cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የኦርቶደክስ ልጆች መማርያ

የኦርቶደክስ ትምህርቶችን እንመማር በዚሁ ቻናላችን

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
406
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን #በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ። በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው። ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን! #መጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ_ገብረ_ኪዳን
Показать все...
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፡ አሀዱ አምላክ እሜን። #የእውነት የተዋሕዶ ልጅ የሆነ ሁሉ #SHARE ያደርገዋል። #ድንግል_ማርያም_ሆይ_አንቺን_መውደዴ_ስህተት_ከተባለ_መቸም_ትክክል_መሆን_አልፈልግም ። እመቤቴ ማርያም፥ እመ አምላክ፥ እሙ ለአዶናይ፥ ኪዳነ ምህረት፥ እመ ብርሀን፥ የጌታዬ እናት፥ የአምላክ እናት፥ የፈጣሪ እናት፥ ዘመን የተቀየረባት፣ ዓመተ መዓቱ ዓመተ ምህርት የተባለባት፣ የሰው ተስፋ እውን የሆነባት፣ የሰማያት ምሥጢር የተገለጠባት፣ ሰማይና ምድር አንድ የሆኑባት፣ መላእክት ከሰው ጋር የዘመሩባት፣ ፈጣሪ ሰው የሆነባት፣ ነቢያት የተነበዩላት የፃፉላት፣ ለማየት የጓጉላት፣ የዲያብሎስ ሴራ የተደመሰሰባት፣ የአዳም ድህነት፣ የአቤል ፅድቅ፣ የሴት መታዘዝ፣ የሄኖክ እድሜ፣ የኖህ ህይዎት፣ የሴም ምረጫ፣ የአብርሃም ሃይማኖት፣ የይስሐቅ ርህራሄ፣ የያእቆብ ጥበብ፣ የዮሴፍ በረከት፣ የሙሴ ጸሎት፣ የዓሮን እጣን፣ የዳዊት ዝማሬ፣ የሰሎሞን ፍርድ፣ የኢዮብ ፈውስ፣ የኢሳይያስ ድንግልና፣ የኤልያስ እርገት፣ የኤልሳእ በረከት፣ የኤርምያስ እምነት፣ የሕዝቅኤል ምሥጢር፣ የዳንኤል ራእይ፣ የነቢያት ትንቢት የነቢያት ምሳሌ፣ የክርስቶስ እናት፣ የብርሃን እናት፣ የእሳት እናት፣ የፈጣሪ እናት፣ የአምላክ እናት፣ የመለኮት እናት፣ የፀሐይ መውጫ ፣ የትንቢት ፍፃሜ፣ የሐዋርያት ስብከት፣ የሊቃውንት ምሥጢር፣ የመነኮሳት ገዳም፣ የባህታውያን ዋሻ፣ የምእመናን እምነት፣ የንፁሐን ንፅሕና፣የደናግል ድንግልና፣ የቅዱሳን ቅድስና፣ የታመሙት ፈውስ፣ የተሰደዱት እረዳት፣ የተራቡት ምግብ፣ የተጠሙት መጠጥ፣ የታረዙት ልብስ፣ የተማሪዎች ትምህርት፣ የፊደል ገበታየ አመሰግንሽ ዘንድ ምን አደበት አለኝ አምላኬን በዓይኔ ያሳየሽኝ ጨለማው ህይወቴን ያበራሽልኝ ቅድስት ሆይ ለኔ ለባርያሽ #ለምኝልኝ። እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ ገብርኤል ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ያለሽ፥ ኤልሳቤት የጌታዬ እናቱ ያለችሽ፥ ዳዊት ንግስት ሆይ ያለሽ፥ ሰሎሞን እቴ ሙሽራየ ያለሽ፥ ኢሳያስ ድንግል ሆይ ያለሽ አንች ግን ድንግል ሆይ እራስሽን ዝቅ አድርገሽ እኔ ለእግዚአብሄር ባርያው ነኝ አልሽ እመቤቴ ሆይ ትህትናሽን አድይኝ፥ ድንግል ሆይ እንዳንች እሩህሩህ እሆን ዘንድ ያንችን በረከት አሳድሪብኝ፥ ድንግል ሆይ ትእግስትሽን አድይኝ፥ ድንግል ሆይ አንቺ የገብርኤልን ቃል ሳትጠራጠሪ እንደተቀበልሽው እኔም የጌታየን ማዳን ሳልጠራጠር እንዳምን እርጅኝ፥ እመቤቴ ሆይ በሃይማኖቴና ባንች አማላጅነት በቅዱሳን ተራዳኢነት በመላዕክት ጥበቃ እንዳምን እርጅኝ። እመቤቴ ሆይ ከምንም በላይ ልጅሽን አምላኬን ተስፋ አድርጌ እንድኖር ነገሮችን በትእግስት እንዳሳልፍ እርጅኝ። አሜን # ቅድስት_ሆይ_ለምኝልን ። #እናቴ እመቤቴ ማርያም ሆይ ክብር ምስጋና ይገባሻል። #የጌታ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_እናት_ለእኔም_እናቴ_ናት ። "¶ስለ ኹሉም ነገር ክብር ለእግዚአብሔር ይኹን" አሜን ወአሜን ለይኩን ለይኩን። ይቀላቀሉ @yeortodex
Показать все...
ጽዮን የሊባኖስ ዝግባ የሰይፍ ሰገባ መጠጊያ አምባ የሔዋን ከፍታ የአዳም ኮረብታ ደልዳላዋ ቦታ የጽድቅ ተራራ የብርሐን ጮራ የአብ ሙሽራ የመዳን ከተራ ፍኖተ ጽድቅ ልዩ ምስራቅ የፀሐይቱ መውጫ የድህነት መምጫ የኅጥኣን መንጫ የሰይጣን መርገጫ የህይወት መሠረት የመዳን ምክንያት የአዳም መድሀኒት የሔዋንም እረፍት የዳዊት ትንቢቱ የሙሴ እህቱ የአምላክ እናቱ የማክሰኞ እርሻ የጻድቃን መንገሻ ርስት መውረሻ የመንግስት ደጃፍ የመጽደቂያ በራፍ ድህነት ለሰብዕዓለም ድንግል ለዘለዓለም ዘኢይመስል ነገር የሚመስልሽ የለም አዳ'ም
Показать все...
+ ስሞት ዓይኔን የሚከድንልኝ ማን ይሆን? + አንድ ሁልጊዜም መማር የማይታክታቸው አባት ነበሩ:: በጣም የተማሩ ቅኔ አዋቂ መጻሕፍት የመረመሩ ሊቅ ቢሆኑም ሁሌም ከአትሮንስ ሥር የማይጠፉ ተማሪ ነበሩ:: ይህንን ልምዳቸውን ያየ አንድ ሰው "እርስዎ ብዙ የተማሩና ያነበቡ ሰው ነዎት ከዚህ በኁዋላ ማረፍ ሲገባዎት ለምን ጊዜዎን በትምህርት ያጠፋሉ?" አላቸው:: እርሳቸውም "መልአከ ሞት መጥቶ ወደ ፈጣሪ በወሰደኝ ጊዜ 'የት አግኝተህ አመጣኸው?' ሲባል ከአትሮንስ ሥር ቁጭ ብሎ የአንተን ቃል ሲሰማ አገኘሁት ብሎ እንዲነግርልኝ ነው" አሉ:: መልአከ ሞት አሁን በዚህ ሰሞን መጥቶ ቢወስድህ ምን ሲያደርግ አገኘሁት የሚል ይመስልሃል? ሲጸልይ? ሲመጸውት? ሲመርቅ? ሰዎችን በፍቅር ቃል ሲናገር? ሲያማ? ሲሳደብ? ሲያስታርቅ? ሲያጣላ? እውነትም የእኚህ አባት ጭንቀት እጅግ ተገቢ ጭንቀት ነበር:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን "እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነት ሦስትነትህን በማመን አጽናን" ብላ በቅዳሴዋ የምትጸልየው በሞት የምወሰድበት ወቅት ምናልባትም ክፉ የምንሠራበትና ፈጣሪን የምንክድበት ጊዜ እንዳይሆን ነው:: "ሽሽታችሁ በክረምትና በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ" እንዲል እንደ ክረምትና ሰንበት ሥራ አቁመን ከበጎ ምግባር በራቅንበትና በሰነፍንበት ሰዓት እንዳንሞት እንጸልያለን:: ሌላው ቅዱስ አባት ነባቤ መለኮት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ደግሞ ከሞቱ በኃላ ስለሚከሰተው የመጀመሪያ ክስተት ሲናገር "ስሞት ዓይኔን በጣቶቹ የሚከድልኝ ማን ይሆን?" (Who will lay his fingers upon my eyes when I die?) ብሎአል:: (On His own life 43) ምናልባት "ስሞት ዓይኔን ማንስ ቢከድነው ምን ለውጥ አለው?" ብለን እናስብ ይሆናል:: ሆኖም የመጨረሻዋን ቅጽበት የዓይናችን መከደን ጉዳይና የሚከድነው ሰው ማንነት ትልቅ ዋጋ ያለው ነው:: እግዚአብሔር በበጎነታቸው ለወደዳቸው ቅዱሳን ከሚመርቀው ምርቃት አንዱ "ልጆችህ ዓይንህን ይከድናሉ" የሚል ነበር:: ያዕቆብን እንዲህ ሲል መረቀው "ወደ ግብፅ አብሬህ እወርዳለሁ : ከዚያም አወጣሃለሁ ልጅህ ዮሴፍም እጁን