cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ሸምሸ ዳኒ [ ዳና የሀድራ ጀመዐ ] chennel

በቻናሉ ይቀላቀሉ 👇👇 @yedanawecuchannnneel አስተያየት ካለወት 👇 @ibnu_abdery_bot የዩቲብ ቻናሉን ለመጎብኘት 👇👇 Watch "የዳናው Tube" on YouTube https://youtube.com/channel/UCQp9Vh7556u4HpK8ZpXR5pg

Больше
Эфиопия9 087Амхарский7 779Категория не указана
Рекламные посты
326
Подписчики
Нет данных24 часа
-27 дней
-730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

https://t.me/Danayehadira #በነብዩ መውሊድ የሰለሙት ባልና ሚስት #ኪታብ ሸረፊል ዓናም በወንድም_አወል ሰዒድ
Показать все...
My Song 8.ogg29.09 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
በወንድም አወል ሰዒድ #ኪታብ ሸረፊል አናም ርዕስ በመውሊድ የሰለሙት ባልና ሚስት
Показать все...
⭕️ ዝክረ ባቲ ድል መንበራ ➿ ክፍል ❿ 🍂 የእንስቷ ጀግና ያቺ ድል ወንበሯ፥ አብራ የጀገነች ለሒጃብ ለክብሯ፥ ጀግና የጀግና ልጅ ዕንቁ ሴት የሆነች፥  የታሪክ  አሻራን  አስፍራ   አልፋለች፡ 🌸 ከጎጆዎች ጀርባ ለጥ ባለው መስክ ልጃገረዶች የዒድ አልፈጥርን በዓል ለማክበር ተሰባስበዋል። በሌላኛው ማዶ ወንዶቹ እየተጫወቱ ነበር። ብዙዎቹ የቤተ ዘመድ ልጆች ናቸው። ለመገናኘት ይህችን ቀን እንደናፈቁ ያስታውቅባቸዋል። 🍂 በዒዱ ቀን ወላጆቻቸው ከጎጆዎች ውስጥ በቁም ነገር ተጠምደው እየተዋያዩ ነበር። #የአዳሉ ሱልጣን ሙሐመድ በአጼ ልብነድንግል ጦር ጥቃት ፈጽመው ሲመለሱ በድንገት ከተገደሉ ወዲህ የተመረጡት ሱልጣኖች ሀገሩን በሰላም ማስተዳደር እንደከበዳቸው ተወሳ። በተለይም የክርስቲያኑ መንግስት የጥቃት ዒላማ የሆነችው የአዳል ዋና ከተማ ከዳካር ወደ ሐረር የቀየረው ሱልጣን አቡበከር ቢን ሙሐመድ ከአቅም ማነስ ባሻገር ለሸሪአዊ ድንጋጌዎች ግድ እንደሌለው መነጋገሪያ ሆነ። 🌸 በሱልጣን አቡበከር አስተዳደር ቀድሞ የማይታወቁ ኢስላማዊ ያልሆኑ ባዕድ ባህሎች በስፋት እየተቀላቀሉ እንደሆነ ሁሉም መሰከረ። ለሀይማኖቱ ቀናኢ የሆነው ማህበረሰብ የሱልጣኑን ሸሪአ አፍራሽ ድርጊት ለመመከት እየታገለ ያለው #ገራድ_አቡን_ሀዳሽ ለሶስት አመት ሰላም በማውረድና በማረጋጋት የሰራውን ከፍተኛ ጥረት አደነቀ። ➿ #ገራድ በአካባቢው የተፈጠረውን መጥፎ ገጽታ ለመለወጥ በመልካም በማዘዝ በመጥፎ መከልከሉ ቁማር ማገዱ የሙዚቃ መሳሪያ መከላከሉ ሽፍቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ፥ ኡለሞችንና መሻኢኾችን ወደራሱ ማስጠጋቱ ለኢድ በአል በተሰበሰቡት ዘመዶች ክብሩን ጨመረለት። 🍂 የአዋቂዎቹ ውይይት ልጃገረዶቹም ዘንድ በሌላ ቅርጽ ጨዋታ ሆነ። ሱልጣን አቡበከር ፈሳድ በማብዛቱ እየተጋፈጠው ካለው #ገራድ አቡን ዘንድ አንድ ጀግና ወጣት ፈረሰኛ እንዳለ አወሩ። "ስሙ አህመድ ይባላል። ማዶ ዘአካ ነው ቤቱ1" ትላለች አንዷ ሌላኛዋ "በአንድ የሰይፍ ምት ሁለት ካፊር ይገድላል!" ብላ ታጋንናለች። "ጠላቶች እሱን ለማረከ ሺ ግመል እንሰጣለን ብለዋል!" አለች ሶስተኛዋ አራተኛዋ "አጼ ልብነድንግል ታናሽ እህቴን ልዳርህ ብሎ ልኮበታል" ብላ ታጦዘዋለች። 🌸 ሁሉም ልጃገረድ የገራድ አቡን ታማኝ ፈረሰኛ እና ጀግና ሙጃሂድ ስለሆነው #አህመድ_ቢን_ኢብራሂም አል'ጋዚ የተለያዩ  የአድናቆት ቃላት ሲያዘንቡ የባቲ ድል ወንበሯ ልብ በደስታና በጭንቀት ተረብሸ። ➿ #አገልጋይዋ ሐሊመት ቀረብ ብላ "እመቤቴ አላልኩሽም!" አለቻት። ባቲ ድል ወንበሯ በረጅሙ ተንፍሳ በሹክሹክታ "ሀገሩ ሁሉ ስለሱ ጀግንነት ብቻ እኮ ነው የሚያወራው..."ብላ በመገረምና በግራ መጋባት መንፈስ ተመለከተቻት። "አንቺ ምኑን ሰማሽው... እረኛው በሜዳ፣ ገበሬው በመስክ፣ ኮረዳዋ በማጀት ስለ #አህመድ ነው የሚያንጎራጉሩት... ኮረዳውማ..."ብላ ሀሊመት ሰረቅ አድርጋ አየቻት። ባቲ በተቀመጠችበት ስትቁነጠነጥ አየቻት። 