንፈስ
ዳግም ልትወለዱ ግድ አላችሁ›› ብሎ አስረድቶታል፡፡ ዮሐ
3፡3 የሐነስ መጥምቅም ፈሪሳውያንን እና ሰዱቃውያንን
ደገሰጻቸው በኋላ ‹‹እኔ የንስሐ ጥምቀት አጠምቃችኋለሁ
የጫማውን ጠፈር ልፈታ የማይገባኝ ከኔ በኋላ
የሚመጣው ግን እርሱ በመንፈስ ቀዱስ አሳትነት
ያጠምቃችኋል፡፡›› ብሎ ግልጽ ቃል ተናግሯል፡፡ ሜቴ 3፡
11 ለዚህ ነው በመንፈስ ቅዱስ ዳግም ከእግዚአብሔር
እንወለዳለን ያልነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም
ለመንፈስ ልጁ ለቲቶ ‹‹የመድኃቲታችን የእግዚእብሔር
ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ እንደምሕረቱ
መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆን መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ
በመታደስ አዳነን›› ቲቶ3፡5 ብሎ ድንቅ ቃል ተናግሯል፡፡
ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች እንባላለን፡፡ እናንተን
ግን ልጆቼ ብያችኋለሁ ባሮች አይደላችሁም እንዳለ
ለነቢያት ያልታደለ የልጅነት ክብር በጥምቀት እናገኛለን፡፡
3. ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞቱን በሚመስል ሞት ሞተን
ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ እንነሳለን፡- ይህ ከጌታችን
ጋር በጥምቀት ከሞቱና ከትንሣኤው ጋር እንሳተፋለን
ማለት ነው፡፡ ሞቱን በሚመስል ሞት እሞታለን ሲል
ጌታችን አንድ ጊዜ ሞቶ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው
እንደለየ እኛም በጥምቀት ከኃጢአት እንለያለን ማለት
ነው፡፡
4. የኃጢአት ሥርየት እናገኝበታለን፡- ከጥምቀት በፊት ያለ
ኃጢአት በጥምቀት ከጥምቀት በኋላ ያለ ኃጢአት ደግሞ
በሥጋወደሙ እንደሚሠሬ ተጽፏል፡፡ በዚህም ሰው
ከኃጢአት በመለየቱ በጸጋም ከእግዚአብሔር በመወለዱ
የመንግሥተ ሰማይ ወራሽ ይሆናል፡፡ ሕዝ 36፡25
ሐዋርያትም ‹‹ኃጢአታችሁ ይሠረይ ዘንድ ንሥሐ ግቡ
በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ስም
ተጠመቁ›› ሐዋ 2፡38 በማለት አስተምረዋል፡፡ ከእነርሱ
በኋላ የተነሱት ሠለስቱ ምዕትም ኃጢአት በሚሠረይባት
በአንዲት ጥምቀት እናምናለን ብለው በጸሎት ሃይማኖት
ጽፈውልናል፡፡
1. በጥምቀት የቤተክርስቲያን አባል እንሆናለን፡- በዘመነ
ኦሪት የእግዚአብሔር ሕዝብ የአብርሃም ልጆች ለመባል
ግዝረት ሃይማኖታዊ ግዴታ ነበር፡፡ ጥምቀትም በክርስቶስ
ለሚያምኑ ሁሉ ከቅድስት ቤተክርስቲያ የሚገኝ ጸጋ
ተካፋይ ከማድረጉም በላይ ራሱን ተጠማቂውን
የእግዚአብሔር ልጅ ያሰኘዋል፡፡ ቆላ 2፡11 በዚህ
የክርስቶስ ቤተሰቦች የቤተክርስቲያን አባል እንሆናለን፡፡
የጥምቀት አመሰራረት በሐዲስ ኪዳን
ጥምቀት በሐዲስ ኪዳን የመሠረተው የሁሉ መሠረትና
መሥራች የሆነው ጌታችንና አምላካችን መክኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሲመሠርተውም በ3 መልኩ ነው፡፡
ሀ. በትምህርት፡- ለኒቆዲሞስ በማስተማር ዮሐ 3፡5
ለ. በትእዛዝ፡- ሐዋርያትን መርጦ ካጸናቸው በኋላ እርሱ ወደ ሰማይ
እንዳረገ ዓለምን ዞረው ወንጌልን እንዲሰብኩ አሕዛብንና
ያላመኑትን ሁሉ ‹‹በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጉ›› ብሎ በማቴ
28፡19 በማዘዝ መሥርቶታል፡፡
ሐ. በተግባር፡- እኛ ክርስቲያኖች ራሱ አምላክ ከኃጢአት በቀር
ሳያደርገው ለኛ ለልጆቹ አድርጉ ያለን አንዳች ነገር የለም፡፡
ተጠምቆ ተጠመቁ ፣ ጹሞ ጹሙ ፣ መከራ ተቀብሎ መከራ
ተቀበሉ፡፡ ስለዚህ ጥምቀቱንም በ30 ዘመኑ በእደ ዮሐንስ
በባሕረ ዮርዳኖስ ተጠምቆ በተግባር መሥርቶአልና፡፡
በምሥጢረ ጥምቀት ሙሉ ጸጋ የተሰጠው ግን በበዓለ
ሃምሳ ለሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ
መውረድ በኋላ ነው፡፡
✍የጌታ ጥምቀት
ጌታ መቼ ተጠመቀ?
ከእመቤታችን በተወለደ በ30 ዘመኑ በዘመነ ሉቃስ ጥር 11ቀን ማክሰኞ ሌሊት 10 ሰዓት፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን መጠመቅ ለምን አስፈለገው?
