Nejashi Printing Press
Открыть в Telegram
ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።
Больше4 718
Подписчики
-124 часа
Нет данных7 дней
-930 день
Архив постов
በዚያ ዕለትም ‘ሠንየተል ወዳዕ’ በተባለው ሥፍራ በርካታ የመዲና ሕዝብ ተሰብስቦ ምስጋናና ውዳሴ እያሰማ ተቀበላቸው፡፡ መዲና በታሪኳ እንደዚያ ቀን የደስታ እልልታ ገጥሟት አያውቅም፡፡
ዕለቱ በእርግጥም ኢስላም ጠባብ ከሆነው የመካ አስጨናቂ ሕይወት ወደ ሠፊውና አስደሳች ወደ ሆነው የመዲና ሕይወት ሽግግር ያደረገበት ታሪካዊ ቀን ነበር፡፡ የመዲና ሕዝቦች የአላህን ታላቅ በረከትና ጸጋ በደስታ ተቀብለው ምስጋናና ውዳሴ ያሰሙበት ድንቅ ዕለት፡፡ ለምን አመስጋኝ አይሆኑ!! ምድራቸው ታሪካዊውን የኢስላም ብርሃን ለዓለም እንድታደርስ ተመርጣለች፡፡ የመጨረሻውንና የነብያት ሁሉ መደምደሚያ የሆኑትን ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ተቀብላ ለማስተናገድ ከመታደል የበለጠ ምን ልቅና ትሻለች! ዕድለኛ ከተማ፡፡ በጊዜው ሁሉም “የአላህ መልዕክተኛ! የአላህ መልዕክተኛ! ሙሐመድ!” እያለ ደስታውን ሲገልጽ ይታይ ነበር።
ዝነኛው የጠለዐል በድሩ ዐለይና ነሺዳም በዚያ ቀን ተነሸደ።
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በታሪክ ገጾች የሚስተካከለው በሌለ የደመቀ አቀባበል መዲና ከገቡ በኋላ የሚያርፉበትን ሥፍራ ራሳቸው መወሰን አልፈለጉም ነበር፡፡ ከዚያ ይልቅ “ግመላቸው መለኮታዊ ምሪት” እንዳላትና እርሷ የምታርፍበትን ቦታ ትክክለኛው ማረፊያቸው እንደሆነ በማሳወቅ ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ በመጨረሻም የአቡ አዩብ አል-አንሷሪ (ረ.ዐ) ቤት ሲደርሱ አቡ አዩብ (ረ.ዐ) ተሸቀዳድመው ጓዛቸውን በመያዝ እቤታቸው አስገቡት፡፡
ከ" ለዓለማት እዝነት" መጽሐፍ
ትርጉም : አቡ ቢላል
Repost from ABX
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ነጃሺ ማተሚያ ቤት ከዚህ በታች በተዘረዘረው ክፍት የስራ መደብ ዝርዝር መሰረት አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
*የስራ መደቡ መጠሪያ:- የማርኬቲንግ ባለሙያ
*ብዛት:-1
*የት/ት ደረጃ:- በማርኬቲንግ ወይንም ተዛማጅ የት/ት ዘርፍ የተመረቀች/ቀ
*የስራ ልምድ:-2 አመትና ከዚያ በላይ
*ፆታ:-ሴ/ወ
*ደሞዝ:-በስምምነት
አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁንና የስራ ልምዳችሁን 09_45_85_85_85 በቴሌግራም ወይንም
nejashipress@gmail.com ላይ መላክ ትችላላችሁ
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
https://t.me/MuhammedSeidAbx
+1
ያ ጉድጓድ ውስጥ የተጣለው፣
በባልዲ ተንጠልጥሎ ከጉድጓዱ የወጣው እና
በርካሽ ዋጋ የተሸጠው፤
ኋላ ላይም ሚኒስቴር ሆኖ፣
ቀጥሎም የግብፅ ዋና ገዥ ሊሆን ጥቂት ቀርቶት የነበረው ነቢዩ ዩሱፍ (ዐ.ሰ.) ታሪኩ ምን ያስተምረናል መሰለህ…
በዘመንህ ውስጥ የሚያጋጥሙህ ከባባድ የሕይወት ገፆች ሁሉ፣
በሕይወት ውስጥ ወደፊት የሚመጣውን እጅግ ውቡን ሕይወትህን መንገድ ለመጥረግ የተላኩ መቅድሞች ሊሆኑ ይችላሉና ታገስ!