🍂 "ኮረዳው ምን ብሎ ያንጎራጉራል?" አለች #ባቲ_ድል_ወንበሯ ፍላጎቷን ስላናረችው ደስ ብሏት  "ይህ ትንሽ ልቤ ትልቅ አህመድ ወዶ ስጋዬ ቤት ያድራል መንፈሴ ከማዶ አላህዬ ባክህ ስማ ተለመነኝ የዱንያ ጀነትክን አህመድን ወፍቀኝ..." 🍂 ባቲ ድልወንበሯ ፈገግ ኮስተር እያለች "እኔም እኮ" ብላ መሬት መሬቱን እያየች መናገር የፈለገችውን ከአንደበቷ ማውጣት ከበዳት። ቢያንስ በስሱ ማስተላለፍ የሚገባትን ተንፈስ ማለት ፈለገች" እሺ ተስማምቻለሁ በቃ!" ሀሊመት በደስታ ለመዝለል ቃጣት። አላመነችም! 🍂 ቀጠለች ባቲ ድል ወንበሯ "ግን እኔው እራሴ የምነግረው ልዩ የመኽር ስጦታ እፈልጋለሁ" ሀሊመት ፊቷ ፈካ "እመቤቴ አንቺ ለትዳር ተስማሚለት እንጂ ማንኛውም ነገር ሊፈጽምልሽ ፈቃደኛ ይሆናል!" አለቻት። 🍂 ጀግንነቱ ከዳር እስከዳር እየናኘ ያለው ወጣቱ አሕመድ ግራኝ በወደፊቱ የአዳል ሱልጣኔት ትልቅ ቦታ እንደሚኖረው የገመቱት አለቃው ገራድ አቡን ሁነኛ ከሆነ ቤተሰብ የተገኘች ተስማሚ ልጃገረድ ሊድሩት ሽማግሌ ሰብስበው ሲማከሩ በአንድ ድምጽ የጸደቀው በኢማም ማህፉዝ ልጅ በባቲ ድል ወንበሯ ነበር። ሴት ሆና በመፈጠሯ እንጂ ወንድ ብትሆን ከአባቷ የማትተናነስ ጀግንነቷን ሁሉም ያወራዋል። ጭምት፣ ቁጥብ፣ ብሩህ አእምሮ ያላት፣ በዘመኑ ሴቶች የማይሞከሩ ፈታኝ ሀላፊነቶች እየወሰደች የምትተገብር፣ በፈረስ ግልቢያ፣ ሰይፍ፣ ቀስት፣ ጦር ውርዋራ... ብቃት ያላት መሆኗ ተነግሮላታል። ተፈጥሮዋዊ ውበቷን ሴቶች ሳይቀሩ ያደንቁላታል። በዘንካታ ቁመናዋ የተዘራው ውበቷ በሸፈናት ሂጃብ የተደበቀ አልነበረም! የደረሰ ወጣት ያላት እናት ለልጇ የምትመኛት ቆንጆ የቀይ ዳማ፥ የዛጎል አይኗን ግርማ ያጎላ ጥቅጥቅ ያለ ሽፋሽፍት የታደለች፥ ሰልካካ አፍንጫዋ ስር ምትሀታዊ ስስ ከናፍሮች የተቸረች፥ የረዘመው አንገቷ የተተከለበት ክፈፍ ትከሻ ያላት፥ መልከ መልካም ሴት ናት። 🌸 #ገራድ አቡን የኢማም ማህፉዝ አድናቂ እንደመሆናቸው ከጀግና ቤት የተገኘች ይህች ልጅ ለአህመድ ቢን ኢብራሂም መዳር እንዳለባቸው አመኑ። ለቤተሰቧም በባህሉ መሰረት ሽማግሌ ላኩ። እናትና የተቀረው ቤተሰብ ጥያቄውን ተቀብለው ከባቲ ድል ወንበሯ ጋር ተወያዩ። ከእምቢተኛነት ላስብበት ወደሚል ሀሳቧ እስክትወርድ ወር አስፈለጋት። ከእናቷ እስከ ግል ደንገጡሯ ሲያግቧቧት ከርመዋል። ጀግናው አህመድ ቢን ኢብራሂም በበኩሉ በፊት ለፊት ሽማግሌ መላኩ እንዳለ ሆኖ በጀርባ በኩል ድል ወንበሯን እንዲያግባቡለት የኢማም ማህፉዝ ቤት አገልጋይ አሰማርቷል። 🍂 የባቲ ድል ወንበሯ  ደንገጡር ሀሊመት  ማዶ ያለው ባሏ ዘንድ ሄዳ "እመቤት ትዳሩን እሺ ብላ ተስማማች" አለችው። ፊቱ ወገግ ብሎ "አልሀምዱሊላህ!" አላት። "እንግዶች ሲሄዱ ማምሻውን ወደ አህመድ ቀዬ ሄጄ እነግረዋለሁ" "ቃል የገባልህን ሀዲያ እንዳትረሳው!" ብላ ወደ እመቤቷ ባቲ ድል ወንበሯ አቀናች። 🍂 ወላጅ አባቷ ኢማም ማህፉዝ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው በለጋ እድሜዋ አስክሬናቸውን ያየችው ባቲ ድል ወንበሯ እንደማንኛውም ሰላማዊ ልጅ አላደገችም። አእምሮዋ ላይ የተቀረጸ፥ የህይወት ግቧ አድርጋ የወሰደችው አቋም አለ። አላህ ስለፈጠራት ብቻ ሳይሆን አላማዋን በመፈጸም ተልእኮ የምትኖር ነበረች። ለዚህም ይመስላል ቀልድ፣ ጨዋታ፣ ሳቅ... አያውቋትም፥ አታውቃቸውም። ሰርግ ቤት ሄዳ በደስታ ከማሳለፍ ይልቅ በቤተሰብ ወይም ቤተዘመድ በመዘየር ጊዜዋን ማሳለፍ ትመርጣለች። ቁርአን፣ በርካታ ኪታቦች ከመሀፈዟ በተጨማሪ አረብኛ ቋንቋ እንደአፍ መፍቻዋ ገርቶላታል። ➿ ባቲ ድልወንበሯ በትዳር ሀሳቡ መስማማቷ ከተረጋገጠ ወዲያ ለሽማግሌዎች የእሺታ መልስ ተሰጥቶ ኒካው ታሰረ። በዚሁ አጋጣሚ ሌላ አስደንጋጭ ክስተት ተፈጠረ። የአዳልን ኢስላማዊ ገጽታ እያበላሸ፥ ፈሳድ እንዲስፋፋ ምክንያት የሆነው ሱልጣን አቡበከር የገራድ አቡንን አካሄድ አልወደደውም። ከነገራድ ጋር ግጭት ውስጥ ገባ። የሱልጣኑ ጥላቻ ዳብሮ ገራድ አቡንን ማክሰኞ ሜይ 30/1525 በሽፍታ አስገደለዉ። ⚠️ ኢንሻ አሏህ ይቀጥላል...! 🈴JOIN ➲https://t.me/+XBeaC-I2mctmNjE8
Показать все...