1. ጥምቀት ለሚያስፈልገን ለእኛ አርአያ ለመሆን
ነው፡- እርሱ ተጠምቆ ተጠመቁ ባይለን ኑሮ
ጥምቀት አያስፈልግም፡፡ አስፈላጊ ቢሆንማ ጌታ
ራሱ ተጠምቆ አብነት በሆነን ነበር እንዳይሉ
መናፍቃን ምክንያ አሳጣቸው፡፡ሊቁ ቅዱስ
ዩሐንስም” ወአርኃወ ለነ አንቀጸ ጥምቀት ከመ
ንጠመቅ፤ እንጠመቅ ዘንድ የጥምቀትን በር
ከፈተልን”ሲል የጥምቀትን ምስጢር ያስረዳናል፡፡
2. ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ፡- ‹‹አቤቱ ውኃዎች አዩህ
ውኃዎች አይተውህ ፈሩ ጥልቆችም
ተነዋወጡ ወኃዎችም ጮሁ ደመኖችም
ድምጽን ሰጡ ፍላጾችም ውጡ ›› (መዝ77፡
16-17) የሚል ትንቢት ነበርና ይህ
እንዲፈጸም፡፡
3. በዮርዳኖስ ውስጥ የነበረውን የዕዳ ደብዳቤ
ለመደምሰስ( ሰኞ ውዳሴ ማርያም)
4. አንድነትና ሦስትነቱን ለማስረዳት፡- ከዚህ በፊት
የሥላሴ ሦስትነት በግልጽ አይታወቅም ነበር፡፡
ጌታ በዮርዳኖስ በሚጠመቅበት ጊዜ ግን
ምሥጢረ ሥላሴ ግልጽ ሁኖ አብ በደመና ሁኖ
የምወደው ልጄ ይህ ነው በማለቱ የወልድ
አባት መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ
ሕይወቱ መሆኑ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ
ተቀምጦ ሲታይ ወልድ በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ
ሲጠመቅ ታየ
✍ጌታችን ለምን በባሕረ ዮርዳኖስ ተጠመቀ?
፩. ትንቢቱና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ጌታችን
አምላካቸን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ
ዩሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ እንደሚጠመቅ ከልደተ
ክርስቶስ በፊት በአንድ ሺህ ዓመተ ዓለም ነቢየ
እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት የዘመራቸው የትንቢት
መዝሙሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ትንቢቱ፡
“ቃለ እግዚአብሔር ላዕለ ማያት አምላከ ስብሐት
አንጎድጎደ እግዚአብሔር ላዕለ ማያት ብዙኀ
፤የእግዚአብሔር ቃል በውኃዎች ላይ ነው፡የተመሰገነ
አምላክ ድምጹን አሰማ እግዚአብሔር በብዙ ውኃዎች
ላይ ነው፡፡”(መዝ 28 ፤3-4)
“ርእዩከ ማያት እግዚኦ ርእዩከ ማያት ወፈርሁ ደንገጹ
ቀላያተ ማያት ወድምጸ ማያቲሆሙ ፤አቤቱ ውኃዎች
አዩህ ውኃዎች አዩህና ፈሩህ፤የውኃዎች ጥልቆች
ደነገጡ ማዕበላቸውም ተሰማ”(መዝ7፤6)
“ በእንተዝ እዜከረከ እግዚኦ በምድረ ዮርዳኖስ
በአርሞንኤም በደብር ንዑስ ቀላይ ለቀላ ትጼውኦ
በቃለ አስራቢከ፤ሥለዚህ በዮርዳኖስ ምድር
በአርሞንኤምም በታናሹ ኮረብታ አስብሃለሁ ………
(መዝ 41፤6-7)
‹‹ ባሕርኒ ርእየት ወጎየት ወዮርዳኖስኒ ገብአ
ድኀሬሁ አድባር አንፈርዐጹ ከመ ሐረጊት ፤ ባሕርአየች
ሸሸችም ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ ተራሮች እንደ
ኮርማዎች ኮረብታዎችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ፡፡ አንቺ
ባሕር የሸሸሽ ዮርዳኖስም ወደ ኋላሽ የተመለሽ ምን
ሆናችኋል? ›› በማለት ነብዩ አስፍቶና አጉልቶ
ዘምሮአል፡፡ ይላል ትንቢት ስለነበር ጌታችን ከሌሎች
አፍላጋት ሁሉ መርጦ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ፡፡ መዝ113፡3-5
ምሳሌው፡– አባታችን አብርሃም ነገሥተ ኮሎዶ ጎሞርን
ድል አድርጎ ከገንዘቡ ዐሥራት በኩራት በማውጣት
ዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሮ ወደ ካህኑ መልከጼዴቅ ሲሄድ
ኅብስተ አኮቴት ጽዋዐ በረከት ይዞ ተቀብሎታል፡፡
አብርሃም የምእመናን የዮርዳኖስ ወንዝ የጥምቀት ካህኑ
መልከጼዴቅ የቀሳውስት ፤ ኅብስተ በረከት ጽዋዐ አኮቴት
የሥጋ ወደሙ ምሳሌ ነው(ዘፍ 14፡17-20፤ ዕብ 7፡1-8)
ዮርዳኖስ አንድ ወንዝ ሲሆን ዝቅ ብሎ በዮር እና በዳኖስ
ተለይተዋል፡፡ ዮር በእስራኤል በኩል ያለው ሲሆን ዳኖስ
በአሕዛብ በኩል ያለው ነው፡፡ዝቅ ብሎ ደግሞ ሁለቱም
ተገናኝተዋል፡፡ ሁለቱ በተገናኙበት ቦታ ጌታ ተጠምቋል፡፡
ይህ ምሳሌ ነው፡፡ ዮርዳኖስ ከላይ አንድ እንደሆነ ሁሉም
የሰው ዘር የአንድ የአ
4 374
ምሥጢረ ተክሊል
5) በአንድ ቀን የሚሰጡ ምሥጢራት
· ምሥጢረ ጥምቀት
·ምሥጢረ ሜሮን
· ምሥጢረ ቁርባን
እነዚህ ምሥጢራት በቤተክርሰቲያን ውስጥ በሚታይ
ሥትዓት የማይታዩ ጸጋን ሥልጣነ ክህነት ባላቸው አባቶች
የሚሰጡ መንፈሳዊ ሀብት ናቸው፡፡ ከሰው ላጅ አስተሳሰብ
በላይ ስለሆኑ እግዚአብሔር ካልገለጸልን በቀር መርምረን
አንደርስበትም ከፍፃሜያቸው አንዘልቅም፡፡ በዚህም
ሥርዓት ዲያቆናት በአገልግሎት ሲራዱ ቀሳውስት ደግሞ
ሜሮን ከማፍላትና ክህነትን ከመስጠት ውጭ ሁሉን
ይፈጽማሉ፡፡ ጳጳሳት ሁሉን ምሥጢር በመፈጸም
ያገለግላሉ፡፡
ምሥጢረ ጥምቀት
ጥምቀት፡- ማለት ‹‹አጥመቀ›› ከሚለው የግእዝ ግሥ
የወጣ ሲሆ ትርጉሙም ማጥመቅ ፣ መጠመቅ ማለት
ነው፡፡ ይኸውም ከራስ ፀጉር እስደ እግር ጥፍር ድረስ
በተጸለየበት ውሃ /ማየ ሕይወት ወይም ማየ ገንቦ/
ውስጥ በሥላሴ ስም መጥለቅ መዘፈቅ ማለት ነው፡፡
ምሥጢረ ጥምቀት ሌሎች ምሥጢራትን ለመፈጸም
የመግቢያ በር ነው፡፡ ወደ ሐዲስ ኪዳን ጥምቀት
ከመሔዳችን በፊት ጥምቀት በብሉይ ኪዳን ምን
እንደሚመስል እንመልከት::
ጥምቀት በብሉይ ኪዳን
በብሉይ ኪዳን ጥምቀት በውሃ በታጠብ ፣ መጥለቅና
መንፃት ነበር፡፡ በብሉይ ኪዳን በዓል ሲከበር በዓሉን
ለማክበር የሚሰበሰበው ሕዝብ በሙሉ በውሃ በመረጨት
ለበዓሉ ዝግጅት የሚፈልጉ ዕቃዎችን ሁሉ በውሃ
መታጠብና መንፃት ነበረባቸው፡፡ ዘሌ 6፡27
በብሉይ ኪዳን ሰውን ወይም ዕቃን ያረክሳሱ ተብሎ
የሚታመንባቸው ነገሮች ነበሩ ለምሳሌ፡- ለመሥዋዕት
የታረደችውን ጊደር ደም በጣቱ የነካ የዝግባ እንጨትና
ግምጃ ወስዶ የጊደሪቱን ሥጋና አጥንት ለሚቃጠልበት
የጣለ ካህን ልብሱንና ገላውን በውሃ ካልታጠበ ወደ ሰፈር
መግባት አይፈቀድለትም ነበር፡፡ የሞተ ሰው አስከሬን የነካ
በሞተበተ ድንኳን ውስጥ የገባ ሁሉ እንደርኩስ የቆጠር
ስለነበር በውሃ መታጠብና መንፃት የተለመደ ሕግ ነበር፡፡
ዘፀ 19፡18 ፣ መዝ 50፡51፡፡ ከብሉይ ኪዳን ውጭ የነበረ
ሰው የኦሪቱን አምነት ሲቀበል ከማኅበረ አይሁድ
ከመግባቱ በፊት መገረዝና መታጠብ ገድ ነበር፡፡
ከተገረዘና ከታጠበ በኋላ እንደ አይሁድ ሥርዓት መባዕ
ማቅረብና ከማኅበሩ ጋር አንድ መሆን ይፈቀድለታል፡፡
ከሌላው እምነት ወከ ይሁዳነት ሊገባም ዕለት
እንደተወለደ ሕፃን ይቆጠር እንደነበር መጻሕፍት
ይነግሩናል፡፡ እራሱን ከኢግዙርነት መለየት ከመቃብር
እንደመውጣት ነው ተብሎም ፈይታመን ነበር፡፡
ሌላው የብሉይ ኪዳን ጥምቀት የዮሐንስ ጥምቀት ነው፡፡
የሐንስ የንስሐ ጥምቀትን ያጠምቅ ነበር፡፡ ማር 1፡4
የዮሐንስ ጥምቀት አማኞችን ለክርሰቶስ ጥምቀት
የሚያዘጋጅ የክርስቶስን ጥምቀት ለመቀበልና
በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ባለቤት ለመሆ
የሚያበቃ ነበር፡፡ ሜቴ 3፡11 የሚያጠምቅበትም ዓለማ
ሰዎችን ከኃጢአት ወደ ሥርየት ከአምልከኮተ ጣኦት ወደ
አምልኮተ እግዚአብሔር መመለስና ሥርየተ ኃጢአት
አግኝቶ ከማሕበረ ጻድቃን ጋር አንድ መሆንን ያሳያል፡፡
