cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™

#አባቶችን_ጠይቅ_ይነግሩሃል ● ጠቢብ ከሰነፍ ጋር ቢጣላ፥ ሰነፍ ወይም ይቈጣል ወይም ይስቃል፥ ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ፍጹሙን ሰው ይጠላሉ፥ ደግሞም የቅኑን ሰው ነፍስ ይሻሉ። ሰነፍ ሰው ቍጣውን ሁሉ ያወጣል፤ ጠቢብ ግን በውስጡ ያስቀረዋል። ○ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ. 29 ○ ሀሳብ ካላችሁ @habmisget

Больше
Рекламные посты
23 201
Подписчики
+3424 часа
+5257 дней
+1 66530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ + የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው:: ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል:: እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል:: ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን:: ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው:: በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ:: ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም:: ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል::  የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም:: የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው:: ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ?  እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም? ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም? እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ:: አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው:: ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :- "ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29) @mekra_abaw
Показать все...
Показать все...
💕መስከረም🌸
💕ጥቅምት🌸
💕ኅዳር🌸
💕ታህሳስ🌸
💕ጥር🌸
💕የካቲት🌸
💕መጋቢት🌸
💕ሚያዝያ🌸
💕ግንቦት🌸
💕ሰኔ🌸
💕ሀምሌ🌸
💕ነሀሴ🌸
💕🌸🌸ጷግሜ🌸🌸💕
Показать все...
3🙏 1
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ አባ መቃርስ ካልዕ +"+ +ይህ ቅዱስ "መቃርዮስ: መቃርስ: መቃሬም" ይባላል:: ትርጉሙ በ3ቱም መንገድ አይለወጥም:: ምክንያቱም ሥርወ ቃሉ በዮናኒ ልሳን "ብጹዕ: ንዑድ: ክቡር" ማለት ነውና:: +ከስሙ ቀጥሎ "ካልዕ-2ኛው": አንዳንዴ ደግሞ "እስክንድርያዊ" እየተባለ ይጠራል:: "ካልዕ-2ኛው" የሚባለው ከቀዳሚው (ታላቁ መቃርስ) ለመለየት ሲሆን "እስክንድርያ" ደግሞ ተወልዶ ያደገባት ሃገር ናት:: +አባ መቃርስ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ገዳማዊ: ጻድቅና ትሩፈ-ምግባር ነው:: በዓለም ለ40 ዓመት ሲኖር እንደ ሕጉ ፈጣሪውን ደስ ያሰኘ ሰው ነው:: ጻድቃን እንደ ከዋክብት በበዙበት በዚያ ዘመን የታላቁ መቃርስን ዜና ሰምቷልና ይህቺን ክፉ ዓለም ከነግሳንግሷ ንቋት በርሃ ገብቷል:: +እንደሚገባ ሥርዓተ ገዳምን ጠብቆ: ለአበው ታዞ: በጾም: በጸሎት: በትሕትናና በስግደት ተጠምዶ ቢያገኘው ፈጣሪ አከበረው:: በዚያ ጊዜም ለታላቁ ገዳመ አስቄጥስ መናንያን አበ ምኔት ሊሆን መረጡት:: +እርሱም እረኝነትን ያውቃልና በጐቹን (መነኮሳትን) ከተኩላ (ሰይጣናት) ይጠብቅ ዘንድ ብዙ ተጋ:: ከብቃቱ የተነሳም ሳያስታጉል: ሳይበላ: ሳይጠጣና ሳይቀመጥ እስከ 40 ቀን ይጸልይ ነበር:: ሲጸልይ ደግሞ በልቡ እየተቃጠለ በፍቅረ ክርስቶስ ነበርና አጋንንት ይርዱለት ነበር:: +እርሱ ጸሎት ሲጀምርም በገዳሙ ዙሪያ ያሉ አጋንንት እየጮሁ ይሸሹ ነበር:: ከተጋድሎው ጽናትና ከትሕትናው ብዛት የተነሳ ያዩት ትዕቢተኞች ሁሉ ይገሠጹ ነበር:: በዘመኑም ብዙ ተአምራትን ሠርቷል:: +አንድ ቀን በበዓቱ ሳለ ጅብ መጥታ ተማጸነችው:: አብሯት ወደ ዋሻዋ ቢሔድ ልጆቿ በሙሉ ዓይነ ሥውራን ሆነው አገኛቸው:: እርሱም ወደ መሬት ምራቁን እትፍ ብሎ በጭቃ ለውሶ ቢቀባቸው የሁሉም ዐይናቸው በርቷል:: +ስለ ውለታውም ጅቢቱ የበግ ቆዳ እየጐተተች አምጥታ ሰጥታዋለች:: (ከሰው ልጅ በቀር እንስሳት ውለታን አይረሱምና) ቅዱስ መቃርስም ለወትሮው ባዶው መሬት (አፈር) ላይ ይተኛ የነበረው ከዚያ ቀን በኋላ በአጐዛው ላይ የሚተኛ ሁኗል:: +በሃገሩ እስክንድርያም ለ2 ዓመታት ዝናብ በመጥፋቱ ሕዝቡ ተጨንቆ ነበርና "ናልን" ሲሉ መልዕክት ላኩበት:: እርሱ መጥቶ ሲጸልይም መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ ጣለ:: ዝናቡም ያለ ማቆም ለ2 ቀናት በመዝነቡ ሕዝቡ ፈርተው "አባታችን ስለ ኃጢአታችን እንዳንጠፋ ለምንልን?" አሉት:: እርሱም በጸሎቱ (በፈጣሪው ኃይል) እንደ ወደዱት ዝናቡን አቁሞላቸዋል:: +የአባ መቃርስን ዜና ሕይወትና ተአምራት ተናግሬ አልፈጽመውም:: ግን አንዲት ብቻ ላክል:: ሁሌ ሳስበው ስለሚገርመኝም ነው:: +ብዙዎቻችን የጌታችን ሥጋና ደም አንቀበልም:: ለምን ያከበርነውና የፈራነው አስመስለን ኃጢአትን ለመጥገብ ቦታን ( አጋጣሚን) ስለምንፈልግ:: በተቃራኒው ደግሞ አንዳንዶቻችን መለኮት የተዋሐደውን የጌታ ሥጋና ደም እንደ ተርታ ነገር (ያለ ጥንቃቄ) ስንቀበል ይታያል:: 2ቱም ግን ስሕተት ነው:: +ፈርተን (ፍርሃቱ ጤነኛ ባይሆንም) ስለ ራቅን በፍርድ ቀን ማምለጥ አንችልም:: "ሥጋየን ያልበላ: ደሜንም ያልጠጣ የዘለዓለም ሕይወት የለውም" ይለናልና:: (ዮሐ. 6:52) +በድፍረት ለምንቀበልም ሥጋው እሳት ሁኖ እንዳይበላን: ደሙም ባሕር ሆኖ እንዳያሰጥመን ልናከብረው ይገባናል:: "ሳይገባው ከጌታ ሥጋና ደም የተቀበለ የጌታ ሥጋ ዕዳ አለበት" ይለናልና:: (1ቆሮ. 11:27) << ታዲያ የሚሻለው ለሁላችንም ንስሃ ገብቶ: በፍርሃት ሆኖ መቅረቡ ነው:: >> +ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና አባ መቃርስ ወደ በርሃ እንደ ገባ ሥጋ ወደሙን ተቀብሎ ነበር:: ቅዱሱ ይህንን እያሰበ ለ60 ዓመታት ምራቁን ሳይተፋ ኑሯል:: ለዚያ አይደል አበው "ብታከብሩት ያከብራቹሃል" ያሉት:: +ሊቃውንቱም ይህንን ሲያደንቁ:- "ኢታስተማስልዎ ለቁርባን ከመ ሕብስት ዕራቆ:: አኮኑ ሥጋ መለኮት ዘይትላጸቆ:: መቃርዮስ አብ ዕበየ ቁርባን ለአጠይቆ:: ድኅረ ተወክፈ በአሚን እንበለ ያብዕ ናፍቆ:: መጠነ ዓመታት ስሳ ኢተፍአ ምራቆ::" ብለዋል:: +ቅዱስ መቃርስም በ100 ዓመቱ በ5ኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በዚህች ቀን ዐርፏል:: ❖ጌታችን ከክብሩ: ከበረከቱ አይለየን:: =>ግንቦት 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አባ መቃርስ ገዳማዊ 2.እናታችን ቅድስት ሰሎሜ ኢትዮዽያዊት 3.አባ ይስሐቅ ጻድቅ 4.ቅድስት ዲላጊና 4 ሴት ልጆቿ (ሰማዕታት) 5.ቅዱስ ዳናስዮስ ሰማዕት 6.ቅዱስ በንደላዖስ ሰማዕት (የታላቁ ኤስድሮስ አባት) 7.አባ አሞን ጻድቅ (ዽዽስናን አልፈልግም ብሎ የሸሸ አባት) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም 2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን 3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል 4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ 5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ 6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ 7.ቅድስት ሰሎሜ 8.አባ አርከ ሥሉስ 9.አባ ጽጌ ድንግል 10.ቅድስት አርሴማ ድንግል =>+"+ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው:: እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ:: ሥጋዬ እውነተኛ መብል: ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና:: ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል:: እኔም በርሱ እኖራለሁ:: +"+ (ዮሐ. 6:53-56)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> @mekra_abaw✝️❤️🙏
Показать все...
👍 2
💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️ 💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️ 👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️ ⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️ 🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️ በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት                 👇👇👇      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel 👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽          የይቱብ ቻናላችን              🔔   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌ ❤️በናታኒም ቲዩብ❤️          👇🏽👇🏽 https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
Показать все...
❤️ናታኒም ቲዩብ❤️
💁‍♂ትዳር ማለት ምን ማለት ነው⁉️
⛪️ቤተክርስቲያን በትዳር ዙያ ምን ታስተምራለች⁉️
💁‍♂የትዳር መሰረቱ ምን ድነው⛪️
Показать все...
🔐ክፈት🔐
💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️ 💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️ 👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️ ⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️ 🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️ በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት                 👇👇👇      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel 👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽          የይቱብ ቻናላችን              🔔   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌ ❤️በናታኒም ቲዩብ❤️          👇🏽👇🏽 https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
Показать все...
❤️ናታኒም ቲዩብ❤️
💁‍♂ትዳር ማለት ምን ማለት ነው⁉️
⛪️ቤተክርስቲያን በትዳር ዙያ ምን ታስተምራለች⁉️
💁‍♂የትዳር መሰረቱ ምን ድነው⛪️
Показать все...
💕መስከረም🌸
💕ጥቅምት🌸
💕ኅዳር🌸
💕ታህሳስ🌸
💕ጥር🌸
💕የካቲት🌸
💕መጋቢት🌸
💕ሚያዝያ🌸
💕ግንቦት🌸
💕ሰኔ🌸
💕ሀምሌ🌸
💕ነሀሴ🌸
💕🌸🌸ጷግሜ🌸🌸💕