PART ➑ ➿ ⭕️ ዝክረ ባቲ ድል መንበራ 🍂 የባቲ ድል መንበራ አባት ኢማም መህፉዝ በጠራው ሠማይ ፍንትው ብላ የምትታየው ጨረቃ የተራራውን ጀርባ በብርሀን አድምቃለች። ኢማም ማህፉዝ ከሰራዊቱ ፈንጠር ማለት እንደፈለጉ አጃቢዎቻቸው ስላወቁ ቀደም ብለው አካባቢውን ቃኝተው በመመለስ በምልክት ሰላማዊነቱን ነገሯቸው። 🍂 በአክብሮት የሚመለከቷቸው የአዳሉ ሡልጣን ሙሐመድ ኢብኑ ዛህረዲን ደገፍ አድርገው ከተቀመጡበት አነሷቸው። ማሾ ይዘው ከቅርብ ርቀት የሚከተሏቸው ጀሌዎች እንዳይሰሙ ድምጻቸውን መጥነው የአዳሉ ሱልጣን "ያ ኢማም ምን ወሰንክ?" አሏቸው። "እኔ" ብለው ኢማም ማህፉዝ ወደ ሠማይ በተስፋ በማንጋጠጥ "ይህን ጨለማ በጨረቃ ባደመቀው አላህ ተማምኜ መዋጋቱን ወስኜበታለሁ" ንግግራቸውን ቀጠሉ " ይሄ ዟሊም ንጉስ ዛሬ ለስምምነት የፈለገን ከባህር ነጋሽና ካባቱ ጠላቶች የሚሰነዘርበት ጥቃት ስላስጨናነቀው እንጂ ኸይር ፈልጎልን አይደለም። ♻️ አያቱ ዘርዐያቆብ በሙስሊሙ ላይ ከሰራው በደል ያልተናነሰ አባቱ በዕደማርያም ሰርቶብናል። እነዚያ ግፎች ከህጻንነቴ እየሰማኋቸው ስቆጭባቸው የኖርኩት ሳያንስ ዛሬ አላህ ሰራዊቴን አግርቶት የዘይላ ህዝብ ለዲኑ ፊዳ ለመሆን ተዘጋጅቷልና ከሱ ጋር የማያዛልቅ አህድ [ቃለ መሐላ] አልገባም። ከርሱ ጋር አህድ ለመግባት ከተፈለገ ደግሞ በቅድሚያ በሠራዊቱ የተወረሩ ሡልጣኔቶችን ይመልስልን። ያ ባልሆነበት ብቸኛው አማራጭ በጂሃድ የአላህን ነስር መፈለግ ብቻ ነው" ብለው ቁርጥ አደረጉ። 🌸 ከአጼ ዘርዐ-ያእቆብ ወዲህ በሙስሊም ሱልጣኔቶች ላይ የደረሰው ከፍተኛ ጥቃት ወታደራዊ አቅሙንና የሙስሊሙን ኡማ ስነልቦና በከባዱ እንደጎዳ አበክረው የተገነዘቡት የአዳሉ ሡልጣን ዳግም አቅም በመገንባት ለመደራጀት እንዲያመች ከአጼ በዕደማርያም አራቱ ሚስቶች መካከል ከሮማነወርቅ የተወለደው አጼ ናኦድ ጋር መስማማት እንደሚሻል ያቀረቡላቸውን አማራጭ የሐረሩ ኢማም ማህፉዝ ውድቅ አደረጉት። ♻️ ለሹራ ከሩቅ መንገድ የመጡት የአዳሉ ሡልጣን  ሙሐመድ ኢብኑ ዛህረዲን ከኢማም ማህፉዝ አንድ አቋም መያዝ ባይችሉም "አላህ ይርዳህ!" ብለው መረቋቸው። ኢማም ማህፉዝ በአክብሮት ጭንቅላታቸውን ስመው ወደተዘጋጀው ማዕድ መሯቸው። ሱልጣኑ ካጀባቸው ሰራዊት ጋር እራት ተመገበው በተሰበረ ልብ ወደቀያቸው ተመለሱ። 🍂 ከዘይላዊው ላድእ ኡስማን መገደል በኋላ  በዘይላ ትግል የጀመሩት ኢማም ማህፉዝ በግዳጅ ክርስትና የተነሳችው ሮማን ወርቅ ሙስሊም ወገኖቿን ልጇ አጼ በዕደማርያም እንዳይጎዳ መከልከል እንዳልፈለገች ወይም እንዳልቻለች ከተገነዘቡ በኋላ ኢስላማዊ ሱልጣኔት የነበሩትንና በክርስቲያኑ መንግስት ቁጥጥር ስር የገቡት ክልሎችን ነጻነት ለማስመለስ መዋጋትን መረጡ። 🍂 ኢማሙ ሰራዊታቸውን ሰብስበው "...እናንተ ሙስሊሞች ሆይ! ካፊሮች በተረጋጋንበት ሀገር፣ በተወለድንበት መንደር በሰላም እንዳንኖር ሊዘርፉን እየመጡ ነው። ሴቶቻችን ሊደፍሩ፣ በሚናራችን መስቀል ሊተክሉ አቆብቁበዋል። በጦር ካዳከሙት ጉልበታችን በተረፈ ያረስነውን ሊያስገብሩን ይፈልጋሉ። የሙስሊሙን ሱልጣኔት በየተራ እየወረሩ ኩፍራቸውን እያስፋፉበት ነው። ይሄን ጥቃት ተቃውመን ባንድ እንቁም ያልናቸው አንዳንድ ወንድሞቻችን ከነሱ ጋር አህድ ብንገባ ይሻላል እያሉ ነው። እኔ ደግሞ ኢስላምን እያጠፋ ካለ ወራሪ ጋር አህድ አልገባም ጂሃድ እገጥመዋለሁ እያልኩ ነው ምን ትሉኛላችሁ?"ብለው ቁልቁል ሜዳውን ተመለከቱ። 🍂 ሠራዊቱ "አላሁ አክበር! አላሁ አክበር!