በዓይኖችህ ላይ ያኖራል" ዘፍ 46:4 የምንወደውን ሰው ዓይን ከድኖ መሰናበት "ሲቀብር ይቆርጥለታል" ከሚባለው ልማዳዊ ብሂል በላይ ፍጹም ዕረፍት የሚሰጥ ስንብት ነው:: ምንም ስቃዩና ኀዘኑ ጥልቅ ቢሆንም የመጨረሻዋን ሕቅታ ሰምቶ የምንወደውን ሰው ዓይን ከድኖ የመሸኘትን ያህል የሕሊና ዕረፍት የለም:: ለአባት "ልጆችህ ዓይንህን ይከድናሉ" መባል ምርቃት የመሆኑን ያህል ለወላጆች የልጅን ዓይን መክደን ግን እጅግ ከባድ ኀዘን ነው:: ሆኖም ምንም ኀዘኑ ጥልቅ ቢሆን ልጅን ዓይን ከድኖ መሰናበት ኀዘንን የሚያቀልል ስንብት ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በአንድ ልጃቸው ሞቶ በኀዘን በተሰበሩ ወላጆች ቤት ገብቶ ይህንን የማጽናኛ ቃል ተናግሮ ነበር :- "ጻድቁ ኢዮብ የልጆቹን ዓይን ለመክደንና አፋቸውን ለመግጠም ሰውነታቸውንም ለማስተካከል እንክዋን አልታደለም ነበር:: እናንተ ግን ቢያንስ የልጃችሁን የመጨረሻ ቃል ሰምታችኃል ዓይኖቹንም ከድናችኃል አፉንም ገጥማችኃል:: እናንተ ዐሥር ልጆቹን ካጣው ኢዮብ በላይ ስለምን ታዝናላችሁ?" ቅዱስ ጎርጎርዮስ "ዓይኔን የሚከድንልኝ ማን ይሆን?" አለ:: ይህንን አስበነው እናውቅ ይሆን? ማን እንዲሸኘን እናስብ ይሆን? ቅድስት መቅሪና ስትሞት ወንድምዋ ጎርጎርዮስ ዓይንዋን እንዲከድንላት ትመኝ ነበር:: ሆኖም በሞተችበት ዕለት ሳትሞት በፊት በወሰዳት እንቅልፍ ምክንያት ዓይንዋ ተከድኖ ነበር:: (St.Gregory of Nyssa, On the life of St Makrina) ቅዱስ ፍላብያኖስ ዘአንጾኪያም እኅቱ ዓይንዋን እንዲከድንላት ስትመኝ ኖራ በሞተች ዕለት እርሱ ለጸሎት ወደ ቁስጥንጥንያ ሔዶ እንደነበረ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ተናግሮአል:: ለአንዳንድ ቅዱሳን ደግሞ ማን መጥቶ ዓይናቸውን እንደሚከድን አስቀድሞ ፈጣሪ ይገልጥላቸው ነበር:: ከሃያኛው ክፍለ ዘመን ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ፓትርያርክ ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ለአንድ ወጣት ጦቢት የሚል ቅጽል ስም አውጥተው ይጠሩት ነበር:: ለምን ጦቢት እንደሚሉት ባያውቅም ስሙን ግን አውቆ በጠሩት ቁጥር አቤት ይል ነበር:: ፓትርያርኩ በሞቱበት ዕለት ይህ ወጣት እግር ጥሎት ቀድሞ የደረሰው እርሱ ነበር:: ዓይናቸውን የከደነና አፋቸውን የገጠመው የዕረፍታቸውን ዜናም ለሌሎች ያሳወቀው ቀብሩንም ያስፈጸመው እርሱ ነበር:: ይህ ከሆነ በኁዋላ "ጦቢት" ብለው የሚጠሩበትን ምክንያት አስታውሶ መጽሐፈ ጦቢትን ሲያነብ ይህንን ጥቅስ አገኘ :- "ጦቢትም እንዲህ አለ :- በነነዌ አደባባይ የሞተ ሰው ሳገኝ እቀብረው ነበር" ጦቢ 1:4 ጻድቁ ይህ ወጣት እንደሚቀብራቸው አውቀው ራሱን ለአደጋ አጋልጦ ድሆችን ይቀብር በነበረው በጦቢት ስም ይጠሩት ነበር:: እኔና አንተ ግን የማናውቅ ስለሆንን እንዲህ እንላለን "ስሞት ዓይኔን የሚከድንልኝ ማን ይሆን?"
