cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ውሉደ ጥምቀት ዘገዳመ ኢየሱስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት በገዳመ ኢየሱስ ቤተ-ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል መነሻ በማድረግ የተቋቋመ ማህበር ነው

Больше
Рекламные посты
427
Подписчики
-124 часа
-67 дней
-1030 дней
Время активного постинга

Загрузка данных...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Анализ публикаций
ПостыПросмотры
Поделились
Динамика просмотров
01
💒#መልካም ዕለተ ሰንበት💒 "' አቤቱ አምላኬ የሕይወቴ ጌታ ሆይ የስንፍናን መንፈስ፣ ተስፋ መቁረጥን፣ ስልጣን መሻትንና ከንቱ ወሬን ከእኔ አርቅልኝ ነገር ግን በምትኩ የንጽሕናን፣ የትሕትናን፣ የትዕግስትንና የፍቅርን መንፈስ ለእኔ ለባሪያህ አድለኝ አዎን፣ ጌታና ንጉሥ ሆይ የራሴን መተላለፍ እንድመለከት እንጂ በወንድሜ ላይ እንዳልፈርድ አድርገኝ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ምስጉን ነህና'' ✍#ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።" (ኦሪት ዘጸአት 20:8) ✝️መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ✝️
531Loading...
02
Media files
510Loading...
03
ጤና ይሰጥልኝ እንደምን አደራችሁ ዛሬ ወራዊ ፀሎታችን ነው በዚሁ አጋጣሚ የመለከት እና ነጋሪት አገልግሎት ስልጠና የምትፈልጉ ሰዎች ለምናደርገው የአገልግሎት ክፍተት እና ቅሬታ እንዳይፈጠር መጥታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን!!!
540Loading...
04
Media files
591Loading...
05
Media files
611Loading...
06
Media files
790Loading...
07
Media files
750Loading...
08
Media files
971Loading...
09
+ በዓለ ዕርገት + ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ ሞቶ ከተነሣ በኋላ ለ40 ቀናት ያህል ደቀ መዛሙርቱን ሲያስተምራቸው ቆይቷል ። "ደግሞ ዐርባ ቀን እየታያቸው ስለእግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው " ሲል ቅዱስ ሉቃስ እንደገለጸው ከትንሣኤው በኋላ በምድር ላይ የቆየው ለዐርባ ቀናት ብቻ ነው ። ከዐርባ ቀናት በኋላ በክብር በይባቤ ወደ ሰማይ ዐርጓል ። " ....ይኽን ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው" እንዲል ። (ሐዋ 1፥1-9 ) ጌታችን ያደረገውን /ዕርገቱንም/ ከደብረ ዘይት ተራራ ነው ። (ሉቃ 24-50-53) ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው ሲያስተምር "እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል ?" በማለት እንደገለጸው ዕርገቱ ፣ ክብሩ በሚገለጽበት በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ለመቀመጥ ነው ። (ዮሐ 6፥62) ይኽን ቅዱስ እስጢፍኖስ በዐይነ ሥጋው ለመመልክት መብቃቱን "እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ " በማለት ገልጾታል ። (ሐዋ 7፥57 ) ይኽን ጉዳይ አስመልክቶ ቅዱስ ጳውሎስ "እንግዲህ በሰማያት ስላለን ፣ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ " ብሎአል ። (ዕብ 4፥14 7፥26 ) ስለጌታችን አምላክነት ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ባስረዳበት አንቀጽ "......በሥጋ የተገለጠ ፣ በመንፈስ የጸደቀ ፣ ለመላእክት የታየ፣ በአሕዛብ የተሰበከ ፣ በዓለም የታመነ ፣ በክብር ያረገ "ሲል ገልጾታል ። (1ኛ ጢሞ 3፥16 )   ( "በዓላት" ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ገጽ 111-112)
941Loading...
10
✞✝✞ እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝ +*" ዕርገተ እግዚእ "*+ =>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን 2 ጊዜ ታከብራለች:: አንዱ "ጥንተ በዓል": ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል:: ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል:: +የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ (በሕማሙ: በሞቱ) ዓለምን አድኖ: 40 ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል:: +በ40ኛው ቀን 120ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው: ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጉዋል:: +ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን እርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሳኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በ40ኛው ቀን ዐረገ:: +አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል:: <<ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ:: ወእግዚእነ በቃለ ቀርን:: ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ:: >> (መዝ. 46:6) =>ከበረከተ ዕርገቱ ይክፈለን:: +"+ እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ ሰማይም ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ:: +"+ (ሉቃ. 24:50-53) <<< ስብሐትለእግዚአብሔር >
930Loading...
