cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ሸገርን በግጥም

ቻናላችንን በመቀላቀል እነዚህን እና ሌላም ትርፍ ያግኙ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ኢትዮጵያዊነትን እንዘምራለን🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 1. አዳዲስ ግጥሞች 2. ግጥም ካለዎት እንፖስታለን 3. ልብ ወለዶች 4. አጫጭር ወጎች 5. አስገራሚ ነገሮች ለበለጠ መረጃ 👇 @Itz_what_itz @Sonofyeshi ቻናላችንን ስለተቀላቀሉ እናመሠግናለን

Больше
Рекламные посты
761
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ወገን ንቃ ንቃ
Показать все...
Показать все...
Mela Muziqa - Teddy Yo (ቴዲ ዮ) - ወንበርሽ | Wenbersh New Ethiopian Music 2022 (Offical Video)

#ethiopiannewmusic2022 #teddyyo #melamuziqarecords Any unauthorized use, copying, or distribution is strictly prohibited. Copyright©2022: Melamuziqa Records LLC አዳዲስ እና ቆንጆ ስራዎችን ከቅርብ ጊዜ ወዲ ወደ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ገበያ ላይ ይዞ እየመጣ የሚገኘው መላ ሙዚቃ @melamuziqarecords አዳዲስ የሙዚቃ ቪድዮ ስራ (ምስል ቅንብር) ለመላው የሙዚቃ አፍቃሪያን እነሆ ይላል መላ ሙዚቃ የሁላችን ምርጫ! Follow Mela Muziqa Records

https://t.me/+PYOGiuhMgU9iOTZh

https://www.tiktok.com/@melamuziqarecords

https://www.facebook.com/MelaMuziqa

https://instagram.com/melamuziqarecords

https://melamuziqa.com

የወንዜ ልዩ ነሽ አዎ አማላይ በውበትሽ ሰው ገዳይ የኔ እያሉሽ ያለከልካይ ስንቱን አየን ባቺ ጉዳይ እውነት እውነቱን እስቲ ልናገር ሁሉም ይበል ባንቺ ጥንቅር ተወል ደናል እኛ ሸገር እንደሌለው ሆንን ሀገር እደጊ ብዬ ብዬ ቤቴን ለቀኩልሽ ያላቀና ጎዳና ሲጠልሽ እትብቴን አቅረሽ ተፋሽ ይሁና አንቺን ግን አይክፋሽ ሰውም አይኖር ያለመሬት መሬትም አይኖር ያለሰው ዝም ያለው ልጅ የሸገር ሰው ወዴት ይሆን ሄዶ የሚያርሰው አዝማች--- የወንዜ የወንዜ የወንዜ ትርምስ ጥያቄ ብቻ ንው መልሱ ላይመለስ የወንዜ የወንዜ የወንዜ አራት ኪሎ ወንበርሽ ይፋጃል ጠፋ ሁሉን ጥሎ ያራዳ ልጅ መሆን እድለኛ የፀዳ ነው ከዘረኛ ለመጣው ሁሉ ለተረኛ ማጨብጨብ ነው ለቀማኛ ሸገር ተወልዶ ማደጉ የቱጋ ነው አስቲ ጥቅሙ በስጋት ቤት ማጉረምረሙ መኖር አፈር እየቃሙ ይባስ ካምናው ዘንድሮ ልቤ ከቀዬው ተባሮ በቃ እሺ ልጀምረፍ ጉዞ ክፉ ከማይ ከዚ ብሶ በፍቅር ስኖር ባንቺ ኮርቼ አላውቅም ነበር ተከፍቼ ግዜ ጌታ ነው ተገፍቼ ስደት መረጥኩ ተገፍቼ አስቤ አላውቅ ባህር ማዶ ክፋት ሲበዛ ስር ስር ሰዶ ፍቅር እኛ ጋር ኪስ ግን ባዶ በዚም ተቀና አይስቁም ወዶ አዝማች ------ አርንጋዴ ቢጫ ቀይ አርማችን የኛ መመኪያችን ፍቅር መስጠት ያስተማረችን ሸገር እናታችን ቀዬ ፈርሶ ህንፃ ቢደረደር ለይቀረፍ ችግር ሰው አይተካ ዲንጋይ ቢራረብ ጠፍቶ መተሳሰብ ጎበዝ ንቃ ንቃ ንቃ ሰግጣ ስቃ ስቃ ስቃ ከበረች ዝቃ ዝቃ ዝቃ ሄደች ልቃ ልቃ ልቃ ሲረኞች አንቺን ለማዋረድ ሳያውቁሽ ከውጪ ማጎብደድ ግን ሆነሽ የኣፍሪካችን ዘውድ ይዘውታል ክፋትን ማላመድ ስም አወጡልሽ የዳቦ ዳቦሽን ሳይቀምሱ በጉቦ ሊበላሽ ካሰበው ተርቦ ይጠብቅሽ አምላክ አስቦ አዝማች--- የወንዜ የወንዜ የወንዜ ትርምስ ጥያቄ ብቻ ንው መልሱ ላይመለስ የወንዜ የወንዜ የወንዜ አራት ኪሎ ወንበርሽ ይፋጃል ጠፋ ሁሉን ጥሎ #ethiopiannewmusic2022 #teddyyo #melamuziqarecords Any unauthorized use, copying, or distribution is strictly prohibited. Copyright©2022: Melamuziqa Records LLC አዳዲስ እና ቆንጆ ስራዎችን ከቅርብ ጊዜ ወዲ ወደ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ገበያ ላይ ይዞ እየመጣ የሚገኘው መላ ሙዚቃ @melamuziqarecords አዳዲስ የሙዚቃ ቪድዮ ስራ (ምስል ቅንብር) ለመላው የሙዚቃ አፍቃሪያን እነሆ ይላል መላ ሙዚቃ የሁላችን ምርጫ! Follow Mela Muziqa Records