Показать все...
አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ። ትንቢተ ሕዝቅኤል 36:26 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ይህ የግዕዝ መማሪያ ቻናል ነው። በቻናሉም የሚሰጡ ትምህርቶች #ዓረፍተ_ነገር #ቃላት #የሰላምታ_ልውውጥ #መንፈሳዊ_ትምህርት ብዙ ብዙ ትምህርቶች ይገኙበታል #join_&_hare @yegeez_memariya
Показать все...
[ፈጥኖ የሚረዳን የቅዱስ ሚካኤል ክብር በሊቁ በቅዱስ ያሬድ ድጓ] ✍ [በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ] ❖♥ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ስለኾነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፣ ውበት፣ ምልጃ ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው እንዲኽ ይላል፡- ╬ “ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ” (የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል) ይላል፡- ❖♥ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ከመኾኑ ጋር ይልቁኑ ዮሐንስ በራእዩ በምዕ 8፡2 ላይ “በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ” ካላቸው፤ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በመዠመሪያ የሚጠቀሰው ቅዱስ ሚካኤል ነውና ሊቁ ያሬድ፡- ╬ ♥ “እስመ እምአፉሁ ይወጽዕ ነጐድጓድ ሕብረ ክነፊሁ ያንበለብል ነድ እምሊቃነ መላእክት የዐቢ በዐውድ ሚካኤል ውእቱ መልአኩ ለወልድ” (የወልድ አገልጋዩ ሚካኤል ነው፤ በዙሪያው ኹሉ ካሉት ከሊቃነ መላእክት ይበልጣል፤ የክንፉ መልክ ነባልባላዊ እሳትን ያቃጥላል፤ ከአንደበቱ ነጐድጓድ ይወጣልና) ይላል፨ ╬ ♥“አዕበዮ ንጉሠ ስብሐት ለሚካኤል ሊቀ መላእክት ዘይስእል በእንተ ምሕረት መልአከ ሥረዊሆሙ ለመላእክት” (የምስጋና ባለቤት ክርስቶስ ለመላእክት ጭፍሮች አለቃቸው የኾነ ስለ ምሕረት የሚማልድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ከፍ ከፍ አደረገው) በማለት ይጠቅሰዋል፡፡ ❖♥ የስሙ ትርጓሜንም ስንመለከት ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን ሚ- ማለት “ማን”፤ ካ- “እንደ”፤ ኤል- “አምላክ” ማለት ነውና ሚካኤል ማለት “መኑ ከመ አምላክ” (ማን እንደ አምላክ) ማለት ነው፡፡ ❖♥ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ይዞ ╬ “ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ” (የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም ጋር ለተባበረ ስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድም፡- ╬ “መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ መልአኮሙ ሥዩሞሙ የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ” (ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤ የተሾመላቸው አለቃቸው ርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል) ይላል ❖♥ በብሉይ ኪዳን ለአበው ነቢያት እየተገለጠ፤ ለሐዋርያትም በስብከት አገልግሎታቸው እየተራዳ፤ ለሰማዕታት፣ ለቅዱሳን አበው በተጋድሏቸው እየተገለጠላቸው አስደሳች መልኩን ያዩት ነበር። ❖♥ ይኽነን የቅዱስ ሚካኤልን ውበት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡- ╬ “መልአከ ፍሥሐ ዘዐጽፉ መብረቅ ሐመልማለ ወርቅ ሚካኤል ሊቅ” (መጐናጸፊያው መብረቅ የኾነ የደስታ መልአክ፤ አለቃ ሚካኤል የወርቅ ዐመልማሎ ነው) ❖♥ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ውበቱን ሲገልጠው፡- ╬ “ሰላም ለአክናፊከ እለ በሰማያት ያንበለብሉ ከመ ሠርቀ ፀሓይ ሥነ ጸዳሉ” (የጸዳሉ ውበት እንደ ፀሓይ አወጣጥ የኾነ በሰማያት ለሚያንበለብሉ ክንፎችኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡ ❖♥ ቅዱስ ያሬድ ደግሞ፡- ╬ “ውእቱ ሊቆሙ ወመልአኮሙ ሚካኤል ስሙ ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ” (ዐይኑ የርግብ (እንደ ርግብ የዋህ፣ ጽሩይ) የኾነ ልብሱ የመብረቅ መጐናጸፊያ የኾነለት የወርቅ ዐመልማሎ ስሙ ሚካኤል የተባለ ርሱ የመላእክት አለቃቸው መሪያቸው ነው) ይላል፡፡ ❖♥ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና አማላጅነት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡- ╬ በ፲ወ፬ቱ ትንብልናከ ዐቢይ ልዕልናከ በመንክር ትሕትናከ አስተምህር ለነ ሰአልናከ” (በዐሥራ አራቱ ልመናኽ ምልጃኽ፤ በታላቅ ልዕልናኽ በሚያስደንቅም ትሕትናኽ ሚካኤል ትለምንልን ዘንድ ማለድንኽ) ╬ “ዘወሀበ ትንቢተ ለኤልዳድ ወሙዳድ አመ ምጽአቱ ይምሐረነ ወልድ ሰአል ለነ ሚካኤል መንፈሳዊ ነገድ ከመ ንክሃል አምስጦ እምሲኦል ሞገድ” (ለኤልዳድና ለሙዳድ የትንቢትን ጸጋ የሰጠ የሚኾን ወልድ በሚመጣ ጊዜ ይምረን ዘንድ ከረቂቅ ነገድ ወገን የኾንኸው ሚካኤል ከሲኦል እሳታዊ ሞገድ ማምለጥ እንችል ዘንድ ለእኛ ለምንልን) ይላል፡፡ ╬ “ከናፍሪሁ ነድ ዘእሳት አልባሲሁ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ውእቱ ይዕቀብክሙ ነግሀ ወሠርከ ሌሊተ ወመዐልተ” (ከናፍሮቹ የእሳት ልብሶቹ የመብረቅ የኾነ የመላእክት አለቃ ሚካኤል በተራኢነቱ በጠዋትም፤ በሠርክም፤ በቀንም በሌሊትም ይጠብቃችኊ) አለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፨ ❤ ቅዱሳን መላእክት ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ቅድመ እግዚአብሔር በማድረስ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው በማምጣት ሰውን ከአምላካቸው ጋር በማማለድ ጸንተው ያሉ እንደኾኑ በብዙ ሥፍራ ላይ ተዘርዝሯል፡- ✍️ ለምሳሌ ያኽል ዘፍ 48፥15፤ ዘጸ 23፥20፤ መሳ 6፥11፤ ኢዮ 33፥23፤ መዝ 33፥7፤ 88፥6፤ 90፥11፤ 1ነገ 19፥5፤ 2ነገ 6፥15፤ ዳን 3፥17፤ 4፥13፤ 8፥15-19፤ ዘካ 1፥12፤ ማቴ 18፥10፤ ሉቃ 1፥19፤ 13፥6-9፤ 15፥7፤ ዮሐ 20፥11፤ የሐዋ 12፥6፤ ዕብ 1፥14፤ ራእ 8፥3-4ን ይመልከቱ)፡፡ የቅዱስ ሚካኤል በረከት ይደርብን።
Показать все...