11
Media files
810Loading...
12
ወር በገባ በ4 ነባቤ መለኮት  ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። ጥበቃው አይለየን ወቶ ከመቅረት ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውረን።🙏❤
1382Loading...
13
Media files
1091Loading...
14
ከበዓታ ለማርያም በረከት ረድኤት ይክፈለን። ከቤተ መንግሥቱ ግቢ ውስጥ ያለሽ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም:-ለሀገራችን ቅን መሪ፥ለቤተ ክርስቲ ያናችን ቅን አገልጋይ አድዪን።በአማላጅነትሽ ኢትዮጵያ አገራችንን፥ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ከነደደ እሳት አውጪልን፥የመከራውን ዘመን አሳጥሪልን።
1181Loading...
15
"#እባክህን_ከእሳቱ_ላይ_አትውረድ"    አንድ ወንድም አባ ጴሜንን "ምከረኝ" ብሎ ጠየቀው። አባ ጴሜንም "ድስት በእሳት ላይ እያለ ምንም አይነት ተባይ ሊቀርበውና ሊያበላሸው አይችልም። ከእሳት ወጥቶ ሲቀዘቅዝ ግን ነፍሳት ሁሉ ለመግባትና ለማበላሸት ይቻላቸዋል። ክርስቲያንም ከመንፈሳዊ ተግባር ካልራቀ ጠላት የድቀት ምክንያት አያገኝበትም" አለው። ወዳጄ ሆይ ሕይወት ቀዝቅዛብሃለችን? ከእሳቱ ወደ መሬት ወርደህ በርደሃልን? የሕያውነትህ ሙቀት እሳት በማጣት ተንዘፍዝፏልን? ድስት የተባለ ሰውነትህ ክረምት የሚያህል ጉድን ተሸክሟልን? ዙሪያ ገባህ ፀሐይ እንደማትወጣበት ምእራብ ጨለማን የሚጠራ ሆኗልን? ማንነትህ እሳት እንዳጣ ምግብ ጥቃቅን ነፍሳት በተባሉ ኃጢአቶች (ቁጣ፣ ቸልተኛነት፣ ስስት፣ አልታዘዝ ባይነት፣ ጭንቀት፣ ሁሉን የመናቅ ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ...) ተወርሮ፣ መዓዛ ቅድስና ተለይቶት እጅ እጅ ብሏልን? ሞቅ የሚያደርገው አጥቶ በዓለማዊነት ሻግቷልን? የተባዮች መጫወቻ፣ የተውሳኮች መቀለጃ ሆኗልን? እንግዲያውስ በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡ ወዳጄ ሆይ ሃይማኖት በተባለችና ከሰማይ በወረደች ልዩ እሳት (ሉቃ.12፥49) ላይ ተቀምጠህ የድስትነትህን ሙቀት መልስ፡፡ እምነት፣ ተስፋና ፍቅር (1ቆሮ.13፥13) በተባሉ ሦስት ጉልቻዎች ላይ በምቾት ተጥደህ የሕይወትህን የኃጢአት ብርድ አስወግድ፡፡ ንስሐ በተባለች ነበልባል ውበትነት የክረምትህን ጽልመት በምስራቃዊ በጋነት ድል ንሳ፡፡ በሥጋ ወደሙ ፍምነት ድስት የተባለ ሰውነትህን በከዊነ እሳትነት ቀድስ፡፡ እባክህን በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡ ሃይማኖት የተባለ እሳትን ተባይ አይቀርበውም፡፡ እምነት ተስፋና ፍቅር የተሰኙ ጉልቻዎችን ተውሳኮች ሽቅብ አይወጡአቸውም፡፡ የነበልባለ ንስሐን ብርሃንና ሙቀት ነፍሳተ ጽልመት መቋቋም አይችሉም፡፡ ስለዚህ በእሳቱ ላይ እስካለህ ድረስ (በመንፈሳዊ ተግባራት እስከጠነከርክ ድረስ) አንተ ሁሌም ከተባይና ከነፍሳት ብልሽት (ከአጋንንት) የራቅክ ነህ፡፡ ወዳጄ እባክህን ከእሳቱ ላይ አትውረድ፡፡ እሳቱ በደንብ ይነድ ዘንድ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት የተባሉ እንጨቶችንና ምጽዋት የተባለ ጋዝን መጨመርህን እንዳትዘነጋ፡፡ እንዲህ ከሆነ ዘንዳ ድስትነት ሁሌም የሞቀ ይሆናል፡፡ እጅ እጅ ከማለት፣ ከመሻገትና የተባይ መጫወቻ ከመሆን ትድናለህ፡፡ ወዳጄ ሆይ እባክህን ከእሳቱ ላይ አይትውረድ፡፡ በኃጢአት "እጅ እጅ '' ከማለትና በበደል ከመሻገት እግዚአብሔር ይሠውረን! አሜን
1201Loading...