https://t.me/+PYOGiuhMgU9iOTZh

https://www.tiktok.com/@melamuziqarecords

https://www.facebook.com/MelaMuziqa

https://instagram.com/melamuziqarecords

https://melamuziqa.com

Check Out New Ethiopian Entertainment Videos by Subscribing @Mela Muziqa Records Melamuziqa Records is the ultimate next generation Ethiopian Music Producer, and the Largest distributor, a global leader in the Ethiopian film MELA MUZIQA RECORDS WORLDWIDE RECORD LABEL OPERATING FROM ADDIS ABABA(ETHIOPIA) & UNITED STATE, Washington D.C. Check Out New Ethiopian Entertainment Videos by Subscribing @Mela Muziqa Records Melamuziqa Records is the ultimate next generation Ethiopian Music Producer, and the Largest distributor, a global leader in the Ethiopian film MELA MUZIQA RECORDS WORLDWIDE RECORD LABEL OPERATING FROM ADDIS ABABA(ETHIOPIA) & UNITED STATE, Washington D.C. #መላሙዚቃሪኮርድስ #melamuziqa #newmusiceveryweek #ethiopianmusic #melamuziqa #newmusiceveryweek #ethiopianmusic2021 #ethiopianmusic2021 #addisabeba #ethiopiannewmusic2022 #amharicmusic #amharicmusic2022 #newamharicmusic #Ethiopianpopsong #Ethiopianpopsong #ethiopianlovesong #Ethiopianlovesong2022 #amhariclovesong2022 #amhariclovesong #addisababamusic2022 #samidanmusic2022 #newethiopianmusic #newethiopianmusic2022 #Ethiopiansong http://vevo.ly/DDrBqo