በአላህ ላይ መልካምን ብቻ ጠርጥር!፡፡
በአያመ ተሽሪቅ ውስጥ የሚፈፀሙ ሥርዓቶች
*
ከዒድ ቀን በኋላ ያሉ ሦስቱ የዚል-ሒጃ 11ኛ፣ 12ኛ እና 13ኛ ቀናት ቀናት “አያመ ተሸሪቅ” በመባል ይታወቃሉ፡፡ የዒድ ቀናቶች ናቸው፡፡ በነኚህ ቀናት ውስጥ ይበላል፣ ይጠጣል፣ የጠጠር ውርወራ ሥርዓት ይከናወናል፡፡
ውርወራው ሰባት ሰባት ጠጠሮች በሦስት ቦታዎች ላይ በመወርወር ይከናወናል።
ቦታዎቹና ቅደም ተከተላቸውም "ጀምረቱል-ኡላ" (የመጀመሪያው ጠጠር መወርወሪያ) "ጀምረቱል ውስጧ" (የመሃለኛው) ጠጠር መወርወሪያ እና "ጀምረቱል ዐቀበህ" የመጨረሻው የጠጠር መወርወሪያ ቦታዎች ናቸው።
የመወርወሪያ ጊዜም ፀሐይ ከእኩለ-ሰማይ ወደ ምእራብ ከወረደች በኋላ ጀምሮ እስከምትጠልቅ ድረስ ባለው ወቅት ነው።
በ "ጀምረቱል ኡላ እና በ ጀምረቱል ውስጧ የጠጠር መወርወሪያ ሥፍራ ላይ ጠጠሮችን ወርውሮረው እንደጨረሱ ወደ ቂባላ ዙሮ ዱዓእ ማድረግ ይመረጣል።
በ "ጀምረቱል_ዐቀበህ" (በመጨረሻው) የጠጠር መወርወሪያ ስፍራ ላይ ግን ጠጠሮችን ወርዉሮ መመለስ እንጂ ዱዓእ አይደረግም።
ትንሹን፣ መካከለኛውንና ትልቁን (የመጨረሻውን) የጠጠር ውርወራ ሥርዓት መፈፀም ተገቢ ነው፡፡ ለእያንዳንዳቸው ሰባት ሰባት ጠጠሮች ይወረወራል፡፡
እያንዳንዱን ጠጠር ሲወረወር ተክቢራ በማድረግ ይወደዳል፡፡ ሰባቱንም ጠጠሮች አከታትሎ መወርወር ሱንና ነው፡፡
የውርወራውን ሥርዓት በቅደም ተከተል መፈፀሙ መስፈርት ነው፡፡ በትንሹ ይጀምራል፡፡ መካከለኛውን ያስከትላል፡፡ በትልቁ ያጠናቅቃል፡፡
ጠጠሮች በሚወረውሩበት ገንዳ እና በሰውዬው መካከል ሦስት ክንድ እና ከዚያ በላይ ርቀት መኖሩ ሱንና ነው፡፡ ርቀቱ ከዚያ ያነሰ ከሆነ መጣል እንጅ መወርወር አይባልምና፡፡
የጠጠር ውርወራ ሥርዓት የሚጀመርበትን ወቅት በሚመለከት ታላቁ የውርወራ ሥርዓት ከዒድ ሌሊት አጋማሽ በኋላ የሚጀመር ሲሆን ሦስቱም ከዒድ ቀን አጋማሽ በኋላ ይጀመራሉ፡፡ በአያመ ተሸሪቅ የመጀመሪያው ቀን ተጀምረው በመጨረሻው (ዒድ በዋለ በአራተኛው ቀን) ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ይጠናቀቃሉ፡፡
ሐጅ አድራጊ ጠጠር መወርወር ሲጀምር ‹ለበይክ…› ማለቱን ማቆም ይኖርበታል፡
ከሐጅና ዑምራ መጽሐፍ
https://t.me/Nejashipp
https://www.tiktok.com/@nejashibooks
https://nejashibooks.com/
ስምንተኛው ቀን አመሻሽ ላይ
የውም አት-ተርዊየህ
*****
የሐጅ ተግባራት ዛሬ ዚል-ሒጃ ስምንተኛው ቀን ላይ ጀምረዋል። በሐጅ ወቅት የኢሕራም ልብስ ከለበሱ በኋላ ሐጅ ይነየታል።
የኢሕራምን ሁለት ረከዓዎችን ከሰገዱ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ ሆይ! ሐጅ አስቤያለሁና አግራልኝ፤ ተቀበለኝ። አንተ ሰሚም፣ ዐዋቂም ነህና።”