በብሉይ ኪዳን ይፈጸም የነበረው ጥምቀት ምንም እንኳን
ምሳሌነት ቢኖረውም በሐዲስ ኪዳን እንደሚፈጸመው
ጥምቀት ምሥጢር አልነበረም፡፡ የብሉይ ኪዳን ጥምቀት
ፈየመንጻት ጥምቀት ነበር እንጂ፡፡
ዮሐ 2፡6
የጥምቀት ምሳሌ በብሉይ ኪዳን
ስለ ጥምቀት አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን ብዙ ምሳሌ
ተመስሏለወ ትንቢትም ተነግሯል፡፡ ከምሳሌዎቹም
ጥቂቶቹን ስንመለከት፡-
1ኛ የኖህ መርከብ ዘፍ 7፡17 1ኛ ጴጥ 3፡20 መርከቧ
የጥምቀት ምሳሌ ስትሆን በመርከቧ ተጠልለው የዳኑት
ሰዎች የአማንያን ምሳሌ በንፍር ውሃ የጠፉት የኢአማንያን
ምሳሌ ናቸው፡፡ በመርከብ ውስጥ የነበሩት እንደዳኑ
በጥምቀት አምነው የተጠመቁ ሁሉ ከሲኦል ባህር
ከመስጠም ሲድኑ ከመርከቧ ውጭ የነበሩት ሰጥመው
እንደጠፉ በጥምቀት ባለማመን ጸንተው ያልተጠመቁም
በሲኦል ባህር ሰጥመው ይቀራሉ፡፡
2ኛ ግዝረት፡- ዘፍ 17፡14 ግዝረት የተገረዙ ሁሉ
የአብርሃም ልጆች ይባሉ እንደነበር ያለተገረዙ ሁሉ ደግሞ
ከአብርሃም ልጅነት የወጡ ነበር፡፡ አሁንም የተጠመቀ ሁሉ
የእግዚአብሔር ልጅ በመባል ሲኖር ያልተጠመቀ ደግሞ
ከእግዚአብሔር ልጅነት ይለያሉና ግዝረት ለጥምቀት
ምሳሌ ሆነ፡፡
3ኛ እስራኤላውያን ባህረ ኤርትራን መሻገራቸው፡-
እስራኤላውያኑ የክርስቲያኖች ምሳሌ ግብፃውያን
የአጋንንት ምሳሌ ባህረ ኤርትራን መሻገራቸው የጥምቀት
ምሳሌ ነው፡፡ እስራኤላውያን በግዞት ከነበሩበት ከግብጽ
ባርነት ነፃ የወጡት ባህረ ኤርትራን ከተሻገሩ በኋላ ነው፡፡
ባህረ ኤርትራ ለፈርኦንና ለሠራዊቱ ሞትን ሲያስከትል
ለእስራኤላውያን ግን ሕይወት ፣ ደስታንና ነፃነትን
አጎናጽፏቸዋል፡፡ ክርስቲያኖችም በጥምቀት በርኩሳን
አጋንንት ከመገዛት ከዘለዓለም ሞት ነፃ ወጥተዋል
የኤርትራን ባህር ለፈርኦንና ለሠራዊቱ ድል መንሻ እንደሆነ
በጥምቀትም አጋንንት ድል ሆነዋል፡፡
4ኛ እስራኤላውያን በኢያሱ መሪነት ፈለገ ዮርዳኖስን
መሻገራቸው ኢያሱ 4፡1-9 እስራኤላውያን ዮርዳኖስን
ተሸግረው ከነአን እንደገቡ ክርስቲያኖችም ተጠምቀው
ወደ እርሳቸው ገነት መንግሥተ ሰማያት ይገባሉና፡፡
5ኛ አብርሃም ፈለገ ዮርዳኖስን ተሸግሮ ከመልከጼዴቅ
ኅብስተ አኮቴት ጽዋዓ በረከት መቀበሉ ዘፍ 14፡17
-አብርሃም የምእመናን ምሳሌ
-መልከጼዴቅ የክርሰቶስ /የካህናት/ ምሳሌ
-ሕብስተ አኮቴት ጽዋዓ በረከት የክርስቶስ ሥጋወደም
ምሳሌ
-ዮርዳኖስ የጥምቀት ምሳሌ
አብርሃም ዮረዳኖስን ከተሻገረ በኋላ ህብስተ አኮቴት
ጽዋዕ በረከት እንደተቀበለ እኛም ከተጠመቅን በኋላ
የጌታን ሥጋና ደም እንቀበላለንና፡፡
የጥምቀት ትንቢት በብሉይ ኪዳን
1ኛ ‹‹ጥሩ ውሃ እረጫችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ››
ሕዝ 36፡25 ጥሩ ውሃ የተባለው የምንጠመቅበት ውሃ
ነው፡፡ በንፁህ ውሃ የታጠበ ነገር ደዕድፈቱ እነደሚጠራ
ሰውም አምኖ ሲጠመቅ ኃጢአቱ ይሠረይለታልና፡፡ ሌላው
2ኛ ‹‹ምህረትን ፈየወዳልና… ኃጢአታችንንም በባህር
ጥልቅ ይጥለዋል›› ሚክ 7፡19 በጥልቅ ባህር
የተመሰለው ጥምቀት ነው፡፡ በባህር ውስጥ የገባ ፍፁም
እንደማይታይ በጥምቀትም የተሠረየ ኃጢአት ፈጽሞ
አያስቀጣም በፍዳ አያሲይዝምና አንድም ከባህር ውስጥ
በክንፋቸው የሚበሩ በእግራቸው የሚሄዱ በደረታቸው
የሚሳቡ ተገኝገዋል፡፡
በጥምቀትም አንድ ልጅነት አግኝተው በመንፈስቅዱስ
የጸጋ ስጦታዎች አማካኝነት ለተለያ ደረጃዎች
በቅተዋልና፡- በክንፍ የሚበሩ የሰማዕታት ምሳሌ ፣
በእግራቸው የሚራመዱ በገዳም ተወስነው የሚኖሩ
መነኮሳት ምሳሌ ፣ በደረታቸው የሚሳቡ ደግሞ በዓለም
በሕግ የሚኖሩ የክርስቲያኖች ምሳሌ ናቸው፡፡
ጥምቀት ለምን ምሥጢር ተባለ?