#ህዳር_11_የእመቤታችን_እናት_ቅድስት_ሐና_አረፈች † እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ሃና በዓለ እረፍት መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን የቅድስት ሃና ረድኤት በረከት አይለየን አሜን !!! † የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ቴክታ በጥሪቃ ይባላሉ፤ ይህ ቀራቸው የማይባሉ ባለጸጎች ነበሩ፤ ብዕላቸውም የወርቅ፣ የብር፣ የፈረስ፣ የበቅሎ፣ የሴት ባሪያ፣ የወንድ ባሪያ ነው፡፡ ከወርቁ ብዛት የተነሣ እንደ አምባር እንደ ቀለበት እያሠሩ፤ ከበሬው ከላሙ ቀንድ ያደርጉት ነበር፡፡ ይህን ያህል አቅርንተ ወርቅ፤ ይህን ያህል አቃርንተ ብሩር ተብሎ ይቈጠር ነበር እንጂ፤ የቀረው አይቈጠርም ነበር፡፡ ከዕለታት ባንደኛው ቀን ጴጥሪቃ ከቤተ መዛግብት ገብቶ የገንዘቡን ብዛት አይቶ፤ “ቴክታ እኔ መካን፤ አንቺ መካን ይህ ሁሉ ገንዘብ ለማን ይሆናል?” አላት “እግዚአብሔር እንጂ ከኔ ባይሰጥህ ወይ ከሌላ ይሰጥህ ይሆናል፤ አግብተህ አትወልድምን?” አለችው፡፡ “ይህንስ እንዳላደርገው አምላከ እስራኤል ያውቃል” አላት፤ በዚህ ጊዜ አዘኑ፤ ወዲያው ራእይ አይተዋል፤ ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስታወጣ፣ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ስታደርስ ስድስተኛይቱ ጨረቃን፣ ጨረቃ ፀሐይን ስትወልድ አይተው፥ በሀገራቸው መፈክረ ሕልም /ሕልም ተርጓሚ/ አለና ሂደው ነገሩት፤ “ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ፤ ጨረቃይቱ ከፍጡራን በላይ የምትሆን ልጅ ትወልዳላችሁ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም እንደ ነቢይ እንደ ንጉሥ ያለ ይሆናል” አላቸው፡፡ እነርሱም “ጊዜ ይተርጉመው” ብለውት ሄዱ፡፡ ከዚህ በኋላ ፀነሰች፤ ወለደች ስሟን ሄኤማን አለቻት፤ ሄኤማን ማለት ረካብኩ ስእለትየ ረከብኩ ተምኔትየ /የፈለግሁትን የለመንኩትን አገኘሁ/ ማለት ነው፡፡ ሄኤማን ዴርዴን፤ ዴርዴ ቶናን፣ ቶና ሲካርን፣ ሲካር ሄርሜላን፣ ሄርሜላ ሐናን ወለደች፡፡ ሐና አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደ ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት:: እያቄምና ሐና በንጽህና በቅድስና የሚኖሩ ልጅ ግን አልነበራቸውም ህዝቡም ቅድስት ሐናን ይህቺ የበቅሎ ዘመድ ቢወልዷት እንጂ የማትወልድ፤ እግዚአብሔር እኮ ያደረቃት በኃጢያቷ ነው እያሉ ይዘልፏት ነበር ወደ ቤተ እግዚያብሔር መባ ይዘው ሲሄዱ አይቀበሏቸውም ነበር፤ በዚህም ሲያዝኑ ኖሩ ልጅ እንዲሰጣቸውም እግዚአብሔርን ዘወትር ይለምኑት ነበር፤ በኋላም እግዚአብሔር ጎበኛቸው ነሐሴ በባተ በ 7ኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ዓለሙ ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሷን ጸጉር የማያህል ደግ ፍጥረት ተወልዳለችሁ ብሎ ቅዱስ ገብርኤል አበሰራቸው፤ ሐና ጸነሰች ይህም በአገሬው ታወቀ ሊጠይቋት የሚመጡ ማህጸኗን እየዳሰሱ ይፈወሱ ነበር፤ አይናቸው የበራላቸውም ነበሩ፤ ግንቦት 1 ቀን ሊባኖስ ተራራ ላይ በነብያት ብዙ የተባለላት የድህነታችን መጀመሪያ የንጽህናችንም መሰረት የሆነችውን እመቤታችንን ወለደች፤ ቅድስት ሐና በቅድስና በንጽህና ኖራ ህዳር 11 ዕለት አረፈች:: ከእመቤታችን እናት #ከቅድስት_ሀና_በረከት_ረድኤትን_ይክፈለን፡፡
Показать все...