አላሁ አክበር! ጂሀድ፣ ጂሀድ፣ ጂሀድ..."ብሎ ድጋፉን አሳያቸው። 🍂 ኢማም ማህፉዝ በደስታ ማዕበል ተውጠው የዑመር ኢብኑል ኸጣብን ንግግር አስታወሱ:- ( እኛ አላህ በኢስላም ያከበረን ህዝቦች ነን። ክብርን በሌላ መንገድ ከፈለግነው ያዋርደናል)" 🍂 ኢማሙ የኢፋት፣ ባሌ፣ ሀዲያ፣ ደዋሮ፣ አራቢኒ፣ ሻርካ፣ ደራህ ሰባቱ ኢስላማዊ መንግስታት ከክርስቲያኑ ወራሪ ሀይል ፍጹማዊ ሉአላዊነታቸው የሚከበርበት ጂሃድ መካሄድ እንዳለበት በአጽንኦት አመኑበት። ለዚህም የሚያስፈልገውን መስዋዕትነት ለመክፈል ወሰኑ። ጎበዝ ፈረሰኞች፣ እግረኞች እንዲዘጋጁ አዘዙ። ♻️ ኢማም ማህፉዝ በአጼ በእደማርያም የተወረሩ ኢስላማዊ ሱልጣኔቶች የማስመለስ ጥቃት በጀመሩበት ጊዜ ከአጼው ስምምነት የተፈራረሙት የአዳሉ ሱልጣን መህመድ ገለልተኛ ሆነው መቀመጥ መረጡ። ያም ሆኖ ኢማሙ የተወረሩትን ኢስላማዊ አካባቢዎች ከክርስቲያኑ መንግስት ቀንበር ነጻ ለማውጣት ለረጅም አመታት እልክ አስጨራሽ የትጥቅ ትግላቸውን ቀጥለዋል። ከአጼ ናኦድ ጋርም ውግያ ገጥመዋል። የደዋሮ፣ የሀዲያ ባላባቶች በሰላም ሊገብሩ የተስማሙለት አጼ ናኦድ ኢማም ማህፉዝን በማያዳግም እርምጃ ለማሸነፍ ምርጥ የተሰኘ ክርስቲያናዊ ጦር አዘጋጅቶ ወደ ሀረር አቀና። ወናግ ጃን የተባለው የአጼ ናኦድ የጦር መሪ ክርስትና እምነቱን ትቶ ኢስላምን በመቀበል ከኢማም ማህፉዝ ጦር ተቀላቀለ። በአጼ ናኦድ የተወረረችዋን የባሌ ኢስላማዊ መንግስት ነጻ ለማውጣት ዘምቶ በክርስትያኖች ጦርነት ቢከፍትም ተሸንፎ ተማረከ። አጼ ናኦድ ወናግ ጃንን በክብር ይዞት ወደክርስትና እንዲመለስ አደረገው። በባሌ አስተዳዳሪነትም ሾመው። ሆኖም ልቡ ለኢስላም ፍቅር ያደረ ነበርና ኢስላምን የሚረዳበት መንገድ ያውጠነጥን ጀመር። ክርስትናንም እንደሽፋን ተጠቅሞ ክርስትናን ለማዳከም መጣጣሩን ቀጠለ። እንደ ቀድሞ ዘመን ኢስላም በባሌና አካባቢዋ የበላይ ይሆን ዘንድ ውስጥ ውስጡን መስራት ያዘ። 🍂 የክርስቲያን ጦር መሪዎችን ለማስገደል ሲጣጣር ቢቆይም ስትራቴጂው ብዙ ሊያስኬደው ስላልቻለ ከሙስሊሙ ጦር በመቀላቀል የክርስቲያኑን ጦር በመዋጋት ዋቢ ሸበሌ ወንዝ አቅራቢያ በአላህ መንገድ ሸሂድ ሆነ። ♻️ አጼ ናኦድ ራስ ምታት የሆኑበት ኢማም አህመድን በመግደል የሙስሊሞቹን አመጽ ለመስበር በርካታ ሙከራዎች አድርጎ አልተሳካለትም። በመጨረሻም በኢፋት ሙስሊሞች ጥቃት ለመክፈት በዘመተበት ጁሙዓ 1508 'ጂንጂኖ' ልዩ ስሙ 'መካነስላሴ' በተባለ ስፍራ አጼው በሙስሊሞች እጅ ተገደለ። ♻️ በአጼ ናኦድ መገደል መጠነኛ እፎይታ ያገኙት ኢማም ማህፉዝ ሰራዊት የማደላደል ውጥን እንደያዙ የአስራ አንድ አመቱ ልብነድንግል የአባቱን ዙፋን ተረክቦ በአጼነት ተሾመ። እድሜው ገና በመሆኑ የቅድመ አያቱ ዘርአያእቆብ ሚስት የነበረችው ንግስት እሌኒ ሙሐመድ በሞግዚትነት ከአጠገቡ ሆነች። ♻️ የሀድያው ሱልጣኔት ንጉስ ሙሐመድ ልጅ የሆነችው እሌኒ አጼ ዘርአያእቆብ ክርስትና አንስቶ ያገባት ነበረች። በከፍተኛ ጸረ ኢስላም አስተሳሰብ እንድትጠመቅ ከተደረገች በኋላ በክርስቲያኑ መንግስት ተጽእኖ ፈጣሪ መሆን ችላ ነበር። ንግስት እሌኒ አጼ ልብነድንግል በነገሰ በአመቱ በ1509 "ኢስላምን ለማጥፋት እንተባበር" ስትል ለፖርቹጋሉ ንጉስ ዶም ማኑኤል 3ኛ ደብዳቤ እስከመላክ የገፋ የኢስላም ጥላቻ የነበራት ሰው ሆነች። ⚠️ ኢንሻ አሏህ ይቀጥላል...! 🈴JOIN ➲https://t.me/+XBeaC-I2mctmNjE8
Показать все...
