cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የምዕመናን መረጃ መለዋወጫና ትምህርት መስጫ አውታር ነው፡፡

Больше
Рекламные посты
35 057
Подписчики
+1024 часа
-147 дней
+66330 дней
Архив постов
በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የሚከበረው የጌታችን ትንሣኤ ለሰው ልጅ ያለው መንፈሳዊ ትርጉም እጅግ የላቀ ነው፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን በሙሉ በተለይም የሰው ልጅን ሲፈጥር በፍጹም ፍቅር ነው፡፡ ለዚህም የሰው በአርአያ እግዚአብሔር መፈጠር በቂ ማስረጃ ነው፤ ሰው በበደሉ ምክንያት ለሞት ቢዳረግም የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅር ጨርሶ አልተለየውም፤ እግዚአብሔር አንድ ቀን ሞትን ከሰው ጫንቃ አሽቀንጥሮ እንደሚጥል በየጊዜው ይገልጽ ነበረ፤ ያም በራሱ ልዩ ጥበብ እንደሚከናወን አረጋግጦ ለሰው ልጅ ተስፋውን አሳውቆ ነበር፤ ያም ልዩ ጥበብ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዕውቀትና ጥበብ ድንበር የለውምና ከፍጥረተ ዓለም በፊት ሳይቀር የሰው ድኅነት በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንደሚፈጸም በእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ነገር ነበረ፤ ጊዜው ሲደርስም በህላዌና በክዋኔ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ እግዚአብሐር ወልድ የሰውን ሰውነት ተዋሕዶ ሰውን የማዳን ስራውን አንድ ብሎ ጀመረ፡፡ ሰዎች በኃጢአትና በዲያብሎስ በደዌና በሞት ላይ ሥልጣን ያለው አዳኝ እሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ የማዳን ስራውን በመዋዕለ ሥጋዌው በስፋት አከናወነ፡፡ ልዩ ልዩ ደዌና በሽታ የሚያሠቃያቸውን ፈወሰ፤ ኃጢአተኞችን በይቅርታ ተቀበለ፤ ኃጢአታቸውንም ደመሰሰ፤ አጋንንትንም በትእዛዝ አስወጣ፤ ወደ ጥልቁም አሰመጣቸው፤ ዲያብሎስንም ድል ነሥቶ አባረረ፤ ሙታንንም አነሣ፤ በባሕር ላይ በእግሩ ተራመደ፤ ነፋሳትን ገሠጸ፤ በአምስት እንጀራ ከአምስት ሺሕ ሕዝብ በላይ መገበ፤ ውሀውንም ወደ ጠጅ ለወጠ፡፡ ሰውን ሁሉ በፍቅርና በይቅርታ ይቀበልና ያገለግል ነበር እንጂ በአንዱ ስንኳ የመጨከንና የማግለል መንፈስ አላሳየም፤ ይህ ሁሉ ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፍቅር ማሳያ ነበረ፡፡ በፍጥረት ሁሉ ላይ መለኮታዊ ሥልጣን እንዳለውም ማረጋገጫ ነበረ፤ መልእክቱም ዓለም መዳኛዋና አዳኝዋ እሱ መሆኑን አውቃ በአእምሮ እንድትከተለውና የድኅነቱ ተቋዳሽ እንድትሆን ማስቻል ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! በእግዚአብሔር አሠራር ኃጢአት ያለ ቤዛነት አይሰረይም፤ በመሆኑም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ኃጢአተኛ ሆኖ ስለተገኘ ቤዛ ሆኖ የሚያድነው ያስፈልገው ነበር፤ ቤዛ መሆን የሚችለው አካል ደግሞ ራሱ ፍጹም ንጹህ መሆን ነበረበት፡፡ ከዚህም አንጻር በእግዚአብሔር ፊት ለሱ የሚመጥን ንጹህ ኣካል ከፍጡራን ወገን አልተገኘምና እሱ ራሱ ሰው ሆኖ የሰው ቤዛ ለመሆን በሥጋ ተገለጠ፤ በዚህም መሠረት የሰው ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ በመሰቀል ንጹህ ደሙን አፈሰሰ፤ በዚህ ደም ምክንያት የሰው ኃጢአት በሥርየት ተዘጋ፤ ለዚህም ነው ቅዱስ መጽሐፍ “ያለ ደም ሥርየት ወይም ይቅርታ የለም” ብሎ የሚነግረን፡፡ ከዚህ ደም መፍሰስ በኋላ ወደ ሲኦል ወርዶ በዚያ የነበሩ የኃጢአት ግዞተኞችን በሙሉ ፈትቶ ወደ ቀደመ ስፍራቸው ወደ ገነት መለሰ፤ ከስቅለተ ክርስቶስ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ያለው የሰው ኃጢአት በሙሉ በክርስቶስ ደም ይደመሰሳል፡፡ ሆኖም ይህ ሥርየት የሚገኘው በእምነት መሆኑን ቅዱስ መጽሐፍ አበክሮ ይነግረናል፣ በክርስቶስ አምኖ በደሙ የነጻ ሁሉ ክርስቶስ በተነሣው ዓይነት ትንሣኤ ይነሣል፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! የጌታችንን ትንሣኤ ስናከብር የኛንም ትንሣኤ በማሰብ ሊሆን ይገባል፤ ትልቁ ነገርም የኛን ትንሣኤ ማሰቡ ላይ ነው፤ ምክንያቱም የክርስቶስ ትንሣኤ ለኛ ተብሎ የተደረገ በመሆኑ ነው፡፡ የሱ ትንሣኤ ለኛ ትንሣኤ በኲር ነው፤ ማሳያና ማረጋገጫም ነው፤ እግዚአብሔር በየዕለቱ የሚፈልገው የኛን ትንሣኤ ማየት ነው፤ የኛ ትንሣኤ በአንድ ቀን በቅፅበት የሚሆን አይደለም፤ ትንሣኤያችን አምነን ስንጠመቅ ተጀምሮ ከመቃብር ስንነሣ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር ዛሬም እያንዳንዱ ሰው በትንሣኤ ሕይወት እንዲመላለስ ይጠራል፤ ምክንያቱም የኋለኛው ትንሣኤ የሚገኘው በፊተኛው ትንሣኤ እንደሆነ እግዚአብሔር በመጽሓፉ ነግሮናልና ነው፤ በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕ ነው፤ በሱ ላይ ሞት ሥልጣን የለውምና ነው፤ ለሰው ልጆች ተጠብቆልን ያለው ተስፋ ይህ ነው፡፡ ተስፋውን እውን ማድረግ የሚቻለውም በኛ ሃይማኖታዊና ተግባራዊ ተሳትፎ እንደዚሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ ደም ነው፤ የነገውን ትንሣኤ ተሳታፊ ለመሆን ዛሬ መነሣት ግድ ይላል፤ ይህም የሚቻል እንጂ የማይቻል አይደለም፡፡ በእምነት ትንሣኤ፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር ትንሣኤ፣ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ትንሣኤ፣ በፍቅር ትንሣኤ፣ በሰላም ትንሣኤ፣ በይቅርታ ትንሣኤ፣ በመከባበር ትንሣኤ፣ በአንድነት ትንሣኤ፣ በመተሳሰብ ትንሣኤ ወዘተ በመሳሰሉ ሃይማኖታዊና ግብረ ገባዊነት ጸንተን መኖር ከቻልን የፊተኛው ትንሣኤ ማለት እሱ ነው፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር እያንዳንዳችን ይህንን ትንሣኤ እውን አድርገን ስንኖርና ስንመላለስ ማየት ይፈልጋል፡፡ በአንጻሩም ክሕደትን፣ ከሕገ ተፈጥሮ ያፈነገጠ ጸያፍ ተግባርን፣ ጥላቻን፣ ጦርነትን፣ መለያየትን፣ ራስን ብቻ መውደድን፣ መጨካከንን፣ ግብረ ኃጢአትን፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ገንዘብ አለማድረግን፣ ፈጣሪን አለማመንን የተጸየፈ ምእመንን ማየት ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ኃጣውእ አፅራረ ትንሣኤ ናቸውና ነው፤ ኃጣውእ በምድርም በሰማይም የሰው ጠላቶች ናቸው፤ በምድር ለሥጋዊና መንፈሳዊ በሽታ ይዳርጉናል፡፡ በተለይም በእግዚአብሔር ፊት እጅግ አስጸያፊ የሆነው የነውረ ኃጢአት ርኲሰትና በጋብቻ ያልታሰረ ሩካቤ ሥጋ ትውልድን እንደ ቅጠል እያረገፈው እንደሆነ፣ ምንም ዓይነት ፈውስ ላልተገኘለት የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ ዋነኛ መተላፊያም ይህ ነውረ ኃጢአት እንደሆነ ተደጋግሞ ተነግሮአል፡፡ ይሁንና አሁንም ጥንቃቄ በጎደለው ድርጊት ስሕተቱ በመቀጠሉ በጦርነት ከሚያልቀው ሕዝብ ባልተናነሰ በዚህ ገዳይ በሽታ ብዙ ወገን እያለቀ ነውና እባካችሁ ሕዝበ እግዚአብሔር አንድ ለአንድ በመተሣሰርና በተቀደሰ የጋብቻ ሕይወት በመወሰን ትንሣኤያችንን እናብስር፡፡ በመጨረሻም በዓለ ትንሣኤ የእግዚብሔር ፍቅር መገለጫና የተስፋችን ማሳያ መሆኑን በመገንዘብ ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰው ልጆች ደኅንነት በአንድነት በመቆም ለተራቡት፣ ለተጠሙት፣ ለታረዙት፣ ለታመሙትና ለታሰሩትም ሁሉ ካለን ከፍለን በመስጠት ከኛ ጋራ በመንፈስና በሞራል በዓለ ትንሣኤውን እንዲያሳልፉ እናደርግ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን። በድጋሚ በዓሉን የሰላም የዕርቅ የይቅርታ የትንሣኤ ኅሊና ወልቡና ያድርግልን፤   እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን። አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሚያዝያ 27 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
Показать все...
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት / His Holiness Patriarch Office: #ቃለ_በረከት_ዘብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወስድስቱ ዓመተ ምሕረት፡፡ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ፡- የትንሣኤ ሙታን በኲር በመሆን ቀድሞ የተነሣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ! “ወይእዜኒ ክርስቶስ ቀደመ ተንሥኦ እምኲሎሙ ሰብእ ሙታን@ አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኲር ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል” (1 ቆሮ 05.!)
Показать все...
የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ በትናንትናው ዕለት ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ አሳውቀን ነበር። በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን እየገለጽን፣ በሂደቱ ጉዳዩን በመረዳት አፋጣኝ ምላሽ የሰጡንን የመንግሥት የጸጥታ አካላት እናመሰግናለን። በተጨማሪም በትዕግሥት ስትከታተሉና በጸሎት ስታስቡ ለነበራችሁ አባቶች፣ ምእመናን እና የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እያመሰገንን፣ በዓሉ የሰላምና የበረከት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ማኅበረ ቅዱሳን!
Показать все...
🙏 309 88👍 82🤔 19👏 9🥰 1
፯. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩-፶፬)፡፡ ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤ ፩. ‹‹ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)››፤ ፪. ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ››፤ ፫. ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው››፤ ፬. እመቤታችንን ‹‹ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ››፤ ደቀ መዝሙሩንም ‹‹እናትህ እነኋት›› በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤ ፭. ‹‹አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ›› ፮. ‹‹ተጠማሁ››፤ ፯. ‹‹ዅሉ ተፈጸመ›› (ማቴ. ፳፯፥፵፭-፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫-፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲-፴)፡፡ ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ኾኖ ከቈየ በኋላ ከዘጠኝ እስከ ማታ እንደ ተለመደው ብርሃን ኾኖአል፡፡ ‹‹ወፍና ሠርክ ይበርህ ብርሃነ ፀሐይ›› እንዲል (ዘካ. ፲፬፥፯)፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. ፪፥፲፤ ቈላ. ፩፥፳)፡፡ ጌታችን ጠዋት በሦስት ሰዓት ተገረፈ፤ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ (ማቴ. ፳፯፥፩-፴፯፤ ሉቃ. ፳፫፥፩-፵፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፩)፡፡ በዘጠኝ ሰዓት ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. ፲፱፥፴፬)፡፡ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዘው ቀበሩት (ሉቃ. ፳፫፥፶-፶፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፴፰-፵፪)፡፡ ቅድስት ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነጻ አወጣች (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፱)፡፡ በዚህ ጊዜ በርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ፡፡ ስለዚህም ‹‹ንሴብሖ ለእግዚአብሔር›› እየተባለ ይዘመራል፡፡ ከሆሣዕና አንሥቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል፤ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
Показать все...