ከዚያም “ተልቢያ” ለብበይከ-ልላሁምመ ለብበይክ… ይባላል።
በዚሁ ቀን ጸሐይ ከወጣች በኋላ ወደ ሚና ጉዞ ይጀመራል። ይህ ቀን የተርዊየህ (ውሃ የማጠጣት ቀን) ተብሎ ይታወቃል። በጥንት ጊዜ የሐጅ እንግዶችን የሚቀበሉ ሰዎች ለሐጃጆች ውሃ በማቀበል የሚያሳልፉት ቀን ነው።
በዚሁ ቀን ተልቢያን /ለብበይከ-ልላሁምመ ለብበይከ… ማለትን ማብዛት ይወደዳል። ዚክር ማድረግ፣ ለአላህ መተናነስና ለሱ ያለንን ፍራቻ መግለጽ አስፈላጊ ነው።
ወደ ሚና መሄድና እዚያው ማደር በነጋታው ለሚደረገው የዐረፋ ላይ የመቆም ሁኔታ ያዘጋጃል።
አሥሩ የዚል-ሒጃ ቀናት፡፡
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ፡፡
*
* ዛሬ ዚል-ቂዕዳ 30ኛ ቀን ላይ ነው ያለነው፡፡
* በኢስላማዊው አቆጣጠር ነገ ሰኞ 1 ብሎ የሚገባው ወር የዚል-ሒጃ ወር ይባላል፡፡
* ዚል-ሒጃ እጅግ የተከበረ ወር ነው፡፡
* ጦርነት በውስጡ ከተከለከለባቸው ከአራቱ የተከበሩ ወራት ውስጥም አንዱ ናት፡፡
* ከወሩም የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት እጅግ የተከበሩ ናቸው፡፡
* ቀናቶቹ የዚል-ሒጃ ወር ሲጀምር ይጀምራሉ፡፡ የዒድ አል-አድሓ ቀን ያበቃሉ፡፡
*ፆም ምርጥ የአምልኮ ተግባር እንደመሆኑ በነኚህ የመጀመርያዎቹ ዘጠኝ ቀናት ውስጥ መፆም ይወደዳል ።
* ከነኚህ ቀናት ውስጥ ከ8ኛው ቀን ጀምሮ የሐጅ ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡
* እነኚህ ቀናት እጅግ ክቡር መሆናቸው የታወቀ ቢሆንም ብዙዎች በነኚህ ቀናት ዉስጥ ሲዘናጉ ይታያሉ፡፡
* በነኚህ ቀናት ዉስጥ የሚሠሩ መልካም ሥራዎች በየትኛዉም የዱንያ ቀናት ዉስጥ ከሚሠሩት በላይ አላህ ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፡፡
* የዐረፋ ቀን ፆም (ዘጠነኛው ቀን) የሁለት ዓመት ኃጢኣት ያስምራል፡፡ ያለፈን አንድ ዓመት እና የሚቀጥለዉን አንድ ዓመት፡፡
* የዐረፋ ቀን ፆም የሐጅ ሥራ ላይ ለሌለ ሰው ነው። ዐረፋ ላይ የሚቆም ሰው ይህን ቀን አይፆምም።
* ሐጅ አድራጊ በዚህ ቀን ውስጥ በዱዓና ኢስቲግፋር መበርታት ይኖርበታል ።
* አሥረኛው ቀን ዒድ ነው።
* የዒድ ቀን መፆም የተከለከለ ነው።
* ቀንም ሆነ ሌሊት በነኚህ ቀናት ዉስጥ በዒባዳ መበርታት ይገባል፡፡
* ለዒዱ ኡድሒያ ማረድ ሀሳቡ ያለው ሰው ቀነኚህ ቀናት ውስጥ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን መቆረጥ የለበትም።
* በነኚህ አሥር ሌሊቶች አላህ (ሱ.ወ.) ምሎባቸዋል፡፡ ይህም የቀናቱን ታላቅነት ያሳያል፡፡
* በነኚህ ቀናት ውስጥ የሚሠሩ መልካም ሥራዎች ተወዳጅ የመሆናቸውን ያህል በውስጣቸው የሚሠራ ኃጢኣትም ጥፋቱ ክቡድ ነው፡፡
* እነ ኢብኑ ዐመር እና አቢ ሁረይራ (ረ.ዐ.) በነኚህ ቀናት ዉስጥ ተክቢራ እያደረጉ ወደ ገበያ ይወጡ ነበር፡፡ ሰዎችም አብረዋቸው ተክቢራ (አሏሁ አክበር) ይላሉ፡፡
* በነኚህ ቀናት ዉስጥ ዚክር ማብዛት፣ አላህን ማላቅ ይወደዳል፡፡
* በነኚህ ቀናት ውስጥ ሱብሐነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ላ ኢላሀ ኢልለላሀ አላሁ አክበር ማለት ይወደዳል፡፡
* በዐረፋ ቀን ዱዓ መብዛት ይመረጣል፡፡ በተለይ ላ ኢላህ ኢልለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁልሙልኩ፣ ወለሁል ሐምዱ፣ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር … የሚለዉን፡፡
* በነኚህ ቀናት ዉስጥ የሚሠሩ የዒባዳ ዓይነቶች ቀናቶቹን ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ሶላት፣ ፆም፣ ሶደቃ፣ ሐጅ … ሁሉም የተሰባሰቡባቸው ናቸው፡፡
* ደጋጎች እነኚህን አሥርቶች ልዩ ትኩረት ይሠጧቸው ነበር፡፡
- የረመዷን ወር የመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት፣
- የዚል ሒጃ ወር የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት፣
- የሙሐረም ወር የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት፡፡
አሥርቱ ዚል ሒጃ ቀናት፤ ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ በመባል ይታወቃሉ፡፡
ያስታውሱ ቀናቱ ነገ ይጀምራሉ፡፡
መልካም ጊዜ
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር
https://t.me/Nejashipp
https://www.tiktok.com/@nejashibooks
https://nejashibooks.com/
እጅግ በርካታ የኢስላም ሊቃውንት አርባ ምርጥ ሐዲሦችን ለመሰብሰብ ጥረት አድርገዋል፡፡ ከሁሉም ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሳካላቸውና ኪታባቸው በያንዳንዱ ሙስሊም ቤት ገብቷል የሚባልላቸው ታላቁ ሸይኽ ኢማም ነወዊ ናቸው፡፡ ስብስባቸውም አርበዒን አን-ነወዊ “የነወዊ አርባ ሐዲሥ” በመባል ይታወቃል፡፡ ከስብስብ ሐዲሣቸው መካከል አንዱን እንጋብዛችሁ፡-
ሀያ ሦስተኛ ሐዲሥ
አቡ ማሊክ አልሓሪሥ ኢብኑ ዓሲም አል-ዐሸዐሪይ (ረ.ዐ) እንዳወሩት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
“ንፅህና የእምነት ግማሽ ነው፡፡ አልሐምዱሊላህ ማለት ሚዛንን ትሞላለች፡፡ ሱብሓነሏህ ወልሐምዱሊላህ በሰማይና በምድር መካከል ያለውን ክፍተት ይሞላሉ፡፡ ሶላት ብርሃን ናት፡፡ ምፅዋት የእምነት ማረጋገጫ ነው፡፡ ትዕግስት ወገግታ ነው፡፡ ቁርአን ይመስክርልሃል ወይም ይመሰክርብሃል፡፡ እያንዳንዱ ሰው (ባለበት ቦታ) ይማለዳል ሕይወቱን (ለአላህ) በመሸጥ ነፃ ያወጣታል፤ ወይም ወንጀልን በመስራት ያጠፋታል፡፡”