🗡ታላቁ ሙጃሒድ ኢማም አህመድ ⚔️ ➿ 🌀 ኢማሙ አህመድ ኢብን ኢብራሂም አል'ጋዚ 🌸 ፡ PART ❼ ፡ እውነት ታግሎ ሲወድቅ ሐቅ በሐቅ ተደግፎ ፥ በጀግና  ቅብብሎሽ  ዘመን ዘመንን አልፎ፥ ሲያጠቁሩት የማይጠፋ ላይደበዝዝ የታተመ፥ እወቅ የሽንብራ ኩሬን ገድል ታሪክ አለህ የቀደመ። ✍️ የሙስሊሞች የቀኝ ክንፍ ምድብ ላይ ከአንደኛው የካፊር ረድፍ ጥቃት ተሰነዘረባቸው። ወደ ሁለተኛው ቀጠለ፡፡ ከሶስተኛውም እያለ ጦርነት በመካከላቸው እንደንፋስ መዘዋወርን ተዘዋወረች፡፡ ጭንቅላቶች እየተቆረጡ በረሩ፡፡ የመስቀላዊያኑ ስብስቦች በሙስሊሞች የቀኝ ክንፍ ላይ በብዛት ተረባረቡ፡፡ ሙስሊሞች ያማረ መቋቋምን ተቋቋሟቸው፡፡ 🍂 ካፊሮች የተጨመረላቸውን ድጋፍ ሰጪ ጦር ኢማሙ አህመድ ወደሚገኝበትና ባንዲራው ከፍ ብላ ወደ ምትውለበለብበት ወደ መሃከለኛው ረድፍ አስጠጉ፡፡ እዚያ ላይ አጠንክረው ጫና በመፍጠር ተጋደሉ፡፡ ♻️ ምንኛ ያማሩ የአላህ ባሮች ናቸው እነዚያ የሙስሊሞች የባህር ክፍለ ጦሮች! ከፈረሰኛው ፊት ቀጥ ብለው ተዋጉ፡፡ ጦርነት ባንድ እግሯ ቆመች፡፡ አቧራዋ ጨሰ፡፡ ምድሪቱ በተገደሉ ሰዎች ጀናዛ ተሞላች፡፡ ቁስለኛው በሁለቱም ክፍለ ጦሮች በኩል ተበራከተ፡፡ ➿ ውጊያው በሁለቱ ኃይሎች መካከል ያለ አንዳች መቋረጥ ከዱሐ ወቅት ጀምሮ እስከ አስር ሰላት መጨረሻ ወቅት ድረስ ተካሄደ፡፡ ሙስሊሞች በተህሊል፣ በተክቢራ፣ አብሳሪና አስጠንቃቂ በሆኑት ነቢይ ﷺ ላይ ሰለዋት በማለት ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፡፡ ጮሁ፡፡ አላህ ድልን አወረደ፡፡ በካፊሮች ልብ ውስጥ ድንጋጤ ለቀቀ፡፡ ጀርባቸውን አዞሩ፡፡ ሙስሊሞች አሳደዷቸው፡፡ እየማረኩ፣ እየገደሉ ጨለማው ጋረደ፡፡ ሙስሊሞች ድል አድርገው የበላይነትን ተጎናፀፉ። 🍂 ከመስቀላዊያን ጦረኞች ሺዎች ተገድለዋል፡፡ ልካቸውን አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ ብዙ ጳጳሳትም በሠይፎች አንገታቸው ተቀነጣጥሷል፡፡ 🌸 ሙስሊሞች ልክ የሌላቸው የጦር ፈረሶች፣ ሠይፎች፣ ጋሻዎችና የተለያዩ የጦር ዕቃዎችን ማርከዋል፡፡ አንድ ትልቅ ጳጳስ የንጉሡም አማች የሆነ ማርከው ይዘዋል፡፡ #ተኽለመድህን ይባላል፡፡ ወደ ሀገራቸው ይዘውት ሄዱ፡፡ አምስት መቶ ወቄት ወርቅ ቤዛ ከፍሎ ነፍሱን ታደጋት፡፡ 🍂 ከዚያም ኢማሙ ወደ ሀገሩ ወደ “ሐረር” በተጠናከረ የድል አድራጊነት መንፈስ፣ የአሸናፊነትን ሞገስ የተጎናጸፈ ሆኖ በረጀብ ወር መጀመሪያ በዚያው ዓመት የመልስ ጉዞ አደረገ፡፡ የኢማም አህመድ ታሪክ እንኳን በተከታታይ ቀርቦ ይቅርና በመፅሀፍ ራሱ ተፅፎ ያዳግታል እና ለጊዜዉ የኢማሙ ታሪክ ጋብ አድርገን የባለቤቱ ባቲ ድል መንበራ ታሪክ እንቀጥላለን......🌸 ⚠️ ⭕️ ይህም የሆነበት ምክንያት ባለቤቱ በጅሀዱ ወቅት ትልቅ አስተዋፅኦ ስላበረከተች ልንዘክራት የግድ ይላል የሶን ስንጨርስ የኢማሙ ታሪክ እንቀጥለዋለን...! ኢንሻ አሏህ ይቀጥላል...! 🈴JOIN ➲https://t.me/+XBeaC-I2mctmNjE8
Показать все...
🗡ታላቁ ሙጃሒድ ኢማም አህመድ አል’ጋዚ⚔️ ➿ 🌀 ኢማሙ አህመድ ኢብን ኢብራሂም አል'ጋዚ 🌸 ፡ PART ❺ ፡ “እናንተ ወንድሞቼ በአላህ እንመካ፥ በብዛት   አደለም   ቅዋ    የሚለካ፥ እንዲያማ  በሆነ  መስፈሪያ ሚዛኑ፥ በበድር ሜዳ  ላይ እንደዛ  ባልሆኑ ፥ ሺ  ሆነው  ጀምረው   ባልተበታተኑ።” ብሎ አርቆ መክሮ.....! አጠንክሮ ነግሮ .......! ወደ ፍልሚያ ሜዳ ወደ እሳቱ ገብተው፥ በድል ተመለሱ ዲኑን ነጃ አውጥተው፥ በቆፈሩት  ጉድጓድ  ገቧት በየተራበሽንብራ ኩሬ ኢስላም ታሪክ ሰራ። 🍂 ኢማሙ አህመድ ተነሳና ባልደረቦቹ መሀል ቆመ፥ አላህን አመሰገነ፥ አወደሰው፡፡ በነቢዩም ﷺ ላይ ሰለዋት አወረደ አላሁ'መ ሰሊ ወሰሊም ዐለይሂ.....