Фото недоступноПоказать в Telegram
ይብላኝ ለሞተ እንጂ፡ እድሜው ለተገታ፡ ወጊ ተቃቀፈ፡ ገዳይ ትጥቁን ፈታ። @yegtm @yegtm
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#እህህ ይብላኝ እንጂ ላንተ፡ ዘመንህ ለመሸ፡ ገዳይህ ተፈታ እየተሞካሸ። @yegtm @yegtm
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#እኔን እኔን እናት አለም፡ እኔን እናንዋ፡ የኔ ደግ እንስፍስፍ፡ የኔ ገራም ጨዋ። @yegtm @yegtm
Показать все...
#ሰው_ሁን_በይኝ በቀደም ለት ጉንጬ መሐል በከንፈሯ ብትዳብሰኝ፣ ሙት አካሌ ፊት እንዳለኝ አስታወሰኝ፣ ደሞ ድንገት ቀልድ ነግራኝ ስቄ ስቄ እንዳባራሁ ፤ "ጥርስህ ሲያምር" ስላለችኝ ዘላለሜን ማልቀስ ፈራሁ ፤ ተካተትኩኝ ከተፈጥሮ እፍ ...አልሸብኝ ድብቅ ውበት፤ እስቲ ባክሽ አሁን ደሞ 'ሰው ሁን ብለሽ ሹሚኝና ሰው መሆኔን ልመንበት ፤ ሰው ተብዬ ልጠራበት። 🔘አስታወሰኝ ረጋሳ🔘 @yegtm @yegtm
Показать все...
ሰሞኑን እንጃልኝ """""""""" """"""""""" ሳማሽ እውላለሁ ሰው ባጣም ለራሴ ፣ መልክሽን ስስለው ፈገግ ይላል ጥርሴ ፣ አጃኢብ ያሰኛል ተለዋውጫለሁ ተቀያይሬያለሁ ፣ ፍቅርሽ ገብቶልኛል ተረጋግቻለሁ ። ሰሞኑን እንጃልኝ ፈጣሪ ጠብቆኝ. ባይመታኝ እንቅፋት ፣ ፈረስ ቢያስጋልብም የጎዳናው ስፋት ፣ ጥጉን እሄዳለው..... አይኖቼን አቅንቼ ፣ ባገኝሽ እያልኩኝ ባየሁሽ እያልኩኝ .........ልቤን አሞኝቼ ። ሰሞኑን እንደዚህ ግራ እየተጋባው ፣ ሌቱን እያሰብኩሽ ሳልተኛ እየነቃው ፣ ሳገኝሽ ስታስሪው ያንደበቴን ድፍረት ፣ ስለይሽ በራሴ........ ሳዝንና ስፀፀት ፣ እናልሽ የኔ አለም ከሀሳቤ ላወጣሽ ሞክሬ አቅቶኛል ፣ ማፍቀሬን ልነግርሽ ፈልጌ አቅቶኛል ፣ ሰሞኑን እንጃልኝ እንዲህ ያደርገኛል ። #በረከት_ዘውዱ @yegtm @yegtm
Показать все...
ልቤ ለምን ይክፋው          (ሃያት ) ላይኖረኝ የምለው ይሄ  ጎደለብኝ ሆደባሻ ሆኜ ልቤም ሲከፋብኝ ሆሄ ፊደል ሲያጥር ማፅናኛ ቃል ጠፍቶ ካልታየ የልቤ ቁጥርቱ ተፈቶ ምሏል ወይ ላይለቀኝ ማዘን መተከዜ የአለም ጎደሎነት ላይሞላ ሁልጊዜ ይሻለው ነበረ መቻልን መላመድ መናገር ያስከፋል ሳይለይ ወዳጅ ዘመድ ትግስትኮ ጌጥ ነው ሁልጊዜም ያምራል ከመናገር በላይ ዝምም ይናገራል ስለዚህ  ልቤ ሆይ ለምን ይከፋሀል መቻል እና ትግስት  ቀን ያሳልፍሀል። @yegtm @yegtm
Показать все...
ታዘበኝ ልጅነት """"""""""""""""""" ደግመን ብንገናኝ ከልጅነቴ ጋ ፣ አመታት አይበቁም የውስጤን ሳወጋ ፣ ስማኝ ልጅነቴ በድሎኛል ማደግ ጨቁኖኛል እድሜ ፣ ተገፏል ከላዬ የልጅነት ህልሜ ፣ አወቅኩኝ መግፋትን ፍቅርን ታገልኩት ፣ ይቅር ባዩን ልቤን ቂመኛ አደረኩት ። ስማኝ ልጅነቴ ተነፍጓል ያ መልኬ ጎድፏል ንፁህ ልቤ ፣ እየሞትኩኝ አለሁ መኖርን አስቤ ፣ የእውነት ሳቅ የለኝም የልጅነት ደስታ ፣ መቦረቂያ እድሜዬ አልፏል ያኛው ለታ ። ታዘበኝ ልጅነት ታሰርኩኝ በጊዜ ፣ ነፃነት ተነጠኩ.....ከበበኝ ትካዜ ፣ ተቀይሬያለሁኝ አሁን አታውቀኝም ፣ ለራሴ ደስታ እንጂ ለሰው ግድ የለኝም ። ከተኛሁ ቆየሁኝ እንቅልፍ አጥቷል ቀልቤ ፣ ወጪ ወራጁን ሲያይ ይሸበራል ልቤ ፣ እይታዬ ሰፍቷል ማስተዋሌ ገዝፏል ፣ ግና ምን ያረጋል ከደጀ ሰላሙ............. አካሌ ርቋል ። ታዘበኝ ልጅነት ጥለኸኝ ብትሄድም ላትመለስ ዳግም ፣ ምከረኝ ልጅነት ከህመሜ ላገገም ፣ ታምሜያለሁ እና በንዋይ መጠማት ፣ አድፌያለሁና ሆዴን እያጠገብሁ ነፍሴን እያስራብኳት ፣ አኖራት እያልኩኝ.... ስን'ግዜ ገደልኳት ። . . . . . ታዘበኝ ልጅነት ፣ አሁን የለም እና ምታውቀው ማንነት ። #በረከት_ዘውዱ @yegtm @Yegtm
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የዘመኑ ትምርት! በተቆረጠ ግንድ ቅጠል በጎደለው እንጨት ላይ ተቀምጦ እስትንፋስ በሌለው መምሩ በውሸት ሲያሳምን በተስፋ ህዝቡ አሜን ይላል ሆዱን እያሰፋ [ዳዊት ጥዑማይ] @yegtm @yegtm
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.