(ሙስሊም ዘግበውታል፡፡)
+1
የአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ይህችን ዓለም ሲሰናበቱ መዲና የሙስሊሙ ዓለም ዋና ከተማ ሆና ነበር። ከዚያም መንበሩን የተረከቡ ኸሊፋዎች የሚቀመጡባት እንዲሁም ኢስላማዊ ሕግጋትን ለማርቀቅ የዕውቀት ባቤቶች የሚሰበሰቡባት ከተማ ሆና ቀጥላለች።
ከዚያ በኋላ ግን የሙስሊሙ ኢምፓየር ድንበሮች እየተለጠጡ ሄደው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብና ሰፊ መሬት እንዲሁም በርካታ ክ/ሀገራትና ከተሞች ተጨመሩ።
በዑመር (ረ.ዐ0) የአመራር ዘመናት በርካታ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች ተቀማጭነታቸው መዲና ነበር። ይህ በአጋጣሚ የሆነ አልነበረም። ብዙ ሙስሊሞች ሀገር በመክፈትና ኢስላምን ከአጥቂዎች በመከላከሉ ተግባር ተሰማርተው በግንባር ይገኛሉ።
ዑመር (ረ.ዐ) በርካታ ቁጥር ያላቸው ዋና ዋና የሚባሉ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች ከጎናቸው እንዳይለዩ በማድረግ መዲና እንዲቀመጡ ይፈልጉ ነበር። ይህን በማድረግም ካላቸው እምቅ ዕውቀት እና ከምክራቸው ተጠቅመዋል።
በዚህ የዑመር ፖሊሲ ምክንያት 130 የሚሆኑ በሙፍቲ ደረጃ የተቀመጡ ሰሓባዎች (አላህ የሁሉንም ሥራ ይውደድላቸውና) መዲና ይገኙ ነበር።
ከነዚህ ሙፍቲዎች መካከል ራሳቸው ዑመር (ረ.ዐ)፣ ዐሊ (ረ.ዐ)፣ ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ)፣ ዓኢሻ (ረ.ዐ)፣ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት (ረ.ዐ) ዐብደላህ ኢብን ዐባስ (ረ.ዐ) እና ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) ዋነኞቹ ናቸው። እነዚህን ሰባት ታላቅ የዕውቀት ባለቤቶች አስመልክተው ሙሐመድ ኢብን ሐዝም እንዲህ ብለዋል፡- “እያንዳንዳቸው የሰጧቸው ፈትዋዎች (በመጽሐፍት መልክ ቢዘጋጁ) ትልልቅ ጥራዝ ያላቸው መጽሐፍት በወጣቸው ነበር።
ከአል-ፋሩቅ ዑመር መጽሐፍ የተወሰደ
አዘጋጅ ፡ ሸይኽ ዶ/ር ሙሐመድ ዐሊ አሶላቢ
ትርጉም ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
ከጠቢባን አንደበት
****
ዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አላህን የሚፈራ ሰው አላህ ሁሉም ነገር እሱን እንዲፈራው ያደርጋል፡፡ አላህን የማይፈራ ሰው ደግሞ ሁሉንም ነገር ይፈራል፡፡›
ሰልማን አልፋሪሲ (ረ.ዐ.) እንዲህ ብለዋል፡-