🌸 ♻️ በመቀጠልም የጦር ባልደረቦቹን “እናንተ የጉብዝናና የመከራ ባለተቤቶች ናቸሁ” አለ፡፡ ዝግጁና ጥንቁቅ እንዲሆኑም አዘዛቸው፡፡ “ሰዎች ሆይ! በአላህ ተወከሉ! በአላህ የማመንን ገመድ አጥብቁ” በማለት መከረ፥ ሙስሊሞች ነቃ ተጋ አሉ፡፡ ፈረስ ጋላቢ ሙስሊሞች ከፊሉ ከፊሉን የሚያበረታቱ ሆነው መጡ፡፡ 🍂 ኢማሙ “ምን ሀሳብ አላችሁ?” ሲል ጠየቀ፡፡ የኢማሙ አህመድ ባልደረቦች ተናገሩ፡፡ እንዲህም አሉ- “እኛ በአላህ መንገድ መጋደል ዓላማችንና ምኞታችን ነው፣ የሠይፍን ምትና የጦርን ውጋት ተቋቁመን ጀነትን ለማግኘት እንጓጓለን። ከመታገስም አንወገድም። አላህ በመካከላችን እስከሚፈርድም ድረስ እንታገሳለን እርሱ የተሻለ ፈራጅ ነውና” አሉ፡፡ 🍂 ኢማሙ በንግግራቸው ተደሰተ፡፡ “አላህ ወፍቋችኋል መርጧችኋልም። ለወሳኙ ፍልሚያ ተዘጋጁ” አላቸው፡፡ የአላህን ዲን የበላይ ለማድረግ ጂሃድ ሊዋጉ መሆናቸውን እያሰቡ ዕሉቱን በደስታ ስሜት አሳለፉ፡፡ 🍂 ፈጅሩ ወገግና ወለል እንደማለት እያለ ሲመጣ ሙአዚኑ ሐያ ዐለል ፈላሕ በማለት ተጣራ፥ ሙስሊሞች ተነስተው ቆሙ፡፡ የሱብሒን ሰላት ሰገዱ፡፡ ♻️ “ሽንብራ ኩሬ”ን አቋርጠው ወደ ምሥራቅ “አፋዚዤ” ተጓዙ፡፡ የሐበሻ ንጉሥ ከፊት በኩል ከወደ ምሥራቅ አቅጣጫ መጣና ሙስሊሞች ላይ እንደተበተነ አንበጣ ግልብጥ አለባቸው፡፡ ለጳጳሳቱም ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ክፍለ ጦሮቹንና የጦር ዓርማዎቻቸውን ይዘው የሚንደቀደቅ ጅረት መስለው ወጡ፡፡ ሁለቱ ጭፍሮች ተፋጠጡ፡፡ ካፊሮች ቆሙ፡፡ የጦር ኃይልቻቸውንና ክፍለ ጦሮቻቸውን ዝግጁነት ፈተሹ፡፡ 🍂 ሰባት የውጊያ ረድፎችን ሠርተዋል፡፡ እያንዳንዱ ረድፍ የግራ የቀኝ ጫፉ አይታይም፡፡ 🌸 በሙስሊሞች የጦር ሰልፍ የግራ ክንፍ ላይ የሱማሌ ጎሳ አባል የሆነችው “ሀርቲ” ትገኛለች፡፡ በሷ ምድብ ውስጥ በጉብዝናቸውና በጥንካሬያቸው የሚታወቁ ሶስት መቶ ክንደ-ብርቱ ሰይፈኞች አሉ፡፡ ከያባሬ ጎሳም ወደ አራት መቶ የሚሆኑ እግረኛ ቀስተኞች ነበሩ፡፡ ኢማሙ በመሀከለኛ ረድፍ ላይ ከተጣዱት አምስት መቶ ተዋጊዎች ጋር ደመራቸው፡፡ እንዲህም አላቸው- “ቦታችሁ ላይ እርጉ፣ አንዳችሁም ንቅንቅ እንዳትሉ” ➿ የገሪ ጎሳ በፈረስ ግልቢያ ከሚታወቁት ትመደባለች። ኢማሙ የጦር ሰልፉን አንዳደራጀ ሁለት ሁለት ረከዓ እያደረገ በጀመዐ ሰገደ፡፡  ♻️ ፈቂሁ ዓብደላህ ከበቅሎው ጀርባ ላይ ወረደ፡፡ ጋሻውንና ሠይፉን አቅንቶ ያዘ፡፡ ለአላሁ ተዓላ ተናነሰ፡፡ ዛሂድ፣ አላህን ፈሪ፣ ዓቢድና ዓሊም ነበረ፡፡ ካፊሮችን ሲመለከት ራሱን መያዝ አልቻለም፡፡ በአላህ መንገድ ለመጋደል የሚናፍቅና የሚቸኩል ሁነ። እንደተቆጣ የግመል ኮርማ አቅበጠበጠው፡፡ የፍጥረታቱን ጌታ ደስ ማሰኘትና የተመኘውን እንዲሰጠው ሲል መታገስ አልሆነለትም፡፡ 🌸 ጦርነቱ ተጀመረ። ሁለቱ ሠራዊቶች ተገናኙ። የቀስተኞች ፍላፃ አየሩን ሞላው። ሠይፍ ከሠይፍ ተጋጨ። የፈረሶች ኮቴ ያስነሣው አቧራ ወደ ሰማይ ተበትኖ እንደደመና ፀሐይን ጋረዳት። 🌸 የዐፄ ልብነ ድንግል ጦር ጥቃቱን አፋፋመ። ወደ ማሸነፍ ተቃረበ። ፡ በግራ በኩል የሶማሌያውያን ጦር ሁሉም በጎሣው አለቃ መሪነት ተሰልፈዋል። ጦርነቱ ሲያይል ከግራው የሙስሊሞች ብርጌድ ሦስት ሺህ ሙስሊሞች ተሰዉ።  በተለያየ አቅጣጫ ሙጃሂዶች መሰዋታቸው እየበዛ ሄደ። ማፈግፈግም ሆነ መሸሽ ብሎ ነገር የለም። ጦርነቱ በረታ። አቧራ አየሩን ሞላው። ጦሩ የራሱን ወገን መለየት ሁሉ አቃተው። "አላሁ አክበር!"… "የሙሐመድ ጦር ጽኑ…" "ላ ኢላሃ ኢለላህ…" "ድል የሙስሊሞች ነው" የሚሉ መፈክሮች በተደጋጋሚ በሙጃሒዶቹ መካከል እዚያም እዚህም ይሰማሉ። 🌸 ሙጃሒዶች ንቅንቅ ሳይሉ መጋደል ቀጠሉ። 🌸 የዐፄውንና የኢማሙን ጦር ብዛት ልዩነቱ ሰፊ ነው። 216,000 ለ 12,560 እያንዳንዱ የኢማሙ አህመድ ወታደሮች እያንዳንዳቸው 17 የአፄዎችን መስቀላዊያን ጦር ወታደሮችን ነበር የገጠመው . . . . . .‼️ ⚠️ #ኢንሻ_አሏህ_ይቀጥላል...🙏 🈴JOIN ➲https://t.me/+XBeaC-I2mctmNjE8
Показать все...