16
የንጉሥ ሥልጣን በሥጋ ላይ ነው፤ የካህን ሥልጣን ግን በነፍስ ላይ ነው፡፡ ንጉሥ ይቅር ቢል የገንዘብን ዕዳ ነው፤ ካህን ይቅር ሲል ግን የበደል የኃጢአት ዕዳን ነው፡፡ ንጉሥ ያዝዛል፤ ካህን ግን ያስተምራል ይዘክራል። ንጉሥ ያስገድዳል፤ ካህን ግን ነጻ ፈቃድን ያያል፡፡ ንጉሥ ቁሳዊ የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፤ ካህን ግን ረቂቅ (መንፈሳዊ) የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፡፡ ንጉሥ የጦር ዕቃ መሣሪያውን ቢሰብቅ አንገዛም ብለው ባመፁት (እንዲሁም ከወራሪዎች፣ ሥጋውያን ደማውያን) ላይ ነው፤ ካህን ግን ውጊያው ከጨለማ አበጋዞች ከአጋንንት ጋር ነው፡፡ ስለዚህ ሥልጣነ ክህነት ከሥልጣነ መንግሥት ይበልጣል፡፡ እንዲህም በመኾኑ ንጉሥ አንገቱን ለካህናት እጅ ያጎነብሳል፡፡ (#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ፣ ትንቢተ ኢሳይያስ፣ ድርሳን ፬ በተረጎመበት ድርሳኑ)
980Loading...
17
“እገድልኻለሁ ያልከኝ እውነትም ገደልከኝ’’ በአንድ ወቅት ከቤ/ክን አገልጋይ ከነበረ ሰባኪ ሲመሰከር ከሰማሁት እውነተኛ ታሪክ ላካፍላችሁ። አንድ እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚያገለግል ዲያቆን ነበር። የዚህ ዲያቆን ጎረቤት የሆነ ሰውም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ይኽን ዲያቆን በጣም ጠምዶ ይዞት ነበር። በመንገድ ላይ ባገኘው ቁጥር በጣም አስፀያፊ ስድብ ከመስደብ ጀምሮ ቆሻሻ ውኃ በላዩ ላይ እስከመድፋት እንዲሁም ካልደበደብኩት እያለ በገላጋይ ነበር የሚለመነው ዲያቆኑ ግን ይኽ ኹሉ ሲሆን "እግዚአብሔር ይባርክህ ያስብኽ" ከማለት ውጪ ምንም የክፋት ቃል ከአንደበቱ አይወጣም ነበር። ከእዕታት በአንዱ ቀን ግን ዲያቆኑ ምርር ብሎት ሰውየውን “እገድልኻለሁ’’ ብሎት ይሔዳል። ሰውየውም ይኽ ዲያቆን እገድልኻለሁ ያለኝ ምን ገዝቶ ነው ቦንብ ነው ?  ሽጉጥ ነው? ዱርየ ነው ? በማለት መጨናነቅ ይጀምራል። ታዲያ ከዕለታት በአንዱ ቀን ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ ዲያቆኑ ከቅዳሴ ወጥቶ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲሔድ መንገድ ላይ ሕዝብ ተሰብስቦ ያያል። ጠጋ ብሎ ምን እንደተፈጠረ ይጠይቃል። ሰዎቹም አንድ ተሽከርካሪ አንድ ሕጻን ልጅ ገጭቶ እንዳመለጠ ይነግሩታል። ጠጋ ብሎ ሲያይም የተገጨው የዚያ እርሱን የሚሰድበውና የሚያዋርደው ሰው ልጅ መኾኑን ይረዳል። በኋላም ልጁን ከነደሙ ይሸከምና ኮንትራት ታክሲ ጠርቶ ልጁን ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ይወስድና ያሳክመዋል። የልጁ አባትም ሥራ ቦታ ነበርና ልጁ ተገጭቶ ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል መወሰዱ ተደውሎ ይነገረዋል። ሰውየውም ዘውዲቱ ሆስፒታል ሔዶ ልጁ የተኛበት ክፍል ሲገባ ልጁ ጉሉኮስ ተሰክቶበት ተኝቶ አጠገቡ ደግሞ ያ አልወደውም ጠላቴ እያለ የሚሰድበው ዲያቆን ሲያስታምመው ያያል። በአካባቢው የነበሩ ጎረቤቶቹም ልጁ በመኪና እንደተገጨና ያ ጠላቴ የሚለው ዲያቆን አምጥቶ እያሳከመው እንደሆነና እሱ ባያሳክመው ልጁ ሊሞት ይችል እንደነበር ነገሩት። ሰውየውም ዲያቆኑን ጠርቶ  “እገድልኻለሁ ያልከኝ እውነትም ገደልከኝ’’ ። አሁን ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለኽ ? " ሲለው ዲያቆኑም "እኔ ምንም አልፈልግም ከነ ቤተሰቦችህ ንስሐ ግባ ሥጋ ወደሙ ተቀበል። እኔ የምመኝልህ ይኽን ብቻ ነው።" ብሎ አለው። በኋላም ዲያቆኑን የሚያውቁት ሰዎች "ለመሆኑ ሰውየዉን እገድልኻለሁ ያልከው ለምንድን ነው? " ብለው ሲጠይቁት ዲያቆኑም "እኔ እኮ እገድልኻለሁ ያልኩት ሰውየውን አይደለም እኔ እገድልኻለሁ ያልኩት በሰውየው ላይ አድሮ የሚረብሸኝን ዲያብሎስን ነው። እግዚአብሔርም ዲያብሎስን መግደያ ምክንያትና ጥበብ እንዲሰጠኝ ስጸልይ ነበር። ልጁ የተገጨውም እግዚአብሔር ለእኔ ዲያብሎስን መግደያ ምክንያት ሊሰጠኝ ነው። እኔም የሰጠኝን ምክንያት ተጠቀምኩና እንደዛትኩት ዲያብሎስን ገደልኩት።" ብሎ አላቸው። ግሩምና በጣም ጣፋጭ ትምህርት ነው። እኔ እራሴን ታዘብኩት እናንተስ? ከዲያቆኑ ምን ተማራችሁ? በእውነት የዲያቆኑ ጥበብና የቀናች የሃይማኖቱ ትሩፋት ትደርብን አሜን ።
951Loading...
18
Media files
1230Loading...
19
Media files
1230Loading...
20
Media files
1060Loading...
21
ወርኀ ግንቦትን በቸርነቱ ላስፈጸመን እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን አምላካችን ከወዳጆቹ በረከትን ይክፈለን ሰኔ ወር የበረከት ወር ያድረግልን አሜን።🤲🌷 የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን
990Loading...
22
Media files
1310Loading...
23
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሠረት፡- 1.በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤ 2.በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤    3.በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 4.የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ 5.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስምልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል፤ 6.የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ 7.በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ 8.ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ 9.በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡ 10.ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 11.የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 12.በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡  በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
1310Loading...