26👍 16🙏 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) እንኳን አደረሰን! ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡ ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. ፳፯፥፩-፶፯)፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ ‹‹ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?›› ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡ ‹‹ክፉ የሠራ ባይኾንስ ወደ አንተ ባላመጣነውም ነበር›› በሚል የሸፍጥ ቃል ሲያጕረመርሙ ጲላጦስ መልሶ ‹‹እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ እናንተወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት፤›› አላቸው፡፡ አይሁድም ኦሪት ‹‹ኢትቅትል ብእሴ ጻድቀ ወኀጥአ ኢታኅዩ፤ ጻድቅን ሰው አትግደል፤ ኀጥኡንም ከፍርድአታድን፤›› ትላለችና ‹‹እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም፤›› ብለዋል (ዮሐ. ፲፰፥፳፰-፴፩)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ‹‹በሕጋችን ጻድቀ ባሕርይክርስቶስን መግደል አይገባንም ሙሉ በሙሉ ጥፋተኞች ነን፤›› ሲያሰኛቸው ነው፡፡ በኋላም እርሱ ሞቶ ዓለም ይድን ዘንድ ወደ ምድር መጥቷልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጥፋቱ ሞት ተፈረደበት፡፡ ስለዚህም ገርፈው ሰቀሉት፡፡ ጌታችን ሲሰቅልም የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤ ፩. ፀሐይ ጨለመ፤ ፪. ጨረቃ ደም ኾነ፤ ፫. ከዋክብት ረገፉ፤ ፬. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤ ፭. አለቶች ተፈረካከሱ፤ ፮. መቃብራት ተከፈቱ፤
Показать все...
25🙏 10👍 7
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸው ታውቋል። የሁለቱ አገልጋዮች መኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ ሲሆን የተያዙበት ምክንያት አልታወቀም። ዝርዝር እንደደረሰን እናቀርባለን።
Показать все...
🤔 193👍 34 8🙏 5
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸው ታውቋል። የሁለቱ አገልጋዮች መኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ ሲሆን የተያዙበት ምክንያት አልታወቀም። ዝርዝር እንደደረሰን እናቀርባለን።
Показать все...
ጌታችንም ጊዜው ሲደርስ ከሐዋርያት ጋር በአንድነት መጣ፤ ስምዖንም ከቤቱ ወጥቶ ሮጦ ከጌታ እግር ሥር ሰገደ፤ ወደ ቤቱም ከሐዋርያት ጋር አስገባቸው፡፡ ይሁዳ ግን ይህን ሰዓት አልነበረም፤ ውጪ ከሻጭና ለዋጭ ጋር ገንዘብ ሲደራደር ነበር፤ ስምዖንም ለሚስቱ አክሮሲና ጌታና ሐዋርያት የሚገቡበት በእግራቸው የሚረግጡት ምንጣፍ እንድታነጥፍ አዘዛት፡፡ አክሮሲና ግን የጌታን መልክ አታውቀውም ነበር፤ ያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ጸሎት ሲጸልዩ አይታ ‹‹ከእናንተ ውስጥ መምህሩ ማነው›› አለቻቸው፤እነርሱም ዝም አሉ፤ መልከ መልካም ወደ ሆነውና የጌታ ወዳጅ ወደሆነው ዮሐንስ ተመልክታ እርሱ ይሆን አለች፤ ጴጥሮስ ግን ቀበል አድርጎ ‹‹ጌታ ኢየሱስ ከውስጠኛው ክፍል ቆሞ ይጸልያል፤ ጌታ እርሱ ነው›› አላት፡፡ እርሷም ገብታ ሰገደችለት፤ ይሁዳም በመጨረሻ ሳጥን ተሸክሞ መጣ፤ ጠባቂውንም እኔ የጌታ ደቀ መዝሙር ነኝ አለው፡፡ በር ጠባቂውም እለእስክንድሮስም የተነጠፈውን እስካጥፍ ጠብቅ ብሎ ዘለፈው፤ ልብሱንም አንስቶ አስገባው፤ /ግብረ ሕማማት ፭፻፹፫-፫፻፹፭/፡፡ በአንደኛው ሰዓት ሌሊት (ሐሙስ ለአርብ ምሽት)፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ልብሱን አኖረ፤ማበሻ ጨርቅም አንስቶ ወገቡን ታጠቀ፤ ይህችውም ሥራ የምታሠራና የምታስጌጥ ናት፤ ለዛሬው የመነኮሳት መታጠቂያ አብነት ናት፡፡ ለምሳሌ፡- ኢዮአብ ወደ ሰልፍ ሲገባ እየለበሳት ይገባ እንደነበረችው ያለ ዓይነት ነው፤ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጥብ ዘንድ በጴጥሮስ ጀመረ፤ ጴጥሮስ ግን እኔ ባንተ ልታጠብ አይገባኝም አለ፤ ጌታችንም መልሶ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ እኔ እግርህን ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም›› (ዮሐ.