🗡 ታላቁ ሙጃሒድ ኢማም አህመድ አልጋ’ዚ⚔️ ➿ 🌀 ኢማሙ አህመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ 🌸 ፡ PART ❹ ፡ ዲኑን ለመጠበቅ  ሕይወቱን ሊገብር ከሽንብራው ሜዳ ከኩሬው ጋራ ስር አንገቱን ቀና አርጎ "አንተ የበድር ጌታ ለነሱ እንደዋልከው ለኛም ዋል ውለታ፥ ነስር [እርዳታ] ለኛ ይሁን አድርገን የማን ረታ"የኢማሙ ጦር የዳዕዋ ክፍል ሙስሊሙን ማነሳሳት ጀመረ። 🍂 #ኡስታዝ አቡበክር ቢን ነስረዲን (ዓርሹናእ) ለሙስሊሙ ሠራዊት ስለ ጂሃድ ዳዕዋ ማድረግ ጀመሩ። ስለጀነት ታላቅነት፣ ለኢስላም ሲሉ በጽናት መዋጋት እንዳለባቸው መከሩ። ሸሂድ መሆን አላህ ዘንድ ያለውን ደረጃ በማስታወስ ሙጃሂዱን አስለቀሱ። ብዙ መከሯቸው። የጂሃድ ስሜታቸውን አነሳሱ። ስለጂሃድ ደረጃ የሚያወሱ የቁርኣን አንቀፆችን አነበቡላቸው። ሠራዊቱ የጂሃድ ስሜቱ ተቀጣጠለ። ወኔው ተቀሰቀሰ። ለኢስላም ሲል ለመሞት ቆረጠ። 🍂 ኢማሙ አህመድን "በአፄዎቹ የሚመሩትን መስቀላዊያንን እናጥቃቸው" ሲል ጠየቀ። ኢማሙ ግን "ቦታችሁን ያዙ። እነርሱ መጋደል እስኪጀምሩ ድረስ ጥቃት አትጀምሩ። ጦራችሁን በተጠንቀቅ ያዙ። ከቆዳ የተሠራውን የጦር መከላከያ ልብስም ልበሱ። አላህን እያስታወሳችሁ ቢሆን እንጂ ለአንዲት እርምጃ እንኳን እግራችሁን አታንቀሳቅሱ" ሲል አዘዘ። 🍂 "አላህ ሆይ! ሁላችንንም ታጋሽና ለሃይማኖትህ አሸናፊዎች አድርገን" ሲል አላህን ለመነ። ➿ ⭕️ ሽንብራ ኩሬ ሲወሳ‼️ በአራተኛው ቀን ኢማሙ ክፍለ ጦሮቹን አስከተተ፡፡ የንቅናቄው አቅጣጫ “ግንደበለት” የምትባል ከተማ ናት፡፡ መንገድ መሪው ፈረሰኛው አሚር አህሙሽ ቀይዋን ባንዲራ ከፍ አድርጎ ከሠራዊቱ ፊት ፊት ቀድሟል፡፡ ቀኑን ሙሉ ወጣ ገባ በበዛው ሰበርባራ መሬት ተጓዙ፡፡ ሰውም ከብቱም ደከመ፡፡ ከመንገዱ ጥበትና ጨነቅናቃነት የተነሳ የኢማሙን ሚስት በሰዎች ትከሻ ላይ አንከብክቦ መጓዝ የግድ ብሏል፡፡ ፀሐይ ስትረግብና የመግሪብ ወቅት በገባ ጊዜ ሠራዊቱ እርጋ ተባለና የኢማም አህመድ ድንኳን “ድቄ” የተባለ ቦታ ላይ ተተከለች፡፡ 🍂 ሥፍራው የጫት ተክል ይበዛበታል፡፡ ድንኳን ተከላውን ያካሄደው ከሠራዊቱ ቀዳሚ ረድፍ ላይ የነበረው አሚር አህሙሽ ከብዙ ልፋት በኋላ ነበር ድንኳኑን ማቆም የቻለው። 🍂 ዘጋቢው  እንዲህ ይላል - ለሊቱ ሲጋመስ ኢማሙ ከጦሩ የኋላ ረድፍ ወደ ማረፊያ ድንኳኑ ማዘዣ ጣቢያው መጣ፡፡ ሁሉም መንገድ አድክሟቸው ስለነበር ዝም ብለው ተኙ፡፡ ሰውነታቸው ከመዛሉ ብዛት እህል ውሃ መቅመስ አልቻሉም፡፡ ጦሩ ማልዶ ተነሳና “ባዘምሊ” ወደምትባል ቀጣይ መዳረሻ ንቅናቄ አደረገ፡፡ 🍂 በቀጣዩ ቀን መንገድ መሪያቸው መንገድ ሳተባቸው፡፡ ይዟቸው ዛፎች ጥቅጥቅ ወዳለበት ደናማ መሬት ገባ፡፡ “ይህቺ የምትታወቅ መንገድ ነበረች፣ የሚሄድባት ሰው እያነሰ በመምጣቱ ፋናዋ የጠፋ ይመስላል” አለ መንገድ መሪው ለኢማሙ አህመድ። ርቀው አልተጓዙም፡፡ እንደ አዙሪት እየሆነባቸው እዚያው ደኖቹ መሃል ራሳቸውን ያገኛሉ፡፡ ዛፎቹ እርስ በርስ ተጋምደዋል፡፡ መውጫው በየት እንደሆነ ማወቅ አልተቻለም፡፡  ሙስሊሞቹ ዛፎች መሃል እንደታገቱ ናቸው፡፡ 🍂 ኢማሙ አህመድ ወደ ጦሩ በመዞር  - “ዛፎቹን በሠይፎቻችሁ በሏቸው” አለ፡፡ ትላልቅ ዛፎች ነበሩ፡፡ ጦሩም የተመከረበትን ፈጸመ፡፡ ከዱሐ ሰላት የጀመሩ ለመግሪብ ወቅት ፀሐይዋ እስከምትቃረብ ድረስ ዛፉን በሠይፍ ገነዳደሱት፡፡ “ኩፋሮችን ነበር የምንጋደለው አሁን ግን ዛፎችን መዋጋት ይዘናል” አለ ኢማሙ አህመድ፡፡ ሥራውን አጠናቀው ወደ ገላጣ መንገድ ሲወጡ ግን ተአጀቡ፡፡ አላህንም አመሰገኑ፡፡ || ⚠️ #ኢንሻ_አሏህ_ይቀጥላል...! 🈴JOIN ➲https://t.me/+XBeaC-I2mctmNjE8
Показать все...