ጥምቀት ምስጢር የተባለበት ምክንያት ከላይ
እንደጠቀስነው በሚታይና በሚሰማ አገልግሎት የማይታይ
ረቂቅ ጸጋ ስለሚሰጥበትና ላመኑት ብቻ የሚፈጸም
በመሆኑ ውሃው ተለውጦ ከጌታ ጎን የወጣውን ውሃ /ማየ
ገቦ/ ሲሆን የምንጠመቅበት ገንዳ ከግሞ ማኅጸነ
ዮርዳኖስ ሲሆን አለመታየቱ ከመምህር ተምሮ በልቡና
በማመን የሚታወቅ በመሆኑ አንድም እግዚአብሔር
የገለጠልንን ያህል ካሆነ በስተቀር ስለማነውቀው
ምሥጢር ተባለ፡፡
✍የጥምቀት አስፈላጊነት /ጥቅም/
1. ድህነት እናገኛለን፡- ማር16፡16 ‹‹ያመነ የተጠመቀ
ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል›› ይላል፡፡ ይህን
ይይዙና ‹‹ያላመነ›› እንጂ ‹‹ያልተጠመቀ›› ይፈረድበታል
አይልም ስለዚህ አለማመን አንጂ አለመጠመቅ
አያስፈርድም ይላሉ፡፡ ይህ ግን አይደለም ባይጻፍም
በውስጡ ‹‹ያልተጠመቀ›› የሚለው ቃል እንዳለ
እናስተውል፡፡ ምክንያቱም ከፊት ያድናል ያለው ያመነ ብቻ
ሳይሆን የተጠመቀም ነው የሚለው፡ታዲያ ያመነና
የተጠመቀ
4 374
✍ @EOTC2921 ✍
✍ @EOTC2921 ✍
✍ @EOTC2921 ✍
☞☞☞ምዕራፍ ፩
✍✞ምስጢራተ ቤተክርስቲያን✞✍
ምሥጢር ማለት ምን ማለት ነው?
ምሥጢር ፡- ‹‹አመሥጠረ›› አራቀቀ ካለው የግእዝ ግሥ
የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ረቂቅ የማይታይ ፣ ኅቡዕ ፣
ሽሽግ ማለት ነው፡፡ አንድም
ምሥጢር ፡- በመንፈሳዊ ትርጉሙ ሲታይ የሰው ልጅ በራሱ
ጥበብ መርምሮ ሊደርስበትና ሊያውቀው የማይችል
አምላካዊ ግብር መንፈሳዊ ረቅቅ የማይታይ የሚደንቅ
ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ 5ቱ አእማደ ቤተክርስቲያን
ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን በእምነት ካልሆነ በቀር
በሥጋዊ ጥበብ ሊቀበሉት አይችሉም ከሰው አእምሮ
በላይ ናቸውና፡፡ ለዚህም ግልጽ የሆኑ ቃላትን በመጽሐፍ
ቅዱስ መመልከት ይቻላል፡፡
ለምሳሌ ጌታችን በዮሐ 6፡56 ላይ‹‹ ሥጋዬን የበላ ከሜን
የጠጣ የዘለአለም ሕይወት አለው›› ብ የቅዱስ ቁርባንን
ምሥጢርናት ሲያስተምራቸው ብዙዎች ወደኋላ
እንደተመለሱ ቅጥር 66 ላይ ይናገራል፡፡ እንዲሁም አሉ
‹‹ ይህ ነገር የሚያስጨንቅ ንግግር ነው ማን ሊሰማው
ይችላል?›› ዮሐ 6፡60፡፡ በሌላም ቦታ ላይ በዮሐ 3፡3
ላይ ‹‹ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሕርን
መንግሥት ሊያይ አይችልም›› ብሎ ለኒቆዲሞስ
ምሥጢረ ጥምቀትን ሲሰብከው ይህ ረቂቅ የሆበት
ኒቆዲሞስ የመለሰው መልስ ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ
እንዴት ይወለዳል?›› ነበር ያለው፡፡ ጌታ በእምነት
ሊቀበሉት ስለሚችል ምሥጢር ሲነግረው እሱ ግን ስለ
ምድራዊ /ሥጋዊ/ ያስባል ያ መንፈሳዊ ይህ ሥጋዊ
ከዛም አለው ነፋስ ሲነፍስ ታያለህ ከወዴት እንደሚመጣ
ግን አታውቅም ዳግም መወለድም እንዲሁ ነው ብሎ
ረቅቅነቱን ነግሮታል፡፡ ስለዚሀ ሁሉም ምሥጢራት ከኛ
አእምሮ በላይ ስለሆኑ በእምነት ብቻ መቀበል አለብን
ያልነው ለዚህ ነው፡፡ በዳዊት ትርጓሜ ላይም ‹‹ በሬ
ቀንበር ከተጫነበት ያ ቀንበር ሲያስጨንቀው እንደሚውል
እንዲሁም ባሕርየ ሥላሴን ወይም የእግዚአብሔርን ሥራ
ምሥጢር እመረምራለሁ የሚል ሰውም እንዲሁ ሲጨነቅ
ይኖራል›› ይላል፡፡ ስለዚሀም ሠለስቱ ምዕት ያለመመርመር
እንመን ያሉት፡፡ እኛ ሥጋውያ ሰዎች እንኳን ምሥጢራተ
እግዚአብሔርን ልንመረምርና ልናውቅ ቀርቶ በውስጣችን