፲፫፥፰)፡፡ ሌሎቹንም ሐዋርያት አጠባቸው፤ አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳንም እግሩን አጠበው፡፡ ጌታ አሳልፎ እንደሚሰጠው ሳያውቅ ቀርቶ አልነበረም፤ ፍቅርን ሲያስተምረውና ለንስሐ ጊዜ ሲሰጠው ነው እንጂ፤ እኛንም ለሚወደን ብቻ ሳይሆን ለሚጠላን እንኳን በጎ ማድረግ እንደሚገባ ሲያስተምረን ነው፡፡ ጌታችን ጾመና ጹሙ አለን፤ተጠመቀና ተጠመቁ አለን፤ ጸለየና ጸልዩ፤ ሰገደናም ስገዱ አለን፤ የሐዋርያትንም እግር አጥቦ እናንተም እንዲህ አድርጉ ብሎ መምህረ ትሕትናነቱን ገለጠልን፡፡ ዛሬም ከፓትርያርኩ ጀምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፤ካህናት በየመአርጋቸው የምእመናኑን እግር በማጠብ የጌታን የትሕትና ሥራ ያስቡታል፡፡ ለሐዋርያት ትሕትናን ሲያስተምራቸው ጌታችን እግራቸውን እንደ አጠባቸው ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ከዚያም ዝ ውእቱ ሥጋየ ዝ ውእቱ ደምየ ብሎ ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው፤ ዛሬም የልጅነት ጥምቀት የሚቀበሉ ምእመናን በዚያኑ ዕለት ከክርስትና ቤት ወደ ቤተ መቅደስ ሔደው የጌታን ክቡር ሥጋና ደም ይቀበላሉ፤ መሠረቱም ጌታችን ለሐዋርያት ያደረገውን ተመርኩዞ ነው፡፡ ከፍ ከፍ ሊል የሚወድ ራሱን ዝቅ ያድርግ ብሎም አስተምሯቸዋል፤ አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ ምሥጢር ጌታ ለጴጥሮስ ‹‹እኔ እግርህን ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም›› ያለውን ሲተረጉሙ ‹‹እኔ በአገልጋይ አምሳል እግርህ ካላጠብኩህ አንተም ከበታችህ ላሉት ራስህን ዝቅ ለማድረግ አትችልም፤ ራስህን ዝቅ ዝቅ ካላደረግህ አለቃ ልትሆን አትችልም›› ለማለት ነው ብለው ተርጉመውታል፡፡ ጌታችን ደግሞ አምላክ ፈጣሪ መምህር ሳለ ዝቅ ብሎ እንዳጠባቸው እነርሱም ክህነታቸውንና መምህርነታቸውን በትሕትና እንዲጀምሩ ሲያስተምራቸው ነው፡፡ በሁለተኛው ሰዓተ ሌሊት ምሽት፤ ጌታችን ሕብስቱን ባርኮ ለዐሥራ ሦስት ፈትቶ ሰጣቸው፤ ዐሥራ ሦስተኛውን እርሱ የሚቀበለው ነውና ነገር ግን የሚረባውና የሚጠቅመው አይደለም፤ ‹‹ዝ ውእቱ ሥጋየ ዝ ውእቱ ደምየ›› ብሎ ሕብስቱን ባርኮ ‹‹ይህ ሥጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ ›› ወይኑንም ባርኮ ‹‹ይህ ደሜ ነው እንካችሁ ጠጡ›› ብሎ ሰጣቸው፡፡አስራ ሦስት አድርጎ መፈተቱ ሐዋርያትን እንዳይገርማቸው (እንዳያስፈራቸው) ነው፤ እራሱም ጥዒሞ አጥዐሞሙ/ቀምሶ አቀመሳቸው/ እንዲል አብነት ለመሆን፤ አንድም ነገ በመልዕተ መስቀል አስራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል እቀበላለሁ ሲል ነው፤ ጌታ ይህን ባያደርግ ኖሮ ዛሬ ካህኑ የጌታን ሥጋና ደም ሳይቀበል አቀብሎ ብቻ በሄደ ነበርና ለእነርሱ ለማስተማር ነው፡፡ ማዕዱንም እየበሉ ጌታችንም ‹‹እውነት እውነት እላችኋለሁ! ከእናንተ መካከል አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል›› አላቸው፤ (ዮሐ.፲፫፥፳፩)፡፡ ሐዋርያት ሁሉ ደነገጡ! እርስ በርሳቸው ተያዩ፤‹‹እኔ እሆን? እኔ እሆን?›› ተባባሉ፤ ጴጥሮስም ዮሐንስን ጠጋ ብሎ ‹‹ማነው አሳልፎ የሚሰጠህ ብለህ ጌታን ጠይቀው›› አለው፤ወንጌላዊው ዮሐንስም ጌታን ጠጋ ብሎ ጠየቀው ጌታችንም ‹‹ከእኔ ጋር እጁን ከወጪቱ የሚያገባ እርሱ አሳልፎ ይሰጠኛል›› አለ፤ (ማቴ.፳፮፥፳፫/ሉቃ.፳፪፥፳፩)፡፡ ሐዋርያትም ‹‹ሁላችን ከወጪቱ የምንጠቅስ አይደለምን?›› ሲሉ ጌታችን ‹‹እኔ ከወጡ አጥቅሼ የምሰጠው ነው›› አላቸው፤ ያንጊዜ አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው፤ ስለዚህ ወንጌላውያኑ ይህን ታሪክ ይዘው አንድ ሳለ በተለያየ አገላለጥ ገለጡልን፡፡ ይሁዳም እንደቸኮለ ሰው ይቅበዘበዝ ነበር፤እርሱም ጌታን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጠው በልቡ እያሰበ ነበር፡፡ ጌታም ወደ ይሁዳ ጠጋ ብሎ ‹‹ወዳጄ ይሁዳ ሆይ! ልትሠራው የምትሻው ሥራ ካለ ሒድ›› አለው፤ (ዮሐ.፲፫፥፳፯)፤ ይሁዳም ፈጥኖ ወጥቶ ወደ አይሁዳውያን ጌታን አሳልፎ ሊሰጥ ዋጋ ሊነጋገር ሔደ፡፡ ከሦስተኛው ሰዓተ ሌሊት እስከ አምስተኛይቱ ሰዓተ ሌሊት ድረስ ለደቀ መዛሙርቱ ሲመክራቸው የመንፈስ ቅዱስንም መምጣት አብዝቶ ሲነግራቸው፤ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አቀና፤ እርሱ ከአባቱ ጋር አንድ እንደሆነም ነገራቸው፤ ለብቻው ፈቀቅ ብሎ ወዙ እንደ ደም እስኪፈስ እየሰገደ ጸለየ፤ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመለሰ፤ ተኝተው አገኛቸው፤ ቀሰቀሳቸው፤ ጴጥሮስንም አንድ ሰዓት ያህል እንኳን ከእኔ ጋር መትጋት አቃታችሁን? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ አለው! (ሉቃ.፳፪፥፲፬-፵፮)፡፡ የጌታችን በአይሁድ መያዝ (ስድስተኛው ሰዓተ ሌሊት) ጌታችንም ከአብ ጋር ስላለው አንድነትና ክብር ለሐዋርያት ካስተማራቸው በኋላ ‹‹ኢየሱስም ይህን ተናግሮ አትክልት ወደ አለበት ስፍራ ወደ ቄድሮስ ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ በዚያም ገባ›› (ዮሐ.፲፰፥፩)፡፡ወንዙን ተሻግሮ ያለውን ዛፍ አልፎ ወዳለው ዱር ገባ፡፡ ይሁዳም ይህችን ስፍራ ቀድሞ ጌታ ይመጣባት ስለነበር ያውቃት ነበርና ጭፍሮችንና የካህናት አለቆችን ፈሪሳውያን ሌሎች ፋና ጋሻ ጦርም የያዙትን አስከትሎ መጣ፡፡ ጌታችንም ‹‹ተነሡ እንሂድ! እነሆ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል›› አላቸው ወደ እነርሱ መጥቶ ቀረበ፤ ይሁዳም ወደርሱ ቀርቦ፤ ‹‹መምህር ሆይ ቸር ውለሃል፤ ሰላም ላንተ ይሁን›› ብሎ ሳመው፤ ይህ መሳም ለአይሁድ ጥቆማ ወይም ምልክት ነበር፡፡ ምክንያቱም የጌታ መልክና የወንጌላዊው የዮሐንስ መልክ ይመሳሰልባቸው ነበርና ሲለይላቸው ነው፤ ጌታችንም ‹‹በስኢምኑ ታገብኦ ለወልደ ዕጓለ እመሕያው፤ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጠዋለህን?›› አለው (ሉቃ.፳፪፥፵፰)፡፡
Показать все...