🗡 ታላቁ ሙጃሒዱ ኢማም አህመድ አልጋ'ዚ ⚔️ ➿ 🌀 ኢማሙ አህመድ ብኑ ኢብራሂም አልጋዚ 🌸 ፡ PART ❸ ፡ ኢማሙ አህመድ ከቦታ ቦታ ይሸሽ ጀመሩ። ሱልጣኑ ሸሪዓን የሚጠብቅ ከሆነ #ኢማሙ_አህመድ ለሱልጣኑ ሊታዘዝ በዑለመሞች ጫና ዳግም ተስማሙ። ➿ መስፈርቱ ለጥቂት ጊዜያት ተፈፃሚ ሆነ ነገር ግን ዳግም ሱልጣኑ ወደ ነበረበት አቋም ተመለሰ። ፈሳድ ተስፋፋ። ⚠️ ዑለሞች ለሦስተኛ ጊዜ ለማስማማት ጣሩ። አሁን ግን ሱልጣኑ ስምምነቱን ተቃወመ። ኢማሙ አህመድን ለመግደልም ዛተ፥ ጦር አዘመተ። ፡ ኢማሙ አህመድ ለፈሳድ መስፋፋት ምክንያት የሆነውን ሱልጣን አቡበክርን ማስወገድ ብቸኛ መፍትሄ ሆኖ አገኘው። ጦርነት ገጠመው። ሱልጣን አቡበክር ተገደለ። የሱልጣኑን ወንድም ዑመረዲንን በሱልጣንነት ሾመ።  🍂 ብዙም ሳይቆይ #ደገልሃን የተሰኘው የዐፄ ልብነ ድንግል አማች ደገልሃን መልአከ ኃይል አዳልን አጠቃ። ኢማም አሕመድ ከሐረር በስተደቡብ ምዕራብ በሚገኘው አማሬሳ ወንዝ አቅራቢያ ጦሩን አደራጀ። #ደገልሃንን ‹ዲር› በተሰኘ ሥፍራ ኢማሙ ድል አደረገ። በርካታ ሠራዊትን ማረከ። ወደ ሱማሌ ክልል በመሄድ መረጋጋትን አሰፈነ። ተበታትኖ የነበረውን ሕዝበ ሙስሊም አደራጀ። አሰለጠናቸው፥ በስነ ምግባር አንጾ ለጂሃድ አዘጋጀ። የ21ዓመቱ ኢማሙ አህመድ ሠራዊቱን ይዞ እ.አ.አ. በ1527 (በ934 ዓመተ ሂጅራ) በድል አድራጊነት ሐረርን ተቆጣጠረ። 🌸 ሠራዊቱንም በክፍለ ጦር አዋቀረ። በአሚር ሑሴን አል ታጉሪ የሚመራውን ፈረሰኞች እና እግረኞች ያለበትን ክፍለ ጦር ቀይ ባንዲራ አስይዞ አዘመተ። 🍂 መቶ ፈረሰኞችና እግረኞች ያሉበትን ሌላ ክፍለ ጦር በወዚር ኑር መሪነት ነጭ ባንዲራ አስይዞ ለጂሃድ አሰማራ። 🍂 ሁለት መቶ ፈረሰኛና እግረኞች ያሉበትን ሠራዊት ኢማሙ በራሱ መሪነት በቢጫ ባንዲራ ሥር አዋቀረ። ሰባት ሺህ እግረኛ ጦርን በአምስት አሚሮች ሥር አዋቀረ። ➿ የክርስቲያኑ ጦር ሙስሊሙን ለማጥቃት ሲመጣ መመከቱ እንደሚያስጠቃ የተረዳው ኢማም ከመከላከል ይልቅ የማጥቃት ስትራቴጂን ተከተለ። ♻️ ትግሉ በሙስሊሙ ክልሎች ሳይሆን በመስቀለኛዎቹ ዐፄዎች ይዞታ ውስጥ መሆን እንዳለበትም ወሰነ። #ደዋሮን በማጥቃትም ከክርስቲያኑ መንግሥት አገዛዝ ነፃ አወጣ። ወደ መስቀላዊያኑ ከተማ ጦሩን ሄዶ እንዲያጠቃም አዘዘ። ➿ የኢማሙ አህመድ ባለቤት ባቲ ድል ወንበሯ እስከ ኢፋት ድረስ ሸኘቻቸው። ኢማሙ አህመድ ከሽንብራ ኩሬ ጦርነት በፊት የተለያዩ ድሎችን ቢያስመዘግብም ሽምብራ ኩሬ ግን ወሳኙና የዐፄውን ጦር ወኔ ያላሸቀ ነበር። 🌸 #ሽንብራ_ኩሬ በአዳማና ቢሾፍቱ መካከል በሞጆ ወንዝ አቅራቢያ ነበር የተካሄደው። 🍂 ኢማም አሕመድ ጦሩን አደራጅቶ ከጨረሰ በኋላ ከዝቋላ ወደ ሞጆ ወንዝ አቅራቢያ ተጓዘ። ስትራቴጂያዊ በሆነው የሽምብራ ኩሬ መንደር ጦሩን አሰፈረ። የዐፄ ልብነ ድንግል ጦር ኢማሙ ዝቋላን ለቆ መሄዱን ተመለከተ። ወደ ሞጆ ተከተለው። የሽንብራ ኩሬ ጦርነት ሊጀመር ነው። ልብነ ድንግል 16 ሺህ ፈረሰኞችና 200 ሺህ እግረኛ ጦር አሰልፏል። ➿ #ኢማም_አሕመድ  560 ፈረሰኞችና 12 ሺህ እግረኞች ያሉት ሠራዊት አሰልፏል። ሙስሊሙን ሲጨፈጭፍ የነበረው የዐፄው ጦርና ኢማሙ አህመድ ሊጋጠሙ ተፋጠዋል።  🍂 #1 ለ17 ሙስሊሞች አንድ መስቀላዉያን አስራ ሰባት በአቬሬጅ ማለት ነዉ የኢትዮጵያ ታሪክ የቀየረዉ የሽብራ ኩሬ ጦርነት ሊጀመር ነዉ...! ⚠️ ኢንሻ አሏህ ይቀጥላል...! 🈴JOIN ➣https://t.me/+XBeaC-I2mctmNjE8
Показать все...
01:04
Видео недоступноПоказать в Telegram
ሸይኽ አብዱል'ዐዚዝ ኣራያ ሀፊዞሁሏህ ሙጀሲማዎች ለመክፈራቸው ያዘጋጁት ምርጥ ኪታብ #በትግራይ_ቲቪ የምርቃን ፕሮግራሙ ቀርቧል። ♻️ ለእኛ በ PDF ደርሶናል እንልክልዎታለን! #JOIN_US 🌸 https://t.me/+XBeaC-I2mctmNjE8
Показать все...
3.56 MB
ሸይክ ሐጅ ኑራድስ ወሎ-መርሳ [ረሒመሁሏሁ] 🌀 🗣 ስለሙጀሲማ ምን አሉ? 👂 አብረን እናዳምጥ ⚠️ ሙጀሲማዎችን ተከትሎ መስገድ አይበቃም ‼️ ⚠️ አሏሕ በአቅጣጫ በቦታ አይገልፅም ‼️ ⚠️ አሏሕን በቦታና በአቅጣጫ የሚገልፅ ይከፍራል‼️ ➿ JOIN ➣https://t.me/+XBeaC-I2mctmNjE8
Показать все...
0.71 KB
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.