☆• • ☆ #ሥርዓተ_____ቅዳሴ____ ☆• • ☆+ #በቅዳሴ___ጊዜ 5ቱ መሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው? 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት እነማን ይሆኑ? ካህናት በቅዳሴ ወቅት 2: 3: 4: 5: 7: 12: ወይም 24: ሆነው ከቀደሱ ምሳሌነቱ ምን ምን ይሆን? እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር 4 ነገሮች እናገኛለን ምን ይሆኑ? አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ እንዴት? ፨ ፨ ፨ አውቀነው እንጠቀምበት ዘንድ ይነበብ.....ለሌሎች ሰማያዊ ምሥጢርን አካፍለን የተሰጠንን መክሊት እናተርፍበት ዘንድ እንትጋ ሼር ሼር ☆• • ☆ #ቅዳሴ ☆• • ☆ ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ፭ቱ ምሥዋዕቶች ተሞልተው ይገኙበታል እዚህንም ፭ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡ ፩. የቁርባን መስዋዕት፡- + በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ውስጥ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ፀሎት ነው ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል፡፡ ፪. የከንፈር መስዋዕት፡- + ካህኑ፣ ዲያቆኑና ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡ ፫. የመብራት መስዋዕት፡- + በቅዳሴ ጊዜ የሚበራው ጦፍ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የሚሰጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡ ምሳሌነቱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው ይህውም ጌታችን ጨላመ ለሆነ ዓለም ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡ ፬. የዕጣን መስዋዕት፡- + የዕጣን ፀሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ በደሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበር እንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡ ፭. የሰውነት መስዋዕትነት፡- + በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዞሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው፡፡ ☆• • ☆ • • ☆• • ☆ ይህ የፀሎት ክፍል (ቅዳሴ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላ ፩. የዝግጅት ክፍል ፪. የንባብና የትምህርት ክፍል ፫. ፍሬ ቅዳሴ እነዚህ ፍሬ ቅዳሴያት እንደየበዓሉ ይለዋወጣተሉ ብዛታቸውም ፲፬ (14) ናቸው እነዚህም፡- ፫.፩. ሥርዓተ ቅዳሴ ፫.፪. ቅዳሴ ዘሐዋርያት ፫.፫. ቅዳሴ እግዚእ ፫.፬. ቅዳሴ ማርያም ፫.፭. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ ፫.፮. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት ፫.፯. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ ፫.፰. ቅዳሴ ባስልዮስ ፫.፱. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ፫.፲. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ ፫.፲፩. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ ፫.፲፪. ቅዳሴ ዘቄርሎስ ፫.፲፫. ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ ፫.፲፬. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ -የጌታችን በዓል ከሆነ … (ቅዳሴ እግዚእ) #መልካም_ቀን_ይሁንላችሁ
Показать все...
#መልካም_አእምሮ_ያስፈልገናል " የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፤ የኃጥኣን ምክር ግን ተንኰል ነው። (መ.ምሳሌ12:5) ✝ይ🀄️ላ🀄️ሉን👇 @yeortodex አእምሮዎ ለእርስዎ መልካም ወይም ለእርስዎ ጥፋት ሊሠራ ይችላል ፡፡ #ለእርስዎ_መልካም በሚሰራበት ጊዜ ቀና ሆነው እንዲቆዩ ፣ ግቦችዎ ላይ መድረስ እና በየቀኑ እንዲደሰቱ ይረዳዎታል ፡፡ ግን መጥፎ ሲሰራ አሉታዊ እና ተስፋ መቁረጥ ሊያደርግብዎት ፣ ወደኋላ ሊልዎት እና እራስን ማጉደል የሚያስከትሉ ሀሳቦችን እንዲያስቡ ያደርግዎታል ፡፡ ስለዚህ ከመጥፎ ይልቅ አእምሮዎን መልካም እንዲሠራ ያስተምሩ ፡፡ ይህንን ለማድረግ በጣም አስፈላጊው መንገድ በእምነት ማሰብ ነዉ ውሳኔ ማድረግ ነው ፡፡ አሁን አንጎልዎ ይህንን አዲስ ሚና በአንድ ሌሊት ማከናወን አልቻለም። ሥር ነቀል ለውጥ እንዲደረግ እየጠየቁት ሊሆን ይችላል ፣ እና ያ ጊዜ ይወስዳል። ነገር ግን ያንን በትጋት እና #በእግዚአብሔር_እርዳታ ፣ በእርስዎ ላይ ከመሰራት ይልቅ አንጎልዎ ለእርስዎ ይሰራል እናም በህይወትዎ ውስጥ አዎንታዊ ኃይል ይሆናል ፡፡ የእውቀት (ኮግኒቲቭ) የነርቭ-ሳይንቲስት ምሁር የሆኑት ዶክተር ካሮሊን ሊፍ እንዳሉት አንጎል ለማደግ አሥራ ስምንት ዓመት እና ዕድሜው እስከ ብስለት ድረስ ይወስዳል ፡፡ ይህ ነጥብ እንዳያመልጥዎት! በተወለዱበት ጊዜ እና ሰውነትዎ እያደገ ሲሄድ ሰውነትዎ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ የአካል ክፍል ሙሉ በሙሉ የተገነባ ሲሆን አንጎሉ ለማደግ በእውነቱ አሥራ ስምንት ዓመታት ይወስዳል ፡፡ እና አንዴ ከተሰራ በኋላ #እስከሚሞቱበት_ቀን ድረስ ማደግ ይቀጥላል። ያ ማለት ምንም ያህል እድሜ ቢኖራችሁ ፣ አንጎልዎ #አሁንም_እያደገ ነው ፡፡ ይህ በጣም ጥሩ ዜና ነው ፣ ምክንያቱም በድሮ ወይም የተሳሳቱ አስተሳሰብ ስርዓቶች ውስጥ ተጣብቀው መቆየት የለብዎትም ማለት ነው። አንጎላችን አሁንም እያደገ ነው ፣ ይህ ማለት በአስተሳሰባችሁ ውስጥ አሁንም ማሻሻል ይችላሉ ማለት ነው ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው "የጻድቅ አሳብ ቅን ነው።" ✝ይ🀄️ላ🀄️ሉን👇 @yeortodex
Показать все...