🙏 16👍 6🤔 3 1
ይሁዳም ከጭፍሮቹ ጋር መጣ፤ ጌታ ኢየሱስንም ከበውት ወደ ሽማግሌዎችና የካህናት አለቃ ቀያፋ ወዳለበት ወሰዱት፤ ጴጥሮስ ግን ከሩቅ ሆኖ ይከተለው ነበር፤ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ከአንደኛው ቅጥር ግቢ ገብቶ ተቀመጠ፡፡ አይሁድም በክርስቶስ ላይ ሁለት የሐሰት ምስክሮችን አመጡ ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ በሦስተኛው ቀን እሰራዋለሁ›› ብሏል ብለው ከሰሱት፤ ሊቀ ካህናቱም ተነስቶ ‹‹እንዲህ ሲያጣሉህ አትሰማምን›› አለው፡፡ ጌታችን ግን ምንም አልመለሰለትም፤ሊቀ ካህናቱም ‹‹ክርስቶስ ተብሎ የተነገረልህ የእግዚብሔር ልጅ አንተ እንደሆንክ ንገረኝ›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹አንተ አልክ›› አለው፤ ያን ጌዜ ሊቀ ካህናቱ ተናዶ ልብሱን ቀደደው፤ራሱንም በብረት ዘንግ መቱት፤ የስቃዩ ጅማሬ ይህን ጊዜ ነበር፡፡
Показать все...
🙏 25 14👍 6🤔 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጸሎተ ሐሙስ! እንኳን አደረሰን! ጸሎተ ሐሙስ ጌታችን ምሥጢረ ቊርባንን ከምሥጢረ ጸሎት ጋር አዋሕዶ የገለጠበት ዕለት ነው፡፡ በወንጌልም እንደተጻፈው ፋሲካውን የሚያከብሩበት ቀን ሲደርስ ጌታ ኢየሱስም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሒዳችሁ ፋሲካን እንበላ ዘንድ አዘጋጁልን አላቸው፤ እነርሱም በየት እንድናዘጋጅልህ ትወዳለህ አሉት? ወደ ከተማ ገብታችሁ የውኃ ማድጋ የሚሸከም ስምዖን የተባለ ሰው ታገኛላችሁ፤ ወደ ገባበት ቤት እርሱን ተከተሉት፤ መምህር ከደቀ መዛሙርቶቼ ጋር ፋሲካ የሚያደርግበት አዳራሽ ወዴት ነው ይልሃል? በሉት እርሱ የተነጠፈውንና ታላቁን አዳራሽ ያሳያችኋል፤ በዚያም ፋሲካን አዘጋጁልን አላቸው፤ እነርሱም ወደ ተላኩበት ከተማ ገብተው አልዓዛርን የውኃ ማድጋ ተሸክሞ አገኙት፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስም ለስምዖን ጌታ በቤቱ ፋሲካን ሊያዘጋጅ መሻቱ እንደሆነ ነገሩት፤ እርሱም የፍጥረታት ጌታ በቤቱ ሊመጣ እንዳለ አስቦ ተደሰተ፤ ወደ ሚስቱ አክሮሲናም ሔዶ ይህ አልዓዛርን ከሞት ያስነሳ እኔንም በኃጢአቴ ይቅር ይለኛል፤ ያነጻኝ ዘንድ ከሐዋርያት ጋር በቤታችን ይመጣል አላት፤ አክሮሲናም እጅግ ተደሰተች፡፡
Показать все...