24
#ኃጢአትህን_ኹሉ_በዲያብሎስ_ላይ_አታሳብብ በንስሐ ተስፋ ከቆረጥክ ዲያብሎስ ይወድሃል፡፡ ግን እርሱ እንዲረካ አታድርግ፡፡ ለድኅነት ቀንም ሁሌም ዝግጁ ሁን፡፡ እነዚህን ኹሉ የተናገርኩት ዲያብሎስን ከነቀፋ ነፃ ለማውጣት ሳይሆን እናንተን ከስንፍና ነፃ ለማውጣት ነው፡፡ ኃጢአታችንን ኹሉ በእርሱ እንዳናሳብብ በእውነት ይስፈልጋል፤ ለሁሉም ክፋታችን ሰይጣንን ተጠያቂ የምናደርግ ከሆነም የራሳችንን ቅጣት እንጨምራለን፤ ጉዳዩን ኹሉ ወደ እርሱ ስላስተላለፍንም ይቅርታ አናገኝም - ልክ ሄዋን ይቅርታን እንዳላገኘች ሁሉ፡፡ ግን ይህን አናድርግ፡፡ እራሳችንን እንወቅ፡፡ ቁስላችንን እንወቅ። ከዚያም መድኃኒቶቹን ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን፤ ደዌውን የማያውቅ ሰው፣ ድካሙን አይፈውስምና፡፡ ብዙ ኃጢአት ሠርተናል፤ ይህን በሚገባ አውቃለሁ፡፡ ሁላችንም ቅጣት ይገባናል፡፡ እኛ ግን ያለ ይቅርታ አይደለንም፣ ከንስሐ አንቀርም፤ አሁንም በአደባባይ ቆመናል፤ በንስሐም ተጋድሎ ውስጥ ነን፡ አርጅተኻል እና በመጨረሻው የሕይወት ደረጃ ላይ ነህ? አሁን እንኳን ከንስሐ እንደወደቅክ አታስብ፡፡ በራስህ መዳን ተስፋ አትቁረጥ፤ በመስቀል ላይ ነፃ የወጣውን ዘራፊ አስብ፡፡ እርሱ ዘውድ ከተቀዳጀበት ጊዜ የበለጠ ምን አጭር ነገር አለ? ያም ሆኖ ይህ ለእርሱ መዳን በቂ ነበር፡ ወጣት ነህ? በወጣትነትህ አትተማመን፣ ከፊትህ ረዥም ጊዜም እንዳለ አታስብ “የእግዚአብሔር ቀን እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና" (፩ኛ ተሰ. ፭፣፪) ለዚህም ነው ፍጻሜያችንን የማይታይ ያደረገው፣ ተግተን እንድንጸና። ማንም ኃጢያተኛ ሊያደርግህ አይችልም ይላል አቡነ ቴዎድሮስ - ዲያብሎስም ቢሆን፡፡ ለኃጢአት የመስማማት ወይም የመቃወም ኃይል ያለው በአንተ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ አሁን እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ክፋት እንዲሆን የፈቀደ እንደሆነ አልያም በሌላ ምክንያት እንደሆነ እንመርምር። በስንፍና በልቡም ምኞት ወደ ራሱ ኃጢአትን ከሚያስገባ ሰው በቀር፣ ኃጢአት በማንም ላይ ሊጫን አይችልም፡፡ ፈቃደኛ ባልሆነው እና ኃጢአትን በሚቃወመው ሰው ላይ ዲያብሎስ ኃይል የለውምና፡፡ ዲያብሎስ በኢዮብ ላይ ይህን የኃጢአት ክፋት ለመጫን የክፋት ዘዴውን ኹሉ ከተጠቀመ በኋላ ዓለማዊ ንብረቱን ኹሉ ገፍፎት፣ በሞት ሰባቱን ልጆቹን ነጥቆት፣ ከጭንቅላቱ ፀጉር እስከ እግሩ ጥፍር ድረስ የሚያስፈሩ ቁስሎችን፣ የማያባሩ ስቃዮችን ከሰጠው በኋላ የኃጢአት እድፍ በኢዮብ ላይ እንዲጣበቅ ለማድረግ በከንቱ ሞከረ፤ ኢዮብ በዚህ ኹሉ ጸንቶአልና፤ ከቶ አምላኩን ለመሳደብ ፍቃደኛ አልነበረም። (የነፍስ ምግብ - #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዳስተማረው ገጽ 80-82 #በፍሉይ_ዓለም የተተረጎመ)
1551Loading...