+♥ #ቅድስት_ሶፍያ_ቡርክት♥+ ይሕች ቅድስት እናት ኢጣሊያዊት (የአሁኗ ጣልያን አካባቢ) ስትሆን የነበረችው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ነው:: ትውልዷ የነገሥታቱ ዘር ውስጥ እንደ መቆጠሩ እጅግ የተከበረች ሴት ነበረች:: ምንም ሥጋዊ ክብሯ እንዲህ ከፍ ያለ ቢሆንም መንፈሳዊነቷ የሚደነቅ ነበር:: ከነገሥታቱ ዘር ካገባችው ባሏም 3 ሴቶች ልጆችን አፍርታለች:: በሃይማኖት ምክንያት መከራ ሲመጣ ስለ ልጆቿ ስትል ሃገሯን ጥላ ተሰደደች:: ስለ ክርስትናም በባዕድ ሃገር መጻተኛ ሆነች:: ያም ሆኖ ክፉዎቹ እግር በእግር ተከትለው ደረሱባት:: #ቅድስት_ሶፍያ ከዚህ በላይ መሸሸትን አልፈለገችም:: ከልጅነታቸው ለተባረኩ ልጆቿ ገድላተ ሰማዕታትን ታስጠናቸው ነበርና አሁን የነገር መከናወኛ ደርሷል:: ልጆቿን ቁጭ አድርጋ አዋየቻቸው:: "ልጆቼ! #ክርስቶስን የወደደ ክብሩ በሰማይ እንጂ በምድር አይደለም:: ገድላቸውን ያነበባችሁትን ቅዱሳት አንስትን አስቡ" አለቻቸው:: 3ቱ ሕጻናትም "እናታችን አትጨነቂ:: እኛ ለአምላክ ፍቅር ተገዝተናል:: ስለ ስሙም ደምን ልንከፍል ቆርጠናል:: ብቻ የርሱ ቸርነት: ያንቺም ምርቃን አይለየን እንጂ" አሏት:: ቅድስት ሶፍያ በሰማችው ነገር እጅግ ደስ አላት:: +ከዚያ ጉዞ ወደ ምስክርነት አደባባይ አደረጉ:: ቅድስቷ እናት 3ቱንም ሕጻናት በመኮንኑ ፊት አቀረበች:: አንድ በአንድ ጠየቃቸው:: ሁሉም ግን መልሳቸው የተጠናና ተመሳሳይ ሆነበት:: "#እኛ_የክርስቶስ_ነን " ነበር ያሉት:: መኮንኑ በቁጣ 3ቱንም እያከታተለ አስገደላቸው:: +ቅድስት #እናት_ሶፍያ በእንባ እየታጠበች ልጆቿን በየተራ ቀበረች:: ስለ ሃይማኖቷ ክብሯን: ሃገሯን: ሃብቷን: መንግስቷን ሰጠች:: ከምንም በላይ ግን ልጆቿን ሰጠች:: ከዚህ በሁዋላ ግን በመጨረሻው ወደ ልጆቿ መቃብር ሒዳ በእንባ ለመነች:: "ልጆቼን አይ ዘንድ ናፍቄአለሁና ጌታ ሆይ! ውሰደኝ" አለች:: ከደቂቃዎች በሁዋላም እዚያው ላይ ዐረፈች:: የአካባቢው ሰዎች ደርሰው እርሷንም ከልጆቿ ጋር ቀበሯት::
Показать все...