🙏 19👍 6 6
በ አውሮፓ ማእከል የዩኬ ንዑስ ማእከል አዘጋጅነት የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡ በእንግሊዝ ሀገር በ ሃደርስ ፊልድ ከተማ በደብረ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የደብሩ ካህናት እና  አገልጋዮች እንዲሁም ተጋባዥ ካህናትና መምህራን  ከተለያዩ የዩኬ ከተማዎች የተሰባሰቡ ምእመናን በተገኙበት ለ6ኛ ጊዜ የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ተካሄዷል። በመርሐ ግብሩ ላይ የስዊድን፣ ስካንድናቪያን እና ግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ  እና ከሀገር ቤት መምህር ያረጋል አበጋዝ ተገኝተዋል፡፡ በምክረ አበው ክፍለ ጊዜ ከምእመናን ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የተሰጠ ሲሆን፤  “ፈውስ እና ድኅነት፣ ክርስቲያናዊ ጋብቻ፣ የቤተሰብ አስተዳደር ፈተናዎች እና መፍትሔዎቻቸው” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ተኮር ትምህርቶችም ተሰጥተዋል፡፡ ከትምህርት እና ከአጥቢያው መዘምራን እና ሕጻናት ክፍል መዝሙር በተጨማሪም ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ቤት ስብከተ ወንጌልን ከማስፋፋት እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ከመደገፍ አንጻር ያከናወናቸውና በሂደት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በሚመለከት በምስል ወድምጽ የታገዘ ዘጋቢ ዝግጅት ቀርቧል፡፡ በ መጨረሻም የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ሳሙኤል ለማኅበሩ እና ለተጋባዥ መምህራን ምስጋና እና የምስክር ወረቀት እንዲሁም ለቅዱሳት መካናት እና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሚውል የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ መርሐ ግብሩ በጸሎት  ተጠናቅቋል፡፡  ከመደበኛው የሐዊረ ሕይወት በተጓዳኝ የሕጻናት መርሐ ግብር ለብቻው  በእንግሊዝኛ ቋንቋ በሁለት መምህራን መሠጠቱን ንዑስ ማእከሉ ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡
Показать все...
👍 36 10🙏 7
በማኅበረ ቅዱሳን የጀርመን ንዑስ ማእከል ለገዳማትና ጉባኤ ቤቶች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አካሄደ። ንዑስ ማዕከሉ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጉባኤውን  በሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ያሬድ ምስጋናው፣ መምህራነ ወንጌል፣ ካህናት እና ምዕመናን በተገኙበት አከናውኗል።  በዚህ መርሐ ግብር በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አህጉረ ስብከት ለሚገኙ ለአብነት ትምህርት ቤት መምህራን እና ተማሪዎች ድጋፍ የሚውል  የገቢ ማሰባሰብ ሥራ ተከናውኗል። ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች የተገበራቸውን ፕሮጀክቶችና ልዩ ልዩ ድጋፎችን ገለጻ የተደረገ ሲሆን በዚህም ምእመናን እየተተገበሩ ስላሉ ሥራዎች ግንዛቤ አግኝተዋል። የሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ያሬድ ምእመናን የቤተ ክርስቲያን አእማድ የሆኑ ገዳማትና ጉባኤ ቤቶችን እንዲደግፋ ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት መሠረት ድጋፍ መሰብሰብ ተችሏል። በተመሳሳይ ሚያዚያ 12ና 13 /2016 ዓ.ም በሩስልስሃይም ደ/ምጥማቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ አብርሃም፣ የደብሩ ካህናትና ምእመናን በተገኙበት ዐውደ ርዕይ እና ለገዳማትና አብነት ት/ቤቶች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን በወቅታዊ ጉዳይ ጉዳት ለደረሰባቸው ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ገንዘብ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ የተሰበሰቡ ድጋፎች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች በማኅበሩ በኩል እንደሚውል ንዑስ ማእከሉ አስታውቋል።
Показать все...
👍 23 4🙏 4👏 3
Показать все...
30🙏 13👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
🙏 23 15👍 8
ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ለ582 ደቀመዛሙርት ማዕረገ ክህነት ሰጡ። ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የምዕራብ አርሲ ፣ጉጂ፣ምዕራብ ጉጂ  ፣ቦረና  ሊበን  ሃጉረስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለ582 ደቀመዛሙርት ማዕረገ ክህነት በዛሬው እለት በሻሸመኔ ደብረ አስቦ አ/ተ/ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰጥተዋል። ለዲቁና ለቅስና እና ለቁምስና ፈተና ሲፈተኑ የቆዩ ተማሪዎች 546 ዲቁና፤34 የቅስና እና 3 የቁምስና ማዕረግ የተሰጣቸው ሲሆን  ከእነዚህ ውስጥ 171 ዲቁና እና 5 የቅስና ማዕረግ በአጠቃላይ 176 የተሰጣቸው በማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማዕከል እና ሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት  ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ጋር  በመተባበር ሲያስተምራችው የነበሩ ደቀመዛሙርት ናቸው። ማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማዕከል ከሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት  ጋር በመተባበር በዚህ ዓመት ከዚህ ቀደም ማዕረገ ክህነትን የተቀበሉ 61 ካህናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 237 ማዕረገ ክህነት እዲቀበሉ አድርጓል። በዛሬው ዕለት ክህነት የተቀበሉት አገልጋዮች በአካባቢው ያለውን የአካህናት እጥረት ለመፍታት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው ተጠቋሟል።
Показать все...
👍 68 20🙏 10🥰 6🤔 6👏 5
https://youtu.be/Q0WJSswrkTo?si=ajqfBbrGS6e31m5Y ሰላምሽ ዛሬ ነው ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም ወደ አንቺ መጥቷልና አምላክ ዘለዓለም/፪/ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ ሕፃናት በኢየሩሳሌም አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/፪/      አዝ ሆሣዕና እያሉ አመሰገኑት በኢየሩሳሌም አእሩግ ወሕፃናት/፪/   አዝ ኪሩቤል መንበሩን  የሚሸከሙት መስቀል ተሸክሞ ሆነን መድኃኒት/፪/   አዝ የኢየሱስን ሕማም ደናግል አይተው እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/፪/
Показать все...