ስላለች ነፍስ እንኳን ምን እንደሆች ግብሯን ጠባይዋን
ባሕርይዋን መርምረን አልደረስንበትም፡፡ በውስጣችን
ያለችን ነፍስ መርምረን ካለደረስንባት ረቂቅ የሆነውን
የእግዚአብሔርን ምሥጢራትማ እንዴት? ስለዚህ
እግዚአብሔር ያሳወቀንን
/የገለጠልንን/ ያህል መረዳት እንጂ መመርመር ጉዳት
እዳለው ከላይ የጠቀስናቸው ያስረዱናል፡፡
ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን በሚታይ መንፈሳዊ አገልግሎት
የማይታይ መንፈሳዊ ጸጋና በረከት የምናገኝባቸው
የዘለአለም ሕይወት የሚያሰጡን መንፈሳዊ መሣሪያዊች
ናቸው፡፡ ይኸውም ለዘላለም ተሰውሮ የነበረ አሁን በሐዲስ
ኪዳን በወንጌል የተገለጠ ከእግዚአብሔር የወጣ የእውነት
ቃል /ትምህርት/ እና እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆኖ
ድኅነትን ለዓለም ሁሉ ማቅረቡ ነው፡፡ ሮሜ 16፡26 ፣ ኤፌ
1፡9
የምሥጢር አከፋፈል
ምሥጢር በ3 ዓይነት አከፋፈል ይከፈላል፡፡
1. ጊዜያዊና ፣ ዘለአለማዊ
ጊዜያዊ ምሥጢር፡- ብዙዎች የማፈያውቁት ጥቂቶች ብቻ
የሚያውቁት ጊዜሊፈታው የሚችል ማለት ነው፡፡
ዘለአለማዊ ምሥጢር፡- ከእግዚአብሔር በቀር በማንም
የማይታወቅ፡፡ ለምሳሌ 5ቱ አእማደ ቤተክርስቲያን
ስንመለከት በእምነት ብቻ እግዚአብሔር ያሳወቀንን ያህል
ስለምንረዳ ዘላለማዊ ምስጢር ተባሉ፡፡ ይህንንም
አባቶች፡- ‹‹ የገናናነቱን ነገር ለመመርመር የነቢያትና
የሐዋርያት አንደበት አይታቻለቸውም፡፡ ስለዚህ አንመርምር
ጥልቅነቱንም አንጠናቀቅ›› አባ ሕርያቆስ በማለት
ያስረዱናል፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያም ‹‹
የእግዚአብሔርን የጌትነቱን ነገር በነገር ትችት መመርመር
ድፍረትም ኃጢአትም ነው›› የሚል ቃል ተናግሯል፡፡
1. የፈጣሪና ፣ የፍጡራን
የፈጣሪ ምሥጢር፡- ተምረው ተመራምረው የማይደረስበት
በእምነት ብቻ የሚገለጥ ምሥጢር ነው፡፡ ፍጡር
ስለፈጣሪ ሊያውቅ የሚችለው የተገለጠለት ያህል ብቻ
ነውና፡፡ ይህ ምሥጢር በተለይ የተገለጠው በሐዲስ ኪዳን
ነው፡፡ ይህም ቢሆ ግን እንደየብቃታችን እንጂ ለሁሉም
እኩል አይገለጥም፡፡ ሮሜ 16፡25
የፍጡራን ምሥጢር፡
- 1ኛ የሰዎች ፤በሰዎች መካከል በድብቅ ለተወሰነ ጊዜ
በምጢር ከቆየ በኋላ የሚገለጥ ነው፡፡
- 2ኛ የመላዕክት ምሥጢር፤ መላእክት ረቅቃን ከመሆቸው
የተነሳ የሰው ላጅ ስለመላእክት የሚያውቀው በመጸፍ
የተገለጠለትን ብቻ ነው፡፡ ቅዱሳን እንኳን ሲበቁ
ምሥጢራቸውን ያውቃሉ እንጂ ለሁሉም ኩል
አይገለጥም፡፡
1. ፍጻሜ ያለውና ፣ ፍጻሜ የሌለው
ፍጻሜ ያለው፤ የሰው ልጆች ሊረዱ በሚችሉበት መንገድ
ስለሚገለጡ የፍጡራን ምሥጢርና ጊዜያዊ ምሥጢር
ፍፃሜ ያላቸው ምሥጢራት ይባላሉ፡፡
ፍጻሜ የሌለው፤ የፈጣሪና የዘለአለማዊ ምሥጢር ፍፃሜ
የሌላቸው ምሥጢራት ናችው፡፡ ምክንያቱም ከሰው ልጅ
አእምሮ በላይ ስለሆኑ ነው፡፡
ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርሰቲያን
በመሠረቱ ምሥጢር ሲባል ለተወሰነ ሰው ብቻ የሚነገር
ሁሉ ሊሰማው የማይገባ በወዳጅ ዘንድ በምሥጢርነት
የሚቆይ ለሌላ የማይገለጥ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም
ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ለተለዩና በክርስቶስ ክርስቲያን
ለተባሉ በጥምቀት ለከበሩ ብቻ እንጂ ለማንም የማይሰጥ
እንዲሁም ላመኑት ብቻ ፀጋንና ረቅቅ ሀብትን የሚያሰጥ
ስለሆነ ነው፡፡ በሜቴ 13፡11 ጌታ ትምህርቱን በምሳሌ
ሲያስተምር ሐዋርያት ጌታን ለምን በምሳሌ
