cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

🇪🇹Ethiopia🇪🇹🇪🇹 News🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

True Breaking News

Больше
Не указана странаНе указан языкНе указана категория
Рекламные сообщения
153Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረችሁ መልዕክት አስተላለፉ ------------------------- ግንቦት 05/2013 (ዋልታ) -ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ1ሺህ 442ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ ዓልፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዚዳንቷ በትዊተር ገጻቸው ላይ ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በደህና አደረሳችሁ ብለዋል። በዓሉን በቤታቸው ለማክበር ዕድሉን ያላገኙትን ወገኖቻችንን በማስታወስ ፣ በመደገፍና ያለንን በማካፈል ልናከብር ይገባል ብለዋል ። በዓሉ የሰላምና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
Показать все...
ዶ/ር አብርሃም በላይ ለኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረችሁ መልዕክት አስተላለፉ --------------------------------- ግንቦት 05/2013 (ዋልታ) - የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ ለህዝበ ሙሰሊሙ እንኳን ለ1ሺህ 442ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል። ይህን በአል ስናከብር አንድነታችን ይበልጥ የምናጠናክርበትና በተለያዩ ቦታዎች የተፈናቀሉ ወገኖች የምናግዝበት በአል ሊሆን ይገባል ብለዋል። በተጨማሪም የተቸገረን በመርዳትና በመተሳሰብ መሆን አለበት ብለዋል ዶ/ር አብርሃም በላይ በመልእክታቸው፡፡
Показать все...
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የቢላሉል ሐበሽን ማዕከል ጎብኙ ------------------------- ግንቦት 05/2013 (ዋልታ) - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ጥንታዊ እስላማዊ ቅርሶች መገኛ የሆነውን ቢላሉል ሐበሺ የማህበረሰብ ሙዚየምን ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡ ማዕከሉ የኢትዮጵያውያንን ችግሮች ለመፍታት፣ ድኾችን ለመርዳትና ዕውቀትን ለማስፋፋት የሚያደርገው ጥረት አድንቀዋል። በተለይም የረዥም ዘመናት ታሪክ ያለውን የኢትዮጵያን እስልምና ቅርሶች ለማሰባሰብና ለትውልዱ ለማሳየት የተመሠረተው ሙዝየም በከተማችን ሊጎበኙ ከሚገባቸው ቦታዎች አንዱ ነው ሲሉም ገልፀዋል። ተቋሙ ከዚህ የበለጠ ነገር ለኢትዮጵያ እንደሚሠራም እምነቴ ነው ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።
Показать все...