11👍 6
ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም፣ ቤተ ፋጌ በቀረበ ጊዜ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሁለቱን ሐዋርያት ወደ ቤተ ፋጌ ልኮ የታሰረች አህያ እንደሚያገኙና ፈትተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፤ ነገር ግን ጥያቄ የሚጠይቅ ሰው ከመጣ ‹‹…ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ…›› አላቸው፤ (ማቴ.፳፩፥፫) ፈትታችሁ አምጡ ማለቱ ሕዝቡን ከማዕሰረ ኃጢአት የሚፈቱበት ጊዜ እንደ ደረሰ ሲያጠይቅ ነው፡፡ ዛሬ ዓለም በሥጋዊ ጥቅም በኃላፊ ደስታ ዓይነ ልቡናችንን ጋርዳ፣ ሥጋዊ ፈቃዳችን ከፈቃደ ነፍሳችን አይሎ በኃጢአት ማዕሰር ታስረናል፡፡ ጌታችን በትምህርቱ ‹‹…ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው፤ ባርያም ለዘለዓለም በቤት አይኖርም…›› በማለት እንደገለጸው በበደላችን በኃጢአት ባርነት ቀንበር ሥር ወድቀን በዲያብሎስ ባርነት ታስረናል ፤ (ዮሐ.፰፥፴፬) ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን››፤ ከታሰርነበት የጥላቻ፣ የቂም፣ የዘረኝነት፣ የጎጠኝነት የኃጢአት ማሰሪያ ይፈታን ዘንድ ‹‹እባክህ አሁን አድነን!›› እንበለው፡፡   ‹‹እባክህ አሁን አድነን››፡- አይሁድ፣ ጸሐፍት ፈሪሳውያን የምስጋና ባለቤት ከሆነው ዘንድ በተሰጣቸው ኃላፊነት ምስጋና የባሕርይው የሆነን ፈጣሬ ዓለማት መድኅን ዓለም ክርስቶስን ማመስገን፣ አመስግነው መመስገን፣ ቅዱስ ስሙን ጠርተው መቀደስ ሲገባቸው በተቃራኒው ልባቸው በጥላቻና በቅናት ተመልቶ የሚያመሰግኑት ዝም ይሉ ዘንድ ጠየቁ፤ አንደበትን ለምስጋና የፈጠረ ጌታ ግን ‹‹እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ›› አላቸው፤ ምንም የሚሳነው የሌለ ጌታም ድንጋዮች ያመሰግኑት ዘንድ አደረገ፡፡ (ሉቃ.፲፱፥፵)   ጌታችን በትምህርቱ ‹‹ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፤ ክፉም ስለሆነ ሥራው እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም›› በማለት እንደገለጸው የክፋት ሥራቸውን የሚገልጥ፣ ጨለማ አስተሳሰባቸውን የሚያበራ የብርሃን ጌታ ሲመጣ የእርሱ መገለጥና መመስገን እነርሱን የሚያሳንስ ስለመሰላቸው ተቃወሙ፡፡ ክህነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነና  የሰጣቸውም እርሱ እንደሆነ ማስተዋል ቢሳናቸው የራሱን ገንዘብ ምስጋናውን ለማስቀረት ፈለጉ፤ (ዮሐ.፫፥፳) ማድረግ የማይቻላቸውን ሊያስቀሩ ደፈሩ፤ ክፉዎች  የቅኖች ደግነት፣ የመልካሞች በጎ ሥራ፣ የትሑታን የተሰበረ መንፈስና  የአመስጋኞች ምስጋናቸው ይረብሻቸዋል፡፡ ልቡናቸውን ለጠላት ዲያብሎስ ማኅደር ስላደረጉ የቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ስሙ ሲጠራና ምስጋናው ሲደመጥ ሰላም ይነሳቸዋል። ዲያብሎስ  እግዚአብሔር ሲመሰገን፣ ሰው ንስሐ ሲገባ፣ የምሥራቹ ወንጌል ሲነገር፣ ምእመናን በቤተ እግዚአብሔር ሲበዙ፣ ሰላም ሲሰፍን፣ ሰዎች ሲፋቀሩ አንድነት ሲጸና፣ ሕገ እግዚአብሔር ሲከበር፣ ክርስትና ሲሰፋ፣ በዓላት ሲከበሩ ማየትና መስማት አይሻም፤ የግብር ልጆቹን እያሰማራ መንፈሳዊውን ዓለም ያውካል፤ ሁሉም እንደ እርሱ ከፈጣሪው ተጣልቶ በክህደት እንዲኖር ይፈልጋሉ። ዓለም ሳይፈጠር ባሕርይው ባሕርይውን እያመሰገነ ምስጋናው ሳይቋረጥ የኖረውን ጌታችንን በእናታቸው እቅፍ ያሉ ሕፃናት፣ አዕባን (ድንጋዮች) “ለምን አመሰገኑት” ብለው የቅናት ጥያቄ እንደጠየቁት ማለት ነው።   ዛሬም በሥጋ ለባሹ የሰው ልጅ አድሮ “ለምን አመሰገናችሁ? ለምን አምልኮተ እግዚአብሔር ፈጸማችሁ” በማለት ምስጋናውን ሊያስቀር ይጥራል፤ ግን አይቻለውም! እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በስሙ እንዳያስተምሩ፣ ባስፈራሯቸውም ጊዜ  ‹‹… ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል…›› አሉ፡፡ (የሐ. ሥራ ፭፥፳፱) እኛም ልጆቻቸው የአሠረ ፍኖታቸው ተከታይ ነንና! ዛቻና ማስፈራራቱን ሳንፈራ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ  አሁን አድነን››  እንላለን፡፡ አመስግነን እንመሰገን፣ ቀድሰን እንቀደስ ዘንድ ከባለጋራችን ዲያብሎስ የተቃውሞ ዛቻና በትር እንዲታደገን ዘንድ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን…መድኃኒት ሁነን›› ብለን እንዘምራለን፡፡   ዲያብሎስ በግብር ልጆቹ ልቡና አድሮ በግፍ በትር ሊሸነቁጠን በተስፋ መቁረጥ ገመድ አስሮናልና  ቅዱሳን በቃል ኪዳናቸው ይፈቱን ዘንድ ይልክልን ዘንድ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን›› እንበለው፤ በነቢዩ ዘካርያስ  አማካኝነት ‹‹…የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በይ፥ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል…›› በማለት በተናገረው ቃል መሠረት መምህረ ትሕትና የዓለም ጌታ መድኅን ክርስቶስ በአህያይቱና በውርንጭላይቱ  ዘባን ( ጀርባ) ተቀምጦ ሲመጣ  በኢየሩሳሌም የነበሩ ልብሳቸውን ከምድር አነጠፉ፤ (ዘካ.፱፥፱) “እንኳን ለአንተ ለተቀመጥክባት አህያም ክብር ይገባል” ሲሉ! ትሕትናን ከእርሱ በተግባር ተምረዋልና በትሕትና የለበሱትን ልብስ አውልቀው ከምድር አነጠፉ፤ በጥቂት የትሕትና ሥራቸው ዝቅ ካሉበት ከሰጠሙበት የበደል አዘቅት ከፍ ያደርጋቸውና ያከብራቸው  ዘንድ  ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን…!