ታስተምራለህ? ቢሉት ‹‹ ለእናንተ ምሥጢርን የማወቅ ፀጋ
ተሰጥቷችኋል ለነሱ ግን አልተሰጣቸውም›› በማለት
እነዚህን ምሥጢራት ለሁሉም እንደማይነገሩና ግልጽ
እንደማይሆኑ አስረድቶናል፡፡
ምስጢር፡- ሲባል በዓይን የማይታይ በእጅ የማይጨበጥ
ተመርምሮ የማይደረስበት በእምነት ብቻ የሚቀበሉት
ማለት ነው፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንም
ከፍ ያለ ጸጋን የሚያሰጡት እንዴት እንደሆነ ስለማይታይ
እና ስለማይታወቅ ምሥጢር ተብለዋል፡፡
እነዚሀም ምሥጢራት በጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ
መሥራችነት የተመሠረቱ ሲሆን ጸጋንና በረከትን
የሚያስተላልፍባቸው ራሱ በዕለተ ዓርብ ካደረገው የማዳን
ሥራ የመነጨ ይህም የማዳን ሥራ እስከ ዘለአለም ኃይሉ
የሚታወቅባቸው ታላላቅ ምሥጢራት ናቸው፡፡
7ቱን ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንም 7 መሆቸው በመጽሐፈ
ምሳሌ 9፡1 ላይ ‹‹ጥበብ ቤቷን ሠራች ሰባቱንም
ምሰሶዎችዋን አቆመች›› ይላል፡፡ ጥበብ የተባለ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ሰባት ምሰሶች
የተባሉት ደግሞ የ7ቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ምሳሌ
ነው፡፡ እነዚህም
1. ምሥጢረ ጥምቀት፡- መንፈሳዊ ልደት
2. ምሥጢረ ሜሮን፡- መንፈሳዊ ዕድገት /በመንፈስ ቅዱስ
መበልጸግ/
3. ምሥጢረ ቁርባን፡- መንፈሳዊ ምግብ /የዘለአለም
ሕይወት/
4. ምሥጢረ ንስሐ፡- መንፈሳዊ ድኅነት /ሥርየተ ኀጢአት/
5. ምሥጢረ ተክሊል፡- የጋብቻ ጽናት
6. ምሥጢረ ክህነት፡- የማሠርና የመፍታት ፣ የማስተማር ፣
የማደስ ፣ የማጥመቅ ፣ ሥልጣን /መንፈሳዊ ኃይል/
7. ምሥጢረ ቀንዲል፡- ሥጋዊና መንፈሳዊ ኃይል /ከበሽታ
መፈወስ/
የ7ቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን አከፋፈል
1) ለሁሉም የሚሰጡ ምሥጢራት
· ምሥጢረ ጥምቀት
· ምሥጢረ ሜሮን
· ምሥጢረ ቁርባን
· ምሥጢረ ንስሐ
2) ለሁሉም የማይሰጡ ምሥጢራት
· ምሥጢረ ተክሊል
· ምሥጢረ ክህነት
· ምሥጢረ ቀንዲል
3) የሚደገሙ ምሥጢራት
· ምሥጢረ ንስሐ
· ምሥጢረ ቀንዲል
· ምሥጢረ ቁርባን
4) የማይደገሙ ምሥጢራት
· ምሥጢረ ጥምቀት
· ምሥጢረ ሜሮን
· ምሥጢረ ክህነት
·
4 374
…✞… ወዴት እንታደስ? ...✞…
o ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና ወደ የቱ ሐይማኖት?
o ከቀደመዉ መንገድ ወደ የትኛዉ ህይወት?
o ከአባቶቻችን ሐይማኖት ወደ እነማን እምነት?
o በክርስቶስ ደም ከተዋጀች ቤተ ክርስቲያን ወዴት?
///….. ነዉ ወይስ ….. ////
o ከጾም ወደ መብል ብቻ?
o ከጥምቀት ወደ አለመጠመቅ?
o ከቁርባን ወደ አለመቁረብ?
o ከስርዓት ወደ ስርዓት የለሽነት?
o ከቤተ ክርስቲያን ወደ አዳራሽ?
o ከቅዳሴ ወደ ጩኸትና ሁከት?
o እግዚአብሔርን ከማምለክ ፈላስፎችን ወደ መከተል?
o የክርስቶስን ክብር ከፍ ከማድረግ ዝቅ ወደ ማድረግ?
o ፈራጁን ጌታ አማላጅ ነዉ ወደ ማለት?
o ቅዱሳኑን ከመቀበል ወደ አለመቀበል?
o ቅዱሳኑን ከማክበር ወደ መቃወም?
o ቅዱሳኑን አማላጅ ከማለት ምንም ቦታ የላቸዉም ወደማለት?
o ጸበልን እንደ ተራ ዉኃ ወደ ማየት?
o ከበሮን በጊታር ወደ መቀየር?
o ጸናጽልን በኦርጋን ወደ መለወጥ?
o ዕጣኑን በዓለማዊ ሽታ ወደ መተካት?
o እምነት ብቻ ብሎ ሥራን ወደ መርሳት?