25
#ግንቦት ፳፰ (28) 📚 ከታሪክ መዛግብት 👉. የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል የተተከለው በ1905 ዓ.ም በልጅ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት ነው። የመጀመሪያውን መቃኞ ያሠሩት ፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ሲሆኑ ጽላቱም በጎንደር ክፍለ ሀገር የነበረና ከዚያ መጥቶም በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የተቀመጠ ነበር። 👉. ታድያ ፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ያሠሩት የመጀመርያው መቃኞ ለአገልግሎት ምቹ ስላልነበር ሁለተኛ መቃኞ ድጋሚ ተሠርቶ ታቦቱ እንዲገባ ተደርጓል። 👉. ንግሥት ዘውዲቱ በግንቦት 28 በ1914 ዓ.ም የዐማኑኤልን በዓል ተገኝተው ሲያስቀድሱ ምርጊቱ ተደርምሶ ሲወድቅ በማየታቸው ሦስተኛ መቃኞ እንዲሠራ አዘዙ። የደብሩ አስተዳዳሪ በጊዜው የተክለ ሃይማኖትን ቤተክርስቲያንም አንድ ላይ ያስተዳድሩ የነበረ በመሆኑ ንግሥቲቷ የቤተ መንግሥታቸውን አጣኝ የመጀመርያው አስተዳዳሪ ሆነው ደብሩን እንዲጠብቁ አደረጉ። አለቃው ሦስተኛ መቃኞ አሠርተው ታቦቱ ወደ ተዘጋጀለት መቃኞ ገባ። 👉. በ1920 ሕዝቡ እየበዛ በመምጣቱ አገልግሎቱ እንዲሰፋ ስላስፈለገ በንግሥት ዘውዲቱ አማካኝነት አዲስ ሕንፃ ቤተ መቅደስ ግንባታ ተጀመረ። በ1931 ታኅሣሥ 28 ቀን ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ታቦቱ ወደ መንበሩ ገብቷል። ንግሥት ዘውዲቱ ፍጻሜውን ሳያዩ ያረፉ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ደግሞ ክብ ቅርጽ ነበረው። 👉. አሁን ያለው ቤተክርስቲያን በጥር 28 ቀን 1969 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው የተጀመረ ሲሆን የወቅቱ የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ በነበሩት በሊቀ ሊቃውንት ንቡረ ዕድ አባ ተፈራ መልሴ አስተባባሪነት በምእመናን ርብርብና በቅዱስ ዐማኑኤል አከናዋኝነት ግንቦት 28 ቀን 1978 ዓ.ም ተጠናቆ ታቦተ ሕጉ ወደ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ገብቷል። #እንኳን_አደረሰን_መልካም_በዓል!
1133Loading...
26
“ክርስቲያን” ተብለህ መጠራትህ ዋስትና አይኾንህም፤ ዋስትና የሚኾንህ … በመንገድ ዳር ላይ ዘርን የሚዘሩ ሰዎች ምንም የሚያገኙት ጥቅም እንደ ሌለ ኹሉ፥ እኛም ለልጅነታችን የሚገባ’ ምግባር ከሌለን ክርስቲያኖች ተብለን ከመጠራት የምናገኘው በቁዔት የለም፡፡ ይህ እንዴት ይኾናል የምትለኝ ከኾነም የጌታችን ወንድም የተባለው ያዕቆብን ምስክር አድርጌ እነግርሃለሁ፡፡ እርሱ፡- “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ብሎአልና (ያዕ.2፡17)፡፡ ስለዚህ ለእኛ (ለክርስቲያኖች) ምግባር መያዝ ግዴታ ነው፡፡ ምግባር ከሌለን ግን “ክርስቲያን” የሚለው ስም ለእኛ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እንኪያስ ንገረኝ ! በዓውደ ውጊያ የማይሳተፍ፣ ለሚመግበው ንጉሥም የማይዋጋ ከኾነ አንድ ወታደር ወታደር ተብሎ ቢጠራ ምን ጥቅም አለው? ለንጉሡ ክብር የማይዋጋ ከኾነስ ወታደር ተብሎ ባይጠራ ይሻለዋል፡፡ ይህ ሰው በንጉሡ የሚመገብ ኾኖ እያለ፥ ነገር ግን ንጉሡ በጠላቱ ላይ ድል እንዲያደርግ የማይዋጋ ከኾነ እንዴት ከቅጣት ሊያመልጥ ይችላል? ንጉሡን ምሳሌ አድርጌ ልናገረው የፈለግሁትስ ምንድን ነው? ልለው የፈልገሁት እግዚአብሔር በትንሹ ስለ ገዛ ነፍሳችን እንድንጠነቀቅ (ምግባር መያዝ እንድንችል) ኃይል (ዓቅም) ሰጥቶናል ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ንስሐና ምጽዋት መጽሐፍ
1473Loading...