›› በማለት ተማጸኑት፤ እኛም ከልቡናችን እልፍኝ በጎ ሥነ ምግባር ልብሳችንን አንጥፈን ይገባበት ዘንድ ‹‹በሰማይ ያለ መድኃኒት ናልን›› ብለን እንጋብዘው፡፡   በሆሣዕና በዓል ዕለት በምስጋናው ጊዜ ዘንባባን እንይዛለን፤ ጌታችን በአህያና በውርንጭላይቱ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ከልብሳቸው በተጨማሪ የዘንባባ ዝንጣፊም ይዘው ነበር፤ በብሉይ ኪዳን ዘንባባ የደስታ መግለጫ ነው፤ አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ ደግሞ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ወጡ፤ ዮዲት ወገኖቿን ሲያስጨንቅ ንጹሐንን በግፍ ሲገድል የነበረውን ሆሎፎርኒስ የተባለን ሰው ገድላ በተመለሰች ጊዜ ዘንባባን ይዘው ደስታቸውን ገልጠዋል፡፡ አንድም ይላሉ መተርጉማነ አበው ‹‹ዘንባባ እሾኻማ ነው፤ ትእምርተ ኃይል (መዊእ) አለህ›› ሲሉት አንድም ዘንባባን እሳት አይበላውም፤ ለብልቦ ይተወዋል፤ ባሕርይ አይመረመርም›› ሲሉ ነው፡፡ የሰላም አለቃ፣ ኃያል፣ ልዑል፣ ባሕርይው የማይመረመር አምላካችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒት ይሆነን፣ ያድነን ዘንድ በሕጉ ተጉዘን፣ ትእዛዙን፣ አክብረን፣ በትሩፋት ሥራ አጊጠንና የምግባር ዘንባባን ይዘን ጠላት ዲያብሎስን ድል አድርገን ‹‹ሆሣዕና›› እንበለው፡፡ (የማቴዎስ ወንጌል አድምታ ትርጓሜ ፳፩፥፰) ዝቅ ካልንበት ከፍ ያደርገን ዘንድ ከእግሩ በታች ራሳችንን እናዋርድ፤ ‹‹… በመጠን ኑሩ፤ ንቁም ባለጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና …›› እንደተባለው፤ (፩ኛጴጥ. ፭፥፰) በአህያ ውርንጭላ ጀርባ ተቀምጦ ስለ እኛ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከፍ አድርጎናል፤ ዳግመኛ በኃጢአት ቀንበር ወድቀን በባርነት እንዳንያዝም በጾምና በጸሎት ልንተጋ ያስፈልጋል፡፡   ‹‹አምላካችን ሆይ! እባክህ አሁን አድነን!›› ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ! አሜን  
Показать все...
33👍 18🥰 5🙏 5👏 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
  ‹‹እባክህ አሁን አድነን!››   ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹…ከእኔ ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና…››  በማለት  ትሕትናን በአንደበቱ ትምህርት ከማስተማሩ በተጓዳኝ በተግባር ሕይወቱም ተግብሮ ካሳየባቸው ዕለታት አንዱ በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት ነው፤ (ማቴ.፲፩፥፳፱) ይህ ግሩም አምላክ በትሕትና ከተገለጠባቸው ዕለታት አንዱ የሆነው ድንቅ ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሆሣዕና›› በመባል ይታወቃል፡፡ ሆሣዕና መተርጉማነ አበው በአንድምታቸው ‹‹ ሆሣዕና በአርያም በሰማይ ያለ መድኃኒት››  ብለው ተርጉመውልናል(ማቴ.፳፩፥፱ ወንጌል አንድምታ)  አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ደግሞ በመዝገበ ቃላታቸው ሆሣዕና ማለት ‹‹…እባክህ አሁን አድነን፤…መድኃኒት፣ መድኃኒት መሆን …›› በማለት ገልጸውታል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ ፫፻፸፫)   ‹‹እባክህ አሁን አድነን››፡- ይህን የተማጽኖ ቃል የተናገሩት ጌታችን በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ በኢየሩሳሌም የነበሩ ሕዝብ ናቸው፡፡ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው፣ አንድም የወይራ ቅጠል እንዲሁም ልብሳቸውን ከምድር አንጥፈው ከልብ በመነጨ፣ ምስጋናቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያሉ ሆሣዕና በአርያም ‹‹…እባክህ አድነን…›› በማለት አመሰገኑት፡፡ የነቢየ እግዚአብሔር ንጉሥ ዳዊት ትንቢት ተፈጽሞ በእናታቸው ጀርባ ያሉ የሚጠቡ ሕፃናት አመሰገኑ፤ ‹‹…ከሕፃናት ከሚጠቡ ልጆች አፍም ምስጋናን አዘጋጀህ…›› እንዲል፡፡ (መዝ.፰፥፪) 
Показать все...
👍 22 6👏 5🥰 2
ዝክረ ቅድስት እናት ኢሪን እና መንፈሳዊ የትርጉም ፊልም የምረቃት መርሐግብር ተከናወነ። በማኅበረ ቅዱሳን መዝሙር እና ኪነ ጥበባት አገልግሎት ማስተባበሪያ አዘጋጅነት የዘመናችን የ21ኛው ክፍለ ዘመን ቅድስት እናት ኢሪንን የሚዘክር መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተካናውኗል። በመርሐ ግብሩ ላይ የቅድስቷን  የተጋድሎ ሕይወት እና ኦርቶዶክሳውያን ከሕይወቷ መማር የሚገባንን ትምህርት በተመለከተ መነሻ ጽሑፍ ቀርቧል። በዕለቱ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የማኅበሩ አባላት እና ምእመናም የተገኙ ሲሆን በእናት ኢሪን ዙሪያ የተዘጋጀው መንፈሳዊ ትርጉም ፊልም የምረቃትም ሥነ ሥርዓትም  ተከናውኗል። መንፈሳዊ ፊልሙ  በዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን የዩቲዪብ ቻናል ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። https://youtube.com/@-zemawetibebzmk7905?si=2jTnKZXGAfEJWRi7
Показать все...
19👍 8