////…….. እሽ ወዴት እንታደስ? …....///
o ራስን ለካህን ወደ አለማሳየት?
o መጽሐፍትን እንደ ራስ ፈቃድ ወደ መተርጎም?
o መዝሙርን ዘፈን መሰል ወደ ማድረግ?
o 365 ቀን ራስን ለሆድ ወደ ማስገዛት?
o የሉተርን ፍልስፍና ወደ መከተል?
o የእግዚአብሔርን ታቦት ጣዖት ነዉ ወደ ማለት?
o በቅዱሳን ስም ምጽዋትና ዝክርት ማድረግን ወደ መርሳት?
///……ነዉ ወይስ……..////
o ሴቶች ራሳቸዉን ሳይሸፍኑ ወደሚጸልዩበት?
o ሐሰተኛ ነቢያት ወዳሉበት?
o ነገረ ሥራቸዉ ሁሉ ተቃዉሞ ብቻ ወደሆነበት?
o ስግደትን በዝላይ ወደ መቀየር?
o ጸሎትን ወደ መተዉ?
o ገዳምን ንቀዉ የስጋን ዓለም ወደመረጡት?
ብሉይ ኪዳን ተሽሯል ወደሚል ክህደት?
o ንዋየ ቅድሳትን እንደ ተራ ዕቃ ወደ ማሰብ?
o ማዕተብን ወደ መበጠስ?
o መንፈሳዊ በረከት ከሚገኝበት ብርና ዶላር ወደሚቸረቸርበት?
o የጌታ እናት ወላዲተ አምላክን እንደ ማንም ፍጡር ወደ
መመልከት?
o የቅዱሳን ተጋድሎ እንደ ተራ የሕይወት ጉዞ ወደ መቁጠር?
o መስቀሉን ተራ እንጨት ነዉ ወደሚል ንቀት?
o በትዕቢት ተነፍቶ እኔ ቅዱስ ነኝ ወደማለት?
o ከካህን ወደ ፓስተር?
o የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸዉን መጻሕፍት ወደ
አለመቀበል?
o የቅዱሳንን መታሰቢያ ዘላለማዊነት ጊዜያዊ ወደ ማድረግ?
o ከህይወት ወደ ሞት?
///…… ተሃድሶ ስትሉ ወዴት? ……..////
o በዓላትን ወደ አለማክበር?
o ከምንኩስና ወደ ዓለም ናፋቂነት?
o ወንጌልን ወደ ማጣመም?
o ሴት ልጅ በድፍረት የወንድ ልብስ ለብሳ አስተማሪ ነኝ
ወደምትልበት?
o ከእዉቀት ወደ ምንምነት?
o ከእዉነተኞቹ ነቢያትና ሐዋርያት ወደ ሐሰተኞቹ?
o ከምሉዕነት ወደ ባዶነት?
o ከቅድስና ወደ ርኩሰት?
o ከነጻነት ወደ ባርነት?
o ከንግስተ ሳባ እምነት ወደ ዘመኑ ፈላስፎች?
o ከኢትዮጵያዊዉ ጃንደረባ ክርስትና ወደ ምንፍቅና?
o ከመንፈሳዊነት ወደ ዓለማዊነት?
o ከክርስትና ወደ ፍልስፍና?
///……. እሽ ተሃድሶ ስትሉ ወዴት እንታደስ? ……..// እንንቃ ጓደኞቼ!!!
✍ @EOTC2921 ✍
✍ @EOTC2921 ✍
✍ @EOTC2921 ✍
4 374
✞ልጆቻችሁን እንዲህ ብላችሁ አስተምሩ✞
~ሀይማኖት ምንድን ነው----- ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
~ማን ፈጠራችሁ--------------ቅድስት ስላሴ
~ስላሴ ስንት ናቸው------------አንድም ሶስትም
~ምን ማስረጃ አለ-----------ኦሪት ዘፍጥረት 18፤1-5
~አንድነታቸው ምንድን ነው---በአገዛዝ በስልጣን
በመለኮት በመሣሰሉት
~ሶስትነታቸው በምንድን ነው---በስም በአካል በግብር ነው
~አብ ግብሩ ምንድን ነው----መውለድ ማስረጽ
~የወልድ ግብሩ ምንድን ነው--መውለድ ነው
~የመንፈስ ቅዱስስ ------ማስረጽ ነው
✍ @EOTC2921 ✍
4 374
♦️መርቆሬዎስ ♦️
መርቆሬዎስ(፬)
ለችግሬ ደራሽ ና በፈረስ
እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ
ባስልዮስ ጎርጎርዮስ ሰምሯል ልመናችሁ
ስዕሉ ዘለለ ተአምራት አያችሁ
እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ
ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆሬዎስ
አዝ ።።።።።።።።።።
ዑልያኖስ ተገሏል ሃይማኖት ይስፋፋል
ብሎ መሠከረ መርቆሬዎስ ኃያል
ገጸ ከለባቱ ባሕርይ ቀየሩ
እሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ
አዝ።።።።።።።።።።
ትካዜ ኃዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ
መርቆሬዎስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ
በጸሊም ፈረሱ እየገሰገሰ
መርቆሬዎስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ
አዝ።።።።።።።።።።
ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዮስ ወደደ
ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ
በጋለ ሹል ብረት መርቆሬዎስ ተወጋ
ስሙ ተሰየመ ከሰማዕታት ጋ
አዝ።።።።።።።።።።
አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር
መፍቀሬ አብ ካለ ፒሉ ፓዴር
ቂሳርያ እስር ቤት መርቆሬዎስ ታሰረ
ወህኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ
....................❤️🕯❤️................
✍ @EOTC2921 ✍