‹የምትመኛቸውን ነገሮች ማግኘት የምትችለው ስሜትህ የሚፈልገውን ነገር በመተው ብቻ ነው፡፡ ተስፋ የምታደርገውንና የምታልመውን ነገር የምትጨብጠው በምትጠላው ነገር ላይ ስትታገስ ነው፡፡ ንግግርህ አላህን ማውሳት ይሁን፡፡ ዝምታህ ማስተንተን፣ እይታህ ማስተዋል የተሞላበት ይሁን፡፡ ዱንያ ትቀየራለች፡፡ ድሎቷም ሆነ ደስታዋ ይለወጣል፡፡ በሷ አትታለል፡፡ ቤትህ መስጅድ ይሁን!›
ዐብዱላህ ኢብኑ አልሙባረክ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አስተዋይና ብልህ ሰዎች ስድስት ነገሮችን አያምኑም፡፡ ያለፈ ወንጀላቸውን በተመለከተ አላህ ምን ሊያደርጋቸው እንደሚችል፣ ከእድሜያቸው የቀረው ክፍል ስንት ጥፋቶችን ይዞባቸው ሊመጣ እንደሚችል፣ የተሰጣቸው ችሮታና ጸጋ ለፈተና ይሁን ለማዘናጋት ስለመሆኑ፣ መልካምና ቆንጆ ነገር መስሎ የሚታያቸው ነገር በርግጥም መልካም ስለመሆኑ፣ አሁንም አሁንም ሊመጣባቸው ከሚችል የቀልብ መንሸራተት፣ ሳያውቁና ሳያስቡ ድንገት በዐይን ብልጭታ ሊነጠቁ ከሚችሉት እምነታቸው፡፡›
ፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አላህን የሚፈራ ሰው፤ ለሱ ያለው ፍራቻ መልካም ወደተባለ ነገር ሁሉ ያመላክተዋል፤ ይመራዋል፡›
ፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አላህን የሚፈራን ሰው ማንም ሊጎዳው አይችልም፡፡ ከአላህ ውጭ የሚፈራን ሰው ማንም ሊጠቅመው አይችልም፡፡›
ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹የአላህ ፍራቻ አንዳንድ ጊዜ ከምግብና መጠጥ ይከለክለኛል፡፡ ሞትን ሳስታውስ የዚህች ዓለም ጉዳይ ምንም ሆኖ ይታየኛል፡፡ እንበላለን፣ እንጠጣለን፣ እንለብሳን፡፡ ያለችን ቀን ጥቂት ናት፡፡ ከድህነት የሚስተካክል ምንም የለም፡፡ መንገድ ባገኝ ምንም መታወስ በማልችልበት መልኩ ከዚህች ዓለም በወጣሁ ነበር፡፡›
ሓቲም አልአሶም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላል፡-
‹ለሁሉም ነገር መዋቢያ ጌጥ አለው፡፡ የአምልኮ ተግባራት (ዒባዳ) ጌጡ የአላህ ፍራቻ ነው፡፡ የአላህ ፍራቻ ምልክቱ ደግሞ ምኞትን ማሳጠር ነው፡፡›
ሉቅማን ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ልጄ ሆይ! በሱ ላይ ተስፋ ማድረግህ ወንጀልን እንድትዳፈር በማያደርግህ መልኩ በአላህ ላይ ተስፋ አድርግ፡፡ ከሱ እዝነት ተስፋ በማያስቆርጥህ መልኩ ፍራቻ አላህን ፍራ፡፡›
https://t.me/Nejashipp
https://www.tiktok.com/@nejashibooks
https://nejashibooks.com/
Уже доступно! Исследование Telegram 2025 — ключевые инсайты года 