27
Media files
1390Loading...
28
Media files
1390Loading...
29
Media files
1350Loading...
Фото недоступноПоказать в Telegram
💒#መልካም ዕለተ ሰንበት💒 "' አቤቱ አምላኬ የሕይወቴ ጌታ ሆይ የስንፍናን መንፈስ፣ ተስፋ መቁረጥን፣ ስልጣን መሻትንና ከንቱ ወሬን ከእኔ አርቅልኝ ነገር ግን በምትኩ የንጽሕናን፣ የትሕትናን፣ የትዕግስትንና የፍቅርን መንፈስ ለእኔ ለባሪያህ አድለኝ አዎን፣ ጌታና ንጉሥ ሆይ የራሴን መተላለፍ እንድመለከት እንጂ በወንድሜ ላይ እንዳልፈርድ አድርገኝ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ምስጉን ነህና'' ✍#ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።" (ኦሪት ዘጸአት 20:8) ✝️መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ✝️
Показать все...
👍 1🎃 1
ጤና ይሰጥልኝ እንደምን አደራችሁ ዛሬ ወራዊ ፀሎታችን ነው በዚሁ አጋጣሚ የመለከት እና ነጋሪት አገልግሎት ስልጠና የምትፈልጉ ሰዎች ለምናደርገው የአገልግሎት ክፍተት እና ቅሬታ እንዳይፈጠር መጥታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን!!!
Показать все...
2
02:53
Видео недоступноПоказать в Telegram
IMG_0829.MOV34.36 MB
54.37 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
+ በዓለ ዕርገት + ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ ሞቶ ከተነሣ በኋላ ለ40 ቀናት ያህል ደቀ መዛሙርቱን ሲያስተምራቸው ቆይቷል ። "ደግሞ ዐርባ ቀን እየታያቸው ስለእግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው " ሲል ቅዱስ ሉቃስ እንደገለጸው ከትንሣኤው በኋላ በምድር ላይ የቆየው ለዐርባ ቀናት ብቻ ነው ። ከዐርባ ቀናት በኋላ በክብር በይባቤ ወደ ሰማይ ዐርጓል ። " ....ይኽን ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው" እንዲል ። (ሐዋ 1፥1-9 ) ጌታችን ያደረገውን /ዕርገቱንም/ ከደብረ ዘይት ተራራ ነው ። (ሉቃ 24-50-53) ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው ሲያስተምር "እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል ?" በማለት እንደገለጸው ዕርገቱ ፣ ክብሩ በሚገለጽበት በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ለመቀመጥ ነው ። (ዮሐ 6፥62) ይኽን ቅዱስ እስጢፍኖስ በዐይነ ሥጋው ለመመልክት መብቃቱን "እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ " በማለት ገልጾታል ። (ሐዋ 7፥57 ) ይኽን ጉዳይ አስመልክቶ ቅዱስ ጳውሎስ "እንግዲህ በሰማያት ስላለን ፣ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ " ብሎአል ። (ዕብ 4፥14 7፥26 ) ስለጌታችን አምላክነት ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ባስረዳበት አንቀጽ "......በሥጋ የተገለጠ ፣ በመንፈስ የጸደቀ ፣ ለመላእክት የታየ፣ በአሕዛብ የተሰበከ ፣ በዓለም የታመነ ፣ በክብር ያረገ "ሲል ገልጾታል ። (1ኛ ጢሞ 3፥16 )   ( "በዓላት" ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ገጽ 111-112)
Показать все...
✞✝✞ እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝ +*" ዕርገተ እግዚእ "*+ =>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን 2 ጊዜ ታከብራለች:: አንዱ "ጥንተ በዓል": ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል:: ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል:: +የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ (በሕማሙ: በሞቱ) ዓለምን አድኖ: 40 ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል:: +በ40ኛው ቀን 120ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው: ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጉዋል:: +ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን እርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሳኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በ40ኛው ቀን ዐረገ:: +አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል:: <<ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ:: ወእግዚእነ በቃለ ቀርን:: ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ:: >> (መዝ. 46:6) =>ከበረከተ ዕርገቱ ይክፈለን:: +"+ እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ ሰማይም ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ:: +"+ (ሉቃ. 24:50-53) <<< ስብሐትለእግዚአብሔር >
Показать все...